cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መ ረ ቅ

መረቅ በደም የተዛመዱንን፣በትምህርት እንዲሁም በስራ አጋጣሚ ተዋውቀን የተቆራኙንን፣ያስተማሩንን፣ ያሳደጉንን፣ እኛነታችንን በመገንባት መንገድ የድርሻቸውን ያዋጡ ባለአሻራዎችን ሰብስባ የምታኖር የቤተሰብ ጎጆ ናት!

Mostrar más
Etiopía10 146Amárico8 067La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
221
Suscriptores
-124 horas
-17 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
LESS IS MORE
Mostrar todo...
✍ ♾ ራስን በክፍልፋይ ካዩት የብዙዎች መዋጮ ነን። ተበታትኖም ተደጋግፎም መልክ ሰርቶልን እኛን ሆነን ተሰፍረን ያየነው ኢምንት ኢምንት በመዋጮ ነው። ሁሌም የማስበው ይህንኑ ነው። ዛሬ የመሰልኩትን ለመምሰል የብዙዎች መለከት ሲነፋ የትኛው በተለየ እኔ ላይ አርፎ እኔን ሰራ እጠይቃለሁ። እንደ ደራሽ በድንገት ደርሰውብን እንደ ወንዝ ግን ሲፈሱብን ለመኖር የሚገጥሙን ሰዎች አወቁትም አላውቁትም ህልውናቸውን ሰጥተውን ሄደዋል። ዛሬና ትላትና ድንበራቸው የየእኩል ነው ሲባል አንዱ የሌላውን ገፅ ይወርስና ትላንት የተፃፈበት ሳይደበዝዝ በሌለኛው ገፅታው በኩል ዛሬ ይነበባል ማለት ነው። አንባቢዎች ታዲያ ግን ብዙ ይላሉ። ትላትሽን እርሽውና ዛሬ አዲስ ቀን ነው ኑሪው ይሉናል። እሺ ብለን እንደ ቃላቸው ትላንትን ብንሰርዝላቸው ዛሬ የሚያነቡትን መሳጭ ስንኝ አብረን ጨምረን እንደምንፍቀው ይስቱታል። መነጣጠል ውስጥ ማማር እንደሌለ ካልሞከሩት አይገባቸውም። ሰው የተፈጠረው ለሰው ነው ብለው ከሚያስቡት ወገን ነኝ። በመስታወት አይደለም እራስ የሚታየው፤ አጠገብ ባለ ሰው ውስጥ እንጂ። ዛሬ በተገኘው የበረከት ስሜት ውስጥ ተነክሮ ትላንትን መስበር አካላዊ ባልሆነ መንገድ የትላንት ሰዎችን ጨምሮ መስበር ነው። የራስ ልብን መስበር እንደማለት በተለዋዋጭ አማርኛ። ከትላትና እና  ከዛሬ ውዥርብኝ ስንወጣ ደግሞ ነገ ወደሚባል የባሰበት አዙሪት እንገባለን። ስለነገ ምንም እርግጠኛ አይደለንም። ከዚህ ይጀምራል ሲያወዛግበን። የወጣት ሊያውም ሴት አለቃ ይዘዝባችሁና (ምርቃት ነው አሜን በሉ) በእኔ ላይ የወራቶች እድሜ ያላት ሴት አለቃ አለችኝ። አንዳንድ ሰዎች ሲያኮርፉኝ ምሳ የምታባላኝ፤ አብረኝ ቡና የምትጠጣ አይነት። ዛሬ ታዲያ ከስራ ሰዐት ውጪ አዲሱን