cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዘውጀቲ ልዪ🎁

Yenebi wedaj yehone 😍ልብ የሚነካ የረሱል(ሰ.ዐ.ወ)ሀዲስ 🍂መሳጭ ታሪክ🍃 🌾ለመከታተል🌾 🌾🌻🌹🌻🌹 @ZEWJETI_CHANNALE ✒COMMENT👉 @Nebaye6541 ☝👇 @ZEWJETI_bot (((((join )))) JOIN ወንዶች ለእህቶቻቹ SHARE እህቶቼ JOIN https://t.me/ZEWJETI_CHANNALE

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
281
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ሂክማ ክፍል_ሀያ አንድ ፡ ትንሽ ወደ ራሷ መለስ ካለች ቡሀላ ፊት ለፊቶ የተቀመጠውን የውሀ ብርጭቆ አንስታ መኝታ ክፍሌ ድረስ አሯሯጠችኝ ክፍሌ ገብቼ በሩን ስዘጋባት እየተነጫነጨች ተመልሳ ሄደች። ይሄን ቃሪያ ምላሷን እንዲህ በቃሪያ ማቀጠል ካልሆነ በቀር ማን ይችለዋል። ...እንደተለመደው አጥንቼ እንደጨረስኩ ሂክማን ፍለጋ ወደ ፌስቡክ መንደር ጎራ አልኩ። የዛሬውን የውሎ ሪፖርት እስክነግራት ቸኩያለሁ። ምናልባትም ከሁለትና ሦስት ቀናቶች በኋላ ፎቶዋን ልካልኝ እንዲህ ልቤን ያንበረከከችውን ጀግና ማንነት ማወቅ እችል ይሆናል። ሂክማ ኦን ላይን ላይ ነበረች። ቀድሜ ኢስላማዊ ሰላምታ አቀረብኩላት። እሷም አፀፋዊ ምላሽ ሰጠችኝና፤ "ሶላት እንዴት ነበር?" ስትል ጠየቀችኝ። "ይሄው አንድም ሳላስቀር ስሰግድ ነው የዋልኩት።" አልኳት። "እስኪ ሳትዋሽ ንገረኝ ሁሉንም በአግባቡ ሰግደሃል?" ስትል ጠየቀችኝ። ምን መመለስ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ እንዳልዋሻት ሁሉንም አውቃለሁ ስላለችኝ ምናልባት እንደዋሸኋት አውቃ 'ቃሌን አልሞላልህም!' እንዳትለኝ ሰጋሁ። እውነቱን ብነግራት ደግሞ 'ዛሬ ሙሉ ሶላት ስላልሰገድክ ከነገ ጀምሮ ነው መቆጠር የሚጀምረው።' ብላ የዛሬውን ልፋቴን ከንቱ እንዳታረግብኝና ሶላት የምሰግድበትን ቀናቶች እንዳታራዝምብኝ ፈራሁ። ስላንተ ሁሉንም አውቃለሁ ያለችው ለማስፈራራት ያህል ሊሆን ይችላል ብዬ በማሰብ መዋሸቱን መረጥኩና፤ "አዎ ሁሉንም በሰዓቱና በአግባቡ ነው የሰገድኩት።" አልኳት። "እሱን እንኳን ተወው! ፈጅርን ፀሐይ ከወጣ በኋላ ነው የሰገድከው። ያው የመጀመሪያ ነው በሚለው ልናልፈው ካልሆነ በቀር!" ብላ አስደነገጠችኝ። እውነት ለመናገር