cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ገድለ ቅዱሳን ዘእለታት

ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
536
Suscriptores
+124 horas
Sin datos7 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

††† ✝እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃን ወከዋክብተ ገዳም አቡነ ኪሮስ: አባ ብሶይ እና አባ ሚሳኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።✝ ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ✝አቡነ ኪሮስ ጻድቅ✝ ††† ††† የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል:: #አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር #ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው (ታላቁ #ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ ( #ገዳመ_አስቄጥስ) መጡ:: እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ #ቅዱስ_ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል:: ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል:: አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ:: ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር:: ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ:: #ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም:: †††✝ የበርሃው ኮከብ አባ ብሶይ✝ ††† ††† ታላቁ አባ ብሶይ (ቢሾይ):- =>በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ =>በመላእክት መሪነት የመነኑ =>የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ባልንጀራ =>የአባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር የነበሩ =>በአጭር ጊዜ የብዙዎች አባት የሆኑ ሰው ናቸው:: ††† እንቅልፍን የማያውቁ =>በ40 ቀን ብቻ እህል የሚቀምሱ =>የጌታችንን እግር በየቀኑ እያጠቡ የሚመገቡ =>ፈጣሪያቸውን በጀርባቸው ያዘሉ (ነዳይ መስሎ አግኝተውት) =>በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተጉ =>በርካታ ጻድቃንን የወለዱ ታላቅ የፍቅር ሰው ናቸው:: በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሰርተው: ቤተ_ክርሰቲያንን በንጽሕናቸው አስደስተው: ሐምሌ 8 ቀን ዐርፈዋል:: ግብፅ ውስጥ የሚገኘው ገዳማቸው ዛሬም ቤተ አበው: ተአምራት የማይለዩትና ተወዳጅ ነው:: ቦታው #መካነ_ሱባዔ_ወመንክራት ነውና:: ††† ✝አባ ሚሳኤል ነዳይ✝ ††† ††† መቼም ያ ዘመን (4ኛውና 5ኛው ክ/ዘመን) እጅግ የተባረከ ነው:: ቅዱሳኑ በብዛት የባለጸጐችና የነገሥታት ልጆች ናቸው:: አባ ሚሳኤልም የኬልቄዶን ንጉሥ ልጅ ሳሉ መንነው በበርሃ ለ65 ዓመታት ተጋድለዋል:: በመጨረሻ ግን በደዌ ምክንያት ወደቁ:: ለ5 ዓመታት መነኮሳቱ ሲጠይቁዋቸው ቆይተው ሰለቹ:: ከዛም ለ15 ዓመታት ላበታቸው በግንባራቸው እየተቀዳ: ያለ ምንም ምግብ እያቃሰቱ በበዓታቸው ወድቀው ኑረዋል:: ቸሩ አምላክ ግን 4ቱን ሊቃነ መላእክት ( #ሚካኤል: #ገብርኤል: #ሩፋኤልና #ሳቁኤልን) አዞላቸው ሲጠብቁዋቸው ኑረዋል:: በዚህች ቀንም #አቡነ_ኪሮስ መጥተው አጽናንተው: ጌታችንንም ጠርተው እንዲያርፉ አድርገዋል:: መላእክት እያጠኑና እየዘመሩ ጻድቁ ቀብረዋቸዋል:: በመቃብራቸውም ላይ ፈውስ የሆነ ጸበል ፈልቁዋል:: ††† እግዚአብሔር የእኛን ያይደለ የጻድቃኑን ቅድስና አስቦ ይራራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ሐምሌ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አቡነ ኪሮስ ጻድቅ (አረጋዊና ገዳማዊ) 2.አባ ብሶይ ጻድቅ (ኮከበ ገዳም) 3.አባ ሚሳኤል ነዳይ (ጻድቅ) 4.አባ ቢማ ሰማዕት 5.አባ በላኒ ሰማዕት 6.ቅዱሳን አቤሮንና አቶም (ሰማዕታት) ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 4.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ††† "በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው:: የኃጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሠቢያ ለበረከት ነው::" ††† (ምሳ. 10:7) †††"እግዚአብሔርፍርድንይወድዳልና::ቅዱሳኑም አይጥላቸውምና::ለዘለዓለምምይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††(መዝ. 36:28-31) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል። https://telegram.me/gedlekdusan
Mostrar todo...
ገድለ ቅዱሳን ዘእለታት

