cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ድርሳነ ጥበባት

ሰላም !! ይህ ቻናል ለተጠቃሚዎቹ የስነ~ፅሁፍ ጥበባትን ለማሰናዳት ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም የአንዳንድ ወጣቶችን ብቃት ለማሳየት እንሞክራለን። "እኛ ሰዎች አከባቢያችንን ነው መሆን የሚንችለው። አከባቢያችንን እንኖራለን ያለንበትን ማህበረሳብ እንሆናለን። ማህበረሰብ የምንገነባው ከእያንዳንዱ ቤት ነው። መሠረት የሚጣለው ቤታችን ውስጥ ነው። መሠረቱ ላይ እንሥራ።" Admin: @Mcmole

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
563
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

መንገሪያ! ከነገ ቅዳሜ _ሐምሌ 3 /2013 ዓ.ም ጀምሮ በእዚህ ቤት ይተላለፍ የነበረው የደብዳቤና ጦማር ቀን እንደተጠበቀ ሆኖ ከዘ_ፍጥረት እስከ ምፅዓት ከኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ጋር የተቋጠረው የዓባይ ጉዳይ የሚዳሰስበት "የዓባይ ነገር"የተሰኘ ዝግጅት እንደምንጀምር እናሳውቃለን። እናንተ የቤቱ ሰዎችም በዚህ አምድ ስር ታላቁን ወንዝና ተፋሰሱን ከየ አንፃሩ እየተመለከታችሁ መሶባችንን ሙሉ እንድታደርጉ ትለመናላችሁ! ሐምሌ_2_ቀን_2013 ዓ.ም ታመነ መንግስቴ ፤አዲስ አበባ _ኢትዮጵያ የሻታችሁን ሁሉ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
ልባሽ አለበሱን (በታመነ መንግስቴ) ከአፄ ፋሲል በፊት፤እንደዋዛ አሰሱን በምኒልክ ዘመን፤ዳግመኛ ከለሱን ፋሽስት ሆኑና፤ያው ትንሽ ቀመሱን አሁን ሰምሮላቸው፤ ልባሽ አለበሱን። ግጥሙ ግጥም ነው።ተውት! የዛሬው ጨዋታችን በአንዲት የደቡባዊ አፍሪካ አገር ላይ የተሰራን ትዕይንተ ዶሴ(Documentary Film) መሰረት አድርጎ የተዋዛ ነው። ርዕሱ በፈረንጅ አፍ"T_Shirt Travels"ይላል።በእኛ አፍ መተርጎሙ አስፈላጊ አልመሰለኝም።ለነገሩ መተርጎሙም ከባድ ነው።ብዙዎቹን የእንግሊዝኛ ቃላት በማደንቀው የአማርኛ ቋንቋ ለመክተብ ስታትር እንዲህ ተራራ የሆኑ ቃላት ይገጥማሉ።"Shirt"ን "ካናቴራ" ማለት ባይሳነኝም "T"ን "ቲ"ማለት ተገቢ አይመስለኝም።ነገሩ ከነገሬ ጋር ስለሚገናኝ እንጅ በቋንቋ ላይ አንድ ቀን እንደምንጨዋወት አልዘነጋሁኝም(አትርሱብኝና ቋንቋ መደባለቅ ለማይምነት መቅረብ መሆኑን በሆነ አፍታ አሳያችሗለሁ)! እንዳልኳችሁ ትዕይንተ ዶሴው የተሰራው በደቡባዊት አፍሪካ ውስጥ ባለች አንድ እባብ የመሰለ ካርታ ያላት አገር ነው።በልጀነታችን ከምንሰማቸው አስቂኝ ቀልዶች መካከል የሆነ ተማሪ ዋና ከተማዋን ሲጠራ "ልዑል ካሳ" ማለቱ ነበር።ለስሟ የቀረበ መጠሪያ ያለው ወንዝ ያጠጣታል።ምናልባትም የአፍሪካ ትልቁ ፏፏቴ በዚያ ይገኛል።ስሟን መንገር "አታውቁም"ማለት ይሆንብኛል😀 አገሪቱና ዋና ከተማዋ ብሎም ወንዟ ማን እንደሆኑ እየገመታችሁ መጨዋወታችንን እንቀጥልማ__ "ኧረ እርየ እርየ _ኧረ እርየው መላ ጎጃም ተገበየ__ፍቅርና ተድላ"ይላል ቆምጫጫው ጎጀ። (ተነገሬ ጋር ምን ያገናኘዋል? ምንም😀) ትዕይንተ ዶሴው ሲጠቃለል"አፍሪካ ማለት ነፃነቷን መልሳ በማጣት ላይ ያለች የምዕራቡም የምስራቁም ዐለም የቆሻሻ ማራገፊያ ናት።"ማለት ይመስለኛል። ጉድ እኮ ነው ሰዎቸ__ አሜሪካዊያን ለብሰውትም፣አጥበውትም፣ጥለውትም ፣አንስተውትም፣መልሰው ጥለውትም ቤት እያጣበበ ያስቸገራቸውን "ውራጅ"ጨርቅ በየ መንገዱ"ስጡን"ለሚሏቸው ሰዎች ይቸሯቸዋል።በትዕይንተ ዶሴው ላይ እንደሚሉት"ምንም ልብስ ለሌላቸው ሰዎች የሚሰጥ፣ለአሜሪካ የጦር ኃይል በነፃ የሚለገስ "ይመስላቸዋል።በአፍሪካ ምድር ሁነኛ የገንዘብ መከመሪያ መሆኑን ማን ይነግራቸዋል? የማወጋው ወግ ግር ያላችሁ በስድስት ኪሎና አካባቢዋ፣በመገናኛ መንገድ፣በሜክሲኮ አካባቢ፣በዚህ በአራዳ መንደር(Piazza)"በረረች፣በረረች፣ሱሪ በሞቶ፣ጫማ በሞቶ "የሚሉ ቀማኞችን ታውቃላችሁ? በቃ ይሄንን ነው የምላችሁ። እናንተ ሆየ(ራሴ እንዴት እንደተንገላታሁ ልንገራችሁ።ከቴስ ከጎዳና ገዝቸ መሰላችሁ? ከመርካቶ ዘግኘ እኮ ነው ጉድ የሆንኩላችሁ።ተምወደው ተወዳጀ ጋር አንድ መልከ መልካም ኮት_Jacket_[ኮት =ኩታ__ይችንም አንድ ቀን እናወጋታለን] ገዛሁላችሁ።ተዚያማ ሲያቀብጠኝ በምናምን ቀኑ አጠብኩላችሁ።ተዚያ ቀለሙ ምን ሆነ ልበላችሉ? ነጭ፣ቀይ፣ቢጫ፣ጥቁር፣የማላውቀው በቃ ጉድ ሆንኩላችሁ።) "ዋጋው በጣም ተራ ሆኖ ነው" ታላችሁ።አባ ይሙት ትሳሳታላችሁ።ማነው 900(ዘጠኝ መቶ) ብርን ተራ ነው ያላችሁ? ይሄ ብር የብዙ አዲስ አበቤ ተቋማት ጥበቃዎች ደመዎዝ መሆኑን ለማታውቁ ልንገራችሁ።