es
Feedback
ዘፀአት ሜዲካል (ZeTse@ Medical)

ዘፀአት ሜዲካል (ZeTse@ Medical)

Ir al canal en Telegram

This channel is created for discussion of health related issues in Amharic. ስለጤና/ሕክምና የምንማማርበት ቻናል ነው::

Mostrar más
307
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
-530 días
Archivo de publicaciones
አዲሱ ዓመት ስለጤናችን በሰላም የምንመክርበትና ሰላም በሀገራችን የሚሰፍንበት ዓመት ይሁንልን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት!
አዲሱ ዓመት ስለጤናችን በሰላም የምንመክርበትና ሰላም በሀገራችን የሚሰፍንበት ዓመት ይሁንልን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት!

ገጠመኝ ከዕለታት ባንድ ቀን ነው በስራ ላይ ሳለሁ በጣም የታመመ ወጣት (በ30ዎች ዕድሜ ያለ) በጤናው ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ወደ ቢሮየ ይመጣል:: እንደተለመደው ስለህመሙ ጠየቅሁት:: እሱም
ገጠመኝ ከዕለታት ባንድ ቀን ነው በስራ ላይ ሳለሁ በጣም የታመመ ወጣት (በ30ዎች ዕድሜ ያለ) በጤናው ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ወደ ቢሮየ ይመጣል:: እንደተለመደው ስለህመሙ ጠየቅሁት:: እሱም ከፊንጢጣ አከባቢ ለነበረው ህመሙ (በነሱ ግምት ኪንታሮት) በቤተሰቡ ግፊት ወደ ባህል ህክምና እንደሄደና ለተከታታይ ቀናት በፊንጢጣ አከባቢ መድኃኒት እንደተደረገለት (የሚቀባና በመርፌ) ከዚያ በኋላ በፊንጢጣ አከባቢ ከባድ የህመም ስሜት እንዳለው እንዲሁም ሰገራ መውጣት ሁሉ እንደከበደው ነገረን:: ባደረግነው አካላዊ ምርመራ ደግሞ የፊንጢጣ ዙሪያው በጣም ቆስሏል። ሰገራው ደርቆ ተጠራቅሟል:: ህክምና: የመጀመሪያ ዙር: የሰገራ ማለስለሻ ፣ የህመም ማስታገሻና ተጨማሪ አጋዥ ህክምናዎች ተሰጥተውት ወደ ቤቱ ተሸኘ:: ነገር ግን ህመሙ ስለበረታበት ከ5ቀናት በኋላ ተመልሶ መጣ:: ሁለተኛ ዙር: ጊዜያዊ የሰገራ መውጫው በሆዱ ጎን (colostomy) ተደረገለት:: ቁስሉ በተደጋጋሚ ተጠረገለት:: በዚህ ሁኔታ ለ4ወራት ከቆየ በኋላ ቁስሉ ዳነ:: ሦስተኛ ዙር: ጊዜያዊ የሰገራ መውጫው ተዘግቶ ወደ ነበረበት ተመለሰ። ቁስሎቹ መዳናቸው ተረጋግጦ ከክትትል ተሰናበተ:: ይህ የዕለት ተዕለት ገጠመኞች አካል ሲሆን ይህኛው ባስ ያለ በመሆኑ አጋራኋችሁ። የባህል ህክምና በሀገራችን -ከምን እስከምን ይሁን? -የህግ ማዕከፍና ተጠያቂነትስ እስከምን ድረስ ነው? -ሙያዊ ፈቃድስ አላቸው?

