es
Feedback
የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

Ir al canal en Telegram

በግጥም የውስጥ ስሜትን እናጣጥም

Mostrar más
6 776
Suscriptores
Sin datos24 horas
-257 días
-9530 días
Archivo de publicaciones
ኑሮኝ ባደርግልሽ ላንገትሽ ወርቅ ሀብል _ ለጣትሽ ደግሞ እንቁ ቤትም ብሰራልሽ _ ቪላ በትልቁ በእግርሽ እንዳቴጂም _ ብገዛ ራቫፎር ልብሶችሽን ከቱርክ _ ሜካፕ ከሲንጋፖር ሽቶሽን ከፍራንስ ደስ ባለ
ኑሮኝ ባደርግልሽ ላንገትሽ ወርቅ ሀብል _ ለጣትሽ ደግሞ እንቁ  ቤትም ብሰራልሽ _ ቪላ በትልቁ   በእግርሽ እንዳቴጂም _ ብገዛ ራቫፎር ልብሶችሽን ከቱርክ _ ሜካፕ ከሲንጋፖር ሽቶሽን ከፍራንስ ደስ ባለሽ ብራንድ _ በፈለግሺው ግላስ ኑሮኝ ብገዛልሽ _  እንዳሻሽ ባሰልፍ  ደስታው ለኔ ነበር _ ካንቺ በላይ በጥፍ አቅም አንሶኝ እንጂ  _ ገንዘብ ቢኖር ከጄ  በመንደሩ ሰው ልክ _ ሙክት ሰንጋ አርጄ ደግሼ ባገባሽ _ ጉድ በሚያሰኝ ሰርግ ደስታው ለኔ ነበር  _  ላንቺ ምንም ባረግ ግን የለኝም በቃ  _ በዚህ መጠን ወረት አሁን ባለሁበት _ ሁኔታ ማንነት  የምትወጂኝ ከሆን _ ከልብሽ የእውነት አብረን እንድንኖር ... ግዴታኮ አይደለም _ ወርቅና ጌጣጌጥ ግዴታኮ አይደለም_  ድግስን መለጠጥ  ግዴታኮ አይደለም _ መኪናና ቪላ ግዴታኮ አይደለም _  መኖር እንደሌላ ስላንቺ ያለኝን መውደድና _ ክብር በውል እያወቅሺኝ ነገዬን ልቀይር በምችለው  መጠን ስለፋ እያየሺኝ ለጊዚያዊ  ምቾት _  አስበልጠሽ ገንዘብ የኔን የእውነት ፍቅር _ ካቃተሽ መገንዘብ  ግድ ቆዪ ብዬ _ አላስረፍድሺም ሂጂ ዛሬውኑ _  ክፍት ነው መንገዱ  ባንቺ አልተጀመረም _ እንዲህ ነው አንዳንዱ ልቡን እያስራበ _  ኗሪ ነው ለሆዱ #ሼን ✍ @seanlph

አላስኬድ ካለኮ _ እግርም ይቆረጣል ያንቺ ልብ አሁንም _ ሰው ይለማመጣል ተይ ይከብዳል አትበይ _ እድሜኮ ያመልጣል በሾህ ንግግሩ _ አድምቶ እየወጋ ደጋግሞ ነግሮሻል _ ስላንቺ ያለውን ስሜትና ዋጋ
አላስኬድ ካለኮ _ እግርም ይቆረጣል  ያንቺ ልብ አሁንም _ ሰው ይለማመጣል ተይ ይከብዳል አትበይ _ እድሜኮ ያመልጣል በሾህ ንግግሩ _  አድምቶ  እየወጋ ደጋግሞ ነግሮሻል _ ስላንቺ ያለውን ስሜትና ዋጋ ሴትነትሽን ንቆ _ በመግፈፍ እንደጨርቅ መሄጃ ቢስ አርጎሽ _ እንደዛ  ሲሳለቅ እልፍ አስተውለሻል ... ይወደኛል እያልሽ _  እራስሺን አትካጅ በግድ ያቆየሺው _ አይሆንሽም ወዳጅ   ሂወት ስለማይቆም _ ባንድ ሀዘን ተሰብሮ የሰው ልጅ ይኖራል _ እናቱንም ቀብሮ ያለፈው በቃ አልፏል ዋጋሽን አክብረሽ _  ጀምሪ አዲስ ኑሮ   ያልተወደድሺበት _ ያልተከበርሺበት ያልተፈለግሺበት _   ጥንቅር ይበል ጎጆ  በምንም ሁኔታ _ ከዚህ የተሻለ ይገባሻል ቆንጆ #ሼን ✍ @seanlph

በፖፖ ከአፍሪካ 1ኛ ከአለም 8ኛ ነኝ|| ፖፖ 666 ነዉን ? || ዛሬዉኑ ይጀምሩ #sherefmedia #poppo ... https://youtube.com/watch?v=zhhYRgrpixU&si=aQSQbuLcaSVWNKI1

