cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አትሮንስ 📖

ምስጢረ ሥላሴ ምስጢረ ቁርባን ምስጢረ ሥጋዌ ምስጢረ ጥምቀት ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ቤ/ክ ታሪክ ነገረ ማርያም ነገረ ክርስቶስ ፅሁፍ፣አስተማሪ የድምፅ መልእክት ብሎም ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ካልዎት @kimi_king ሊቀበልዎት ዝግጁ ነዉ።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 025
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

መልካም ወጣት መልካምነት ለራስ ነዉ እንዲሉ አበዉ ፤ መልካም ሆኖ መገኘትን የመሰለ ለወገን አስፈላጊ ነገር የለም ነገር ግን እራሱ መልካምነትን በቅጡ መገንዘብ ከሁሉ በላይ አስፈላጊ ሆኖ እናገኘዋለን መጀመርያ እስኪ መልካምነት ምን እንደሆነ እራሳችንን ለራስ የምናስረዳበትን መንገድ እንፍጠር ፤ ለምሳሌ ሽቱ ሁሉ መልካም መአዛ በዉስጡ የያዘ ሆኖ ሳለ በሚኒ ባስ ተሳፍረን አንድ ወዳጅ የተቀባዉ መልካም መአዛ ለኛ ለምን ይረብሸናል ? አሱም ይቅር እሺ ለበጎ ብለን በመልካምነት የሰራነዉ ተግባር ለምን ለሌላዉ ከፍቶ እናገኛለን ? እንደኔ መልካምነት እንደ እያንዳንዳችን እይታ ይለያያል የሚል ድምዳሜ መሰል ሀሳብ ላይ ልደርስ ትንሽ ቀርቶኛል ። መልካም ወጣት ለሀገርም ለወገንም እንደሚጠቅም ይታወቃል ነገርግን በስራዉ የታደሰ ለህይወቱም ተሀድሶን ያቀበለ ወጣትም እንደዛዉ ። ችግሩ ምን እየታደሰ መልካም ለመሆን እየተሞከረ ነዉ የሚለዉን ስናይ ነዉ ። ሀይማኖትን ? ፤ ዶግማን ወይንም የቤተክርስቲያንን ተግባራትን አድሰን መልካም እንሁን ካልን ፀአዳ ግድግዳን ያለ የሌለዉን ሁሉ ቀላቅለን በማፅዳት ዥንጉርጉር ቀለምን ከመፍጠር ፈቀቅም አንልም ። ወዳጄ መታደስ ዘረኝነትን ጥሎ ፍጡሩን ሁሉ ማክበሩ ላይ ነዉ ፥ ለቤተክርስትያን እኔ ምን ልስራ ብሎ ማሰቡ ለይ ነዉ ፥ መልካም መሆን እመብርሃን እንዳሳየችን ለተቸገሩ ሁሉ ወዳጅ መሆን ላይ ነዉ ፥ መልካምነት ከሚታየዉ በላይ ሆኖ መገኘት ነዉ ፥ እናት ሀገርን እና እናት ቤተክርስትያንን መዉደዱ ላይ ነዉ ። እኛም እንዲ አልን “ መልካምነት ከራስ ይጀምራል እና በአምላክ አምሳል የተሰራዉ ሰዉነታችንን እናክብር ፥ እንዉደድ ፥ ወደመልካም ቦታም እንዲዉል እንፍቀድ ” ስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን!
Mostrar todo...
