cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

Mostrar más
Advertising posts
497Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🇪🇹🇪🇹#እንኳን_ለ፳፻፲፭_ዓመተ_ምሕረት ለበዓለ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ******************              #በዓለ_ጥምቀት ******************* የጥምቀት ትርጉም፡- ጥምቀት የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። ጥምቀት በፅርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒ፣ በግእዝ አስተርእዮ፣ በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው፡፡  ምሥጢረ ጥምቀት በምሥጢራዊ ፍቺው በተጸለየበት ውሓ (ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው (ማቴ ፳፰፡፲፱)። ምሥጢር ማለት የተደበቀ፣ የተሸሸገ፣ ለሁሉ የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ለአመኑት እንጅ ላላመኑት የማይነገር በመሆኑና በሚታይና በሚሰማ አግልግሎት በኢየሱስ ክርስቶስ ማይ ገቦ ተጠምቀን የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንገኛለን፤ ይህን በእምነት የምንቀበለው ስለሆነ ነው፡፡ ካህኑ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ስመ ሥላሴን ጠርቶ ጸሎት ሲደርግና መጸሐፈ ክርስትና ጽሎት ሲያደርግበት ውሐው ወደ ማይ ገቦ (ማየ ሕይወት ሲሆን) ስለማይተየን ምሥጢር ጥምቀት ተብሏል። #እንኳን_ለብርሃነ_ጥምቀቱ #በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። መልካም የጥምቀት በዓል! Baga Ayyaana Cuuphaa Nagaan Geessan! Ayyaana Gaarii ርሑስ በዓል ጥምቀት! https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop 🟢ሠናይ🟡ሶቤ🔴
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

#ጥምቀት_በኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹 \\\\\\\\\\\\ ////////////////// በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀው የንግሥት ሕንደኬ በጅሮንድ አቤላክ(ባኮስ) ‹‹እነሆ ውሃ አለ፣ ታድያ መጠመቅን ማን ይከለክለኛል?›› /የሐዋ. ፷፥፳፱-፴፮/ ብሎ በሐዋርያው ፊልጶስ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ሥርዐት ግን ተስፋፍቶ የቀጠለው በነገሥታቱ በአብርሃ ወአጽብሐ (315-351ዓ.ም.) የቤተ መንግሥቱ ጃንደረባ በነበረውና ኋላ ጳጳስ በሆነው በፍሬምናጦስ(አባ ሰላማ) ዘመን ነው፡፡ በዓሉ ግን አሁን በምናከብረው ዓይነት ሥዕላዊ በሆነ መልኩ መከበር የጀመረው ከማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ ዜማ መስፋፋት ጋራ በአፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (530-544ዓ.ም.) እንደሆነ ይነገራል፡፡ ፠ ገዳማቱና አድባራቱም በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የውኃ ምንጮች በተናጥል በመውረድ በዓለ ጥምቀትን ያከብሩ ነበር፡፡ ተቀራርበው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያሳድሩ ዐዋጅ የታወጀው፥ ትእዛዝ የተላለፈው በጻድቁና በጠቢቡ ንጉሥ ላልይበላ(1140-1180ዓ.ም.) ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ በዚሁ ዘመን የነበሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአኵሱም በመቀለና በመርጡለ ማርያም ያሉ ጥምቀተ ባሕሮችን ባርከዋል፤ በአፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን ደግሞ በአቡነ ተክለሃይማኖት አሳሳቢነት ሥርዐተ ጥምቀቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዐዋጅ ታውጇል፡፡ እስከ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ድረስም ታቦታቱ ዕለቱን ጠዋት ወጥተው ማታ ይመለሱ ነበር፤ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግን ታቦታቱ በዋዜማው ጥር 10 ከሰዐት በኋላ ወደ ትምቀተ ባሕር ወርደው እንዲያድሩ፤ አገሩንም በኪደተ እግር እንዲባርኩ፤ በሄዱበት መንገድም እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ቀጥሎም አፄ ናዖድ ሕዝቡ ታቦታቱን አጅቦ ወደ ጥምቀተ ባሕር እንዲሄድ በዐዋጅ አስነገሩ፡፡ ይህ ሥርዐትም እስካሁን ከኛ ዘንድ ደርሷል፡፡ በዘመናት ውስጥም የጥምቀት በዓል ሲከበርባቸው ከነበሩ ቦታዎች ዐበይቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤ #በአኵሱም_የንግሥተ_ሳባ_መዋኛ_ ‹‹#ማይ_ሹም›› #በጎንደር_የአፄ_ፋሲል_መዋኛ_ገንዳ #በቅዱስ_ላሊበላ_የዮርዳኖስ_ወንዝ #በሸዋ_የአፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_ፍርድ_መስጫ_አደባባይ #44ት #ታቦታት_የሚያድሩበት_የሸንኮራ_ሜዳ ‹‹#ኢራንቡቴ_ጥምቀተ_ባሕር›› #በአዲስ_አበባ_የጃንሆይ_ሜዳ_ (ጃንሜዳ) #በአዲስ_አበባ_የእንጦጦ_ማርያምና_ቅዱስ_ራጕኤል_ታቦት_ማደሪያ #ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ ዐበይቶቹ ናቸው፡፡ ምንጭ፦ በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ :: https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop 🟢ሠናይ🟡ሶቤ🔴
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

🇪🇹 #የገና__ዛፍ🎄 \\\//// የቀጠለ.. 👉ይህ እጅግ አሳዘኝ ነገር ነው በእውነት! በአንድ ወቅት በምዕራባውያን የገና በዓል ሰሞን በ‹BBC channel 4› ላይ የበዓል መርሀ ግብር /program/ ቀርቦ ነበር። በመርሀ ግብሩ ላይ የተለያዩ የዕምነት ድርጅቶች የበዓል አከባበር፣የጸሎትና የመዝሙር ሥርዓትና ሌሎችንም ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ከቀረቡ በኋላ የመርሀ ግብሩ መሪ በመጨረሻ እንዲህ ነው ያለው፡- “now let us see the real Christianity” ማለትም “አሁን እውነተኛውን የክርስትና ሃይማኖት እንመልከት” በሚል መሸጋገሪያ የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የበዓል አከባበርስነ-ሥርዓት ማስተላለፍ ጀመረ። ካህናት አባቶች ወረብ ሲያቀርቡ፣የቅዳሴውን ሥርዓት፣ መዝሙሩ ሲዘመር፤ ጧፉ እየበራ ወንጌሉ ሲነበብ፣ እጣኑ እየጤሰ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲቀርብ..ሁሉንምበየተራ ማቅረብ ጀመረ።