cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

HollyProductovab

This channel is aimed to share any types of holly productes that throughly builds ones spritual personalty and wellbeings!! It may contain #poems #motivational advices #songs #and some other issues that is considered to be constructive and important.

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
153
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Let us keep talking all our #feelings with #God!! እስቲ እናዉራ እየፈረደ ሳይሆን እየማረ እያቋረጠ ሳይሆን እያስጨረሰ ከሚሰማንና እንደየሁኔታችን የመሰለውን ሳይሆን ትክክለኘውን መፍትሔ ከሚሰጠን ከ ልብ አምላክ ከእየሱስ ጋራ!!!
Mostrar todo...
ትለኛለህ ?ከቤቴ ስትመጣ ?እየኝ ትለኛለህ ?ድንኳኔም ስትገባ ?ስማኝ ትለኛለህ ጥሪህን አክብሬ ላይህ ስመጣ ግን ከቦታውም የለህ!!! By Ab
Mostrar todo...
ኤሊዬ ኤሊዬ የኔ ቀርፋፋ ጠበኩሽ ብዙ ቀን በተስፋ እንደው መች ይሁን ምትደርሽ ጭር ብሎ የለም ወይ ቤትሽ
Mostrar todo...
🦅ከፍ ብለህ እይ🦅 ከፍ ስትል ብዙ መጋረጃወችን አሻግረህ ታያለህ ከፍ ስትል ብዙ ሚስጥሮችን ትተነትናለሕ ከፍ ስትል አመለካከትህን በአዲስ መልክ ትቀርፃለህ ከፍ ስትል ብዙ ነገሮችን ለካ አንዲናቸው ትላለህ ከፍ ስትል የመሠለህ ነገር እንደመሰለህ እንዳልነበር ተገነዘባለህ ከፍ ስትል አንጋጠህ ምታየውን ረግጠህ ትቆማለህ ከፍ ስትል ዝቅ ብለህ ዝግ ነው ያልከውን ብዙ ክፍት መንገድ ትቀይሣለህ ከፍ ስትል ከተራራ ጋር ፊት ለፊት ትፋጠጣለህ ከፍ ስትል ከፍ ባለ ነፋስ ትነፍሳለህ ከፍ ስትል ከፍ ባለው አምላክ ፊት ዝቅ ትላለህ። ❤️መልካም ምሽት💙 ከ አቤኒ ሣሚ
Mostrar todo...
💐💐ወደ እግዚያብሄር ጉባኤ በማስተዋል እንግባ💐💐💐 ✍እሁድ ነው ።የዝማሬው ፣የአምልኮው ፣የምስጋናው ድምፅ ገና ከበር ያስተጋባል ።ትንሽ አርፍጄ ነበር የመጣሁት ።አዪ ሳላመልክ ኤ....ጭ በርግጥ ኳየርም ስላለ ከነሱ ጋር አመልካለሁ ። ስገባ እያንዳንዱ ሠው በመንፈስ ተይዞ እያመለከ ነበር ።ሁሉን ለመታዘብ እንዲመቸኝ ይመስል ከፀሎት ቤቱ የመጨረሻ ወንበር ጥግ ላይ ተንበረኩ ።እውነት ለመናገር ያው ሲገባ መፀለይ ደንቡ ስለሆነ ነው እንጂ ምንም የምፀልየው ነገር አልነበረኝም ።ልነሣ አሠብኩና አሁን ከመንበርከኬ ስነሣ ሰው ምን ይለኛል ብዬ ትንሽ ቆየሁ ። ኧረ ጉድ ለካ ኳየር ነበር የዘመረው አ...ዪዪ በጊዜ የወጣሁ መስሎኝ ነበር ።ጠዋት ቃና ላይ የ 3 ሠዓቱን ፊልም አይቼ ነበር የወጣሁት ።በቅርብ የገዛሁት አዲሷን ስልኬን ከቦርሣዬ አወጣሁና ሠዓቴን ተመለከትኩ ።