ቆዳ ልጠፋ (skin graft) በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት የአካል ክፍል ቆዳ ሲታጣ ከሌላ የሰውነት ክፍል ወስዶ መለጠፍ ቆዳ ልጠፋ ይባላል፡፡ ቆዳ ወፍራምና ብዙ ድርብርቦች ያሉት በመሆኑ ከላይኛው
+5
ቆዳ ልጠፋ (skin graft) በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት የአካል ክፍል ቆዳ ሲታጣ ከሌላ የሰውነት ክፍል ወስዶ መለጠፍ ቆዳ ልጠፋ ይባላል፡፡ ቆዳ ወፍራምና ብዙ ድርብርቦች ያሉት በመሆኑ ከላይኛው (ውጨኛው) ቆዳ ስስ ሽፋን ተወስዶ ሌላ ቦታ ላይ ሲለጠፍ ሁለቱም ቦታዎች ቆዳ እንዲኖራቸው ይሆናል፡፡ አንድ ቁስል በጊዜ ካልዳነ ወደ ካንሰር ሊቀየር ስለሚችል በቆዳ ልጠፋም ሆነ በሌላ መንገድ በቶሎ እንዲድን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ለሚመለከተው ሁሉ አዳርሱ
ለሚመለከተው ሁሉ አዳርሱ

Organ transplantation
+3
Organ transplantation

የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ (organ transplantation) በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት የሰውነት አካል ክፍሎች ከአገልገሎት ውጭ በሚሆኑበት ጊዜ ከሌላ ሰው ተለግሶ መተካት የዘመናዊ ህክምና አንዱ መንገድ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ የሰው ልጅ ሲፈጠር ከራሱ አልፎ ለሌላ ሰው ሊሆኑ የሚችሉ የአካል ክፍሎች አሉት፡፡ አንዳንዶቹ ሁለት ሆነው የተፈጠሩ (ለምሳሌ፡ ኩላሊት) ሌሎች ደግሞ ተከፍለው ሊለገሱ የሚችሉ (ለምሳሌ - ጉበት) ናቸው፡፡ በዘመናዊ ህክምና ታሪክ የመጀመሪያው የአካል ክፍል ንቅለ-ተከላ የተደረገው በአሜሪካን ሀገር የዛሬ 70ዓመት በ1954 እ.ኤ.አ. ሲሆን ከመንትያ ወንድማማቾች የአንዱ ኩላሊት ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ከመንትያ ወንድሙ ኩላሊት ተወስዶ ተተክሎለታል፡፡ ቀዶ ህክናውን የመራው ሀኪምም ዶ/ር ዮሴፍ ሙሬይ ይባላል፡፡ ከዚያ ጊዜ ወዲህ የሰውነት አካ ክፍል ንቅለ ተከላ በብዙ ሀገራት ሰፍቶ እድገቱ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ የሰውነት አካል ክፍሎች በህይወት ካሉ እንዲሁም ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች ተለግሰው በመተከል ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን የሰውነት አካል ክፍሎች ለመጥቀስ ያክል፡ • ኩላሊት • ጉበት • ቆሽት • ሳንባ • ልብ • አንጀት • ስጋና ቆዳ ባንድነት (composite tissue graft) አሜሪካ ንቅለ-ተከላ የተደረገላቸውን ታካሚዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን (1000000) ማድረሷን ያሳወቀችው ከሁለት አመታት በፊት ነው፡፡ አፍሪካ፡ የመጀመሪያው ንቅለ-ተከላ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ ሲሆን ጊዜውም እ.ኤ.አ. 1966 ነበር፡፡ ብዙዎቹ የሰሜኑ አፍሪካ ሀገራት የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላን በስፋት ይሰጣሉ፡፡ ከሰሀራ በታች ያሉ ሀገራትም በብዛት አገልግሎቱን መስጠት ጀምረዋል፡፡ ከአንድ አመት በፊት በታተመ ጥናት መሰረት ጎረቤታችን ኬንያ ንቅለ-ተከላ አገልግሎትን ከ1978 እ.ኤ.አ ጀምሮ እየሰጠች ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን በሰባት ማዕከላት ትሰጣለች፡፡ ኢትዮጵያ፡ ሀገራችን በአሜሪካ ሀገር ካለ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ2015 እ.ኤ.አ. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኩላሊት ንቅለ-ተከላ አገልግሎትን ማስጀመር ችላለች፡፡ በዚህ አገልግሎት እስከ 2020 እ.ኤ.አ. ድረስ 137 ሰዎች ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸዋል፡፡ አሁን ላይ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች እየተሰጠ ነው፡፡ ነገር ግን በግብዓት አቅርቦት ችግር ምክንያት የሚፈለገውን ያክል እየተሰራ አይደለም፡፡ ሰላም! References: 1.Bamgboye EL. Kidney Transplantation in Sub-Saharan Africa: History and Current Status. Kidney360. 2023 Dec 1;4(12):1772-1775. 2. Shimels T, Getachew A, Tadesse M, Thompson A. Providers' View on the First Kidney Transplantation Center in Ethiopia: Experience From Past to Present. Health Serv Res Manag Epidemiol. 2021 May 25;8:23333928211018335 3. Ahmed, Momina M.; Tedla, Fasika M.; Leichtman, Alan B.; Punch, Jeffrey D. Organ transplantation in Ethiopia, The Transplantation society journal.

የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ (organ transplantation) - ምንድን ነው? - መቼ ተጀመረ? - የት ተጀመረ? - አገልግሎቱ በሀገራችን ይሰጣል ወይስ አይሰጥም? ........ ነገ በዚሁ ch
+1
የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ (organ transplantation) - ምንድን ነው? - መቼ ተጀመረ? - የት ተጀመረ? - አገልግሎቱ በሀገራችን ይሰጣል ወይስ አይሰጥም? ........ ነገ በዚሁ channel ይጠብቁን::

ይነበብ ፤ ጥንቃቄ እናድርግ
ይነበብ ፤ ጥንቃቄ እናድርግ

ትርፍ አንጀት በእንግሊዝኛ (APPENDIX) የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን በቀጭንና ወፍራም አንጀት መገናኛ ላይ በወፍራሙ አንጀት ክፍል በጎን ተቀጥሎ የሚገኝ የሰውነታችን ክፍል ነው፡፡ ትርፍ አንጀት የተረፈ አንጀት ከሚለው ይልቅ የተቀጠለ (ቅጥያ) አንጀት የሚለው የተሻለ ይገልፃዋል፡፡ የእንግሊዝኛው Appendix የሚለውም ቅጥያ (ተያያዥ) እንጂ ትርፍ የሚለውን አይገልጽም፡፡ ሁሉም ጤነኛ ሰው በሚባል ደረጃ ትርፍ አንጀት ይኖረዋል፡፡ በጣም ጥቂቶች (1/100000) ግን በተፈጥሮ ትርፍ አንጀት የላቸውም፡፡ በአፈጣጠር ደረጃ ትርፍ አንጀት ከ8ኛው የፅንስ ሳምንት ጀምሮ ተለይቶ ይገኛል፡፡ የትርፍ አንጀት ህመሞች (diseases of appendix) ትርፍ አንጀት እንደሌሎቹ የሰውነታችን ክፍሎች በተለያዩ በሽታዎች ሊጠቃ ይችላል፡፡ ከአነዚህም መካከል፡ ብግነት (ቁስለት) (inflammation) ዋናው ሲሆን ሌሎች የተለያዩ ዕጢዎች ከትርፍ አንጀት ሊነሱ ይችላሉ፡፡ የትርፍ አንጀት ብግነት/ቁስለት (appendicitis) አብዛኛው ሰው ትርፍ አንጀት አሞኛል ብሎ የሚገልፃው በሽታ ሲሆን ከህፃናት እስከአዋቂዎች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከ10 – 30 ዓመት ያሉ ዕድሜዎች ግን ቅድሚያ ይወስዳሉ፡፡ መነሻ፡ ብዙውን ጊዜ በአንጀታችን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ቁስለቱን ያመጣሉ፡፡ ለቁስለቱ እንደመነሻ የሚሆነው ደግሞ ትርፍ አንጀት በአንድ በኩል ዝግ ሆኖ የተፈጠረ አካል በመሆኑ የደረቀ ሰገራ ወይም ሌላ ባዕድ አካል ባንድ በኩል ሲዘጋ ውስጡ በከፍተኛ ግፊት ስለሚሞላና ደም በበቂ ሁኔታ ስለማይደርስ ለባክቴሪያዎቹ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ይም ቁስለቱ በፍጥነት ጉዳት እንዲያመጣ ያደርገዋል፡፡ ምልክቶች፡ የተለያዩ የሰውነት ብግነት ምልክቶች ያሉ ቢሆንም ዋና ዋዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ - የሆድ ህመም (ቁርጠት) - በእንብርት አከባቢ የሚጀምርና ቆይቶ ወደ ቀኝ ታችኛው የሆድ ክፍል የሚሄድ - ትኩሳት - ማቅለሽለሽና ማስታወክ - ምግብ ማስጠላት አልፎ አልፎ ደግሞ ተቅማጥ ምርመራዎች፡ ዋናው በሽታውን የመለያ ዘዴ የታማሚውን ህመም ምልክቶችንና አካላዊ ምርመራ ላይ የሚገኙ ምልክቶችን በማገናዘብ የሚገኝ የሀኪም ውሳኔ ነው፡፡ እንደተጨማሪ ግን - በደም ምርመራ የሚታዩ የቁስለት ምልክቶች - የአልትራሳውንድ ምርመራ - ሲቲ ስካን ምርመራ እና ሌሎች ሊያግዙ ይችላ፡፡ ህክምና፡ የትርፍ አንጀት ቁስለት በዋናነት የሚታከመው በቀዶ ህክምና ነው፡፡ ቀዶ ህክምናው በተለያዩ መንገዶች ሊደረግ ይችላል፡፡ -በመክፈት (open appendectomy) -በላፓሮስኮፒ (laparoscopic appendectomy) -በሮቦት በመታገዝ (robotic appendectomy) አንዳንዴ የታካሚውና የበሽታው ሁኔታ ታይቶ በመድኃኒት የሚታከምበት አጋጣሚም አለ፡፡ ታሪክ፡ የመጀመሪያው የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና የተደረገው በ1735 በእንግሊዝ አገር ሲሆን በአለም ላይ በስፋት ተቀባይነት ሊያገኝ የቻለው ግን በ1902 ሊነግስ ሁለት ቀናት የቀሩት 7ኛው ንጉስ ኤድዋርድ በትርፍ እንጀት ቁስለት ታሞ ንግስናው ተራዝሞ ቀዶ ህክምና ከተደረገለትና ከዳነ በኋላ ነው፡፡ ንጉሱ ቀዶ ህክምናውን የንግስና በዓሉን ምክንያት በማድረግ ላለመቀበል ጥያቄ ቢያነሳም ሀኪሙ ‘ቀዶ ህክምናው ካልተሰራልህ የንግስና በዓሉ ወደ ቀብር ስነስርዓት ይቀየራል’ በማለቱ ቀዶ ህክምናውን ተቀብሎ እደተሰራለት ይነገራል፡፡ References: 1. Schwartz's text book of surgery 2. Skandalski's text book of surgical anatomy 3. Google (SAGE journals)

የትርፍ ነገር
ሰሞኑን በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ስንጓለል የሆኑ ሀሳብ ያጡ ሰዎች ይመስሉኛል የታክሲ ሹፌር ትርፍ ጭነሃል ሲባል "ሰው እንዴት ትርፍ ይባላል?" ብለው ሲያወሩ ሰማሁ ከዛማ እኛ ሰፈር (ሀኪሞች ሰፈር) ሁልጊዜ ትርፍ ትርፍ ምትባል አንዲት ነገር አለች እና ስለሷ መፃፍ ፈለግኩ፡፡ ትርፍ አንጀት ግን ምንድን ናት? መቼ ነው የምትበቅለው? ለምንስ ትተርፋለች? ህመም የምታመጣውስ መቼና ማን ላይ ነው? ምልክቶቹስ ምን ምን ይሆኑ? ህክምናውስ ምንድን ነው? በቅርቡ…..