cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

yena Tube

@yeboLij

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
397
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🎯Telegram Update ከሆነ ቦኋላ ያመጣቸው አዳዲስ ገራሚ ፊውቸሮች🔥 🎙Protected Content in Groups and Channels🛡 ብዙዎችን ያስደሰተ በተለይ የTelegram ቻነል ና ግሩፕ ላላቸው ሰወች እንደምናውቀው Copypast እና Forward ለብዙ የቻነል Owneሮች ራስምታት ና ሲያስመርር የቆየ ነገር ነው አንዱ ላብን ጠብ አድርጎ ግዜውን ሰውቶ ቻነሉ ላይ የፃፈውን ማንኛውም Program ሌላኛው ዘና ፈታ ብሎ ወደ ራሱ ቻነል Copy past በማድረግ እራሱ እንዳዘጋጀው አስመስሎ ይለቃል ይሄ በራሱ የሚሰራውን ሰዉ Moral ይገላል አንዳንዶቹ ደግሞ Credit እያሉ Copy ና Forward ያደርጋሉ ከዚህ ቦኋላ ከማንኛውም ቻነል Copypast ና Forward ማድረግ አይቻልም. ቁርጥሽ እወቂ አዳሜ እስካሁን ያዛጋቹን ይበቃል😏 🎙Auto Deleted Message ይሄ ፊውቸር ደግሞ ለ አንድ ሰው መልክት ልከን ከ 24 ሰአት ከ 1ድ ሳምነንት ና ከ 1ድ ወር ግዜ ቦኋላ ከላክልነት ሰውዬ ጋር Automatically Deleted እንዲሆን የሚያስችል ነው. 🎙New emoji ለምሳሌ የአንድ ሰዉ Bio ላይ ይሄን emoji 💔 ብንመለከት በቀላሉ ስለ ሰውየው feeling Guess እናደርጋለን እንደሚታወቀው emojiወች የሰወችን Emotion ወይም ስሜት ከቃላት በማይተናነስ መልኩ ይገልፃሉ Telegramምም ይህን በመገንዘብ ሰወች በይበልጥ የተሰማቸውን ስሜት እንዲገልፁ አዳዲስ emoji አምጥቷል በጥቂቱ 😮‍💨😵🤝❤️‍🩹❤️‍🔥 🎙Delete My Message ይህኛው ፊውቸር ደግሞ ከ አንድ ሰዉ ጋር ካወራነው የChat History ላይ የኛን Message ብቻ ከላክልነት ሰውዬ ጋር ነጥሎ ያጠፋል🔥 የClear History እህት በሉዋት😆 🎙Change Color / Theme ይሄ ደግሞ የChat Background Color ና Themeን ለመቀየር ና ለማስዋብ የሚያስችለን Setting ሲሆን በፊትም ነበር ሲሆን አሁን ግን ተሻሽሎ በአዳዲስና ማራኪ Themeሞችና Background colors መቷል ሞክሩት 🎙Attach ከስሙ እንደምንረዳው Attach ማያያዝ ሲሆን ማንኛውንም ፃሁፍ ከPhoto ጋር አንድ ላይ ለማያያዝ ያስችላል ትንሽ ቀለል ብሎ መጣ እንጂ ድሮም ያለ ፊውቸር ነው እንደ ከአለም ጋለሪ የድንቃድንቅ የግጥም Channel ላላቹ Owneሮች ምርጥዬ ናት 👌 🎙Automatic Terminate ይሄ ፊውቸር ደግሞ ከኛ ስልክ ውጪ በሌላ ሰዉ ወይም በጓደኛችን ስልክ የTelegram አካውንታችንን Login ካደረግንና ከተጠቀምን ቦኋላ Automatically ከጓደኛችን ስልክ አካውንታችንን በራሱ Logout ያደርጋል እኛ Logout ማድረግ አይጠበቅብንም.🤗 ይሄ ሚሆነው ግን በገባንበት ሰው አካውንታችንን Automatic Terminate ከሞላን ነዉ 🎙Jump to Next Channel እንደምናውቀው አብዛኞቻችን Telegram ላይ የተለያዩ ቻነሎች ውስጥ join ብለናል ይሄ ፊውቸር ምንድነው የሚያደርገው አንድ ቻነል ላይ ተገብታቹ የሆነ ነገር እየተመለከታችሁ ወይም እያነበባቹ ወደ ሌላኛው ቻነል ለመሄድ ከዛ ቻነል መውጣት አይጠበቅብንም የስልካችንን Screen ወደ ላይ Scroll ስናደርገው ወደ ሌላኛው ቻነል ይወስደናል or ያልፋል🚀 🎙Live Stream live stream is a one-way video broadcast System. Live Stream ማለት ባጭሩ ቀጥታ ስርጭት ማለት ነው ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሲያዘጋጅ እኛ ቤታችን ሆነን በቀጥታ በTvያችን ቴዲን እንመለከታለን እሱ ግን እኛን አያየንም ቴዲ መመልከት የሚችለው ኮንሰርቱን ላይ የታደሙትን ነው ስለዚህ Live Stream የተባለው Technology አንድን ሰው የትም ቦታ ሆነን በTv በTablets በስልክ ቀጥታ መከታተል ያስችላል ኮንሰርቱን ታደምን ማለት ነዉ Telegram ይህን ፊውቸር ነው ያመጣው 🙈 🎙Flexible Forwarding ይሄ ፊውቸር ጥቅሙ ለምሳሌ አንድ ሰዉ message ቢልክልን ያን መልክት ለሌላ ሰዉ ሶስተኛ ወገን ስልንክ መጀመሪያ የላከውን ሰው Name Hide ያደርጋል ይሄ ደግሞ መጀመሪያ ላይ ለላከው ሰውዬ privacy ደህንነት የተጠበቀ ያደርገዋል.🤟 🎙Unpin All Message ቻነላቸን ላይ Pin ያደረገውን Post በሙሉ በአንዴ Unpin ለማድረግ የሚያስችል ፊውቸር ነው እያንዳንዱን Post Unpin ከማድረግ ይታደገናል😎 Telegraph ሌሎችም ብቹ ገራሚ ፊውቸር አምጥቷል Telegram በዚህ ከቀጠለ Social mediaውን መቆጣጠሩ አይቀርም Facebook IG Twitter WTs'App የመሳሰሉት ላይ የሌለ ፊውቸር ነው እያሳየን ያለው Developeሮቹ ማሻሻያውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል👍
Mostrar todo...
አልፋና ከሪማ ክፍል_አንድ የገዘፈው ሁኔ ከመቸው ረገደ አንቺን አንቺን ሲል በሀሴት ነደደ 😭 ከዋክብት ብቅ ሳይሉ ጨረቃ ቀደመች ቀኑን ሙሉ ሀይሏን ዝቅ እያረገች እየጨመረች ስትንበለበል የነበረችዋም ፀሀይም ሰማዩ ላይ ሌላ ምህዋር በመተካት ተሰለበች ታችኛዋ ምድር ላይ ያለሁት እኔ ግን ቢመሽም ቢነጋ ሂወቴ ይቀጥላል 😊😊 በተፍጥሮየ ከየዋህነት ባህሪ ፍፁም የራቅኩ ነኝ ራሴን ከሁሉም በላይ በመውደዴ የብዙወችን ጥላቻ ባተርፍም ለማንም ግድ አለመስጠቴ ኩራት ሚሉትን ባህሪ እንዲለጥፉብኝ አስገድዷቸዋል 😐 ከማንም የውጭ ሰው ጋር የሳቅም የጨዋታም ምሳሌ አይደለሁም ጭምት ማይፈታ ሰው እንጂ ምናልባት በሂወቴ ቅርብ ከሆኑ ሰወች ጋር እንጂ ፍፁም ሌሎች ጋር ቀረቤታ የለኝም !! የሳምንቱ የመጀመሪያ እለት ላይ ነኝ በእሁዱ የእረፍት ቀን ገና በማለዳው ፀሀይ እንኳን በቅጡ ሳትወጣ በሩ እየተንጋጋ ሰሚር የሚል ድምፅ ይሰማል ልክ በሩን ሲከፍቱት ይህ ቀውስ የሆነ ልጅ ነው የሰው ልጅ እንዴት በዚህ መልኩ አእምሮውን እስኪስት እብድ ብሎም ኬር ይሆናል ሲፈጥረው ለሰው አትጨነቅ የልብህን ስራ ብሎታል በዛ ላይ ምንገድ ላይ እየጮሀ ሲያወራ ሽምቅቅ ያረገናል ከጉሮሮ በታች ማያስቅ ቀልዱን እየቀለደ ለብቻው ይስቃል ማሜ እና አብዱ ለሞራሉ ቢስቁም እኔ እንኳን ጥርሴ ሊከፈት ፊቴ ላይ (ምንድነው ሚጃጃለው) አይነት ስሜት ይነበባል አይ ማሂር ቶሎ በሩ እንደተከፈተለት ገባና ግቢ ፀጉሬን እየታጠብኩ እያለ ሰሚር ሰሚር 😳 ዛሬ የአብዱ አክስት ብር ልካለች ቶሎ ለባብስና ፈታ ስንል እንውላለን እየጠበቁን ነው አለኝ ☺️ ሳምንቱ የተመታ ሳምንት ስለነበ ነው መሰለኝ በጣም ደስ አለኝ ምንም ሳልመልስለት ክፍሌ ገባሁ ልለባብስ ስዘገጃጅ እንደድንገት አባየ ( ጋሽ አህመድ )ሰሚር የት ልትሄድ ነው አለኝ ? እኔም ማሂ ጋር መሆኔን ነገርኩት አባየ ሲበዛ ጠርጣራ እና የተረጋጋ ሰው ነው በኢስላሚክ ተርቢያ ልጆችን ለማሳደግ ሁሌም ይጥራል ነገር ግን እንደአዋዋልህ እንጂ እንደምትመከረው አይደለም መቼስ🤷‍♂ ልክ ለባብሼ እንወጣሁ ያየሁትን ማመን ከበደኝ ማሜ ቪትዝ መኪና ይዞ አብዱ ጋቢና ነበረ ዛሬማ ልዩ ቀን ነው ብየ እየሮጥኩ ገባሁ አንተ ቀውስ ከየት አባህ አመጣህ ስለው ማሂሩ ፈጥኖ ትናንት ተከራይቷት ነው አለኝ እና ትንሽ ሁላችንም ዝም ካልን በኋላ አንድ ላይ ጋቢና ወዳለው አብዱ ዞርን ከዛም ማሜ የዛሬው ሙሽራችን አብዱ ነው አክስቱ ብል ልካለች አለ ስንት አስገባች ስለው አብዱን ትከሻውን እየመታሁ ብሩን ሳይነግረኝ ሰሚርየ ዛሬ በአል ነው በቃ አለኝ ውይ ሳልነግራችሁ ስሜ ሰሚር አህመድ ይባላል ሰሙ እያሉ ሲጠሩኝ ያመኛል🙄 ምክኒያቱም ሰሚራንም ሲያቆላምጧት ሰሙ ነው 😏 ማሜ አብዱ ማሂሬ ፉአድ የሌለ ሚጃለሱኝ ጓደኟች ናቸው ፉአድ እንኳ ድሬ ዩኒቨርስቲ ሂዷል አሁን እሱ የለም ለማንኛውም በማሜ ጊዜያዊ መኪና መሄድ እንደጀመርን ማሂ ከተፍ ብሎ የቪትሷን ብሉትዝ አገናኘው እና የሆነ በደንብ ማይሰማ እንጉርጉሮ ከፍቶ እናሽቅ እያለ ጭንቅላቱን ማወዛወዝ ጀመረ እኔና አብዱ ወዲያውኑ ጮህንና አቦ አታላዝንብን ቀይረው አልነው ማሂሬ የሀድራ ሰው ነች አረንጓዴ ልብስ ለብሳ ማበድ ነው ስራዋ ከኛ ውስጥ የዲን አዋቂው አብዱ ነው ከሱ ጋር ሁሌ ይከራከራሉ ይጨቃጨቃሉ እኔ ብዙም አይገባኝም ብቻ ሁሌም ክርክራቸው