cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የባ/ዳር አህለሱና ሰለፍያ ወጣቶች ገፅ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
452
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

👉 ቃላት ያጥረኛል ምስጋና ለዐለማቱ ጌታ ለብቸኛው አምላክ አላህ የተገባ ይሁን ። የሐራው ጉደኛ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቋል ። ሐራ ላይ ሁሉም የሀገራችን አንጃዎች አሉ ማለት ይቻላል ። ሱፍያ ፣ ኢኽዋን ፣ ሀጃዊራ ፣ ተክፊር ፣ እንዲሁም ወሰጥይ ሰለፍዮች ይገኛሉ ። ይህ ታላቅ የተውሒድና ሱና ዳዕዋ ፕሮግራም የተዘጋጀው በሰለፍይ ወጣቶች ነበር ። እነዚህ ወጣቶች ካሉት የተለያዩ አንጃዎች ሲነፃፀሩ 80% ይሆናሉ ። ፕሮግራሙ ከመድረሱ በፊት ሱፍዮችና ኢኽዋኖች እንዳይካሄድ የሚችሉትን ሁሉ አድርገው ነበር ። ከዞን እስከ ክልል በመደወል የተለያየ ስም በመለጠፍ የሽብርተኛ ቡድን የሚሰባሰብ በማስመሰል ቢኳትኑም ድካማቸው መና ሆኖ ሊቀር ችሏል ። ይህ ሊሆን የቻለው ከላይ ከተጠቀሱት አካላት ወደ ከንቲባው ሲደወል ከንቲባው ፕሮግራሙን ያዘጋጁት የሐራ ሶፋ መስጂድ ኢማም የሰላም አምባሳደር እንደሆኑና የከተማዋን ሰላም ከኛ በላይ የሚያስጠብቁ ስለሆኑ እኔ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ በማለቱ ነበር !!!!!። ፕሮግራሙ ከተጀመረ በኋላም የይድረሱልን የጣር ጩኸት ሳያቋርጡ ቢያሰሙም በቁጭታቸው እንዲሞቱ የሚነገረው ነገር ወንጀል መሆኑን በቂ ማስረጃ ሳታመጡ አይቋረጥም ብሎ መፈናፈኛ በማሳጣት የሚገርም ሚና ተጫውቷል ። አላህ ከንቲባውንና አብረውት ላሉ ሙእሚን ወንድሞቹ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው ። የሱና ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ሰበብ እንደሆኑት ለጠመሙት ሂዳያ ሰበብ ያድርጋቸው ። የሐራ ሶፋ መስጂድ ኢማምና አስተማሪ የሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት በዒልማቸው የጠለቁ ፣ በአንደበታቸው ሩቱእ የሆኑ ፣ በስነምግባራቸው የሚያስገርሙ ፣ በዐቂዳና ሚንሀጅ የሚያስደንቁ ፣ በትህትናቸው የሚያስጨንቁ ፣ በቀረቧቸው ቁጥር ፍቅር የሚጨምሩ ፣ ሲርቁዋቸው የሚናፈቁ ታላቅ ዓሊም ናቸው ። ለሐራ ወጣት ወደ ሰለፍያ መግባት ሰበቡ እሳቸው ናቸው ። አላህ እኛንኝ እሳቸውንም በሐቅ ላይ የምንፀና ያድርገን ። የሐራ ሰለፍይ ወጣቶች ምን ብዬ እንደምገልፃቸው አላውቅም ። በጣም ትሁት ፣ ሰው አክባሪ ፣ ለሱና ዘብ የቆሙ ፣ ለባጢል ፊት የማይሰጡ ፣ ለተውሒድና ሱና የትኛውንም ዋጋ ለመክፈት የተዘጋጁ ፣ ዝግጅታቸው ሒሰን ወማዕነን የሆነ ፣ አንድ ሰው ከራሱ ጋር ሊግባባ በማይችለው መልኩ የሚግባቡ ፣ የሚከባበሩ ፣ ለሸይኹ ትእዛዝ በተጠንቀቅ የቆሙ ፣ ለሚያያቸው ልለያቸው ነው እንዴ ብሎ ጭንቀት እንዲዘው የሚያደርጉ ፣ ከዲናቸው አልፈው የከተማዋን ሰላም የሚያስጠብቁ ፣ ለትውልድ አረአያ መሆን የሚችሉ ብርቅዬ የሰለፍይ ስብስቦች ናቸው ። ከሌላው ለየት የሚያደርግ ድንቅ ተግባር አላቸው ። ይህም ወጣቱ አንድ ለማግባት መከራውን በሚያይበት በአሁኑ ጊዜ ሁለት ሁለት አግብተው ለሶስተኛ ሚስት እየተዘጋጁ ያሉ ናቸው አላህ ይጨምርላቸው ። የሐራ ሶፋ መስጂድ ኢማምና ወጣቶች ለብዙ ሱፍዮች ፣ ተክፊርዮችና ሌሎችም ሂዳያ ሰበብ ሆነው እንዲመለሱ አድርገዋል ። በዚህ አይነት ጥምረትና አንድነት ባለው ጀማዓ ተዘጋጅቶ የነበረው ፕሮግራም የማይታመን ታሪክ ተሰርቶበት በሰላም ተጠናቋል ። አላህ ሐቅን የበላይ አድርጎ ባጢልን አርክሶ ኡማውን ወደ ተውሒድ መልሶ አይናችንን ያሳርፍልን ። ሐቅን አውቀው ከሚከተሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ። https://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ተለቀቀ አዲስ መፅሐፍ "ከጅሐድ ጥበብና ህግጋት ምርጥ ፍሬዎች" በሸይኽ ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል`በድሪ ሃፊዞሁሏህ ተዘጋጅቶ በአቡ ዓብዱልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ወደ አማረኛ የተመለሰ በዚሁ ቻናል በPDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚተላለፍ ይሆናል ተብሎ ቃል በተገባው መሰረት እነሆ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርቧል ሸር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን! የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq
Mostrar todo...
ከጅሐድ_ጥበብና_ህግጋት_ምርጥ_ፍሬዎች.pdf3.01 MB
የጁመዓ ኹጥባ (ምክር) ርዕስ "ረመዷንን እንዴት እንቀበለው?" በኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ በባህር ዳር መስጅደል ቡኻሪ መጋቢት ‐ 01 ‐ 2015 #Size_6.96_MB የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Mostrar todo...
01_07_2015,_ረመዷንን_እንዴት_እንቀበለው,_በኡስታዝ_ዩሱፍ_አህመድ.mp36.96 MB
ይህ " አል-ኢስላሕን እናቋቁም " በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ላይ ንብረትነቱ የአጠቃላይ የሐገራችን ሰለፊዮች የሆነ አንድ የሰለፊዮች ማዕከል ለመገንባት የሚደረግ እንቅስቃሴ የቴሌግራም ግሩፕ ነው። የግሩፑ ባለቤትነት የኢትዮዽያ ሰለፊዮች ሆኖ በሰለፊ መሻኢኾች የሚመራ ነው። t.me/letsbuildalislaah
Mostrar todo...
አል-ኢስላሕን እናቋቁም!!!

