cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

በቃል ጥበብ

🚩 Channel was restricted by Telegram

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
4 301
Suscriptores
-224 horas
-127 días
-7130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Prohibited content
መጨነቅ ሳይሆን «ማሰብ» ነው የእኛ አቅም!  ነገር ሁሉ ለበጎ ነውና፤ በዙሪያችን ያሉ ስለፈጠኑ እኛ አልዘገየንም። በሰውኛ ጊዜ ሳይሆን በፈጣሪ የስራ ሰዓት እንመን፤ ማርፈድ ከእርሱ ዘንድ የለምና'። @melos3 @melos3
Mostrar todo...
Prohibited content
ማፅናኛዎችና ሀሳቦቻቸው ይደክሙኛል! የማይገባኝን ዋጋ የተከፈለልኝ እንደሆነ ከራሴ ጋር እንድሟገት ያደርጉኛል። በእርግጥ ከሰው በላይ ለሆነው፥ ባለማመን ለመሸሽ አልሞክርም። ደሞ ከባዱ ነገር በእውቀት ስም ካለርህራሔ የማራክሰው ነባር ሀቅ። ሀቅ ከእውነት ይበልጣል። ይህን አለመቀበሌ ውስጤን ያርደዋል። ጠፍቻለሁ? ምናልባት ይህን ስለምታዘብ ይሆን? ፡ ምክንያቱ ለውጤቱ የገዳል-ማሚቱ የሆነ እውቀት መሳይ የሰዋሰው ግርግር፤ ፡ ፋይዳ ቢስ፣ መመዘኛው ግለ-ተኮር የምክር ጋጋታ፤ ፡ ካልተኖረ ህይወት የሚቀዳ፥ መንገድ ጠራጊነኝ የሚል ተግሳፅ ቢጤ ጫጫታ፤ ፡ ቃሉን እየወደደ፣ እየሰማ፥ እየኖርኩት ነው እያለ የትንቢት መፈፀሚያነትን የሚሸሽ አማኝ እና የሀይማኖት አባት፤ ፡ እርግማንን በሳቅ የሚቀበል ትውልድ፤ ፡ ህልምን፣ ፍላጎትና እቅድን ከገደል የሚከቱ ህሊና እና ሆድን ማግባባት የቸገራቸው መሪዎች፤ ፡ የፀጉራቸው ቀለም የነጣ፥ እድሜ ያከበራቸው የባለ አንቱታዎች ምርቃት መሳይ የግል ምኞት፤ ፡ ክብርን ለመስጠት ከሰውነት ክብር መጉደል፤ ፡ በስመ' መሰዋዕትነት ከእራስ ጉድለት ላይ የባሰ መጉደል፤ ፧ ከእለት ተእለት የህይወት ቅኝት፤ ከማሰብ ከመብከንከኑ፤ ለዚህ ሁሉ ትዝብት መፍትሔ የሚሆን አንድ ጠጠር መጣል ያቃተኝ እኔ! ጠፍቻለው? እናንተስ? መልካም ሰኞ፤ በቸር ያውለን🤲 እያነበብን! @melos3 @melos3
Mostrar todo...
