cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ስብዕናችን #Humanity

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Mostrar más
Advertising posts
30 705Suscriptores
-1224 hours
-647 days
-26530 days
Archivo de publicaciones
💡ያለፈበት ብቻ ያውቀዋል!! ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱን ሰዎች ስለ ትናንት ህይወታቸው ስትጠይቃቸው ሁሉም ፊት ላይ ደስተኝነትን አታነብም:: ሁሉም በእምባ እናም በትጋዜ ተሞልተው ይነግሩሀል፣ ከሙቀት ዋሻህ ውስጥ የምትወጣበት፣ከተወዳጅነት አጀብታ ለነፍስህ ፍላጎትና ለህልምህ የምትወርድበት ጥልቁና አስፈሪው የህይወት መንገድህ ነው። 📍ያስፈራል ልብ ያርዳል ነገር ግን ነፍስን ለጥበብ ይቀርፃል። በዛ ውስጥ ሰው ይርብሀል ።ተቃዋሚህ ይበዛል:: እጅ ጠቋሚው ተሳላቂው ይከብሀል:: ብታወራ የሚረዳህ አንዳች አይኖርም!! የሚፈርድ እልፍ ይሆናል...ህመሙ ጥልቅ! የስሜት ጉዳቶቹም ብርቱዎች ናቸው። ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ትልቅ ህልም እያላቸው ትንሽ ሆነው መኖርን የሚመርጡት!አስፈሪውም ትልቅ ህልምህ ወደ ትልቅነት የሚመራህ በትናንሽ የህይወት ጉዳዶች ውስጥ መሆኑም ነው። ብቻህን የምታለቅስበት ብቻህን የምትፋለምበት ብቻህን ሞትን ምትናፍቅበት ግን ደግሞ ብቻህን የምትዘምርበት ብቻህን የምትፀልይበት ብቻህን አምላኬ ብለህ ከፈጣሪህ ጋር የምትነጋገርበትም መንገድ ነው። 💡መከራ የፈጣሪ ትህምርት ቤት ነው። "ስቃዮች መገፋቶች መድከሞች መውደቆች  ሁሉም የነፍስ ጥልቅ ህመሞችህ በስተጀርባ መምህሩ አምላክህ አለ።ለዛም ነው ማስተርስ ጫንኩኝ ከሚለው ሰው በተሻለ ህይወት ያስተማረቻቸው አለምን ሲመሩ ሲቆጣጠሩት የትምመለከተው! ''ሰውን ካስተማረው ፈጣሪ በጥበብ አስውቦ የቀረፀው ይበልጣል'' ከሙቀት ጎጆህ ስትወጣ! ህልምህን ከፈጣሪህ ምሪት ጋር ትከተለዋለህ! የግድ ይሆንብሀል አማራጭ ታጣለትህ ብትቀመጥ የሚወጋህ ሺ ስለሚሆን ይግድ ትጓዛለህ እየዛልክ ትጠነክራለህ እየሞትክ ህያው ትሆናለህ እየወረድክ ከፍፍ ትላለህ የግድ ይሆንብሀል...! 📍ህይወት ፊቷን የምምትሰጠው ጠንካራ ጡንቻ ላላቸው ሳይሆን ጠንካራ መንፈስ ላላቸው ነው። ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን። 💡ወደ ቁልቁለቱም ድፈር! ወደ አስፈሪው መንገድ በድፍረት ጥለቅ ፣ አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር....። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል። 📍የህይወትህን ሲኦል ካልተጋፈጥክ የስኬትህን ብርሀን መቼም አትለብሰውም ፣ የከፍታውን መንገድ በመውርደት ፣ የደስታውን መንገድ በሀዘን ፣ የንግስናን መንገድ በባርነት ፣ የመሪነትን መንገድ በተመሪነት ፣ የስኬትንም መንገድ በውድቀት በኩል ውስጥ ትገናኛቸዋለህ! አለም ለደፋሮች ታደላለች። ወደ ከፍ ያለ ማንነት ጉዞ ፣ስትጀምር የነፍስክ ጥንካሬ ተአምራዊ ወደ ሆነ ቦታ ያደርሥሀል፣ ድፋር ሁን! ለህልምህ ቆራጥ ሁን ፣ የህይወት ብርሀንህ የሚወለደው ከዛ እርምጃህ ነው! ዉብ ጊዜን ተመኘን ❤ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
41👍 38👎 3
👍 1
💎አንዳንዱ ሰው ዛሬ የሚኖርበት ቀን ትናንቱ ነው:: ትናንት ወድቆ ነበር፣ ተሳስቶ ነበር ፡፡ ትናንት የሆነ ነገር በህይወቱ አልፏል፡፡ ትናንቶቹ በትዝታ እየመጡ ዛሬውን ይነጥቁታል፡፡ የሰው ልጅ ውድቀቱ ብቻ ሳይሆን ስኬቱም ጠላቱ ነው ይባላል፡፡ 📍በረጋ ውሀ ላይ ሁሉም ሰው ጎበዝ ካፒቴን መሆን ይችላል፤ግን የእውነተኛው ካፒቴን ችሎታ በማእበሉ ጊዜ ይታያል፣ እንደሚባለው ሁሉ የህይወታችንም መሪነት ትናንት አሁንና ወደፊት በገጠሙንና በሚገጥሙን መሰናክሎች ይፈተናል። የውስጥ ጥንካሬያችንም በነዚሁ ጊዜያት ይፈተሻል። የተሳካ ህይወት መኖር የማይፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሁሉም ሰው ታሪክ መፃፍ ይፈልጋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ራሱን መመርመር አለበት ፣ የሰው ልጅ ከፍታና ዝቅታ፣ መነሳትና መውደቅ በሚገነባው የስብዕና ጥንካሬ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን በምናወራበት ሰዓት ነገ ብለን ስናስብ፣ ጊዜያችንን አዲስ ማድረግ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም አእምሮዋችን ስላለ ፣ አእምሮዋችን ሁሉን ያስታውሳል፡፡ 💎እራስን መለወጥ ቀላል ጉዞ አይደለም። እንደ አብዮት ቆጥረን ለዘመናት ተብትቦን የኖረውን ማንነት ገርስሰን መጣል አለብን ፣ ደካማው ማንነታችን ወርዶ ስኬታማው ማንነታችን ሊነግስ ይገባዋል። ብዙዎቻችን ውስጣችን ትርምስምስ ብሏል፤ የምንፈልገውን አናውቅም፤ የምንራመድበትን መንገድ አናውቅም፤ ብዙ ሃሳቦች በውስጣችን አሉ፤ ግን በየትኛው ሃሳብ ጸንተን እንኑር? ለዚህ ነው በራሳችን ላይ አብዮት መጥራት የሚያስፈልገን። ህይወት እጅግ አጭር ናት፤የፈለግነውን አይነት ኑሮ ለመኖር፤ እራሳችንን መለወጥ ግድ ይለናል፤ ደካማውን ጥለን፤ መልካሙን እኛነታችንን ልንተክል ጊዜው አሁን ነው።            ውብ ቅዳሜ❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Mostrar todo...