እናም እነርሱ ማለት #ምዕራባውያን ስለ ዕምነት ጉዳይ እውነት የሆነውን ነገር ፍለጋ ፊታቸውን ወደ እኛ ባዞሩበትወቅት እኛ ደግሞ እውነተኛውንማንነታችንን ባንጥልና የአጉልባህል ተገዢዎችባንሆን ብሎም በአምልኮጣኦታቸውተሳታፊዎች ባንሆን መልካም ነው። መልካም ነው ብቻም ሳይሆን መንፈሳዊና ሞራላዊ ግዴታዎችም አሉብን። በእርግጥ እኛ የዚህ ዘመንትውልዶችየግሎባላይዜሽን ጎርፍ ጠራርጎየወሰደን ስለሆንንና ‹‹በጣም ስልጡኖችና ዘመናውያንም›› ስለሆንን ይህ ምንማለት እንደሆነ ላይገባን ይችላል፤ እንዲገባንም አንፈልግም፡፡ የሴቶቻችን እርቃንመሄድ፣ አካሎቻቸውን መነቀስና መበሳት፣ የወንዶች አለባበስና ፀጉር አቆራረጥ…እነዚህና ሌሎቹምነገሮች በዘመናዊነት ሰበብ የመጡብን የዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውጤቶች ናቸው፡፡ በግል አዳኝ ‹‹ኢየሱሴ›› ስም ብዙኃኑን ሕዝባችንን ፈጣሪውን አስክደው አምላክ የለሽ አደረጉትና ለግሎባላይዜሽናቸው የተመቸ ዝርው ትውልድፈጠሩ፡፡ አሁንማ ጭራሽ ለይቶላቸው ‹‹church of Satan›› በማለት ‹የሰይጣን ቤተክርስቲያን› ከፍተው አባሎቻቸው በሆኑ ‹‹ታዋቂ የሂፖፕ››አቀንቃኞቻቸው አማካኝነት የአባላቶቻቸውንቁጥር ለመጨመር እኛም ሀገር ብቅ ብለውልናል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት እንደግለሰብ ነፃነት አድርጋችሁ ካልተቀበላችሁ እርዳታ አንሰጣችሁምም ተባልን፡፡ እሺ እነዚህና ሌሎቹም አስከፊኃጢአቶቻቸውን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪእንድንቀበል ቢያስገድዱንም ቢያንስ እኛ በራሳችንጊዜ ለምን የራሳችንንባሕል ድምጥማጡን በማጥፋት የእነርሱን ባሕል እንከተላለን?የዘመናዊነት መገለጫው የራስንባሕልና እምነት በሌሎች መተካት ሆነ እንዴ? ድሮ ቅኝ ቅዛት ተገዝተንቢሆን ኖሮ ምንድን ነበር የምናጣው? ቀላል ነው መልሱ፡- የራስ ማንነት፣እምነት፣ባሕል፣ታሪክ..አይኖረንም ነበር፡፡ አሁን ታዲያ በዘመናዊው ቅኝአገዛዝ ሥርዓት ምክንያት እነዚህን ነገሮች አላጣናቸውም ይሆን? ማሳሰቢያ?‼️ ✅ እንዲያው በመድኃኔዓለም! እባካችሁ ከፊት ለፊታችን በታላቅ ጉጉትና ተስፋ የምንጠብቀውን ከድቅድቅ ጨለማ ወጥተን ብርሃን ያገኘንበትን የአማኑኤልንየልደት በዓል የገናንዛፍ በመጠቀም ከነጮቹ ባዕድና ጣኦት አምልኮ ጋር አንቀላቅለው፡፡ልደቱን ቅድስትቤተክርስቲያን እንደሚገባው አድርጋ ታከብረዋለችና እኛምልጆቿ እንደሚገባው መጠን ልደቱን እናክብር፡፡ የገና ዛፍ የባዕድአምልኮ መገለጫ ነው።ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ምንድን ነበር ያለው! ‹‹ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ...።2ኛ ቆሮ 6፡14-16፡፡ “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ” 2ኛቆሮ 13፡5፡፡ ምንጭ፡- አናቆጸ ሲኦል በብርሃኑ ጐበና፤ ሐመር 5ኛ ዓመ https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop 🟢ሠናይ🟡ሶቤ🔴
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

🇪🇹🇪🇹#የገና__ዛፍ🎄🌲 \\\\\\////////// ///////\\\\\\\\ የገና ዛፍ የነጮች የባዕድ አምልኮ መገለጫ መሆኑን ያውቃሉ?? የገና ዛፍ ታሪክና አመጣጡ የገናን ዛፍ የት መጣውን /ምንጩን/ ስናጤነው ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ይነግሩናል። የአምድ ክፍላይንም እነሆ አላችሁ በዞራስተርን የሁለት አማልክት ዕምነት የሚያምኑት ምዕራባውያን አዲሱን ዓመታቸውን /2023/ ተቀብለዋል። ☢በዞራስተርን የሁለት አማልክት ዕምነት መሠረት ክፉውና ደጉ የተባሉ ሁለት አማልክቶች አሉ። እንደ ዕምነቱ አስተሳሰብ ከሆነ እዚህ ምድር ላይ የሆነው እየሆነው ያለውና የሚሆነውም ማንኛውም ነገር በሙሉ የሚከናወነው በእነዚህ በሁለቱ አማልክቶች ፉክክር ነው። ክፉው አምላክ ከሰለጠነ /የበላይ ከሆነ/በምድር ላይ ክፉ የሆኑ ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። በተቃራኒው ደግሞ ደጉ አምላክ ከሰለጠነ በጎ ነገሮች ይከሰታሉ ማለት ነው።