cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
13 355
Suscriptores
+2024 horas
+1037 días
+29530 días
Archivo de publicaciones
"ሳራ ነኝ ሰለምቴዋ" በሚል አካውንት የምናውቃት እህታችን በኦንላይን ሾፒንግ የሚከተሉትን አልባሳት የመሸጥ ስራ ጀምራለች። የወደዳችሁትን ልብስ በመግዛት አበረታታቷት፦ ስልክ ቁጥር፦ +96654 798 4638 📞
Mostrar todo...
👍 71 13🎉 1
ከጎኑ የሚሰግደውን ሰው የለቅሶ ሲቃ በመጠኑም ሰምቶ ነበርና ሲጨርሱ ወደሱ ዘወር ብሎ "ምን ያክል ትርጉሙ ቢገባህ ነው እንዲህ ያስለቀሰህ?" አለው ሰውየውም በትካዜ "የቁርአኑ ትርጉሙ አልገባኝም፤ ያስለቀሰኝም እሱ ነው" አለው። ለስንቱ የዱንያ ሀጃ በርካታ ስራዎችንና ሳይንሶችን ለብዙ አመታት ያጠናው ጭንቅላታችን የአሏህን ቃል ግን ትርጉሙን እንኳን አለማወቁን ማሰብ እንዴት ሀዘን ይፈጥራል?
Mostrar todo...
😢 122👍 19 8
ከፈትዋ ውጭ ላሉ የንጽጽራዊ ጥያቄዎች ብቻ፦ t.me/Yahyanuhe1
Mostrar todo...
👍 42 2
ቲክቶክ እንደገባሁ ፕላትፎርሙ ለአጫጭር ቪዲዮዎች የተገነባ በመሆኑ ምን መስራት እንዳለብኝ ጊዜ ሰጥቸ ማሰብ ጀመርኩ። ከመጡልኝ ሀሳቦች መካከል "ስቲሮት - ከ100 በላይ የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች" የተሰኘውን መጽሀፌን ሙሉውን በአጫጭር ቪዲዮ በማቅረብ መጽሀፉን ላላነበቡ ሰዎች አሰልቺ ባልሆነ መንገድ ማቅረብ ነበር። ሀሳቡን ካመጣሁ በኃላ በምን መቅረብ እንዳለበትም የራሴን ምልከታ ይዠ ሁሌም ወደሚተባበረኝ ግራፊክስ ዲዛይነር ወንድሜ ሄድኩ። ከዚህ በፊት እንደነበረው ነጻ ትብብር እንዲያደርግ ሳይሆን ቋሚ ስራ ስለሚሆን የማክዮቶም ቢሆን የሆነ ነገር ለአንድ ቪዲዮ እያሰብኩለት እንዲሰራልኝ ነገርኩት፥ ብዙም አላሳሰበውም፣ ሁሉኑም የዳዕዋ ስራዎቼን ከመጽሀፎቼ ኢዲት ጀምሮ ስለሚሰራልኝ አጅሩ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርግ አቃለሁና እምቢ እንደማይለኝ በመገመት ነበር የሄድኩት፣ ተስማምተን ስራውን ጀመረው፥ ቪዲዮዎቹ በተጀመሩ ሰሞን ጥቂት ሰዎች ቪዲዮዎቹ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከወዳጅ ዘመድ እየተላከላቸው ማግኘታቸውን እየገለጹ ቴሌግራሜን አፋላልገው እስልምና ላይ ያሉ ጥያቄዎቻቸውን ይጠይቁኝ ጀመር። ብዙዎቹ ጋ ደስ የሚል ተግባቦት ፈጠርን። ከብዙ ቀናት በኃላ ሀገራችን ካፈራቻቸው ታላላቅ ዓሊሞች መካከል አንዱ የሆኑት ሸይኽ ትምህርቶቹን በብዙ ቦታዎች እንደሚያሰራጯቸውና እንደወደዷቸው ብዙ ፍሬም እንዳመጡ ነገሩኝ። ለካ ቪዲዮዎቹ ከተሰሩ የትም ቦታ መድረስ ይችላሉ በሚል ትልቅ ሞራል ነበርና ስራውን ማስፋት እንዳለብኝ አመንኩ። ወንድማችን ጋር በመነጋገር ግጭቶቹ 100ዎቹም በአሏህ ፍቃድ ለመዳሰስ ተስማማን። በተጨማሪም የመጽሀፍ ቅዱስ የንባብ ልዩነቶችን/Textual Variants/ አስመልክቶ "የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች" በሚል የተጀመረው ፕሮግራምም ይደርሳል። - የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች 35 ክፍል የደረሱ ሲሆን በቲክቶክ፣ በፌስቡክ በቴሌግራምና በዩቲዩብ ይለቀቃል - የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች እስካሁን 4 ክፍል የተለቀቀ ሲሆን ከረመዷን በኃላ በአሏህ ፍቃድ በሰፊው መድረስ ይጀምራል - መጽሀፍ ቅዱስና ጥያቄዎቼ እስካሁን 5 ክፍሎች የተለቀቀ ሲሆን እንደሁኔታው እሱም በአሏህ ፍቃድ ይቀጥላል። ትምህርቶቹን ባገኛችሁት አጋጣሚ በቀናነት ለወገኖቻችን ሼር ማድረግ አትርሱ፤ የትኛው ትምህርት ለሒዳያ ሰበብ እንደሚሆናቸው አናውቅም። የኛ ኃላፊነት በታዘዝነው መልኩ ማድረስ ብቻ ነው፥ በኒያችን ልክ እንመነዳለን። አሏህ ከፈቀደ ደግሞ በዚህች ትንሽ ስራ በርካታ ሰዎችን ወደ ሒዳያ ሊመራልንም ይችላል። አሏህ ይገዘን..! 📌 ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@yahyaibnunuhe?_t=8ktCFn5kjJt&_r=1 📌 ቴሌግራም https://t.me/Yahyanuhe 📌 ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/LUWjmvQRLtVVzsSX/?mibextid=qi2Omg 📌 ዩቲዩብ https://youtube.com/@YahyaIbnuNuhe?si=-ffuMuU8R4Dp7w85
Mostrar todo...
👍 38 6
Photo unavailableShow in Telegram
ስምህ በሰዎች ዘንድ መታወቁ አልያም ስራዎችህ ሰዎች ዘንድ አጀንዳ መሆናቸው ለአኼራ ስኬትህ ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም። وَرُسُلًا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ “...ባንተ ላይም ያልተረክናቸውን መልክተኞች (እንደላክን ላክንህ)..” ቁርአን 4፥164 በሰዎች ዘንድ የማይታወቁ አሏህ ﷻ ዘንድ ግን የሚታወቁ በርካታ ነብያት አሉ። አሏህ ዘንድ ለመታወቅ በርትቶ መስራት ትልቁ ስኬት ነው። የፍጡራን ሙገሳና እውቅና እዚህው ምድር ላይ የሚቀር ትርጉም አልባ ቅጽበት ነው። በምድር ባይታወቁም በሰማይ ከሚታወቁት አሏህ ያድርገን..! مجهولون في الأرض معروفون في السماء،!
Mostrar todo...
👍 59 19🥰 10
05:46
Video unavailableShow in Telegram
👍 31🥰 8
05:05
Video unavailableShow in Telegram
👍 28 7👏 4
02:33
Video unavailableShow in Telegram
👍 40 4
02:47
Video unavailableShow in Telegram
👍 33 6
02:47
Video unavailableShow in Telegram
Downloaded via: @downloader_tiktok_bot
Mostrar todo...
02:32
Video unavailableShow in Telegram
◾️ ኢየሱስ የተከበረ መባሉ ፈጣሪ ያሰኘዋል? | ምላሽ - 13 🎙ኡስታዝ አቡ ሐይደር ___ https://t.me/Yahyanuhe
Mostrar todo...
