cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ETV ዜና 🎤

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
556
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"ወንድሜ ሲሪል ራማፎሳ በቶሎ እንድታገግም ምኞቴ ነው"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ************************ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮቪድ-19 የተያዙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ። ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኮቪድ-19 ተይዘው ክትትል ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንኑ አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ "ወንድሜ ሲሪል ራማፎሳ በቶሎ እንድታገግም ምኞቴ ነው" ብለዋል።
Mostrar todo...
ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደማይችል የተረዳው አሸባሪው ህወሓት በምትኩ ትውልድ የሚገነባባቸውን ተቋማት አውድሟል ********************* አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደማይችል ሲገባው ትውልድ የሚገነባባቸውን ተቋማት ማውደሙን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ ገለጹ። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሶስቱም ካምፓሶች በአሸባሪው ህወሓት ሙሉ ለሙሉ ዘረፋና ውድመት ተፈፅሞባቸዋልም ብለዋል። አሸባሪው ህወሓት "ኢትዮጵያን ማፍረስ"ን ግቡ አድርጎ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች የህዝብና የግለሰቦች ሃብትን እንዲሁም የመንግስት ተቋማትን በመዝረፍ የቀረውን አውድሟል። የሽብር ቡድኑ በገባባቸው አካባቢዎች ሴቶችን ደፍሯል፣ የእምነት ተቋማትን የውጊያ ምሽግ በማድረግ አርክሷል፤ በማቃጠልም ውድመት አስከትሏል። በወሎ ወረራ ፈፅሞባቸው በነበሩ አካባቢዎችም ተመሳሳይ እኩይ ተግባር የፈፀመ ሲሆን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሶስቱንም ካምፓሶች ዘርፏል፤ አውድሟል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ እንደገለጹት አሸባሪው ህወሓት የዩኒቨርስቲውን ደሴ፣ ኮምቦልቻና ጢጣ ካምፓሶችን ሙሉ ለሙሉ ዘርፏል፤ የቀረውንም አውድሟል። በመሆኑም የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የሚያስተናግደው ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ሃይል እንዳልነበር ሆኗል ብለዋል። የዩኒቨርሲቲው ህንፃዎች፣ ዘመናዊ ቤተ ሙከራዎች፣ ቤተ መጻህፍት፣ የኢንተርኔት ሰርቨር እና ሌሎችም ንብረቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። በዚህም የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአሸባሪው ሃይል ዋነኛ የጥፋት ኢላማ መሆኑን ዶክተር መንገሻ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Mostrar todo...
ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ **************** ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል። ከደብረብርሃን ኮምቦልቻ ድረስ ያሉት ከተሞች በ132 እና በ230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ኃይል ያገኙ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይሁንና የኃይል ተጠቃሚው ህብረተሰብ በፍጥነት ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ለጊዜው በማቆየትና ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመሩን በአስቸኳይ በመጠገን ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል አግኝተዋል። የጥገና ሥራው ወደ ደሴ ከተማ ቀጥሎ እስከ ሀርቡ ባለው አካባቢ መስመሮችን የመጠገን ሥራም እየተካሄደ ነው። አሁን አስቸኳይ ጥገና እየተደረገለት ያለው 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የከሚሴ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ እንዲሁም ዓለም ከተማና በምዕራብ አፋር የሚገኙ ከተሞችን ኃይል እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። በተያያዘ ዜና በሚሌ ባቲ ያለው መስመር ላይ ሁለት ኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች በከባድ መሳሪያ በመመታቸውና ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ምሶሶዎቹን እንደገና የመትከል ስራ ተጀምሯል።
Mostrar todo...
ጆ ባይደን ለጉብኝት በሄዱበት ካንሳስ ከተማ ከኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጠማቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጉብኝት በሄዱበት ካንሳስ ከተማ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን ሚዙሪ ግዛት በምትገኘው ካንሳስ ከተማ ረቡዕ ከሰዓት የሥራ ጉብኝት ያካሄዱ ሲሆን፤ በጉብኝቱ ወቅት በከተማዋ የሚገኙ የኢትዮጵያውን ማህበረሰብ አባላትና የትራምፕ ደጋፊዎች ተቃውማቸውን አሰምተዋል። ተቃዋሚዎቹ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር በሚያካሂደው እንቅስቃሴ ቁጣቸውን እንዳሰሙ የዘገበው ኬ ኤም ቢ ሲ “በኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደውን የውክልና ጦርነት እና ጣልቃ ገብነት እኛ በቃ፣ በቃ እንላለን” ማለታቸውን አስነብቧል። ተቃዋሚዎች “የጆ ባይድን አስተዳደር በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን የህወሃት ቡድን የመደገፍ እንቅስቃሴውን ሊያቆም ይገባል፣ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ለማጥፋት የሚያካሄደው ጣልቃ ገብነትም ሊቆብ ይገባል” ብለዋል። በተቃውሞው ተሳታፊ ከነበሩት መካከል ሄኖክ ተከስተ እና ፀደንያ ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት ፤እኛ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ገለልተኛና ነጻ መንግስት አለን ጣልቃ ገብነቱ እንዲቆም እናሳስባለን” ብለዋል። በተቃውሞው የተሳተፉት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችም አሜሪካ ከአፍጋኒስታን እንድትወጣ በተላለፈው ውሳኔና የባይደን አስተዳደር የኮቪድ-19 ቀውስን ለመቋቋም በሚሰጠው ምላሽ ላይ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
Mostrar todo...