የሂክማ ነገር ከማስበው በላይ ግራ እያጋባኝ ነው። የውጭ ሰው ናት እንዳይሏት የውስጥ ሚስጥሬን ሳይቀር ታውቃለች። የውስጥ ሰው ናት እንዳልል ደግሞ ከቤተሰቦቼ ውስጥ በሷ ደረጃ የሚጠረጠር ሰው የለም። ሪ ስልክ አትይዝም። የማሚ ስልክም ኢንተርኔት የማትሰራ ትንሽዬ ስልክ ናት። አባቢም ቀንም ማታም ቢዚ ስለሆነ ለዚህ የሚሆን ትርፍ ጊዜ የለውም። እንዲያው አንዳቸው ናት ብንል እንኳን፤ ማናቸውም የሷን ያህል በሳልና አቅሜን ሊፈታተን የሚችል የለም። ታዲያ ማን ትሆን? ግራ ተጋባሁ። ሀምዱ ነው ብዬ የጠረጠርኩት ጥርጣሬ ስህተት እንደሆነ አረጋገጥኩ። እሱ ሱቢህ በጊዜ ልስገድ አልስገድ ይቅርና ዙሁር እንኳን መስገዴን ያወቀው ገና መስጂድ ውስጥ ያየኝ ሰዓት ነው። "ቆይ አንች ግን ማን ነሽ? እንዴትስ የውስጥ ሚስጥሬን ልታውቂ ቻልሽ? መቼም ጠንቋይ መሆን አለብሽ!" "ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም! ሲባል አልሰማህም?" "እሱም እኮ ስለሰዎች እንጅ ስለራሴ አውቃለሁ አላለም።" "ከፅንስነቱ ጀምሮ አብሮት ስላለው ራሱ ማወቅ ያልቻለ ስለሰው ያውቃል ብለህ ታስባለህ?" አለችኝ። ከዚህ በላይ ልከራከራት አልቻልኩም። "አሁን ማረሳሳቱን ተይና የጠየቅኩሽን መልሽልኝ!" አልኳት ትዕግስቴ አልቆ። "ይሄን ለማወቅ እኮ ብዙ መልፋት አይጠበቅብኝም።" "እኮ እንዴት??" "አንድ ለብዙ አመት የሱቢህን ሶላት ያልሰገደ ሰው የመጀመሪያ ሶላቱን በወቅቱ ሊሰግ ያለመቻሉ እድል ሰፊ ነው። አንተ ደግሞ እንቅልፋም ስለሆንክ ከረፈደ ነው ምትነሳው ተሳሳትኩ?" አለችኝ። መቸም እኛ ሰዎች አዕምሯችንን በአንድ ነገር ላይ ካሳመንነው ከዛ አንግል ባለፈ ሊመለከት አይችልም። በዚህ መልኩ ይሆናል ብዬ በጭራሽ አልጠበቅኩም ነበር። አሁን ደግሞ ሀምዱ ላይ የነበረኝ ጥርጣሬ የመጀመሪያ ቦታውን ተቆጣጠረ። አሁንም ግን ሌላ አሻሚ ነገር ንግግሯ ውስጥ አገኘሁ። አዎ እንቅልፋም እንደሆንኩና አርፍጄ እንደምነሳ እንዴት አወቀች? የጥያቄውን አቅጣጫ ወደሷ አዙሬ ጠየቅኳት። ይቀጥላል.........
Mostrar todo...
