cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

በዝህ የቴሌግራም ቻናል 👉 ስለ ህፃናት የጤና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው 👉 ስለ ጨቅላ ህፃናት እና ታዳጊ ህፃናት እንክብካቤ 👉 ስለ ህፃናት አመጋገብ 👉 ስለ ህፃናት አስተዳደግ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎች ይቀርባሉ ❤️ ማንኛዉም አይነት የህፃናት ሕክምና(የቆዳ፣ የአይን፣ የነርቭ ፣የአንገት በላይ እና ሙሉ የህፃናት የዉስጥ ደዌ ሕክምና ቀጠሮ ለማስያዝ ይደውሉ:: 👉 0984650912

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
36 285
Suscriptores
Sin datos24 horas
-1017 días
-38130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🔊 ስለ ቶንስል እና እንጥል ህመም የተሳሳቱ 7 አመለካከቶች 👇👇 https://youtu.be/dpCJWAhDjLI?si=jHyBPkoAzSEJWFsl
Mostrar todo...
ስለ ቶንሲል ህመም የተሳሳቱ 7 አመለካከቶች | 7 Myth and facts about tonsillitis | #health #doctor #habesha

7 ሰለቶንሲል የተሳሳቱ ሃሳቦች | 7 Misconceptions About tonsillitis Certainly! Here are seven common misconceptions about tonsillitis, along with explanations to clari...

👍 11
🔊 እህታችን ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች። ከጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ዶክትሬት ድግሪ ተመርቃ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርቲ በህክምና እና በማስተማር ሲታገለግል ቆይታ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመቀላቀል የራዲዮሎጂ ስፔሻሊት ስልጠና ከጨረሰች ገና 3ኛ ወሯ ነው ትዳር ከመሰረተች ደግሞ ገና 2ኛ ወሯ ነው። ዶ/ር ቤቴል የመመረቋን እና የማግባቷን ደስታ ገና ሳታጣጥም እንደቀልድ ለቶንሲል ህመም ምርመራ ለመደረግ በሄደችበት ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረዳች። ዶ/ር ቤተል የደም ካንሰር በአይነቱም acute lymphoblastic leukemia የሚባል በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት። የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድ አፋጣኝ የሆነ የመቅኔ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplant) ከሀገር ውጭ እንዲደረግላት ወስኗል። የደም ካንሰር ምንም እንኳን አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኔ ንቅለ ተከላ ከተደረገ የመዳን ዕድል ያለው በሽታ በመሆኑ ፣ እናንተ ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን ሀኪም ህይወት በደጋግ እጆቻችሁ ተባብራችሁ እንድትታደጉ ስንል በፈጣሪ ስም እንለምናችኋለን። ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ የምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት። እንደ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰቧም ሆነ ባለቤቷ አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም። ቤቲ የምታገለግላችሁ እናንተ ኢትዮጲያዊያን፣ እናንተ ቤተሰቦቿ ናችሁ እና በፈጣሪ ስም የመልካምነት እጃችሁን ዘርግታችህ የቤቲን ሀዘን የቤተሰቦቿን ድንጋጤ እንድትመለከቱ እንላችኋለን። CBE- 1000105102384 Bethel Germamo Ganebo GoFundMe: https://gofund.me/fdc9a0b3 የፈጣሪ ሰላም እና ጤና ቤታችሁን ይጎብኝ። በቅንነት #share ያድርጉት
Mostrar todo...
Urgent Battle: Dr. Bethel's Fight Against Leukemia, organized by Amu Bazenu

"This is Dr. Bethel Germamo. I hope this message finds you well. I am a … Amu Bazenu needs your support for Urgent Battle: Dr. Bethel's Fight Against Leukemia

