cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Amharic Poem❤️

ግራ የገባዉ ሰው ምንኛ ታደለ ቀኝም ሆነ ግራ ያልገባው ስንት አለ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
929
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

መቼ ነው የሚፈቱሽ????? የአንድ ወጣት ዛሬ ነገ ዘላለም ነው ከህይወት ውብ ገጾች ምንድነው ቀን መቅደድ፣ ምንድነው በልጅ ነፍስ ተልካሻ ገበያ ጅል ንግድ መነገድ? መቼ ነው የሚፈቱሽ?? ህዳር ሲኮበልል ህዳር መንገደኛው፣ አገር ጭስ ሲያፍነው ሲስል አገርኛው? ጪስ እያጫጫሱ መሳል ከለከሉን፣ ሳላችሁ ወደ ሰው ይዛመታል አሉን ወዘተ ‘ሚል ብሶት በሳል መልክ ይወጣል፣ ሳል የሰጠው ህዝብሽ መሳያ ሀገር ያጣል። መቼ ነው የሚፈቱሽ??? ታህሳስ ግርግር ታሪኩ ሲወሳ? እንራጭ ይሆን ወይ ከጋን ሰቆቃ ውስጥ በደል ተቀንሳ። ከዛ በፊትሳ? መቼ ነው ሚፈቱሽ??? ጥርን እንጠርጥር? ወይስ መፈታትሽ እንዳማረን ይቅር?? ክፉ እኮ ነው መውደድ ክፉ ነው መላመድ፣ ክፉ ነው በምድር በሀቅ መንገድ መንጎድ፣ መቼ ነው የሚፈቱሽ??? የእውነት አስበው ትንሳዔ እሚሰጡሽ........ @amharicpoem1221
Mostrar todo...
👍 3🥰 3
አባትነት እኮ ቅብዓ-ሰማያት ሆኖ ፣ ክህነት ቢረቅም ቃሉ: የሕፃን ትንንሽ እጆች ፣ ከካህን ይባርካሉ። ልጄ ሆይ ! አባትህን ባርከኝ ልጄ ሆይ! ፍቅሬ ሆይ! ላከኝ "አቤት!" ልበልህ "እንዳልከኝ" እርግብግብ ፣ልብ ርግብ ፣ የሚታዘዝ ልኮ አባትነት ልጄ ፣አባትነት እኮ የቆሙ መምሰል ነው፣ ድሆ ተንበርክኮ። ምጥን አለመጮህ ፣ ፍርሐትን መደለል እያሰቡ ኖሮ፣ ያላሰቡ መምሰል አብነት ነው ልጄ፣ የነገን ተላሚ ትሁት ቸልታ ነው ፣ ከቋሚ ጋር ቋሚ። አባትነት እኮ ፣ አባትነት ማለት ተኮሳትሮ መሮ ፣ ለመድኃኒትነት በልብ ማፍሰስ ነው ፣ የ' ሹሩሩ ጅረት እሹሉሉ ልጄ ... እምድነው እሹ እሹሉሉ ልጄ ... ትንሹ ቅዱሹ ኸለ ኸነ ገታ ፣ ኸለ ኸነ ሽኮ መኮለታተፍ ነው ፣አባትነት እኮ። @amharicpoem1221
Mostrar todo...
👍 5
▪1. eaes.et ላይ በመግባት Check Result የሚለውን በመጫን ማየት ይችላሉ! ▪2. በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር ) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በማላክ ማየት ይችላሉ! ▪3. በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ መመልከት ይችላሉ! ማየት ያልቻላችሁ admission number & School Code ከላይ ለተዘረዘሩ ልጆች በመላክ እንዲያይሏችሁ አድርጉ!
Mostrar todo...
