cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ... 👇👇👇👇👇👇👇👇 👉 @behlateabew 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆 https://t.me/+RICJUxY54uwNbPXe

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
10 786
Suscriptores
-624 horas
-217 días
-5830 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
ክርስቶስ ተነሥቷል(Christ Risen) በሚለው ቃል ውስጥ ያለው መንፈሳዊ ኀይል። በአባ ዮሐንስ ገባሬ መንክራት (St. Jonh Maximivotch) የተደረገው ተአምር። አባ ዮሐንስ ገባሬ መንክራት በአንድ ወቅት የብርሃን ሳምንት ተብሎ በሚታወቅበት ሳምንት አንድ የታመመ ኦርቶዶክዊ ምዕመንን ለመጠየቅ ጉዞውን ወደ አንድ የአይሁዳውያን ሆስፒታል ያደርጋሉ። አባ ዮሐንስ በሆስፒታሉ በአንደኛው ዋርድ ፊትለፊት ሲያልፍ ድንገት ቆመና በመጋረጃ በተሸፈነው ክፍል ውስጥ አንዲት አይሁዳዊት አሮጊት ሕይወቷ አልፏል በመባሉ ሸፋፍነዋት አልጋ ላይ እንዳስተኟት ይረዳል። አባ ዮሐንስ ገባሬ መንክራት ድንገት ከተጋረደው ክፍል ፊትለፊት ቆመና ቅዱስ መስቀሉ አውጥቶ ድምጹ ከፍ አድርጎ ጮኸና "ክርስቶስ ተነሥቷል" እያለ በመስቀል ምልክት እያማተበ ተናገረ፣ ድንገት ይኸንን በሚያደርግበት ወቅት ሞተች የተባለችዋ እናት አእምሮዋ ተመለሰላትና ቃል አውጥታ ውሃ ስጡኝ ብላ ጠየቀች። አባ ዮሐንስም አንዷን ነርስ ጠራት እንዲህ አላት ታማሚዋ ውሃ እየፈለገች ነው ብሎ ሲነግራት ይኸንን የሰሙ የሆስፒታሉ ሠራተኞችም አስቀድማ አርፋለች ተብላ የነበረችው ታማሚዋ ባሳየችው አስገራሚ ለውጥ በጣም ተደነቁ ከዚያ በኋላ ታማሚዋም በተደረገላት አስደናቂ ተአምር ተሽሏት አገግማ ከሆስፒታሉ ወጥታ ወደ ቤቷ ሔደች። አባ ዮሐንስም በክርስቶስ የትንሣኤው ኃይል በማያምኑት መካከል አስደናቂውን ተአምር አደረጉ። አቤቱ ሆይ የትንሣኤህ ኃይል ይገለጥ ሰይጣን ከነ ሠራዊቱ ይሸነፍ፣ ሞትም ከነ መውጊያው ይወገድ፣ ሲኦልም ከነ ድል መንሣቷ ትሻር፣ ኃጢአት እና አለማመን ከእኛ ይራ፣ ሕይወታችን የተቀደሰች ትሁን ዙሪያችን በትንሣኤው ኃይል በትንሣኤው ብርሃን የታጠረ ይሁን። ክርስቶስ ተነሥቷል በእውነት እርሱ ተነሥቷል።
64911Loading...