👍 20😢 14 6🙏 4
Photo unavailableShow in Telegram
🔊 ✝️ ❤️ ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ‼️
Mostrar todo...
33👍 7🙏 6
የበዓላት ሰሞን ምግቦችን ከጤና አንፃር 🌲በበዓላት ሰሞን ጤነኛ ባልሆነ የምግብ ስርአትና በሚፈጠር የምግብ ለውጥ ምክንያት ብዙ ሰው አዳዲስ የህመም ስሜት ሲሰማው ወይም ነባር ህመሙ ሲባባስበት ማየት የተለመደ ነው 🍜በበዓላት ሰሞን በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ የተለመዱና ቤት ውስጥ ከማይጠፉ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዶሮ ወጥ ፣ ቁርጥ (ጥሬ ስጋ)፣ ክትፎ ፣ ጥብስ ፣ እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል 🍲ከነዚህ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዶሮ ወጥ (በዶሮ ወጥ መንገድ የሚዘጋጁ) ምግቦችን አንስተን ከጤና አንፃር የሚያስከትሉትን ችግር ለማየት እንሞክር:- 🍅ዶሮ ወጥን ለመስራት ከምንጠቀምባቸው ግብአቶች ውስጥ ሽንኩርት ፣ ቲማቲም ፣ በርበሬ ፣ ዘይት (ቅቤ) እና ሌሎች ቅመማቅመሞችን መጥቀስ ይቻላል 🍜የዶሮ ወጥ ዝግጅት ሂደት በከፍተኛ ሙቀት ዘይትን በማጋል ሽንኩርት እና ሌሎች ግብአቶችን ለረጅም ጊዜ ማቁላላት (ማብሰልን) ይጠይቃል በዚህ ሂደት:- 🍅በሽንኩርትና ሌሎች ግብአቶች ውስጥ የሚገኙ ሙቀት መቋቋም የማይችሉ ለጤና እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖችና ውህዶች ሊጠፋ (ሊቀንሱ) ስለሚችሉ ከምግቡ ተገቢውን ጥቅም አናገኝም 🍟በተጨማሪም የምንጠቀመው ፈሳሽ ዘይት ውስጥ የሚገኘው ሲስ (cis) ተብሎ የሚጠራው ጤነኛ እና ተፈጥሯዊ የዘይቱ ክፍል ትራንስ (trans fat) ወደሚባል እጅግ መርዛማ ቅባት ይቀየራል 🍟ከዶሮ ወጥ በተጨማሪ ይህ መርዛማ ቅባት በተጠበሰ ስጋ ወይም አሳ፣ ችፕስ ፣ ሳንቡሳ ፣ ቦንቦሊኖ እና በመሳሰሉት ምግቦች ውስጥ ይገኛል 🥫ሌላኛው እና ዋነኛው የትራንስ ቅባት (trans fat) መገኛ ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ነው 🥫አንዳንድ የዘይት አምራቾች በተለያየ ምክንያት በከፍተኛ ሙቀትና ግፊት hydrogenation የሚባል ሂደትን በመተግበር ፈሳሽ የአትክልት ዘይትን ወደ ጠጣር ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ይቀይራሉ 🥫በዚህ ሂደትም ከፍተኛ መጠን ያለው ትራንስ (trans) እና ሳቹሬትድ ቅባት (saturated fat) ይፈጠራል 🥫እነዚህ የቅባት አይነቶች "partially hydrogenated oil" በመባል የሚታወቁ ሲሆን ጤና ላይ በሚፈጥሩት ከፍተኛ ችግር ምክንያት በብዙ ሀገራት እገዳ (ክልከላ) የተደረገባቸው (FDA, 2020) ቢሆንም በእኛ ሀገር ግን በሰፊው እየተመረቱና ለተጠቃሚ እየቀረቡ ይገኛሉ 🥫በብዙ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ትራንስ ቅባት (trans fat) LDL ተብሎ የሚጠራውን መጥፎ ኮሌስትሮል (bad cholesterol) እና TAG የሚባለውን የቅባት አይነት በመጨመር፣ HDL ተብሎ የሚጠራውን ጠቃሚ የኮሌስትሮል አይነት በመቀነስና የኢንሱሊን መጠን በመጨመር:- 🥫የደም የኮሌስትሮል መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርጋል 🥫የደም ግፊት ፣ የልብ ፣ የስትሮክ እና የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል ወይም ችግሮቹ እንዲባባሱ ያደርጋል 🥫ትራንስ ቅባት ለሰውነታችን ምንም አይነት ጥቅም የሌለው እና በአንፃሩ ጤና ላይ እጅግ ከፍተኛ ችግር ስለሚያስከትል እንዳትጠቀሟቸው እንመክራለን 🍚ሌላኛው ለጤና ጎጂ ናቸው ከሚባሉ የቅባት አይነቶች ውስጥ አንዱ ሳቹሬትድ ቅባት (saturated fat) ነው 🍚እነዚህ የቅባት (የዘይት) አይነቶች በመደበኛ አከባቢያዊ ሙቀት የመርጋት ባህሪ ያላቸውን እንደ ቅቤ፣ ጮማ ስጋ ፣ የሚረጋ ዘይትና የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ 🍚ሳቹሬትድ ቅባት የትራንስ ቅባትን ያክል ባይሆንም በብዛት የሚወሰድ ከሆነ LDL ተብሎ የሚጠራውን ኮሌስትሮል በመጨመር የልብ ጤናን ያውካል 🦴ስለዚህ የኮሌስትሮል የስኳር፣ የኮሌስተሮል፣ የግፊት፣ የስትሮክ፣ የልብና ተያያዥ የጤና ችግሮች ያሉባችሁ ከሆነ በምግብ ከሚገኘው ጊዚያዊ ደስታና እርካታ ይልቅ ከላይ የዘረዘርናቸው ምግቦች የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖን በመረዳት አለመመገብና በምትኩ በውሃ የተቀቀሉና ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ቅመማ ቅመሞች የተጨመሩባቸው እንደ አሳ፣ የዶሮ የደረት ስጋና እንቁላል መመገብ የሚመረጥ ሲሆን የተቀነባበሩ ዘይቶችንና ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ከመጠቀም ይልቅ ተፈጥሯዊና ጤነኛ የቅባት ምንጭ የሆኑ እንደ ተልባ፣ ሱፍ፣ ሰሊጥ፣ አቮካዶ፣ ኦቾሎኒና የመሳሰሉትን መጠቀም ይመከራል 🥦ምግብ መድኀኒትም መርዝም ነው! ለይቶ መጠቀሙ ደግሞ የኛ ፋንታ ነው! እያንዳንዱ ጉርሻ ጤና ላይ በኈ ወይም አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል ✍️ ሙሉቀን ፈቃዴ (የሜዲካል ባዬኬሚስትሪና ስነ ምግብ ረ/ፕሮፌሰር) ምንጭ: ሀኪም page
Mostrar todo...
Hakim

Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.

👍 63 3🥰 1
🔊 ውድ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ሐሙስ 24/08/16 እና ነገ 25/08/16 የህፃናት ሕክምና ለማንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን:: ቅዳሜ ጠዋት 3:30 - 9:30 ድረስ አገልግሎቱን ማግኘት ይቺላሉ ☎️ የቀጠሮ ስልክ : 0984650912
Mostrar todo...
👍 10
" የተጠየቀው የህክምና ወጪው በመንግሥት የሀኪም ደመወዝ እና በቤተሰቦቼ አቅም የሚቻል አይደለም " - ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ላጋጠመው የጤና እክል መታከሚያ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩት ጠየቀ። ዶክተሩ 2015 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሙያ ትምህርት ነው የተመረቀው። ከተመረቀ በኃላም ለ6 ወራት በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኑን ሲያገለግል ቆይቷል። በድንገት ግን ሚዛኑን ስቶ መውደቅ እና ሌሎችም ምልክቶችን በማሳየቱ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ምርመራ ካደረገ በኋላ ' የጭንቅላት እጢ ' እንዳለበት ተነግሮታል። የናሙና ምርመራ ተደርጎ ' GradeIII Astrocytoma ' እንዳለበት ተገልጾለታል። " ትልቅ ቦታ ደርሼ ማየት ለሚመኙት ቤተሰቦቼና ከኔ በታች ላሉት እህት ወንድሞቼ ዜናው በጣም ትልቅ ዱብዳ ነው የሆነባቸው " ያለው ዶክተር ይስሃቅ " የጥቁር አንበሳ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ህክምና ማድረግ እንዳለብኝ ወስነዋል " ሲል ገልጿል። ለህክምናው ወጪው እስከ 👉 2.3 ሚሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግም እንደተነገረው አስረድቷል። ይህን ከፍተኛ ወጪ በመንግስት ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝም ሆነ በቤተሰቦቹ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ሁላችሁም የቻላችሁትን እንድትረዱት ተማጽኗል። ዶ/ር ይስሃቅ " በየሃይማኖታችሁ ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ እንዲረዳኝ በጸሎታችሁ አስቡኝ " ሲልም ጠይቋል። ከዶክተሩ የተላከ የህክምና ማስረጃን መመልከት የቻልን ሲሆን  ወላጅ እናቱን ብርሃኔ በየነን በስልክ ቁጥ ር +251911353752 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል። እገዛ ለማድረግ የምትፈልጉ ፦ ዶክተር ሳምሶን ይስሃቅ በየነ ንግድ ባንክ ፦ 1000139965691 አዋሽ ባንክ ፦ 013201172039000 ብርሃኔ በየነ ሚደቅሳ (እናት) ንግድ ባንክ ፦ 1000549927681 አዋሽ ባንክ ፦ 01347903970500 GoFundMe👇 https://gofund.me/618fc8ee
Mostrar todo...
Help save the doctor, organized by Abigia Aschalew