ክርስትናን በጥልቅ ማገናዘብ [Orthodoxy critical thinking] ⴲ ከታዳሚ እንደጥያቄ የቀረበ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከሁሉ በፊት ስለ ክርስትናን በጥልቅ ማገናዘብ ከማውራት በፊት በጥልቅ ማገናዘብ ማለት ምን ማለት ነው?................ አባቶች በየነገሮቻቸው ሁሉ ማገናዘብ የግድ አስፈላጊ መሆኑን በደንብ በትውፊት አስተምረውናል “ በንግግር መሃል በጥሞና ማዳመጥ በጥልቅ መገንዘብን ያመጣል ለዛም ነው ሁለት ጆሮ የተሰጠን። ” ሲሉ አባቶች ከመናገር በፊት በጥልቅ መረዳት የሚል ጠቃሚ ብሂል አስቀምጠዋል። ጠንከር ያለ አባባል ነው ግን እንደዚህ አይነቱን ጥሩ ነገር ምንስናደርግ ነው መጠቀም የምንችለው? እንግዲህ አንድ ሰው ሲናገር ቃላቶችን እየሰነጠቁ ነገሮችን ከታሰበላቸው አንድምታ ለይቶ መረዳት አይደለም እንደው በደፈናው ምንለማለት ተፈልጎ መሆኑን ከመረዳት በኋላ የራስን የአስተሳሰብ መነጽር በመጨመር እስከ ውስጥ ገብቶ መረዳት ነው ። ንባብንም ለመረዳትከዚሁ የዘለለ ልዮ አስማታዊ ጥበብ አይፈልግም ። ከርዕሳችን ርቀን በረሃ ላይ እንዳንቀር ታድያ ክርስትናን በጥልቅ ማገናዘብ [Orthodoxy critical thinking] ለማምጣትስ ምን እናድርግ ? @eotceotc በ [THE ORTHODOX WAY , Archimandrite Kallistos Ware : ST. VLADIMIR'S SEMINARY PRESS CRESTWOOD, NY I 0707 1986] የሚል መጽሐፍ ውስጥ ክፍል ውስጥ እንደሚከተለው ሲሉ ስለ ቤተክርስትያን ጽፏል =〉 ” The Church gives us not a system, but a key; not a plan of God's City, but the means of entering it. Perhaps someone will lose his way because he has no plan. But all that he will see, he will see without a mediator, he will see it directly, it will be real for him; while he who has studied only the plan risks remaining outside and not really finding anything. ” Fr George Florovsky በትርጓሜውም “ቤተክርስቲያን ስልትን አልሰጠንም, ነገር ግን ቁልፍ ነው. የእግዚአብሔርን ከተማ እንጂ ዕርምጃ ለመግባት መንገድ አይደለም. ምናልባት ምንም እቅድ ስለሌለው አንድ ሰው መንገዱን ያጣል ይሆናል. ነገር ግን የሚያየው ሁሉ, ገዢውን ያያል, እርሱ በቀጥታ ያየዋል, እሱ ለእሱ እውን ይሆናል. እቅዱን ብቻ ያጠኑ ግን ውጭ ውጭ ይቆማሉ እና ምንም ነገር አያገኙም.” የሚል ትርጉም በአባት ጆርጅ ዶሮቭቭስኪ ጽሁፍ ውስጥ እናገኛለን እኝህ አባት በንግግራቸው ሊያስረዱን በክርስትና ውስጥ ያሉት አስተምህሮ ቀጥታ ወደ መጨረሻ የሚወስዱ ሳይሆኑ በራስ ተገባር የተማርነውን ስንጠቀም የሁሉ ቀዳሚ ሆነን እንገኛለን ነገር ግን ይህንን ስን ያገኘነውን ሁሉ በመዘባረቅ እናውቃለን ማለት አለብን አይደለም እንደው አንዳንድ ጊዜ ከአቅም በላይ ሲሆን “አላውቅም አነብና አሳውቅሀለው” ማለትን መልመድ አለብን በዚሁ መጽሃፍ ላይ ስለዚሁ ሊያስረዳ አንድ ታሪክን አንስቶ ነበር እንደሚከተለው ይላል @eotceotc  “ One day some of the brethren came to see Abba Antony, and among them was Abba Joseph. Wishing to test them, the old man mentioned a text from Scripture, and starting with the youngest he asked them what it meant. Each explained