👍 1
ከግጥም ባሻገር ዓለም እኮ ሰፊ ነች! ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡ ቀና በሉ! • ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ! • ከቡድናችሁ ውጪ ሌላ ቡድን አለ! • ከመስሪያ ቤታችሁ ውጪ ሌላ መስሪያ ቤት አለ! • በአካባቢች ካሉት ሰዎች ውጪም ሌሎች ሰዎች አሉ! • አሁን ካላችሁ የገቢ ምንጭ ውጪ ሌላ የገቢ ምንጭ አለ! ከፈጣሪ የተሰጣችሁን ሰፊ ዓለማችሁን አታጥብቧት፡፡ ምርጫችሁ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነ ስታስቡና በዚያ ዙሪያ ብቻ ስትሽከረከሩ ዓለማችሁ እሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ትጠባላችሁ፡፡ “ከዚህ ሁኔታ ውጪ መኖር በፍጹም አልችልም” ብላችሁ ያሰባችሁትን ሁኔታ በብዙ የሚያስንቁ ሁኔታዎች አሉ፡፡ “ከእነዚህ ሰዎች ውጪ በፍጹም መኖር አልችልም” ብላችሁ ካሰባችኋቸው ሰዎች በብዙ የላቁ ሰዎች አሉ፡፡ “ከዚህ ስራ ውጪ በፍጹም መኖር አልችልም” ካላችሁት የስራ መስክ በብዙ የተሸሉ የስራ እድሎች አሉ፡፡ አትወጣጠሩ! አትጨናነቁ! ለክክለኛው ነገር ታማኝ መሆናችሁን ሳትለቁ በዙሪያች ብዙ እድሎች እንዳሉ አትዘንጉ፡፡ @Amharicpoem1221
Mostrar todo...
🥰 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
✞ሁሉም ነገር ሆነ✞ መስቀሌን በመስቀል - እንዳለ በቃሉ በግሸን አደረ - ግማደ መስቀሉ ክርስቲያኖች ሁሉ - እንጓዝ ከደጅዋ ትኖራለችና - ድንግል ከነልጅዋ በገነት መስሎ - ጌታ ያስቀመጠው የአምላክ ተአምር ልኬት ስፍር የለው ግሸን ደብረ ከርቤ - የታቦር ተራራ ሁነሽ የተመረጥሽ - የመስቀል ማደሪያ እንማፀናለን - ከደጅሽ ላይ ሆነን ባንቺ አማላጅነት - ጌታ እንዲለመነን አሜን
Mostrar todo...
7
✞ሁሉም ነገር ሆነ✞ መስቀሌን በመስቀል - እንዳለ በቃሉ በግሸን አደረ - ግማደ መስቀሉ ክርስቲያኖች ሁሉ - እንጓዝ ከደጅዋ ትኖራለችና - ድንግል ከነልጅዋ በገነት መስሎ - ጌታ ያስቀመጠው የአምላክ ተአምር ልኬት ስፍር የለው ግሸን ደብረ ከርቤ - የታቦር ተራራ ሁነሽ የተመረጥሽ - የመስቀል ማደሪያ እንማፀናለን - ከደጅሽ ላይ ሆነን ባንቺ አማላጅነት - ጌታ እንዲለመነን አሜን
Mostrar todo...
​​​ህይወት:- ፍቅርን ታስተምርሃለች ጊዜ:- ማንን ማፍቀር እንዳለብህ ታስተምርሃለች  ሁኔታዎች:- ደግሞ ማን እንደሚያፈቅርህ ያስተምሩሃል። 👉👉ባለፈ ነገር ተማር እንጂ ተፀፅተህ አትለፈው‼️ መልካም አዳር🙌 @Amharicpoem1221 #ሼር አደራ🙏
Mostrar todo...
4
የተዘጋበት ቁልፍ (ኤፍሬም ሥዩም) የተዘጋን ጎጆ የተቆለፈን በር የተራበ ህፃን ለመክፈት ሲታገል በታላቅ ሰንሰለት የታሰረን አጥር ማን ዘጋው እያለ ጎበዙ ሲያማርር፡፡ ሌሊት ይመስለኛል ተኝቼ በህልሜ ካንድ ታላቅ ባህር አጠፋብ ላይ ቆሜ፡፡ የተዘጋውን በር የቆሙት ሲያንኳኩ ተስፋ የቆረጡት ወድቀው በየመስኩ፡፡ ተመልክቼ ነበር በትንሿ እድሜዬ ከእንቅልፌ ላይ ባለች በህልም ጊዜዬ። ለካስ በዚያች ሀገር…. እያንኳኳ ነበር ትውልድ የሚኖረው እልሁ በርትቶ በሩን እስኪሰብረው አዎ በዚያች ሀገር!... አባት በልጁ ላይ ቆልፎበት ነበር በእዳ በተሰራ በታላቅ ብረት በር። የዚያች ምስኪን ሀገር ቁልፉ ግን የጠፋው ከደጂ አልነበረም ውስጥ ጓዳዋ ነው፡፡ እውነት የትኛው ነው? ፍሬ ነው አበባ ወይስ የፍሬ ግንድ መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ እሚማገድ ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሚሰብረው ከተጠያቂነት ነፃ የሚባለው? እናም በዚች ሐገር መፍትሔ እሚባለው፣ ቁልፉን ማግኘት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው፡፡ እውነት የትኛው ነው? ፍሬ ነው አበባ ወይስ የፍሬ ግንድ መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ እሚማገድ ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሚሰብረው? አዎ በዚች ሀገር!... የእናቶች እንባ ሰማያትን ቀዷል የህፃናት ጩኸት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት፣ እንደ ጭቃ ሆኗል አዎ በዚች ሀገር… የሚያንኳኩ እጆች ቁጥሮች ጨምሯል ተስፋ የቆረጡ እርማችን ነው ያሉ ባህር ተሻግረዋል። እኛስ ለምንድነው ለዘመን ዘመናት በሩን የምንመታው ቁልፉን ዘግተውበት በዚች ሀገር እኮ! መፍትሔ እሚባለው፣ ቁልፉን ማግኘት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው!!! @amharicpoem1221
Mostrar todo...
