cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Wolaita Sodo University

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University Our Official Website : http://www.wsu.edu.et/ Our Official Facebook page : https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
18 754
Suscriptores
+2624 horas
+1097 días
+23530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለዳዉሮ ታርጫ ካምፓስ መምህራን የምርምር አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለዳዉሮ ታርጫ ካምፓስ መምህራን በቴማቲክ የምርምር ንድፈ-ሃሳብ አዘገጃጀት እና የምርምር ፕሮጀክት ሃብት አፈላለግ ስልት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ለተወጣጡ መምህራን በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው ላይ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውድነህ ቶማስ እንደገለጹት በምርምር ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንዲቻል ዩኒቨርሲቲው እንደ ከፍተኛ የአፕላይድ ሳይንስ ትምህርት ተቋም በያዘው ራዕይና የተልዕኮ አቅጣጫዎች፣ በልየታ በተሰጡት የትኩረት መስኮች እንዲሁም አካባቢያዊ ጸጋዎችን መሠረት በማድርግ የመምህራንን አቅም በማጎልበት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት በጥራት እንዲተገበር በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ግዜያት ጥራት ላለው የምርምር ሥራዎች መጎልበት ለመምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱን ምክትል ፕሬዝዳንቱ የገለጹ ሲሆን፤ ለዳዉሮ ታርጫ ካምፓስ መምህራን በቴማቲክ የምርምር ንድፈ-ሃሳብ አዘገጃጀት እና የምርምር ፕሮጀክት ሃብት አፈላለግ ስልት ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠቱንም አሳውቀዋል። ሥልጠናው ተመራማሪዎች በግልም ይሁን በጋራ ለሚሰሯቸው የምርምር ስራዎች የበለጠ መነሳሳት እና ልምድ እንዲለዋወጡ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ዶ/ር ዘውድነህ ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በዚህ የማያበቃ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ የ2017 በጀት ዓመት በዕቅድ ተይዞ እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ዶክተር ዘውድነህ ከተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት ያገኙትን ተሞክሯቸውንና ልምዳቸውን ለስልጠናው ተሳታፊዎች አጋርተዋል። ስልጠናው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ መምህራን በሆኑት ዶ/ር ታገሰ አቦ እና ዶ/ር ሲሳይ በላይ “How to find research grant and wiriting proposal” በሚል ርዕስ ተሰጥቷል። ሥልጠናው በርካታ ነገሮችን እንድናውቅና ስለ ምርምር ብዙ ማንበብና መዘጋጀት እንዳለብን የሚያስገነዝብ ነው ሲሉ በስልጠናው የተሳተፉ መምህራን ጠቁመዋል። በስልጠናው ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች የተወጣጡ ከ30 በላይ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን፤ ይህንን መሰል የአቅም ማጎልበቻ መድረክ ቀጣይነት እንዲኖረው አስተያየት ሰጥተዋል። ➭ «ዕውቀትን በተግባር!!» 📷የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!! ➤ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም (ወሶዩ) ◼ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ🔻 ▪Telegram ➲ https://t.me/WolaitaSUniversity ▪Facebook ➲ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424 ▪YouTube ➲ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos Website ➲ http://www.wsu.edu.et/
Mostrar todo...
Wolaita Sodo University

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University Our Official Website : http://www.wsu.edu.et/ Our Official Facebook page :

https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

👍 6 2
Mostrar todo...
Marketing_Management_Philip_Kotler,_Kevin_Lane_Kel.pdf21.48 MB
👍 3
📚Management Accounting: Principles and Applications ✍Hugh Coombs, David Hobbs and Ellis Jenkins For more Books Join Us ━━━━━━━━━━━━━━━ ♡❤️ ✍🏻📩  📥⎙   📤 ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ     @ t.me/BookzHorizon ━━━━━━━━━━━━━━━
Mostrar todo...
Management_Accounting_Principles_and_Applications_PDFDrive_.pdf1.26 MB
👍 3 2🙏 1
📚Financial Management: Theory and Practice ✍Eugene F. Brigham (University of Florida) & Michael C. Ehrhardt (University of Tennessee) For more Books Join Us ━━━━━━━━━━━━━━━ ♡❤️ ✍🏻📩  📥⎙   📤 ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ     @ t.me/BookzHorizon ━━━━━━━━━━━━━━━
Mostrar todo...
Financial Management -Theory & Practice.pdf12.23 MB
👍 3🙏 1
A_History_of_World_Literature.pdf4.25 MB
1
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ በተለያየ ምክንያት የ “ Management, Business administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship” ፈተና ያልወሰዳችሁ ተፈታኞች ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደተመደባችሁበት ተቋም በመሄድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ማሳሰቢያ • ሁሉም ተፈታኞ ፈተናው ከመጀመሩ ከ 30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣብያ መገኘት ይኖርባቸዋል፣ • ሁሉም ተፈታኞ User Name Password ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።
Mostrar todo...
👍 12 1
በዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች "የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና" በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል። በ 2015 ዓ.ም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠት የተጀመረው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ዘንድሮም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማካሄድ ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል። ለቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ በመታገዝ የሚሰጠው መውጫ ፈተና እስከ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን፤ ከመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ አዲስ እና ድጋሚ ለፈተና የሚቀመጡ 4 ሺህ 266 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ፈተናውን የሚወስዱ መሆኑ ተመላክቷል። በዛሬው ዕለት ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ መሰጠት በጀመረው የመውጫ ፈተና በዩኒቨርሲቲው ዕጩ ተመራቂ የሆኑ የማኔጅመንት፣ ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እና ዲቨሎፕመንት ማኔጅመንት ተማሪዎች ተሰጥቷል። በዩኒቨርሲቲው ዛሬ በተጀመረው መውጫ ፈተና ሂደት 1 ሺህ 160 ተማሪዎች የተቀመጡ መሆኑንና የፈተና ደንብ ጥሰት ሳይፈጸም የዕለቱ መርሃ ግብር በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል። ለፈተናው ውጤታማነት አስፈጻሚ ግብረኃይሉን በማመስገን ፤ በነገው ዕለትም ሂደቱ የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንዲሚገባ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር አሳስቧል። ነገ ሰኔ 15/2016 የፈተናው ሂደት ሲቀጥል ጠዋትና ከሰዓት በአካውንቲንግ፣ አካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ አግሪካልቸራል ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ አርባን ላንድ አድሚኒስትሬሽን፣ ቬተርነሪ ሜዲሲን እና በኬሚስትሪ የትምህርት መስኮች መውጫ ፈተናው ይሰጣል። ➭ «ዕውቀትን በተግባር!!» 📷የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!! ➤ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (ወሶዩ) ◼ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ🔻 ▪Telegram ➲ https://t.me/WolaitaSUniversity ▪Facebook ➲ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424 ▪YouTube ➲ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos Website ➲ http://www.wsu.edu.et/ አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን🙏🙏
Mostrar todo...
Wolaita Sodo University

This is the official telegram channel of Wolaita Sodo University Our Official Website : http://www.wsu.edu.et/ Our Official Facebook page :

https://m.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804

👍 3🙏 2 1👏 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.