cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መረጃ//mergaa

@ethomergaa 🎩ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ፣ 🎩የአስተሳሰብ ምህዳሮች ፣ 🎩የምሁራን እይታዎች እና መጽሐፈቶች ፣ 🎩የአለም ሙሉ መረጃ እና የታሪክ ልዩ መዛግብቶች ። ለማንኛውም መረጃ 👉 @Natiyt ኢትዮጵያዊ ሆኘ የተወለድኩ ኢትዮጵያዊ ሆኘ ያደኩ ኢትዮጵያዊ ሆኘ መሞት የምፈልግ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር አሜን !!! የናንተው ቻናል ነው

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 791
Suscriptores
Sin datos24 horas
-117 días
-3230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ደቡብ ጎንደር❗❗ በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ዛሬ አዳሩን ወረቀት በመበተኑ አዲስ ውጥረት መኖሩን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የተበተነው ወረቀት "የሀገር መከላከያ ሰራዊት እስከ መስከረም 3 ለቆ እንዲወጣ እና ካልሆነ ግን ከተማ ውስጥ ውጊያ እንደሚከፈት" የሚል ነው ብለዋል። በዚህ የተነሳ ይሄን ወረቀት በትነዋል የተባሉ ግለሰቦች እየታሰሩ ነው ብለዋል። @ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
ደፈጣ ጥቃት❗👇 በሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረሲና ከተማ ዝቅ ብሎ በዋናው መስመር ልዩ ስሙ አርማኒያ በሚባል አካባቢ ትናንት 11:00 አካባቢ ሎጂስቲክ በጫኑ የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞ ጉዳት ደርሷል ብለዋል። በዚህም ለአንድ ሰዓት የቆየ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን መንገዱ እስከ ምሽቱ 1:00 ድረስ ዝግ እንደነበር የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
Mostrar todo...
01:23
Video unavailableShow in Telegram
በደቡባዊ የመን በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መካከል የተደረገው ደም አፋሳሽ ፀብ ይህን ይመስላል። ያሳዝናል።
Mostrar todo...
19.44 MB
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲሱ ዓመት የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉ የመሳሪያ አፈ ሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት አለባቸው ሲሉ አቡነ #ማትያስ ጥሪ አቀረቡ‼️ #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክተው ከሰሜን አሜሪካን ባስተላለፉት ያሳለፍነው አመት ችግሮች ወደ ቀጣይ #አመት እንዳይሸጋገሩ በማድረግ አዲሱን አመት እንቀበል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብጹእነታቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአዲሱ ዓመት የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉ የመሳሪያ አፈ ሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። ያለፈው ዓመት ያሳረፈብንን ሁለንተናዊ ተጽዕኖ በሚገባ አስተውለን፣ ዳግም ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገርብን ካላደረግን አዲሱ ዓመት ለኛ የሚሰጠን ትርጉም ምንድን ነው ሲሉ የጠየቁት ብጹእነታቸው ባለፉት ዓመታት በሃይማኖት፣ በባህል፣ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም በሕዝባችን ሥር የሰደደውን የእርስ በርስ መጠራጠር ከልብ መርምረን ወደ ድሮው እኛነታችን ካልተመለከትንስ አዲስ ዘመን እያልን ማክበራችን ምን ፋይዳ የለውም ብለዋል። ያለፈውን ጎጂ ነገር በመተው፤ ጠቃሚውን ግን ይበልጥ በማጠናከር አዲሱን ዓመት መቀበል አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በምንጃር እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ኢጀሬ እና ማክሰኞ ገበያ ዛሬ ከፍተኛ የሚባል ውጥረት እንዳለ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል። ሰሞኑን የተካሄደው ውጊያ ቆም ብሎ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግን ለየት ያለ ውጥረት እንዳለ እና በማንኛውም ሰዓት ተኩስ ሊጀመር ይቻላል ብለዋል።
Mostrar todo...
አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ሥጋት ደቅኗል ተባለ‼️ በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ወታደራዊ ኃይል (አትሚስ) በፈረንጆች 2024 ሙሉ ለሙሉ ከሶማሊያ ለቆ ሊወጣ በመሆኑ አልሸባብ ለኢትዮጵያ ስጋት ሆኗል ሲል ዓለም አቀፍ ጥናትና ትንታኔዎች በመስራት የሚታወቀው ዘጀምስ ታውን ፋውንዴሽን ባወጣው ዘገባ ገልጿል። ይህም የሽብር ቡድኑ ከሶማሊያ ጋር ረዥም ድንበር የምትዋሰነውን ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ዓመታት ረጅም የሆነ ግጭት ዉስጥ ሊያስገባት እንደሚችል ጠቁሟል። አልሸባብ ከፈረንጆች 2006 እስከ 2009 በሶማሊያ ባደረገው ወረራ ይዞት ከነበረው በሞቃዲሾ የሚገኘው እስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት ከስልጣን እንዲወርድ መደረጉን ተከትሎ፤ በኢትዮጵያ ላይ ሰፊ ቅሬታ እንዳለውም ተመላክቷል። ኢትዮጵያ ለ15 ዓመታት በሶማሊያ በቆየው የአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ኃይል ውስጥ ትልቅ ተሳትፎ የነበራት መሆኑን እና በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ እንዲሳካ ቁልፍ ሚና መጫዎቷምን ዘገባው ገልጿል። አልሸባብ ለኹለት አስርት ዓመታት በሶማሊያ እያደረሰ ባለው ጥቃት ኢትዮጵያ የምትጫወተው ሚና የአልሸባብ የረጅም ጊዜ ዒላማ እንድትሆን አድርጓታል የተባለ ሲሆን፤ ታጣቂ ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጥላቻ እየጨመረ የመጣ ይመስላልም ነው የተባለው። የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ኃይል (አትሚስ) ባለፈው ሰኔ ወር ከ22 ሺሕ ወታደሮች መካከል 2 ሺሕ የሚሆኑትን ከሶማሊያ ያስወጣ ሲሆን፤ በመጪው መስከረም ወር 3 ሺሕ ወታደሮችን ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት ማቀዱን አመላክቷል። ምንም እንኳን የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ ኃይል ዋነኛ ዓላማ የሶማሊያን ደህንነት በማረጋጋት ኃላፊነቱን ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ማስተላለፍ ቢሆንም፤ የአልሸባብ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል። ኢትዮጵያ በአትሚስ ካላት ወታደራዊ ተሳትፎ በተጨማሪ ባለፈው መጋቢት ወር ኢትዮጵያ፣ ጅቡቱና ኬንያ ሞቃዲሾ ላይ ተገናኝተው ባደረጉት ምክክር ተጨማሪ 1000 ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ልካለች። በዚህም አልሸባብ የጥቃቱን ዋነኛ ትኩረት በውጭ ወታደሮች ላይ አንጣጥሮ ቆይቷል። አልሸባብ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ድንበር ጥቃት ለማድረስ ሲሞክር የሚስተዋል ሲሆን፤ ባለፈው ሰኔ ወር ላይም በሶማሌ ክልል ዶሎ ከተማ ጥቃት ማደረሱ ይታወሳል። በተለይም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው፤ ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ካለው ጽኑ ፍላጎት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የጸጥታ ችግሮች ጋር ተዳምሮ አልሸባብ በሚቀጥሉት ወራትና ዓመታት ተከታታይ የሽብር ጥቃት ሊከፍት እንደሚችል ነው የተጠቆመው። የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ዋነኛ ስጋት የሆነው እስላማዊ ቡድን በተለይ በሶማሊያ በሚፈጽማቸው አውዳሚ ጥቃቶች የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል። አዲስ ማለዳ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ጥንቃቄ❗️ ከባዕድ ነገሮች ጋር የተቀላቀለ 1 ሺህ 440 ኪሎ ግራም ቅቤ ተያዘ‼️ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከባዕድ ነገሮች ጋር የተቀላቀለ 1 ሺህ 440 ኪሎ ግራም ቅቤ መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ በተጨማሪም ከቅቤ ጋር ሊቀላቀል የነበረ ንጽህናው ያልተጠበቀ 3 ሺህ 360 ኪሎ ግራም የአትክልት ቅቤ እና ፓልም ዘይት መያዙን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየርጤና እና ቻይና ካምፕ አካባቢዎች በተደረገ ቁጥጥር እንዲሁም በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ቅቤ የተያዘው፡፡ በተጨማሪም ከ650 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያለው ከቅቤ ጋር ለመቀላቀል የተዘጋጀ ንጽህናው ያልተጠበቀ የአትክልት ቅቤ እና የፓልም ዘይት መያዙን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ከበዓላት ጋር በተያያዘ እንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ድርጊቶች ሊስተወሉ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ የምግብ ምርቶችን ሲገዛ ፈቃድ ካላቸው ተቋማት መሆን እንዳለበት ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡እንዲሁም አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከትም በ8482 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል፡፡
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በሞሮኮ መሬት መንቀጥቀጥ ሙሉ በሙሉ ከፈረሰ መንደር ውስጥ የተረፈው መስጊድ‼️ ሞሮኮ 6.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበውና በሞሮኮ ታሪክ ያልተለመደና እጅግ ክፉኛ የተባለው የሞሮኮ ርዕደ መሬት ከ1 ሽህ በላይ ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ  በታሪካዊቷ ማራካሽ ከተማ ጥንታዊ ህንጻዎችን ዶግ አመድ ማድረጉ ታውቋል። በሞሮኮ ተራራማ አካባቢ የምትገኝ አንድ መንደርም ሙሉ በሙሉ የወደመች ሲሆን፤ ከዚያ ውስጥ ግን ሁለት ህጻች ምንመ ነገር ሳይሆኑ ይታያሉ፤ በርእደ መሬቱ ምንመ ጉዳት ካልደሰረበት ህጻ ውስጥም አንደኛው የአካባቢው መስጊድ መሆኑ ግርምትን ፈጥሯል። @ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.