Hello my name is Abigia and I'm fundraising to help my brother Dr.Samson Yishak Beyene a 28 year … Abigia Aschalew needs your support for Help save the doctor

😢 32👍 23 11
Mostrar todo...
የጨቅላ ህፃናት ሆድ ቁርጠት 10 መፍትሄዎች | 10 tips for Infantile colic #ebs #health #babyfood

የጨቅላ ህፃናት ሆድ ቁርጠት 10 መፍትሄዎች | 10 tips for children's stomach aches and crying. Certainly! Stomach aches and crying in children can be distressing for both the child and the parents. Here are **10 tips** to help manage stomach discomfort and soothe your little one: 1. **Ruling Out Emergencies**: - If your child experiences **severe pain**, blood in stool or vomit, green-colored vomit, signs of anaphylaxis (like swelling or hives), or pain in the lower right quadrant (which could indicate appendicitis), seek **emergency care** immediately¹. 2. **Location Matters**: - Pay attention to where your child feels pain. Stomach pain around the **belly button** is usually benign and often caused by stress or mild indigestion. Encourage rest, check if they need to use the bathroom, offer water, and distract them with a book or quiet game¹. 3. **Appendicitis Alert**: - **Lower right abdominal pain** could be a sign of **appendicitis**. Watch for other symptoms like fever, nausea, vomiting, difficulty passing gas, loss of appetite, constipation, or diarrhea. If you suspect appendicitis, contact your pediatrician promptly¹. 4. **Left-Side Pain**: - Pain on the **left side** of the abdomen might be due to **constipation** or more severe conditions like **pancreatitis**. Assess other symptoms and consult a doctor as needed¹. 5. **Infants and Toddlers**: - With young kids, rely on mood cues. Watch for signs like grumpiness, crying, refusal of favorite snacks, or unusual behavior. If your intuition says something is wrong, consult your pediatrician¹. 6. **Ask Questions**: - As children grow, they can express their discomfort better. Ask where it hurts, what it feels like, how long it's been bothering them, and if anything else feels off. Their answers will guide your next steps¹. 7. **Warm Compress or Massage**: - Place a **warm compress** or heating pad on their stomach. Gently **massage** their belly to ease gas and indigestion⁴. 8. **Hydration**: - Offer small sips of **water**. Sometimes, mild stomach pain is due to slight dehydration¹. 9. **Bland Foods**: - Feed your child **bland white foods** like plain whole wheat bread, dry crackers, or plain rice. These can help absorb excess stomach acid². 10. **Distraction and Comfort**: - Engage your child with **stories**, movies, or board games to take their mind off the pain while waiting for relief. 💖 ለልጆዎ ጤናማ የእድገት ክትትል ለማድረግ ወይም ማንኛዉም ህፃናትን ሕክምና ሙሉ ምርመራ በህፃናት ስፔሻልስት ሀኪም ማድረግ ከፈለጉ በዝህ ስልክ ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ:: ☎️ 0984650912/0939602927 💝 በቤትዎ ሆነው ስለ ጨቅላ ልጅዎ ጤንነት፣ እድገት ወይም አመጋገብ ዶ/ር ፋሲልን ለማምከር ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ ከ google play ላይ አውረደው በቀጠሮ ማማከር ይቺላሉ❗️ 📞 ለበለጠ መረጃ 9394 ወይም 0964686464 ደውለው ስለ application አጠቃቀም መረዳት ይቺላሉ :: 📢 በቴሌግራም እና ፌስ ቡክ ይከታተሉን‼️ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔷 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil 🔷 FB:fb.me/drfasilpediatrician

