cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ግጥም-በእኛ 💌

"ይሄ ምናገባኝ የምትሉት ሀረግ እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደበግ..." 👇 የተለያዩ ሀሳብ ያላቸው "ግጥሞች ትዝታ፣ፍቅር ፣ናፍቆት የሚወጡበት ቻናል እንዲሁ ለመጋበዝ ከፈለጉ ሁሉም አለ ምን ጎሎ.. ሰላማቹ ይብዛ ሀሳብ ካላቹሁ በዚ ያካፍሉን 👉 @KHaileab @romeoDm አጋር ቻናል ይቀላቀሉ @manbabemulusewyaderegal

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
480
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ነገን እንጃ ግን "አይዟችሁ!" በአድዋ ጦርነት የጣልያን ወታደሮችን ያስደነገጠ ነገር ነበር:: የተጠመደ ቦንብ ላይ ለመውደቅ ውድድር የገጠሙ ሐበሾችን ተመለከቱ:: መተኮስ ችሎ ጠላትን ባይጥል ግን ደረት በመስጠት የሚወድ ገበሬ ምነው ቢሉት "ጥይት ማባከን" ይላል:: ሌላ ጉምቱ ተኳሽ እንዳይፈነዳበት ፈንጂ ላይ በመውደቅ ማምከን :: "እነዚህ ሀበሾች እብዶች ናቸው" አሉ:: ፍቅርን እንደዚህ ሲገለጥ አይተውት አያውቁምና:: ግን ሐበሾቹ አንድ ነገር ገብቷቸው ነበር:: "በመሞት መግደልን" እኛም እንዲቀር የምንጠብቀው መከራ የለም እንድንችለው እንጂ:: ሸክም ካልቀረልን ትከሻችንን እናስፋ:: 👉 እግዚአብሔርን እንታጠቀው! 👉 ለፈሩ ሁሉ መከታ እንሁን:: 👉 ለተጨነቁ አለሁ እንበል:: ከኛ የሚጠበቅብን አንድ ነገር ነው:: እሱም "አንድ" መሆን:: ነገን እንጃ ግን "አይዟችሁ!" ኤልያስ ሽታኹን
Mostrar todo...
"በአፍሪካ የትምህርት ስርአት እንግሊዝኛ ቋንቋን መማር ግዴታ ሲሆን ግብርናን መማር ግን ምርጫ ነው፡፡ ለዚያም ነው እንግሊዝኛ ተናጋሪ ረሀብተኛ የሆንነው!" — ሮበርት ሙጋቤ አየህ ቋንቋቸውን የሚያስተምሩህ ትእዛዛቸውን እንድትሰማ ነው። እንግሊዝኛ ቋንቋቸው ሆድህን አይሞላ፣ ረሃብህን አያስታግስ። ደግሞም እንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ አይደለም፤ የአውሮፓ ታሪክ፣ የምእራባውያን ፍልስፍና ወዘተ ብዙ ኮተቶችን ትማራለህ። አንድ ቁራሽ እንጀራ ለመብላት ጠቅሞህ አያውቅ። የአፍረካ ትምህርት የሚፈጥረው የተማረ ደንቆሮ ነው። ትምህርት ኑሮን ካላሻሻለ፣ አመለካከትን ካልሞረደ፣ ተጨባጭ ለውጥ ካላመጣ ምኑን ትምህርት ሆነ። ግቡ መመረቅ፣ ጋዋን መልበስ፣ በእንግሊዝኛ የበቀቀን ዲስኩር ማድረግ አይደለም። የማህበረሰቡን ኑሮ መቀየር ነው። 📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜 ረምሃይም ኢትዮጵያዊ ቀለም  ፤  የሐበሻ ጦማር @YEHABESHA_TOMAR     @REMHAI 📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
Mostrar todo...
ለጁምኣችን! 💛 'ጦርነት' ማለት ምን ማለት ነው? (እውነተኛ ፍቺው?) ጦርነት ማለት፦ "አሳምረው የሚተዋወቁ፣ የሚጠላሉና ቅራኔያቸውን በሠላም መፍታት ያልቻሉ፣ ዕድሜያቸውን ያመነዠኩ ሰዎች - የማይተዋወቀውን፣ የማይጠላላውንና ቅራኔውን በሠላም ለመፍታት የማይገደውን ወጣት፣ በሠላም ከተቀመጠበት ከሞቀ ቤቱ ጠርተው፣ እርስበርሱ የሚያጨፋጭፉበት የተረገመ መንገድ ነው" "War is an abominable situation in which old people, who knew each other, hate each other, and failed to solve their problems peacefully, would drag the young people, who do not know each other, who do not hate each other, and who are willing to make peace with each other, to kill each other." @Ethiohumanity @Ethiohumanity
Mostrar todo...
