cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሰሌዳ | Seleda

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! @seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
50 385
Suscriptores
+2224 horas
-537 días
-12330 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
‹‹ዛሬ በባህርዳር ከተማ የተመረቀው የአባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው። ከግዘፋዊ ቁሳዊ መዋቀሩ ባሻገርም ልዩነቶችን የማጥበብ፤ በተቃራኒ ጎራ ላሉ ሰዎች መገናኛ ድልድዮችን የማነፅ ርዕያችን መዘርጊያ ምልክት ነው። ኅብረታዊ ምሉዕነትን ለማፅናት ከክልላዊ ወሰኖች የሚሻገር ትርክት የመቅረፅ ትልማ ማሳያ ነው። ግባችን በክልከላ እና ቁንፅልነት የሚመሩ የአእምሮ ውቅሮች እና ትርክቶችን በማስወገድ በሁሉም ዘንድ ትብብርን እና አንድነት ማሳደግ ነው።›› -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
2 8441Loading...
02
ዛሬ ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል 🔥 በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ደጋፊዎችን ያፈሩት ከቀድሞው የፕሪምየር ሊግ ምስረታ ጀምሮ በከፍተኛ ትንቅንቅ ይፎካከሩ የነበሩት አሁን እንዱ እንደስሙ ማደር የተነሳነው አንዱ ከቀድሞ ስሙን ለመመለስ በመጣር ላይ ሆነው በሊጉ 37ኛ ሳምንት ተገናኝተዋል። የሁለቱ ጨዋታ ሲኖር ዲኤስቲቪ ቤቶች በቶሎ ይሞላሉ ጠጠር መጣያ እስኪታጣ ድረስ ወንበሮች ጢም ብለው ይሞላሉ ብሽሽቁ ይደራል ነቆራው ከየቦታው ይሰማል ለ 90 ደቂቃም ከተማው ፀጥ ረጭ ይላል። 37ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪምየር ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል የጨዋታ ሰዓት - አመሻሽ 12:30 🏟️ ስታድየም - ኦልድትራፎርድ ማን ያሸንፋል…? ዩናይትድ የመድፈኞቹን ጉዞ ያደናቅፋል ወይስ መድፈኞቹ ቀያይ ሴይጣኖችን አጋድሞ ያልፋል?
4 1503Loading...
03
በዚህ መርሐግብር መሰረት ተዘጋጁ👆 የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡ መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:— ✔ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ✔ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።
3 81214Loading...
04
ከፒያሳ በሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ለኮሪደር ልማት ፕሮጀክት 3,250 አባወራዎች ይነሳሉ ተባለ ከፒያሳ በመነሳት በሳር ቤት በኩል እስከ ወሎ ሠፈር ድረስ የሚገነባው አዲሱ የኮሪደር ልማት፣ 3,250 አባወራዎችን ወይም ከ14 ሺሕ በላይ ሰዎችን እንደሚያስነሳ ተመላከተ፡፡ ተነሺዎችን ለማስፈር 21 ሔክታር መሬትና ስድስት ቢሊዮን ብር የካሳ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡ ከአሥር ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ከፒያሳ በመነሳት እስከ ብሔራዊ፣ ከብሔራዊ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሳር ቤትና ከሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ተብሎ በአምስት ንዑስ ፕሮጀክቶች ተከፋፍሎ ዲዛይን እንደወጣለት ሪፖርተር የተመለከታቸው የዲዛይን ዶክመንቶች ያሳያሉ፡፡ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ አምስት ክፍላተ ከተሞችን የሚነካ ሲሆን እነዚህም አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክና ቦሌ ናቸው፡፡ ጠቅላላ ፕሮጀክቱ 460 ሔክታር መሬት ይዞታ የሚነካ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 114 ሔክታር ለመልሶ ማልማት ነፃ እንደሚደረግ ዶክመንቱ ያሳያል፡፡ ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለአብነት ያህል ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ለፈጣን የአውቶቡስ መስመር ግንባታ ይውላል፡፡ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማኅበራዊ ቤቶች ግንባታ፣ ስድስት ቢሊዮን ለተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ አራት ቢሊዮን ብር ለመንገድ ግንባታ፣ ሦስት ቢሊዮን ለፓርክ (Green Park) ተመድቧል፡፡ በተጨማሪም የፓርኪንግ ቦታዎች፣ ሰባት ያህል ድልድዮች፣ የመሠረተ ልማትና የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ይገነባሉ፡፡ ወጪ የሚደረገውን 40 ቢሊዮን ብር በአምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ለማስመለስ መታቀዱንም ሰነዱ ያመለክታል፡፡ በኮሪደር መስመሩ ላይ መንግሥት 114 ሔክታር መሬት ነፃ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፣ ይኼንን መሬት 70 ሺሕ ብር በካሬ ለአልሚዎች በማከራየት በአምስት ዓመት ውስጥ 99 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ዶክመንቱ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዚህ መስመር ላይ መንግሥት ሊያከራያቸው ካቀዳቸው የመኖሪያ፣ የንግድና የቢሮ ሕንፃና ቤት ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ በየዓመቱ ገቢ ለማስገኘት መታቀዱ ታውቋል፡፡ ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ አብዛኛው ቦታ ለአረንጓዴ ልማት ማለትም ለሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ታቅዷል፡፡ አምባሳደር አካባቢ ያለው የመከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ሙዚየም፣ ካፌና መዝናኛ የሚኖረው የባህል ማዕከል እንደሚቀየር ዲዛይኑ ያሳያል፡፡ የሰይጣን ቤት ተብሎ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ያለው ቦታ ወደ ባህል ማዕከልና መዝናኛ ቦታ በመጠነኛ ለውጥ ያደርጋል፡፡ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት ያለው 1.2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ‹‹የአፍሪካ ማዕከል›› ለመገንባት ይውላል፡፡ ማዕከሉ ሙዚየም፣ ላይብረሪ፣ የባህልና መዝናኛዎች ሲኖሩት አጠቃላይ አካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ ያለው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አገልግሎት ይቀየራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሜክሲኮ ሳር ቤት ባለው ንዑስ ፕሮጀክት ከታሰቡት ብዙ ዕቅዶች ውስጥ ሆስፒታልና አዲሱ ቱሞሮ (Adisu Tomorrow) ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ይገኝበታል፡፡ በዚህ አካባቢ ከአራት ወለል ሕንፃ (G+4) በታች የሆኑ ሕንፃዎች ሁሉም ይፈርሳሉ፡፡ የኮሪደር ልማቱን ለማስፈጸም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት፣ የከተማ አስተዳደሩ፣ የአዲስ አበባ ዕቅድና ልማት ኮሚሽንን ጨምሮ ሃያ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ሪፖርተር | አሸናፊ እንዳለ
3 67517Loading...