📍ወዳጄ ሆይ አስተውል ምድራችን ስለፍትህ በሚያወሩ ግን ደግሞ ለሕግ በማይገዙ፣ፍቅርን በሚሰብኩ ግን በፍቅር ለመኖር ምንም ጥረት በማያደርጉ፣ የፈጣሪን ቃል በሚያደምጡ ግን ደግሞ ቃሉን በማይኖሩ ሰዎች የተሞላች ናት፡፡ ልብ በል ወሳኙ ነገር የምትኖርበት ቦታ ሳይሆን አኗኗርህ ነው፡፡ ከምታምንበት ነገርም በላይ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባው ባመንክበት ነገር እንዴት ትኖራለህ የሚለው ነው 💡ወዳጄ ሆይ፥ ከዚህ አገር እዚያ አገር ፣ ከምዕራብም ምሥራቅ ይሻል በማለት አትዋትት ። ከሁሉ የሚሻለው ሕይወትን ከነሙሉ ትርጕሟ መቀበል ነው ። ማንም ሰው ከጠባቡ ግለኝነት ሕይወት ወደ ሰፊው ጠቅላላው የሰው ልጅ ምልከታ ከፍ እስኪል ድረስ መኖርን ተማረ አይባልም፡፡ እናም ማለዳ ማለዳ አዲስ ትርጉም ባለው መንገድ ለመኖር ራስህን መመልከትህ ወደ ፊት ከመመልከት ጋር ሊዋሐድ ይገባዋል፡፡ ወዳጄ ሆይ ሕይወት በእንግዳ ክስተት የተሞላች ናት ። የታወከ ሌሊት ሲገጥምህ በሰላም ስላደርክባቸው ሌሊቶች አለማመስገንህን አስብ ። ወዳጅና ወዳጅን አጣልቶ አንዱን የአንዱ ጠባቂ በማድረግ ትርፍ ይገኛል ብለህ አትሸወድ፣ ከፍቅር እንጂ ከሴራ አንድም ትርፍ አይገኝም። ጉድጓድ መጀመሪያ የሚቀብረው ቆፋሪውን ነውና ክፋትን አታስብ ። 💡ወዳጄ ሆይ ! እልህ ከራስ ጋር ገመድ መጓተት ነው ። የማይቀጥሉ ነገሮችን መሬት ላይ አስቀምጣቸው ፤ አየር ላይ ከተበተኑ  ጉዳት ያመጣሉ ። “የጨዋ ልጅ ሲፋታ የሚጋባ ይመስላል” እንዲሉ ። ያለትግል ያለሁካታ በሰላም መራመድን ልመድ፣ የሃያ ዓመቱም የሰማንያ ዓመቱም ሁለቱም የዕድሜ ስስት አለባቸው ። በምናልባት መኖር ጉልበት ይጨርሳል ። ውሳኔ ማጣትም ዕድሜን ይፈጃል ፣ መኖርህ አለመኖር እንዳይሆን በማስተዋል ተራመድ ። 📍ወዳጄ ሆይ ትልልቅ ዛፎች የጀመሩት ከችግኝ ነውና ትንሽነትህ ትልቅነትህን አልደርስበትም ብሎ አይስጋ ። በትዕግሥትና በጊዜ ውስጥ የማይደረስበት ነገር የለም። ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ፣ በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሳቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም ። ያለ ውሳኔ በዚህ ዓለም ላይ መንቀዋለል ይቻላል ፣ መጓዝ ግን በፍጹም አይቻልም። እናም ወዳጄ ስንኖር ብዙ ነገሮች የተቀላቀሉባቸው ሰዎች ያጋጥሙናል ። ስለ ሰላም የሚያወራው በአሳቡ ብዙ ጦርነት ላይ ነው የአሳብ ፍልሚያ ያለባቸው ፖለቲካና ሃይማኖት የተቀላቀለባቸው የጦር መሣሪያ የጨበጡ ብዙዎች ናቸው። ጦርነት የሚቀሰቀሰውም የሚቆመውም በአንደበት ነው ። “እፍ ያነዳል ፣ እፍ ያጠፋል” እንዲሉ ። አእምሮ በእውቀት ያጣራል ፣ በጥበብ ያስውባል በማስተዋል ይተምናል ። የትኛውም ሰው ከእንቅልፉ የሚነቃው የህይወቱ ብርሃን ሲበራ ነው። 🔑 ጨለማ በብርሃን እንጂ በጉልበት አይወገድም፡፡ ፈጣሪ ብርሃን ሲሆንልህ ህይወትን በመአቀፋ ስትረዳ ወደ ጠራ ማንነት ትደርሳለህ ። ድፍርስ ቡና የሚጠጣው ሲሰክን ነው። የተቀላቀለ ማንነትም ድፍርስ በመሆኑ እርካታ የለውም። ከጨለማ ህይወት የራቀና ፍጹም ብርሃን የበዛበት ህይወት ይኖረን ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!             ውብ እረፍት ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
❤️አንዳንዶቻችን ከደስታ ይልቅ ሃዘንን፣ ከስኬት ይልቅ ችግር ላይ መቆዘም እንወዳለን። እንዲህ ሆኜ...ተንከራትቼ...በዚህ ወጥቼ በዛ ገብቼ እያለን ችግሮቻችንን ሁሉ እንደከንቱ ውዳሴ ስንደጋግም፣ እንዲሁ ስናከብዳቸው እንውላለን ። ❤️አዎ! እርግጥ ነው ሁሉም ሰው የራሱ የማይመቹ የህይወት መንገዶችን ያልፋል ነገር ግን ችግሩን አብዝቶ ስላወራው ብቻ ከችግሩ ነፃ ይሆናል ማለት አይደለም። ይልቅ ለችግሩ ተገዢ እየሆነ ይሄዳል እንጂ...ከዛም ባለፈ ችግሩን ማንነቱ አድርጎ ይቀበላል። ❤️ወዳጄ ሆይ እስኪ አመስጋኝ እንሁን። ማታ ተኝቶ ጠዋት መንቃት በራሱ እኮ እራሱን የቻለ እድለኝነት፣  እራሱን የቻለ መመረጥ ነው። በጤንነት ብቻ መኖር በራሱ ድንቅ ነገር፣  ድንቅ ስጦታ ነው። በተሰጠን አመስጋኝ እንሁን የቀረው ነገር ወይም የኛ አይደለም ወይም ግዜውን ጠብቆ መምጣቱ አይቀርምና። ፈጣሪ ሆይ ካላየኃቸው እና ከማላቃቸው አደጋዎች ስላዳንከኝ ፣ በፈተና አፅንተህ ስላጠነከርከኝ ፣በፈተናዎች ወድቄ ስለተማርኩኝ ክበሩን አንተ ውሰድ  🙏 ስታበይ እንደመታበዬ ፣ስበድል እንደ በደሌ ፣ ስወድቅ እንዳወዳደቄ፣ ሰጠግብ እንዳጠጋገቤ በሆንኩት ልክ ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ስለምታኖረኝ ክበሩን አንተ ውሰድ 🙏 የሚያስፈልገኝን ሁሉ ስለምትሰጠኝ ፣ በመንገዴ ሞገስ ስለሆንከኝ ፣ ዙሪያዬ በመልካም ሰዎች ስላስከበብከኝ ። አመሰግናለሁ 🙏 በረከቴ ስለሚታየኝ ፣ጤናዬ ስለሚታወቀኝ፣  ህያውነትህን ተጠራጥሬ ስለማላውቅ አመሰግናለሁ 🙏                                ውብ ዛሬ !!❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
📍አንዳንድ ወቅት አለ ስሜት የሚነዳ ፤ የሂወት ድግግሞሽ እንደጦስ ዶሮ የሚያዳክር፤  እጅ እና እግር እንደተጠፈረ  አቅም አልባነት የሚበላ ፤ አካባቢ ላይ ምን እንደተካሄደ የማይገባህ ። አንዳንድ ወቅት አለ ማጤን ማመዛዘን ያንተ የማይሆንበት ፤ የመረጥከው ምርጫ የሚያድሞከሙክኽ።  መባተልን የምትመስልበት፤   የመጣህበት መንገድ አሳስቶህ የማትመለስበት ። አንዳንድ ወቅት አለ ምርጫ የሚያባትልህ ፤   የመፍዘዝ ስሜት የሚሰማህ ፤   ሰው ሁሉ  የጠላኽ የሚመስልህ ፤  ኃላ  የመቅረት ስሜት የሚንጥህ ። አንዳንድ ወቅት አለ  ማድረግ እንደሌለብህ እያወክ  የምታከናወነው ፤ የስሜትህ ባርያ የምትሆንበት ፤ መገኘት እንደሌለብህ እያወክህ የምትገኝበት  ። እንዳንድ እለት አለ ብልጥ ነኝ ባዮች የሚበልጡ ፤ አራዳ ነኝ ባዮች የሚያሞኝህ፤ በዝባዦች የሚበዘብዙህ፤ ባለጡንቻዎች አቅማቸውን የሚለኩብህ እንዲም ሁሉ ሆኖ ሳለ በግዜ እናምናለን ። ግዜ ሃያል ነው ። ሁሉም ይስተካከላል፣ መስመር መስመር ይይዛል  ።አይነጋም ያልነው ጨለማ ስንቴ ነግቷል። ✍አድሃኖም ምትኩ ውብ አዳር ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot      
Mostrar todo...