አንዳንዶቹ ግን ሲበዛባቸው ነው(ስለነሱም አንድ ቀን እናወጋለን😁) ተዚህ ጉደኛ ኮት በሗላ ልብስ ማመን ተሳነኝ(በቃ ጥቁር ሱሪ ገዝቸ ከማጠብ ወያኔ ተሸንፋለች፣መቀሌም አትገባም የሚለውን የባጫ በደሌ😁 መግለጫ ማመን ቀለለኝ።) ሰዎቸ እየቀለድኩ አይደለም።"ቀልድና ቅዘን"አገራችንን ሲያበላሽ እያየሁ አልቀልድም።መራሄ መንግስት ዐቢይ አህመድ በመደመር መፅሐፋቸው ገጽ_66 ላይ፦ "ብዙ በጭቆና ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች የጭቆናቸውን ሕመም የሚቋቋሙትና ኑሯቸውን የሚያስቀጥሉት ራሳቸውን በቀልድ እየደለሉ ነው።"ይላሉ።እስማማለሁ። ካስፈለገ"ዐለምን ለመለወጥ የሚሰሩ ሰዎች አይቀልዱም።እነማን ናቸው ዐለምን የለወጧት ታውቃለህ? ስሚዝ አዳምስ፣ሪካርዶ፣ካርል ማርክስ እነዚህ ዓለማዊ ፈላስፋዎች ናቸው።እና አይቀልዱም።ያለ ጩኸት ዝም ብለው ዐለምን ይለውጣሉ።"የሚለንን የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ላይ የተሳለ ገጸ ባህርይ እጨምርላችሗለሁ።እናም 'ቀልድና ንቅዘት(ቅዘን ላለማለት) አገር ያበላሻል'እላችሗለሁ። ጨዋታችን እንደ አገሬ ቦተሊካ የተሳከረበት እንዳይሆን እንዲህ እንጠቅልለውማ❤ "ዘመነ ሉላዊነት ብዙ ሕዝቦችን እያገለለ፣ዳር እየጣለ እና ካላቸው ነገር እየነጠለ ነው"ሲሉ በቁጭት የሚናገሩት የ"T_Shirt Travels" ትዕይንተ ዶሴ ቃለ መጠይቅ ተደራጊ ኡርባን ጆሃንሰን ናቸው።እሳቸው የUNICEF የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ሃላፊ እንደሆኑ ልብ ይሏል። በዚሁ ትዕይንት ውስጥ እንግዳ የሆኑ አንዲት ሳተና ሴት አፍሪካዊትም"ነፃ ገበያ ነፃ ገበያ ይላሉ(ምዕራባዊያንን ነው) ግን ነፃው ገበያ ለማን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ። ለዚህ ነው የአፍራካ ነፃነት ከብዙ አስርት ዐመታት በሗላም አጠራጣሪ የሆነው።ዛሬም ዳግማዊ ኃይለሥላሴ፣ዳግማዊ ኩዋሚ ንኩርማህ፣ዳግማዊ ከተማ ይፍሩ፣ዳግማዊ ጁሊየስ ኒሬሬ፣ዳግማዊ ጸጋየ ገብረ መድኅን ያስፈልጋሉ።"አፍሪካ ቀዳሚውን የሰው ልጅ ስልጣኔ በዐባይ ሸለቆ ላይ የጀመረች የካም እና ኩሽ ምድር፣በሗላም እናንተ ባሪያ እያደረጋችሁ እስከምትፈነግሉት ታላቁ ቄስ ዮሐንስ(Priester John) የነገሰለት፣መንሳ ሙሳ በቲንቡክቱ ቀየ ወርቅ የነሰነሰለት፣ለሾና ሕዝብ አገሩን "ታላቋ" ዚምባቡየ እያለ ታሪክ የሰገደለት ኃያል ዘውግ የሚኖርባት የምድር ዕምብርት ናት እንዲሉ። አፍሪካና አፍሪካዊያን(ኢትዮጵያዊያንም መጠነኛ ኩራታችንን ተወት አድርገን እንደ አፍሪካዊ ማሰብ አለብን።ከሰሞኑ ስማቸውን የዘነጋሁት ምሁር'ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ቅኝ ያልተገዛች አገር ምናምን ስንልኮ በተገዙት የአፍሪካ ወገኖቻችን ቁስል ላይ እንጨት እየሰደድን ነው'ያሉበትን ንግግራቸው በጣም ወድጀዋለሁ።በተቻለን መጠን አፍሪካን አክብረን ልንመራት ይገባል።ታላቁ ንጉስ ቀኃሥ በመንግስታቱ ማህበርና የተለያዩ አገሮች ዞረው ዞረው በመጨረሻ እንደማይሆን ሲረዱ "የአፍሪካ አባት"መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም።) ስለሆነም አፍሪካና አፍሪካዊያን በሚያኮራው ማንነታችን ሊያሳፍሩን ቢጥሩም ልናፍርላቸው ፈፅሞ አይገባም።ልባሻቸውን እና በቅንዝር የተሞላ ጥቅስ ያጥለቀለቀው ሹራባቸውን አውልቀን ጥለን የእኛን ባህላዊ ልብሶች በብዛት በማምረት መልበስ እንችላለን። እኛን የጎደለን ስነ ልቦናዊ ብስለት ነው።እንመልከት፣እናንብብ፣እንጠይቅ፣እምቢ እንበል። (ኤዲያ ላወጋችሁ ያሰብኩት ብዙ ነበር።አሁን ባስበው ረጅም ጡፍ አታነቡም።ደሞ ይሄ ወንፊት የመሰለ ማህበራዊ መገናኛም ተረዘመ ያፈሰዋል።ዴሞ "ነገር ቢያበዙት በአህያ አይጫንም"ና ለዛሬው ይበቃናል።ትዕይንተ ዶሴውን ተመልከቱት፣የአገሪቱን፣የዋና ከተማዋንና የወንዙን ስም አሁኑኑ ምንም ነገር ሳታዩ እዚሁ ላይ ገምቱና ከሃሳቦቻችሁ ጋር በተለመዱት አድራሻዎቸ ላኩልኝ! የምወዳችሁ ነኝ!) የሻታችሁን ሁሉ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