05
Media files
3 4171Loading...
06
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ-ቤተክርስቲያኒቱ እንዳይዛመት ማድረግ የቻሉ ሲሆን በጋራዡ የነበሩ ቁጥራቸዉ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ማዳን ችለዋል።በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልመድረሱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል። በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የያዙት ነዳጅና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች እንዲሁም ንግድ ሱቆቹ እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ቆርቆሮና መሰል ግብዓቶች መገንባታቸዉ  ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል። የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ጋራዦች ደረጃቸዉን በጠበቁ ግብዓቶች የተገነቡና ከንግድ ሱቆች ከመኖሪያ አካባቢዎች  የራቁ መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል። የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ብስራት ለማወቅ ችሏል። ዳጉ_ጆርናል
4 5719Loading...
07
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማራ ክልል ገብተዋል ጎርጎራ‼ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ቅዳሜ በአማራ ክልል በገበታ ለሀገር በለማው ጎርጎራ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለበት ነው የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጎርጎራ የተገኙት።
4 7715Loading...
08

10Loading...
09
ዛሬ ይቺን ምድር ከፈጣሪ በታች የቀላቀለችን ፤ አለም ፊቷን ብታዞርብን እሷ ግን በደስታ ምትቀበለን ፤ ለኛ ሁሉ ነገራችን የሆነች ፤ ከአይኗ ብሌን በላይ ምትሳሳልን እናታችን ቀኗ ነው በእርግጥም ሁሉም ቀን እናታችንን ማክበር አለብን ነገርግን ዛሬ ልዩ ቀኗ ነው። እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፤ የእናቶቻችሁን ደስታ ያሳያችሁ ፤ መልካም ቀን!
5 0419Loading...
10
አሁን በኤስ ሚላን እና ካግሊያሪ መካከል እየተደረገ ባለ ጨዋታ ነገ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የእናቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ የኤስ ሚላን ሁሉም ተጫዋቾች በማልያቸው ጀርባ ላይ የራሳቸውን ስም በመተው የእናታቸውን ስም አፅፈው ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።😍😍😍
6 2153Loading...
11
የድሬደዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የመንግስት ሰራተኞች 30% ለሚሆኑት የዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች የቤት ኪራይ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፏል። የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በማህበራዊ ዘርፍ እና በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል፦ 1ኛ :- በአስተዳደሩ ከአጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች 30% ለሚሆኑት የዝቅተኛ ደመወዝ ተከፉዮች የቤት ክራይ ዱጉማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላልፏል። 2ኛ:- የሃዊ ቦሩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍል ጥያቄን ለመመለስ በአቅራቢያው ባሉ ክፍት ቦታዋች ግንባታ ለማከናወን በቀረበው አጀንዳ በመወወያየት የ1.2 ሄክታር መሬት እንዲሰጠው ውሳኔ ተላልፏል። 3:-ለድሬዳዋ ጠቅላይ መምሪያ የፖሊስ ማሰልጠኛ መአከል ግንባታ የሚውል የ150 ሄክታር መሬት ተወያይቶ ወሳኔ አስተላልፏል። 4ኛ፦በተጨማሪ በተለያዩ መሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ ካብኔው በመወያየት ውሳኔዋችን አስተላልፉል የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
6 8127Loading...
12
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጨዉን ለማገበያየት የሚያስችለው የግብይት ዉል ማጠናቀቁን ገልጿል ጨውን በዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ለማገበያየት የሚያስችሉ አዋጭነት ጥናትና የግብይት ውል ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታዉቋል ። የጨው አማራቾች በከፍተኛ ልፋት ላመረቱት ጨው ተገቢውን ዋጋ አለማግኘትና ከክፍያም ጋር በተያያዘ ለሸጡት ምርት ክፍያቸውን በአስተማማኝ ኹኔታ እያገኙ አለመኾናቸውንና ይህ ዘመናዊ የግብይት ስርዓቱ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተነግሯል። Capital
6 3854Loading...
13
ሌኖ አራት ጎል በቃመበት ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ አርሰናል እስኪጫወት የሊጉን መሪነት የተረከበበትን ነጥብ ማንችስተር ሲቲ ከፉልሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 4ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል። የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ጆስኮ ግቫርዲዮል 2x ፣ ፊል ፎደን እና ጁሊያን አልቫሬዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል። ማክሰኞ - ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ ታላቅ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
6 7033Loading...
14
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት "የቅስቀሳ ወንጀል" ጥፋተኛ ተባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምስራቅ አዉስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ሃላፊ ሊቀጳጳስ አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት "የቅስቀሳ ወንጀል" የጥፋተኝነት ፍርድ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ችሎት ተላለፈባቸው። ከ3 ወራት በፊት የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ስር እና የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች አቅርቦባቸዋል። በቀረበባቸው ክስ ላይ፤ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በጵጵስና በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሃይማኖታዊ ግዴታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ በታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢዉ በሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት አዉደምህረት ላይ በመገኘት "የአመፅ ቅስቀሳ" ማድረጋቸውን ዐቃቤ ሕግ በዝርዝር ጠቅሷል። በዚህ በቀረበባቸው ክስ ላይ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሌሉበት የተከሰሱባቸው ክሶች በአንቀጽ 247 (ሐ) ስር ተጠቃሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል። ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ፋና ዘግቧል። አዲስ ስታንዳርድ
6 5916Loading...