02:46
Video unavailableShow in Telegram
◾️ኢየሱስ የአሏህ ቅርብ መሆኑ አምላክ ያደርገዋል? 🎙 ኡስታዝ አቡ ሐይደር ___ https://t.me/Yahyanuhe
Mostrar todo...
2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከአሏህ ዘንድ መሆኑ ፈጣሪ ያደርገዋልን? https://vm.tiktok.com/ZMMBnvmt6/
Mostrar todo...
👍 21
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች - 34 https://vm.tiktok.com/ZMMB6LoDB/
Mostrar todo...
👍 14
Photo unavailableShow in Telegram
ማሪባ - ተምሳሌታዊ መንደር በአውስትራሊያ ጠራፋማ አካባቢዎች የምትገኝ ብዙም የማትታወቅ ማሪባ የምትባል ትንሽየ መንደር አለች። ዶክመንትሪው የሚያትተው በመንደሯ የሚኖሩ ሙስሊሞች ያሳለፉትን ታሪክ ነው። በፈገግታ ጀምሮኝ በእንባ እያጀበኝ ጨረስኩት። ከ100 አመት በፊት ከአልባኒያ ተሰደው የመጡ ሙስሊሞች እስካሁን ዲናቸውን አቆይተው ለልጅ ልጆቻቸው እንዴት እንዳስተላለፉት የሚዘግብ ዶክመንትሪ ነበር። በዚህ ሒደት ውስጥ ወንድሞቻቸው ከፍረውባቸዋል፣ ከቤተሰባቸው ጥቂት የማይባለውን በሚሽነሪ ተነጥቀዋል። ብዙ ድንግዝግዝ ገጥሟቸዋል። ... ጥቂቶች ግን በጽናት ዲኑን ይዘው ከነሱም አልፈው ለበርካቶች መስለም ምክንያት ሁነዋል። ከቤተሰባቸው ውስጥ የከፈሩባቸውን አስበው ሲያለቅሱ ውስጥን ይፈታተናል። ከዚያ ሁሉ መከራ በኃላ ግን በፍጹም አልተሰበሩም። እንደገና ተባብረው መነሳት ቻሉ። የከፈሉት መስዋዕትነት በጥቂት ደቂቃ ዶክመንትሪ ሲታይ ቀላል ይመስላል። የኖሩት ስቃይ ግን ሲያወሩት ከፊታቸው ይነበባል። ምን አስታወሰኝ?በየአካባቢያችን ይህንን ዲን ለኛ ለማስተላለፍ በአባቶቻችን የተከፈለው መስዋዕትነት እንዲሁ ቀላል አይደለም። በየቦታው ይዘገብ ቢባል ብዙ የኢማንና የትግል ትምህርቶችን የሚሰጡ ታሪኮችን መስማታችን አይቀርም። የሚያስጨንቀው ግን እኛስ ለልጆቻቸችን ይህንን ዲን ለማስተላለፍ እያደረግን ያለነው አስተዋፅኦ ምን ያክል ነው የሚለው ነው?ሰዎች አምነው እንዲድኑና ጀነትን እንዲያገኙ በመጨነቅ ለሌላው ህዝብ ያደረግነው ጥሪስ ምን ያክል ነው?መርሳት የሌለብን ግን በባከነችዋ እያንዳንዷ ጊዜያችን ልክ የምንቆጭበት ጊዜ እንደሚመጣ ነው። አሏህ ያሳውቀን፥ አሏህ ይገዘን..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Mostrar todo...
👍 71 11
በዚህ ረመዷን በእናንተ እና በጌታችሁ መካከል የሚቀር ሚስጥራዊ ስራን አስቀሩ፥ አሏህ ዘንድ እንጅ ማንም የማያውቀው መልካም ስራ..!
Mostrar todo...
64👍 20
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች - 33 https://vm.tiktok.com/ZMMh5buyX/
Mostrar todo...