ምዕራባውያኑ ታዲያ ደጉን አምላካቸውን ማለትም ጣዖታቸውን ሳተርን ብለው ይጠሩታል። በምዕራቡ ዓለም የክረምቱ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ይረግፋሉ። ልምላሜ አይታይባቸውም። #ፅድ 🎄 ግን በተፈጥሮው ይህን አስቸጋሪ ወቅት ተቋቁሞ የማለፍ ኃይል አለው። በመሆኑም ፅድ ክፉውን ዘመን /ክረምቱን/ ተቋቁሞ መልካሙ ዘመናቸው እስኪመጣላቸው ድረስ በልምላሜ ይቆይላቸዋል። ይህም #ሳተርን /ደጉ አምላካቸው/ ከክፉው አምላክ ለመሸሸግ በፅድ ውስጥ ተደብቆ ይኖራል ብለው ያመናሉ ምዕራባውያኑ። እናም ብራ ሲሆን /በእኛ መስከረም ጠባ እንደምንለው ነው/ የደጉን አምላክ ‹‹የእንኳን ደህና መጣህ›› በዓልን በድምቀት ያከብራሉ። ምስጋና ለፅዱ ይሁንና #ደጉ አምላካቸውን ደብቆ ስላቆየላቸው ባለውለታ ስለሆነ የደጉን አምላክ የእንኳን ደህና መጣህ በዓል ሲያከብሩ ታዲያ ፅድን ለበዓላቸው ማድመቂያነት ይጠቀሙበት ነበር። ይኸው ትውፊታቸው ዛሬም ድረስ አለ። በአጭሩ ከጥንት ጀምሮ እነርሱ ይኽን በዓል የሚያከብሩት ሳተርን ለተባለው #ጣዖት /ደጉ አምላክ/ ያደርጉት የነበረው ሥርዓት ነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን በአዋጅ ካስፋፋበት ጊዜ ጀምሮ በውጭው ዓለም ጥንት የነበሩ ብዙ ጣዖታዊ በዓላት ክርስቲያናዊ በዓል ሆነው አሁንም ድረስ በብዙ ሀገራት እየተከበሩ ይገኛሉ። /ነገር ግን ልደትንና ትንሣኤን ጨምሮ ሌሎችም በዓላት ቢሆኑ ሥርዓታቸውን በጠበቁ መልኩ የሚከበርባቸው አንዳንድ ሀገራት እንዳሉ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ለማስገንዘብ ይወዳል።/ በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ይኸው እስከዛሬ እኛም ይኽንኑ የባዕድና የጣኦት አምልኮ በዓላቸውን በእነሱው ልማድ መሠረት የፅድ የገናዛፍ እየሠራን ስናከብርላቸው ኖረናል። አባቶቻችን ሲናገሩ ‹‹እግዚአብሔር ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰው ሆኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበቡ እጅግ ረቂቅና ጥልቅ ነው›› ይላሉ። እንዴት ደስ የሚል አገላለፅ ነው!ታዲያ ምን ዋጋ አለው? አለመታደል ሆኖ ይሁን አሊያም አለማወቃችን ለስም አጠራሩክብር ምስጋን ይግባውና እጅግ ድንቅ የሆነውን የጌታችንን የአምላካችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ከእንደዚህ ዓይነቱ ምዕራባዊ የጣዖት በዓል ጋር ቀላቅለን እናከብራለን። 👉ይህ እጅግ አሳዘኝ ነገር ነው በእውነት! በአንድ ወቅት በምዕራባውያን የገና በዓል ሰሞን በ‹‹BBC channel 4›› ላይ የበዓል መርሀ ግብር /program/ ቀርቦ ነበር። በመርሀ ግብሩ ላይ.. ...ከቀረቡ በኋላ የመርሀ ግብሩ መሪ በመጨረሻ እንዲህ ነበር ያለው...፡- ይቆየን! ይቀጥላል... የጽሑፉ ምንጮች፡- አናቆጸ ሲኦል በብርሃኑ ጐበና፤ ሐመር 5ኛ ዓመ https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop 🟢ሠናይ🟡ሶቤ🔴
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

..የቀጠለ... ከሁለት ቀናት በኋላም ማለት መስከረም 29 ኤልሳቤጥ ፀነሰች። ለአምስት ወራትም ራሷን ሸሸገች። እንዲሁም በስድስተኛው ወር መልካም ዜናን የሚናገር መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ናዝሬት ከምትባል ከገሊላ አገር ወደ ማርያም ተላከ።(ሉቃ. 1፥23-25) በወንጌል በ6ተ ኛው ወር ገብርኤል ድንግል ማርያምን አበሠራት ሲባል ዮሐንስ መስከረም 29 ተፀነሰ። ከዚህ በኋላም ለ5 ወር ኤልሳቤጥ ራሷን ሸሸገች።(ሉቃ. 1፥24-25) እስከ የካቲት ማለት ነው። በ6ተኛው ወር አበሠራት ያለው መጋቢት 29 መልአኩ ቅድስት ድንግል ማርያምን አበሠራት። ድንግልም ፀነሰች።