✨ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ውስጥ የማጣት ሥጋት፣ ዕረፍትን በመናፈቅ ውስጥ የሕመም ፍርሃት፣ ክብርን በመሻት ውስጥ የውድቀት ሥጋት፣ ሕይወትን በማፍቀር ውስጥ የሞት ፍርሃት፣ ድልን በመጠበቅ ውስጥ የሽንፈት ውጥረት በብርቱ ይታገለናል:: 💎 ንቁ አእምሮ ያለው ሰው በራስ የመርካትም ሆነ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ አይታይበትም:: የዘመኑን መርዶ አዘል ዜናዎች ቢሰማም ለመኖር ከሚያሳየው ጉጉትና ጥረት አይቦዝንም:: የሕይወትን አስቸጋሪ ገጽታዎች ቢጋፈጥም “አበቃልኝ” አይልም:: ይልቁንም የወደፊት ተስፋው በፈጣሪ አስተማማኝ እጆች ውስጥ ፍጻሜ እንዳለው ስለሚያውቅ እያንዳንዱን ዕለት በብልሃት በጭምትነትና በመታዘዝ ያሳልፋል:: አመለካከት የሕይወትን ስኬትና ውጤት ይወስናልና አስተሳሰባችን የቀና ከሆነ ስኬታማነታችንም የተረጋገጠ ነው:: 💫 ማናኛችንም ብንሆን መታወክ የሌለበት ከፈተናና ከውጣ ውረድ የጸዳ መሻታችን ሁሉ የተሟላበት ኑሮ ቢኖረን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ሠው በመሆናችን ብቻ ደስታና ሃዘን፣ ማጣትና ማግኘት፣ መውደቅና መነሣት፣ ማመንና መከዳት እንዲሁም ውጣ-ውረድ የተሞላበት መሠናክል ይፈራረቁብናል፡፡ ዋናው ነገር በነዚህ ነገሮች ተፈትኖና ነጥሮ መውጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ ፈጣሪ ይህንን ድንቅ አዕምሮ ወይም ልዩ መክሊት ሲሠጠን በመጣው ወጀብ እንድንወሠድ ሳይሆን በጥበብና በዕውቀት ችግሮችን ፈትተን፣ ትምህርት ወስደን፣ እንደወርቅ በእሳት ተፈትነን በማስተዋል ነጥረን እንድንወጣ ነው፡፡ 💎አስደሳች ፍጻሜ አጠብቅ ፣ህይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት፣ መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡  መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች። ውብ ጊዜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
💡ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንዳይጠፋ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው  አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም  እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል። ......ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ…….. 📍ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት  ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር። 💡አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ህይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፤ ልምዳችን፤ ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ፤ ስራችንን እንደማስተካከል፤ ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን። 📍የሁላችንንም ቅጠል የሚያጠወልገው ነገር ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን በሱስ እንጠወልጋለን፤ አንዳንዶቻችን በስንፍና፤ አንዳንዶቻንች በቂ ፍቅር ስለሌለን፤ አንዳንዶቻችን በራሳችን ባለመተማመናችን፤ አንዳንዶቻችን ተስፋ በማጣት፤ ብቻ በተለያይዩ ምክንያቶች መጠውለግ እንጀምራለን። መጠወለጉ ሲያንገፈግፈን እና እንደገና ለማበብ ስንወስን ደግሞ መላው ይጠፋብናል። በለፋን ቁጥር ይበልጥ እንጠወልጋለን፤ ልፋታችን ከንቱ ይሆንብናል። ምክንያቱም ብዙዎቻችን እንደ ሰውየው፤ ጊዜያችንን የምናጠፋው ለውጥ በማናገኝባቸው ነገሮች ላይ ነውና። 💡የሁሉም ነገር መሰረት አይምሮዋችን ነው። የጠወለገውን ክፍላችንን እንደገና ህይወት መስጠት የሚያስችለን ብቸኛው መፍትሄ አስተሳሰባችን መቀየር ብቻ ነው። እራሳችንን እንደዛፉ ብንመለከት፤ የትኛው የህይወታችን ክፍል ነው እየጠወለገ ያለው? ልፊያችንስ ከተበላሸው ባህሪያችን ማለትም ከጠውለገው ቅጠላችን ጋር ነው ? ወይስ ስር ከሆነው አስተሳሰባችን ጋር ነው? ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
💡ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንዳይጠፋ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው  አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም  እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል። ......ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ…….. 📍ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት  ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር። 💡አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ህይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፤ ልምዳችን፤ ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ፤ ስራችንን እንደማስተካከል፤ ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን። 📍የሁላችንንም ቅጠል የሚያጠወልገው ነገር ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን በሱስ እንጠወልጋለን፤ አንዳንዶቻችን በስንፍና፤ አንዳንዶቻንች በቂ ፍቅር ስለሌለን፤ አንዳንዶቻችን በራሳችን ባለመተማመናችን፤ አንዳንዶቻችን ተስፋ በማጣት፤ ብቻ በተለያይዩ ምክንያቶች መጠውለግ እንጀምራለን። መጠወለጉ ሲያንገፈግፈን እና እንደገና ለማበብ ስንወስን ደግሞ መላው ይጠፋብናል። በለፋን ቁጥር ይበልጥ እንጠወልጋለን፤ ልፋታችን ከንቱ ይሆንብናል። ምክንያቱም ብዙዎቻችን እንደ ሰውየው፤ ጊዜያችንን የምናጠፋው ለውጥ በማናገኝባቸው ነገሮች ላይ ነውና። 💡የሁሉም ነገር መሰረት አይምሮዋችን ነው። የጠወለገውን ክፍላችንን እንደገና ህይወት መስጠት የሚያስችለን ብቸኛው መፍትሄ አስተሳሰባችን መቀየር ብቻ ነው። እራሳችንን እንደዛፉ ብንመለከት፤ የትኛው የህይወታችን ክፍል ነው እየጠወለገ ያለው? ልፊያችንስ ከተበላሸው ባህሪያችን ማለትም ከጠውለገው ቅጠላችን ጋር ነው ? ወይስ ስር ከሆነው አስተሳሰባችን ጋር ነው? ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
📍መስጠት ዋና ስራህ ይሁን ብዙ በመልፋት ብዙ በመጣር ትልቅ ውጤት ልታመጣ ልታሳካ በሀብት ደረጃ ልትበለፅግ ማግኘት የምትፈልገውን ሀብት ልታገኝ ትችላለህ ነገር ግን ከበፊቱ የተለየ የተሻለ ቆንጆ ምግብ ትመገብ ይሆናል እንጂ ልኩ አይጨምርም ስላለህ ብቻ ሰው መብላት ከሚችለው መጠን በላይ አትበላም በአንድ ግዜ ብዙ ልብስ አትለብስም ሁለት መኪና ባንዴ አትነዳም የምትኖረውም አንድ ቤት ላይ ነው ነገር ግን ስትሰጥ እነዚህን ሁሉ ባንዴ ማድረግ ትችላለህ። ❤️ የተራቡ ስታበላ እርካታው ሚሊዮኖች ከሚበሉት በላይ ነው የታረዙትን ስታለብስ ከለበስከው በላይ ሙቀት ከለላ ይሆንሀል ባንዴ በብዙ ልብስ ታጌጣለህ ህይወትም ትርጉሟ የሚጨምረው ለሌሎች መኖር ስንጀምር ነው ! ሁሌም በጎ በጎውን ማድረግ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ። ለሌላው የሚጠቅም መልካም ድርጊት ወደ ዓለም ስትልክ መልካምነትህ ዞሮ ይከፍልሃል፣ ብድራቱን ታገኛለህ። የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። መልካም መሆንህ ምንም ኪሳራ የለውም። ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል። 💡ወሳኙ የምንሰጠው መጠን ትንሽነትና ትልቅነት ሳይሆን በምንሰጠው ነገር ላይ የምንጨምረው ፍቅር ነው፣ ስላለን ስለሞላን ብቻም ሳይሆን ካለን ማካፈልንም መልመድ እንጀምር። የህይወት መሰረት የሚጣለው ሁሌም ከዛሬ ነው ፣ ከዛሬም አሁን! ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