02
[•• አምስቱ ትንሣኤዎች••]        •••••••••••••• ‹‹...በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡›› ራእ ፳ ፥ ፮ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት «ትንሣኤን» በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲያመሠጥሩት በአምስት ዓይነት ትርጉም ያስቀምጡታል፡፡ ይኸውም ትንሣኤ ኅሊና፣ ትንሣኤ ልቡና፣ ትንሣኤ ሙታን፣ ትንሣኤ ክርስቶስና ትንሣኤ ዘጉባኤ በሚል በአምስት መንገድ ይከፈላል። ፩ኛ. ትንሣኤ ኅሊና ነው ይህ ትንሣኤ ኅሊና ተዘክሮተ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ማሰብ) ማለት ነው። ሙሴ በኦሪቱ ‹‹እመኒ እንዘ ተሐውር ወእመኒ እንዘ ትትነሣእ ኢትርሣእ ተዘክሮተ እግዚአብሔር፡፡ ስትሄድም ስትነሣም እግዚአብሔርን ማሰብ አትርሣ›› ብሎ ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንደተናገረው። ፪ኛ. ትንሣኤ ልቡና ነው፤ ትንሣኤ ልቡና ደግሞ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ማለት ነው:: ይኸውም ሰው ሁለት ጊዜ ይሞታል፤ ሁለት ጊዜ ይነሣል፤ የሰው ልጅ የመጀመሪያው ሞቱ ኀጢአት መሥራቱ ከእግዚአብሔር መለየቱ ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሥጋ ፍትወት በምድራዊ ቅንጦት የሚቀማጠሉትን ሲናገር ‹‹ቅምጥሊቱ ግን በሕይወቷ ሳለ የሞተች ናት›› ፩ኛ ጢሞ ፭ ÷፲ ፯ ሲል በኀጢአት መኖር ትልቁ ሞት እንደኾነ ነግሮናል፣ ሁለተኛው በሥጋ መሞቱ ነው:: ስለዚህ ሰው ሁለት ጊዜ እንደሚሞት ሁለት ጊዜ ይነሣል፤ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ትንሣኤው እንዴትና ምን እንደሆነ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ሲል ነግሮናል፤ ‹‹ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡›› ራእ ፳ ፥ ፮  በማለት ንስሐ ገብቶ ከእግዚአብሔር ታርቆ ትንሣኤ ልቡናን ገንዘብ ያደረገ ሰው ሞተ ሥጋንና ሞተ ነፍስ ድል ነሥቶ እንደሚኖር ነግሮናል፡፡  ለትንሣኤ ልቡና ትልቅ ምክር የሚሆነን በሉቃስ ወንጌል የተመዘገበው ታሪክ ነው፤  ‹‹ይህ ልጄ ሞቶ ነበረና ደግሞም ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷል›› በማለት በኀጢአት መኖር እንደ መሞት ከኀጢአት መመለስ እንደ ትንሣኤ መቆጠሩን አስረድቶናል። ሉቃ ፲፭ ፥ ፳፬ ማንኛውም ሰው ከቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ ሕይወት ከወጣ እንደ ሞተ ነው የሚቆጠረው፡፡ ፫ኛ. ትንሣኤ ሙታን ነው ይህ ደግሞ ለጊዜው የሙታን በሥጋ (በተአምራት) መነሣት ሲሆን፤ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል:: ይኸውም በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ኤልያስ አንድ ሙት፣ ነቢዩ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነሥተዋል፤ በሐዲስ ኪዳን ጌታችን የዐራት ቀን ሬሳ አልአዛርን፣ የዕለት ሬሳ ወልደ መበለትን፣ ወለተ ኢያኤሮስን ከሞት አስነሥቷል፤ ይህ ‹‹ትንሣኤ ሙታን›› ይባላል፡፡ ፬ኛ. ትንሣኤ ክርስቶስ ነው ትንሣኤ ክርስቶስ እንደሚታወቀው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን የሚገልጥ ነው:: ይህ ትንሣኤ የትንሣኤው ሁሉ በኵር ተብሎ ይጠራል᎓᎓ ትንሣኤው ከፍጡራን ትንሣኤ የተለየና ብቸኛ ነው::  ፭ኛ. ትንሣኤ ዘጉባኤ ነው ትንሣኤ ዘጉባኤ ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ዅሉ እንደየሥራው ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ነው። በሕብረት፣ በነገድ፣ በጉባኤ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ የሚደረግ ትንሣኤ በመሆኑ ትንሣኤ ዘጉባኤ ተብሏል። ጌታ በወንጌሉ ስለትነሣኤ ዘጉባኤ ሲናገር «በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ፤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።» ዮሐ ፭ ፥ ፳፱ ሲል በትንሣኤ ዘጉባኤ ከሚደረጉ ተአምራት አንጻር ዛሬ የሚደረጉ ተአምራት ምንም እንዳልሆኑ አስተምሯል። ትንሣኤ ክርስቶስ ለትንሣኤ ሙታን ምስክር ለትንሣኤ ዘጉባኤ በኵር  ነው    ©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
85731Loading...
03
Media files
6762Loading...
04
"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል፤ የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ በአንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡" #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
1 0146Loading...
05
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።" አባ ሕርያቆስ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት አደረሰን 🙏🙏🙏
1 0159Loading...
