cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዘመኔን ለ ኢየሱስ

ለጌታ ክብር እንዘምራለን Join us @worshiplJesusl ዘመኔ ወጣትነቴ እድሜዬ ያንተ ብቻ ነው ኢየሱሴ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
173
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"#ከቦኛል " "የለም አንድም ቀን የኖርኩት ሳላይ አንተን" 🎵አይዳ አብረሃም🎵
Mostrar todo...
ያንን ሰው 🎵ሳሙኤል ንጉሴ 🎵
Mostrar todo...
❓ነጭ ልብስ እና ጥቁር ልብስ ወስደህ በጥላሸት ድብን አድርገህ ብታሻቸው የትኛው ይቆሽሻል⁉️ የብዙዎቻችን መልስ "ነጭ" ይሆን ይሆናል፤ አንዳንዶቻችን ደግሞ ጥያቄው እራሱ ትንሽ ግራ ሊያጋባን ይችላል። መልሱ👉 "ሁለቱም ይቆሽሻሉ"። ልዩነቱ ነጩ መቆሸሹን ከሩቅ ያስታውቃል፤ የጥቁሩ መቆሸሽ ግን ግልፅ ሆኖ የሚታየው ለአጣቢው ብቻ ነው። ከውጪ የሚያይ ሰው ነጩ እንደቆሸሸ እና ጥቁሩ ንፁህ እንደሆነ ይፈርዳል፤ እውነተኛው ፍርድ ግን ያለው አጣቢያቸው ጋር ነው፤ እርሱ የሁለቱንም ገመና ያውቃል። በመጀመርያው አዳም አማካኝነት ሐጢአት ወደ እያንዳንዳችን ዘር ገባ፤ ሐጢአት ሰርቶ ሐጢአተኛ መባሉ ቀርቶ ከአባት መውረስ ተጀመረ። (ሮሜ 5:2-21) ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ሕግ እና ነብያት እንዲሁም የተስፋው ቃል ኪዳን ለእነርሱ መሰጠቱን ምክንያት በማድረግ እነርሱ ንፁህ አድርገው ፤ ሌሎች ወገኖችን ግን ሐጢአተኛ እና አፀያፊ አድረገው ይቆጥሩ ነበር። አጣቢው ሲመጣ ግን የሁሉም ገመና ገልጦ ሁሉም መታጠብ እናዳለበት አሳወቀ። አጣቢው ✋ አይሁድ ከግሪክ፡ ሴት እንኳን ከወንድ (ገላ 3:28) ✋ ያመነዘረው ካላመነዘረው (ዮሐ 8:4-10) ✋ መውደቁ የታወቀበት ካልታወቀበት ✋ ብዙ ሀጢአት የሰራው ጥቂት ሐጢአት ከሰራው (ገላ 3:10) እኩል እንደሆኑ ገለጠ። ሁሉም ሰው ስለቆሸሸና ማንም በአብ ፊት መቆም ስላልቻለ ሁሉም በራሱ ስራ ተስፋ እንዲቆርጥ አደረገ። በአብ ፊት እንዳይቆም በሚያደርገው ጥላሸት እንደተለቀለቀና ሁሉም ሰው በደሙ ካልታጠበ ጥላሸቱ ሊለቀው እንደማይችል ገለጠልን። 👉 የሰው አይን አንዱ ከሌላው እንደሚሻል ሊፈርድ ይችላል። 🤷የአጣቢው ሚዛን ግን ሁሉንም ከሐጢአት በታች ዘግቶታል። ❗ጥሩ ፀባይ ያለውም ሆነ መጥፎ ፀባይ ያለው ❗የሚታዘዝም ሆነ የማይታዘዝ ❗ለእግዚአብሔር ቤት የሚቀናውም ሆነ የሚያሳድደው ❗ነፍስ ያዳነውም ሆነ ነፍስ የገደለው ❗የሰረቀውም ሆነ ያልሰረቀው ከሕግ አንፃር ካየን ሁሉም ከሐጢአት በታች ተዘግቷል (ሮሜ 3:9-24) (ገላ 3:10) ሮሜ 3 ²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ²⁴ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል #እንዲያው_በጸጋው_ይጸድቃሉ። ስለእኛነታችን ወይም ስለስራችን ካነሳን ሁላችንም ከሐጢአት በታች ነን። - ጥቂት ያጠፈውም ሆነ ብዙ ያጠፋው በእግዚአብሔር ፊት እኩል የሆነ የሐጢአት ዕዳ አለበት። "ሰርቼ መፅደቅ አልችልም" ብሎ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመነ ደግሞ በአብ ፊት በድፍረት መቆም የሚችልበት ፍፁም ፅድቅ አለው። 📍አሁን ከእግዚአብሔር የሚለየው ሐጢአት ከእርሱ ዘንድ ተልኮ በመጣው በኢየሱስ አለማመን ነው📍 @worshiplJesusl
Mostrar todo...
