cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መረጃ 24 ሰአት

ቶሎ ቶሎ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶት ላይክ እና ሼር አርጉ ፈጠን ፈጠን ብለን መረጃን አንለቃለን ላይክ ያርጉ ፈጠን በሉ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 018
Suscriptores
-124 horas
-97 días
-1330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ከ100 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዘ ፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ በበኩሉ በሱዳን ጦር ጋር ካምፖች ላይ እንጂ በንጹሃን ላይ ጥቃት አለመፈጸሙን አስታውቋል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን ከ100 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዘ። የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ በጀዚራህ ግዛት ዋድ አል ኑራ በተባለው አካባቢ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል (አርኤስኤፍ) ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት አጥብቀው መቃወማቸውን ቃልአቀባያቸው ስፌፋን ዱጃሬክ ተናግረዋል። በሱዳን እየተፋለሙ የሚገኙት ሃይሎች ንጹሃንን ኢላማ ካደረገ ጥቃት እንዲቆጠቡም አሳስበዋል። በጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ሃይል ከትናንት በስቲያ በዋድ አል ኑራ በከባድ መሳሪያዎች ጭምር በፈጸመው ጥቃት 104 ንጹሃን መገደላቸውን “መዲና ሬዚስታንስ ኮሚቴ” የተባለው የመብት ተሟጋች ገልጿል። የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪና ሩሴል ባወጡት መግለጫም በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈው ውስጥ 35ቱ ህጻናት መሆናቸውን መግለጻቸውን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል። በሱዳን በቀጣይ ወራት 5 ሚሊየን ሰዎች ለከባድ ረሃብ ይጋለጣሉ - ተመድ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል በበኩሉ የቀረበበትን ክስ ውድቅ አድርጓል። የሱዳን ጦር በጀበል አል አውሊያ ጥቃት ሊከፍትብን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ስንረዳ በዋድ አል ኑራ በሚገኙ ሶስት ካምፖቹ ላይ ጥቃት ፈጽመናል እንጂ ንጹሃን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አላደረስንም ሲልም በኤክስ (ትዊተር) ገጹ ላይ አስፍሯል። የዋድ አል ኑራ ነዋሪዎች የተገደሉት በሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች መሆኑንም ነው ያብራራው። በሱዳን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባዋ ክሌመንታይን ንዌታ ሳላሚ በበኩላቸው ተፋላሚዎቹ አካላት ህዝብ በሚኖርባቸው ከተሞችና መንደሮች በከባድ መሳሪያዎች መዋጋታቸው የንጹሃንን ህይወት መቅጠፉን ተናግረዋል። በዋድ አል ኑራ የተፈጸመው ጥቃት በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ተጠያቂነት እንዲሰፍንም ጥሪ አቅርበዋል። ኦማር ሀሰን አልበሽርን ከስልጣን ለማንሳት የተባበሩት ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር የጀመሩት ጦርነት ከ14 ሺህ በላይ ሱዳናውያንን ህይወት ቀጥፏል። ጦርነቱ በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉና ወደ ጎረቤት ሀገራት የተሰደዱ ሱዳናውያንን ቁጥር 9 ሚሊየን በማድረስ ምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር በተፈናቃይ ብዛት ከአለም ቀዳሚዋ አድርጓታል። ሳኡዲ አረቢያ፣ የኢጋድ መቀመጫዋ ጂቡቲ እና ኬንያ ተፋላሚዎቹን ጀነራሎች ፊት ለፊት ለማደራደር ያደርጓቸው ጥረቶችም ሳይሳኩ ቀርተው ፍልሚያቸው የሱዳናውያንን ሰቆቃ ማባባሱን ቀጥሏል።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
2👍 1
በጀት‼️ ለ2017 ዓ.ም የቀረበው ወደ 1 ትሪሊየን ብር የሚጠጋ የመንግስት በጀት ለምክር ቤቱ ተላከ‼️ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2017 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ፤ የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ ተደርጓል። በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣ ለካፒታል ወጪዎች ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ነው። በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሰፊ ሥራዎች ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካላት የቆዳ ስፋት ከግማሽ በላይ የሆነው የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ለማድረግ፣ የደን ዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በአሁኑ ወቅት በተበጣጠሰ መልኩ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በክልል መንግስታት ፋይናንስ እየተደረገ እየተሰራ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተቀናጀና ተገቢውን ሀብት መመደብ በሚያስችል የፋይናንስ አሰራር ስርዓት መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ከዕሁድ'ለት ጀምሮ መቋረጡን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዕሁድ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከጎንደር ወደ ባሕርዳር እንዲኹም ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ እንደኾኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶቹ የተዘጉት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ባስቀመጡት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክልከላ ምክንያት መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ላለፉት አራት ቀናት ከባሕርዳር ወደ ኹሉም የጎንደር አካባቢዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልጸዋል። ከ10 ቀናት በፊት በሦስቱ የጎጃም ዞኖች ተመሳሳይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ እንደነበር ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል። አንድ ጊዜ ለአራት ወራት የተራዘመውና ባጠቃላይ ለ10 ወራት የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ለኹለተኛ ጊዜ ሳይራዘም ትናንት አብቅቷል። ኾኖም መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማብቃቱ በይፋ ያለው ነገር የለም።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2