ትግራይ፦የታሪክ ወለፈንድነት* እና ሰሞነኛ ጣጣ (በታመነ መንግስቴ) እኔ በመራሄ መንግስቱ ዐቢይ አህመድ ፅሕፈት ቤት አልታደምኩም።በነዚያ ነጫጭ ወንበሮች ላይ አልተቀመጥኩም።ከሰውየው ዘንድ ፍርፋሪም አልቀመስኩም።በአሸናፊው አንደበታቸው ተረትቸም አላጨበጨብኩም።ግን ዘመኔ የመረጃ ነውና ሰውየውም ያሉትን ጋዜጠኞቹም የሆኑትን ታዝቤያለሁ።በሚከተለው መጠነኛ የልጅ ትንታኔየ ሰሞነኛውን የተከዜ ማዶ ጣጣ ከታሪክም፣ከተረክም፣ከዛሬም ከነገም አንፃር እመለከተዋለሁ። ስሙን የደበቅሁለት ዘፋኝ ተወዳጀ እንደነገረኝ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ዳንኪራ ቤቶች"እምበር ተጋዳላይ"መቀንቀን ጀምሯል።በዚህም የተነሳ የመዲናይቱ ቀውጢ መጨፈሪያዎች ገበያቸው ተመናምኗል።ብልፅግናውን ፍራቻ የማስደለቅ ቅስማቸው ኮስምኗል። ከተከዜ ማዶ ደግሞ ምናልባትም የቀበሮ ደስታ ቢጤ ሆኗል።በዚያ መራሔ መንግስት ዐቢይ አህመድ በገደምዳሜው"ወጋን"ያሉት ትግሬ "ታጋዮቹን"በፌሽታ እየተቀበለ ይመስላል። የኒያ ደጋግ ሰሜነኞች እጣ ፋንታ በቀናነት ለተመለከተው እጅጉን ያሳዝናል።ያ_ምድር ላለፉት ቢያንስ 5 መቶ ዓመታት የቀውጢ ጦርነቶች ሁነኛ መድረክ ሆኗል።እናም እነ በዓሉ ግርማ እንደሚሉትና ታሪክም ደጋግሞ እንደሚነግረን ቦታው የ"አድር ባዮች"ምድር ሆኗል። ላይኞቹ አንቀፆች መራራ መሆናቸው ይነበበኛል።ነገር ግን የሐበሻ ጀብዱ ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ መኮንን ስለ ጉዳዩ ጠይቄያቸው እንደመለሱልኝ"ተፈርቶ አይኖርም"ና ሃቅ ሃቁን ብንነጋገር ያግባባን ይመስለኛል። በዓሉ ግርማ የሰዎቹን ስነ ልቦና ከተረዱት ጋር ተነጋግሮ ሊፅፈው ችሏል ተብሎ በሚገመተው"ኦሮማይ"የተሰኘ ታሪካዊ ልቦለዱ ውስጥ፦ "ሰለሞን ለመናገር ብሎ የሚናገር ሰው አይደለም።ከተናገረ ስለሚናገረው ነገር ካንጀቱ ስለሚናገር አድማጭ ይስባል።"ብሎ ባስተዋወቀን ገጸ ባህርይው አማካኝነት በገጽ _83_ላይ ከመረብ ማዶ ስላሉት ትግሬዎች ስነ ልቦና ሊነግረን ይሞክራል። "___በኤርትራ ክፍለ ሀገር ታሪክ ውስጥ የበላይነትን ያገኛል ተብሎ የሚገመተውን ኃይል ተቀብሎ የማስተናገድ ዝንባሌ አዲስ ነገር አይደለም።በ400 ዘመን የትግል ታሪክ ውስጥ አንዱ ኃይል ሲሄድና ሌላው ሲመጣ ማየት የተለመደ ነገር ሆኖ ቆይቷልና አድርባይነት ሁለተኛ ተፈጥሮ ሊሆን ምንም አልቀረውም።መጠራጠር ይበዛል።የ"ቶማሶች"ቁጥር ቀላል አይደለም።" ደራሲው ለመረብ ማዶ ሰዎች የከተበው ሃቅ ለተከዜ ማዶዎቹም የሚሰራ ይመስላል።መከላከያው መቀሌ ሲገባ "ጁንታው ጨቁኖን ነበር"ብሎ እነ ደፂ ከጫካ ወደ ከተሞች ሲጠጉ "እምበር ተጋዳላይ" ማለት ከአድር ባይነት በምን ይለያል? በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጨክኖ መተኮስ፣"አንድ ቄስ የማስተማሪያ ድምፅ ማጉያና ክላሽንኮብ"ይዘው መውተርተር ምን ይባላል? ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መጥላት ከዚህ በምን ይለያል? እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ የአራት ኪሎው ባለሟል እንዳሉትም "የጥሞና ጊዜ ያስፈልጋል!" እንደ ኩሩ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከማደንቃቸውና ከሚያሳዝኑኝ ነገስታት መካከል ትግሬው ቆራጥ መሪ ዮሐንስ አራተኛ ይገኙበታል።የእሳቸው በድልም በእድልም የተዋዛ የግዛት ዘመንና በመጨረሻ ለኢትዮጵያ ቁራሽ መሬት ሲሉ አንገታቸው በመሃዲስት እጅ መቆረሱ ከጥፋታቸው በላይ እጅጉን ይጎላብኛል። ይሄንን እያሰላሰልኩ በትግራዋይ ጀግንትና የኢትዮጵያ ስልጣኔ እምብርትነት ስኮፈስ አስቀያሚዎቹ የከሃዲነት አጋጣሚዎች እንደ ሰኔ መብረቅ ብልጭ ይሉብኛል። የሐበሻ ጀብዱ መፅሐፍ ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ መኮንን በተገኙበት የአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ የመፅሐፍት አውደ ርዕይ መድረክ ላይ አስተናባሪ የነበሩት ታላቁ የስነ ፅሁፍ አስተማሪ ሊቀ ምሁሩ ደረጀ ገብሬ በዕለቱ ሲመክሩን"ታሪክ መማሪያ እንጅ መማረሪያ"ስላልሆነ በዚሁ መፅሐፍ ገጽ_307 ላይ ተከትቦ ብዙ ያነጋገረን አንቀፅ ከዚሁ የተከዜ ማዶ ሰዎች ጣጣ ጋር በእጅጉ ይቆራኛል። የዚህ ተወዳጅ መፅሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ የኢትዮጵያው የገበሬ ጦር በብዙ አጋጣሚዎች ድልን በጣሊያን ላይ ተቀዳጅቶ ዳግማዊ አድዋን ሊያበስር ሲል እንከን እየሆኑ በአገራቸው ታሪክ ላይ ቀፋፊ ቀለም ያስቀመጡትን ሰዎች በስም ይጠቅሱና "___በማይጨው ጦርነት በዚያች ቀውጢ ሰዓት በሰሩት ስራ እኔም "አረመኔዎች" ናቸው ከማለት ወደሗላ አልልም።" ሲሉ እጅጉን ያዝኑባቸዋል። በጉዳይ ላይ ብቻ ከተርጓሚው ጋሽ ተጫነ ጆብሬ ጋር መጠነኛ ክርክር ለማድረግ ሞክረናል።