06
#በመቃብር_አደረ "ዳግመኛም ይህ ሥጋ ከመለኮቱ ሳይለይ በመቃብር አደረ ነፍሱም ከመለኮት ሳትለይ በገሀነም ተግዘው ለነበሩ ነፍሳት ድኅነትን ታበስር ዘንድ፤ ነፃም ታደርጋቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች።" ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ
1 60313Loading...
07
Media files
1 92817Loading...
08
Media files
1 1471Loading...
09
Media files
1 1291Loading...
10
Media files
1 0871Loading...
11
Media files
1 1811Loading...
12
".... ዐይኖችን በሚፈጥር ፊት ምራቃቸውን ተፉበት። ዳግመኛም ፊቱን በጥፊ መቱት። ኪሩቤል ፊቱን ከማየት የተነሣ በእሳት አክናፍ የሚሠወሩት ያልበደላቸውን እሱን አይሁድ ፊቱን ጸፉት፤ ፊቱ እንደ መንፈስ ቅዱስ፣ እንደ አባቱ ሲሆን በሥጋው ፊቱን ጸፉት፤ ከፊቱ ግርማ የተነሣ ፍጥረቱ ሁሉ የሚርዱለት፣ የሚንቀጠቀጡለት የፈጣሪያቸውን ፊቱን ጸፉት። መዠመሪያ በመመታቱና የሾኽ አክሊል በመሸዳጀቱ ራሱ የቆሰለ ከመሆኑ በላይ የያዘውን በትር ከእጁ ተቀብለው ራሱን መቱት። ነገር ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ እርግማንን አጠፋልን። ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እባብ ሰባቱን እራሶቹን ዐሥሩ ቀንዶቹን አጠፋልን።"          የኅሙስ ድርሳነ ማኅየዊ
1 40513Loading...
13
"በሠላሳ ብር በርካሽ ዋጋ የተሸጠው እርሱ ዓለምን በውድ ዋጋ ገዛ፤ ይኸውም ክቡር ደሙ ነው።" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
1 41322Loading...
14
ችንካሮች “ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን። ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም። ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን። ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም። እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው። እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው። እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው። እንደ ግምጃ ለበስነው። እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው። እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው። ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው። ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል። እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው። መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"  ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  መጽሐፈ ምሥጢር 24:20
1 38116Loading...
15
* ስብሐት ለከ ኢየሱስ በአፈ ኲሉ ውዱስ፤ + በኹሉም አፍ የተመሰገንኽ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል * ስብሐት ለከ ኢየሱስ ቀዳሴ ሥጋ ወነፍስ፤ + ሥጋንና ነፍስን ያከበርኽ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል * ስብሐት ለከ ኢየሱስ ለዕሩቃን ልብስ፤ + [በኃጢአት] ለተራቆቱት [የጸጋ] ልብስ የኾንኽ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል * ስብሐት ለከ ኢየሱስ ዘኢትሠዐር ንጉሥ፤ + የማትሻር ንጉሥ ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል * ስብሐት ለከ ኢየሱስ ቃለ አብ ቅዱስ + ቅዱስ የአብ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባል። (መቅድመ ተአምረ ኢየሱስ)
1 4077Loading...
16
"ሰላም ለኪ ሐመረ ብዕል፡ ሙዳየ ዕፍረት ቢረሌ ጽዱል፡ ምዕራፈ ተድላኪ በብሔር ጥሉል፡ መልክአ ገጽኪ በአርያም ስዑል" (መልክአ ሕማማት፤ ዘሰዓተ ሠርክ) * "መልክአ ገጽኪ በአርያም ስዑል" - 'የፊትሽ መልክ በሰማይ የተሳለ' ... ህምምም ... ተመስጦ 😇
1 3278Loading...
17
በሰሙነ ሕማማት የካህናት የጸሎት ማሳረጊያ፦ * እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ ዓመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም አሜን። ትርጉም:- * ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማ (ሥቃይ፣ መከራ) ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን በደስታና በሰላም ያድርሰኝ ያድርሳችሁ። * አሜን።
1 31020Loading...
18
Media files
1 2772Loading...