ሚያልቀው በማሂር አንተ የነቢ ፍቅር ገና መች ገባህ በሚል ትችቱ ነው እንደምንም በማላዘኑ አሳምኖት ድቤ እንኳን በሌለው እንጉርጉሮ እያዛጋን ደረስን ማሜ እንኳን ኤርፎኑን ሰክቶ ለራሱ የፈረንጅ ዘፈን ይሰማል እሱ ምን ግድ ሰጠው 🙄 የት እንደምንሄድ ሳይነግሩኝ የሆነ ቦታ ላይ ወረድን ምን የመሰለ ቦታ ገባን ውስጡ ሜዳ ነው ስክሪን ተገጥሞ ፊልም ሚያይ አለ ሚዝናናም አለ ድንቅ ቦታ ነው እዛ ቀኑን ሙሉ ስንዝናና ቆይተን አምሽተን ተመለስን እንደተመለስኩ ጫማየን አውልቄ ለጥ ነው ያልኩት ማይነጋ የለምና ለሊቱ ተሰውሮ በንጋቱ ተቀሰቀስኩ ልክ ከእንቅክፌ ስነቃ ፊትለፊቴ አባየ ቀጥ ብሏል ትናንት ለምን አመሸህ? ሚል ጥያቄ ሰነዘረ ዛሬ ፈጅር ለምን አልመጣህምም አለኝ ? እኔም በቴ ልስገድ ብየ ነው ብየ ዋሸሁት ሰላት ላይ ያለኝ አቋም ቀጥ ያለ ባይሆንም ፈጅር ከፋዘር ጋር ሁሌ ነው ምወጣው ፈዘዝ እንዳልኩ ልብሴን ቀያይሬ ወደ ትምርትቤት አቀናሁ ክላሰ ውስጥ ኮስታራ ነኝ አረ ሂወቴ መኮሳተር በሉት ከጓደኞቼ ፊት ካልሆነ ለማንም ፈገግ እንኳን አልልም ወንዶቹ በዚ ባህሪየ ቀና ብለው አያዩኝም ሴቶቹ ብዙወቹ እንደምመቻቸው እና ወንድ ማለት እንደኔ እንደሆነ ይገልፃሉ በፍፁም ዞር ብየ አይቻቸውም አላውቅም ለቤታችን ብቸኛ ልጅ ስለሆንኩ ብዙም የእህትነት የወንድም ትርጉም አልገነዘብም ድርቅ ያለ ልቦና መገለጫየም ነበር መልኬ ጠየም ብሎ ፀጉሬ የበዛ ብዙም ያልደረቀ ሉጫም ያልሆነ ሚያምር ፀጉር ከደስ ደስ መልክ ጋር ተሰጦኛል ከክፍላችን ልጆች አረ ከትምርትቤቱ የወንዳወንድ መገለጫ የውበት ምሳሌ ነኝ ግን እኔ ብዙም ለዚ ግድ አይሰጠኝም🤷‍♂ የሰው ልጅ ብዙ ሚያዝናናው ነገር አያስደስተኝም ዛሬ መክሰስ አብዱ ልጋብዛቹህ ብሎ ቤቱ ሂደናል ልክ ቤቱ እንደገባን ትንሿ ኢልሃን ማሜ እና ማሂር ላይ ተጠመጠመች እኔ ላይ ብዙም የደስታ ስሜት አላሳየቺም ትንሽ ቅናት ቢጤ ፈጠረብኝ ግን ወዲያውን ረሳሁት ኢልሃን የአብዱ ብቸኛ እህቱ ናት በጣም ደስምትል ተግባቢ ምላሳም ህፃን ልጅ ናት እነ አብዱ ከእናታቸው ጋር ነው ሚኖሩት ያው እናታቸው በንግድ ታስተዳድራቸዋለች ከመካከላኛ ትንሽ ዝቅ ያለ ኑሮ ይኖራሉ ፍቅራቸው ደስ ይላል አብዱ እኛጋ አይማርም ኢስላማዊ መድረሳ ሚሉት የሆነ ሀይማኖታዊ ቦታ ነው ሚማረው እዛ ትምርትቤታቸው ሁሉም ይወደዋል ጎበዝ ተማሪም ነው የዲን እውቀት ላይ ጎበዝ ነው ብር ዘመዶቹ ይልካሉ ማሜም ማሂም በሆነ ምንገድ ብር ያገኛሉ እኔ ግን ብዙም አይደለሁም ድንገት ግን ወደቤት ስመለስ ስራ ምሰራበትን ምንገድ ቤት ላማክር አሰብኩ ምክኒያቱም በገንዘብ እጥረት በጣም ብዙ ነገር ሚስ እያረኩ ስለሆነ በዛሬው እለት ምሽት ሁሌ አእምሮየ ላይ ያለ ጥያቄ ለአባየ ልጠይቀው ወስኜ ነበር ምንም ብፈራው ምላሹ ምን ቢሆን መች ስራ መጀመር እንዳለብኝ ልነግረው ወሰንኩ አባየ ጋር ማታ ራት እየበላን