cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሚዛናዊ ሕይወት

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ፣ ያዝናናሉ ብየ/ለን ያሰብኩት/ናቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ channelና ካነበብናቸው እያሰባሰብኩ/ን አቀርባለው/ን። የአንድ አስተሳሰብ እስረኛ አትሁን። የሰው ልጅ ብስለት የሚለካው አንድ አስተሳሰብ ላይ ሙጥኝ በማለት ሳይሆን የተለያዩ አስተሳሰቦችን በብቃት ማስተናገድ የሚችል አእምሮ በመገንባት እንደሆነ እወቅ። Creator @ela_T

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
198
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የፍቅር ዋጋ! የነገሮች ውድነት ሳይኖሩ ሲቀሩ ይገባናል። የሰላም ዋጋ ክብደት በአለመረጋጋትና ሰላም በማጣት ወቅት ይታወቀናል፤ የመልካም ግንኙነት ዋጋ መግባባት ሲሳነንና ልዩነቶች እየበዙ ሲሔዱ ይገባናል። የፍቅርም ዋጋ እንዲሁ ሳይኖር ሲቀር፣ መገፋፋትና ጥላቻ ሲበዛ ይታወቀናል። ከአንድነት ብዙ ያተረፈ አለ፣ በልዩነት ግን ብዙዎች ወደ ጥፋት ተቃርበዋል፤ በፍቅር ትላልቅ አቀበቶችን መሻገር ተችሏል፣ በጥላቻ ግን ካለንበት ደረጃም መሻሻል አልቻልንም። እስከ መቼ ትናንትን እንደምንኖር፣ በትናንት እንደምንቃረን፣ በታሪክ እንደምንነታረክ አምላክ ያውቃል። ጭፍን እራስ ወዳድነት እኔ ብቻ ከማለት የተለየ አስተሳሰብ የለውም። የዛሬ ህይወታችን የእኛ ብቻ አይደለም፤ እኛ የኖርነውን ህይወት ቀጣይ ትውልዶቹ ልጆቻችንን እንዲኖሩት ካልፈለግን መሰረቱን በፍቅር ላይ መገንባት ይኖርብናል። #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊 #ነገ_መልካም_ነው 🏞 @mizanawihewot
Mostrar todo...
አንዳንዴ ለራስህ ያለህ ግምት ያነሰና በራስ መተማመንህ ዝቅተኛ ሲሆን ሽፋንህን በኩራትና በራስ መተማመኑ ከፍ ባለ በሚመስል ታትመዋለህ። ግን ትርፉ ጉዳት ነው ሽፋን ሌላ ውስጡ ሌላ!       በመጀመሪያ ስለውጪው አትጨነቅ ውስጡን አሳምረው ፣ ገጹን አስውበው! የውስጡ ውበት ውጪውን ስለሚያፈካው!!! (አላዛር ቴዎድሮስ) #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊
Mostrar todo...
“የራስን ሁኔታ እያዩ ሲያዝኑና ከንፈር ሲመጥጡ መኖር ክፉ የተባለው ጠላታችን ነው፡፡ ለዚህ ጠላት ራሳችንን አሳልፈን ከሰጠነው በዚህ ዓለም ውስጥ ምንም ጥበብ የሞላው ነገር ማድረግ አንችልም” – Hellen Keller አንተ “ጎዶሎዬ ይህ ነው” ብለህ ከምታስበው ሁኔታህ እጅግ የባሰ ሁኔታ ውስጥ እያለ የተሟላ ሕይወት የሚኖር ሰው እንዳለ ላስታውስህ፡፡ በአንጻሩም፣ ሙሉ፣ ስኬታማና ደስተኛ ሆኜ ለመኖር ይህኛውና ያኛው ያስፈልኛል ብለህ የምታስባቸውን ነገሮችና ከዚያም በላይ እያላቸው በጣም አሳዛኝና ያልተሟላ ሕይወት የሚኖሩም ሰዎች እንዳሉም ላስታውስህ፡፡ “አንገትህን በፍጹም አታቀርቅር፡፡ ሁልጊዜ ቀና በል፡፡ ይህችን አለም አይን አይኗን ተመልክተሃት በድፍረት ኑር” – Hellen Keller- #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊 #ነገ_መልካም_ነው 🏞
Mostrar todo...
