cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ወግ ብቻ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch@zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
19 348
Suscriptores
-724 horas
-627 días
-18930 días
Archivo de publicaciones
መምህርት ሊያ የ5ኛ ክፍል አስተማሪ ነች ሊያ ተማሪዎቿን አንድ በአንድ የምትከታተል ብርቱ መምህር ነች ከተማሪዎቿ አንዱ ኒክ ይባላል ኒክ አያወራም: ከተማሪዎች ጋር አይጫወትም: ልብሱ ዝብርቅርቅ ያለ ነው: ክፍል ውስጥ አይሳተፍም - መምህር ሊያ በኒክ ደስተኛ አይደለችም መምህር ሊያ የተማሪዎችን የቤት ስራ እና ፈተና ባረመች ጊዜ ሁሉ የኒክን ፈተና በትልቁ ኤክስ (X) የምታደርግ እና በብስጭት ስንፍናውን የምትፅፍ ሆነች - አልወደደችውም በትምህርት ቤቱ ህግ ደግሞ የእያንዳንዱን ተማሪ የቀድሞ አመታት የውጤት ፋይሎችን ማየት ግዴታ ስለሆነ መምህርት ሊያም ይህንኑ ስታደርግ የሁሉንም ፋይል አይታ የኒክ መጨረሻ ላይ ቀረ አነበበችው : ተገረመች : ደነገጠች ! **** የአንደኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው! ፀባዩም ሸጋ ነው: ንፁህ እና ብሩህ ተማሪ ነው" የሁለተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ ጎበዝ ተማሪ ነው: ነገር ግን በዚህ አመት እናቱ በጠና ስለታመመች በውጤቱ ቀንሷል" የሶስተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በእናቱ ሞት ተጎድቷል: አባቱም በሀዘን ተጎድቶ ትኩረት የሚሰጠው ሰው የለም" የአራተኛ ክፍል መምህሩ "አባቱን በሞት የተነጠቀው ኒክ በዚህ አመት ብሶበታል: ብቸኛ ነው: ከማንም ጋር አያወራም: ውጤቱም ወርዷል" *** እለቱ የገና ዋዜማ ነው: ተማሪዎች ለመህራኖቻቸው ስጦታ የሚሰጡበት እለት ነው - ሁሉም ተማሪዎች ለመምህርት ሊያ የሚያምሩ ስጦታዎችን እየሰጡ ነበር ኒክ በስተመጨረሻ መጣ - በእጁ ጌጣቸው የረገፈ አምባር እና ሊያልቅ ቂጡ ላይ የደረሰ ሽቶ ይዟል: የእናቱ የእጅ አምባር እና ሽቶ ነበር - ተማሪዎች ይህንን አይተው ሳቁ : መምህሯ ግን ተማሪዎቹን ፀጥ አሰኝታ አምባሩን አጠለቀችው : ሽቶውን ተቀባች : ኒክን አቀፈችው "ዛሬ እናቴን ትመስያለሽ : እናቴን እናቴን ትሸቻለሽ" አላት : ተማሪዎች ከሄዱ በኃላ ለሰአታት ብቻዋን አለቀሰች ** ከዚያ ጀምሮ መምህርት ሊያ ኒክን ተከታተለችው: ኒክ ጎበዘ: አመቱ መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት አመጣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ "የመምህራን ምርጫ" ተብሎ ለመጠራት የበቃው ኒክ በትምህርቱ ጎበዝ: በፀባዩ ምስጉን እና በባህሪው ደግሞ ተግባቢ እና ደስተኛ ሆነ ብዙ አመታት አለፉ: በእነዚህ አመታቶች ሁሉ በገና እለት ዋዜማ መምህርት ሊያ የቤቷ በራፍ ላይ "በህይወቴ ሁሌም ምርጧ አስተማሪ ነሽ! ኒክ" የሚል ፅሁፍ ታገኛለች ኒክ ተመረቀ: ዶክተር ሆነ: በስራው የታወቀ ሀኪም ሆነ ከእለታት በአንዱ ቀን "መምህርት ሆይ! ጥሩ እጮኛ አገኘሁኝ! እናት እና አባት እንደሌለኝ ታውቂያለሽ:: ስለዚህ የሰርጌ ቀን ከጎኔ ቁሚልኝ! ኒክ" የሚል ደብዳቤ ደረሳት ** በሰርጉ ቀን የእናቱን አምባር አድርጋ እና ሽቶውን ተቀብታ ከጎኑ ቆመች : ዳረችው በሰርጉ መሃል እጁን ይዛ ወደ አዳራሹ ሲገቡ "መምህርት ሊያ ህይወቴን በተለየ መልኩ እንድረዳ እና እንድመለከት ስላደረግሽ አመሰግንሻለሁኝ" አላት መምህርት ሊያ እንዲህ አለች “ዶ/ር ኒክ! አንተ ነህ ሰዎችን እና ይህችን አለም የማይበትን መነጽር እንድቀይር ያደረግከኝ: አመሰግንሃለሁ!"❤️ @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
124👍 36
ሶስት ሆነን አንድ ሪል ስቴት ውስጥ እንኖር ነበር:: ከእረፍት ቀናቶች ውጪ ማታ ገብተን ጠዋት የምንወጣ አይነት ሰዎች ነበርን:: ከኮሚቴው በስተቀር ግቢው ውስጥ ከሚኖረው ማህበረሰብ ጋር ከሰላምታ የዘለለ እምብዛም ንግግር የለንም የሆነ ጊዜ ላይ ለሶስት ሳምንታት ያህል ለስራ ጉዳይ ወደ ክፍለ ሀገር ወጥተን ቆይተን ስንመለስ ከአንዱ ህንጻ አራተኛ ፎቅ ላይ የአንዲት አሮጊት ድምጽ ሰማን 👇🏾 "ልጆች! አይቻችሁ አላውቅም የት ጠፍታችሁ ነው?" ድርብብ ያሉ ሴት ናቸው "ለስራ ጉዳይ ወደ ክፍለ ሀገር ወጥተን ነበር እማማ" "እኔማ ጊዜው ክፉ ስለሆነ እና የሚሰማው ሁሉ ስለሚያስፈራ ልጆቼ ምን ሆነው ጠፉ ስል ነበር" ደነገጥን "ልጆቼ?"🤔 "እሺ እማማ አንጠፋም" ጏደኛዬ ጣልቃ ገባ "እማማ ምናልባት ተሳስተው እንዳይሆን: አውቀውናል ግን ማን እንደሆንን?" "ልጄ አውቂያቸዋለሁኝ: ከሱቁ ቀጥሎ ያለው ብሎክ ላይ ስትገቡ ስትወጡ እዚህ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ትታዩኛላችሁ" ተገረምን "ነጭ መኪና የምትይዘው አንተ አይደለህም እንዴ?" "አዎን እኔ ነኝ እማማ" "አንደኛው ጠቆር የሚለው ጏደኛችሁ ልጄን ያስታውሰኛል: ቦቸራ ልጄ እንደ እሱ ወፍራም ቦጅቧጃ ግን ደግሞ የዋህ ልጄ ነበር: መኪና ቀጠፈብኝ እንጂ" ብለው ተከዙ ዝም አልን ! "በሉ ሂዱ አላቆያችሁ! ሁሌም እፀልይላችኃለሁ" "ይፀልዩልናል እማማ?" "አዎን ልጆቼ: ለሁሉም እፀልያለሁኝ ለእናንተም ጭምር" ***** ምሽት ላይ ወደ ሰፈር ስንመጣ ነጠላ: ጥሬ ቡና: እጃቸውን የሚያፍታቱበት እንዝርት እና ጥጥ: የፀጉር ቅባት: ሻሽ እና አንዳንድ ነገሮች ይዘንላቸው መጣን በስውር ለሚከታተሉን አይኖች እና በቅንነት ለሚፀልዩልን ልቦች ሁሉ - ሰላም ለእናንተ ይሁን❤️ @getem @getem @paappii
Mostrar todo...