❤️ቅናት አንድ ሰው በሚወዳቸው ሰዎች በምላሹ ተወዳጅ እንዳልሆነ ሲያስብ የሚሰማው ህመም ነው፣ ቅናት ሁሌም የሚመነጨው ከንፅፅርና ከውድድር ነው። ከልጅነታችን ጀምሮ እያነፃፀርንና እየተነፃፀርን መኖር ለምደናል። ስንማረው ኖረናል ። የሆነ ሰው የተሻለ ቤት አለው ። ውብ የሆነ ሰውነት ይኖረዋል። አንዳንዱ ከሌላው የበለጠ ገንዘብ አለው። ሌላው ደግሞ መስህብ ያለው የስብዕና ባለቤት ነው፣ እነዚህን ነገሮች እየተመለከትን ከእነዚህ ሰዎች ጋር እራሳችንን እያነፃፀርን ነው የኖርነው። 📍ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው፣  የራስህን ሕይወት በፍጹም ከማንም ጋር አታወዳድር ። ምክኒያቱም እራስንህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆነ ኩራት ሲሆን ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ ቅናት ነው የሚሆነው ። ሁለቱም መጥፎ ውጤቶች ናቸው፣ ቅናት ደግሞ ከንፅፅራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው። እራስህን ማነፃፀር ካቆምክ ግን የቅናት ስሜትህ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል፣ ከምንም በላይ ውበት የሚገለጸው  እራስን በመሆን ነውና ። 💎ቅናት፤ ተንኮል፤ ጥላቻ እና ቂም የሰውነትን ውበት እና ግርማ የሚሰርቁ ቀማኞች ናቸው። ፈገግታ የራቀው ኮስማና ፊት እንደው ዝም ብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም፤ ኮስማና ሃሳቦችን ከማሰብ የሚመጣ እንጂ፣ ሰዎች ደስ የሚሉ ሃሳቦችን ሲያስቡ፤ ሰውነታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ ይናገራል፤ የውስጥ ደስታቸው ደስ የሚል ግርማን ያላብሳቸዋል። ሰውነታችን በቀላሉ እንደአስተሳሰባችን ይለዋወጣል። መልካም እና ክፉ አስተሳሰቦች የየራሳቸውን ተጽዕኖ ያሳድሩበታል። 💡ከንጹህ ልብ፤ ንጹህ ሰውነት ይገኛል፤ ከጤነኛ አስተሳሰብ ጤነኛ ሰውነት ይወለዳል፣ መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን መንገድህ መሰናክል ይበዛዋል ፣ እናም በልብህ ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣በቀል ሳይሆን ይቅርታን ፣ ቅናት ሳይሆን ቅንነትን ፣ ስስት ክፋት ሳይሆን ደግነትን ፣ ትዕቢት ሳይሆን ትህትናን፣ ሁሌም በልብህ ብትሰንቅ ነገ መልሶ የህይወት ስንቅ ይሆናሃል።            ውብ አሁን!!❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
💡ከዜሮ መጀመር ትችላለህ 📍ያለንን ነገር ሁሉ ብናጣ ፡ የተመካንባቸው ሰዎች ቢርቁን ፡ በሽታ ቢያሰቃየን ፡ የባንክ አካወንታችን ባዶ ቢሆን ፡ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢከሰቱብን ፡ ሁሌ ከዜሮ መጀመር ይቻላል። እድሜያችን ቢገፋ እንኳን በልጅነታችን የተመኘነውን ማንነት በየትኛውም ጊዜ መገንባት እንችላለን ። ከኛ የሚጠበቀው ለመለወጥ ያለን ቁርጠኝነታችን ፡ ፅናታችን ፡ እምነታችንና ትዕግስታችን ነው። ማትኮር ያለብን ችግሩ ላይ ሳይሆን ወይም ስለችግሩ ማልጎምጎም ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት የሚረዱንን መሰረታዊ ጽንስ ሀሳቦች ቁርጠኝነት ፡ ጽናትና ፡ ትዕግስት ላይ ነው። 💡 የሕይዎትህ መለወጫ መሪ ያለው በራስህ እጅ ላይ ነው። ሌሎችንና ሌላ ጊዜን አትጠብቅ። ጊዜው አልፏል ብለህም አትቁም ፡ ያንተ ጊዜ አሁን ነው። ጉዳይህ ያለቀና ያበቃለት ቢመስልም አንተ ከጠነከርክ እንዲሁም ከልብህ ፡ እኔ አሁንም ተስፋ አለኝ ብለህ ከባዶ የመነሳቱ ድፍረቱ ካለህ ያኔ አንተ አንፀባራቂ ብርሀንን ታያለህ። ራስህንም ድሮ ከነበርክበት ባዶነት አውጥተህ እንደገና ሕይዎትን የመኖር ፅንሱን ውስጥህ ትፀንሳለህ። ያኔ አንተ ተቆርጠህ ከተጣልክበት ትቢያ እንደገና አገግመህና ፡ አቆጥቁጠህ ትታያለህ። ልምላሜህም ከበፊቱ የበለጠ ይሆናል። ቅርንጫፎችህ ፡ ተቆረጡ እንጂ ዋናውን የሕይዎት ምስጢር የያዘችው አንተን ከአፈሩና ፡ ከውሃው የምታገናኝህ ስራህ አልተቋረጠችምና እንደገና ትለመልማለህ። እንደገና እራስህን በእድገት ምናብ ከዋጀኽው በድጋሚ ታብባለህ። 📍በድጋሚ ቀንበጥ ፡ ቀንበጥ የሆኑ የሚያስጎመጁ ፡ አረንጓዴ ቅጠሎችንና ፡ ቅርንጫፎችን ፡ ታቆጠቁጣለህ። ግመል በበረሓ ስትጓዝ በረሓው ላይ ውሃ እንደሌሌ ታውቃለች። ግን ወደ በረሓው እንድትገባና ፡ እንድትጓዝ ስናደርጋት ፡ ወደ ኋላ አታፈገፍግም ወይም አትፈራም። ምክንያቱም ፡ የሻኛው ጮማ ውስጥ በቂ የሆነ ምግብና ፡ ውሃ እንዳለ እርግጠኛ ስለሆነች እሷ የምትዘጋጀው ከበረሓው ፡ ከመግባቷ በፊት ውስጧ ምግብ በማጠራቀም ነው። አንተም እንደ ግመሏ ውስጥህ ላይ አትኩር። ሌሎችን የበረሓው ግለት ፡ የበረሓው ንዳድ ፡ የበረሓው አሸዋና ፡ የበረሓው መጨረሻ መራቅ ተስፋ ቢስ ሲያደርጋቸው ፡ አንተ ግን ለድል አነሳሳቸው ፡ ውስጣቸው ያለውን የአሸናፊነት  ጮማ ፡ የተስፋ ጮማ ፡ የፍቅር ጮማ ሻኛ እንዳለ ንገራቸው። አንተ ከፊት ሆነህ ባለህ የዕውቀት ፡ የፅናት ፡ የትዕግስት ፡ ብረሀንህ ጉዟቸውን አቅልጥላቸው። 💡አንተ ራስህን ከምንምና ፡ ከባዶ አንስቶ ለትልቅ ደረጃ ፡ የሚያበቃ አቅም በውስጥህ አለ። አንድ ልታውቀው የሚገባህ ትልቅ ቁምነገር ፡ ዜሮ ፡ የቁጥሮች መጨረሻ ሳይሆን ፡ የቁጥሮች መጀመሪያ መሆኑን ነው። ያለህ ነገር ሁሉ ዜሮ የሆነ ከመሰለህ ፡ እንግዲያው አንተ ደስ ሊልህ ይገባል። ምክንያቱም ፡ በህይዎትህ ያለህ ደስታ ሁሉ ፡ ያለህ ሀብት ሁሉ ፡ ያለህ ዝና ሁሉ ፡ ያለብህ ገንዘብ ሁሉ ፡ ያለህ ተቀባይነት ሁሉ ፡ እንደገና ከዜሮ ፡ መጨረሻ ፡ ወደሌለው ቁጥር "ሀ" ብሎ ሊንደረደር ነውና !!!                              📓የኔ ስጦታ ✍ብሩክ የሺጥላ ውብ ምሽት❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@Ethiohumanitybot
Mostrar todo...
የማንን ግጥም ማንበብ ይፈልጋሉ?
Mostrar todo...
የበውቀቱ ስዩም
የኤፍሬም ስዩም
በላይ በቀለ
የሰላሞን ሳህለ
የከበደ ሚካኤል
የፀጋየ ገ/መድን
ልኡል ሃይሌ
ሌሎችም
ሌሎችንም ለመፈለግ ?
የማንን ግጥም ማንበብ ይፈልጋሉ?
Mostrar todo...
የበውቀቱ ስዩም
የኤፍሬም ስዩም
በላይ በቀለ
የሰላሞን ሳህለ
የከበደ ሚካኤል
የፀጋየ ገ/መድን
ልኡል ሃይሌ
ሌሎችም
ሌሎችንም ለመፈለግ ?
መረጋጋት የውሃ ተፈጥሮን በጥሩ ሁኔታ ይወክላል።ለእኛ ለሰው ልጆች አርአያ ሊሆነን ይገባል ምክንያቱም ውሀ ሀይሉን የሚሰበሰበው በእርጋታ ነው።  ራሳችንን የመቀየር ሀሳብ ካለን ቅድሚያ አስተሳሰባችን ምን እንደሚመስል መቃኘት አለብን። ረጋ ብለን ለደቂቃ በጥሞና ውስጣችንን ብንሰማ፤ እጅግ እንገረማለን። ሃሳባችን አንዴ ከትላንት፤ አንዴ ከዛሬ አንዴ ከነገ፤ ሳያቋርጥ ይጋልባል፣ልክ ያለማቋረጥ እንደሚማሰል ኩሬ መንፈሳችንን ያደፈርሰዋል። አእምሮአችን ያለ ማቋረጥ ሀሳብ ሲያበዛ ጭንቀትና ድካም ያስከትላል፣ ውሃን ብቻውን ስንተወው ሳይታወክ ጥርት ረጋ ይላል፣ የረጋ ውሀ ለአናጢው እንኳን ሳይቀር በውሀ ልክ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ግንባታን እኩል ያረጋል። ውሃን ካስተዋልከው ይፈሳል ምንም ጠንካራ ነገር ከመጓዝ አያቆመውም፣ ሁልጊዜ ወደፈለገበት ቦታ ይሄዳል፣ውሃ ትግል አያቅም እንቅፋት ሲገጥመው ዞሮ ያልፋል፣ጠብ እያለም ድንጋይ ይንዳል፣ ስናየው ስስ ነው ግን እሱን የሚያህል ጠንካራ ነገር የለም።በእርጋታ ጊዜ ውሃ እንዲህ ተአምር ከሰራ የሰው ልጅ መንፈስ ረጋ ቢል ምን ውጤት ያመጣል ብለህ አስብ? ወዳጄ  ሆይ አንተም አስታውስ ግማሽ አካልህ ውሃ ነው ፣በእርጋታህ ሀይል መሰብሰብ ትችላለህ ፣እንቅፋት ውስጥ ማለፍ ካልቻልክ አትታገል በዙሪያው እለፍ ፣ በሁኔታዎች አትታሰር ግትር መሆን ጅልነት ነው። በብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ደግሞ ብልህነት ነው። 💧ብልህነት ሁል ጊዜም እንደ ጅረት ውሀ መፍሰስ ነው፣ ነገ የገዛ ራሱን አጋጣሚ ይዞ ይመጣልና የትላንቱ ሃሳብህ ላይ የሙጥኝ አትበል፣የሰው ልጅ እራሱ ከሚፈጥራቸው የመንፈስ ካቴናዎች ነጻ ወጥቶ የመኖር አቅም አለው።የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው።          ውብ ጊዜ❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanitybot
Mostrar todo...