19
✥✥✥ ዕለት ሰኞ ✥✥✥ - ይህ ዕለት አንጽሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለተ ነው፡፡ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን ከቢታንያ ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ፡፡ በለስም ከሩቅ ዓየ፣ በለስዋ ግን ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ምንም ኣላገኘባትም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ ኣይገኝብሽ ከአንቺ ፍሬ የሚበላ ኦይኑር አላት ያን ጊዜውንም በለሲቱ ደርቃለች (ማር.11፥12-19/ማቴ.21፥19/ሉቃ.19፥45-46) በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡- በለስ አገኘ ማለቱ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት ሲል ነው፡፡ ወደ እርስዋም ሄደ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ (ሥርዓተ ኦሪትን ማለት በ8ኛው ቀን መገዘር በ40 ቀን መሥዋዕት ማቅረብን... እየፈጸመ አደገ) ማለት ነው፣ ፍሬ አላገኘባትም አለ ሕግ ከመባልዋ በቀር ድኅነትን አላደረገባትም፣ ፍሬ አይገኝብሽ አላት ሲል፡- ባንቺ ድኅንነት አይደረግ አላት፡፡ ይህም ቅዱ ዳዊት ‹‹መሥዋዕትን ቁርባንን አልወደድሁም ሥጋህን ኣንጻልኝ፣ የሚቃጠለውንና ስለኃጢኣት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም ሲለ የኦሪትን ሕግ (ዐሠርቱ ትዕዛዛትን) አሳለፋቸው ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን በመሥዋዕተ ኦሪት ፍፁም ድኅንነት ኣለመገኘቱን አውቆ ማሳለፉን እና ፍፁም ድኅንነት የምናገኝበትን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ያሳያል፡፡›› አንድም፦ በለስ ያለው ኃጢኣትን ነው፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ኃጢኣትን በዚህ ዓለም ሰፍና ኣገኛት፡፡ ወደ እርሷ ሄደ ፍሬም አላገኘባትም ማለት በአይሁድ አንደበት በሐሰት ኃጢኣተኛ ተባለ እንጂ (ስለ እኛ መተላለፍ እንደበደለኛ ተቆጠረ እንጂ) ኃጢኣትን አልሠራም ሲል ነው፡፡ ፍሬ አይገኝብሽ ሲል፡- ባንቺ በመጣ ፍዳ የሚያዝ አይኑር አላት ማለት ነው፡፡ ➕ ከዚህ በመቀጠል ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ ቤተ መቅደሱም ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ በዚያ ያሉትን ሁሉ አስወጣቸው፡፡ ይኸም በጠቅላላው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ለጆች ኃጢኣት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢኣታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ማቴ.21፥12-17/ማር.11፥15-24/ሉቃ.19፥4)
1 58914Loading...
20
Media files
1 1671Loading...
21
Media files
1 3543Loading...
22
"ከመድኃኒትነቱ የተነሳ ከቤቱ መሠረት ሳይናወጥ ከልዑል መንበሩ ወረዶ ጸጋንና ኃይልን አሳየ ። ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም። "           ቅዳሴ ጎርጎርዮስ እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። አምላከ ቅዱሳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም ያድርሰን!!!
1 4837Loading...
23
".......እግዚአብሔርን ቃል ወደ ምድር ይወርድ ዘንድ ከድንግል ማርያም ሰው ይሆን ዘንድ በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ በበረት ውስጥ ይጣል ዘንድ ከሴት ልጅ ጡቶች ወተትን ይጠጣ ዘንድ ምን አተጋው? ለእኛ ለጠፋናው አይደለምን?" ሃይማኖተ አበው ንባብና ትርጓሜው፤ ዘቅዱስ እለእስክንድሮስ ፲፮÷፪
1 3514Loading...
24
https://youtu.be/8FfDpuoS99o?si=nC-nOCTWV-MNAo7N
2 2337Loading...
25
https://youtu.be/7DaeUh7VRz8?si=0N_6l7jLBxJ6F2Ke
1 2700Loading...
26
በድንግልና መኖር የሚችሉ መጋባትም መውለድም የለባቸውም በሌላ በኩል ደግሞ በድንግልና መኖር የማይችሉ ቢኖሩ ነውር በሆነ መንገድ እንዳይወልዱ ወይም ለመውለድ ሳይፈልጉ ይበልጥ ነውር በሆነ መንገድ ከሌላይቱ ሴት ጋር እንዳይተኙ በሕጋዊ መንገድ ጋብቻን ይፈጽሙ ልጅ ላለመውለድ የጽንስ መከላከያን የሚጠቀሙ ባለትዳሮች ሁሉ ሥራቸው ነውር እና ስህተት ነው፡፡ ልጆች መውለድን በመከላከል ድክመታቸውን በመሸፈን መመከር አይኖርባቸውም፡፡ ቅዱስ አውጉስጢን
1 47419Loading...