15
ስማቸውን ያልጠቀሳቸው የአርሰናል ተጨዋቾች እየደወሉ ማንችስተር ሲቲን እንዳቆምላቸው ጠይቀውኛል ሲል የፋልሀሙ ግብ ጠባቂ በርንድ ሌኖ ተናግሯል። የፉልሀሙ ግብ ጠባቂ በርንድ ሌኖ የቀድሞ የቡድን አጋሮቹ የአርሰናል ተጨዋቾች በነገው ጨዋታ ፋልሀም  ከማንችስተር ሲቲ በሚያደርጉት ግጥሚያ ለማስቆም የቻለውን እንዲያደርግ ደውለው እንደጠየቁት ገልጿል። ግብ ጠባቂው እንደሚለው እኔም መልሼ ስጋት እንዳይገባችሁ ለማስቆም ያለንን ሁሉ እንሰጣለን ብያቸዋለሁ ብሏል። ቁጥሮች ምን ይላሉ😁👇 በርንድ ሌኖ እስከዛሬ ድረስ ከሲቲ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች ... 🏟️ 9 ጨዋታ ❌ 26 ጎል ገባበት 🔓 0 ክሊን ሺት 🚶‍♂🚶‍♂
6 48710Loading...
16
ኢትዮጵያ የፍልስጤም ሀገርነት ደገፈች ትናንት ለሊት በአሜሪካ ኒወርክ በተካሄደ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፍልፄም ሀገር ትሁን አትሁን በሚል ድምፅ የማሰባሰብ ስነስርዓት ተካሂዷል። በዚህም ኢትዮጵያ ፍልፄም ሀገር መሆን ይገባታል ስትል ድምፅ መስጠቷን ከድርጅቱ ገፅ ለማወቅ ተችሏል። ኢትዮጵያ ፍልፄም ሀገር መሆን ይገባታል የሚለው  ውሳኔ እስራኤልን አስቆጥቷል ተብሏል። ፍልፄም በበኩሏ"ለፍልፄም ነፃነት ድምፅ ለሰጣችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ" ስትል ምላሽ ሰጥታለች። በሌላ በኩል ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ያላት አሜሪካ ግን በተቃራኒው ቆማለች፣አሁንም እስራኤልን እደግፋለሁ ብላለች። ኢትዮጵያን ጨምሮ 143 ሀገራት ፍልስጤም ሀገር መሆን ይገባታል ሲሉ ድምፅ ሰጥተዋል። ዘጠኝ ሀገራት ፍልስጤም ሀገር መሆን አይገባትም በሚል የታቀወሙ ሲሆን አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች 25 ሀገራት ደግሞ ድምፀ ታቅቦ አድርገዋል። እስራኤል ከፍልፄም ጋር ከባድ ጦርነት እያካሄደች መሆኑ ይታወቃል። Addis_Reporter
6 93617Loading...
17
የተቆጣ በሬ ባለቤቱን ወግቶ መግደሉን የኮንታ ዞን ፖሊስ አስታወቀ። ነገሩ እንዲህ ነዉ በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ኮንታ ገነት ቀበሌ ነዋሪ አቶ ፍቃዱ ማሞ አንድ የእርሻ በሬ አላቸዉ እሳቸዉ ሻኛዉን እያሹ ቀንበር ከጫንቃዉ በማድረግ ከሌላኛዉ በሬ ጋር ጠምደዉ ያርሱበታል። የበሬዉና የአቶ ፍቃዱ እርሻ ካላቸዉ ጠምደዉ እያረሱ እርሻ ሳይኖር ሲቀር በሬዎቻቸዉን ጥሩ ሳር ያለበት እያሰሩ ይንከባከቧቸዋል።ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሬዉ ያለወትሮዉ ይጮኸል ጥሩ ሳር ወዳለበት ቀይሩኝ በሚል ድምፁን እየሰሙ የነበሩት አቶ ፍቃዱ የታሰረበትን ገመድ ፈተዉ ሻኛዉን ለመዳበስ ሲሞክሩ በሬ ተቆጣ ተቆጥቶም አላበቃም ግለሰቡን በቀንዱ ወጋቸዉ። መሬት ለመሬት እያንከባለለ በእግሩ መሬቱን እየጫረ በቀንዱ እያነሳ ከመሬት ያፈርጣቸዉ ጀመር።በድንጋጤ የተዋጡት አድኑኝ ሲሉ ተጣሩ ቤተሰቡ ከያለበት ወጣ በሬዉ ቁጣዉ በረታ ደጋግሞ መዉጋቱን ቀጠለ ግለሰቡ ድምፅ አላሰሙም። መንደርተኛዉ ተሰባስቦ በሬዉን በድንጋይ በዱላ አባረሩት ተጎጂዉ ህይታቸዉ አለፈ። ጉዳዮ ፖሊስ ዘንድ መረጃዉ ደረሰ ፖሊስ ደርሶ ህ/ሰቡን አስተባብሮ በሬዉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ተደርጎ ከበረት እንዲዉል ተደረገ። ፖሊስ አንዳንድ ጊዜ የምናሳድጋቸዉ የቤት እንስሳት ዉሻ፣ድመት በግና በሬ የመቆጣት ባህሪ ስለሚያሳዩ ህዝቡ ሁሌም መጠንቀቆ ይኖርበታል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል መረጃዉ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነዉ። ፎቶ ከማህበራዊ ሚዲያ የተወሰደ
6 73910Loading...