✨እንካ ለውብ ቀንህ ፍሬድርክ ኒቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው። "ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?" የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት። ✨ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ " ከሳለፍነው ታሪክ ጋር ምንም ቁርኝት (Attachment) ስለሌለን ነዋ!" አሉት። ከአፍታ በሁዋላ "ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?" ሲል ጥያቄዎቹን አዥጎደጎደባቸው ። እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር። "ምኑን ነው የምንደግምልህ?" የሚልና ክው አድርጎ የሚያስቀር ………😁ፎቶው ከፅሁፉ ጋር የሚገናኘው ምኑ እንደሆነ ታውቃላችሁ? እኛም በየቀኑ አዳዲስ የሆኑ እድል ይሰጡናል። የትናንት ጭንቀቶች አጥብቀን ምንሸከም ከሆነ ግን ዛሬን በሙሉ ሀይላችን መኖር አይቻለንም ፣ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የትናንት ምርጥ ተማሪ ካልሆነ ነገውን ውብ ማድረግ አይችልም፡፡ ✨ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይችላል። የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፣ የሕይወት እውነተኛ ክስተት  አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ  ሰላም ፍጠር! ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ፣ ትናንትህን መልቀቅ አለብህ፣ እራስህን አትጋርድ።            ውብ አሁን❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@Ethiohumanitybot
Mostrar todo...
📍ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል! ልብን እና አዕምሮን ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከል ነው፡፡ ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶ በነበረበት ጊዜ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለጆሮ በሚከብድ  ቃል እንዲህ ብሎት ነበር:: "ንጉስ ሆይ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!" ንጉስ ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ወደፈጣሪው ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም ፣ ነገር ግን ፈጣሪ ግን ልቦናውን አይቶ እድሜ ጨመረለት። ንጉስ ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ሲሉ ይጠይቁታል ንጉስ ሕዝቅያስ ግን ከአልጋው ሳይወርድና ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ "ልቡን" ነበር:: አንተም ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ ፣ ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። ዓሣ  ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከህሊናው ከፈጣሪው ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡ ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም ከልቡ ሆኖ ይቅርታ ሲጠይቅ ፣ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል። 🔑ወዳጄ ሆይ  ልቦናህን አጥራው፣ ስሜትህን ግራው፣  ሕሊናህን ዘወትር በአዲስና በበጎ ሃሳብ ሞርደው፣ ምን ዘንካታ ብትሆንና አለባበስህ ቢያምር ሕሊናህ ከቆሸሸ በሚያምር  ቤትህ ውስጥ ቆሻሻ እንደመከመር ነው፡፡ አንተ ግን ልብህን ካስተካከልክ ቤትህ፣ ስራህ፣ ቤተሰብህ፣ ትዳርህ፣ በዙሪያህ ያሉ ችግሮችህ እና የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ።           ውብ ምሽት❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
የሚያሳዝነው እኛ ሰዎች ሙሉ ሕይወታችንን መኖር ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ሆነን ሳንኖር መሞታችን ነው። Eckhart Tolle “ይህንን ባገኝ ደስተኛ እሆን ነበር” የሁላችንም መፈክር አይደለም? ወይም የለመድነው የኑሮ ሂደት። ከላይ የሰፈረው የኤካርት ቶሌ አባባል ይህንን አኗኗራችን በደንብ ይገልጸዋል ብዬ አስባለው ። ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፣ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለው እያለን ለኑሮዋችን ቀጠሮ ስንሰጥ፤ ያሰብነው እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰንን ነው። የሰው ልጅ ምኞት ማለቂያ የለውም። በጠየቅን ቁጥር ፈጣሪ ያልነውን ቢሰጠን እንኳን እንደሰው እረክቶ ለመኖር ይከብደናል። ለዚህ ነው ደስታችንን ነገ ከምናገኛቸው ነገሮች ጋር መቋጠር ዛሬን በሰመመን እንድንኖር የሚያደርገን፣ ያሰብኩት እስኪሳካ ደስተኛ መሆን አልችልም ማለት ነው “አስከዛው አልኖርም” ማለት ነው። የነገው ህይወታችን ትልቅ ትርጉም አለው፤ ዋጋው ግን የዛሬን ያህል በፍጹም አይሆንም። በዚች አጭር ፁሁፍ እንለያይ፣ ለመኖር ስሟሟት ነበር :- "በመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ለመጨረስ እና ኮሌጅ ለመጀመር ስሟሟት ነበር፣ ከዚያም ኮሌጅ ጨርሼ ሥራ ለመጀመር ተሟሟትኩ ቀጥሎም አግብቼ ልጅ ለመውለድ ስሟሟት ነበር ፣ከዚያም ልጆቼ አድገው እድሜያቸው ለትምህርት  እንዲደርስ እኔም ወደ ሥራ ቶሎ ለመመለስ ስሟሟት ነበር። ከዚያም ጡረታዬ ደረሰ እሱንም ለማግኘት ተሟሟትኩ ፣አሁን ግን መሸብኝ እኔም እየሞትኩ ነው።በሕይወቴ ውስጥ ለነገዬ ስሟሟት፣ዛሬን መኖርን እንደረሳሁ ድንገት ገባኝ" ይላል ፀሀፊው። እናም ወዳጄ ውብ አሁን በቃ!😊 @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
🛑ምክር ለወዳጅ ወዳጄ  ሆይ 💡በራስህ መስታወት የራስህ አቅም የቱንም ያህል ጉዙፍ መስሎህ ቢታይህም በሕይወትህ ረጅም መንገድ የለህምና የወደቀውን በማንሳት ፈንታ በውድቀቱ አትሳቅ፣በእብደቱ አትሳለቅ ፣ በማጣቱ አትፈንድቅ ፣ እብሪት የውድቀት ዋዜማ ነው ፣ በኋላም ሆነ ነገ ጊዜ ባንተ ላይ ምን እንደሚያመጣ አታውቅምና ስትኖር ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣ በቀል ሳይሆን ይቅርታን፣ትዕቢትን ሳይሆን ትህትናን በልብህ ሰንቅ። ወዳጄ ሆይ 💡ዛሬን ማግኘትህ ትልቅ ስጦታ ነውና በጥልቅ ሀሴት ተሞልተህ ደስ ይበልህ፤ የፈጠረህን በእጅጉ አመስግን፣ በትንሹ ለፀሐይ ብርሃን፣ለምትተነፈሰው አየር ክፈል ብትባል ቅንጣቱን እንደማትችል ሁሉ አስበህ ከማንም እንደማትበልጥ፤ከማንም እንደማታንስ አውቀህ ተራመድ ፣ በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካምና በደስታ ለመኖር ሥጋህን ተጠንቀቀው፤ነፍስህን ቁጠራት፣እምነትህን ጠብቀው፡፡ የትም ግባ፣የትም ውጣ በነገሮች አትደነቅ፣ብርቅ አይሁንብህ ዓለምን በሩጫም በእርምጃም ብታስስ ከድካምህ ባለፈ አዲስ ነገር አታይም ፣ ደግሞም ለምድሪቱ ትልቅ  ስራ ባልንጀራህን እንደራህ አድርገህ መውደድ ነውና ዋጋ ለማታወጣበት ነገር ለማንም ያልተጓደለ ክብር ስጥ፣ፍቅር አሳይ፡፡ ወዳጄ ሆይ 💡ዕድሜህ ሃያ ዓመትህ ስለሆነ ብቻ ከዚህ በኋላ ብዙ ቀሪ ዕድሜ እንዳለህ እያሰብክ አትኮፈስ በሆነ ገጠመኝና ክስተት ዛሬን ሳያገኙ በምሽቱ ምድሪቱን የተሰናበቱ አያሌ ናቸውና፡፡ ደግሞም ባለህ አያሌ ሀብት፣ባለህ የተንጣለለ ህንፃ፣ባለህ ሠፊ ዕውቀት፣ባለህ ችሎታህ፣ባለህ ጉብዝናህ፣ባለህና በተማመንክበት ሁሉ ዛሬን ለማለፍ ዋስትናህ አይደለምና ከሚሆነው ነገር ተጠበቅ፣ከምታደርገውም ነገር ተጠንቀቅ፡፡ እናም ወዳጄ 💡ተግባርህ በመልካም የተሞላ ይሁን፣አንድ ዳቦ አጥተው ጎዳና የወደቁ ሠዎች መኖራቸውን ባይንህ እያየህ ባንክ ላጠራቀምከው ሚሊዮን ብሮች ከሳሳህ ሠው የመሆን ድርሻህ ምንድነው? ምድር ላይስ የመቆየት ዓላማህ ምን ይሆን? የገነባህው ህንፃ፣ያጠራቀምከው ገንዘብ፣ያነፅከው መኖሪያ ቪላ ከሠዎች ማግኘት ማጣት፣መብለጥ ማነስ በሚል ስሌት አትስራበት፡፡ በመኖርና በመሞት መካከል ያለው ርቀት የቅፅበት ያህል ነውና፡፡ 🔑 በዓለም ላይ የትኛውንም ያህል የገንዘብ ብዛት አንድ ቀንን ገዝቶ የአንተንም ዕድሜ፣የዓለምን ፍፃሜ የማራዘም አቅም የለውም።  ስለዚህም በምድር ነገር መኩራራትህን ትተህ፣ባለ ነገር መኮፈስህንም አቁመህ፣ምንም ይዘህ እንዳልመጣህና፣ምንም ይዘህ እንደማትሄድ ከገባህ መሽቶ በነጋ ቁጥር ፈጣሪህን ታመሰግናለህ !!!      ዛሬ በሕይወት ስላለህና ይህንንም መልዕክት በማንበብህ ዕድለኛ ነህ.. ደስ ይበልህ!! ይህንን ካነበብክ በኋላ ምን ተሰማህ?? ውብ አሁን❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanityBot
Mostrar todo...