211👍 34
ምን ጊዜም ከልክ ያለፈ ጨዋነት ጀርባ የሆነች እየተካሄደች ያለች ጨዋታ አለች ብለን እንጠርጥር እንዴ !? . አያቴ እንዲህ ይል ነበር "ስቲንጃ ሲበዛ ትርፉ መነጀስ !" ነው። የሆነ ግዜ እንዲህ ሆነ ባል ስራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱ ስታለቅስ ያገኛታል። ይሄኔ ይደነግጥና ለምን እንደምታለቅስ ይጠይቃታል። እሷም "እዚህ ዛፍ ላይ ያለው አሞራ ያለ ሂጃብ ሆኜ ሲያየኝ ጊዜ ወንጅል ሆኖ ታየኝ። ለዛ ነው ማለቅሰው..." ስትል ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች መለሰችለት። ባልም በዚህ ቁጥብነቷ ተደስቶ እቅፍ አደረጋትና ግንባሯን ሳማት። ወዲያውም መፍለጫ ይዞ ወጣ'ና አሞራው ሚያርፍበትን ዛፍ እንዳልነበረ አድርጎ ቆረጠው ! እናላችሁ ከዕለታት አንድ ቀን ባል ስራ በግዜ ጨርሶ ቤት ከች ሲል.... ያችን ቁጥቧን ሚስቱን ፣ ያችን አሞራ አየኝ ብላ ቂያማ ምታቆመውን ሚስቱን ከውሽማዋ ጋር ተኝታ ያገኛታል። ምንም አላደረገም ትቶ ወጣ። ወደ ሩቅ ሀገርም ሄደ። እና የሆነ ከተማ ሲገባ በጣም ብዙ ሰዎች ቤተ መንግስት በር ላይ ተሰብስበው ያገኛቸው'ና ለምን እንደተሰበሰቡ ይጠይቃቸዋል። ሰዎቹም "የንጉሱ ወርቅ ማስቀመጫ ተዘርፎ ነው" ሲሉ ይመልሱለታል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ የሆነ ሰውዬ ጤነኛ ሆኖ በእንብርክኩ ሲንፏቀቅ ያየው'ና.... "ይህ ሰው ለምን ቆሞ አይራመድም?" ብሎ ይጠይቃቸዋል። እነሱም "አይ ይህማ የከተማችን ትልቅ ሸይኽ ነው ! .. በእግሩ ማይራመደው ምናልባት ሳያውቅ በእግሩ ጉንዳን እንዳይገድል ሰግቶ ነው" ብለው ይመልሱልታል። አአአዎ በቃ እዝች'ጋ ተነቃቁ..... ሰውየውም በፍጥነት "ወላሂ ሌባውን አገኘውት...."ብሎ ጮኸ። ንጉሱም ጋር በፍጥበት ገባ'ና "ያኛው ሸይኽ ተብዬ ነው ንብረትህን የሰረቀህ ከፈለግክ አስፈትሸው'ና ውሸቴን ከሆነ አንገቴን ቁረጠው...." አለ። ወታደሮችም በንጉሱ ትዕዛዝ ሸይኽ ተብዬውን ፈትሸው የተሰረቀውን የወርቅ ማስቀመጫ ተቀምጦበት አገኙት። ሁሉም ተገረሙ ፣ ደነገጡ። ንጉሱም ለሰውዬው "እንዴት እሱ እንደሰረቀ ልታውቅ ቻልክ?" አለው ግራ በመጋባት። ሰውዬውም ሚስቱን እያስታወሰ "ቁጥብነት እና መልካምነትን እንዲህ {ድንበር ባለፈ ሁኔታ} ስታገኘው ከጀርባው ትልቅ ክህደት እንዳለ ያመላክታል" ብሎ መለሰለት ። @wegoch @wegoch @paappii By mustejan
Mostrar todo...