የናይጄሪያው ''ቤንቶ'' በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት መጨረሻ በኢትዮጵያ ሥራውን ለመጀመር እያማተረ ነው። የናይጄሪያው የክፍያ መቆጣጠሪያ እና የሰው ኃይል አስተዳደር ቴክኖሎጂ አቅራቢ የሆነው ''ቤንቶ'' በቀጣዩ ዓመት በአፍሪካ በኬንያ፣ ሩዋንዳና ጋና በሌሎች ስድስት ሀገራት ውስጥ ሥራውን ለማሥፋፋት ማቀዱን ገልጿል። ''ቤንቶ'' በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት መጨረሻ ሥራዬን እጀምርባቸዋለው ብሎ ዐይኑን ካሳረፈባቸው ሀገራት መካከል #ኢትዮጵያ የምትገኝ ሲሆን ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያና፣ አንጎላም በዝርዝሩ ተካተውበታል ተብሏል። በ2019 የተመሰረተው ''ቤንቶ'' በአፍሪካ የዘርፉን ገቢያ በመምታት ላይ ይገኛል የተባለ ሲሆን ሥርዓቱ በተለምዶ ደሞዝ ለመክፈል አድካሚ የሆኑ ሂደቶችን የሚያቀል እንዲሁም የሰው ኃብት አስተዳደርን ለመምራት የሚያግዝነው። (TechCrunch)
Mostrar todo...
አሸባሪው ህወሓት በተለያዩ አካባቢዎች የዘር ጭፍጨፋ ፈፅሟል፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት **************** አሸባሪው ህወሓት በአፋር እና በአማራ ክልል ተቆጣጥሮቸው በቆየባቸው በተለያዩ አካባቢዎች የዘር ጭፍጨፋ መፈፀሙን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። አሸባሪው ህወሓት የደረሰበትን መራር ሽንፈት በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳው ሊሸፍነው እንዳልቻለ እና ሊሸፈንም እንደማይችል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል። ዶክተር ለገሰ ቱሉ በመግለጫቸው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ያሸነፉበት እንቅስቃሴ ተደርጓል ነው ያሉት። በዘመቻው ኢትዮጵያውያን በአንድ የቆሙበት እና የላቀ የአመራር ጥበብና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ታይቶ ጠላት ብትንትኑ የወጣበትም ነው ያሉት። የአፋር ክልል፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ሰሜን ሸዋና ሌሎች አካባቢዎች በዘመቻው ሙሉ በሙሉ ነፃ መውጣታቸው፣ በደቡብ ወሎ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎች፥ በሰሜን ወሎም ላሊበላን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎች ነፃ መውጣታቸውን ገልጸው ሌሎች አካባቢዎችም በቅርቡ ነፃ ይወጣሉ ብለዋል
Mostrar todo...
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከ3 የአፍሪካ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከሴኔጋል፣ ከደቡብ አፍሪካና ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንቶችጋር ተወያዩ።"ከሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ጋር ስለነበረን ገንቢ የስልክ ውይይት አመሰግናለው። የሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንሰራለን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡
Mostrar todo...
የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ከስራ አባረሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በሀገሪቱ ያላው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ነው። በቡርኪና ፋሶ ህግ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ ከለቀቁ የሀገሪቱ መንግስት እንደሚበተን ይደነግጋል። https://t.me/EtvNewsRoom
Mostrar todo...
#ኮምቦልቻ_ደሴ በትላንትናው ዕለት የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በትላንትናው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የነበሩት መጋዘኖቹ በህወሓት ኃይሎች በመዘረፋቸው የምግብ እርዳታ ማቋረጡን አስታውቋል። https://t.me/EtvNewsRoom ቃል አቀባዩ ፥ የእርዳታ ምግብ ተከማችተውባቸው የነበሩት መጋዘኖቹ በህወሓት ኃይል በተዘረፉበት ወቅት በስፍራው በነበሩ ሠራተኞቹ መሳሪያ ተደግኖባቸው እንደነበረ አመልክተዋል። በመጋዘኖቹ ላይ በህወሓት በተፈጸመው ዝርፊያ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት የሚቀርቡ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የምግብ አቅርቦት ክምችት ከሁለቱ ከተሞች ተወስደውበታል። በስፍራዎቹ የነበሩ ሠራተኞቹም በጦር መሳሪያ ጭምር ጫናና ማስፈራሪያ ስለተደረሰባቸው ይህንን ዝርፊያ ለመከላከል ሳይችሉ መቅረታቸው ተገልጿል። ይህ ዝርፊያ በአሁኑ ወቅት ከ9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በምግብ እርዳታ ላይ ጥገኛ በሆነበት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግርና የተመጣጠነ ምግብ እጦትን የበለጠ እንደሚያባብሰው ድርጅቱ ተናግሯል። በሌላ በኩል በአማራ ክልል ለሰብአዊ አገልግሎት የሚውሉ ሶስት የWFP መኪኖች በዚህ ሳምንት በወታደሮች ታዝዘው ለራሳቸው ዓላማ መዋላቸውን ዱጃሪች ተናግረው ድርጊቱን አውግዘዋል ሁሉም አካላት የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎችን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁ ጠይቀዋል። ለአንድ ወር ያህል በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር የቆዩት የደሴና የኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተመራው የኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች በዚህ ሳምንት ነፃ መውጣታቸው ይታወቃል። https://t.me/EtvNewsRoom
Mostrar todo...
ሩሲያ በዩክሬን ድንበር የምታደርገው እንቅስቃሴ ያሳሰባቸው ባይደን ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ተወያዩ መሪዎቹ፤ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያለውን ውጥረት እንድታረግብም ጠይቀዋል። ከሩሲያ በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም። https://t.me/EtvNewsRoom
Mostrar todo...