📍በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።   📍መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።   📍ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል። 💎ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም። ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ። 📖አርምሞ ወብ አዳር ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity
Mostrar todo...
A SHORT LIFE LESSON! 💎 Someone graduated at the age of 22, but waited 5 years before securing a good job. 📍 Someone became a CEO at 25, and died at 50, While another became a CEO at 50, and lived to 90 years. 💎Someone is still single, while someone from his school group has become grandfather. 📍Obama retired at 55 & Trump started at 70, Everyone in this world works based on their time zone. 💎People around you might seem ahead of you & some might seem to be behind you. But everyone is running their own race, in their own time, Do not envy them. 📍They are in their time zone, and you are in yours. So, relax. ✨You're not late.You're not early. You are very much on time, and you will achieve your desired goals for Life (Be Encouraged). Happy Saturday❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity @EthiohumanityBot
Mostrar todo...
በአረም የተወረረ እርሻ አትሁን! አንዳንድ ሰው የአረም እርሻ ነው። ብዙ የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ተሸክሞ ይዞራል፣ አንተ ግን የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ከአእምሮህ ጓዳ ቶሎ ቶሎ አጽዳ! በረከቶችህን እንጂ ጉዳቶችህን አትቁጠር፣አእምሮ ሰነፍ ጮማ ስጋ ነው። መጥፎም ይሁን ደግ የተነገረውን ለቀም ነው።ለአእምሮህ የምትነግረው ደግ ደጉን ይሁን። አለዚያ መጥፎ ሃሳብ ከሰጠኸው ያንን ይዞ ይመርዝሃል። አዘውትረህ የምታስበው ሃሳብ በውስጥህ ይደድራል። ውሎ አድሮም ይገዝፋል፣ ሃሳብ ለአእምሮ፣ ስፖርት ለጡንቻ እንደሆነው ነው።መጥፎ ምግብ ሰውነትን ይመርዛል።መጥፎ ሃሳብ አእምሮን ይመርዛል።በመጨረሻም ሰውየውን ገላፈቻ (ከጥቅም ውጭ) ያደርገዋል። መጥፎ ሃሳብን አታመንዥክ የጥላቻ ሃሳብን አታመንዥክ። ይልቅስ መጥፎ ሃሳቦችን ከአእምሮህ እያጸዳህ በመልካም ሃሳቦች ተካቸው፣ስለሰው ስታስብ የሰውየውን መልካም ጎን ለይተህ ለማሰብ ሞክር፣ ችግርን ተጋፈጥ። መልካም ሃሳብን ዝራ፣ መጥፎን በመልካም ሃሳብና ድርጊት ተዋጋ። ይህ ሁሉ ሆኖ ከመጥፎነት አልመለስ ለሚሉ በመጥፎ ሃሳባቸው እንዳትጠመድ ከእነርሱ ራቅ። ሁሌም ደግ ደጉን እናስብ። ደግ ደጉን እንሥራ። መልካምነት ሌላው ቢቀር የአእምሮ ሰላም ይሰጣል። ከጨጓራ ህመም ያተርፋል። ነገ ሲነጋልህ፣  ተነስና በረከቶችህን ቁጠር። ለጤናህ ፈጣሪህን አመስግን። ለቀጣዩ ቀን ውሎህ ሰላምና ስኬት ፈጣሪህን በጥበባዊ ጸሎት ለምን። በዚህ ምን ትጎዳለህ? የተሻለ ምርጫስ አለህ? የቀን ውሎህን አቅድ። ለሥራህ ተዘጋጅና ቆፍጠን ብለህ ውጣ። ፈገግታ ከፊትህ አይጥፋ! ጎበዝ ገበሬ ሁን! የጎበዝ ገበሬ እርሻ ከአረም የጸዳ መልካም ቡቃያ ነው። ✍ Getu k toughe ውብ ጊዜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
✨ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444'ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ዒድ ሙባረክ!❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity
Mostrar todo...
💎 ለመቶ ሚሊየን ሰው 1 ፀሀይ ነው የምትወጣው እንጂ ለሁሉም የተለያየ ፀሀይ አይወጣም፡፡ ፀሀይ ስራዋ መውጣት ነው መሞቅ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ አዲሷ ፀሀይ አዲስ እድል አዲስ ተስፋ አዲስ ስኬት ይዛ በማለዳው ህይወትህን ልታሞቀው ስትወጣ አንተ ዛሬም በትላንት መጥፎ ታሪክህ በእንባ ጥላ ተጠልለህ ትደበቃታለህ፡፡ ሳታሞቅህ ዜናዋን ሳታበስርህ ትገባለች፡፡ 💡ተፈጥሮ ሁሌም ለሁሉም እኩል ናት ፡፡ ለሁሉም አንድ ፀሀይ ነው የሚወጣው ዛሬም በፍቅር ከመኝታህ ተነስ የዛሬዋን ፀሀይ በተስፋ ሙቃት አትደበቃት ከውድቀትህ እንቅልፍ እራስህን ቀስቅስ፣ብርሃን የድምቀት መገለጫ ነው ፣ደማቅ ቀን በብርሃን ውስጥ ደግሞ ደጋግሞ ያበራል። የሚሰጠህ ውስጣዊ ስሜት በፈጠርከው ብሩህ ቀን ይወሰናል ተግባር የእምነት ፍሬ ናትና ። 💎 ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። ስኬትህ የመንገድህ ጥግ ላይ ነው፣ ከምታስበው በላይ ቀርብ ነህ፣ ትንሽ መዘግየቱ የሚመጣው ነገር ስለሚበልጥ ነው፣ ትንሽ ታገስህ መንገድህን ቀጥል ፣ ድልህ ቅርብ ይሆናል። 💡አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገሰህ ተራመድ ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም! ከጨለማው ምሽት በኋላ ሁል ጊዜ ፀሀይ ትወጣለች፣ አንተም በውስጥህ ያለውን ጥንካሬ ሰብስበህ ቀጥል። ውብ ቅዳሜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanityBot
Mostrar todo...