18
"እናቱ ናት ክብሩ" ❤ እናቴን እንደ መውደዴ እናትን ለሚያከብሩም ሆነ ለሚያነግሱ ሁሉ ያለኝ ቦታ ከፍ ያለ ነው። በሀገራችን የእግር ኳስ ታሪክ በልምምድ ሜዳ ፣ በጨዋታ ሜዳም ሆነ በሚንቀሳቀስበት ስፍራ ሁሉ የእናቱን ስም በጠለቀ የፍቅር ስሜት ሳይጠራት ውሎ አያድርም ወጣቱ ተጫዋች። ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን መገኛውን ሲያደርግ ነበር የማውቀው በወቅቱ ትልቅ ቦታ እንደሚደርስ ጥርጥር ባይኖረኝም መነሻ የሆነውን ክለብ በመተው ለሀምበሪቾ ፣ ነቀምት እና ንብ በከፍተኛ ሊጉ ጥቂት ዓመታትን በመስመር አጥቂነት ሲጫወት የተመለከትነው ሲሆን በሊጉ ላይም ጎሎችን ከማስቆጠር ባለፈ የየጨወታው ምርጥ ተብሎ ሲሸለም ታዝቤያለሁ ጎል አስቆጠረም ፣ ተሸለመም ወይንም ምንም ነገርን ብቻ ያድርግ የእናቱ ፎቶ ከውስጥ ልብሱ እና ስሟም ከአፉ ጠፍቶ አያውቅም። በያዝነው ዓመት በፕሪምየር ሊጉ ለመጫወት ለሻሸመኔ ከተማ ፊርማውን አኑሮ የነበረ ቢሆንም የተለመደው የሀገራችን እግር ኳስ አሰራር በትልቁ የሊግ ዕርከን ላይ እንዳናየው በማድረጉ ተጫዋቹ በመጨረሻም ባለፈው ዓመት ወደነበረበት ንብ ክለብ ተመልሶ አስደናቂነቱን ከማሳየት በተጨማሪ የእናቱን ስም ፣ ክብር እና ፍቅሯን በየጊዜው ሜዳ ላይ ማውሳቱንም ቀጥሏል። በዚህ ዘመን እኛ ሰዎች ሲደላን ከድሎታችን ውጪ መነሻችንን በምንረሳበት እና የመጣንበትን መንገድ ሁሉ እየረሳን በምንገኝበት በዚህ ዘመን እንደ ታምራት ስላስ ያሉ ወጣቶች ዘጠኝ ወር ከመሸከም አልፋ አቅፋ ፣ ተንከባክባ ላሳደገች እናት ምንም ቢደርግላት ፣ ስሟን በፍቅር ብንጠራትም ሆነ ብናከብራት ያንስባታል 💪 እናትን ለሚያከብሩ ሁሉ ክብር አለኝ ለምን እናቴ ለእኔ ብዙ ነገሬ ስለሆነች ብቻ ታሜ እናትህን ፈጣሪ በዕድሜ በጤና ያቆይልህ አንተ በርታ 🙏🙏🙏 በ ቴዎድሮስ ታከለ ነገ የእናቶች ቀን ነው 🥰
6 8874Loading...
19
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ያስገነባቸውን ቤቶች አስተላለፈ የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በኮየ ፈጬ እና በቃሊቲ ሳይቶች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስተላለፈ። በቤቶቹ ማስተላለፍ በስነ-ስርዓት ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ቤቶቹ በኦቪድ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የተጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል። (ኤፍ ቢ ሲ)
6 2345Loading...
20
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የደቡብ አፍሪካ ጉዞአቸውን የሰረዙት ራሳቸው ናቸው - ይኸን አስመልክቶ የሐሰት ዜና መሰራጨቱ ቤተክርስቲያንን አሳዝኗል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣ ቅዳሴ ቤቱን ለማክበርና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ እንዲሁም ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ማለዳ ከቅዱስነታቸው ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ መርሐ ግብር ይዘው እንደነበር ይታወቃል። ይሁን እንጂ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ካለባቸው ተደራራቢና አስቸኳይ ሥራዎች አንጻር ለአሥር ቀናት ከጽሕፈት ቤታቸው ርቀው መቆየት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎች ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር በመስጋታቸው እንዲሁም ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊውና ምክትል ሥራ አስኪያጁ በሌሉበት በቢሮኘቸው በሌሉበት ሁኔታ ለበርካታ ቀናት ከጠቅላይ ጽሕፈቱ ርቀው ከተጓዙ ሥራዎች ስለሚበደሉ ቀደም ሲል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉዞ ከቅዱስነታቸው ጋር በጥሞና በመወያየት ለመሰረዝ ተገደዋል። ይሁን እንጂ እውነታው ይኸው ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ ብፁዕነታቸው ወደ ኤርፖርት እንዳይሔዱ እንደተከለከሉና ፓስፖርታቸው እንደተያዘ በማስመሰል የሚሰራጨው ዜና ፍፁም መሰረተ ቢስና የሐሰት ዜና ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
6 2756Loading...