በዚያች አፍታ ከተሰነዘሩ የታዳሚያን ዕይታዎች መካከል የማረከኝና በዚህ ፅሁፍ ውስጥም ጎልቶ ቢነበብ የሚያግባባን "ባንዳነት ከGeographical Location አንፃር"ቢታይ ሲሉ አንድ ሰው ያነሱት ሃሳብ ተመችቶኛል። የነገሩን ሁነኛነት ለመፈተሽ ባደረግሁት ጥረት የዚሁ መፅሐፍ ደራሲ በተጠቀሰው ገጽ ላይ ከብስጭታቸው ቀጥለው"ራያዎች በዘር ኦሮሞዎች ናቸው ይባላል"ያሉበት አገላለፅ ቀን የከፋ ለታ የትኛውም "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው"የሚል ብሔር አገሩን አሽቀንጥሮ ከመጣው ጋር አሸሸ ገዳሜ ሊል እንደሚችል ማሳያ ይሆናል። "ቀን ዘመድ እኮ ልዠ እናትና ልዡን የሚያስተቃቅፈው የቀኑ ማማር ነው።"ስትል የአያቴ ምሽት የነገረችኝ በኑረት የተፈቸነ ሃቅም በእንዲህ ያሉ ተጠየቆች ይሰራል። "ብሔርም ባዕዳ ነው፤ይገለባበጣል አብሽሪ ኢትዮጵያ፤የአንች ቀን ይመጣል።"** በዚህም ተባለ በዚያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ መውጣቱ በአንፃራዊነት ለሁሉም ይበጃል።መራሔ መንግስት ዐቢይ አህመድ ለጋዜጠኞቹ ሲነግሩ እንደሰማነው ሕዝበ ትግራዋይ የመከላከያን ጣዕም" ቢያንስ በወር ውስጥ ቢበዛ በሁለት"ሊረዳው ይችላል።እስካሁን ግን ለብዙ ክፍለ ዘመናት ታሪክ እና ዕድል ፊታቸውን አዙረውበት መጠነኛ የአገር ክህደቶችና በትህነግ(TPLF) ስብከቶች የተማረከ ይመስላል። "ከድህነት ነፃ እስካልወጣን ድረስ ባንዳነት አይጠፋም።"የሚለው የጋሽ ተጫነ ጆብሬ መኮንን ሃሳብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ይሰራል።የራበው ታማኝ ውሻ ጎን ሲርቀው ማጀት ማማተሩ ወይም ጎረቤት ሄዶ ተከርቸም መሆኑ መች ይቀራል? ስለዚህ ዘመቻችን ድሕነት በሚባል ሁነኛ ጠላት ላይ ቢሆን ይሻላል።ጠብመንጃው ስራ ይባላል።ስራ ሰውን ሳይሆን እንጀራን ያበላል። ይቆየን! *.ወለፈንድነት___Paradox ለሚለው ቃል አንፃራዊ ፍች እና ግራ አጋቢ፣የሚያምታታ ማለት ነው። **.ግጥሙ ፦ሰውነት ባዕዳ ነው፤ ይገለባበጣል አብሽሪ ቲኑየ፤ የአንች ቀን ይመጣል" ከሚለው የትህትና መኩሪያ ግጥም ቃላት ብቻ ተቀይረው የተወሰደ ነው። ሃሳባችሁን ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
ምሽት 12:00 ላይ "የጋራ ነው"የሬዲዮ ዝግጅት በአዋሽ FM 90.7 መደመጥ ይጀምራል። ስለ ደግነት አርማዋ እማማ አበበች ጎበና መነጋገራችን እንደተጠበቀ ሆኖ፦ 👉ሰሞነኛ የታሪክ አጋጣሚዎችን በምናወሳበት አፍታ በሐምሌ ወር ተወልዶ በሰኔ ስለሞተው "የወራሪዎች ንጉስ "ጨዋታ ይዘናል። 👉ባህልና ወግ ላይ "አሻም አሻም"እያለ ለኢትዮጵያዊ ባህልና ጋዜጠኝነት ሲተጋ ኖሮ በጎልማሳነቱ ስላጣነው ጋዜጠኛ ካሳሁን አሰፋ ጉዳይ ይኖረናል። 👉በኪነ ጥበብ ሰዓታችንም ወደ ወሎ ተጉዘን በዚያ ከ"እሪኩም ዘመዳ" እስከ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት አዘል ግጥሞች ምጥን ዝግጅት ይዘናል። 👉በፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዳሰሳ ጊዜ ወደ ልበ ተራራዋ ትንሽየ አገር ኩባ እናመራለን። 👉ከእናንተ አድማጮች ጋር ለመወያየት የመረጥነውም "ዘመናዊነት እና ኢትዮጵያ ምንና ምን ናቸው?" የሚል ርዕስ አለን። ክቡራትና ክብራን ከእናንተ ጥሞና እና ተሳትፎ እንጠብቃለን። አጫጭሮቹን መልዕክቶቻችሁ በድምፅም እየቀረፃችሁ፦ 👉6804 ላይ ላኩልን። በቀጥታ የስልክ መስመርም፦ 011 5 54 33 16 ወይም የመጨረሻውን 19 እያደረጋችሁ ደውሉልን። ሃሳባችሁን በማህበራዊ መገናኛውም፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
እውስ | ባህላዊ የወንጀል ምርመራ ጥበብ በአለሙ ባንቴ "አንቺ አያልነሽ!? እቴ ማን ነሽ ነይማ ወደውስጥ። ምን እዚያ ማብሰያ ተቀምጠሽ ምን ትሰሪያለሽ? አየ አረጀሁ መሠል ስም ሁሉ ይሳተኝ ጀመር" "ኧረ መጣሁ እመ። ቅድም ዝናቡ ስለ መታኝ ጠፈፍ ልበል ብየ እሳት እየሞቅሁ ሁኖ'ኮ ነው።" አለቻቸው። "ንሽማ እንግዲህ ጋሽ ግብርናው መጥቶ የለም ከሱ ከአንድ ቀኑ ቆረጥ ቆረጥ አርጊና ወጡ ላይ ጣል አርጊበት። አየለንም ላም ሲያጣባ የዛሬውን ወተት እንዳትቀላቅለው ብላሃለች በይው።"አሉና ወደ ውስጥ ተመልሰው ገብተው ከሰኞ መደቡ ላይ ቁጭ አሉ። እማሆይ የልፌ የጉልበታቸው አቅም እና የሰውነታቸው አቋም እድሜ ቢጫነውም አስተሳሰባቸው ግን በእድሜ ብዛት እንደ ወይን የጣፈጠ ሆኗል።ደስ ይላሉ ፤የአስተሳሰብ ቁመናቸው የእሳቤ አድማሳቸው ፥ ከስብሰባው ስንመለስ የነገሩኝ። ጮቄ፥ መሃል ጮቄ የተገኘሁበት በግብርና ሞያተኝነት ቢሆንም ማህበረሰባዊ ግብዣው እኔንም እንድካተት አደረገኝ። እንዲህ ነበር፦ በአጠገቤ አንድ ሰው ፈጠን ፈጠን ብሎ ባንዲራ እና ጥሩምባ ይዞ እያለፈ "ደህና አደራችሁ" ብሎ ምንም ሳይቆይ ሄደ፥በፍጥነት።