#ሂክማ ክፍል_ሀያ : "ቆይ አንተ ሰሞኑን ምን አይነት ፀባይ ነው እያሳየኸኝ ያለኸው? አስጠላሁህ እንዴ?" አለችኝ ጭንቅላቷን ቀና አድርጋ እየተመለከተኝ። "እኔ እንደዛ የሚል ቃል ወጣኝ?" "እና እሽ ያ ሁሉ የፍቅር ቃላት የት ገባ? አልታወቀህም እንጅ ፀባይህ ተቀያይሯል እኮ።" አለችኝ ፊቷን ክስክስ አድርጋ። አይኖቿ ለማንባት እያቆበቆቡ እንደሆነ ያሳብቃሉ። ደግነቱ ምላሽ ሳልሰጣት የመግቢያ ደወል ተደወለና ደስ እንዲላት ብቻ ጉንጯን ስሜ ተለየኋት። የዕለቱ ትምህርት ተገባዶ ወደ ቤት ስንለያይ ዮኒ፤ "በል እንግዲህ መልካም የስብከት ምሽት ይሁንልህ¡" አለኝ። "እንዴ ዙሁር እኮ አልሰገድክም ልትዋሻት ነው ወይስ ከአሱር ጋር ሰግደህ ሰግጃለሁ ልትላት ነው?" አለ ሃሚ። "ውይ ሚስኪኪኪኪን! ለካ የ7 ሰዓቱን ስግደት አልሰገድክም። አሁንስ አንጀቴን በላሃኝ። በቃ ለምን አትተዋትም?" ሲል ዮኒ አስተያየቱን ሰነዘረልኝ። "አዎ ዮኒ እውነቱን ነው በቃ አንዳንዴ እኮ ሽንፈትን አምኖ መቀበል ጥሩ ነው።" ሲል ሃሚ የዮኒን ሃሳብ አጠናከረ። "አይ ቢያንስ እንኳን ማንነቷን ልወቅ እንጅ!" አልኳቸው። "እሽ እንደፈለክ።" አለ ዮኒ። በዚህ መልኩ ተለያይተን ወደዬ ቤታችን አቀናን። ቤት ገብቼ አሱርን ስሰግድ ሰግጄ እስክጨርስ ድረስ ሪሃና ተገርማ ቆማ አየችኝ። ማሚም እንዳላፍርና እንዳልሸማቀቅ ስለሰጋች ችላ ያለች ብትመስልም በሳሎን ቤቱ ባለፈች ቁጥር የደስታ ሳቅ ውስጧን እየተናነቃት በቆሪጥ እያየችኝ ነው። ሰግጄ ስጨርስ ሪሃና፤ "አንተ ልጅ ግን ዛሬ በደህናህ ነው?" ስትል ጠየቀችኝ። "ምነው ደህና አልመስል አልኩሽ እንዴ?" አልኳት የሰገድኩበትን መስገጃ እያጣጠፍኩ፡፡ "ቀላል! ቆይ የምትሞትበት ቀን ተነገረህ እንዴ?" አለችኝ። ሪ ስለሞት ስታነሳ መሞት የሚባል ጣጣ እንዳለ ትዝ አለኝ። እውነትም ቆይ እንዲህ በተዘናጋሁበት ሰዓት ብሞትስ? የጀነት ነኝ ወይስ የጀሀነም? ለነገሩ ምንም ጥያቄ አያስፈልገውም ጀሃነም ውስጥ VIP ተይዞልኝ እንደሚጠብቀኝ ግልፅ ነው። በሃሳብ ውስጥ ሰምጬ ሳልመልስላት ስቀር ማሚ የተጨነቅኩ መስሏት፤ "አንች ልጅ ምናለበት ባትጨቀጭቂው?" አለቻት። "እንዴ ማሚ ይሄ ልጅማ በደህናው ከመሬት ተነስቶ ሶላት ሊጀምር አይችልም። ግድ የለሽም አባቢ ይምጣና ቁርዓን ይቅራበት።" አለቻት። "አስተግፊሩላህ! አንች ልጅ እንዴት እንዴት ነው ምትናገሪው? ካልሽስ አንች ላይ ነበር ማስቀራት!" አለቻት። "ማሚዬኮ ስወድሽ! አሁን እች ካንች ማህፀን ነው የወጣችው ቢባል ሰው ያምናል?" አልኳት ተነስቼ ግንባሯን እየሳምኩ። "እናንተማ ቆይ! እኔ ላይ እያበራችሁ አስቸግራችኋል።" አለች ሪ እንደ መቅናት እያረጋት። "አሁን ጭቅጭቁን ተዉ እና ውሃዋ ሳትሄድ ባልዲውን ሙሉ!" ብላ ስራ ሰጠችን ማሚ። መግሪብ እና ኢሻዕንም በሰአቱ ሰገድኩ። ማታ አባቢ መጥቶ እራት እየበላን እያለ ሪሃና የዛሬውን ሁኔታዬን ለአባቢ ነገረችው። አባቢም፤ "እንዴ በዷህዋ የተጀመረው የሳሊሜ ሶላት እስከ ኢሻዕ ዘለቀ ማለት ነው?" ብሎ ቀለደብኝ። "ኢንሻ አላህ! ነገ ለሱብሂ ስትነሳ ከቀሰቀስከኝ ሱብሂንም በሰዓቱ እሰግዳለሁ!" አልኩት። "እንዴ ሳሊሜ ኢንሻ አላህ ሲል ሰማሁት ልበል?" አለች እች ሙጢ ሪሃና። እኔንም ጨምሮ ሁላችንም ሳቅን። ሪሃና እውነቷን ነው። ከዛሬ ውጭ አንድ ተራ ሙስሊም ዘንድ የሚዘወተሩ ሀይማኖታዊ ቃላቶችን እንኳን በንግግሬ መሃል ቀላቅዬ አላውቅም ነበር። እድሜ ለሂክማ ዛሬ አንድ ቃል ለማለት በቃሁ። "አራት አውቃት ሶላት ሰግዶ ይሄን ያህል ለውጥ ካሳዬማ፤ ነገ ሱብሂን በሰዓቱ ሲሰግድ ሀይለኛ ዳኢ ነው ሚወጣው!" ብላ ቀለደችብኝ ማሚ። "ማሚዬ አንችም? አንችም እንደነሱ እኔ ላይ ማሾፍ ጀመርሽ?" አልኳት። "እኔ አላሾፍኩም ሳሊሜ የምሬን ነው። አልተጠቀምከውም እንጅ ፈጣን ጭንቅላት ነው ያለህ።" አለችኝ። "አይ እንግዲህ ማዕድ ላይ አትሞጋገሱብን!" አለች ሪ። "አንች ቆይ በኔና በማሚ እንዲህ ሚያስቀናሽ ምንድን ነው? ጡቴን ጠባሽብኝ እንጅ አልጠባሁብሽ?" ስል ነካኋት። ብዙ ጊዜ ታላቅ በታናሹ ሲቀና እንጅ ታናሽ በታላቁ ሲቀና አይቼ ስለማላውቅ ነው እንደዛ ያልኳት። በወሬያችን ዝም ብሎ ሲስቅ የቆየው አባቢ፤ "እናንተ ለማዕድ ክብር ይኑራችሁ እንጅ! ማዕድ እየተበላ አይወራም!" አለን። በልቼ እንደጠገብኩ በደረቅ እንጀራ ቃሪያ ጠቅልዬ፤ "እስኪ ነይ ላጉርስሽ እኔ እንዳንች ምቀኛ አይደለሁም።" አልኩና ለሪሃና አጎረስኳት። የጎረሰችውን ስታላምጠው ቃሪያው አንገበገባት። ሲጀመርም ቃሪያ አትወድም ነበረና ላብ እስኪያጠምቃት ድረስ ተንገበገበች። እነአባቢ በሳቅ ፈረሱ። ማታ ይቀጥላል ........
Mostrar todo...
የአረብኛ ወራት ሹሁሩል ዐረቢያ (الشهور الهجري) 1 መስከረም ሙሐረም (محرم) 2 ጥቅምት ሰፈር. (صفر) 3 ህዳር ረቢዓል አወል(ربيع الأول) 4 ታህሣሥ ረቢዓ ሳኒ(ربيع الثاني) 5 ጥር ጁማደል አወል(جمادى الأولى) 6 የካቲት ጁማደ ሳኒ(جمادى الآخرة) 7 መጋቢት ረጀብ(رجب) 8 ሚያዝያ ሻዕባን(شعبان) 9 ግንቦት ረመዳን(رمضان) 10 ሰኔ ሸዋል(شوال) 11 ሐምሌ ዙል ቃዒዳ(ذو القعدة) 12 ነሃሴ ዙል ሒጃ(ذوالحجة)
Mostrar todo...