Prohibited content
ያመኑት ፈረስ በደንደስ እንዲሉ ጥርጣሬ ልኩን አይለፍ እንጂ ጉዳት የለውም ክፋትም አይደለም። በተለይ ደሞ በዚህ ዘመን። አምኖ በመከዳት ያሳለፍኩትን ያሳለፈ የምለውን ነገር በደንብ ይረዳዋል። ለዛም ነው የሀገሬ ሰው «ያመኑት ፈረስ በደንደስ» ብሎ የተረተው። በሌላ አባባል «ባጎረስኩ ተነከሱ» የሚተካው ይመስለኛ። ያለምንም ገደብ፣ ሀሳብና ከልካይ የሚታመነው ፈጣሪ ብቻ ነው። ለሰው ልክ ያስፈልገዋል። መከልከል ያለበት ብዙ አለ። ልብ ሙሉ ለሙ ክፍት አይደረገም። ይገባው' እንደሆን መጠናት አለበት። ምክንያቱም ሰዎች በፍላጎታችን የምንመራ፤ በነበርንበት ሁኔታና ጊዜ ፍልስፍናችንም፣ ርእዮተ አለማችንም፣ እቅድና ውጥናችን የሚለዋወጥ ከውሻ ያነሰ ታመኝነትን ያነገብን ብኩን ፍጡራን ነን። አይምሰልህ ወዳጄ አንዳንድ ሰዎች የሚታመኑት አንተ ላይ ላላቸው ፍላጎት ነው። ይህ ማለት በአጭሩ ከአንተ የሚፈልጉትን ካገኙ በኋላ ፍላጎታቸውን እንዳሳኩ ታማኝነታቸው ያበቃል። so ነቃ በል🙂 ከስህተት መማር፤ ከመውደቅ መነሳት፤ በማንበብ መሻል፤ በመሞከር ማወቅ ከሁሉም በላይ የራስን ዋጋ መረዳትና በተረዳኸው ልክ ለአዲስ ትግል እራስን በማዘጋጀት፤ በማብቃት ውስጥ መኖር። መራጭ እንሁን። ሁሉን አንቀበል፤ ሁሉን አንመን። ህልም፣ ምኞት፣ ሀሳብና ውጥን እንዲሁም ጊዜን አናግበስብስ እንኳን እኔና አንተ፥ ❝ንስር የበሰበሰ አይበላም❞።
Mostrar todo...
Prohibited content
በጸጥታ የመሰናበቻ ጊዜያት፣ የትዝታ ሹክሹክታን አንድም በደስታ አንድም በሀዘን ስስ ክሮች በልባችን ውስጥ ሸምነው ያቆያሉ። እያንዳንዱ መሰናበቻ ክብደትን የያዘ፣ በተለያዪ ነፍሳት እንደየ ቋንቋቸው የሚዘፈን የስሜት ዜማ ነው። በዚህ ሁኔታ፥ በጋራ ሳቅ ላይ ፀሀይ ስትጠልቅ፥ በእንባ የሰውነታችንን ትስስር እንረዳለን። ጊዜያዊ ተፈጥሮን እንቀበላለን። በስንብት ክንዶች ውስጥ፥ እኛን የገለፁልንን ምዕራፎች ላለመልቀቅ፣ ለመንከባከብ እና ለማክበር ድፍረትን እናገኛለን። ስንብት ፍጻሜ ሳይሆን ለውጥ የሚያመጣ ቆም ማለት ነው። ከምን መሰናበት እንዳለብን ማሰብና ምርጫው ላይ ብልህ መሆን አስፈላጊ ቢሆንም እውነታው፤ ወደድንም ጠላንም ከአንዱ ባህር ዳርቻ ወደ ሌላው የሚያደርሰን ድልድይ ነው። ለዛም ነው በፍፃሜው ለአዲስ ጅምር መንገድ እንደሚጠርግ በመረዳት መጽናኛ የምናገኘው። ማንነት ይቀየር አይቀየር ምላሹ ወይም የፍፃሜው መደምደሚያ በምርጫ የሚቃኝ ቢሆንም ያለፈው የተተወው ባህሪ ግን ለዛሬ አዲስነት የጠባሳው ክብደት ቀላል አይደለም። ምክንያቱም ከትናት በዛሬ ወደ ነገ መሰደድ በምርጫ ሳይሆን በሁኔታዎች ጭካኔ በነፍስ ውስጥ ጥልቅ ቁስሎችን የሚተው ጉዞ ነው። ሆኖም፣ በስንብት መሀከል፣ በችግር ጊዜ የተስፋ ብርሃን የሆነ ጠንካራ መንፈስ ብቅ ይላል። የሀዘን ነበልባልን መቋቋም፣ መልሶ ለመገ'ንባት የሚያስችል ጥንካሬ እና ባልታወቁ እውነቶች ውስጥ አዲስ ጅምርን ለመጓዝ ቁርጠኝነትን ያላብሳል። so መተው ያለብንን እንተው፤ ማቆም ያለብንንም እናቁም፤ መሰናበት ያለብንን እንሰናበት። እናቴ ሁሌ እንደምትለው፤ ❝ጀምበር ስትጠልቅ ይመሻል እንጂ አይጨልምም።❞ ሁላችንንም የነፍሳችን ባለቤት የሆነው ፈጣሪ ይጠብቀን፤ ያበርታን🤲 መልካም ምሽት።
Mostrar todo...