ካፌያቸውን ልታስጎበኘኝና በዛውም ቡና እንድንጠጣ ወደ ቦሌ መሄጃ አከባቢ እያመራን ሳለ ምን ጠየኳት መሰላችሁ በመሀል ፡ _ ሰዎችን ለማመስገን ምን አይነት ጊዜ ትመርጫለሽ አልኳትኝ _ ስለነገ መኖሬን እርግጠኛ ስላልሆንኩኝ ዛሬን እመርጣለሁ፤ ከተቻለኝ ደግሞ አሁንን አለችኝ። ብታንስም ብትበዛም የኔ ከምላት የመኖር እርቀት ላይ ለዛሬዬ የተረፈ ሰው ነው። ቢደረደሩ ውሃ ማንሳት በማይችሉ ቃላቶች ለምን አደክመዋለሁ በሚል ምስጋናዬ ደርሶት አያውቅም። አንዳንድ አመሻሽ ላይ ይሄ ህሊናዬ የሚያጫውተው የቀን ማለዘቢያ ካሴት ምስቅልቅል ያለ እኔነት ላይ ደርሶ ሲያጠነጥን ይሰማኛል። እሱ ባይኖር ኖሮ, ምናልባት እዛ ግሩፕ ላይ ባንገናኝ ኖሮ , ምናልባት ምናልባት ደግሞ እኔ የኳስ ወዳጅ ባልሆን ኖሮ, ምንአልባትም በዛች ሰዐት ኦንላይን ባልሆን ኖሮ , ምናልባትም ደግሞ በመጀመሪያው ቀን ከሌሎች ሰዎች የተለየ ስሜት ለእሱ ባይኖረኝ ኖሮ የእውነት ዛሬ እኔ እኔን እሆን ነበር? የሚል ሙዚቃ ያሰማኛል። ለአንድ ሰው የሚሰላ ክፍያ ምንያህል ነው? ለመሆኑስ ግን በክፍያ ይሰላል? ዝርዝሩ እስቲ ይቅርብኝና እንዲሁ ልኑረው እንዳልል አየህ ቀድማ ለከፈችኝ። ነገ መናገር ባትችይስ ብላ አሳሰበችኝ። አንተስ መስማት ባትችል? ምናልባት ነገ ባይኖርስ? ወይም ነገ ከዛሬ ቢከፋስ የሚል ሰቀቀን ታነበው አታነበው ይድረስህ አይድረስህ ሳላውቅ ወጥተው የልብን በማያረኩ ቃላት ልቤን እየጎተትኩ መፃፌን የግዴ አደረኩት። ባይችሉ እንኳን መጣጣር አለባቸው። የመኖር ክብር የታለ? ስፍራው የት ነው ሲባል ትርጉሙን በመፈለግ ውስጥ ይመስለኛል። በግለሰብ ሲታሰብ ደግሞ ከማንም በፊት የራስ ሀሳብ ተከታይነትና የራስን መስመር እየገመቱ በማስመር በእዛ ውስጥ መጓዝ ሲቻል ትርጉሙ እየተገለጠ ይሄዳል የሚል ሀሳብ ሲያራምደኝ በድንገት ሰዎች የተለየ ነገር ያደረኩኝ ይመስላችኋል። ከእኔ መዋልን አግዝፈው ይመለከቱታል። ሁሉን የጨረስኩኝ አድርገው ይወስዱኛል። እነሱን ለሀሳባቸው ትቼ ወዳራሴ ስመለስ ግን ከአንተ ጋር እላተማለሁ። ባትኖር ማንን እመስል ነበር ፣ መገኛዬ የትስ ነበር ? ይሄኔ አድራሻዬን ሳምስ ወይም የተገኘው ሁሉ አድራሻዬ ነው ስል እገኝ ነበር እላለሁ። ብዙ ማውራት አልችልም። እንዲህ ነው እንዲያ ነው ማለት ይከብዳል። የረገጥኩት ሁሉ ዳናህን ነው። አየህ አይለቀኝም። ለሌላው ማንበብ የሆነው ለእኔ መፃፍ ነውና ከባድ ነው። ስለአንተ ሲሆን ደግሞ በጣም ይከብዳል። በአጭሩ የሚባል ቀላል መታጠፊያ ያጥረዋል። ለዚህ ለዚህ ነገር አመሰግንሃለሁ ልልህ እፈልግና "ለዚህ ለዚህ" እንዴት ነው የሚገለፀው? ስል አቆማለሁ። አንድ የሚቆረቁረኝ ነገር ግን ምንም አላደረኩላትም የሚል ተደጋጋሚ ቃል ነበረህ። ይሄን ሳስብ ዛሬ ላይ የት ይድረሱ የት የማላውቃቸው (ፈልጌ ይሆናል የማላውቃቸው) እነዛ እንደ ውሀ የሚጠሙኝ መሰረቴ የምላቸው ፁሁፎችህን ያስታውሰኛል። ዳግመኛ አያቸው ዘንድ እራሴን ከከለከልኩት አመት የሚደፍኑ ወራቶች በፍቃደኝነት አልፈውኛል። እኩያዬ የሚመስለኝን ዛሬን በትውስታቸው ብቻ አላስገፋ ብለውኛል እንኳንስና አይቻቸው። ግን በልብ ሰሌዳ አስታውሳቸዋለሁ። ከኖርነው እኩል ልረሳቸው አልችልም። እንደነገርኩህ ከሁሉ የሚያሳዝነኝ ምንም አላረኩልሽም የምትለኝ ነው። ምን ብጠበብም በቀሽም ቋንቋ ልንገርህና አንተ በፈጠርክብኝ ማንነት እኔን  ወደው ሳይጨርሱ ... አንተን ጠልተው ከትላንት ላይ ሊያጠፉ ከሚታገሉ ጋር በፍቅር ስም እውላለሁ። ይሄን ሳይ ታዲያ ከአንተ ለእነሱ አዝናለሁ። ባትኖር ኖሮ እኔን እንደማያገኙ ማን በነገራቸው እላለሁ። ዛሬ ከላዬ ላይ እየጠቀሱ የሚያደንቁትን ነገር፤ ሳይበርድ ከአፋቸው ላይ ተቀብዬ ይሄን እኮ እሱ ነው የሰጠኝ እኔ ትንሽ ነው የጨመርኩት ብላቸው አይዋጥላቸውም! እንዲህ ሲሆን ታዲያ "እየቀለጠ ሊያበራላቸው፤ እየዘቀጠ ካብ ሊሆናቸው" የሚል ስንኝ ልቤን ያሞቀኛል። ሲቆይ ደግሞ ይሰብረኛል። ትላንት የወደድነው ለዛሬ መጠለያ ይሆናል። ለዛሬው ህይወታችን እንቅፋት ሳይሆን መሰረት ነው ብል የሚሰማ ጠፋ። (እስቲ ተለመን ይሄ ለአንተ ነው። ምክንያቱም ይሄን ለእሱ ልለው አልችልም ለኔም የነገረኝ እራሱ ነው።)  የትላንቴ አድማስ ብትሆንም ዛሬ ላይ የነበር ብርሀንህ ከፊቴ በምረግጥበት ሁሉ ይነጠፋል። በቃ እንዲህ ነው። የሆነውን ከመሆን ውጪ ምንም መሆን አንችልም። ብርሀኑን ወዶ ሰጪውን መጥላት ደግሞ አይገባም። ለአንድ ሰው የሚበቃው ምስጋና ምን ያህል ነው? አመሰግናለሁ ብቻ ለእኔ ተራ ሆኖብኛል
Mostrar todo...
Ali Gatie - Moonlight.mp38.73 MB
ሄዶን የትላንት እንግዳ ቀብሮ ያከሰለው ያጋየውን እሳት አንተን ሆኖ ላየው መች ተደገምክ ይላል ሲፈቅድህ ቢከስም የነበር ህያው መልክ ሙት አይከሰስም። ከተዘጋ መዝገብ ጠባቂ አልባ ግዛት ከተሰደረ ገፅ ስርዓት አልባ ቃላት ባልተገራ መቸር በከሸፈ እሺታ የደበዘዘ እውነት በሰው መሆን ሽታ ለታምር ሲፈጠር ሲደገስ ትዝብቱ መሸነፍ አይደለም መታገል ነው ሞቱ ። መ ረ ቅ
Mostrar todo...