89👍 61👎 5🤔 5👏 3
አንድ ወጣትና ሽማግሌ አይሁድ በባቡር ይጓዛሉ። ወ፤ ስንት ሰዓት ነው? ሽ፤ ዝም። ወ፤ ይቅርታ ጌታዬ፣ ስንት ሰዓት ነው? ሽ፤ ጭጭ። ወ፤ ይቅርታ ጌታዬ እያናገርኩዎትኮ ነው፣ ለምንድነው የማይመልሱልኝ!! ስንት ሰዓት ሆኗል? ሽ፤ ስማ አንት ጉብል። የሚቀጥለው ፌርማታ በዚህ መስመር የመጨረሻው ነው። አታውቀኝም አላውቅህም። ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ትመስላለህ። ለጥያቄህ መልስ ከሰጠሁ፣ ጨዋታ ልንጀምርና በዚያው ልንግባባ ነው። ስንወርድ "ወደቤት ጎራ በል" ማለቴ አይቀርም። እንደማይህ መልከመልካም ነህ፤ እኔ ደግሞ ቆንጆ ልጃገረድ ልጅ አለችኝ። ኋላ ፍቅር ውስጥ ትገቡና የመጋባት ፍላጎት ያድርባችኋል። እስቲ አንድ ነገር ንገረኝ፤ ምን ቆርጦኝ ነው የእጅ ሰዓት እንኳን መግዛት ለማይችል ሞሳ ልጄን የምድረው😊 By mengedenga @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😁 149👍 19👏 5🔥 1
ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል “እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም" ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ "እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለኩላቸው አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል" ቀጠሉ አሮጊቷ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" 50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ "ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?" በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው By zemelak endrias @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
176👍 25🥰 14👏 6🔥 3
አንድ - ፩ ሶስት ግዜ  ነው በጣም የፈራሁት ። ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ ።አምቦ  university economics   ነበር የምማረው አያይ  አሞታል ና አለቺኝ ታላቅ እህቴ ። አያይ ልጆቹ ያወጣንለት የአባቴ ስም ነው ። ቅዳሜ ነበር አራት ሰአት አካባቢ  ቁምጣ እና ቲሸርት አድርጌ ደራራ ሆቴል ጋ ነበርኩ የህቴ ድምፅ ጥሩ ስላልነበር አብራኝ ከነበረችው ቤዛ ሁለት መቶ ብር ተቀብዬ ግቢ ሳልገባ በዛው ቤት ሄድኩ አባቴ ሞቶ ነበር ። ከመሰላል ላይ ወድቆ ግማሽ ቀን ታሞ ነው የሞተው አሉ ።ስምህን ሲጠራ ነበር አሉ ። ይበርታልኝ አለ አሉ ። ምንም ሳላደርግለት አለ አሉ ።እሱ የኔ ነገር አይሆንለትም አለ አሉ .... ብዙ ነገር አለ አሉ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንኳን ይፈልገኛል ። ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ያላረገልኝ ነገር ነው የሚቆጨው፣ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንዳልሰንፍ ያሳስበዋል ፣ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እንደምወደው ያውቃል ፣ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ይጠራኛል ። እውነት እንዳይሆን ፈለኩ ከቅዠት እንድነቃ ከዚ ቀደም ሲናፍቀኝ ሞቶ አይቼ ስባንን ውሸት ሆኖ ሲለሚያቅ እንደዛ ፈለኩ አልሆነልኝም ። አንገቴን እንደደፋው እንዳላዛር ከሞት አስነሳልኝ አልኩት እግዜርን። እግዚአብሔርም ምላሽ አልሰጠኝም ። ከሶስት ቀን በኃላ የአባቴ ገላ የሚመስለኝን ኮት ለብሼ ካምፓስ ተመለስኩ ።  ማታ ማታ ሁሌ እፈራ ነበር ። አባቴን ሳስበው ልቤ በሃይል ይመታል ። ኮቱን ሳልቀይርለት ጠጅ ሳልጋብዘው የተሸከመኝን ኢምንት  ሳልሸከመው አይነት ድብርት  ።  አለመኖሩን የማመን ፍርሃት ተጫወተብኝ ።     By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😢 94👍 24 5
Radric Davis ( ጉቺ ሜን ) አሜሪካዊ ራፐር ነው ። ከጎኑ ያለችው ደሞ Keyshia Ka'Oir ትባላለች ፡ ሞዴሊስት ፡ ጎበዝ አክትረስና ፡ ኢንተርፕረነር ነች ። እና ፡ ከአመታት በፊት ፍቅረኛዋ ጉቺ ሜን ፡ በአንድ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበና ፡ የሶስት አመት እስር ተፈረደበት ። ..... ጉቺ ሜን ፡ ይህን የዳኞቹን ውሳኔ እንደሰማም ፡ ፍቅረኛውን ኬይሽያን ፡ ወደ እስር ቤት እንድትመጣ ላከባት ። .... እየውልሽ ፡ በእስር ቤት ቆይታ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም ። ስለዚህ በስሜ ያለውን ሁለት ሚሊየን ዶላር ፡ ወደ አንቺ ባንክ እንዲዛወር እፈልጋለሁ አላት ። ... እና በባንክ ያለውን ብር በሙሉ ለፍቅረኛው ኬይሽያ ሰጣት ። ጓደኞቹ ቀለዱበት ። ታስረህ ስትፈታ ጎዳና ልትወድቅ ነው ? ይህን ሁሉ አመት ትጠብቀኛለች ብለህ አታስብ አሉት ። ..... Keyshia Ka'Oir ፍቅረኛዋ የሰጣትን ገንዘብ ከባንክ ያወጣችው ብዙም ሳይቆይ ነበር ። እናም በገንዘቡ የራሷን Ka'Oir የሚባል የኮስሞቲክስ ማምረቻ ከፍታ መንቀሳቀስ ጀመረች ። .... ጊዜው ሳይታወቅ ሄዶ ፡ ፍርደኛው ራፐር ጉቺ ሜን የእስር ጊዜውን ጨርሶ ወጣ ። ጓደኛው ኬይሺያ ፡ በስራ ምክንያት ቢዚ ብትሆንም ፡ አልፎ አልፎ እየመጣች ትጠይቀው ነበር ። እና እንደተፈታ በዘመናዊ መኪና መጥታ ፡ ወደ አዲስ ቤት ይዛው ሄደች ። ከዚህ ሁሉ አመት መለያየት በኋላ ትጠብቀኛለች ብሎ ባያስብም ፡ እሷ ግን ከአመታት በኋላም ሳትቀየር ነበር ያገኛት ። እና ቤት ደርሰው አረፍ ካሉ በኋላ ፡ " ጉቺ እስር ቤት ስትገባ ፡ በወቅቱ ሚስትህ ሳልሆን ፡ ትክደኛለች ሳትል ፡ ሁለት ሚሊየን ዶላር ሰጠኸኝ ነበር አይደል የገባኸው ? " አለችው ። አዎ አላት ። ይኸው ስድስት ሚሊየን ዶላር ሆኖ ጠብቆሀል አለችና ፡ የባንክ ቡኳን እንዲያየው ሰጠችው ። ..... ዛሬ ላይ ፡ ጉቺ ሜን ፡ ከዛች ፍቅሩን ብቻ ሳይሆን የሰጣትንም ገንዘብ በእጥፍ አሳድጋ ከጠበቀችው Keyshia Ka'Oir ፡ ጋር ተጋብተው ፡ ትዳራቸው በልጅ ደምቆ , አብረው ይኖራሉ ። ..... መታመን ! @wegoch @wegoch @paappii By Wasihun Tesfaye
Mostrar todo...