አባየ አልኩት በለዘበ ድምፅ ወየ ልጄ አለኝ አባየ ስራ መስራት እፈልጋለሁ አልኩት ቀጥታ እሱም አፍጦ ካየኝ በኋላ ለምን አለኝ ትንሽ ግራ አጋባኝ ድንግጥ ብየ አረ ለምንም ብየ ክፍሌ ገባሁ ትንሽ ክፍሌ ውስጥ ማሰብ እንደጀመርኩ በሩ ተንኳኳ አባየ በመቆጣቴ መጦ ነው ብየ ስከፍት አሚ ናት እናቴ ከሁሉ በላይ ትረዳኛች ለኔ መሸፈን እንጂ ፈፅሞ ጫና አታበዛብኝም አትቆጣኝምም ጭምር ትከሻየን እያሸች እንዴት ይህን ጥያቄ አነሳህ ሰሚሬ አለቺኝ ከዛም በመገረም የራሴ የሂወት ምእራፍ እና ጎዳና የለኝምን ? እኔስ ወደፊት ሂወትን መኖር ገንዘብ ማግኘት አያምረኝም አልኳት ከዛም ትምርት ሳጨርስ ምን አይነት ችኩልነት ነው ከየት አመጣሀው አለቺኝ እኔም እየሰራሁም መማር እንደምችል ያለሁበት ሁኔታ ብር ሚያስፈልገኝ ዋና ሰአት ላይ እንደሆንኩ ነገርኳት ትምርቱም ላይ ሁላችሁም ፍላጎት እንደሌላችሁ አውቃለሁ አልኳት....
Mostrar todo...
👍
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ፬ እርምጃ °°°°°°°°°° [ናዝሬት] ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው ስሰክር ስሰክር ወይ ሲለኝ ድንግር ግር እኔ የምራመደው። እህ በይኝ እና ልንገርሽ አንቺዬ ስሚኝ ባዛኝቱ ባይጥምም አይመርም ያፍቃሪ እውነቱ የናፍቆት ዝለቱ እህ በይ እህ በይ እህ በይ በማርያም ሰሚው እውነታዬን ስሰክር ስከፋ የምረግጠውን ሃቅ የውነት እርምጃዬን በጎዳናው መሃል በድንጋዩ ንጣፉ ካብታሞቹ ሰፈር ስኔድ ትዝ ካለሽ ወሬ ስንረሳ ወሬ ስንጀምር ምነዋ አንቺዬ እንደውም ፍጡራን አለም ከሰሩበት በከተማ መሐል ገነት የሚመስል አነስተኛ ገነት ከቆረቆሩበት አዎን እዛ ሰፈር አንድ ሁለት ብዬልሽ ባየሁት ያልሽውን ስካር ሰክሬልሽ ቆምያለው ብቻዬን አንቺን እያሰብኩኝ ለሊቱ ተጋምሷል ለኔ ግን ነጋልኝ ሰሞኑን አንቺዬ ያመጣሁት ፀባይ ለሰው ሲጨልም ነው እኔ ንጋት የማይ ብቻ ቆሜ ሳለው ድንጋዩን አየሁት የጎዳናውን ጠርዝ ባሳቤ ውስጥ አየው የፍቅርን ስንደዶ ከሰፌዱ ስንመዝ ቱ.. አፌን እሳት ይፍጀው ታቦት ፅላቴን ነው ድንጋይ ነው የምለው? ያ ድንጋይ ለኔማ ከአክሱም በላይ ነው ፍቅርሽ እና ፍቅሬ በፍቅር የጠረበው ያ ድንጋይ ለኔማ የምስጢር ፅላት ነው በስውር መዳፋ ስውር ድብቅ ህመም እግዜር የቀረፀው ሙሴው የኔ መዳፍ ናፍቆት ሊሰባብር ለሁለት የከፈለው እናም ይሄ ፅላት የጎዳናው ማዕዘን ከንፈር አነካክሶ ዙፋን ሲሸልመን በንግስና ዳና የረገጥነው ወጉ ያ ነው ለኔ ማለት የ1 እርምጃ ጥጉ ... የሰካራም ነገር ምን አስቀባጠረኝ ብቻ ምን አለፋሽ ከዚሁ ድንጋይ ስር እርምጃ ጀመርኩኝ ..... ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው ናፍቆትሽ ሲመራኝ እኔ ምራመደው ፅላቴን አልፌ አይኔን ስወረውር ልቤ ተላተመ ከአንድ ደጅ እግር ስር እግዜር ይቀድሰው የደጃፉን ሰሪ ያፀዱን ባለቤት ከበራፉ አብቧል የፍቅራችን ትንፋሽ የፍቅራችን ሂወት ለኔና ለልቤ ላንቺና ለልብሽ ከለላ ለመሆን ጥላውን የጣለው እሳት ከከለለው ከገነት ደጅ ይልቅ ይሄ ደጅ ንዑድ ነው እርምጃ ቁጠሪ ከደጁ ትይዩ እስከ ማርያም ድረስ ሁለት ይቀረናል ፍቅርሽን ለመሸሽ ፍቅሬ ጋ ለመድረስ ---------------------------- ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው ስሰክር ስሰክር ወይ ሲለኝ ድንግር ግር እኔ የምራመደው። እህ በይኝ እና ልንገርሽ አንቺዬ ስሚኝ ባዛኝቱ ባይጥምም አይመርም ያፍቃሪ እውነቱ የናፍቆት ዝለቱ እህ በይ እህ በይ እህ በይ በማርያም ሰሚው እውነታዬን ስሰክር ስከፋ የምረግጠውን ሃቅ የውነት እርምጃዬን ሶስተኛው እርምጃ ከሁሉም ይልቃል እዚኛው ገፅ ላይ ልቤ ምት ያቆማል ምክኒያቱም አለሜ ይሄ ሰፈርሽ ነው የግዛትሽ ጥለት በሌት አነደደኝ የፀሐይሽ ግለት ሰማይ በዚ ቦታ ሁሌም የጠራ ነው ጨለማውን ሊገልጥ ኮከብ ጨረቃ ነው 360 ቀን ፀሐይ አትዞርም ለ30 ቀናት ጨረቃም አትጎልም እንደ ፀባኦቱ ልክ እንደ ማደርያው የመቅደስ እጣን ነው የዚ ሰፈር ሽታው ለካንስ በሌሊት እንደኔ ሲሰክሩ እዚ ሰፈር አለ የመለኮት ክብሩ ብቻ ምን አለፋሽ የዳዊት በገና የእዝራ መሰንቆ እዚ ሰፈር አለ ቤትሽ ተደብቆ በቦዘዘው አይኔ እጣኑን ብጠራ እግዚያርን ባየው አልጠየቅ እኔ ይሄ ሰፈርሽ ነው የማይጠፋው ፋኖስ የማያልቀው ሻማ በርምጃዬ መሐል አለ ፍቅርሽ ' እማ ' ሰሶስተኛው እርምጃ እንደተረገጠ ነጋ መሰል ሌቱ ድሮስ ከሰፈርሽ አይደለም አለሜ የዚ ንጋት ቤቱ? ----------------------------- ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው አይንሽን ስራበው ክንድሽን ስራበው ልብሽን ስራበው እኔ የምራመደው። አራተኛው ዱካ የልቤ ማረፍያ የእመቤቴ አፀድ የልፍኟ መኖርያ ድሮም የፍቅር ገፅ ሲነበብ አርስቱ ልብ ነው የሚደርስ ከገፁ ፍፃሜ ከማርያም ከእናቱ ከቦሌ እስከ ማርያም አራት እርምጃ ነው ልቤ ደጇን ሲራብ እናት ሲናፍቀው እግሬ የሚራመደው አናጭ አፍራሽ ልጅሽ የመንገዱ ጌታ የርምጃ ፈጣሪ ቅድስት የተባረክሽ አስታርቀሽ አዳሪ ታድያ ከደጃፍሽ ጋን የሚያስንቅ ልሳት የረከሰ ገላ ይዤ ምቆምበት አላገኝም ጥላ ይልቅ ተሻግሬ ከመንገዱ ማዶ እኔ ልጅሽ አለኝ የምነግርሽ ብስራት የማረዳሽ መርዶ - ብስራት የምስራች ማርያም የማፈቅራት ፍቅሬ ያቺ ውብ አበባ ልትሞሸርልሽ ከደጃፍሽ ቀርባ ቀናቱን ቆርጣለች እናቴ ጠብቂያት ተክሊል አዘጋጅተሽ - መርዶ ከሰፈሬ ደጅሽ እስክመጣ ድረስ የረገጥኩት መንገድ ያደከመኝ እግሬ ስካሬም እስኪበርድ ከዚው ከደጃፍሽ እንዳታስጠልይኝ እማምላክ እናቴ ፍቃድሽን ስጪኝ ስለ እማምላክ ብዬ ልብ እያራራውኝ ጉርሴን እንድበላ ስምሽን አውሽኝ በንተ ስምሽ ልኑር እስኪለቀኝ ስካር ፈቅደሽ ካደረግሽኝ ያድባርሽ ስር አድባር ልመና ነበረኝ ስለ ቸርነትሽ ለኔ ተለመኝኝ እማምላክ እባክሽ አበርችኝ እናቴ ልቤ እንዳይዝልብኝ ሰርጓን ባላደምቅም እንቅፋት እንዳሎን ቀናት ለምኝልኝ። ተፈፀመ። ALONE : @yeboLij ©ቅንጭብጭብ ኢትዮጵያ