ሄዶን ከ'ልፍ የህይወት ጅረቶች በተጨለፉ እልፍ ስቃዮች የነቃ አዕምሮ የሰው መሆንን አቅም ሊለካ በማሰብ ሲጠመድ ልክ የተበጀለት ደካማነታችን ከልኬት አልባው የራስ መውደዳችን ስሜት እየተጋጨ ከዛሬ አልፎ ለነገ ብሎም እስከ ሞት አፋፍ ድረስ ለሚኖረን ጉዞ ረብ አልባ የከንቱ መሆን ስሜት ይቸረናል። ይህ የማይናድ የሚመስል ጥሬ እውነት ተጨባጭ ግንዛቤ ባላበጀንለትና ከንቱ ባልነው የስጋ ስሜት መሟላት በቀላሉ የሚከስም እንዲሁም ከንቱ ባልነው የስጋ ስሜት መጉደልና በመሰልቸት ስሜት ገዝፎ የሚያጠላ የተጭበረበረ እውነት መሆኑን ስንቶቻችን አስተውለናል? "ሰው መሆን ከንቱ !" የመኖር ድርጊቶችን መሰረት ያደረገ ግንዛቤ ሲሆን በሞት ካልሆነ በምን ይገለፃል? እናም እላለሁ መሸ ያልነውን ቀን ነግቶ እስካየነው ገና ተስፋ አልቆረጥንም!! መ ረ ቅ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
𝚈𝚘𝚞 𝚊𝚛𝚎 𝚜𝚘 𝚋𝚛𝚊𝚟𝚎 𝚊𝚗𝚍 𝚚𝚞𝚒𝚎𝚝 𝙸 𝚏𝚘𝚛𝚐𝚎𝚝 𝚢𝚘𝚞 𝚊𝚛𝚎 𝚜𝚞𝚏𝚏𝚎𝚛𝚒𝚗𝚐. 𝙴𝚛𝚗𝚎𝚜𝚝 𝙷𝚎𝚖𝚒𝚗𝚐𝚠𝚊𝚢 | 𝙰𝚛𝚝 : 𝙿𝚊𝚛𝚒𝚜𝚊 𝙺𝚊𝚛𝚘𝚘𝚗. Via - sost kilo
Mostrar todo...
እናም የፈጠርከን.. ከድውያን ሁሉ የኔን ድምፅ ሰምተህ ዐይኔን ስታበራ. እኔ ፍርድ አሎድም ለማየው ጉድ ሁሉ ሚዛን አንተ ስራ..
Mostrar todo...
Ejigayehu_Shibabaw_GIGI_እጅጋየሁ_ሽባባው_ጂጂ_Ethiopian_Music_ናፈቀኝ_Nafekeñ0.m4a4.99 MB
ደገኛው ቄስ ሞገስ በፈረስ ተራራ ገደሉን አቋርጦ እነ ጂጂ ቤት ይሄዳል:: ሲደርስ ሁሉንም አሳልሞ ወደ ቤት ሲዘልቅ ቤተሰብ ጎረቤቱ እልል እያሉ ቄስ ሞገስን ሲቀበሉ ፣ አያና ድማሙ ከ'ነጂጂ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ትልቅ ዋርካ ላይ ተቀምጦ ዋሺንት ሲጫወት ፤ ጂጂ ወደ ዋርካው ሮጣ ሄዳ ጥላው ስር ቁጭ ብላ አያና ድማሙን በተመስጦ ስታዳምጥ ፤ አባቷ አያ ሽባባው "ተነስተሽ ወደ ቤት ግቢ" ብለው ሊገርፏት ሲወጡ ጎረቤታቸው አያ ታዴ (ጂጂን ሆዴ እያሉ የሚጠሩት) ጂጂን ከግርፋት ለማዳን አያ ሽባባወን ልመና ዘብ ሲቆሙና "ተው እንጂ አያ ሽባባው የገና በዓልም አይደል እንዴ ትጫወት እንጂ ይልቅ ገብተው ከቄስ ሞገሴ ጋር ሆነው ቤተሰቡን ይመርቁ" እያሉ ሲመልሷቸው፤ አያ ሽባባውም በቀዬው የከበሩት የከብቶች ጌታ ወደ ግቢያቸው ገብተው ከእነ ውሃ ጃሪ ፤ ውሃ ኩሉ ማደሪያ በረት ውስጥ ሙክት በግ አውጥተው ባርከው ሲያርዱ:: የቀየው ወጣቶችም ለገና ጨዋታ ሽመል ይዘው ሆ እያሉ አያ ሽባባው ሲመጡ:: በዛም ተሰብሰበው ማዕድ ሲጋሩ ሲበሉ ሲጠጡ ፣ አያ ሽባባውም ብሉ ጠጡ ተጨወቱ.... ሲሉ በጂጂ (ናፈቀኝ) ዘፈን ውስጥ ይታየኛል... ♪♪ ናፈቀኝ ደገኛው ቄስ ሞገስ በፈረስ በበቅሎ ተጉዞ ሲመጣ በአመት በዓል ጨዋታ ሰው እልል እያለ ሲቀበል በምቢልታ አንተዬይ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ የሀገሩ ገነኛ ሆ እያለ ሲመጣ አባዬ ናፈቀኝ የከብቶቹ ጌታ ሲባርክ ሲመርቅ የቤቱን ጨዋታ ዮአኪን ቻፒ እንደጻፈው ...
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
መልካም ልደት ንግስቷ
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.