cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ገድለ ቅዱሳን

@Gedelat ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡ በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
6 669
Suscriptores
-224 horas
-37 días
-830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

00:46
Video unavailableShow in Telegram
                          †                          [ የምታሰድዳት ከሆነ ... ግድ የለም ! ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን ፥ ዘመናትም ፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት። ❞ [ ራእ.፲፪፥፲፫ ] ❝ ህፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ ❞ [ ማቴ . ፪ ፥ ፲፫ ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Mostrar todo...
1.99 MB
1
Photo unavailableShow in Telegram
[ ያለ እምነት - ፲ - ] .mp310.89 MB
Photo unavailableShow in Telegram
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊         [     ያ ለ    እ ም ነ ት !     ]                         [  ክፍል - ፲ -  ]      💖    ድንቅ ትምህርት   💖 🕊 በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊 ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ❞ [ ዕብ . ፲፩ ፥ ፮  ]  ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሊሰማው የሚገባው እጅግ ድንቅ ተከታታይ ትምህርት !  💞 †                       †                         † 💖                    🕊                     💖                          👇
Mostrar todo...
D.M.Silemayneger sitotaw hulu.mp33.90 MB
ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል ✞.mp39.33 MB
Photo unavailableShow in Telegram
                          †                           🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 ❝ ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርአዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳዕ ዘተኃጕለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ ፤ ❞ ትርጉም ፦ [ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን በጻድቃን ላይ የሚያበራ ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ነው ፣ የጠፋው ይረዳ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደ እኛ መጣ [ ሰው ሆነ ] ] [ ድጓ ዘአስተምህሮ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🕊 [ † እንኳን ለኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን እና ለእናታችን ቅድስት ማርታ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † 🕊 †  አቡነ ተጠምቀ መድኅን  †  🕊 † ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ፲፮፻፲ [1610] ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ-ክርስቶስና ወለተ-ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ ፪ [2] ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር ፲፩ [11] ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ-እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ:: ሕጻን እያሉ ቃለ-እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን: ነብሩን: ተኩላውን ሰብስበው:- "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ: ከፍየሉ: ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን: ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ:: ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: ፳፫ [23] ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል:: ከዚሕ ጊዜ በሁዋላ ለ፴፯ [37] ዓመታት:- ፩. በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል ፪. ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል ፫. ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል [ካህን ናቸውና] ፬. ፯ "7" ገዳማትንና ፲፪ "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል:: † ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ፷ [60] ዓመታቸው በ፲፮፻፸ [1670] ዓ/ም [በአፄ ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን] ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬ በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል:: 🕊   †  ቅድስት ማርታ  †   🕊 † እናታችን ቅድስት ማርታ በቀደመ ሕይወቷ እጅግ ኃጢአቷ የበዛ ሴት ነበረች:: እጅግ ቆንጆ መሆኗን ሰይጣን ለኃጢአት እንድትጠቀምበት አባበላት:: እርሷም ተቀበለችው:: በወጣትነት ዘመኗ በመልኩዋና በገላዋ በርካቶችን ወደ ኃጢአት ሳበች:: መጽሐፍ እንደሚል ለሁሉም ሰው የመዳን ቀን ጥሪ አለውና አንድ ቀን [በበዓለ ልደት] ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች:: ዘበኛው ግን ሲያያት ተጸይፏልና አትገቢም አላት:: ተከራከረችው: ለመነችው:: ግን አልተሳካላትም:: ሰዓቱ የቅዳሴ ቢሆንም እርሷ እሪ አለች:: ለቅዳሴ የቆሙ ሁሉ በመታወካቸው ዻዻሱ ወጥቶ ገሰጻት:: ያን ጊዜ ነበር ወደ ልቧ የተመለሰችው:: በጉልበቷ ተንበርክካ መራራ ለቅሶን አለቀሰች:: ዻዻሱንም ተማጸነችው:- "እጠፋ ዘንድ አትተወኝ:: ወደ ጌታየ አድርሰኝ" አለችው:: ወዲያውም ወደ ቤቷ ሔዳ የዝሙት እቃዋን አቃጠለች:: ጸጉሯን ተላጨች:: ንብረቷን ሁሉ ለነዳያን አካፈለች:: ዻዻሱም ንስሃ ሰጥቶ ወደ ገዳም አሰናበታት:: ወደ ገዳም ገብታ: በዓት ተቀብላ: ጾምና ጸሎትን ከእንባ ጋር አዘወተረች:: ለ፳፭ [25] ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ከበዓቷ ሳትወጣ: አንድም ሰው ሳታይ ኖረች:: ከማረፏ በፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጋለች:: † የቅዱሳን አምላክ ለእኛም እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሐ አይንሳን:: ከበረከታቸውም ያድለን:: † 🕊 [ †  ሰኔ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅድስት ማርታ ተሐራሚት ፪. አቡነ ተጠምቀ መድኅን ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ] ፫. ቅዱስ ኢላርዮን ሰማዕት ፬. ቅዱስ ኮርዮን ሰማዕት [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን] ፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ ፭. አቡነ ዜና ማርቆስ ፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል † " አልሞትም : በሕይወት እኖራለሁ እንጂ:: የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ:: መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ:: ለሞት ግን አልሠጠኝም:: የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ:: ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ:: ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት:: ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ:: ሰምተኸኛልና: መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ:: " †  [መዝ.፻፲፯፥፲፯-፳፪] (117:17-22) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Mostrar todo...
[ ስንክሳር ሰኔ - ፫ - ] .mp36.35 MB