👍 17
Photo unavailableShow in Telegram
በሚሴንጀር መልዕክትም ሆነ ቲክቶክ ንጽጽር ለማስተማር ላይቭ ስንገባ አንዳንድ ሰዎች ፈትዋ ይጠይቁናል። ብዙ ሰው የንጽጽር ተማሪ በቀላሉ ፈትዋ መስጠት የሚችል ይመስለዋል። ፈትዋ እውቀትና ጥንቃቄ የሚፈልግ ባለቤትም ያለው መስክ ነው። ፈትዋ የሚሰጠው ዑለማ ብቻ ነው፣ እኛ እስልምና ላይ በሚነሱ ሹበሀዎች ላይ መልስ የምንሰጥ የንጽጽር ተማሪዎች ብቻ ነን። አጋጣሚ ትላንትናም ቲክቶክ ላይቭ ላይ አንድ ሰው ሲጠይቀኝ እሱም ሆነ ሌላ ሰው ጥያቄያቸውን ለሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን እንዲጠይቁ ተናገርኩ፤ እንዴት እንደሚያገኟቸው ግን አልተናገርኩም ነበር። ይህንን ፍቃድ ለመጠየቅ በማሰብ ላይቭ ሲገቡ ድንገት ስላየሁ ጠየቅኳቸው። ስልካቸውን ለፈለገ ሰው ሁሉ እንድሰጥ ነገሩኝ፥ እንዲያ ከሆነ እንደሚቸገሩ ሀሳብ ባነሳም "በፍጹም" አሉኝ። ሰዎች ፈትዋ ፈልገው የሚደውሉት ያስጨነቃቸው ጉዳይ በመኖሩ መሆኑን ጠቅሰው እንደፈለጉ ደውለው ወይንም በዋትስአፕ በኩል መጠየቅ እንደሚችሉ ገለጹ። ባይሆን እኩለ ሌሊት የሚደውሉ ሰዎች ስላሉ ሰአቱን ቀይረው ቀን ቢያደርጉላቸው እንደሚሻላቸው አነሱ። የሚገርመው ግን እኩለ ሌሊት ቢደወል እራሱ ከእንቅልፋቸው ተነስተው ፈትዋ እንደሚሰጡ ጠቅሰዋል። ይህንን ስናወራ እራሱ ፊታቸው ላይ ከፍተኛ ድካም ይታያል። አሏህ እድሜያቸውን ያርዝምልን። ይኸው ስልካቸው፣ በዋትስአፕም መጠየቅ ትችላላችሁ፦ +251932232390
Mostrar todo...
👍 82 21
Photo unavailableShow in Telegram
እውን እስልምና የመዳን ዋስትና የለውም? https://vm.tiktok.com/ZMMrTVJkR/
Mostrar todo...
👍 18
በብዛት የምትጠቀሙትና ለንጽጽር ስራዎች ቅርባችሁ እንደሆነ የምታምኑት አፕልኬሽን የቱ ነው? ትምህርቶችስ በዋናነት በየትኛው የማኅበራዊ ሚዲያ አፕ በኩል ቢለቀቅ ትመርጣላችሁ?በተጨማሪም በጹሁፍ ማንበብ ወይንስ በቪዲዮ መመልከት ይቀላችኃል?Anonymous voting
  • ፌስቡክ
  • ቴሌግራም
  • ቲክቶክ
  • በጹሁፍ ማንበብ እመርጣለሁ
  • ቪዲዮ መመልከት ይሻለኛል
0 votes
👍 39 1
Photo unavailableShow in Telegram
እዚህ ውስጥ ብዙ ወንጀሎች አሉ። ዳሩ ግን የጴንጤ ባለስልጣናት ላይ እየሄዱ መጸለይ ግለሰቡን ከህግ በላይ ያደረገው ይመስላል..! https://vm.tiktok.com/ZMMrFmXVA/
Mostrar todo...