21
በትግራይ 81 በመቶ ወጣት ስራ-አጥ ነው፣ 89 በመቶ ወጣቶች ትዳር መመስረት አንፈልግም ብለዋል ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የነበረችው ትግራይ በጦርነቱ ማግስት ከገጠሟት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አንዱ የወጣቶች በገፍ ክልሉን እየለቀቁ መሰደድ ነው። በትግራይ ስደት ከጦርነቱ በፊትም የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ ግን እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ እንደጨመረ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ሓይሽ ሱባጋድስ ለዋዜማ ተናግረዋል። እድሜያቸው ከ 15 እስከ 18 የሚሆኑ ታዳጊዎች ትምሕርታቸውን አቋርጠው ከአገር እየወጡ እንደሆነ፣ አብዛኞቹ በየመን እና ሳውዲ አረቢያ እስር ቤት ወስጥ ቀሪዎቹ ደግሞ በሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች እጅ እንዳሉና በርካታ ወጣቶችም በመንገድ ላይ እና በበረሃ እየሞቱ እንደሆነ መረጃዎች ይደርሱናል ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል። ከወራት በፊት የመንን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊገቡ ሲሉ በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ከተገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና፣ ጅቡቲ ላይ በጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ካጡት መካክል፣ አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊው ለዋዜማ አረጋግጠዋል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት እየታየ እንኳን በቀሪዎቹ ወጣቶች ላይ የመሰደድ ፍላጎት ሲቀንስ አለመታየቱ በትግራይ ክልል ያለው ችግር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ይላሉ ሓይሽ። እንደ አይ ኦ ኤም ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጡት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዚህ ውቅት እንደ አገር ያለው የስደት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሚያሳይ ሲሆን ፣ በትግራይ ያለው ግን ከዚያ የተለየና ለመቆጣጠርም አዳጋች የሆነ ነው። ትግራይ ውስጥ ባሉ የተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከ 500 ሺሕ በላይ ተፈናቃይ ወጣቶች አሉ፣ በመጠለያ ጣቢያው በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ባለመኖሩና ምንም አይነት ለነገ የሚሉት ተስፋ የሚታያቸው ባለመሆኑ ወጣቶቹ ስደትን ቀዳሚ ምርጫቸው አድርገዋል ብለዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ ወጣቶቹ በብዛት እየተሰደዱ ያሉት ከምሥራቅ እና ደቡብዊ ዞኖች፣ከሰሜን ምዕራብ እና ሰሜናዊ የትግራይ አካባቢዎች፣ከመቀሌ ከተማ እና አካባቢዋ በተወሰነ መልኩ እንደሆነ ኃላፊው ሓይሽ ተናግረዋል። ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንዲሁም የሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ለመሰደዳቸው ሌላው ምክንያት እንደሆነ ሓይሽ ያስረዳሉ። ዋዜማ በዚሁ ጉዳይ ላይ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማኅበርን ያነጋገረች ሲሆን ማኅበሩ በክልሉ ያለው ሥራ አጥነት ያስከተለው የወጣቶች ስደት እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል። የክልሉ ወጣቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ሠናይ ከሓሳይ ለዋዜማ እንደተናገሩት ማኅበሩ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በመተባበር በ 10 ወርዳዎች፣ በ 30 ቀበሌዎችና በ1 ሺህ 200 መቶ ወጣቶች ላይ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ማድረጉን ገልጸዋል። የጥናቱም ፍለጋ ከጦርነቱ በኋላ የወጣቱ መተዳደሪያ ምንድነው?፣ትምሕርት ጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ከማግኘት አንጻር ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ለዋዜማ አስረድተዋል። ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ባለመኖራቸውና በክልሉ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም የሚጨበጥ ተስፋ ባለመኖሩ ምክንያት ካሉት ወጣቶች መካከል ግማሽ ያህሉ የመሰደድ ሃሳብ ያላቸው እንደሆኑ በተደረገው ጥናት መሰረት ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። ጥናቱ እንደሚያመለክትው በዚህ ወቅት ትግራይ ውስጥ ካሉ ወጣቶች መካከል 81 በመቶ የሚሆኑት ሥራ አጥ መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ እነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ከጦርነቱ በፊት የራሳቸው ተቋም የነበራቸው፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ፣ መልካም የሚባል ሕይወት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸውና ከጦርነቱ በኋላ ግን ያላቸውን ጥሪት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያጡ ናቸው ሲሉ። ከትምህርት ፍላጎት ጋር ተያይዞ በወጣቶቹ ላይ በተደረገው ጥናት ካሉት ወጣቶች መካከል 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የመማር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው የሚሉት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት በጦርነቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸን ያላቸውን ነገር በሙሉ ስላጡ እኛን የሚያስተምሩበት አቅም የላቸውም የሚል እንደሆነ አብራርተዋል። ከሥራ ፈጠራ አንጻር፣ 31 በመቶ የሚሆኑት የራሳችን ሥራ ፈጥረን እንሰራለን የሚሉ እንደሆኑ 29 በመቶዎቹ ደግሞ በተለያዩ መንግሥታዊና የግል ተቋማት ተቀጥረን መስራት አለብን የሚል ሃሳብ ያላቸው፣ ቀሪዎቹ ግን የመሰደድ ፍላጎት ያላቸው ናቸው ብለዋል ከነዚህ የመሰድድ ፍላጎት ካላቸው ውስጥ 53 በመቶዎቹ እድሜያቸው ከ 26 እስከ 35 ባለው መካከል የሚገኝ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ግን ከ 15 እስከ 25 ባለው መካከል እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ በክልሉ ካሉ ወጣቶች 78 በመቶ የሚሆኑት ምንም አይነት የበይነ መረብ አገልግሎት እንደማያገኙ 97 በመቶ የሚሆኑት የኮምፒዩተር አገልግሎት፣ 29 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የስልክ አገልግሎት የሌላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ሥራ ለመፈለግና የሚወጡ የሥራ እድሎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን ለማየት አስቻይ ሁኔታ የላቸውም በማለት ተናግረዋል። ከማኅበራዊ ሕይወታቸው ጋር ተያይዞ 89 በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ትዳር የመያዝ፣ ኃላፊነት የመውሰድና ቤተሰብ የመመስረት ፍላጎት እንደሌላቸው ባደረጉት ጥናት ማረጋገጣቸውን ተናገረዋል። በሌላ በኩል ትግራይ ከጦርነቱ መገባደድ በኋላ የዝናብ እጥረት ያስከተለው ድርቅ፣ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ተደማምረው የደቀቀው ምጣኔ ሀብቷ ለወጣቱ መሰደድ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል። ዋዜማም በሕገወጥ መንገደ ተሰደው በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች በስልክ አነጋግራለች። ሕሉፍ ዓባይ ተወልዶ ያደገው በሽረ እንዳ ሥላሴ ከተማ ገባር ሽረ በተባለ አካባቢ እንደሆነ ለዋዜማ የገለጸ ሲሆን፣ በዚያም የሚተዳደረው በብረት ብየዳ ሥራ እንደነበር፣ በጦርነቱ ምክንያት ግን ያለው ሃብት ንብረት በሙሉ እንደወደመትና ባዶ እጁን እንደቀረ ይናገራል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት መሆኑን የሚገልጸው ሕሉፍ የሚያደርገው ቢጠፋው የራሱንንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማሰንበት በሕገ ወጥ መንገድ መሰደድን መምረጡን ገልጿል። ሕሉፍ ያሰበውና የሆነው ለየቅል እንደሆነበትና በሳውዲ አረቢያ የጸጥታ ኃይሎች ተይዞ በእስር ቤት ውስጥ አስቸጋሪ ሕይወት መግፋት ከጀመረ አምስት ወራት መቆጠራቸውን አስረድቷል። ሌላኛው ከውቅሮ ከተማ ተሰዶ እንደወጣና ትምህርቱን ከአስራ አንደኛ ክፍል እንዳቋረጠ የሚናገረው ሀበን ተስፋይ ቤተሰቦቹ ሊያስተምሩት አቅማቸው ባለመፍቀዱ ስደትን መምረጡን ገልጿል። በእስር ቤቶቹ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰደው የወጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች መኖራቸውን ዋዜማ በእስር ቤቱ ወስጥ ካሉ ሰዎች ማረጋገጥ ችላለች። ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገረቻቸው የክልሉ ወጣቶች ቢሮና የወጣቶች ማኅበር ወጣቶቹን ከስደት ለመታደግ በፌዴራል መንግስቱም ይሁን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት እጅግ አነስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ዘገባው የዋዜማ ነው
6 04311Loading...
22
Media files
5 6443Loading...
23
በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል 460 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ከምዕራብ ኤሲያዊቷ ሀገር ኦማን ማቆያ ጣቢያዎች ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተጠቆመ። በህገወጥ መንገድ ገብተዋል በሚል በሀገሪቱ ማቆያ ጣቢያዎች ታስረው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል በትላንትናው ዕለት ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም 230 ዜጎች (ሁሉም ወንዶች ናቸው) ተመልሰዋል ተብሏል። ከሚያዚያ 29 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከኦማን ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 460 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተጠቁሟል። በኦማን የሚገኙ 1590 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር ለመመለስ መታቀዱን ከሴቶች እና ህጻናት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
6 3574Loading...
24
ኪሊያን ምባፔ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ ይፋ አደረገ ኪሊያን ምባፔ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ በማህበራዊ የሚድያ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡ ፈረንሳያዊው አጥቂ ምባፔ ሪያል ማድሪድን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
7 1055Loading...
25
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ጋር ለሁለት ዓመት የሚያቆያቸውን ውል ተፈራርመዋል። በሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ እየተሳተፈ የሚገኘውን ብሔራዊ ቡድን በማሰልጠን ላይ የምትገኘው አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ጊዜያዊ ኮንትራቷን ቋሚ በማድረግ እስከ 2018 ድረስ የሚያቆያትን ውል በዛሬው ዕለት በይፋ ተፈራርማለች።
7 2533Loading...
26
በእስያዊቷ ኢንዴኖዢያ የተፈጠረው ክስተት አያድርስ ያስብላል🙆‍♀ ስጦታ ለመውሰድ ሲል ሴት መስሎ ጋብቻ የመሰረተው ጎረምሳ መጨረሻው ዘብጥያ መውረድ ሆኗል፡፡ ስሙ ያልተጠቀሰው የ26 ዓመቱ ይ ኢንዶኔዢያዊ በፌስቡክ አንድ መልከመልካም ሴት ይተዋወቃል፡፡ ከዚህ ቆንጆ ሴት ጋር በየቀኑ ያወራሉ፣ ይደዋወላሉ፡፡ ይህ መላመድ ወደ ፍቅር አድጎ በአካል ወደ መገናኘት ያመራ ሲሆን ይህም ድግግሞሽ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ ነበር ተብሏል፡፡ በዚች ቆንጆ ፍቅር መውደቁን ያመነው ይህ ሰውም የፍቅር ጥያቄ አቀርቦ ጥያቄውም ተቀባይነት ያገኛል፡፡ በሀገሩ ባህል እና ሀይማኖት መሰረትም ጋብቻ ለመመስረት ይስማማሉ፡፡ ይሁንና ሚስት ለመሆን የተስማችው ይህች ቆንጆ እናቷ በቅርቡ እንደሞተች መላው ቤተሰቧም ሀዘን ላይ በመሆናቸው ሰርጓ ላይ መገኘት እንደማይችሉ ባሏን አሳምናለች፡፡ ባልየውም ቅር እያለው የእሱ ቤተሰቦች በተገኙበት ጋብቻቸው ይፈጸማል፡፡ ልጃቸው ቆንጆ ሚስት በማግባቱ ደስ የተሰኙት የሙሽራው ቤተሰቦችም ከምራታቸው ጋር ለመቀራረብ እና ለመላመድ ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ ሙሽራው እና ቤተሰቦቹ ባዩት ነገር ቅር መሰኘታቸውን ተከትሎ ጉዳዩን ለማጣራት ይወስናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ባደረጉት ማጣራትም መልከ መልካሟ ሴት የ25 ዓመት ጎረምሳ መሆኑን ደርሰውበታል ሲል የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡ ጉዳዩን ወደ ፖሊስ የወሰዱት የባል ቤተሰቦችም ሴት መስሎ ያታለላቸው ጎረምሳ ቤተሰቦቹ በህይወት እንዳሉ ጋብቻውን ሴት መስሎ የፈጸመውም ስጦታ ለመቀበል ሲል እንደሆነ ፖሊስ በምርመራው ደርሶበታል፡፡ መዋቢያዎችን እና አልባሳትን ተጠቅሞ ሴት መስሎ ጋብቻ የፈጸመው ጎረምሳም በፖሊስ ተይዞ ለእስር የተዳረገ ሲሆን ባደረገው ማጭበርበር ለተጎጂ ቤተሰቦች የሰርግ ወጪ ካሳ እንዲከፍል ክስ ተመስርቶበታል፡፡ እንዲሁም ለፈጸመው ማጭበርበር ወንጀልም የአራት ዓመት እስር ይጠብቀዋልም ተብሏል፡፡ via  Ouddity central and Al ain Amharic
7 56922Loading...