(ሉቃ. 1፥26) እዚህጋ ልብ: በማለት የቀድሞ የሒሳብ ስሌታችንን በመከሰ:ት እናስላ፤ የአሁኑን የፈረንጆቹን ካሪኩለምን በአይናችን ገርመም አድርገን በማየት፤ በቀድሞው እናስላ..... ከመጋቢት 29 እስከ ታኅሣሥ 29 ድረስ ዘጠኝ ወር ሲሆን የ13ተኛ ወራችንን የጳግሜን 5 ቀናት ሲጨመር ዘጠ ኝ ወር ከአምስት ቀን ሲሆናት እናታችን፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በከብቶች በረት ተወለደ። ሊቃውንቱም "በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ እፎ ተሴሰየ ሀሊበ ከመ ሕፃናት፤ ተወልደ በአምሳሊከ ከመ ይለድከ በአምሳሊሁ' በአምሳሉ ይወልድህ ዘንድ አንተን መስሎ ተወለድ" "ሰው አምላክ ይሆን ዘንድ አምላክ ሰው ሆነ" አከተመ። ... "ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር" ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ። አሜን!!! 💚💚💚🇪🇹💛💛💛🇪🇹❤️❤️❤️ https://t.me/QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

.የቀጠለ... በታላቁ መጽሐፍ በትንቢተ ኢሳይያስ በምዕራፍ ፶፫(53)፥፰(8)ላይ "ከትውልዱ ማን አስተዋለ" ይላል፤ እውነት እኮ ነው የሀገሬ ልጆች ማስተዋል ተስኖናል ደግሞም እንዴት ነው ብለን የመጠየቅ ባህላችን ደክሟል። ለምን አንጠይቅም??? ለምን በታኅሣሥ 29(28) የጌታ ልደት ነው ብለው አባቶች ነገሩን ብለን ለምን አንጠይቅም፤ ነጮቹን ትተንiii ለማንኛውም እንዲ አድርገው አበው የቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶቻችን አመሳጥረው አትተውልናል..... የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት ቀን ለማወቅ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የተፀነሰበትን ዕለት መነሻ በማድረግ ነው። በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1፥6-14 ላይ ያለውን ቃል በደንብ ማየትን ያሻል። ታሪኩ ግልጽ እንዲሆን አንብቡት ወንጌሉን። .....ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተመቅደስ ገብቶ መልአኩ ያበሠረበት ቀን በዕብራውያን ዘንድ "በዓለ ስርየት" ተብሎ በሚከበርበት ዕለት ነው። በዓለ ስርየትም በዕብራውያን አቆጣጠር በሰባተኛ(7ኛ) ወር(በታስሪን) በዐሥረኛው ቀን ነው።(ዘሌዋ. 16፥29-34፣ ዘኁል. 29፥7-11) በዚህ ዕለት ካህኑ ዘካርያስ የክህነት ሥራውን እየሠራ መልአኩ አበሠረው። ወንጌሉም እንደሚነግረን "በቤተመቅደስ አንድ ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፤ እሱም ይጠቅሳቸው ነበር፣ ድዳም ሆነ" የአገልግሎት ጊዜውን ሲጨርስ ወደ ቤቱ ሄደ። ...ይቀጥላል..... "ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር" ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ። አሜን!!! ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን j o i n ... 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