አጠገቤ ያለውን የገጠር አመራር " ምንድን ነው?" ብየ ጠየቅሁት። "እንጃ አይነገርም።ብቻ የሆነ ችግር አሁኑኑ ተከስቶ ነው።እኛም እንሄዳለን አንቀርም።አንተ ም አትቀር።" አለኝ። "እኔ ደሞ ምን ቤት ነኝ።ይልቅስ ስራየን ሰርቼ ቶሎ እንዳልመለስ አንተን ሊወስዱብኝ ነው" አልኩት። ወዲያውኑ ያ ሰውየ ይዞት የነበረውን ባንዲራ አንድ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተከለና ጥሩምባ መንፋት ጀመረ።እኔና አብሮኝ የነበረው አመራር ለቦታው ቅርብ ስለነበርን ቶሎ ፈጥነን ደረስን።መጀመርያ ጥሩምባ የነፋው ሰውየ ቀጥሎ እኔናአመራሩ ተገኘን።አምስት ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ግን ቦታው ተጥለቀለቀ ፥ በሰው።ይህ ሁሉ ሰው ከየት እንደመጣ አላውቅም።ብቻ ግን ከዚያች በአብዛኛው በሳር ቤት ከተመሠረተች መንደር ብቻ አይመስልም።አንዳንዶቹ አለባበሳቸው ሁሉ ስርዓት የሌለው፥ እጃቸው ሊጥ ጋር ይዘው መጡ።ሳይታጠቡት። "ምነው? የሰው ሁኔታ ተለየብኝሳ?አልኩት አሁንም ያንኑ አመራር። "እንዴት?" "አሁን ያች ሴትዮ ወደዚህ ያለችዋ ሊጥ ስታቦካ ነበር መሠለኝ።ግን እንዴት ታጥቦ መምጣት አቃታት? ደሞ ሌላኛዋ አየሃት አሁን አለባበስ እንዲህ መሆን አለበት?" "አይ ጋሼ ተጎጂው እየጮኸ እሷ ልብስ ልምረጥ ካለች ምኑን ለችግሩ ደረሰችለት? ሊጥ ልታጠብ ምጣድ ላውጣ ገለመሌ የምትል ከሆነ ምኑን ደረሰችለት? ለሰው ስትደርስ የራስህን አቋርጠህ ለሰው ቅድሚያ ሰጥተህ ነው።" ገረመኝ።እንዲህ አይነት የማህበራዊ ስሪት እሳቤ የደረሰ ማህበረሰብ አለን? ደግሞ ከኋላ በኩል ባንዲራ ተክለው ሰቅለው። ከመሐል አንድ አደፍ ያለ ጋቢ የለበሱ ሰውየ ተነስተው ቆሙና "እንግዲህ ብዙም የቀረ ሰው የለም። የሚመጡትም እየመጡ ነው።" ብለው ጀመሩና ሁኔታውን ቃኘት ቃኘት አደረጉ።(እኛ ዘመንን የምንሎቺ አቴንዳንስ የምንለውመሠለኝ) ካደረጉ በኋላ "እናውጋው ፥ እናውጋው ገበየሁ ስርቆት ተሰርቂያለሁ። ንብረት ጠፍቶብኛል ብሎ ለኛ ነገረን። ያው እንግዲህ እኛም አባቶቻችን ባቆዩን ደንብ መሰረት ፣የአባት ቅብቃብ ነውናኖ እናንተን ጠርተን ወይ ንብረቱን አግኝተን፥ወይ እውስ አውጥተን ወይ ቀን ቀጥረን ለመለያየት ነው" እንዳሉ አንዲትሰው ከመሐል "እና ተነስቶ ይንገረን እንጂ"አሉ።እናውጋው በታዘዘው መሠረት የጠፋበትን ንብረት አስረዳ። _የጠፋበት አንድ ዳውላ ገብስ እንደሆነ _የገብሱ አይነት ተጋድሜ የሚባለው እንደሆነ _የጠፋው በምን ሰዓት እንደሆነ እንደማያውቅ አስረዳና ተቀመጠ። ማህበረ ሰቡ በችግሩ በስፋት ተወያየ።በድፍረት ግን በጨዋነት። የኔ ሚና መከታተል ነበረ። በማደማደሚያው እኒያ ጀምረውት የነበሩት ሽማግሌ ቆሙና "ያው እንግዲህ ዝናብም እየመጣ ነው።ምሸቱም እንዲሁ። እና የሰጣችሁንን አሳብ ተቀብለናል።ዙሮ ዙሮ ስርቆት አለ ችግር አይከሰትም። ያ ሰው እርቦትም ይሆናል። ቸግሮትም ይሆናል። ደሞ እናውጋውም እንደምታውቁት ልጆች አሉት።ኑሮ አለው እሱ ወጣት ነው መሬት እንኳን ብዙ የለው።እና ምንድን ነው ከዚያ ሁሉ ያየ አየሁ አይልም አምጥታችሁ በሌሊት በሩ ላይ ጣሉት አስቀምጡት።ብትታዩ አትጋለጡም። አንተም ደሞ እናውጋው ቤትህንም ሚስትህንም አኗኗርህንም ፈትሽ።ቤትህን ያስቀመጥህበትን ሚስትህን ደሞ አጠቃቀሟን ወይ ተፈጭቶ ቢሆንስ ሌላው አኗኗርህንም ፈትሽ ።" አሉ ሽማግሌው። ቀጠሉ፤ "እንግዲህ እውስ በሰጣችሁን መሠረት ዛሬ ሌሊት ካልተጣለ ነገ ጠዋት ምርመራ እናረጋለን"አሉና የጉባኤው መበተን እና ለነገ መቀጠር ተነገረ። የኔ መንገድ አሳሳቢ ሆነ።አልደርስም። እንደ ወታደር ሰፈር እና ቤት ተመረጠልኝ።የእማማ የልፌ ቤት።እኔና እማማ የልፌ በመንገድ ላይ ብዙ ቁም ነገር አወራን።ጨዋታቸው ጥሩ ነው። "እንዲያው እማማ ስሪያችሁ በጣም ያስደስታልኮ" አልኳቸው። "አይ አንተ አንድ አገር ሲኖር ሰሪ መሪ ያስፈልገዋል።ያለ ስሪ የሚሆን ነገር የለም። ይኸ ልጅ አሁን ለማን ይናገር ነበር።የአባቶቻችን ሁኔታ ባናስቀጥል እና ስሪያቸውን ባናከብር ኖሮ።እናንተ ከተሜዎች እማ ለፎሊስ ነው የምትናገሩ።ፎሊስ ሌባ አያስወጣምኮ። " "እንዴት እማማ?" "እየውልህ ሌባን ለማውጣት፥ ስርቆትን ለማስቀረት ባህሪን መቅረጽ የሚችል ስሪ ያስፈልጋል።ጸባይን የሚያርቅ ሰው ያስፈልጋል።የኛ አሁን የተቀረጸ ማህበረሰብ አለን።በማህበረሰቡ መካከል ሲኖር የስሙ ክብር የሚያስጨንቀው፥ የአባቴን ስም አላበላሽም የሚል።" "ጥሩ ነው በጣም" አልኹኝ ተሳትፎየን ለማረጋገጥ ። ቀጠሉ "እና ፎሊስ ይህን ማስቀጠል አልቻለም።እንዲያውም እኛ እውስ ብለን ስንል ወንጀል ነው ይሉናል።እነሱ ተጠርጣሪ ብለው ሲያስሩ ምንም።ማህበረሰባዊ ስሪታችንን በማስተካከል ስም እየሸረፉብን ነው። ደሞ ልንገርህ ልጄ አንዱ ችግር ፎሊስ ቋሚ ተቋም የለውም።