Mostrar todo...
ትግራይ : በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተመድ እና የኢሰመኮ ምርመራ ይጀምራል ! ኢሰመኮ ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ጋር በመሆን፣ በትግራይ ተፈጽመዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የሚደረገው ምርመራ ኢትዮጵያውያን ተጠልለው የሚገኙበትን ሱዳን ሊጨምር እንደሚችል መገለፁን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ሁለቱ ተቋማት መጋቢት ወር አጋማሽ ነበር በትግራይ ተፈጽሟል የተባለውን የመብት ጥሰት በጋራ ለማጣራት ስምምነት ላይ የደረሱት። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ከሁለቱ ወገን ከእያንዳንዳቸው 6 የመርማሪ አባላት ያካተተ የባለሙያዎች ቡድን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ የተመረጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች እንደሚያመራ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጸዋል። ዶ/ር ዳንኤል ፥ ስምምነቱ ከተደረገ ጀምሮ የመርማሪ ቡድኑ አባላት ለምርመራ የሚያስፈልጉ የቅድመ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቦታ ልየታ፣ የምርመራ ሥልቶችን መለየትና የትራንስፖርት ሁኔታዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። ከ12 የመርማሪ ቡድኑ አባላት በተጨማሪ የሕግ፣ የሥርዓተ ፆታ፣ የደኅንነትና የትርጉም ባለሙያዎችን ጨምሮ የምርመራ ቡድኑ 30 ያህል አባላት ሊኖሩት እንደሚችል ገልጸዋል። የምርመራውን ነፃነትና ገለልተኝነት ለማረጋገጥ ሲባል የመርማሪ ቡድኑ አባላት የሚሄዱበትን ቦታና አካባቢ ከመጥቀስ ቢቆጠቡም ፣ እንዳስፈላጊነቱ ምርመራው በሱዳን የተጠለሉ ኢትዮጵያዊያንንም ሊያካትት እንደሚችል ግን ጠቁመዋል። ምርመራውን ለማከናወን ሦስት ወራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ካለው ሁኔታ አኳያ ከእዚያም በላይ ሊጨምር እንደሚችል መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። @yeboLij
Mostrar todo...