ሰላም አግኝ! እዘኑ አዝናችሁም ሰላም አግኙ ፤ በመከራም አመስግኑ ፤ ስሙንም አወድሱ ፤ በቃሉም ተፅናኑ ፣ በአስቦቱም እረፉ ። የአምላክ ቃል ህያው ነው ፤ ስም የሚሰጠውና ትርጉሙን የሚያዛባው ሰው ደግሞ በሚታየው ስጋው ጠፊ ነው ። ማንም ሰላምን ቢፈልግ ዋጋ ይከፍላል ፤ ማንም ስረዓትን ሊያሰፍን ቢወድ ዋጋ ይከፍላል ፤ ማንም ለእምነቱ መታመንን ቢወድ ዋጋ ይከፍላል ። አዛኝ ሃዘኑን የረሳ እለት ሌላ አለም ይታየዋል፤ ተረጂ ከእርዳታ ሲላቀቅ አዲስ ህይወት ይጀምራል ። የክፋትን አስከፊነት ፣ የጥፋትን ነውርነት በልቡ እያወቀ የክፉ የሆነና የሚያጠፋ ግን መጥፊያውን እንደሚያበጃጅ ያውቀዋል ። አንዳንዶች በእርግጥም መጪው ይታወቃቸዋል ፤ የታቀደው ተገልጦላቸዋል ፤ ሃሳቡ ገብቷቸዋል ፤ ነገር ግን ማድርግ የሚገባቸውን ለማድረግ አቅም ያንሳቸዋል ። #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊 #ነገ_መልካም_ነው 🏞 @mizanawihewot
Mostrar todo...
ሰላም አግኝ! እዘኑ አዝናችሁም ሰላም አግኙ ፤ በመከራም አመስግኑ ፤ ስሙንም አወድሱ ፤ በቃሉም ተፅናኑ ፣ በአስቦቱም እረፉ ። የአምላክ ቃል ህያው ነው ፤ ስም የሚሰጠውና ትርጉሙን የሚያዛባው ሰው ደግሞ በሚታየው ስጋው ጠፊ ነው ። ማንም ሰላምን ቢፈልግ ዋጋ ይከፍላል ፤ ማንም ስረዓትን ሊያሰፍን ቢወድ ዋጋ ይከፍላል ፤ ማንም ለእምነቱ መታመንን ቢወድ ዋጋ ይከፍላል ። አዛኝ ሃዘኑን የረሳ እለት ሌላ አለም ይታየዋል፤ ተረጂ ከእርዳታ ሲላቀቅ አዲስ ህይወት ይጀምራል ። የክፋትን አስከፊነት ፣ የጥፋትን ነውርነት በልቡ እያወቀ የክፉ የሆነና የሚያጠፋ ግን መጥፊያውን እንደሚያበጃጅ ያውቀዋል ። አንዳንዶች በእርግጥም መጪው ይታወቃቸዋል ፤ የታቀደው ተገልጦላቸዋል ፤ ሃሳቡ ገብቷቸዋል ፤ ነገር ግን ማድርግ የሚገባቸውን ለማድረግ አቅም ያንሳቸዋል ። ስራውን ለሰሪው የመተው ብርታት ይኑርህ ፤ ብርቱው ይበረታ ዘንድ ፣ ጀግና ነኝ ባዩ ይጀግን ዘንድ ተወው ። አላዋቂ በትንሿ እውቀቱ ተጠልፎ ይወድቃል ፤ በጉልበቱ የሚመካ ፣ እብሪት የያዘውም መጨረሻው የተለየ አይደለም ። የከረረውን በማላላት ማሸነፍ ትችላለህ ፤ እምነትህን በማጠንከር ፣ ፅናትህን በማዳበር ፣ ምግባርህን በማሳመር ሰላምን ማምጣት ፣ ፍቅርን ማውረድ ፣ መልካምነትን ማስተጋባት ትችላለህ ። ብልህ ሰው የሚያዋጣውን ከጦርነቱ በፊት ያውቀዋል ፤ ለድል የሚያበቃውን ስልት ቀድሞ ያስቀምጣል ። ማንም አጥፊ በመረጠው መንገድ አትጓዝ ፤ አብሮህ ስላለው አምላክ ለሰከንዳት ማሰብ ጀምር ። ሰላምህ በእጅህ እንዳለ አስተውል ። የበደልህ ምላሽ ሁሌም ቀጥታ የሚመለስ አይደለም ። በማይታሰብ መንገድ እራስህን ነፃ ታወጣለህ ፤ ጥላቻን ትገፋለህ ፤ ሰላምህንም በእራስህ ታገኛለህ ። #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊 #ነገ_መልካም_ነው 🏞 @mizanawihewot
Mostrar todo...