👍 25 6👏 1
🔊 ጨቅላ ህፃናት #የሆድ #ቁርጠት (Infantile colic) ክፍል 1 👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/OIv0StpQY_A?si=Z4StKRlmYddPmCFk
Mostrar todo...
የጨቅላ ህጻናት የሆድ ቁርጠት እና 10ሩ መፍትሄዎች | Infantile colic and its 10 remedies | Dr. Fasil | #ebs #health

የጨቅላ ህጻናት የሆድ ህመም እና መፍትሄዎቹ | Infantile abdominal pain and its remedies #ebs #ethiopian #health Abdominal pain in infants can be distressing for both the baby and the parents. It's important to understand that while abdominal pain is common in children, especially during a baby's first year, there are several potential causes and remedies to consider: **Common Causes of Infantile Abdominal Pain**: - **Colic**: Defined as increased fussiness or crying for three hours at least three times a week¹. - **Excess Gas**: Can cause discomfort and typically peaks at 6-8 weeks of life¹. - **Constipation**: Fewer than three bowel movements in one week or painful/difficult to pass stools². - **Gastroenteritis**: Infection of the intestines caused by viruses². - **Food Intolerance**: Such as lactose intolerance². **Remedies and Comfort Measures**: - **Warm Compress**: Can soothe stomach pain³. - **Probiotics, Gripe Water, or Gas Drops**: May help with colic, but consult your pediatrician first¹. - **Feeding Techniques**: Avoid feeding when overly hungry to reduce swallowed air, and consider anti-colic bottles¹. - **Burping**: Helps to reduce excess gas. Burp your infant before, halfway through, and after a feed¹. - **Massage and Tummy Time**: Can help move the gas through the intestines¹. It's crucial to consult with a pediatrician if you're concerned about your infant's health or if the abdominal pain persists. They can provide a proper diagnosis and treatment plan tailored to your baby's specific needs. Remember, while home remedies can be helpful, professional medical advice is always the best course of action for health-related concerns. 💖 ለልጆዎ ጤናማ የእድገት ክትትል ለማድረግ ወይም ማንኛዉም ህፃናትን ሕክምና ሙሉ ምርመራ በህፃናት ስፔሻልስት ሀኪም ማድረግ ከፈለጉ በዝህ ስልክ ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ:: ☎️ 0984650912/0939602927 💝 በቤትዎ ሆነው ስለ ጨቅላ ልጅዎ ጤንነት፣ እድገት ወይም አመጋገብ ዶ/ር ፋሲልን ለማምከር ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ ከ google play ላይ አውረደው በቀጠሮ ማማከር ይቺላሉ❗️ 📞 ለበለጠ መረጃ 9394 ወይም 0964686464 ደውለው ስለ application አጠቃቀም መረዳት ይቺላሉ :: 📢 በቴሌግራም እና ፌስ ቡክ ይከታተሉን‼️ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔷 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil 🔷 FB:fb.me/drfasilpediatrician Premature baby care tips NICU home care Preemie baby home routine Caring for a premature newborn Home care essentials for premature infants Premature baby feeding and hygiene Kangaroo care at home Developmental milestones for preemies Creating a nurturing environment for premature babies Preemie homecoming preparation

👍 14