27
Media files
1 5223Loading...
28
Media files
1 5507Loading...
29
Media files
1 9577Loading...
30
አቤቱ አንተን የሚመስል ማነው? “መኑ ይመስለከ፡ እምነ አማልክት እግዚኦ፡ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ፡ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኀይለከ፡ ወአድኀንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ ሖርከ ውስተ ሲኦል፡ ወአዕረገ ጼዋ፡ እምህየ ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኀከነ፡፡ በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ፡ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል፡ ቡሩክ አንተ እግዚኦ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ፡፡” (ሥርዓተ ቅዳሴ) አቤቱ ፈጣሪያችን፡ መድኀኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፤ “አማልክት” ከተባሉ፡ አማልክት ከሆኑባቸው ከእነ ዜውስ፡ ከእነ አርጤምስ አንተን የሚያህል፡ አንተን የሚተካከል ማነው? አማልክት ከሆኑብን ከአምሮት፤ ከስስት አንተን አንተን የሚተካከል እውነተኛውን ደስታ መስጠት የሚችል ማነው? እኒህ ሁሉ አማልክት ሕዝብህን ከክፉው እና ከክፋት ማዳን አይችሉምና፤ ሕዝብህን ከክፉ በማዳንም ድንቅን አላደረጉምና፤ እንዲያውም ሕዝብህን ወደ ሞት ይወስዳሉና፡፡ አንተ ግን በከበረች ኀይልህ፡ እኛን ልታከብር፡ እኛ ከገባንበት ደይን (ሲኦል) ለማውጣት፡ ወደ ሲኦል ሄድኽ፡፡ እኛን ለመፈለግ በፍቅርህ ብዛት ወደ ምድር መጣህ፡፡ ፍቅርህ እውነተኛ ናትና “ወደ ምድር መጣሁላቸው፤ እሱ ይብቃቸው” ብለህ ፍቅርህን ሳትቆጥር፤ በደላችን ከምድር በታች (ሲኦል) ወስዳናለችና፡ እዚያም ሄድኽ፡፡ ክቡር እና ልዑል ለሆነ አባትህ ምርኮን ማረክህ፤ እኛን ወደ እርሱ አቀረብከን፡፡ እኛን ከከፋችው ቦታ አወጣኸን፡፡ ለዘለዓለም የሚሆን ነጻነትን (ጸጋን) ዳግመኛ ሰጠኸን፡፡ ጥንት የሰጠኸንን ነጻነት አንተን ላለመውደድ፤ ሕግህንም ላለማድረግ በጥመት ተጠቅመንበት ነበርና፡፡ አሁን ግን ወደን፡ ፈቅደን ለአንተ እንድንገዛ ከሰይጣን ባርነት፤ ያንተን ወደምትመስል ነጻነት መለስከን፡፡ ታዲያ እኛ ምን ብለን፡ ምን አድርገን እንመልስልህ? “የቡሩክ አብ ልጁ፡ ቡሩክ ወልድ” ብለን እናመስግንህ እንጂ፡፡ “እኛን ክፉ ከተባለው ሁሉ ጠብቀን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ “እኛን ከራሳችንም ጠብቀን፤ አድነን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ አንተ መጥተህ (ሰው ሆነህ) አድነኸናልና፡፡ አሁንም በመምህራን ትምህርት፤ በካህናት መሥዋዕት፤ በምዕመናን ጸሎት መጥተህ ታድነናለኽና፡፡ አቤቱ ከአማልክት አንተን የሚመስል ማነው? አቤቱ ማረን! በቴሌግራም እንገናኝ - http://t.me/Micah_Mikias
1 98912Loading...
31
Media files
1 5070Loading...
32
Media files
1 6942Loading...
