cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን / Werabe Communication

Publicaciones publicitarias
2 582
Suscriptores
-124 horas
+107 días
+2730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በከተማው ዓመታዊ የግብር አሰባሰብ ስራ እንደቀጠለ ነው! ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሐምሌ 3/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] በወራቤ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓመታዊ የግብር ክፍያ እና የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት እየተከናወነ ይገኛል። በከተማ አስተዳደሩ የአልከሶ ማዕከልን ጨምሮ በአምስት ጊዜያዊ የግብር መክፈያ ማዕከላት ነው የታክስ አሰባሰብ እና የንግድ ፈቃድ እድሳት ስራው እየተከናወነ የሚገኘው። በመሆኑም ባሉ አጭር ጊዜያት ውስጥ ማህበረሰቡ ግብርን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ተቋም እና የከተማው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። #ግብር_ለሀገር_ክብር🇪🇹
Mostrar todo...
👍 3
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  ሀገራዊ የቁርዓን ውድድር ሊያካሂድ መሆኑን ገለጸ! ~~~~ ሐምሌ 3/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሞሮኮው ንጉስ ሙሐመድ  ስድተኛ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ሀገራዊ የቁርዓን ዉድድር ዓርብ ሐምሌ 5/2016 (ሙሐረም 6/1446 ዓ.ሒ) በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚያካሂድ በጠቅላይ ምክር  ቤቱ  የዓሊሞች ጉባዔ ፅ/ቤት ኃላፊ  ሼይኽ ሙሐመድ ዘይን ዛኽረዲን ተናግረዋል። የሞሮኮዉ ንጉሥ ሙሐመድ 6ተኛ ፋውንዴሽን ዋና ፀሐፊ የዶክተር ሲዲ ሙሐመድ ሪፍቂ አማካሪ በሆኑት ዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን የተመራ የልዑካን ቡድን የቁርኣን ውድድር ለመዳኘት አዲስ አበባ ገብተዋል። የልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርት ና ማህበራዊ አገልግሎቶ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ዶክተር  አብደላ  ከድር እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል። በዑስታዝ ዑስማን ሰ ቀሊ ሑሴን የተመራው የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ የገባው፣ የፊታችን ጁምዓ ሐምሌ 5፣ 2016 ዓ.ል. (ሙሐረም 6፣ 1446 ዓ.ሒ) በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የቁርኣን ዉድድርን ከሀገራችን ዓሊሞች ጋር በጋራ ለመዳኘት ነው።   የፊታችን ጁምዓ የሚጠናቀቀው ሀገራዊ የቁርኣን ዉድድር በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዓሊሞች ጉባዔ ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲኾን፣ ለአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የደረሱት ሐፊዞች በክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤቶች በተዘጋጁ ውድድሮች ተሳትፈው ያሸነፉ መኾናቸውን ዶክተር አብደላ ተናግረዋል። በስካይላይት ሆቴል የሚካሄደው ውድድር በቀጣይ ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚለዩበት መሆኑ ዉድድሩን በጉጉት የሚጠበቅ እንደሚያደርገው ዶክተር አብደላ ተናግረዋል። ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በቁርኣን ዉድድር የሀገራችንን ስም በዓለምአቀፍ ደረጃ ያስጠሩ ወጣቶች እንዳሉ የጠቀሱት ዶክተር አብደላ በዚህ ዉድድር አሸናፊ የሚኾኑ ሐፊዞችም በዓለምአቀፍ የቁርኣን ውድድር መድረክ ሀገራቸውን ወክለው እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል።መረጃው የኢት/እ/ጉ/ጠ/ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ነው!
Mostrar todo...
👍 4 1
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 31ሺ 283 ተማሪዎች የ12 ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው! ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሐምሌ 3/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 31ሺ 283 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12 ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ፈተናውን በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት በወራቤ፣ወልቂጤ፣ ዋቻሞ ዋናው ግቢና ዱራሜ ካምፓስ እንዲሁም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ነው እየተፈኑ የሚገኙት። ከእነዚህ ውስጥ በክልሉ ለመጀመርያ ጊዜ 368 የሚሆኑ ተማሪዎች በኦንላይን የሚፈተኑ ናቸው። ፈተናው በሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን አቶ አንተነህ መናገራቸውን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ለዚህም ኩረጃን በማስቀረት በራሱ የሚተማመን ተማሪ ለማፍራት የተደረገው ቅድመ ዝግጅት አስተዋጽኦ እንዳለው የጠቆሙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ የትምህርት ጥራትና ፈተና አስተዳደርና ተማሪውን በአካዳሚና በስነ ልቦና ዝግጁ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ውጤት እያመጡ መሆኑን ጠቁመዋል።
Mostrar todo...