✍ መግባቢያ ቋንቋዬ ******************** በቋንቋ ህመም ፣ በብሄር ስቃይ በነገድ ደዌ ፣ እንዳልሰቃይ ኢየሱስ ዋጅቶኝ ፣ ከነዚህ ሁሉ አይገባኝ አለ ፣ ብሄሬ ሲሉ ቋንቋዬ ሲሉ ነገዴ ሲሉ ዘሬ ማንዘሬ ፣ ጎሳዬ ሲሉ ለአለም አዝኖ ፣ ላለም የሞተው ላንዱ ራርቶለት ፣ አንዱን የማይተው ለኔ ኢየሱስ ነው ፣ የሆነኝ ወገን የእግዚአብሔር ልጅ ፣ ያደረገኝ ዘር ለኔ ኢየሱስ ነው ፣ የነፍሴ ስንቋ ከእግዚአብሔር ጋር ፣ ያግባባኝ ቋንቋ ✍ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ እንጂ በእንግሊዝኛ አይግባባም!! #ሄኖክ_አሸብር
Mostrar todo...
✍ የእኔና የአንተ ፍቅር❤❤❤ ************************ አንተ እኔን ስትወደኝ ፣ክብርህን በመጣል እኔ አንተን ስወድህ ፣ ውርደት ለመዳን አንተ እኔን ስትወደኝ ፣ ነፍስህን በመስጠት እኔ አንተን ስወድህ ፣ ነፍሴን ለማስመለጥ አንተ እኔን ስትወደኝ ፣ እስከነበደሌ እኔ አንተን ስወድህ ፣ ምክንያቴን ቆጥሬ አንተ እኔን ስትወደኝ ፣ በሀጥያቴ ሞቼ እኔ አንተን ስወድህ ፣ ወደኸኝ አይቼ እናማ ውዴ ሆይ........... ወደደኝ ብዬ እንጂ ወደድኩህ በማለት ፣ እኔ አልደነቅም አንተ የወደድከኝ እኔ ከወደድኩህ ፣ እንደሚራራቀው......... ምስራቅ ከምዕራብ ሰማይም ከምድር ፣ እንደዚህ አይርቅም ብጠላህ ላ'ጠላኝ ወደኸኛልና ብጠላህ ነው እንጂ ፣ ብወድህ አይደንቅም!! ♥♥♥ ትወደኛለህ ♥♥♥ #ሄኖክ_አሸብር
Mostrar todo...
ለኢየሱስ ነው !! ዘሪቱ ከበደ 🎵New song🎵
Mostrar todo...
........... ........ .......... ............... #ለካስ #ምህረትህ #ነው ትውልድ ሁሉ #ሊሰማው የሚገባ
Mostrar todo...
✍ ማንም አልተወለደም ****************** ከኢየሱስ በቀር......... ✍ ማንም ያለወንድ ፈቃድ አልተወለደም!! 📌 ማንም ከድንግል አልተወለደም!! ✍ ማንም ፈቅዶ አልተወለደም!! 📌 ማንም ራሱ ተንብዮ አልተወለደም!! ✍ ማንም ቀድሞ ኑሮ አልተወለደም!! 📌 ማንም ንጉስ ሆኖ አልተወለደም!! ✍ ማንም አምላክ ሆኖ አልተወለደም!! 📌 ማንም ከሰማይ መጥቶ አልተወለደም!! ✍ ማንም ነፍሱን ሊሰጥ አልተወለደም!! 📌 ማንም ነፍስ ሊያድን አልተወለደም!! ✍ ማንም የሀጥያት መስዋዕት ሊሆን አልተወለደም!! 📌 ማንም ተፈፀመ ሊል አልተወለደም!! ✍ ማንም ሀጥያተኛ ወዶ አልተወለደም!! 📌 አወላለዱ ልዩ የሆነው ኢየሱስ አዳዳኑ ልዩ ነው.......የወንጌል ርዕስ ኢየሱስ ተወልዷል ሳይሆን ኢየሱስ ያድናል ነው!! ✍ የምስራቹ ያለው መወለዱ ላይ ሳይሆን የመወለዱ ምክንያት ላይ ነው......ተወለደ ብሎ የሚቆም ወንጌል የለም.........ተወለደ ብቻውን ወንጌል አይደለም........ለምን ተወለደ? መጽሐፍ እንደሚል ሉቃስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ደግሞም መጽሐፍ እንደሚል....... “ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” — ሮሜ 1፥3-4 ✍ ✍ ለኢየሱስ ትልቁ ጉዳይ ሚልዮኖች የሚያከብሩለት የእርሱ ልደት ሳይሆን የአንድ ሰው ዳግም ውልደት ነው!! 📌 የተወለደው ልደት ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ሰው ፍለጋ ነው!! ✍ ወንጌል ስለ ልደቱ ሳይሆን ስለ ልጁ ነው!! #ሄኖክ_አሸብር
Mostrar todo...