ክርስቶስ ተነሥቷል(Christ Risen) በሚለው ቃል ውስጥ ያለው መንፈሳዊ ኀይል። በአባ ዮሐንስ ገባሬ መንክራት (St. Jonh Maximivotch) የተደረገው ተአምር። አባ ዮሐንስ ገባሬ መንክራት በአንድ ወቅት የብርሃን ሳምንት ተብሎ በሚታወቅበት ሳምንት አንድ የታመመ ኦርቶዶክዊ ምዕመንን ለመጠየቅ ጉዞውን ወደ አንድ የአይሁዳውያን ሆስፒታል ያደርጋሉ። አባ ዮሐንስ በሆስፒታሉ በአንደኛው ዋርድ ፊትለፊት ሲያልፍ ድንገት ቆመና በመጋረጃ በተሸፈነው ክፍል ውስጥ አንዲት አይሁዳዊት አሮጊት ሕይወቷ አልፏል በመባሉ ሸፋፍነዋት አልጋ ላይ እንዳስተኟት ይረዳል። አባ ዮሐንስ ገባሬ መንክራት ድንገት ከተጋረደው ክፍል ፊትለፊት ቆመና ቅዱስ መስቀሉ አውጥቶ ድምጹ ከፍ አድርጎ ጮኸና "ክርስቶስ ተነሥቷል" እያለ በመስቀል ምልክት እያማተበ ተናገረ፣ ድንገት ይኸንን በሚያደርግበት ወቅት ሞተች የተባለችዋ እናት አእምሮዋ ተመለሰላትና ቃል አውጥታ ውሃ ስጡኝ ብላ ጠየቀች። አባ ዮሐንስም አንዷን ነርስ ጠራት እንዲህ አላት ታማሚዋ ውሃ እየፈለገች ነው ብሎ ሲነግራት ይኸንን የሰሙ የሆስፒታሉ ሠራተኞችም አስቀድማ አርፋለች ተብላ የነበረችው ታማሚዋ ባሳየችው አስገራሚ ለውጥ በጣም ተደነቁ ከዚያ በኋላ ታማሚዋም በተደረገላት አስደናቂ ተአምር ተሽሏት አገግማ ከሆስፒታሉ ወጥታ ወደ ቤቷ ሔደች። አባ ዮሐንስም በክርስቶስ የትንሣኤው ኃይል በማያምኑት መካከል አስደናቂውን ተአምር አደረጉ። አቤቱ ሆይ የትንሣኤህ ኃይል ይገለጥ ሰይጣን ከነ ሠራዊቱ ይሸነፍ፣ ሞትም ከነ መውጊያው ይወገድ፣ ሲኦልም ከነ ድል መንሣቷ ትሻር፣ ኃጢአት እና አለማመን ከእኛ ይራ፣ ሕይወታችን የተቀደሰች ትሁን ዙሪያችን በትንሣኤው ኃይል በትንሣኤው ብርሃን የታጠረ ይሁን። ክርስቶስ ተነሥቷል በእውነት እርሱ ተነሥቷል።
Mostrar todo...
👍 11 7
[•• አምስቱ ትንሣኤዎች••]        • ‹‹...በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡›› ራእ ፳ ፥ ፮ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት «ትንሣኤን» በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲያመሠጥሩት በአምስት ዓይነት ትርጉም ያስቀምጡታል፡፡ ይኸውም ትንሣኤ ኅሊና፣ ትንሣኤ ልቡና፣ ትንሣኤ ሙታን፣ ትንሣኤ ክርስቶስና ትንሣኤ ዘጉባኤ በሚል በአምስት መንገድ ይከፈላል። ፩ኛ. ትንሣኤ ኅሊና ነው ይህ ትንሣኤ ኅሊና ተዘክሮተ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ማሰብ) ማለት ነው። ሙሴ በኦሪቱ ‹‹እመኒ እንዘ ተሐውር ወእመኒ እንዘ ትትነሣእ ኢትርሣእ ተዘክሮተ እግዚአብሔር፡፡ ስትሄድም ስትነሣም እግዚአብሔርን ማሰብ አትርሣ›› ብሎ ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንደተናገረው። ፪ኛ. ትንሣኤ ልቡና ነው፤ ትንሣኤ ልቡና ደግሞ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ማለት ነው:: ይኸውም ሰው ሁለት ጊዜ ይሞታል፤ ሁለት ጊዜ ይነሣል፤ የሰው ልጅ የመጀመሪያው ሞቱ ኀጢአት መሥራቱ ከእግዚአብሔር መለየቱ ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሥጋ ፍትወት በምድራዊ ቅንጦት የሚቀማጠሉትን ሲናገር ‹‹ቅምጥሊቱ ግን በሕይወቷ ሳለ የሞተች ናት›› ፩ኛ ጢሞ ፭ ÷፲ ፯ ሲል በኀጢአት መኖር ትልቁ ሞት እንደኾነ ነግሮናል፣ ሁለተኛው በሥጋ መሞቱ ነው:: ስለዚህ ሰው ሁለት ጊዜ እንደሚሞት ሁለት ጊዜ ይነሣል፤ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ትንሣኤው እንዴትና ምን እንደሆነ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ሲል ነግሮናል፤ ‹‹ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው ሁለተኛው ሞት በእርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡›› ራእ ፳ ፥ ፮  በማለት ንስሐ ገብቶ ከእግዚአብሔር ታርቆ ትንሣኤ ልቡናን ገንዘብ ያደረገ ሰው ሞተ ሥጋንና ሞተ ነፍስ ድል ነሥቶ እንደሚኖር ነግሮናል፡፡  ለትንሣኤ ልቡና ትልቅ ምክር የሚሆነን በሉቃስ ወንጌል የተመዘገበው ታሪክ ነው፤  ‹‹ይህ ልጄ ሞቶ ነበረና ደግሞም ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷል›› በማለት በኀጢአት መኖር እንደ መሞት ከኀጢአት መመለስ እንደ ትንሣኤ መቆጠሩን አስረድቶናል። ሉቃ ፲፭ ፥ ፳፬ ማንኛውም ሰው ከቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ ሕይወት ከወጣ እንደ ሞተ ነው የሚቆጠረው፡፡ ፫ኛ. ትንሣኤ ሙታን ነው ይህ ደግሞ ለጊዜው የሙታን በሥጋ (በተአምራት) መነሣት ሲሆን፤ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል:: ይኸውም በብሉይ ኪዳን ነቢዩ ኤልያስ አንድ ሙት፣ ነቢዩ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነሥተዋል፤ በሐዲስ ኪዳን ጌታችን የዐራት ቀን ሬሳ አልአዛርን፣ የዕለት ሬሳ ወልደ መበለትን፣ ወለተ ኢያኤሮስን ከሞት አስነሥቷል፤ ይህ ‹‹ትንሣኤ ሙታን›› ይባላል፡፡ ፬ኛ. ትንሣኤ ክርስቶስ ነው ትንሣኤ ክርስቶስ እንደሚታወቀው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን የሚገልጥ ነው:: ይህ ትንሣኤ የትንሣኤው ሁሉ በኵር ተብሎ ይጠራል᎓᎓ ትንሣኤው ከፍጡራን ትንሣኤ የተለየና ብቸኛ ነው::  ፭ኛ. ትንሣኤ ዘጉባኤ ነው ትንሣኤ ዘጉባኤ ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ዅሉ እንደየሥራው ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ነው። በሕብረት፣ በነገድ፣ በጉባኤ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ የሚደረግ ትንሣኤ በመሆኑ ትንሣኤ ዘጉባኤ ተብሏል። ጌታ በወንጌሉ ስለትነሣኤ ዘጉባኤ ሲናገር «በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ፤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ።» ዮሐ ፭ ፥ ፳፱ ሲል በትንሣኤ ዘጉባኤ ከሚደረጉ ተአምራት አንጻር ዛሬ የሚደረጉ ተአምራት ምንም እንዳልሆኑ አስተምሯል። ትንሣኤ ክርስቶስ ለትንሣኤ ሙታን ምስክር ለትንሣኤ ዘጉባኤ በኵር  ነው    ©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
Mostrar todo...
👍 7 2
"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል፤ የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ በአንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡" #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
Mostrar todo...
11👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።" አባ ሕርያቆስ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት አደረሰን 🙏🙏🙏
Mostrar todo...
13
#በመቃብር_አደረ "ዳግመኛም ይህ ሥጋ ከመለኮቱ ሳይለይ በመቃብር አደረ ነፍሱም ከመለኮት ሳትለይ በገሀነም ተግዘው ለነበሩ ነፍሳት ድኅነትን ታበስር ዘንድ፤ ነፃም ታደርጋቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች።" ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ
Mostrar todo...
14👍 1