ይህ " አል-ኢስላሕን እናቋቁም " በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ላይ ንብረትነቱ የአጠቃላይ ሐገራችን ሰለፊዮች የሆነ አንድ የሰለፊዮች ማዕከል ለመገንባት የሚደረግ እንቅስቃሴ የቴሌግራም ግሩፕ ነው። የግሩፑ ባለቤትነት የኢትዮዽያ ሰለፊዮች ሆኖ በሰለፊ መሻኢኾች የሚመራ ነው። t.me/letsbuildalislaah

Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና ታላቅ የምስራች ለአል ኢስላሕ መድረሳ ቤተሰቦች በሙሉ ዛሬ የካቲት 9/2015 ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ በታላቁ ሸይኻችን ሸይኽ ሐሰን ገላው ሀፊዘሁሏህ " የነብዩ ውዴታ " በሚል ርእስ ታላቅ ሙሐደራ ተዘጋጅቶላችኋል ።አል-ኢስላሕ መድረሳ https://t.me/medresetulislah
Mostrar todo...
ተለቀቀ አዲስ መፅሐፍ "የአንገብጋቢ ትምህርቶች ለማያውቁ ማህበረሰቦች" በሸይኽ አልዓላማህ ዓብዱልዓዚዝ ብን ዓብዲላህ ብን ባዝ ረሂመሁሏህ ተዘጋጅቶ በሸይኽ  ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል`በድሪ ሃፊዞሁሏህ ትንታኔ ተደርጎለት በአቡ ዓብዱልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ ወደ አማረኛ የተመለሰ በዚሁ ቻናል በPDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚተላለፍ ይሆናል ተብሎ ቃል በተገባው መሰረት እነሆ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርቧል #ለአካለ መጠን ከደረስንበት ጊዜ ጀምሮ ምድራዊ አለምን በሞት እስከምንሰናበት ድረሥ ልንከተላቸው የሚገቡ አምላካዊ ሥርአቶችን በውሥጡ ያቀፈ ምርጥ መጽሐፍ በኡስታዝ ዮሱፍ አሕመድ -ሐፊዞሁሏህ-  በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረቦላችኋል። ሸር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን! የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq
Mostrar todo...
የአንገብጋቢ_ትምህርቶች_ለማያውቁ_ህዝቦች_ትንታኔ.pdf7.68 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.