በሐይለ ስላሴ ነጭ ለባሽ፣ በደርግ አቢወት ጠባቂ ባሁኑ ደግሞ ባለብዙ ስም ነው።ስለዚ ምን ሆነ የመንግስትን እስትንፋስ ጠብቆ የሚንቀሳቀስ።የኛን ደግሞ ተመልከት እስቲ፤ ✍️ይች ባንዲራ የመቼ ናት? የድሮ የአባት የቆየች ✍️ይኸ ሰው የመቼ ነው?ቀጣይ የሚቀጥል ከድሮም በሽግግር የመጣ ✍️ይኸ ስሪ የመቼ ነው? የቆየ የአባት።የምትቀበለው፣ የምታስቀጥለው እንጂ በመንግስት ለውጥ የማትሽረው ነው። እና ምን መሠለህ የመንግስት የናንተ መዋቅር እዚህ አለ። በየጊዜዉ የተለያየ።የኛ ግን ተመሳሳይ።እኔ በ80 አመቴ ሁሌም እዚህ ነኝ ።አሰራሩ አልተለዋወጠም። ስሪ ሰርተናል።እናንተ ግን በየጊዜው........ብለው ዝም አሉ።መምሸቱ እና እሳቸው ቤት ማደሬን ወደድኩት።ምናልባትም ሰው እሳቸው ቤት እንዳድር የፈለገ እንድመከር ፈልጎ ይሆንን? ለመንግስት መልዕክት እንዳደርስ ተፈልጎ ይሆንን?አላውቅም። ለማንኛውም አዳሬን በተመለከተ ገብስ እንጀራ በእርጎ፥በስጋ ወጥ በልቼ ፤ ንፍር ወተት ጠጥቼ በጠፍር አልጋ ተኝቼ ተረጋግቼ አድሬ ጠዋት ወደ ስራየ ተመለስኩ። የሚሰማችሁን ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
ታሪክ ማወቅ በጣም ከመፈንደቅም ሆነ ከመደንገጥ ይታደጋል። የዛሬዋ ቅምጥል ከተማ ፓሪስ በ1780ዎቹ "ሲኦል"ነበረች።ያኔ እንደ እኛ የሞት አቃቂር መታደም የፈረንሳዊያን እጣ ፈንታ ይመስል ነበር። ፈረንሳይ "ሽብር(Terror)"የሚለውን ቃል ለዓለም የሰጠች አስቀያሚ አገር ነበረች። በዚያው ሰሞን በዚያች አገር አብርሆት(Enlightenment) እየፈካ መጣ። ታላላቆቹ ፈላስፎቿ(ቮልቴር፣ዲድሮት፣ሞንትስኩና ሩሶ) በጨለማው ዘመን የሚያበሩ የአብርሆት ከዋከብት ሆኑ። ስለዛሬዋ ፈረንሳይና ፓሪስ ምንም አልልም። ይልቅ ኢትዮጵያ "አብርሆት"የሚባል ቤተ መፅሐፍት በመዲናዋ አዲስ አበባ እየገነባች ነው። መራሂ መንግስቷ ሲበዛ አንባቢ መሆኑን አንብበናል።"ሰውየው"በተሰኘ የእሱን ሕይወት በሚተርክ መፅሐፍ ላይ"__መፅሐፍ ስረቁ"ሳይቀር ይላል። ተወደደም ተጠላም ይህ ሰው ከማይምነት ጋር ጦርነት የገጠመ ይመስላል። የፈሊጥ(Politics) አንጃችን ምንም ይሁን ምንም እንዲህ ያሉ ሸጋ ተግባራትን ብናደንቅ ምን ይለናል? የሚሰማችሁን ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
ቼ ጉቬራ (ጋሽ ስብሃት ገብረ እግዚያብሔር በ"እነሆ ጀግና"ገፆች ላይ ፃፈው፤በላይሁን ፍስሃ[ጎራ ቤል] በእዚህ ቤት ተረከው) ቼ____ 👉"ለሰው ፍቅር ሲል ሰውን የሚገድለው ቆራጥ!" 👉ነፃነትን ከእናት አገሩ ባሻገር ሽቶ የተዋጋ የሃቅ አርማ_የዐለም ዜጋ! 👉በጋሽ ስብሃት ብዕር ከግብፃዊው ፃድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ(አቡየ) ጋር የተነፃፀረ ነፃ አውጭ የሚሰማችሁን ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
አመስጋኝ ትውልድ | በታመነ መንግስቴ የቀጠለ--- የምዕተ ዓመቱን የኢትዮጵያ ትውልድና ጠባይ በተመለከተ የጀመርነው ጨዋታ ቀጥሏል።ጠዋት የነ #ደባልቄን፣#ድጋፍሰጭን ትውልድ መለያዎች ተመልክተን ዛሬ በ#አብዮተኛው ትውልድ ተንደርድረን የኔና የእናንተው #አመስጋኝ ትውልድ ላይ እንገታለን---አብረን እንታደም። ሐ.የአብዮቱ ትውልድ፦ ይሄ ትውልድ በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያ በሆነውና 3ሺህ ዓመት መሠረት ይዞ የኖረውን የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ(ለመጨረሻ ጊዜ ላይሆን ይችላል!-ተመልሶ ቢመጣስ!?---ጊዜ ይዳኘን።) መንግሎ የጣለ፣ንጉሱ(ቀኃሥ) በራሳቸው ገንዘብና ቤተ መንግስት ባስተማሯቸው የምዕራቡ ዓለም ቀለም ቀማሽ ተማሪዎች"የመሬት ላራሹ" ጩኸት የተበረታታ፣ሁለት ክንፍ ፈጥሮ በባለ ቀለም(ቀይና ነጭ) ሽብር ርስ በርሱ የተፋጀ ስሜታዊ የትውልድ ጅረት ነው።የዘመኑ ከዋከብት በዓሉ ግርማና ዋለልኝ መኮነን ይሆናሉ። ዋለልኝ መኮነንን በቅርበት እናውቀዋለን የሚሉ በዘመኑ ያነባቸው በነበሩ የጋርዮሽ(Communism) ቀመስ መፅሐፍት የተማረከና የውድቀት ትንቢቱ በተቃረበው የቀኃሥ መንግስት አገዛዝ ላይ የበሸቀ ወጣት ተማሪ ነበር።የመጀመሪያዋን "የብሄሮች እከልነት"የምትል ሃረግና ዛሬም ድረስ ብዙዎችን የምታጨቃጭቀዋን"ራስ በራስ የማስተዳደር'እስከ መገንጠል'" የተሰኘች በጥባጭ ቃል ከሌኒን መፅሃፍ ላይ ቀንጭቦ በጦማረ ህዝብ(ጋዜጣ) ላይ ያስነበበ፣ማርታ ከምትባል ጓደኛው ጋር ጢያራ ሊጠልፍ ሲሞክር በጃንሆይ ሰዎች ተጠልፎ መቃብሩ የተማሰ_አብዮተኛ ነው። በዓሉ ግርማ ማለት በወጣትነቱ ጀምሮ በአብዮቱ ዜማ የተማረከ፣ግን ቀን እስኪወጣ የተዳፈነ።