Prohibited content
ሀላፊነት ዘርፈ ብዙ ነው። አይነቱም እንደየስራው ባህሪው ይለያያል። ያለባችሁን የስራ ሀላፊነት ሳትበድሉና በአግባቡ እየተወጣችሁ፥ ለቤተሰብ እምነት መብቃት፤ ለታናሽ ወንድምና እህቶች አረአያ መሆን፤ እውቀትን፣ ሀሳብን፣ ጊዜን ለቤተሰብ የተሻለውን መፈለግና ተግባራዊ እንዲሆን መጣር ላይ እንደማዋል ግን የሚያስደስትና ከባድ ሀላፊነት የለም። ይህ ፅሁፍ የሚገልፃችሁ ሁሉ ለእናንተ ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነውና፥ በርቱ እንበርታ🙂
Mostrar todo...
“እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።”   — ማቴዎስ 28፥6 እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሠላም አደረሳችሁ!! ፧ @melos3 @melos3
Mostrar todo...
❝ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጬኹ ነበር ፦ ማቴ 21 ÷ 9❞                   ፧ «እባክህ እርዳ አሁን አድን»።🤲                   ፧ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።🙏
Mostrar todo...
Prohibited content
እየበረታን ወገን😊 በልካችን እንቀሳቀስ፤ ነገ የነገ ነው!
Mostrar todo...
Prohibited content
የማንችለው ብዙ ነገር አለ!
Mostrar todo...
~ሕልሞችህ ላይ መንቃት፥ በመካከላቸው መመላለስ፤ በውስጣቸው መኖር እፈልጋለሁ፡፡ ድንቅ ሕልሞችህ ላይ፡፡እውንህ ላይ ብቻ መኖሬ አይበቃኝም ያንሰኛል፡፡እውን ነጠላ ነው!!ሌጣ ኑረት! ብዙ አለመቻሎች ፡በርካታ ጉድለቶች፡ አያሌ እንከኖች አሉበት!! ፧ በእውን እግር ተራማጅ እንጂ በራሪ አይደለም፡፡እግር ክንፍ አይደለም። በእውን አይን፥ ከግድግዳ አልፎ ከመጋረጃ ጀርባ፥ ከአድማስ ባሻገር ተሻግሮ አያይም!! የተከደነን፣ የተዘጋን፣ የታሸገን አልፎ በውስጥ ምን እንደሚገኝ አያይም። ፊት ለፊቱ የተደቀነን የተገሰጠበትን ያልራቀውን ብቻ ነው የሚያየው፡፡ ፧ በእውን ጆሮ የራቀን አይሰማም። ከየትዬ የለሌ የሚዜምን ጣፋጭ ማኅሌት አያደምጥም። ከሰባተኛው ሰማይ የሚመጣ፤ የሚያድነው ቃል የእውን ጆሮ ጋር አይደርስም፡፡ ያልተወራን አይሰማም፡፡ የእውን ጆሮ ከአጠገቡ የራቀን ድምፅ አይሰማ አይለማ፡፡ በእውን ልብ አይጨበጥም። አስደናቂ ፍቅሩና መሰጠቱ፥ በእውን ልብ በመዳፍ መካከል አይያዝም!!በእውን አካል ከገለባ የቀለለ፤ ከላባ የሳሳና የለሰለሰ አይሆንም፡፡አካል ጠጣርና ግዙፍ ነው። በእውን አካል ሲጠበድል ቋጥኝ፥ ሲኮሰምን ጠጠር ነው። በእውን፡ሲመቸው ትንቡክ፤ ድሎት ሲርቀው ጋጥ ባይ ነው አካል በእውን አየህ?!.....።ለምን ሕልምህ ላይ መንቃት እንደምፈልግ!? ሕልም ብዙ የማይቻሉ ነገሮች የሚቻሉበት ነው፡፡በተለይ፡ የእንዳንተ አይነቱ ድንቅ ሕልም ሲሆን፤ እራሱ ሕልሙ ይዋባል፡፡ ፧ <የቆንጆ ሕልም የተዋበ ነው!! ከቁንጅናዋ ወዘና ሩሑን ይጠነስሳል፤ ከውበቱ ናሙና ነፍስያውን ይቀምራል....።> #redu 21/06/16 (9:32) @melos3
Mostrar todo...