ታሞ ለማያቅ ሰው መታመምህን አትንገረው!! #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊
Mostrar todo...
መሰረትህን አጥብቅ! ቅዱስ መፅሐፍ እንዲህ ይላል "ነፋሳት ነፈሱ ያንቤት ገፉት በዓለት ላይም ስለተመሰረተ አልወደቀም።" የምንም ነገር መሰረት ከምንም በላይ ወሳኝ ነው። አንድ ነገር ስትፈፅም ምክንያት ያስፈልግሃል፤ ምክንያትህም ወደፊት የሚያሻግርህና እርምጃህን የሚፋጣን፣ እስከ ጥግም የሚያታግልህ ነው። ብዙ መጥፎ አጀንዳዎች ሊሰጡህ ይችላሉ፤ ብዙ ነገሮችን የማምታት ጉዳዮች ሊደርሱብህ ይችላሉ ነገር ግን ከጀርባህ ዋጋ ለመክፈል እንኳን የማትሰስትለት ምክንያት ካለህ ማንም ምንም ሊበግርህ አይችልም። አንተ የምታምነውን እምነት ማንም አያምንልህም፤ አንተ ያለህን ፅናት ማንም አይኖረውም፤ ያንተን ድፍረትና ወኔ ማንም አያገኘውም። ውስጥህ ያለው ሃይል በቀላሉ የሚረበሽና የሚሸበር አይደለም። ስም ቢያሰጥህ፣ ለእንግልት ቢያበቃህ፣ ዋጋ ቢያስከፍልህ፣ ቢያስለቅስህ ቢያስነባህ እጅ የምትሰጥለት አይደለም። የቤትህ መሰረት አለት ከሆነ አትወድቅም፤ አሸዋ ከሆነ ግን መውደቅህ አይቀርም። አለት ጥብቅ መሰረት ነው፤ የሚያናውጠው የለም። በአሸዋ ላይ የተመሰረተ ቤት አውሎ ንፋስ ይነቀንቀዋል፤ መሰረቱን ይነቅለዋል፤ እድሜውን ያሳጣዋል፤ ያልተገባ ስፍራ ያደርሰዋል። ቤትህን በአለት ላይ ገንባ፤ ለየትኛውም ተግባርህ ምክንያት ይኑርህ፤ በጥበብ ተመራ፤ እውቀትን ተጠቀም፤ ከየትኛውም ውጫዊ ጫና እራስህን ነፃ አድርግ። ከተበታተነ ሃሳብ ውጣ፤ እራስህን ሰብስብ፤ በምግባር ተመራ፤ ስረዓትን በእራስህ ላይ ሹም፤ በፈቃድህ ለአምላክህ ታመንለት፤ እራስህን አስገዛለት። በእያንዳንዱ እርምጃህ ለምን እንደምትራመድ በጥልቀት እወቀው። መሪህ ምድራዊ ቁስ ሳይሆን ሰማያዊ ህያው ዙፋን እንደሆነ አስተውል። ቸር ቀን ይሁንልን! #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊 #ነገ_መልካም_ነው 🏞 @mizanawihewot
Mostrar todo...
አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከልብህ አስቀድሞ እግርህ ይሔዳል ይህ ያለፋኻል። አንዳንዱ ጋር ደግሞ ከዕግርህ በፊት ልብህ ይሔዳል ይሔ በከፊል የተሻለ ነው! እግር እንድሔድ ልብ ሞተር ሊሆን ይችለዋልና። ከሁሉ ግን ልብና እግር ተስማምተው ቢሔዱ ግኝታቸው ጥሩ ይሆናል!!! #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊
Mostrar todo...
@he_NO_k19 እባክህ አንተ እንኳ ቅረበኝ ከዚህ ሀዘን ለጊዜውም አውጣኝ እንቅልፉ ናና ውሰደኝ 😴😴                             ብለው ብለምነው    እንደሰው ጨከነ የለም አልወሰደኝ       ሁሉ ሲያንቀላፋ ምን በድዬ ይሆን እኔን የሚያለፋ ወሰደ አስተኛ ሁሉን አታለለ ምን አጥፍቼ ይሆን እኔን ያልከጀለ                                እንጃ?📷kiya #ሚዛናዊ_አስተሳሰብ_ለሚዛናዊ_ሕይወት 🕊 #ነገ_መልካም_ነው 🏞
Mostrar todo...