🇪🇹🇪🇹 እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ልደት አደረሳችሁ 🇪🇹 ፩. የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መቼ ነው?? ፪. እንዴት ከቀኝ ገዢዎች ነን ባዮች ጋር በቀን አቆጣጠር ተለያየን?? ፫. የክሪስማስ ትሪ(ፅድ) ለእኛ ምናችን ነው?? ከመቼ ጀምሮስ ማስጌጥን ጀመርን?? ለምን??? ፬. የገና አባትስ ማነው??? እነኚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እናም ሌሎች የሀገራችንን ታሪኮችን ለማወቅ፣ ለመገንዘብ ሊንካችንን j o i n እና share 👇👇👇👇👇 @QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ። ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን!!! 👉👉 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በአባቶቻችን የዘመን ቆጠራ ስሌት መሠረት በታህሳስ ፳፱(29) ሲሆን የወሩን ስያሜ እራሱ ሲተነትኑት ቀደምት አባቶቻችን "ታህሳስ" ማለት በግእዝ "አሠሠ፣ፈለገ ማለት ነው ይላሉ። ነጮቹ ግን ጌታ ተወለደ ብለው የሚያስቡት(የሚያከብሩት) በታህሳስ (25)፳፭ ነው። ለምን ግን በታህሳስ 25 ማክበር ፈለጉ ብለን ቆም ብለን ማሰብ አለብን ከታሪክ አንፃር ስናየው በታህሳስ 25 የተወለደው በግብፅ ሀገር "ራ" ተብሎ የሚታወቀው የፀሐይ አምላክ ነው። ራ የሚባለውን አምላካቸውን የሚያከብሩት አካሉን በዘንባባ ዛፎች መካከል አድርገውት ከታች ሰውነቱን የሰው ቅርጽ ሰጥተውት ከላይ እንደ አሞራ አድርገው ጭንቅላቱ ላይ ደግሞ የፀሐይን ቅርጽ አድርገውለት በዘንዶ የተከበበ ቅርጽ በመስጠት የሚያከብሩት ጣኦት የተወለደበት ነው። ሌላም ሚትራስ የሚባለው በመካከለኛው ምስራቅ በብዛት የሚታወቅ ጣኦትም የተወለደበት ቀን ነው። በተጨማሪም የጥንት የሮማ አምላክ ሳተርኑሊያ የተወለደበት ሲሆን ይህም በ4ተኛው ክፍለ ዘመን የክርስቶስ አማኞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ ፈፅሟል። ታድያ በዚህ ቀን የጌታን ልደት እናስብ ብሎ መነሳት ትክክል ነው?? መልሱን ለልባችው ተውኩት።... ይቀጥላል... "ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር" ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ። አሜን!!! J o i n ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን ... 👇👇👇🇪🇹🇪🇹🇪🇹👇👇👇👇 @QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop https://t.me/QedmitmidreEthiyop
Mostrar todo...
ቀደምት ምድር/ Land of origin Ethiopia

*የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ...*ነውና ነገሩ.... ከቀደምት የሀገራችን እስከ አሁን ያሉ አስተማሪ፣ አሳዋቂ እና አዝናኝ ታሪኮችን፣ ክስተቶችን በቀላሉ ለማወቅ የሀገሬ ልጆች በዚህ @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop ይከተሉን። *የሚጠይቅ ለ፭ ደቂቃ ብቻ ቂል ሲሆን የማይጠይቅ ግን ለዘላለም ቂል ሆኖ ይቀራል*ና ለአስተያየትዎ ይኼው @Banbe

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በእግር ኳሱ ዓለም ትልቅ ስም ያለው ብራዚላዊው ታሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቹ ባጋጠመው ህመም ሆስፒታል ገብቶ ህክምና ሲከታተል የቆየ ቢሆንም ህይወቱን ማዳን አልተቻለም። ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር ሶስት / 3 የዓለም ዋንጫዎችን ማሸናፍ የቻለው ፔሌ በሰማንያ ሁለት ዓመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው። More @tikvahethsport     @tikvahethiopia
Mostrar todo...