📍ወዳጄ ሆይ ብሩህና መልካም ነገር አስብና! ተነስ ወደፊት ስለሚሆነው አትጨነቅ ሁሉንም ነገር እንደ ችግር አትመልከት። በራስህ ችግር አትፈጠር። እያንዳንዱ ፈተና ታርሞ ውጤት እንደሚሰጠው ሀሉ ያንተም ችግር እንደተጋፈጥቀው መጠን ለስኬትህ ግብአት እንደሆነ አስብ፣ ስኬት የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉት እወቅ። 📍የስኬት መጨረሻ የውድቀት መጀመሪያ እንደሌለ እወቅ ፣ ስኬት በተገኘ ነገር ላይ በመርካት እንደሚለካ አስብ። ስኬትን ከአእምሮ እርካታ ጋር እንጂ ከቁስ ጋጋታ ጋር አታዛመድ፣ የሰው ልጅ እራሱን ሊያስደስት የሚችለው በመልካም ባህሪውና በሚሰራው ጥሩ ሥራ እንጂ የሚያምር መልክና አቋም ወይንም በርካታ ሀብት ስላለው አይደለም ... የሚያምር አቋምህና ሀብትህ ምድር ላይ ቀሪ ናቸው ..መልካም ስራህ ግን ለነገ ስንቅ ይሆንሐል ! ባለህበት የህይወት ደረጃ መርካት ከቻልክ በራሱ ስኬት እንደሆነ እወቅ። እናም ወዳጄ 🔑 ሰውን ለመርዳት ጥግ አትያዝ እራስህን ሆነህ ደግ ስራ። በዚህ ምድር ትልቁ ነገር ሰው ሁኖ መፈጠር ሳይሆን ሰው ሆኖ መገኘት ነው ፣ ባለህ ነገር ተደሰት ፣ ተጨማሪ ቁሰ የአኗኗር አማራጭ እንጂ የህይወት ግዴታ እንዳልሆነ እወቅ። ማግኘት የምትችለውን ቁስ እንጂ አንተን የሚፈጥርህ ቁስ ለማግኘት አትጨነቅ ፣  እጅና እግሮችህ ሀብት እንደሆኑ እወቅ ፣ ህልውናህ ብቻውን ስኬት እንደሆነም ላፍታ አትዘንጋ፣ ሁሉም ነገር ሚሆነው አንተ ስትኖር ነው፣ ስለዚም በህይወት ሳለህ ወሳኝ" እና "ጠቃሚ" ሰው ሁነህ ተገኝ ሰዎችን እርዳ። መልካም ሰው መሆን በተግባር  እንጂ በትንታኔ ወይም በምላስ አይገለፅምና ፣በምትኖረው ህይወት ቁም-ነገር ያለው ጥሩ ነገር ሰርተህ እለፍ።             ውብ ጊዜ ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanitybot
Mostrar todo...
🌪ሕይወት በሚታይና በማይታይ ማዕበል የተከበበች ናት! ሰው ሃሳቡ በግንባሩ ላይ ቢጻፍ ማን ማንን ቀና ብሎ ያያል? ደግነቱ በውስጣችን ያለውን ማንም አያውቅብንም። የምናስበውን አስበን፤ የፈለግነውን አሳውቀን የምንደብቀውን ደብቀን የመኖር ጥበቡ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ ጥበብ ነው። ልብ በሃዘን ደምቶ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ፤ ግንባር ኮስተር ብሎ ልብ በሃሴት ሲሞላ ፤ ጉልበት ተንበርክኮ ልብ በትዕቢት ሲቆም ፤ አፍ እንደ ማር ጣፍጦ ልብ እንደ እሬት ሲመር ፤ ማን ማንን ያውቃል ያሰኛል?! የሰው ልጅ በሚታየውና እና በማይታየው ማዕበል ውስጥ ያልፋል፤ የሚታየው ማዕበል ሌሎች የሚረዱት እና የሚያዩት ችግራችን ሲሆን፤ የማይታየው ማዕበል ደግሞ ከሌሎች ደብቀን ለብቻችን የምንጋፈጠው ችግር ነው”። ሌሎች የማውቁት ምን አይነት ጭንቀት ይሆን እያንዳንዳችን በውስጣችን ያለው? ምን አይነት የማይታይ ማዕበል እየተጋፈጥን ይሆን? 🔷አዎ በሰው ፊት እንስቃለን ለብቻችን ግን እንባችንን በገዛ መዳፋችን ያለማቋረጥ እናብሳለን። ከሰው መሃል ደምቀን ለብቻችን ስንሆን መግቢያ እናጣለን። ከህዝብ ፊት ከብረን በቤታችን ግን የሰው ያህል የሚቆጥረን የለም። ጠንካራ መስለን፤ ልባችንን ግን በክህደት ስብርብሩ ወጥቷል። ከላይ ሰላም የሰፈነብን እንመስላለን፤ ውስጣችን ግን በተስፋ መቁረጥ ማዕበል ይተራመሳል። ከውጪ ሲታይ ቤታችን የደመቀ ቢመስልም ውስጡ ግን እንደ ዋሻ ቀዝቅዟል። ተለቀም አነሰም ሁላችንም ለሌሎች የማይታይ ለብቻችን የምንጋፈጠው ማዕበል አለን። 🔵እናም በየመንገዳችን ስንተላለፍ ልብ እንበል፤ ሌላው ከኛ ያነሰ ትግል የሚታገል እየመሰለን ፊት አንንሳው፤ እየረገጥን አንለፈው። የኔ ችግር እና ጭንቀት ከሌላው ይበልጣል የሚል አስተሳሰብ ሲኖረን ለሌሎች የምንዘረጋው እጅ ያጥረናል። ትኩረታችን ሁሉ የራሳችን ችግር ላይ ሲሆን ይበልጥ እናማርራለን፤ ሌሎች ለብቻቸው የሚገፈጡትን ማዕበል ስለማናይ “ምነው እኔን ብቻ” እያለን የሃዘናችንን ጉድጓድ ይበልጥ ወደታች እንቆፍረዋለን። ♦️ከትዳር አጋራችን ጋር ክንድ ተንተርሰን እያደርን፤ እርስ በርሳችን የምንፋለመውን ትግል አናውቅም። ለዚህ ነው ጭቅጭቅ ሲነሳ መሸናነፍ እና እርቅ ማውረድ የሚከብደን፤ ማን የማንን ማዕበል ያያልና? እናም በየመንገዳችን የሚያጋጥሙን ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው፤ በጫማቸው ሳንቆም አንፍረድ። በደቂቃ ውስጥ ያየነውን ምግባራቸውን ተንተርሰን አንፍረድ። 🔴ሌላውም እንደኔ ስሜት አለው የሚል አስተሳስብ መያዝ ስንጀምር፤ የሌላው ህመም ይሰማናል እናም ብዙ ስህተቶችን ከመፈጸም እንድናለን። ምናልባት ለብቻሽ/ ለብቻህ የምትጋፈጠው ማዕበል ካለህ በርታ… አጋዥ የለኝም ብለህ አትስጋ ፈጣሪ የማትችለውን ችግር አይሰጥህም። አንተ/አንቺ ብቻ ከሰው የተለየ መከራ አልተሰጠሽም/አልተሰጠህም እንደየአቅማችን ለሁላችንም የታደለን ነው እንጂ……ከምንም በላይ ግን እርስ በርሳችን እንተጋገዝ፤ እየተገፈታተርን መተላለፉን እናቆም ምክንያቱም ሁላችንም ለየብቻችን በምንጋፈጠው ማዕበል ደክመናልና።                       ✍ሚስጢረ አደራው             ውብ አሁን ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity@EthioHumanitybot
Mostrar todo...
❤️እኛ ኢትዮጵያውያን 🔶ኢትዮጵያዊያን የሰው ክብረቱ ስራ እና አእምሮ መሆኑን ገና አላወቅንም። ሰርዐት የሌለው ህዝብ የደለደለ ሀይል የሌውም። ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው።  የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!                    ✍  በዓሉ ግርማ 🔷 ያለፈው ታሪክ የድሮውም የአሁኑም ኑሮዋችን እጅግ ያሳዝናል። በመላው አለም ላይ ሰላም ሲሰፋ አእምሮም ሲበረታ እኛ በጨለማ እንኖራለን። እርስ በእርሳችን መጠራጠርን አልተውነም። ህዝቦች ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር ተቃቅፈው ስለ ልማታቸው ሲደክሙ እኛ አንድ ዘርና ወንድማማች መሆናችን ገና አልተገለፀልንም። እርስ በርሳችን መፋጀት እስከ ዛሬ ጀግንነት ይመስለናል። ♦️ዘወትርም በስምምና በፍቅር አድረን ብንሆን እስከ ዛሬ ድረስ ብዙውን ትልልቅ ነገር መፈፀም እንችል እንደነበር ጥርጥር የለውም። ፈጣሪ ብዙ በረከት ሰጥቶናል ፣ ካለመስማማታችን የተነሳ ግን ሌሎች ህዝቦች በአእምሮና በጥበብ እየበረቱ ሲሄዱ እኛ ወደ ኋላ ቀረን። እንደ አረመኖች እስኪቆጥሩን ድረስ። ♦️ምነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንቅልፍህ መቸ ትነሳለህ? በአለም ላይ የሚደረገውን ነገር ለማየትስ ዓይንህን መቸ ትከፍታለህ? ለውጥንስ መቸ ትናፍቃለህ? ✍ ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ       ውብ አዳር ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanitybot
Mostrar todo...