😱 13👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
በዛውያ ቲቪ የሚተላለፈውን የሀሩን ሚዲያ "ጀዛከሏህ" የተሰኘ ፕሮግራም ኢፍጣር ሰአት ላይ ከቤተሰብ ጋር እተመለከትን ነበር። ከመላው ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ 400 ደረሳዎችን ስለሚያቀሩ ወጣት ሸይኽና ዓሊም አስመልክቶ የተዘጋጀ መሰናዶ ነው። ሸይኽ ሙሐመድ ጁድ የዓሊም ልጅ ዓሊም ናቸው። ከምንም በላይ ግን መድረሳው እንዳይበተን በመጨነቅ ከማስተማር አልፈው ለተማሪዎች ምግብ ፍለጋ የሚያደርጉት ድካም እንዴት ልብ ይሰብራል?የነገ 400 ዓሊሞችን ምግብ መመገብ የሚቸግር አቅም ማጣት እንዴት ውስጥን ይረብሻል..?! ኡስታዝ አብዱረሕማን ሱልጣንን ጨምሮ የሀሩን ሚዲያ ባልደረቦች ከሸይኹ ጋር በመነጋር መድረሳውን በአቅማችን እንደ ሙስሊም የምንረዳበትን መንገድ ማመቻቸት ቢቻል እጅግ በጣም ትልቅ እመርታ ነበር። ኢንሻአላህ ስራው ከተጀመረና ከተፈለግኩ ለማስተባበርና በተፈለግኩበት ለማገዝ ሙሉ ፍቃደኛ ነኝ። #ረመዷን_2
Mostrar todo...
👍 85 6
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #32 https://vm.tiktok.com/ZMMM9wNWs/
Mostrar todo...
👍 13
Photo unavailableShow in Telegram
💫አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ 💫 🔅በ ክቡር ኮሌጅ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ እነሆ ለረመዳን ለተቸገሩ ወንድም እህቶች የወር አስቤዛ ለመሙላት እንቅስቃሴ እያረጉ ይገኛሉ በዚህም በተማሪ አቅም የተቻላቸውን እያበረከቱ ይገኛሉ በዚህ መልካም ተግባር ላይ አሻራውን ማሳረፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሙስሊም ለዚህ መልካም ሥራ በ አክብሮት እንጋብዘዋለን!🔅 🍇 አላህ ሁላችንም ለ ከይር ሥራ የምን ያድርገን🍇 ☄የ አንድ ቤተሰብ ሙሉ ፓኬጅ 4700 ብር ነው ☄ ፓኬጁም 🥄ዘይት 5 ሌትር 🥄ዱቄት 10 ኪሎ 🥄ሩዝ 10 ኪሎ 🥄ቴምር 5 ኪሎ ነው ::🙏 ንግድ ባንክ -1000608716665(ዩሱፍ : አብዱል ፈታህ : አብዱረሂም ) ለበለጠ መረጃ -+251991923566 - +251904600868 -+251911155794
Mostrar todo...
👍 12 4
ሁሉም ሰው ያስጨነቀውና እንዲሆንለት የሚመኘው ጉዳዮች አሉት። ከዱንያ ሀጃዎች በላይ ደግሞ የአኼራ ክጃሎታችን የላቀ ነው። ይህ ወር ትልቁ የፈረጃ ወር ነው፤ በዱዓ እንቃረብ። አሏህ ይቀበለን.! ረመዷን #1
Mostrar todo...
37👍 12
እንኳን ለተከበረው የረመዷን ወር በሰላም አደረሰን፤ ወሩን በአግባቡ ከሚጠቀሙበት ሰዎች አሏህ ያድርገን!
Mostrar todo...
66👍 21
"ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታልን?" በሚል ርዕስ ለአንድ ወር ሲሰጥ የነበረው የበይነመረብ ስልጠና ተጠናቋል። ቁርአንን እሳቸው ጽፈውታል በሚል የሚነሱ መከራከሪያዎችን መሠረታዊ በሆነ መልኩ የቃኘው ይህ ስልጠና በትላንትናው ዕለት የካቲት 28/2016 ተጠናቋል። ትምህርቱን ተከታትለው ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎችም የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። © ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል Picture - ሰርተፍኬቱን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የሚገኙ ናቸው።
Mostrar todo...
👏 43👍 13 12