cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የቡራዩ ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት

ይህ ገፅ የቡራዩ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት መልዕክቶችን ዘመኑ በሚፈቅደው መንገድ እንዲተላለፍበት በህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚመራ ይፈዋዊ ገጽ ነው። 📞+251944247165 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @finoteselam27 inbox አድራሻችን ነው።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 187
Suscriptores
+324 horas
-17 días
+3030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ቀዳም_ሥዑር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግስት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል ፩ ቀዳም ሥዑር ይባላል በዚህች ዕለት ከወትሮው  በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች እንጂ በዓል መሻርን አይመለከትም:: ይህች ዕለት እንደውም በጌታ ስቅለት የበለጠ ክብር ተሰጥቷታል ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ይሄን ሲገልጹ    " ዓለም መፈጠር በፈጸመ ጊዜ በሰንበት ቀን እንዳረፈ አሁንም ከድካምና ከመከራ ዐረፈ ከአርብ ምሽት እስከ እሁድ ሌሊት በመቃብር ውስጥ ተኛ ቀድሞ ዓለምን ከመፍጠር በማረፍዐ አከበራት አሁን ደግሞ የዓለም መድኃኒት በሞቱ ቀደሳት ቀድሞ በጸጋው ባረካት አሁን በመስቀሉ አተማት " ብለዋል ፪ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ ፫ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ቀዳም ሥዑር ደስታም ኃዘንም የሚታስብባት ዕለት ናት በዕለተ አርብ ጌታ እኛን ለማዳን ሲል የተቀበላቸውን ሕማማተ መስቀል እያሰብን እናዝናለን በፈጸመልን ድህነት ደግሞ ንሴብሖ እያልን እናመስግነዋለን " ገብረ ሰላም በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ " በመስቀሉ ሰላምን አደረገ ትንሣኤውን ገለጠልን እየተባለ የምሥራች ቄጤማ እየታደለ ይዘመርባታል ወደ ከርሠ መቃብር መወረዱን እያሰብን እናዝናለን የነፍሳት ከሲኦል መወጣትን እያሰብን እንደሰትበታለን። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Mostrar todo...
👍 1 1
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27) ---------- 45፤ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። 46፤ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። 47፤ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው። ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ። 48፤ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው። 49፤ ሌሎቹ ግን። ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ። 50፤ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። 51፤ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ 52፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ
Mostrar todo...
🙏 6
በዓለ ስቅለት በግብፅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዎድሮስ 2ኛ በተገኙበተት ተከብሯል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ከካህናትና ምእመናን ጋር በሥርዓቱ ተሳትፈዋል ። |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Mostrar todo...
👍 1
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት (የድኅነት ቀን) በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Mostrar todo...
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ------------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + ---------------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Mostrar todo...
👍 2😢 2
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል ----------------------------------- 1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር(በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ(በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)            + + + + + + + -------------------------------- |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
Mostrar todo...
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ወኆለቊ ኲሎሙ አዕፅምትየ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ (መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 21) ---------- 16፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። 17፤ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።
Mostrar todo...
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19) ---------- 14፤ ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓትም የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም። እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው። 15፤ እነርሱ ግን። አስወግደው፥ አስወግደው፥ ስቀለው እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም። ንጉሣችሁን ልስቀለውን? አላቸው። የካህናት አለቆችም። ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም ብለው መለሱለት። 16፤ ስለዚህ በዚያን ጊዜ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው። 17፤ ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። 18፤ በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። 19፤ ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ። 20፤ ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር። 21፤ ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን። እርሱ። የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። 22፤ ጲላጦስም። የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ። 23፤ ጭፍሮችም ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፍራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት፤ እጀጠባቡን ደግሞ ወሰዱ። እጀ ጠባቡም ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ እንጂ የተሰፋ አልነበረም። 24፤ ስለዚህ እርስ በርሳቸው። ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም። ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። 25፤ ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ። ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። 26፤ ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። 27፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። 28፤ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ። ተጠማሁ አለ። 29፤ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። " ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
Mostrar todo...
🙏 1