27
Media files
6 9872Loading...
28
ናይጄሪያ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን ሞት መቅጣት ልትጀምር ነው በናይጄሪያ ሴኔት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የቀረበዉ በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ላይ የሞት ቅጣት ለመጣል የሚያስችለዉን ረቂቅ ህግ አጽድቋል።እስካሁን ህግ ያልሆነው የሞት ፍርድ ቅጣት አሁን ላይ በመጽደቁ ቀደም ሲል እጅግ ከፍተኛ ተብሎ የተጣለዉን የእድሜ ልክ እስራት ይተካል ተብሎ ይጠበቃል። በዳኝነት እና አደንዛዥ እጾች የመከላከል የጋራ ኮሚቴዎችን በመወከል በሴኔተር መሀመድ ሞንጉኖ ረቂቅ ህጉ ቀርቧል፡፡ረቂቅ አዋጁን የደገፉት ሴናተሮች የሞት ቅጣት ከእድሜ ልክ እስራት በተሻለ ለአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ጠንካራ መከላከያ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ ተከራክረዋል። ነገር ግን እርምጃውን የተቃወሙ የህግ አውጭዎች ያሉ ሲሆን የሞት ቅጣት የማይቀለበስ በመሆኑ የተሳሳቱ የፍርድ ዉሳኔዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።አብዛኛዎቹ ሴናተሮች ህጉን ለመደገፍ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የናይጄሪያ የመድሃኒት ህግ ማስከበር ኤጀንሲ በአደንዛዥ እጽ መከላከል ላይ የሚያደርገዉን ስራ ለማጠናከር ያስችለዋል፡፡ረቂቅ ሕጉ ሕግ ሆኖ ለመተግበር የፕሬዚዳንቱን ፊርማ ይጠብቃል። ናይጄሪያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከካናቢስ እስከ ኦፒዮይድ የሚባሉት አደንዛዕ እጾችን በአዘዋዋሪዎች ሰፊ ሰንሰለት የተነሳ ሰዎች ጋር በቀላሉ እየደረሰ ይገኛል፡፡ በስምኦን ደረጄ
7 4205Loading...
‹‹ዛሬ በባህርዳር ከተማ የተመረቀው የአባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው። ከግዘፋዊ ቁሳዊ መዋቀሩ ባሻገርም ልዩነቶችን የማጥበብ፤ በተቃራኒ ጎራ ላሉ ሰዎች መገናኛ ድልድዮችን የማነፅ ርዕያችን መዘርጊያ ምልክት ነው። ኅብረታዊ ምሉዕነትን ለማፅናት ከክልላዊ ወሰኖች የሚሻገር ትርክት የመቅረፅ ትልማ ማሳያ ነው። ግባችን በክልከላ እና ቁንፅልነት የሚመሩ የአእምሮ ውቅሮች እና ትርክቶችን በማስወገድ በሁሉም ዘንድ ትብብርን እና አንድነት ማሳደግ ነው።›› -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Mostrar todo...
👎 21👍 20😁 4 3
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል 🔥 በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ደጋፊዎችን ያፈሩት ከቀድሞው የፕሪምየር ሊግ ምስረታ ጀምሮ በከፍተኛ ትንቅንቅ ይፎካከሩ የነበሩት አሁን እንዱ እንደስሙ ማደር የተነሳነው አንዱ ከቀድሞ ስሙን ለመመለስ በመጣር ላይ ሆነው በሊጉ 37ኛ ሳምንት ተገናኝተዋል። የሁለቱ ጨዋታ ሲኖር ዲኤስቲቪ ቤቶች በቶሎ ይሞላሉ ጠጠር መጣያ እስኪታጣ ድረስ ወንበሮች ጢም ብለው ይሞላሉ ብሽሽቁ ይደራል ነቆራው ከየቦታው ይሰማል ለ 90 ደቂቃም ከተማው ፀጥ ረጭ ይላል። 37ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪምየር ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል የጨዋታ ሰዓት - አመሻሽ 12:30 🏟️ ስታድየም - ኦልድትራፎርድ ማን ያሸንፋል…? ዩናይትድ የመድፈኞቹን ጉዞ ያደናቅፋል ወይስ መድፈኞቹ ቀያይ ሴይጣኖችን አጋድሞ ያልፋል?
Mostrar todo...
👍 29🔥 7 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በዚህ መርሐግብር መሰረት ተዘጋጁ👆 የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡ መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:— ✔ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ✔ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።
Mostrar todo...