👏 68👍 28 15👎 1
በነገራቹ ላይ መልክ ብቻ ሳይሆን ድምፅም ስታድጉ ይለወጣል:: እኔና ወንድሜ ድምፃችን አንድ አይነት ነበር:: ክፍለሃገር ለዘመድ ጥየቃ የሄደው አባቴ : በጠዋት በቤት ስልክ ደውሎ አነሳሁ:: (እስካሁን በህይወቴ ከነበሩ ትዛዞች ዝንፍ ሳልል ያከበርኩት ስልክ ሚነሳው 3ጊዜ ሲጠራ ነው ሚለውን ብቻ ይመስለኛል)😂😂😂 ከዛ አባቴ ሄሎ ስል የወንድሜ ስም ጠራ:: ልክ ወንድሜን እንደሚያዋራ: ደህና ነህ ምናምን አለኝና.... እናቴ እንደሌለች ጠይቆኝ ስነግረው.....የአንድ ዘመዳችንን ስም ጠርቶ አባቱ እንደሞቱ እና እሱ ቅዳሜ ስለሚመለስ እሁድ መርዶ ስለሚነገረው እንድትዘጋጅ እንድነግራትና ለማንም እንዳልናገር አስጠንቅቆ ነገረኝ:: ስልኩን እንደዘጋው እኛ ሰፈር አካባቢ ካለ ጋራዥ የሚሰራው አባቱ የሞቱበት ልጅ ጋ ሄድኩና... አባቱ እንደሞቱ እና እሁድ ሊነግሩት እንደሆነ ነገርኩት:: ልጁ ተንፈራፈረ :አለቀሰ ምናምን:: እናቴ የግድያ ሙከራ ስታደርግብኝ.... አያቶች ከለላ ሰጥተውኝ እዛ ተወሰድኩ:: እሁድ ለታ...አባባ ሲመጣ ወንድሜን ካልገደልኩ አለ.... ወንድሜ ምንም እንዳላደረገ : በስልክ እንዳላወሩ እየደጋገመ እየማለ ይናገራል:: አባቴ ወንድሜን እየተማታ "ጭራሽ ውሸትም ጀምረህልኛል?.... የሷን እና ያንተን ድምፅ መለየት ያቅተኛል? አንተም አድገህ ልትሸውደኝ? ....." "ሂጂ ንገሪ ብለሃት እንጂ....." አባቴ ጥፍጥፍ አደረገው:: አባቴ በሌለበት ምግቤን ይቀማኝና: ይመታኝ ስለነበር ደስስስ አለኝ:: By ma hi @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😁 44👍 13👎 3
በእድሜ የገፉ አዛውንት ባልና ሚስት በወጣትነት ዘመናቸው ያሳለፉትን የፍቅር ግዜያት ለማስታወስ ይፈልጉና ባልየው " ነስሩ ሱቅ አጠገብ ያለው ጎረምሶቹ የሚቀመጡበት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለሁ ... አንቺም ተሽሞንሙነሽ በአጠገቤ ስታልፊ ለክፌ አስቆምሽና እጅሽን ይዤ እያሽኮረመምኩ አዋራሻለሁ " ይላታል ሚስትም በደስታ ተውጣ ትስማማለች ። . ባል ድድ ማስጫው ላይ ለሁለት ሰዓታት ተቀምጦ ቢጠብቅም ሚስት የውሃ ሽታ ትሆናለች ። ይሄኔ " ምን አጋጥሟት ይሆን ?" በማለት ወደ ቤቱ ያዘግማል.... ቤቱ ሲደርስም ያልጠበቀውን ነገር ተመለከተ ሚስት አቀርቅራ ትንሰቀሰቃለች፣ ጠጋ ብሎ ምን እንደሆነች ሲጠይቃት " እናቴ ከቤት መውጣት ከለከለችኝ "😂 @wegoch @wegoch @paappii By lulit Tadesse
Mostrar todo...
😁 111👍 17 9👏 6🥰 3🔥 1
በሰርጓ ቀን ያማረባት ብቸኛዋ ሴት ናት ለኔ ­-የአጎቴ ልጅ ሜሪ። እንደሌሎቹ የሜካፕ ናዳ ፊቷ ላይ አዝንባ፤ አዲስ መልክ ይዛ አልመጣችም፤ ያው...እግዜር አንዴ ተጠብቦ ተጨንቆ ሰርቷት የለ? ከዚ ወዲያ የሜካፕ ባለሞያዎች ከማበላሸት በቀር ምን ይጨምራሉ?- ምንም። ንጥት ያለው ቬሎዋ መሬት ላይ፤ የተፈጥሮ ፀጉሯ ደሞ ጀርባዋ ላይ ተንፏሏል፤ ውብ ገጿ ላይም አንዳች ሚያክል ደስታ ድሩን ሰርቷል። ሁሌም ደስተኛ ነች የምትባል ሴት ብትሆንም፤ የዛሬው ግን የተለየ ነው፤ የደበዘዘ ሮዝ ቀለም የተቀባውን ከንፈሯን ከፈት እያደረገች፤ሀፍረት የቀላቀለ ፈገግታ ትጋብዘናለች። ፀጉሯ ላይ የሚያንፀባርቅ ነገር ይታያል፤ አክሊል ካናቴራ ነው፤ ሄዶባታል አጥገልፀውም ምክንያቱም... የምር ንግስት የሚያስመስል ግርማ ሞገስ አላት። በቀኝ እጅዋ እንደሷ የፈኩ ነጫጭ አበቦችን፤በግራ እጅዋ ደሞ የመጪው ባሏን ክንድ ቆልፋ ይዛለች፤ በኤሊ እርምጃ ወደ አዳራሹ በማዝገም ላይ ናቸው፤ ብዙዎች ከሁዋላ ሀይሎጋ እየጨፈሩ ያጅቧቸዋል። እኔ እና አጎቴ(የሙሽራዋ  አባት) አዳራሹ መግቢያ ላይ ተሰይመናል፤ በትንሹ እያጨበጨብን፤ በፍቅር አይን ሙሽሮቹን እናያቸዋለን። ሁለታችንም ተመሳሳይ ሱፍ ነው የለበስነው፤ እንደወጣትነቴም፤ እንደ ቁመና ባለቤትነቴም፤ እኔ ላይ ይበልጥ ሳያምርብኝ አይቀርም። በቃ ተውኩት፤ 'ስለ ራስ አይወራም!' ያለኝ ማን ነበር?...ብቻ ማንም ይሁን ማን ልክ ሳይሆን አይቀርም። በአሁኑ ሰአት ግን ሙሽሮቹን ማጀብ ሲገባኝ፤ እዚ ፈዝዤ የቆምኩበት ምክንያት አልገባኝም፤ በርግጥ ሜሪ ቀድማኝ በማግባቷ ትንሽ ደብሮኝ ነበር፤ «አትቀድመኝም!» «አትቀድሚኝም!» የሚል የፌዝ ውርርድ ስለነበረን፤ በመሸነፌ ትንሽ ቅር ብሎኛል። ግን የሷ ደስታ ደስታዬ አይደለም እንዴ?...ይሄን ያክል ፋራ ሆኛለሁ?...