ከኢ/ኦ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተገኙ የእለቱ የቅዱሳን(የጻድቃን) አባቶቻችን እና የቅዱሳን(የጻድቃን) እናቶቻችን ጽድቅ እና ገድላት ይነገርበታል። በመሀልም ጠቃሚና አስተማሪ ነው የምንላቸውን ታሪኮች ወደእናንተ የምናቀርብ ይሆናል።

https://telegram.me/gedlekdusan

እጅግ ምርጡ ጸሎት ''ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ''ማለት ነው።ባህታዊ ቴዎፋን
Mostrar todo...
#ናታኔም ናታኒም ነኝ አገልግሎቴ አይከፋኝም ታናሽነቴ እጠርጋለሁ ደጅህን ጌታ ዝቅ ብዬ ላነሳ ተ ውለታ #አዝ ከነገደ ሌዊ ባልሆን ባልሾምም እንደ አሮን የዜማ እቃ ባልይዝ በገና ላመስግንህ በትህትና ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተሰፋ አድርጌ ስዘምር ቆጠርክልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ #አዝ ከረኝነት ከታናሽ ስፍራ ለንግሥና ምንም ብጠራ ከቀንዲሉ ቀርቧል ሀሣቤ ልቀኝለት በመጥፎ ልቤ ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ #አዝ ሳይከብድኝ የአለም ዝና ተንበርክኬ ልሥጥህ ምሥጋና ምክንያት አለኝ ለማዘንበሌ ናታኔም ነኝ ይቺ ናት ቃሌ ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ #አዝ እንኳን ልቆሞ በፍታን ለብሼ አፍርሀለው እኔ አጎንብሼ የትመክኸት ካባዬን ጥዬ ከመቅደስህ ልግባ ጌታዬ ደጅ ሆኜ ካንተ በር ተስፋ አድርጌ ስዘምር ቆጥረህልኝ እንደዋጋ አከበርከኝ ባንተ ፀጋ
Mostrar todo...
Gere3025 - ___ _ _ _Zemari GebreYohanne eH2mWg2lsG0.m4a5.66 MB
ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ እናቴ ክብርሽን አንግሼ ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ እናቴ ቅድስት አርሴማ ዝናሽ ለዓለም ተሰማ ስመጣ ባልጋ ነበረ ተስፋዬም የተሰበረ በእምነትሽ በፀበልሽ ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ ልናገር ዝናሽን ላውራ ይደነቅ የአምላክሽ ሥራ ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት ሆኖኛል የእምነቴ መብራት ደምግባት ከንቱ ብለሽ ለሰማይ ክብር ታጭተሽ የእምነቴ አሰረ ፍኖት በምልጃሽ አለሁ በህይወት የልቡን ለነገረሽ ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል እርዳታሽ የደረሰለት ያመጣል የልቡን ስለት ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው ባንቺ አፍሮ የሄደው ማነው የልቡን ለነገረሽ ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል
Mostrar todo...
ዘማሪት_ሲስተር_ልድያ_ታደሰ_New_Ethiopian_Orthodox_Mezmur_2022128k.mp35.61 MB
+ ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ? ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡ ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡ + ጸሎት + ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ! አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡ ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!" ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የካቲት 27 2013 ዓ.ም ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Mostrar todo...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

11:23
Video unavailableShow in Telegram
እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደርጋል ጌታ @21media27
Mostrar todo...
እመኑ_በእርሱ_ድንቅ_ያደርጋል_ጌታ_21media27_3vfwQZSlIq8_134.mp418.06 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.