5:48 ይላል አይ ምንም አይልም ደርሻለሁ ።"አሁን ወደ እግዚያብሄር ቃል እንሄዳለን"ተባለ ና ሠባኪው ወደ መሠውያ ወጣ ።አመሠገኑ ፣ፀለዩ ፣ አብረን ተቀመጥን ።ካጠገቤ የነበረችው አንዲት እህት "አቤቱ ቃልህን በባሪያህ አንደበት አኑር " ።ቀና ብዬ ተመለከትኳት ።ጉድ ፈላ እያለቀሠች ነው ። ውይ ምን ሆና ይሆን ከፍቷት ይሆናል አልኩኝ ለራሴ ።ሆሆሆ አሁን ምን የሚያስለቅስ ነገር አለ ።እኔ የማለቅሠው ፊልም ሳይ እሱንም ህንድ ፊልም ከሆነ ።በህይወቴ እንደ mother india አይነት ፊልም አይቼ አላውቅም ።የኛ ሀገሮችም ይሞክራሉ ።ግን አማርኛ ፊልም ሲጀመር እንዴት እንደሚያልቅ መገመት ቀላል ነው ።የሀገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ በጣም ገና ።"ሀሌሉያ "የሚል የአንድ እህት ድምፅ ከሀሣቤ መለሠኝ ።ኦኦኦ ለካ እየተሠበከ ነው ።ሰባኪው በሀይል "እግዚያብሄር አይዘበትበትም "አለ ። ሆሆ ምን የሚያስጮህ ነገር አለ ።ሁሉም በፀጥታ አየሠማ ነው ።እንዴ ካጠገቤ የተቀመጠችው እህት አሁንም እያለቀሠች ነው ። ጉዴ ፈላ!! አይ በቃ ወይ ወላጆች ወይ የቅርብ ሠው ሞቶባት ይሆናል እንጂ ሠውማ በጤናው እንዲህ አያለቅስም ።ሠባኪው አሁንም አየሰበከ ነው ።የሚሠበከውን ለመስማት ሞከርኩ ።"የኛ ጌታ ተራሮች የሚጤሱለት ፣ባህር ክብሩን አይታ የሸሸች ፣ውሀን እንደግርግዳ የሚያደርግ ፣በውሀ ላይ የሚራመድ ታላቅ አምላክ ነው አይዘበትበትም "።ህዝቡ ሁሉ በሀይል አመሠገነ ።ያማቸዋል እንዴ!!ያለውን በትክክል ቢሠሙ ባልተንጫጩ ።አይ ሀበሻ በቃ ምን እንደተባለ ሣያውቅ በቃ መጮህ ይወዳል ።ተናደድኩ ከምር ብሽቅ አልኩ ።እርግጥ ነው ተራሮች ይጤሣሉ ግን እሣተጎመራ ሲኖር ነው ።ባህር ሸሸች አለ ፣ባህር ሸሸች የሚባለው እኮ ልክ አንደ ጣና ና አዋሽ በሙቀት መጨመር ሠበብ በተፈጠረ የዝናብ እጥረት ነው ።በጣም የገረመኝ ግን በዉሀ ላይ የሚራመድ ያለው ነው ። ቆይ ስንት ምሁራን የተጠበቡበት physics ገደል ገባ?ሆሆ አይ ሀበሻ ምንም friction በሌለበት ውሀ ላይ መራመድ ይቻላል ሲባል የሚጮህ ህዝብ እኮ ነው ።ሲገርም ስብከት አለቀ ። ምንም ሣልሠማ አዪዪዪ ።ሰው ሁሉ ሲቆም አብሬ ቆምኩ ።ሁሉም ማውራት ጀመረ ። ውይ የኔ ነገር ለካ አባታችን ሆይ እየተባለ ነው ።".......እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል..."ከዚ በኀላ ምን ነበር!!!""አሜን""ሀሉም ሲል አብሬ አልኩ ። ሠው ሁሉ ሠላም መባባል ሲጀምር ቦርሣዬንና የማላምናትን አዲሷን ስልኬን ይዤ ውልቅ!!! አለቀ💐💐💐💐 ✍ወንድም ቤተክርስቲያን ምትሄደው ለምንድነው ?ወግ ለማድረስ ፣ ለትዝብት ፣ ወይስ ትልቁን የክብር ንጉስ ፍለጋ ። ✍እግዚያብሄር ጉባኤን ሲሰበስብ አብሮ በረከቱን ይልካልና ወደ ታላቁ ወደ እግዚያብሄር ጉባኤ በማስተዋል እንግባ!!!! ለባለታሪኳ መፀለይ ለምትፈልጉ ባለታሪኳ የዚህ ዘመን ወጣት ምሣሌ ናት ። 💐💐 ተባረኩልኝ💐💐💐
Mostrar todo...