ሳምንቱን ሙሉ ጠብ እርገፍ ስል የነበር፤ ዛሬ እንዲ ለመሆን ነው? ራሴን ተቆጣሁት፤ደሞስ የሷ ሰርግ ያልጨፈርኩ የማን ልጨፍር ነው? ከሰመመኑ እንደ ነቃ ሰው ደንገጥ አልኩና ፤ወደ አጃቢዋች ሄጄ ተቀላቀልኩኣቸው። ሜሪ አስተውላኝ ነበር፤ ዲምፕሎቿን አስከትላ  ፈገግ አለችልኝ። ደስ ስላላት፤ ደስ አለኝ። ድምፄን አጠብድዬ እኔ እመራቸው ጀመር፤ የጭፈራውውን ዙር አከረርኩት...። * * * ልጅ እያለሁ ነው ፤ ወደ አስራዎቹ መግቢያ ላይ። ከእናቴጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መነሀሪያ ሄድኩ፤ ተገድጄ ነው እንጂ፤ የመምጣቱ ፍላጎት አልነበረኝም። ቆይቶ ግን አብዛኛውን የማየው ነገር አዲስ ስለሆነብኝ፤በሆድ ማማረሬን አቆምኩ። ገና ከመግባታችን አንድ ሱቅ በደረቴ አዟሪ ልጅ መጥቶ እናቴን ይለማመጣት ጀመር፤ «እናት ሶፍት ይፈልጋሉ?..ማስቲካም አለ ጦር..ባናና..» ምንም እንደማትፈልግ ከይቅርታ ጋር ነግራው፤ መቀመጫ ወዳለበት ሄደን ተቀመጥን። ሲመስለኝ የምንቀበለው ሰውዬ ገና አልደረሰም። ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ፤ እናቴ ሁለት ባሶች ተከታትለው መግባታቸውን አስተውላ፤ ባለሁበት እንድጠብቃት አስጠንቅቃኝ ሄደች። የግቢው(የመነሃሪያው) ስፋትና የመኪኖቹ ብዛት አስገርሞኝ፤ አይኔን ወዲያና ወዲ እያቅበዘበዝኩ ትንሽ እንደቆየሁ፤ ውሃ ሰማያዊ ቀሚስ ያደረገች ሴት ወደ እኔ አቅጣጫ ስትመጣ ተመለከትኩ። ይሄኔ ነው እንግዲህ ጉዴ የሚጀምር። እድሜዋ ከኔ ጋ ተመጣጣኝ ይሆናል፤ አልያ ደሞ በትንሽ ትበልጠኛለች። ከሩቅ እንዳየኋት ቆንጆ መስላኝ ነበር፤ እየቀረበች ስትመጣ ግን እጅግ በጣም ቆንጆ ሆነችብኝ። ከላይ እስከ ታች ባይኔ አላመጥኩኣት፤ ስጋ እንዳየ ውሻ ምላሴን አውጥቼ ለሀጬን ማዝረክረክ ነው የቀረኝ። አፌን እንደከፈትኩ እርምጃዋን ስቆጥር ከአይኗጋ ገጠምኩኝ፤ በጣም ማፍጠጤ ታወቀኝና አይኔን ሰበርኩ፤ ዝቅ አልኩ። ወዲያው የየሆነ ሰው ጥላ እየቀረበኝ መጥቶ ካጠገቤ ሲቀመጥ ተሰማኝ። እሷ መሆኗን ላረጋግጥ ቀና ስል፤ በድጋሚ ካይኖቿጋ ተጋጨሁ፤ እዛው ስብር። ሆ! በምን ሃቅሜ፤ ልቋቋማቸው? ልቤ በፍጥነት እየመታ ነው፤ ሰውነቴም በላብ ተጠምቋል፤ ወደሷ መዞር አቃተኝ፤ የተሸከምኩኣት ያክል ከብዳኛለች። በእርግጥ በጣም የተቀራረብን መስሎ ተሰማኝ እንጂ በመሀከላችን ያለው ርቀት አምስት ሰው ያስቀምጥ ነበር። ከትንሽ መንቀጥቀጦች በኋላ አላስችለኝ ሲል፤ እንደምንም ሰረቅ አድርጌ አየሁአት፤ 'ተመስገን'! አልኩ ከአይኖቿ ጋ ስላልተጋጨሁ መሆኑ ነው ሂሂሂ!!። እንደዚህ አይቼ የደነገጥኩላቸው ሴቶች ጥቂት ነበሩ፤ ግን አንዳቸውንም አውርቼአቸው አላውቅም። ይህቺን ልዕልት መሳይ ግን ዝም ብሎ ያልፋት ዘንድ ልቤ አልቻለም፤ ውስጤ 'አናግራት!..አናግራት!' በሚል የድምፅ ማእበል ተናወጠ። እሷን የማናገር ፍላጎቴ ናረብኝ፤ ከዚህ የፍርሀት አዘቅት ወጥቼ እንዴት እንደማወራት ግራ ቢገባኝም፤ ውሳኔ ላይ ደረስኩ። ቀረብ ብዬ ልተዋወቃት፤ የተሰማኝን ሙሉውን ባልነግራትም፤ የመጣልኝን ብዬ ከበኋላ የህሊና ፀፀቴ ለመዳን ወሰንኩ። ራሴን በራሴ motivate ማድረግ ጀመርኩ፤ እንደሚችል ነገርኩት፤ ተቀበለኝ (ማለቴ ተቀበልኩት)። መመለሷን ስጠብቅ የነበረውን እናቴን ከነ እንግዳው በዛው እንዲቀሩ እየተመኘሁ ፤እግሬን አዘጋጀሁ፤ ጉሮሮዬን ጠረኩ፤ ልብሴን አስተካከልኩ በስተመጨረሻ ብድግ ስል፤ እናቴ ሻንጣ እየጎተተች ካንድ ሰውዬጋ ወደ እኔ ስትመጣ አየኋት። በእውነቱ ያን ጊዜ የተሰማኝን የመንፈስ ስብራት ልገልፅላችሁ አልችልም። ክው ነው ያልኩት፤ እዛው በቆምኩበት ክርር፤ ድርቅ፤ ዝም፤ ምንም። እንባዬን እየታገልኩ መለስኩት፤ ዋጥ!። ደረሱ። እናቴ አጎትህ ነው ብላኝ ከሰውየውጋ አስተቃቀፈችኝ። ሰላም ብዬው አብቅቼ ዞር ስል፤ « አልተዋወቃችሁም እንዴ? » እናቴ ነበረች። « ከማንጋ? » መቼም አጎትየውን እንደማይሆን አውቄ ጠየኳት። « ከ ሷ'ጋ ነዋ! » ጎኔ ተቀምጣ ስታስጨልለኝ ወደነበረችው እንስት በግንጭሏ እየጠቆመች። ይሄኔ ነበር ከቅድሙ በበለጠ በላብ የተዘፈቅሁት። ጉልበቴ ይርበተበት፤ ሰውነቴ ይንቀጠቀጥ ጀመር፤ እንዴት የልቤን አወቀችብኝ? ግራ ግብት አለኝ። የምለው ባጣ፤ አናቴን በአሉታ ግራ ቀኝ ወዘወዝኩላት «በፍፁም!» እንደማለት። ወዲያው ልጅቱን እጅዋን ይዛ አስነሳቻትና.. « እስከዛ ተዋወቂው ብለን ነበርኮ ወዳንተ የላክናት... ለማንኛውም ያጎትህ የሙሌ ልጁ ነች...በሉ ሰላም ተባባሉ » ፈዘዝኩ፤ ህልም ህልም መሰለኝ፤ ስሜቴ ድብልቅልቅ አለ፤ ልደሰት ወይስ ልዘን? እጇን ዘረጋችልኝ፤ ከበድን አካሌ በድን እጄን ልኬ ጨበጥኩዋት፤ እጇ ይለሰልሳል፤ « ሜሪ እባላለሁ! » ፈገግ ብላ ስሟን አከለችልኝ፤ ፈገግ ስትል ጉንጮቿ ሰርጎድ አሉ። ደስ የምትል ልጅ ደስ የሚል ስም አላት። እኔ ግን ስሜን የምናገርበት አቅም አጣሁ፤ ምላሴ ተሳስሯል፤ አንደበቴ ተዘግቷል፤ ዝም አልኩኝ ፤ ዝም። ምናልባት ብዬ ከህልሜ እስኪያባንነኝ፤ ሳምንታትን ጠበቅሁ...ልነቃ ግን አልቻልኩም...እውን ነበር። ∝ By BINIAM EJIGU @wegoch @wegoch @wegoch
Mostrar todo...