🔱 እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል? ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች። በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣ ✨“እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው? ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል ፡፡ ✨ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅና፣ እምነትህም አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጥ፣ ምክንያቱም የአንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል! የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የራስህን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አታነፃፅር ! ውብ የስኬት ጊዜ❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@Ethiohumanitybot
Mostrar todo...
💔 ወርቃማው ጥገና! በጃፓን ሃገር ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት የከረመ ልምምድ አለ፡፡ ጃፓኖች አንድ ከሸክላ የተሰራ እቃ ሲሰበርባቸው እንደገና የመጠገኑን ስራ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) ብለው ይጠሩታል፡፡ ይህ ቃል የሁለት የጃፓንኛ ቃላት ጥምረት ነው፡- “ኪን” (Kin) ማለት ወርቃማ ማለት ሲሆን፣ “ሱጊ”(Tsugi) ማለት ደግሞ ጥገና ማለት ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቃላት ጥምረት የሚሰጣቸው ይህ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) የተሰኘ አንድ ቃል ትርጉም አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ እንደገና በወርቅ መጠገንን የሚያመለክት ነው - ወርቃማ ጥገና! ✨ከዚህ ልምምዳቸው የተነሳ አንድ የተሰበረ የሸክላ እቃ እንደገና ሲጠገን ይህ የጥገና ሂደቱ በእቃው ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ እቃው በመሰበሩ የተነሳ እንደገና ሲጠገን በሶስት መልኩ የላቀ ሆኖ ይወጣል፡- 1) ጥንካሬው ይጨምራል፣ 2) ዋጋው ይጨምራል፣ 3) ውበቱ ይጨምራል፡፡ በሕይወታችሁ ልባችሁን ሰብሮና ስሜታችሁን አቁስሎ የነበረ ያለፈ ልምምድ ካለ፣ አሁንም ተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁና ወደፊትም በሚሰብር ልምምድ ውስጥ ስታልፉ ይህንን የጃፓኖችን የጥገና ሂደት አትዘንጉ፡፡ በሁኔታው ተስፋ በመቁረጥና ተሰብራችሁ ለመቅረት ራሳችሁን ካልጣላችሁ በስተቀር እንደገና ትጠገናላችሁ፡፡ ከተጠገናችሁ በኋላ ግን ከበፊቱ ይልቅ ጠንካራ ሰዎች፣ ዋጋችሁ የከበረና ከበፊቱ ይልቅ እጅግ ውብ ሆናችሁ ነው የምትወጡት፡፡ ✨ሆኖም፣ ጥገና ጊዜን እንደሚፈልግ አትዘንጉ፡፡ ጥገና ያለፈውን ረስቶ ፈጣሪን በመታመን ወደፊት የመገስገስን ቆራጥነትም እንደሚፈልግ አትርሱ፡፡ ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ ውብ አዳር ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity
Mostrar todo...
❣አምላክ ለምን ፈጠረኝ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? ❣እኛ የሰው ልጆች ፈጣሪ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ አናውቅም!! እሱ በጣም ድንቅ አንጎል እና ስሜት ያለበት አፍቃሪ ልብ ሰጥቶናል፣ለመናገር እና ስሜታችንን ለመግለጽ በሁለት ከንፈሮች ባርኮናል፣ ውበትን የሚያዩ ሁለት ዓይኖች፣ በሕይወት መንገድ ላይ የሚራመዱ ሁለት እግሮች፣ ለእኛ ሁለት የሚሠሩ እጆች፣ እና የፍቅር ቃላቶች የሚሰሙ ሁለት ጆሮችን ሰጥቶናል። ፈጣሪ ሰውን ሲፈጥር የራሱን ትክክለኛ ባህሪ እንዲላበስ ነው ፤ የፈጣሪ ባህሪ ርህራሄ ቸርነት ፣ ይቅርታ ፣ ፍቅር እና ደስታ ናቸው። እኛም እሱ እንደፈጠርን ሰው ሆነን መኖር ይገባናል። ♦️ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ ከራስ አልፎ ለሌሎችም ማሰብ መቻል ነው፡፡ ሰው ሁኖ መኖር ማለት ሰውን መግደልና መግፋት ሳይሆን ማዳንና መደገፍ ፣ ማበረታታትና ማረጋጋት ነው፡፡ ሰዎችን ገንዘብንና ስልጣንን ፣ ጉልበትንና ጊዜን ተጠቅመው መከራ የሚያሳዩ ሰዎች ሰው ሁነው ተፈጥረው ዳሩ ግን ሰው ሁነው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ናቸው፡፡ ♦️ሰው ያለሰው ፤ ሰው ያለዙሪያው ህይወትን ሙሉ በሙሉ ሊኖራት አይችልም። ሰው ስንል ግዴታ በአንድ ጣሪያ ስር የሚኖርን ወዳጅ አይደለም፤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ እንጂ። እኛ ከአለም ውጪ አለም ከእኛ ውጪ አንደኛችም መኖራችን አይረጋገጥም ። ለሰው ማሰብ አለመቻል ኅሊና ማጣት ነው፡፡ አንተ ያስፈለገኽና የሚያስፈልግኽ ለሌሎች የማያስፈልጋቸው የሚመስልህ ከሆነ ራስህን ፈትሽ። ሰው አድርጎ መፍጠር የፈጣሪህ ድርሻ ሲሆን ሰው ሁኖ መኖር ግን ያንተ ድርሻ ነው፣ ማንነትን የመርሳት መድሀኒቱ ፈጣሪ ስለሆነ በምንችለው መንገድ ሁሉ ወደእርሱ በመቅረብ ማንነትን ከመርሳት በሽታ እንፈወስ! ውብ አዳር ❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@Ethiohumanitybot
Mostrar todo...
♦️ለመኖር የመጓጓታችንን ያህል መኖራችን ውስጥ የተሰጠንን ፀጋ ምን ያክል እናስተውላለን? ከውልደት እስከ ሞት የሚዘረጋው የስብዕናችን ተረክስ ሁነኛ ልኩ ምንድነው? የህይወት ዳርቻ ስትደርስ ጨለማውን ታየዋለህ።  ተስፋ ካልተለየህ ጭላንጭሏ ላይ ታተኩራለህ። እሷ እንዳታመልጥህ ትታገላለህ።  ካመለጠችህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መውደቅህን ታውቃለህ ፣ ሰው አንዳንዴ የተስፋው ጭላንጭል ስትሟጠጥ እና የህይወቱ ገመድ ተገዝግዛ ልትበጠስ ስትደርስ የመጨረሻው ንቃት ላይ ይደርሳል፣ ታድያ በዚች ቅፅበት ጨለማውን የሚገፍ የተስፋ ብልጭታና እንደገና ጨብጦ የሚወጣበት የምርጫ ገመድ ሲያገኝ የሚፈጠረው ለውጥ አቻ አይኖረውም። 🔷ዛሬ ብንሞትስ ብለህ አስብ እስኪ ለነገ ያሳደርካቸው ብዙ ሀሳቦች አብረውህ ይሞታሉ  ፣ ለነገ ያቆየሀቸው ስንት ግቦች መቃብር ይወርዳሉ  ፣ዛሬ ሳታወጣው የደበቅከው ተሰጥኦህ አብሮህ ይቀበራል ሳይፈነጥቁ የቆዩ ብዙ ተስፋዎች ይቀጫሉ ፣ ለሰዎች ያላሳየሃቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ይሞታሉ ነገ እደሰታለሁ ብለህ ቀን ስትጠብቅ ቀኑ ይጨልምብሀል  ስለዚህ አስብ እየአንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ቁጠራት ማድረግ ያለብህን ዛሬ እያደረክ ተደሰት። 🔶መኖር ጥሩ ነው።  ሌላው ትርፍ ነው።አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' አይምሰልህ ፣ ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ለህይወትህ በይበልጥ ዋጋ የምትሰጠው ልክ የአንበሳ መንጋጋ ገብቶ በተአምር እንደ ተረፈ ነብይ ወይም ጻድቅ ነው።  🔷ከክፉ በሽታና ከሞት ጥግ መመለስ ራሱ ጽድቅ ነው፣ የደረሰበት ብቻ ያውቀዋል፣  ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ዋናው ነገር ለተሰጠህ ለምታውቀውም ለምታውቀውም በረከት ፈጣሪህን አመስግን ፣ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!               ውብ አሁን❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@Ethiohumanitybot
Mostrar todo...