🙊👵ብታሣየኝ ምነው?🙊👵 ፈቃድህን ፈፅመህ በሂወቴ ላይ ደስ የሚያሰኝህን ያንተን ክብር ሳይ ይሔ ነው ደስታዬ የኔማ ትልቁ በፈቃድህ ማጌጥ መዋብ ማብረቅረቁ ቢጫንም በላዬ የሂወት ፈተና እኔን ወደ ሙላት ለማድረስ ነውና የፅድቅህ ተካፋይ እንድሆን ሊያቀርበኝ ስለሆነ ነው ሁሌ ፍቅርህ የሚርበኝ ይምጣ ያስጨንቀኝ ተጭኖ በላዬ ለመልካም ነውና የበዘው ስቃዬ እኔ ላንተ ስኖር ስትኖር አንተ ለኔ የዚያኔ ነው ውበት ሚኖረው ዘመኔ ክብሬ ክብርህ ይሁን ትርጉም እንዲኖረው ሰብሰብ ይበል ቀልቤ ጥሎክ የሚዞረው መጥገብ ልማድ ይሁን ክብርህን አይቼ ለፅድቅ ህያውነት ለሀጥያት ሞቼ ነብሴ እንዳላጎድልሽ አለምን አትርፌ ላምላክ ስራ ሲባል እጄን አጣጥፌ እንዳልኖር በፀፀት በሁዋለኘው ሂወት በልቅሶና ዋይታ ጥርስም በማፏጨት መኖር ላንተ ሲባል ሳላፈገፍግ እንድሔድ ወደፀጋው ወደሙላት ጥግ የራሴን አዝግሜ ያንተን እንዳፈጥነው ያየህልኝን ነገር ብታሳየኝ ምነው ። ✍አቤኒ ሳሚ 👇👇👇 @holyproductovab
Mostrar todo...
✋🤚 የታሸገ መዳፍ👊👊 ትናንት ስንገናኝ ስትመገብ ነበር ዛሬም ተጋጠምን ከዚያው እህል ክምር ለመኖር ሳትበላ ለመብላት የምትኖር ያንተስ ለየት ይላል የሂወትህ ቀመር የንፉግነት ጫፍ ራስ የመውደድ አፋፍ የቁጠባ ደጃፍ የታሸገ መዳፍ ተካፍሎ በመብላት በፍቅር መኖር ሲባል ከደምህ ጠብታ ቅናሽ ይመስልሀል ብቻህን ዘላለም የምትኖር ይመስል የምስኪኑን አንጀት በረሀብ ምታቆስል አንተ የስጋት ሰው የአለም አትራፊ የነብስህ አጉዳይ ነህ የሂወትህ ቀጣፊ ✍ አቤኒ ሣሚ 👇👇👇 @holyproductovab
Mostrar todo...
⏳ለአዕምሮአችን⌛️ መቀላጠፍ ና ጤንነት የሚረዱ 10ነጥቦች !!!! 1. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው ። በቫይረስ መጠቃት የለበትም ። ሁልጊዜ ሊጸዳ ይገባዋል፡፡ አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ - በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡ 2. አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል ። ያስወግዷቸው፡፡ 3. አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡ 4. አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡ 5. ጥሩ ምግቦች አእምሮ ስል እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ የአሳ ዘይትና ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በቀን በቀን ካገኘ ሥራ ማቀላጠፍ ያውቅበታል፡፡ በቂ ውኃ መጠጣት ለአእምሮ እንደ ግሪስ ያገለግላል፡፡ 6. አእምሮ በቫይረስ ይጠቃል፡፡ የአእምሮ ቫይረስ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? አሉታዊ አስተሳሰቦች፡፡ ምቀኝነት፣ ክፋት ማሰብ፣ በማይረቡ ነገሮች መጨነቅ አእምሮን ያውካሉ፡፡ ይህን ቫይረስ ለማጽዳት መልካም መልካሙን ማሰብ ብቻ ይበቃል፡፡ 7. ቁርስ አይዝለሉ፡፡ መኪናዎ ማለዳ ተነስተው እንደሚያሞቋት ሁሉ አእምሮዎንም በአሪፍ ቁርስ ያነቃቁት፡፡ ቀኑን ሙሉ በንቃት እንዲሰራ ጥሩ ቁርስ ያስፈልገዋል፡፡ 8. ተሸፋፍነው አይተኙ፡፡ አእምሮ እጅግ ብዙ መጠን ያለው ኦክሲጂን የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ሲታፈን ግራ ይገባዋል፡፡ መኪና የሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ ኢንደስተሪዎች፣ ብዙ ሲጋራ የሚጨስባቸው አካባቢዎችን ያስወግዱ፡፡ በተቃራኒው መናፈሻ፣ አረንጓዴ ተክሎች የሚበዙባቸው ሜዳማ ስፍራዎች የእግር ጉዞ ቢያደርጉ አእምሮ በጣም ያመሰግንዎታል፡፡ 9. የከሰል ጭስ ለአእምሮ መርዝ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ቤታቸውን በእጣንና በከሰል ጭስ ያፍናሉ፡፡ በነጋታው ኃይለኛ ራስ ምታት ያማቸዋል፡፡የከሰል ጭስ አእምሮን ሊገድለው ይችላልና ይጠንቀቁ፡፡ 10. ለእርስዎ የማያስደስትዎትን ነገር ለሰው ሲሉ ብቻ አያድርጉ፡፡ የማያምኑበትን ነገር በፍጹም አይተግብሩ፡፡ ወደፊት ለጸጸት የሚዳርግዎትን መልካም ያልሆነ ተግባር በድብቅም ቢሆን አይስሩ፡፡ ፀፀትና የሕሊና ወቀሳ ለአእምሮ መርዛማ ነገሮች ናቸው፡፡ ሙሰና፣ ከትዳርዎ ውጭ መማገጥ፣ በሰው ላይ ተንኮልና ሴራ መፈፀም አእምሮን እስር ቤት ውስጥ ማጎር ማለት ነው፡፡ አእምሮ ሰላሙን አጥቶ ሰላምዎን እንዳይነሳዎ መልካም መልካሙን ብቻ ያድርጉ፡፡ 11. መልካም ምክር ለክፉ ጊዜ ስንቅ ነው፡፡ ለሌሎች ሼር ቢያደርጉት የበለጠ ሰዎች እንዲወድዎት ያደርጋል፡፡ እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን! ምስጋናችን ከልብ ነው! @EthioBini @EthioBini
Mostrar todo...
የክረምት ከሰል እና የጤና መዘዙ በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ከሰል ምግብ ለማብሰል፣ ሙቀት ለማመንጨት እና ለተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ያገለግላል። ይሁን እንጂ ከሰል በጣም ብዙ የጤና መዘዝ እንዳለው ይታወቃል። በክረምት ከሚጋጥሙን አሳዛኝ የህክምና ክስተቶች ውስጥ ዋናው በከሰል ጭስ መታፈን፣ መመረዝ እና መሞት ነው። በክረምት ቤትን ለማሞቅ ከሰል አይጠቀሙ። ምንአልባትም መጠቀም ካለብዎት በር እና መስኮት መክፈት አይርሱ። ከሰል ጭሱ ከጠፋ ችግር የለውም በማለት አይዘናጉ። ከሰል ቤት እንዲሞቅ ለማድረግ ሲሉ ብዙ የዋህ ነፍሳትን አጥተናል። ከሰል መርዝ መሆኑን ገዳይ መሆኑን ለአፍታ አይርሱ ሲጠቀሙ ከቤትም ከበርም ያርቁ። ለመሆኑ ከሰል የሚያደርሰው የጤና እክል ምንድን ነው? 1. የመተንፈሻ አለርጂ መቀስቀስ /የመተንፈሻ አካል መበሳጨት / 2. የካርበን ሞኖ ኦክሳይድ ብክለት እና መመረዝ አስከ ሞት ያደርሳል። 3. የነርቭ ስርአት መዛባት ፡ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ፡ መነጫነጭ ፡ የእንቅስቃሴ ስርዓት መዛባት ከሰል የሚለቀው አየር ካርበን ሞኖ ኦክሳይድ እጅግ ለህይወት አስጊ ከሚባሉት የአየር አይነቶች ይመደባል። በሚቀጥለው ቀን በዝርዝር እመለስበታለሁ። መልካም አዳር። ደግሞ የዓለም ስጋት የሆነውን ኮሮና መከላከል አይርሱ። ከየትም ከማንም በተለይ ከቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ እንደሚይዘን አይርሱ። እንጠንቀቅ እንጠበቅ። @EthioBini @EthioBini
Mostrar todo...