በ 0939006488 ቴሌግራም ላይ ይዘዙ 🙏🙏🙏
በ 0939006488 ቴሌግራም ላይ ይዘዙ 🙏🙏🙏

======= 🤔 ለባሌ ስጦታ _ ምን ልስጠው ውድ እቃ ብላ ጠየቀቺኝ _ አንዷ ሴት ተጨንቃ ባል ሚስቱ _ ብትሰጠው ከሁሉ _ ሚያበልጠው አብዝቶ ሚወደው _ እጅግ ውዱ ነገር አንድ ሰላሙን ነው _ ሌላ
======= 🤔 ለባሌ ስጦታ _ ምን ልስጠው ውድ እቃ ብላ ጠየቀቺኝ _  አንዷ ሴት ተጨንቃ ባል ሚስቱ  _  ብትሰጠው ከሁሉ  _ ሚያበልጠው  አብዝቶ ሚወደው _ እጅግ ውዱ ነገር አንድ ሰላሙን ነው _ ሌላኛው መከበር  እኒህን ሁለቱን _ ስጪው ሳትሰስቺ  ያኔ በሱ ልብ ውስጥ_ ትነግሻለሽ አንቺ #ሼን ✍️

====== ተውት አትሰሩት ===== ተውት አትሰሩት _ ልቀቁት በነፃ ዜናም አትዘግቡ _ አትስጡ ገለፃ አንደ ከዚህ ቀደም _ እንደለመዳችሁ ዘጠኝ አስር አመት _ ፍርድን ወስናችሁ በናቲቱ ሀዘን ከምታ
====== ተውት አትሰሩት ===== ተውት አትሰሩት _ ልቀቁት በነፃ ዜናም አትዘግቡ  _ አትስጡ  ገለፃ  አንደ ከዚህ ቀደም _  እንደለመዳችሁ ዘጠኝ አስር አመት _ ፍርድን ወስናችሁ በናቲቱ ሀዘን ከምታላግጡ  ከምትሳለቁ ይሻላል ባንድ ፊት _ባታስሩት ብትለቁ ህዝቡም ቁርጡን ይወቅ_ ህግ አለመኖሩን ሌላውም ይቀጥል _ መግደሉን መድፈሩን ከዛም የሆነ እለት _ ይሄ ያውሬ ምግባር ከቤታችሁ  ገብቶ _ ስታዩት በተግባር በደንብ ሲገባችሁ .... ምን ያክል እንደሆን _  ቁስሉና ሀዘኑ              ያኔ  ታውቃላችሁ .... መዝቀጥ መዛባቱን _  ፍርዳችሁ ሚዛኑ #ሼን ✍️ @seanlph

#ለምን_እስካሁን_እንዳላገባሽ_ልንገርሽ 🤔 አስቀያሚ ሁነሽ _ መልክሽ አስጠልቶ አንቺን የሚፈልግ _ ዙሪያሽ ወንድ ጠፍቶ ወይ ከሌሎች ሴቶች _ አመልሽ ተለይቶ ፍፁም እንዳይመስልሽ _ እድሜሽም ኮብል
#ለምን_እስካሁን_እንዳላገባሽ_ልንገርሽ 🤔 አስቀያሚ ሁነሽ _ መልክሽ አስጠልቶ አንቺን የሚፈልግ _ ዙሪያሽ ወንድ ጠፍቶ   ወይ ከሌሎች ሴቶች _ አመልሽ ተለይቶ ፍፁም እንዳይመስልሽ _ እድሜሽም ኮብልሎ ባገር ጠፍቶም አይደል _  ባንቺ ልክ ቬሎ ወዳጅ ተቸግረሽ _ አፍቃሪ ስላጣሽ ከቶውን አይደለም... መጥፎ ስለሆነ _ የአርባ ቀኑ እጣሽ እየወልሽ እቱ ....🤔 ያላገባሽበት ዋነኛው ምክኒያቱ ላንቺ ግድ የሌለው _ ስሜት የማይሰጠው መጣሽም ቀረሺም _ ከቶ የማይገርመው ሰው እየተከተልሽ _ የማይፈልግሺን ማየት ተስኖሽ ነው 🤔 በዙሪያሽ ያለውን _ የእውነት ወዳጂሽን ======================== #ሼን ✍️ @seanlph

ወደ ሂወትሽ ውስጥ_ ገብተው እየወጡ አስተማሩሽ መሰል _ ሂወትን በቅጡ በደንብ ያስታውቃል _ የባህሪሽ ለውጡ አሁን እንደፊቱ _ በትልቅ በትንሽ መናደድ ትተሻል _ አይተክዝም ፊትሽ ጊዜ እየሰጠሽ ነው
ወደ ሂወትሽ ውስጥ_ ገብተው እየወጡ አስተማሩሽ መሰል _ ሂወትን በቅጡ በደንብ ያስታውቃል _ የባህሪሽ ለውጡ አሁን እንደፊቱ _ በትልቅ በትንሽ መናደድ ትተሻል _ አይተክዝም ፊትሽ ጊዜ እየሰጠሽ ነው _ ለገዛ እኔነትሽ ሳቅና ደስታሺን _ ከሰው አጠብቂም ሰዎች መጡ ቀሩ _ ብዙ አትደነቂም የመጣን መቀበል _ የሄደን መሸኜት ቆዬ ሰነበተ _ ጎንሽ ከቻለበት ተ ለ ው ጠ ሻ ል #ሼን ✍