👍 6 1😁 1
ከፒያሳ በሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ለኮሪደር ልማት ፕሮጀክት 3,250 አባወራዎች ይነሳሉ ተባለ ከፒያሳ በመነሳት በሳር ቤት በኩል እስከ ወሎ ሠፈር ድረስ የሚገነባው አዲሱ የኮሪደር ልማት፣ 3,250 አባወራዎችን ወይም ከ14 ሺሕ በላይ ሰዎችን እንደሚያስነሳ ተመላከተ፡፡ ተነሺዎችን ለማስፈር 21 ሔክታር መሬትና ስድስት ቢሊዮን ብር የካሳ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡ ከአሥር ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ከፒያሳ በመነሳት እስከ ብሔራዊ፣ ከብሔራዊ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሳር ቤትና ከሳር ቤት እስከ ወሎ ሠፈር ተብሎ በአምስት ንዑስ ፕሮጀክቶች ተከፋፍሎ ዲዛይን እንደወጣለት ሪፖርተር የተመለከታቸው የዲዛይን ዶክመንቶች ያሳያሉ፡፡ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ አምስት ክፍላተ ከተሞችን የሚነካ ሲሆን እነዚህም አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክና ቦሌ ናቸው፡፡ ጠቅላላ ፕሮጀክቱ 460 ሔክታር መሬት ይዞታ የሚነካ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 114 ሔክታር ለመልሶ ማልማት ነፃ እንደሚደረግ ዶክመንቱ ያሳያል፡፡ ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለአብነት ያህል ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ለፈጣን የአውቶቡስ መስመር ግንባታ ይውላል፡፡ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማኅበራዊ ቤቶች ግንባታ፣ ስድስት ቢሊዮን ለተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ አራት ቢሊዮን ብር ለመንገድ ግንባታ፣ ሦስት ቢሊዮን ለፓርክ (Green Park) ተመድቧል፡፡ በተጨማሪም የፓርኪንግ ቦታዎች፣ ሰባት ያህል ድልድዮች፣ የመሠረተ ልማትና የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች ይገነባሉ፡፡ ወጪ የሚደረገውን 40 ቢሊዮን ብር በአምስት ዓመታት ውስጥ በእጥፍ ለማስመለስ መታቀዱንም ሰነዱ ያመለክታል፡፡ በኮሪደር መስመሩ ላይ መንግሥት 114 ሔክታር መሬት ነፃ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን፣ ይኼንን መሬት 70 ሺሕ ብር በካሬ ለአልሚዎች በማከራየት በአምስት ዓመት ውስጥ 99 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ዶክመንቱ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዚህ መስመር ላይ መንግሥት ሊያከራያቸው ካቀዳቸው የመኖሪያ፣ የንግድና የቢሮ ሕንፃና ቤት ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ በየዓመቱ ገቢ ለማስገኘት መታቀዱ ታውቋል፡፡ ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ አብዛኛው ቦታ ለአረንጓዴ ልማት ማለትም ለሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ታቅዷል፡፡ አምባሳደር አካባቢ ያለው የመከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ሙዚየም፣ ካፌና መዝናኛ የሚኖረው የባህል ማዕከል እንደሚቀየር ዲዛይኑ ያሳያል፡፡ የሰይጣን ቤት ተብሎ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ያለው ቦታ ወደ ባህል ማዕከልና መዝናኛ ቦታ በመጠነኛ ለውጥ ያደርጋል፡፡ ከአፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት ያለው 1.2 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ‹‹የአፍሪካ ማዕከል›› ለመገንባት ይውላል፡፡ ማዕከሉ ሙዚየም፣ ላይብረሪ፣ የባህልና መዝናኛዎች ሲኖሩት አጠቃላይ አካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ ያለው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አገልግሎት ይቀየራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሜክሲኮ ሳር ቤት ባለው ንዑስ ፕሮጀክት ከታሰቡት ብዙ ዕቅዶች ውስጥ ሆስፒታልና አዲሱ ቱሞሮ (Adisu Tomorrow) ልዩ የኢኮኖሚ ዞንም ይገኝበታል፡፡ በዚህ አካባቢ ከአራት ወለል ሕንፃ (G+4) በታች የሆኑ ሕንፃዎች ሁሉም ይፈርሳሉ፡፡ የኮሪደር ልማቱን ለማስፈጸም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች ጽሕፈት ቤት፣ የከተማ አስተዳደሩ፣ የአዲስ አበባ ዕቅድና ልማት ኮሚሽንን ጨምሮ ሃያ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ሪፖርተር | አሸናፊ እንዳለ
Mostrar todo...
👍 34👎 12 1😱 1🤬 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ-ቤተክርስቲያኒቱ እንዳይዛመት ማድረግ የቻሉ ሲሆን በጋራዡ የነበሩ ቁጥራቸዉ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ማዳን ችለዋል።በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልመድረሱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል። በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የያዙት ነዳጅና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች እንዲሁም ንግድ ሱቆቹ እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ቆርቆሮና መሰል ግብዓቶች መገንባታቸዉ  ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል። የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ጋራዦች ደረጃቸዉን በጠበቁ ግብዓቶች የተገነቡና ከንግድ ሱቆች ከመኖሪያ አካባቢዎች  የራቁ መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል። የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ብስራት ለማወቅ ችሏል። ዳጉ_ጆርናል
Mostrar todo...
😢 13👍 11😱 3 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማራ ክልል ገብተዋል ጎርጎራ‼ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ቅዳሜ በአማራ ክልል በገበታ ለሀገር በለማው ጎርጎራ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለበት ነው የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጎርጎራ የተገኙት።
Mostrar todo...
😁 40👍 25👎 12 2😢 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማራ ክልል ገብተዋል ጎርጎራ‼ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ቅዳሜ በአማራ ክልል በገበታ ለሀገር በለማው ጎርጎራ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለበት ነው የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጎርጎራ የተገኙት።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ይቺን ምድር ከፈጣሪ በታች የቀላቀለችን ፤ አለም ፊቷን ብታዞርብን እሷ ግን በደስታ ምትቀበለን ፤ ለኛ ሁሉ ነገራችን የሆነች ፤ ከአይኗ ብሌን በላይ ምትሳሳልን እናታችን ቀኗ ነው በእርግጥም ሁሉም ቀን እናታችንን ማክበር አለብን ነገርግን ዛሬ ልዩ ቀኗ ነው። እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፤ የእናቶቻችሁን ደስታ ያሳያችሁ ፤ መልካም ቀን!
Mostrar todo...
110👍 16🔥 4😢 1

👍 69 36👏 9