* Update የአውሮፓ ህብረት በፍልስጤም እና በእስራኤል ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ሊቀመጥ መሆኑ ተሰምቷል። የህብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የፊታችን ማክሰኞ በቪድዮ ስብሰባቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ግጭቱ በሚቆምበት መንገድ ዙሪያ ማድረግ ስላለባቸው አስተዋፆ እንደሚወያዩና እንደሚመክሩ ጆሴፕ ቦሬል ገልፀዋል። በሌላ በኩል ዛሬ ጥዋት እስራኤል በጋዛ የሚገኘውን የሀማስ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ክንፍ መሪው ዬይያ አል-ሲንዋር መኖሪያ ቤትን በአየር ጥቃት መደብደቧን የሀማስ ቲቪ ገልጿል። በተጨማሪ እስራኤል ዛሬ በጋዛ በፈጸመችው የአየር ድብደባ የ26 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ በርካቶች መቁሰላቸው እና ህንጸዎች መውደማቸው ታውቋል። ትላንት ለሊቱን ከሀማስ ወደ እስራኤል ከተሞች የሚወነጨፉት ሮኬቶች የቀጠሉ ሲሆን ያደረሱት ጉዳት እንደሌለና እስራኤል በአየርን ዶም መከላከል እንደቻለች ተገልጿል። ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገራቸው ጦር በጋዛ የሚፈፅመው የአየር ጥቃት አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ንፁሃን ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸውም የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነም ተናግረዋል። ኔታንያሁ፥ ‘’አሁን ለተፈጠረው ፍጥጫ ጥፋተኞቹ እኛ አይደለንም፤ እኛ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት ናቸው’’ ሲሉ ተደምጠዋል። አሁንም ባልበረደው እና መፍትሄ ባላገኘው የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት በፍልስጤም በኩል የሟቾች ቁጥር 170 ደርሷል፤ ከነዚህ ውስጥ 41ዱ ህፃናት ናቸው። በእስራኤል በኩል ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 10 ሰዎች ተገድለዋል። በዌስት ባንክ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በትንሹ 13 ፍልስጤማውንን መግደላቸው ተሰምቷል። የተመድ የፀጥታው ም/ቤት ዛሬ በእስራኤልና በፍልስጤም ጉዳይ ስብሰባ ያካሂዳል። መረጃው የተሰባሰበው ከቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ቲአርቲ ወርልድ ነው። @yeboLij
Mostrar todo...
Facebook_Watch(240p).mp42.84 MB
VID_20210516_131828_140.mp41.14 MB
አስገራሚ የእንሰሳት እውነታዎች! *********************** 1. ቀበሮ በሂወት ዘመኑ አንዴ ብቻ ነው ፍቅረኛ ሚኖረው። ምን አልባት ሚስቱ ከሞተች ቀሪ ሂወቱን ብቻውን ነው የሚያሳልፈው! ምስኪን ታማኝ!! 2. የጂብ እድሜ ጣራ 80 ዓመት ነው! 3. አይጦች የራሳቸውን ያልሆነ ልጅ አጥብተው ያሳድጋሉ! 4. የወባ ትንኝ 47 ጥርሶች አላት!!!! 5. ፍየሎች ሴቷን ፋየል ለማማለል ሲሉ እርስበእርስ ይዋጋሉ!!!!! 6. ድመት በሂወት ዘመኗ እስከ 100 ግልገሎች መውለድ ትችላለች!!!! 7. እንደ ሰው ህልም ማየት ሚችለው አንስሳ ፈረስ ብቻ ነው!!!! 8. ዳክየ እንቁላል የምትጥለው ጧት ጧት ብቻ ነው!!! 9. የሌሊት ወፍ ጆረዋ ከተደፈነ መብረር አትችልም!!!! 10. ጊንጥ 12 አይኖች አላት!!!! 11. አዞ ምላሱን ወደውጭ ማውጣት አይችልም!!! 12. ሴት ካንጋሮ ከወንዱ ምትለየው በደረቷ ባለው ከረጢት ነው!!! 13. አይጥ ያለምግብ 14 ቀን መቆየት ትችላለች!! 14. አለም ላይ የመጀመሪያው ለማዳ እንስሳ ውሻ ነው!! 15 .የጊንጥ መርዝ ጊንጥን ሲገድል የእባብ መርዝ ግን እባብን አይገድልም!!! 16. በአንድ ጉንዳን መንጋ ውስጥ እስከ ግማሽ ሚሊየን ጉንዳኖች ሊኖሩ ይችላሉ!!! 17. ማንኛውም ስጋ በል እንስሳ በመብረቅ ተመትቶ የሞተን እንሰሳ አይበላም!!! 18. ቢራቢሮ 12, 000 አይኖች አሏት!!! 19. የመሬት ትል 5 ልቦች አሏት!!! የትኛው ግርምት ፈጠረባቹህ? ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!!!!!!!!! ሼር
Mostrar todo...
Megerm Tarek New Anbebut
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.