👍 1
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመሰረተ ልማት ክላስተር የአባላት ኮንፈረንስ ተጀመረ ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ በኮንፍራንሱ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ሶርሞሎ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፣ ክብርት ወ/ሮ ሙኒቴ ሙንዲኖ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ፣ የተከበሩ አቶ ዳዊት ኃይሉ የመሰረተ ልማት ክላስተር የመሰረታዊ ድርጅት ስብሳቢ እንዲሁም የመሰረታዊ ድርጅት አመራሮች እና አባላት በተሟላ መልኩ በተገኙበት ውይይቱ እየተደረገ ይገኛል ። በኮንፍራንሱ የ2016 በጀት ዓመት የመሰረታዊ ድርጅት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ይቀርባል፣የ2017ዓ.ም እቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል እንዲህም የክላስተሩ እጩ አባላትን ወደ ሙሉ አባል ማሸጋገርና በኮንፈረንሱ ማፅደቅ ይሆናል። መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመሰረተ ልማት ክላስተር ህዝብ ግንኝነት ነው።
Mostrar todo...
02:05
Video unavailableShow in Telegram
የወራቤ ከተማ የግብር አሰባሰብ ሥራ በከፊሉ! ሐምሌ 2/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን]
Mostrar todo...
84.11 MB
ግብር ከእኛ ወደ እኛ የሚከፈል በመሆኑ ግብርን በወቅቱ በመክፈላችን ደስተኛ ነን -  የወራቤ ከተማ ግብር ከፋዮች! ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሐምሌ 2/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] ግብር መንግስት ህዝቡ ለሚፈልጋቸዉ መሰረተ ልማቶች የሚዉል እና ከእኛ ወደ እኛ የሚመለስ ነው ሲሉ የወራቤ ከተማ ግብር ከፋዮች ተናግረዋል። በዚህም ግብርን በወቅቱ በመክፈላቸዉ እንደተደሰቱ ገልጸዋል። ትምህርት፣ ጤና፣ መንገድ እና ሌሎችንም ህዝቡ የሚናፍቃቸዉ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የመንግስት አቅም አንዱ ከዜጎች በሚሰበሰብ ግብር መሆኑ ይታወቃል። ከሀምሌ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዘንድሮዉ የደረጃ "ሐ" ግብር ክፍያ እና የንግድ ፈቃድ እድሳት ዛሬም ቀጥሏል። በከተማ አስተዳደሩ በአምስት ጊዜያዊ የመክፈያ ጣቢያዎች በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ ነጋዴዎች ግብርን በመክፈል የዜግነት ግዴታቸዉን እየተወጡ ይገኛሉ። በዚህ ወቅትም የከተማ አስተዳደሩ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያነጋገራቸው ግብር ከፋዮች በሰጡት አስተያየት ግብር እኛዉ ለምንፈልገዉ ልማት ማሳለጫ የሚዉል በመሆኑ በወቅቱና በጊዜ በመክፈል ሀገራዊ ሃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል። ያለዉ የግብር መክፈያ ወቅት አጭር በመሆኑ ፈጥነዉ ክፍያዎትን በመፈጸም የልማቱ አጋር ይሁኑ መልዕክታችን ነዉ።
Mostrar todo...
👍 1
07:04
Video unavailableShow in Telegram
የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች በሰላምና አንድነት ሩጫ ከተናገሩት!
Mostrar todo...
117.33 MB
02:56
Video unavailableShow in Telegram
የአሊፍ አካዳሚ የ2016 ዩኬጂ ተማሪዎች ምረቃ መርሃ-ግብር በከፊሉ!
Mostrar todo...
93.74 MB
👍 6
#ነገ_ሐምሌ_አንድ_ነው! ~~~~~~~~~~~~~ እንኳን ለ2016 የግብር ዘመን በሰላም አደረሳችሁ! ወርሃ ሐምሌ የመጀመሪያው ቀን ዓመታዊ ግብራችንን አሀዱ ብለን መክፈል የምንጀምርበት ዕለት ነውና የነገ ሰው ይበለን። በድጋሚ እንኳን ለ2016 ዓመታዊ የግብር መክፈያ ቀን አደረሳችሁ! ሰኔ 30/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን]
Mostrar todo...
👎 4
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.