ከእለታት በአንድ ቀን አንድ #ዝሆንና አንድ #ዉሻ በተመሳሳይ ቀን #አረገዙ! \\\\\\//////// \\\\\\\\///////// ከሶስት ወር በኋላ ዉሻዋ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላም በድጋሜ አረገዘች እናም በዘጠነኛዉ ወር ሌሎች ብዙ ቡችሎችን ወለደች ፡፡ ዉሻዋ እንዲህ እንዲህ እያለች ብዙ ቡችሎችን ወለደች፡፡ በ18ኛዉ ወር ግን ግራ የገባት ዉሻ ወደቀድሞ ዝሆን ጓደኛዋ ሂዳ እንዲህ ስትል ጠየቀቻት "እርግጠኛ ነሽ ግን ማርገዝሽን? " ካስታወሽ የ ዛሬ 18 ወር እኩል ነበር ያረገዝነዉ። ይሁን እንጂ ባለፋት ወራት እኔ ብዙ ቡችሎችን ወልጄ አሁን ትላልቅ ሆነዋል፡፡ አንቺ ግን እስካሁን ምንም አልወለድሽም። የምር ግን እርጉዝ ነሽ? ምን እየሆነ ነዉ?” ስትል ጠየቀቻት፡፡ ይህን የሰማችዉ ብልህ ዝሆን በእርጋታ እንዲህ ስትል መለሰች። “ዉድ ጓደኛዬ፥ እንድታዉቂዉ የምፈልገዉ አንድ ነገር አለ፡፡ ያረገዝኩት እኮ ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ በሁለት አመት አንድ ዝሆን ብቻ ነዉ እኔ ልወልድ የምችለዉ፡፡ ነገር ግን ልጄን በወለድኩ ጊዜና ልጄ መሬት ሲረግጥ መሬት ራሱ ትናወጣለች ፡፡ ልጄ መንገድ ሲያቋርጥ የሰዉ ልጆች ሁሉ ቆመዉ በአድናቆት ይመለከቱታል፡፡ እኔ ያዘልኩት ፅንስ ትኩረትን የሚስብ ነዉ፡፡ የያዝኩት ትንሽ ነገር ሳይሆን ሀያል የሆነ ዝሆን ነዉ። “ ብላ መለሰች፡፡ ከዚህ ምን እንማር ይሆን?👇 👉ሌሎች የራሳቸዉን ግብ በፍጥነት ሲመቱ የኔ አይሳካም ብለን ተስፋ አንቁረጥ፣ በሌሎችም አንቅና ምክንያቱም:- 1. የኛ ስኬት የሚወሰነዉ በራሳችን ትጋት (ፅንስ) እንጂ በሌሎች ላይ ስላልሆነ፤ 2. ጥሩ ነገር ሁሌ ጊዜ ይወስዳል (ትልቅ ነገር ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለማሰብም ጊዜ ይወስዳል። ዉጤቱ ግን ታላቅ ነዉ!) 🟢ሠናይ🟡ሶቤ🔴 "ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር" ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ። አሜን። @QedmitmidreEthiyop @QedmitmidreEthiyop
Mostrar todo...
ከእለታት በአንድ ቀን አንድ #ዝሆንና አንድ #ዉሻ በተመሳሳይ ቀን #አረገዙ፡፡ \\\\\\//////// \\\\\\\\///////// ከሶስት ወር በኋላ ዉሻዋ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላም በድጋሜ አረገዘች እናም በዘጠነኛዉ ወር ሌሎች ብዙ ቡችሎችን ወለደች ፡፡ ዉሻዋ እንዲህ እንዲህ እያለች ብዙ ቡችሎችን ወለደች፡፡ በ18ኛዉ ወር ግን ግራ የገባት ዉሻ ወደቀድሞ ዝሆን ጓደኛዋ ሂዳ እንዲህ ስትል ጠየቀቻት "እርግጠኛ ነሽ ግን ማርገዝሽን? " ካስታወሽ የ ዛሬ 18 ወር እኩል ነበር ያረገዝነዉ። ይሁን እንጂ ባለፋት ወራት እኔ ብዙ ቡችሎችን ወልጄ አሁን ትላልቅ ሆነዋል፡፡ አንቺ ግን እስካሁን ምንም አልወለድሽም። የምር ግን እርጉዝ ነሽ? ምን እየሆነ ነዉ?” ስትል ጠየቀቻት፡፡ ይህን የሰማችዉ ብልህ ዝሆን በእርጋታ እንዲህ ስትል መለሰች። “ዉድ ጓደኛዬ፥ እንድታዉቂዉ የምፈልገዉ አንድ ነገር አለ፡፡ ያረገዝኩት እኮ ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ በሁለት አመት አንድ ዝሆን ብቻ ነዉ እኔ ልወልድ የምችለዉ፡፡ ነገር ግን ልጄን በወለድኩ ጊዜና ልጄ መሬት ሲረግጥ መሬት ራሱ ትናወጣለች ፡፡ ልጄ መንገድ ሲያቋርጥ የሰዉ ልጆች ሁሉ ቆመዉ በአድናቆት ይመለከቱታል፡፡ እኔ ያዘልኩት ፅንስ ትኩረትን የሚስብ ነዉ፡፡ የያዝኩት ትንሽ ነገር ሳይሆን ሀያል የሆነ ዝሆን ነዉ። “ ብላ መለሰች፡፡ ከዚህ ምን እንማር ይሆን?👇 👉ሌሎች የራሳቸዉን ግብ በፍጥነት ሲመቱ የኔ አይሳካም ብለን ተስፋ አንቁረጥ፣ በሌሎችም አንቅና ምክንያቱም:- 1. የኛ ስኬት የሚወሰነዉ በራሳችን ትጋት (ፅንስ) እንጂ በሌሎች ላይ ስላልሆነ፤ 2. ጥሩ ነገር ሁሌ ጊዜ ይወስዳል (ትልቅ ነገር ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለማሰብም ጊዜ ይወስዳል። ዉጤቱ ግን ታላቅ ነዉ!)
Mostrar todo...