👍 62 10😁 8👏 2😢 2👎 1
አባቴ ሁሉ ነገርን መጋፈጥ ይሰብራል ይላል ። ጀግና ሁኔታን የሚረዳ ነውም ይላል ። እኔ የምጋፈጠው ለማሸነፍ ጀግናም ለመሆን አይደለም ሲደርሱብኝ ነበር ። አፈግፍጌ አውቃለሁ ። ያፈገፈኩኝ ግዜ የሚሰማኝ ስሜት መጥፎ ነው ። አባቴ "የማያፈገፍግ ታጋይ በቶሎ ይሞታል" እያለ የውትድርና ገጠመኙን ያጣቅስልኛል ። በሂወቱ ምድር ላይ እንደኔ የሚጨነቅበት ጉዳይ ያለ አይመስለኝም "እሱ ማስረዳት አይችልም በዛ ላይ ያፈጣል ....ችግር የሚፈታው አንገት ለአንገት በመተናነቅ ይመስለዋል" ይላል ። "አንዱ ይገለዋል አጉል ቦታ ይመቱታል የሰው ሰው እጁ ላይ ይጠፋል" ይላል "እኔ በሂወት የኖርኩት እጅ ሰጥቼ ነው ። ይሄው ከዛ በኃላ ያገኘሁት መዓረግ እና ደስታ ይቆጠራል ?? " አባቴ ትኩረቱ ስለሆንኩ መሰለኝ ልጁ ስለሆንኩ መሰለኝ ስላሳደገኝ መሰለኝ ስለሚያስብልኝ መሰለኝ ከኔ በተሻለ እኔን ያውቀኛል ። ስለኔ ገምቶ የተሳሳተበት ግዜ አላስታውስም "በጠበል አልወጣ ያለ ጂኒ አለበት" ይላል ። የሆነ ቀን ተሳካልኝ ልጄ ልብ ገዛልኝ ስለቴ ሰመረልኝ ብሎ በመሃበርተኛው ፊት ተናዞ ስለቱን እንዳስገባ የመሃበርተኛው ልጅ አዲሱ ነገረኝ ስለት ካስገባበት ቀን ጀምሮ ሳሰላስል ልብ ገዛ እንዳለው አይነት ሰው ሆኛለሁ ። ደርሰውብኝ ያለፍኳቸው ቀምተውኝ የተውኳቸው ትተውኝ ያለቀስኩበት ስፍራ ብዙ ነው ። ምን ብሎ ተስሎ ይሆን ስለቱ የሰመረው?? ምን አለ አሁን ትልቅ ህልም እና ህልሙን መተግበርያ ጥንካሬ ስጠው ብሎ ቢሳልልኝ By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
54👍 27👏 6🔥 5
ከፋኝ ብዬ ነበር ብቻዬን የሆንኩት ። የምፈልገው ነገር አልሆነም ብዬ ነበር የተሸሸግኩት ። ጠይም ናት ሳቂታ ። ደሞ ስትስቅ ታምራለች ስታወራኝ ረጋ ብላ ነው ። ተገናኝተን ሳንስቅ ሳንሿሿፍ ቀርተን አናውቅም ። ከሆነ ግዜ በፊት የሆነ ወቅት ባገኛት ብዬ አስቤ አውቃለሁ ። ለምን ለኛ የሚሆኑ ሰዎች ወይ ፈጥነው ወይ ዘግይተው ይመጣሉ ? በሰዓቱ ለምን አይመጡም ?? አለመገጣጠም ከመተላለፍ ይሻላል !!። ናይል ድብርት የሚያጠቃት ናት ። ናይል ድብርቷ እየተባባሰባት ነበር። "አግዘኝ መደበር ተስፋ ቢስ መሆን ደክምኛል" አለች። "እሺ" ብዬ አቀፍኳት ። እንድለቃት አልፈለገችም ነበር። ስለድብርቷ ገምቼ አውቄባት እንጂ በቃሏ ምንም ብላኝ አታውቅም ነበር ። ከእቅፌ ሳስወጣት አይኗ እምባ ነበረበት ። ከሶስት ቀን በኋላ ሁሉ ነገር ሲሰለቸኝ ። ስልኬን ዘጋሁት ብቻዬን ሆንኩኝ በተቻለኝ መጠን አልጋዬን ላለመልቀቅ ሞከርኩ ። ከአስራ ሶስት ቀን በኃላ ስልኬን አበራሁኝ ። ናይል ቴክስት ልካልኝ ነበር "ፈልጌሃለሁ" የሚል ወድያው ናይል ጋር ደወልኩ ስልኳ ዝግ ነበር ደጋገምኩት ያው ነው ። በአስራ አራተኛው ቀን እቤቷ ሄድኩ : ናይል አልነበረችም ። ሰፈሯ ስሄድ የሚጠራልኝ ልጅ ፣ባለሱቁ ፣አከራይዋ ሁሉም ራሳዋን አጥፍታለች አሉኝ ። ስላላመንኳቸው ሁሉንም ደጋግሜ ነው የጠየኳቸው ሁሉም ፊታቸው እውነታቸውን እንደሆነ ያስታውቃሉ ። እንዴት እንደከፋኝ .... መኖር እፈልጋለሁ አግዘኝ እያለችኝ ። እራስ ወዳድነት ነው መሰለኝ እንዳልሰማት ከለከለኝ ። ሞቷ ውስጥ እጄ አለበት ። ለመሞት ስትመቻች ሸኝቻት ነበር ። ስቅስቅ አልኩ ። ድብርት ሀዘን ከፀፀት ጋር ከባለፈው በላይ አዝረከረከኝ ። ስልኬን መዝጋት ፈልጌ ነበር እንደ ባለፈው መደበቅ ፈልጌ ነበር ። ፈራሁ የሆነ ሰው ሲጠራኝ ባልሰማውስ ?፣ ቢያመልጠኝስ ? ለራስ ብቻ መኖር ለካ አይቻልም!! By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😢 48👍 38😱 1