it as best he could. But to each one the old man said, 'You have not yet found the answer.' Last of all he said to Abba Joseph, 'And what do you think the text means?' He replied, 'I do not know.' Then Abba Antony said, 'Truly, Abba Joseph has found the way, for he said: I do not know.' “  ” ከዕለታት አንድ ቀን አንዳንድ ወንድሞች አባ ልቶኒን ለመጠየቅ መጡ, ከእነርሱም መካከል አባስ ዮሴፍ ይገኙበታል. አረጋዊው ሰው እነሱን ለመፈተን በመፈለግ ከቅዱስ ቃሉ ውስጥ አንድ ጥቅስ በመጥቀስ ምን ማለት እንደሆነ ጠየቋቸው. እያንዳንዳቸው በተቻለ መጠን ያብራሩታል. ግን ለእያንዳንዱ ሰው አዛውንቱ “ መልሱ ገና አልደረሳችሁም አሏቸው” . በመጨረሻም ለአባባ ዮሴፍ እንዲህ አሉት -<ፅሁፉ ምን ማለት ይመስልሃል ?> እሱም 'አላውቅም' ብሎ መለሰ. ከዚያም አባ አንቶኒ እንዲህ አሉት, “አባባ ዮሴፍ መንገዱን አግኝቷል እኔ አላውቅም አለ. ” “ ምንም ማብራርያ የማያስፈልገው ቀጥተኛ ጽሁፍ እንዲሉ ቃልበቃል የተስተካከለ ለእያንዳንዳችን የሚገባ ምሳሌ ነው እንግዲህ በትንሹ ጫፍዋን ከጻፍን ክርስትናን በጥልቅ ማገናዘብ እንዴት እንደሆነ በጥልቅ ለመረዳት“ በራሳችሁ አካፋ በራሳችሁ ዶማ በራሳችሁ የአስተያየት መነጽር ወደውስጥ ጥለቁ ” እንላለን በትንሹም ቢሆን ጠቃሚ ጽሁፍ እነደነበረች ተስፋ አለን ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር @eotceotc
Mostrar todo...
እርስዎ ስለ ብልጽግና እና ክርስትና ምን ይላሉ?
Mostrar todo...
Add a comment
ብልጽግና እና ክርስትና እንዴት ከረማችሁ ወዳጆቼ ዛሬ አንድ ወዳጄ ቆይ ግን ብልጽግና ከሃይማኖታችን ጋር አይጋጭም ሲለኝ የድንጋጤ ስሜት እናንተን አይሰማችሁ ፤ አሜን በለ ከአፍ ይቀራል ። እንዲህ ሆነ ቁጭ ብለን እየበላን ከኋላችን ለሃገር ሰላም ዘብ የሚቆሙ አካላትም እየበሉ ነበር እና ይህ ወንድሜ ዜና ከምናይበት በድንገት ብልጽና ግን ከክርስትና ጋር ይሄዳል ሲል እኔ ላይ አንባረቀ ። ወድያው አንድ ዲጄ የቀነሰው እስኪመስል የቤቱም የጓደኛዬም ድምጽ እኩል ቀነስ አሉ ። እኔ የታየኝ ከኋላችን “ምን ማለት ፈልገህ ነው ማንጁስ ? ” ከሚል ቃል ጋር በፍቅር የሚያቅፍ ዱላን ነበር ወድያው እንዳልደነገጠ ሆንኩና ማለት ማለት አልኩት የዛኔ ነው እሱም የደነገጠው ለካ አሁን ቃሉ ለሌላ ማዋል ራሱ ተጠጠርጣሪ በሚል ያስቀጣል ። ለካ ጥያቄው ወዲህ ነው ሃብታምነት እና ሃይማኖተኝነት አብሮ ይሄዳል ወይ ? ነው እኔም ረጋ ብዬ ለማስረዳት ሞክሪያለሁ በጥያቄው ላይ በሙሉ መልስ እስክመለስ እናንተ ሃሳባችሁን አጋሩን ሃብታም ሃይማኖተኛ ሊሆን ይችላል?
Mostrar todo...
በጠዋት ተነስተን ጸሎት ማድረግ ለምን ከበደን?
Mostrar todo...
ገርጂ ኆህተ ብርሃን ቅ/ማርያም ሰ /ት/ቤት የክረምት ተከታታይ ትምህርት (ኮርስ) ኦንላይን (online) መመዝገቢያ bot ነው ከሉበት ሆነው ለመዝገብ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇 👉 👉 👉@mezgebe21_bot👈👈👈 👉 👉 👉@mezgebe21_bot 👈👈👈 👉 👉 👉@mezgebe21_bot 👈👈👈 👆👆👆👆👆👆 💡🔑ማሳሰቢያ ተመዝግባችው መማር ለምትፈልጉ ብቻ እንዲሆን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን
Mostrar todo...
Hi
Mostrar todo...
Comments – 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.