· •⊰✿ 💎✿⊱• ❀━┅┉┈ድንቅ ታሪክ ናት┈┉┅━❀ 👳‍♂ በሙሳ ዐ.ሰ ዘመን ነው....አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ። ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል...። እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ 🧕ሚስት ለባለቤትዋ፦"ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች። 👨 እሱም፦"አዎን" ይላታል። "ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው። ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ ሙሳ ዐ.ሰ ቤት ጀመሩ። ሙሳንም ዐ.ሰ አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው። 👳‍♂ሙሳም ዐ.ሰ አላህን ለመኑላቸው። አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ።"ብሎ መለሰላቸው። 👳‍♂ሙሳም ዐ.ሰ ጥንዶቹ ጋ በመሄድ አላህ ዱዓቸውን ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው ሀብታምም እንደሚሆኑ 💰 ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ቢቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው። በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ።ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ። እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ ሚስት ለባሏ እንዲህ 🧕 አለችው፦"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለ አንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን አንድ መልካም ስራ እንስራ" ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል። ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት 🏫 ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ ጠዋት ማታ ምግብ 🍲ይቀልቡ ጀመር...። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ። 👳‍♂ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል.... 👳‍♂ሙሳም ዐ.ሰ ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦ "ያ ረብ ቃል የገበኽላቸው ለ አንድ አመት ሆኖ ሳለ እንዴት እስካሁን እልደኸዩም?"ብለው አላህን ጠየቁ። /እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን የአላህን ሂክማ ለማወቅ ነው የጠየቁት/ ❤️ ቸር የሆነው አላህም፦ "ሙሳ ሆይ! ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው...እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው 🏫ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ። ሙሳ ሆይ! እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው። 🧡 ❀━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━❀ ከተሰጠን ላይ አላህን አመስግነን ስንሰድቅ ይጨመርልናል😇 ሼር ማድረጉን አይርሱ 👇 ✨🔸 🔸✨
Mostrar todo...
"የፍቅር መጀመሪያው ትዳር ሲሆን መጨረሻው ደግሞ ጀነት ነው" 🤲ያረብ ፍቅር እስከ ጀነት ወፍቀን🤲 አሚን!!
Mostrar todo...
ጨለማዉን ወስዶ ብርሀኑን ለለገሰን አላህ ሹኩር ይገባዉ እለዋለሁኝ አልሀምዱሊላህ ✋በሉ እስኪ አልሀምዱሊላህ
Mostrar todo...
ቀንህን ለማሳመር ሰዎች ደስ የሚል ነገር እስኪነግሩህ፣ ጥሩ ዜና እስክትሰማ ወይ ነገሮች እስኪስተካከሉ ድረስ አጠብቅ! እውነተኛው ሰላም የሚመነጨው ከውስጥህ ነው፤ ወዳጄ ፈጣሪ ያደረገልህን በማሰብ ብቻ ቀንህን በደስታ መጀመር ትችላለህ!
Mostrar todo...
#ኢድኡኒ_አስተጂብ_ለኩም✨ ያ አሊም❤️ የሰዎችን እሳቤ...የውስጠታቸውን ምስጢር....በሆድ የተሸሸገ እልፍ ፈተና እንድናውቅ አልታደልም....እንዲያውቁብንም አልተቸሩም....ድብቅ የሆኑ ሺ! ስሜቶች መታፈን ደክሟቸዋልና....አዋቂ ነህና በእውቀትህ.... ካረገዝነው የመከራ መአት አንዷን እንኳ አምጠንም ቢሆን እንወልዳት ዘንዳ ይሁንታህን ወፍቀን!...አንድ ይብቃቹ ስትል መቶ ይቀላልና አቅልልልን! ሰይዲ❤️ <ትእግስታችንን ስትፈትን ለማለፍ እየጣርን በስተመጨረሻ ስንዝል ድጋፍ ሁነን! ጣፋጭ ፍሬ ለናፈቀ ጥፍጥናውን እርም አታድርግበት! ጀነትን የጠየቀ ከጀሀነም ከልለኝ ቢል እሺ በለው ያ ሀይ !> ያ ረብ!❤️ ማ ለና ኢላ ሲዋክ! ወላ ነስጁዱ ኢላ ለክ!
Mostrar todo...
⚘ በሌሎች ሰወች ልብ ውስጥ ተስፍን ቅዱ....ትንሹ ተስፍ ትልቅ ነገር ይሰራል... የደስታ የተዋበ የፈካ ምሽት ተመኘሁላችሁ...❤
Mostrar todo...
‏﷽ ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ ﷺ♥️♥️♥️
Mostrar todo...
0.90 KB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.