"  ብሌኔ ትለኝ የል?" "አዎ" "ያላንቺ በድን ነኝም ብለኸኛል" "ነኝኮ" "ታዲያ ትተኸኝ አትኺዳ? በሌን ብቻዋን ምን እርባን ይኖራታል" "እማዬ ሆዴ! አዎን ማያዬ ነሽ።የእናቴ  ቤት እየተቃጠለ ዓይኗን እየጠነቆሉባት ዓይኖችሽን እያየሁ በፍስሃ ልኑር? አተላ ነገር ነው የሚሆነው።" " አንተ ብቻህን ምን ትፈይድላታለህ?" "ለዛ አይደል መኼዴ?   እንደኔ አይነት ብዙ ወዳሉበት"    "የኔ ጌታ እሺ በለኝና አትሂድ....ምንም አልዋጥልሽ እያለኝ ነው" "እእእ አሁንስ?" አላት ከአገጯ ቀና አድርጎ ከንፈሯን ከሳማት ኋላ። ምንም ቃል ሳይወጣት ለደቂቃ አሻቅባ እያየችው ቆየችና ድንገት በሁለቱም ዓይኖቿ እንባዋን ታረግፍ ጀመር "እናት እንዲሁ ከብዶኛል እንባሽ ተጨምሮ አልችለውም " አለና ለራሱ ደረቱ ላይ አጥብቆ አቀፋት። "አንቺን ሲነኩሽ ማሰብ አልችልም ።ያቺ ሰባት ወንዶች የደፈሩዋት .... ተይው ግን እሳቱ የተቀጣጠለበት ኼደን ካላጠፋነው እሱ  መቶ ያቃጥለናል ።" "እግዜሩ ካልቀጣቸው ሰው በምን አቅሙ ያኚን ጋኔን ይመክታል?  አላማረኝም ተው......" "አልተውም 😂"ግንባሩዋን ጉንጮችዋን አገጭዋን አይኖችዋን ከንፈሩዋን ተራ በተራ ስሞ ሲያበቃ " "አንቺን የመሳሰሉ ጥኒኒጥ ልጆቼ አኚህ የሳጥናኤል ተኩላዎች ባሉበት ተወልደው እንዲያድጉ አልፈልግም" አላት በዓይኖቹ ዓይኖቿን አተኩሮ እያየ። ምንም ብል ድካም ነው ብላ አሰበችና ዝምታን መረጠች።  ዓይኖቻቸው እንደተገለጡ እኩለሌሊት ካለፈ ወዲያ እንግላል በተኛበት  ክንዱዋን ደረቱ ላይ አስሞርክዛ ቀና አለችና ቁልቁል ስትመለከተው "ባንቺ አየን ያንድዬን ስራ ያለእቅድ እንደሚሰራ ፈጣሪ ተራቆብሻል ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል"እያለ ማንጎራጎር ጀመረ። "ስሜትህን ለመደበቅ አትጣር ,የእውነት ምን እየተሰማህ ነው?"                  "እስከዛሬ ሽቅብ አይቼሽ አላውቀውም ወይ ቁልቁል አይተሺኝ አታውቂም? መኮሮኒ አፍንጫ አይደለሽ እንዴ"" "ጌታ የምሬን ነው" አለች ቆጣ ብላ። "ጌታን እውነታው ጎራዳ ነሽ" "ታውቃለህ ግን.......ኡፋ እንደውም ተወው በቃ"አለችና ደረቱ ላይ ተኝታ እጇን ፀጉሩ ስር ሰዳ ማሻሸት ጀመረች። " ዎ አትነካኪኝ,  ለሊት መንገደኛ ነኝ ይደክመኛል" "ስድ ! ሂድ ወደዛ" "ነይ ወደዚ😂😂" ከትከት እያለ ሳቀ።ከደረቱ ላይ ተነስታ ጀርባዋን ሰታው ተኛች።እየሳቀ ዞረና ፊቱን አንገቱዋ ስር ሸጉጦ እጁን በወገቡዋ አዙር ሆዷ ላይ አደረገና እቅፍ አደረጋት። ዓይኗን ስትገልጥ ወገግ ብሏል ።ዞር ስትል ብቻዋን ነች።የሌሊት ልብሷን እንደለበሰች ወርዳ ሩጫ ጀመረች።ቦታውጋ ስትደርስ ማንም አልነበረም።ጠጋ አለችና የመስሪያ ቤቱን ጥበቃ "ምልምሎች የሚሳፈሩት ከዚህ አልነበር እንዴ? አባቴ" " አዎን ከዚሁ ነው በለሊት ወጡ እኮ" እጢዋ ዱብ አለ። " አላለቅስም!! ሰው መንገድ ሲኼድ አይለቀስም ሰላም ተመለስ ነው ሚባለው"ብቻዋን እንደእብድ እያወራች ወደ  ቤቷ ገባች።ከዚያች እለት በኋላ ያወቁዋት ሰዎች "ፍንጭታም ነች ወይንም ጭርሱንም ጥርስ የላትም ይሆናል" እያሉ ያሟታል።ቀበሌ የሚሰራ ሰው ቤቷ አቅራቢያ ስታይ ጉልበቷ ይከዳታል በእጃቸው ወረቀት ይዘው ከሆነ ደግሞ ሰው "አበደች?" እስኪላት አሪ እያለች ታለቅሳለች።ቤቷ ሚመጣ ሁሉም ሰው ሊያረዳት የመጣ ይመስላታል ።    የፈሩት ይደርሳል ሚሉት እውነት ይመስላል።ጎህ ሳይቀድ ተሰብስበው በሯን አንኳኩ ።ከፍታ እንዳየቻቸው እንባዋ ረገፈ። ደብዳቤው ምን ይላል አላለችም ።ሃገሬው ለሁለት ተከፍሎ ገሚሱ በሷ የደረሰ በማንም አይድረስ ሲል ሌላው አሟርታ ገደለችው አላት። ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ሰፈሩ ዳግም በለቅሶ ድብልቅልቅ አለ።      መጣ!!! ሞቷል የተባለ ሰው በህይወት ሲመለስ እንዲህ ያስለቅሳል ማለት ነው በማለት እየተገረመ መልሶ መልሶ "የታለች?" ሲላቸው ። "ሞትህን መቋቋም ከብዷት እራሷን አጠፋች" ብለው መለሱለት።ተሰብስቦ የሚያለቅሰውን ሰው እየከፈለ ወቶ ኼደ።አልተመለሰም። ሰብሰብ ብለው ከቤተክርስቲያን እየተመለሱ እመንገድ ዳር ላይ የተቀመጠውን እብድ እየተመለከቱ "አዪዪ ያን የመሰለ ልጅ እምጽ ...እንዲ ከምያንገላታው በገደለው" ያሻቸውን እንዳሻቸው ፈረዱበት።ስንቱ ይሆን ለነሱ ጋሻ ልሁን ብሎ በተመሰቃቀለ "በገደለውን" ያተረፈ አመድ አፋሽ ።      ጫሪ Enat Kassahun @ethioma1 @wegoch @wegoch @wegoch
Mostrar todo...