ከአብዮቱ ጋር አብሮ በጥበብ ስራዎቹ የፈነዳ።"የቀይ ኮኮብ ጥሪ"፣"የህሊና ደወል"፣"ሀዲስ"፣"ደራሲው" እያለ በቀጥታ አብዮቱን ያንቆለጳጰሰ፣በነዚህ አብዮት ቀመስ መፅሐፍቱ ገፆች ውስጥ ሂሩት፣አይናለም፣ሰብለ የተሰኙ ጠያይም ሴቶችን እየሳለ ስራውን በኪነት ያሰማመረ፣በመጨረሻ"ኦሮማይ" ብሎ ለአብዮቱ ታማኝነቱን በአደባባይ በማሳየት የሃቅ መስዋዕት የሆነ-አብዮተኛ ነበር። መ.ደስታ ጠሪ፦ እኛን በከፊል ቀዳሚዎቻችንን በሙሉ የሚያካትት ትውልድ ነው።ትውልዱ እንደስሙ ደስታ በሌለበት ደስታን ያነፈንፋል፤እያረረ ይስቃል።ጎሜ(ስውር ንግግር) ያዘወትራል።ወሲብ ነክ ቃላትን በአደባባይ ይዘራል።የትውልዱ ዋንኛ አብነቶች በዕውቀቱ ስዩምና ይስማዕከ ወርቁ ሆነው እነ እንዳለ ጌታ ከበደንም ይጨምራል። በዕውቀቱ ስዩም ማለት በሳቅ መሃል እውቀት ነው።ታሪክን በደረቁ ሳይሆን አጣፍጦ ያጫውታል።ዱኛን(ፖለቲካን) ገደም እያረገ መሪዎቻችንን ይወጋጋል።ሃፍረተ ስጋን በልጅነታችን በምንጠራበት አኳሗን ፅፎ አንባቢውን ያሳፍራል-እንደ እውነቱ የእሱን ፅሁፍ በህፃናት ፊት ጮክ ብሎ ከማንበብ አስቀድሞ መመርመርን ግድ ይላል-በመጠኑ ድፍረትን ከነ ስብሃት ገ/እግዚያብሔርና ፈረንሳዊያን ደራሲዎች የተዋሰው ይመስላል፣የትውልዱ ጨዋታ ወዳድነት ያስገደደው---ደስታ ጠሪም ሊሆን ይችላል። ይስማዕከ ወርቁማ ደራሲነትን ይዞት ተወልዷል።ደስታ ጠሪነቱ የተቃራኒ ፆታዎችን በተቀደሱት የጣና ገዳማት እስከማሳሳም ይደርሳል(እዚህ ላይ የመኪና አደጋ ደረሰብኝ ብሎ የታመመ ሰሞን አድናቂዎቹ እሱ በዴርቶጋዳ የፈጠራቸውን መቼቶች ለመጎብኘት በገዳማቱ አካባቢ በተገኙ ጊዜ ጋዜጠኞች የገዳማቱን ሰዎች ስለ ይስማዕከ የሚሰማቸውን ሲጠይቋቸው ቁጣ አዘል አስተያየት ሲሰጡ በአማራ ሬዲዮ መስማቴ ትዝ ይለኛል-አፃፃፉ ሳያበሳጫቸው አልቀረም)፣ይስሜ ግን የወጣቱን ልብ በሚወደው ነገር እያጓጓ በፈጣን የመቼት ቅየራው ልቦለዱን ሃቅ ያስመስለዋል-ብቻ በየ ስራው ደስታ ጠሪነቱን ያጎላዋል። ሠ.አመስጋኙ ትውልድ፦ የዛሬና የነገው ትውልድ ይሰኛል።እኔንና እናንተን ይዟል።ቂም በቀል አያውቅም።ለተደረገለት ነገር ሁሉ ያመሰግናል።በአገራዊ እውቀት ይመካል።በማንም አይፈርድም።በታሪክ ይማራል እንጅ አይጣላም። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በህዝብ እንደራሲዎች ምክር ቤት ከ36 ጊዜ በላይ ሲጠራ ከሰማ ወዲህ የጠሩት ሰውየ ቢተውት እንኳን ራሱ እንደ ገደል ማሚቶ እያስተጋባ ለሚመጣው ትውልድያቀብላል። ህሊና ደሳለኝ የምትሰኝን ደመ ሞቃት ገጣሚት ግጥም እንደዘፈን ደጋግሞ ያጣጥማል፣ዳዊት ፅጌ የተባለን ሳተና ዘፋኝ ከልጅነቱ አጨብጭቦ አሳድጎ ለዘፈን ጥቅል (አልበም) አድርሶ ተደምሞበታል። ዓባይ የሚባልን ገነትን እንዲያጠጣ የታዘዘ ወንዝ ራሱ ከከረሚላ ቀንሶ እያዋጣ ገድቦ አገሩን በብርሃን ማሳውን በጎመን ያደምቃል። በትንንሽ ነገሮች(ጎሳ፣ብሔር፣ቋንቋ፣ድንበር) መጋጨትን እጅጉን ይንቃል።በማህበራዊ መገናኛው ይችን ንፁህ አገር ህልውናቸውን ከፍለው ለሰጡት ምስጋናውን ያቀርባል።ቢያንስ በዓመት አንድ ቀን እነሱን የሚያመሰግንበት ታላቅ ቀን መርጦ ያከብራቸዋል። ማስታወሻ በየትውልዱ ጥበብን እንደ መከፋፈያ መምረጣችን እሷ የሁኔታዎች ነፀብራቅ ስለሆነች ነው።ደራሲያንን ማስቀደማችን ደግሞ የኪነ ጥበብ ምንጩ ድርሰት ስለሚመስለን ነው።የኛው ዘመን ጠቢባን ለአብነት ዳዊት ፅጌና ህሊና ደሳለኝ የተመረጡበት ምክንያት በትውልዱ የጋራ መሰባሰቢያ በሆነው የማህበራዊ መገናኛ ማለትም የፊትገፅ(Face book) እና የእናንተ መግቢያ(You tube) መነጋገሪያዎች በመሆን ቀዳሚነቱን ስለያዙ ነው። ይህ የምስጋና ትውልድ አገሩን በአወንታዊ ዓይን ብቻ ይመለከታታል። በጉዳዩ ላይ በቀጣይ ጊዚያት በዝርዝር የምንነጋገር ሆኖ ለጊዜው ከሃሳቡ ባለቤት መምህር ሀብታሙ አለማየሁ ጋር ዘጋቢው ታመነ መንግስቴ በምስጋና እሰናበታለሁ። የሚሰማችሁን ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