👍 4 4
     ​​​​​​​​​​​​​​                   ❤️‍🔥 ጥርግ በይ😤 መስከረም ላይ መጥተሽ ጥቅምት የምትሄጂ አማራጭ አርገሽኝ የሆንሽብኝ ከጂ😏 አጥፍተሽ እየሄድሽ ይቅርታ ስጠይቅ እንድትመለሺ እግርሽ ላይ ስወድቅ😢 ወንድነቴን ደክሞ ባንቺ ፊት ሳለቅስ አንቺ እየተሳደብሽ ቀናውን ስመልስ💔 ሰው ሁሉ ገፍቼ ላንቺ ብዬ ስኖር ሄድ መጣ እያልሽ ማሰቢያዬ  ሲዞር☹️ ተወደድኩኝ ብለሽ ስትይብኝ ሞልቀቅ እውነት እልሻለሁ ዘጋሽኝ አንድ ቀን🤧 ድጋሚ ላታይ በፍቅር አንድ ሆነን አንዷ ወሰደችኝ ስትንከረፈፊ በይ ፍቅሬ አደረሠ በሌላም ሰው ቢሆን እንዳትታለፊ   ካንቺ የበለጡ ስንት ሴት አገኘው   ጥርግ በይ አሁን እረስቼሻለው 😏 @Amharicpoem ሼር አደራ🙏
Mostrar todo...
7🥰 1😁 1🤯 1
♥️ልቤ ቢጽፍልሽ🥰 ይኸውልሽ ውዴ... 😊 ዝም ብዬ ሳስበው ቃላት ጨርሻለው ወይ አልገዛ ነገር ወይ አልበደረው😟 ግን ውዴ ሳስበው እኔ ዝም ብልም ልቤ የሚልሽ አለው💗 ልቤ ቢጽፍልሽ ምን ይልሻል መሰል... ይድረስ ለሚወድሽ ለሚያስብሽ ሁሌ ምቴን ለጨመርሽው እኔን ያለ አመሌ💓🤗 ቆይ ለኔስ ማን አለኝ ምናለ ባየሽው ጓደኛዬ አንጀትን በልተሽ ጨራረሽው አልኮል ሲገለብጥ ወይ ቀን አይል ማታ ዘመዳችን ጉበት ይኸው መልኩን አጣ😮‍💨 ሚሥጥረኛዬ እንኳን የራስ ቅል ውስጥ ያለው አሁን ሁሉን ትቶ ሐሳቡ አንቺ ጋር ነው😔 ሁለቱ መንትዮች ስራቸውን ትተው ሌላ አላይ ብለዋል አንቺን አስበልጠው😊 እና አጫዋች ሳጣ እንዴት ነህ የሚለኝ ውድ ጎረቤቴ ቡና እንጠጣ አለኝ ግን ቤቱ ብገባ...🙄 ያ የሚያምር ቤቱ ደርሶ ማድ ቤት መስሏል ጣርያ እና ግድግዳው ሁሉ ነገር ከስሏል ምን አጋጠመህ ጃል ብዬ ብጠይቀው🤔 ፊቱን ከሰከሰ ዞር ብሎ ወደኔ እያለቀሰ🥺 በሷ ትዝታ ሀሳብ ሊገለኝ  ነው አለ ሲጋራ እያጤሰ ብሎ ቢያቀረቅር አንገቱን ቢደፍ ሰባራ ሥሜቴ ዳግሙን ተከፋ💔 ቶሎ አለው በይን አንድ ላይ ሳንጠፋ                                    ይኸውልሽ ውዴ❤️ የሚልሽን ነገር ልቤን ከሰማሽው ናፍቆት አይገድለውም ግን ሳይሞት አስታውሺው።❤️‍🔥 (ኪራ) @Amharicpoem1221 ሼር አደራ🙏
Mostrar todo...
3😁 1