#እንኳን_አደረሳችሁ🌼 ለመላው የገጼ ተከታታዮች እንኳን ለ2015 ዓ.ም አደረሳችሁ። ስኬታማ አመትን ተመኘሁላችሁ። 🌼መልካም አዲስ አመት።🌼 🎖 @cekuaa🎖 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! 🕊 @poemers
Mostrar todo...
ጥያቄ """"""""""""""" ለሰላም መዘመር እምነቴ ነው ላለኝ ለዛ ባለ ጦማር ጥያቄ ነበረኝ። የተናገርከው ቃል ፅንፍ እውነት ካለበት ብዕር ይጣላል ወይ ጠመንጃ ለማንገት ብላችሁ በሉልኝ። ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
Mostrar todo...
" ጥልቅ ሀዘን ማለት ማዘን ሲያቅት ነው።ማዘን መልካም ነው፣መኖር ነው፣የህይወት ምልክት ነው። ህይወት ያለው ሁሉ ያዝናል። ማዘን አለመቻል ግን ከሞት ይከፋል።ሰው በመጀመሪያ ስሜት ነው፣ሌላው ሁሉ ተከታይ ነው።ሰው ስሜቱን ካጣ ጎዶሎ ነው።" አለማወቅ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ
Mostrar todo...
በ1971 አንድ ዕለት ሻ/ል አፈወርቅ ዮሐንስ “ውበትሽ ይደነቃል” በሚል ርዕስ የጻፉትን ግጥም እንደ ልጃቸው ለሚያዩት ለጥላሁን ሰጡት፡፡ ግጥሙን ሲሰጡት በግጥሙ ውስጥ ያሠፈሩትን እምቅ ስሜት ጥላሁን እንዳይስተው በመሻት፣ “ለኢትዮጵያችን ነው የጻፍሁት" ብለው ነገሩት፡፡ ጥላሁን በሻምበል ግጥም ውስጥ ያለውን የቁጭት፣ የቁጣ እና የእልህ ስሜት ከደሙ ጋር አዋህዶ የተሰጥዖውን ጫፍ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አስገራሚ ዜማ ሠርቶለት በፍቅር ተጫወተው፡፡ 'ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ ... ምንም ይሁን ምንም እዚህ ቦታ ቀራት ... ቢሉኝ እኔ አላምንም፤ የልቤን ልግለፀው ... ዕውነት በሆነ ቃል ተፈጥሮሽ ፍፁም ነው ... ውበትሽ ይደነቃል፡፡ ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ፣ እኔ እምፈልገው በክፉ የሚያይሽን፣ እንዳያይ ያድርገው እንደጠፋ እሳት ነው እንደተዳፈነ ውበትሽን እያየ፣ ዓይኑን የጨፈነ፡፡ ቁም ነገርሽን ዓይቶ፣ የማያደንቅ ሰው በግልፅ ያስታውቃል፣ ችሎታ እንዳነሰው የጠላሽ ይጠላ፣ ብድሩ ይድረሰው የጎዳሽ ይጎዳ፣ ተፈጥሮ ትውቀሰው፡፡ በከንቱ የሚያማሽ፣ ስምሽን የሚያነሳ ክፉ በመሆኑ፣ አለበት ወቀሳ፤ መንገድሽን የዘጋ፣ በቅናት ተውጦ ፀፀት ያንብግበው፣ ይኑር ተበጥብጦ፡፡' የጥላሁን አድናቂዎችና የሙዚቃ ባለሙያዎችም ጭምር፣ ጥላሁን ካዜማቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘፈኖች “በላጩ የትኛው ነው?” ሲባሉ አንድ ብቻ ዘፈን ለመምረጥ ይቸገራሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ቢያንስ በአንድ ነጥብ ላይ ይስማማሉ - የምርጦች ምርጥ ከሚሰኙ የጥላሁን ዘፈኖች አንዱ “ውበትሽ ይደነቃል” ነው፡፡ የግጥሙ ደራሲ ሻምበል አፈወርቅ ግን “ውበትሽ ይደነቃል” እንዲያ በሚያስደንቅ የድምጽ አወጣጥ ጥበብ በጥላሁን ሲዜም ለማዳመጥ አልታደሉም፡፡ © ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር በዘከሪያ መሐመድ ገፅ፥ 147 @poemers
Mostrar todo...