አመስጋኝ ትውልድ | በታመነ መንግስቴ (የዛሬ ዓመት ገደማ የተፃፈ) ሀሳቡ የወጣቱ መምህር ሃብታሙ አለማየሁ ነው።እሱ መምህርነትን ለፈጣሪው ፀልዮ እንዳገኘው አጫውቶኛል።አሁን በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ ሁለተኛውን ድግሪ(የአማርኛ አቻዋ ጠፋኝ) እየተማረ እዚያው የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪ ወጣቶችን ያስተምራል። መምህሩ እንደሚለው የኔና የናንተ ትውልድ የራሱ ቀለም ያስፈልገዋል።ያሳለፈነውን ምዕተ ዓመት(100ዓመት) በትውልድ እርከን ብንከፋፍለው አሁን ያለነውን ጨምሮ አምስት ትውልድን አቅፏል።ጋሽ ሃብታሙ በሄደበት መከፋፈያ መስመር ለመመስረት ኪነ ጥበብን እነመረኮዛለን።በትውልዶች ጅረት አብረን እንታደም---እስከኛው የምስጋና ትውልድ ድረስ ተከተሉኝ! ሀ.ደባልቄ ትውልድ፦ ዳግማዊ ምኒልክን ተከትለው በነፃዋ ኢትዮጵያ ላይ የራሳቸውን አመክንዮ ለበስ ትውልድ የፈጠሩት የነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝና ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ጅረት አንዱ ነው።በዘመኑ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ "ስልጣኔ" ጋር ገና እየተዋወቀች ነበርና እነዚህ ፊታዊራሪ ደራሲና ጠቢባን ድርሻቸው ጉልህ ነበር። ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ በኢትዮጵያ ቀዳሚው የምጣኔ ሃብት ምሁር ሊያሰኛቸው የሚገባን ስራ ሰርተው ሁለት ጠቃሚና ትውልድ ተሻጋሪ መፅሃፍትን ፅፈው፣ቤተ መንግስት ውስጥ የነበራቸውን ተቀባይነት በሚያሳይ መልኩ በልጅ ኢያሱ መፈንቅለ መንግስት ላይ የውሸት ወሬ በመንዛት ሳይቀር በጉልህ ተሳትፈው፣"አበጀህ" ተብለው ስልጣንን ለብልጣብልጡ ተፈሪ መኮነን የሗላው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንዲመች አድርገው አልፈዋል።የምዕራቡን ስልጣኔ ከእኛው ጋር እንዲጣመር ይታትሩ ነበር_ደባልቄ። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሚያሰኟቸው ሁለት ነገሮች ላይ ተሳትፈዋል።ዘፈንና መንጃ ፈቃድ።ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አሃዱ ብለው ወደ ኢትዮጵያ ያመጧትን መኪና ቀድመው የነዷት ኢትዮጵያዊ ራሳቸው ንጉሱ ናቸው።መንጃ ፈቃድ አውጥተው ያሽከረከሩበት ግን ተሰማ እሸቴ።ነጋድራሱ የመጀመሪያውን በሸክላ የተቀረፀ ሙዚቃ የዘፈኑት ኢትዮጵያዊም ናቸው። ቅኔያም እንደነበሩም ይነገራል_ደባልቄ። ለ.ድጋፍ ሰጭ፦ የዚህ ትውልድ ጠባይ ደጋፊነት ነው።በአብዛኛው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስራዎች ይደመማል፤እሳቸው ያሉትን ቃል ሁሉ እንደ ቅዱስ ይቆጥራል።ንጉሱ ካሉ መፅሐፍ ይፅፋል፣በዓሉ ግርማ "ሀዲስ" የተሰኘ ክሽን ልቦለዱ ላይ እንደፃፈው ይሄ ትውልድ "ቀኃሥ ቤተ ክርስቲያን ተሳለሙ" ብሎ ዜና ይዘግባል።መዘገቡ ነውር ሆኖ ሳይሆን የወሎን ህዝብ ረሃብ ደብቆ መሆኑ ድጋፍ ሰጭነቱን ያስመሰክርበታል።የትውልዱ መሪዎች እነ አቶከበደ ሚካኤልና ብላቴን ጌታ ህሩይወልደ ሥላሴ እንደነበሩ ታሪክ በደማቁ ያትታል። የሗላው ክቡር ሊቀ ምሁራን ከበደ ሚካኤል የጃንሆይ ሁለተኛው ፀሃፈ ትዕዛዝ ሊባሉ የሚችሉና ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ምግባርን ያጎለበቱ(ያስተማሩ ላለማለት-ምክንያቱም የኢትዮጵያዊያን ምግባር ከዚያ በፊት ቢያንስ 5ሺህ ዓመታትን በፈጀ መሠረት ላይ የቆመ ስለነበረ)፣በንጉሱ ቀኃሥ አማካሪነት ብዙ ተረቶችን የፃፉ፣የመማሪያ መፅሐፍትን ያዘጋጁ፣"ጃፓን እንዴት እንደሰለጠነች" ሊያሳዩ የሞከሩ፣የመጀመሪያውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኪነ ጥበብ ሽልማት የተሸለሙና ከንጉሱ ጋር በነበራቸው የበዛ ግንኙነት በአቻዎቻቸው የሚታሙ_ድጋፍ ሰጭ ነበሩ። ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ሥላሴ ደግሞ በዚያው በቤተ መንግስት ከቀኃሥ ጋር የነበሩ፣ጃንሆይ በማይጨው ጦርነት ተሸንፈው ለንደን ሊሄዱ ሲሉ በተነሳ "ንጉሱ አገር ውስጥ ሆነው ጣሊያንን ይታገሉ" እና" ከአገር ውጭ ሆነው ትግሉን ይቀጥሉ" ክርክር ስደቱን ደግፈው አብረው የተጓዙ፣በዚያው በስደት አገር እንግሊዝ የሞቱ፣ለቀኃሥ የንግስና ዓመት መታሰቢያ ቀን ዋዜማ በሚል የታሪክ መፅሃፍ ፅፈው ርዕሱን "ዋዜማ" ያሉ_ድጋፍ ሰጭ ነበሩ። ቀጣዩን #አብዮተኛ የተሰኘ ትውልድና ከዋከብቱን ይዠ እመለሳለሁ። አመስጋኙ ትውልድ የእኛው ነው።እስከዚያ የሚሰማችሁን ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ እኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ። የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Mostrar todo...
ሰው ሁሉ ቅኔ ነው፤ራሱን ይቀኛል የእኔን ትቸዋለሁ፤የአንተ ይበቃኛል። አያ ሙሉጌታ፦ ተቀድሰህ ንገስ፤በልባችን ዙፋን ሁሉ እየተንጫጫ፤መሪው ገዥው ጠፋን። ታመነ መንግስቴ ለባለ ቅኔው ሙሉጌታ ተስፋየ
Mostrar todo...