😢 72👍 34 10🔥 2👏 1🤔 1🤬 1
" ትወደን የለ አበርታን " ( መውደዱን ለመግለፅ ማኖሩ አይበቃም ? ) ✍ ካሊድ አቅሉ ~   ~   ~   ~   ~    ~   ~    ~    ~    ~ ትወደኝ የለ አበርታኝ ትለዋለች አንድዬን እንደሚወዳት እንዴት በእዚህ ልክ ተማመነች ? መማፀንዋ አጊንታው መውደድዋን የገለፀችለት ይመስላል ምንዋ ተነክቶ ነው በእዚህ ልክ ፈጣሪን የተማፀነችው ?  ልጠይቃት አስቤ በማያገባኝ መግባት መስሎ ተሰማኝና እራሴን ቆጠብኩ ። ለሶስት ሰዓት ሙሉ ሊክቸሩ ሲያስተምር እሷ አርሚቸር ወንበርዋ ላይ " ትወደኝ የለ አበርታኝ " ብላ ፅፋ እሱኑ ታደምቃለች ፊትዋ ጥቁር ብልዋል ከፍቅረኛዋ ጋር ተጣልታ ይሆን ? " ይቅርታ የኔ ውድ ካስከፍሁ እንታረቅ " ብላ  ባለንጋ ጣቶችዋ ፀጉሩን ስትዳብስ በምናቤ ታየኝ ። ፍቅር አለብኝ መሰለኝ የእሷዋን መከፋት ከወንድ ጋር ብቻ አያያዝኩት ። እሷ ቃሉን በማድመቅ ላይ ናት ። አይንዋ ያሳሳል ሆድ ያስብሳል አላያትም ብለው ቢገዘቱ የሚረታ ውበት አላት ። በሀሳቤ ፈረስ ስጋልብ የተማሪዎች ጫጫታ  አነቃኝ አይኔን  ቀና ሳደርግ ከሰሌዳው ላይ (Quiz) የምትል ፅሁፍ አስተማሪው አሳርፈው አየው ። ከሴት ፈተና ወደ ቀለም ፈተና ይሄን እስተማሪና ህይወትን ሚያመሳስላቸው ነገር ሳይናገሩ መፈተናቸው ነው ። እኔም ወረቀት አወጣውና እንዲ ብዬ ቃል አሳረፍኩ ( ትወደን የለ አበርታን ) " በእዚህ ልክ እንደሚወዳቹ በምን ተማመናቹ ?" ለምትሉን ጭንቁ ሲጠናብን አንድ መልስ አዘል ጥያቄ እናቀርባለን . . . (መውደዱን ለመግለፅ ማኖሩ አይበቃም ?) ~  ~  ~  ~  ~   ~    ~   ~   ~ ~ ~  ~ @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
55👍 31👏 7🔥 1🥰 1
ከ 35 እስከ 40 አመት እድሜ ክልልን ስትመታ ወይም ስትቃረብ ነገሮች ይቀየራሉ ምን ይቀየራል? 👇🏾 ወላጆችህን: ቤተሰብህን: ወዳጆችህን: ፍቅረኛህን: ልጆችህን ወደህ ወደህ በስተመጨረሻ ራስህን መውደድ ትጀምራለህ የአለም ችግር በአንተ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነገር አለመሆኑን ትረዳለህ: የሚያብሰለስሉህ ነገሮች እና ምክንያቶች ይቀንሳሉ ከምስኪኖች ጋር በጉሊት ንግድ ሂሳብ መከራከር ታቆማለህ: ተፍ ተፍ የሚል ሰው ስትመለከት ከአንተ ኪስ ይልቅ የእነርሱ ላብ እና ድካም ይበልጥብሃል አንድ ሰው የሆነን ታሪክ ደግሞ ቢነግርህ "ነግረኸኝ ነበር እኮ" ብለህ አታሳቅቅም: መደመጥ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ስለምትረዳ ታሪኩን ታስጨርሳለህ - ምናልባት ሰውዬው ታሪኩን ሲያወራ ትዝታውን እያደሰ ይሆናል ሰዎችን በየሚሰሩት ስህተት ፌርማታ እያቆምክ ማረም ይደክምሃል: የዚህችን አለም ስህተቶች የማረም ሃላፊነት የአንተ እዳ እንዳልሆነ ትረዳለህ ከልብስ ይልቅ ማንነት እንደሚበልጥ ትረዳለህ: ከምግብ ይልቅ የውስጥ ሰላም ዋጋ እንዳለው ይገባሃል ከአንተ በእድሜ ያነሱ ሰዎች አጉል አራዳነት ሲጫወቱ እና ያለፍክበን መንገድ ሲሄዱበት አያናድድህም: "እድሜያቸው ነው" ብለህ ታልፋለህ እንጂ አትበሳጭም ከማያከብሩህ ሰዎች እና የማትፈለግበት ቦታ አትውልም: ራስህን አክብረህ ገለል ትላለህ እንጂ የሚተናነቅህ ግብዝነት አይኖርም: በመተው ታምናለህ - ሰዎችን ከማሳደድ ይልቅ ለህሊናቸው አሳልፈህ መስጠት ትመርጣለህ @wegoch @wegoch @paappii By Zemelak endrias
Mostrar todo...
👍 75 33🔥 7👎 1
የእድሩ ስም ጠሪ ----- ከተስፋዬ ገብረአብ ---- እለቱ ሰንበት ነው:: ደብረዘይት። የቢሾፍቱ ቀበሌ የሃዲድ በላይ እድርተኞች ለቀብር ቃጂማ ጊዮርጊስ ተሰብስበዋል። ሰንበት ስለሆነ ነው መሰል ቀብር ላይ በርከት ያለ ሸኚ ተገኝቶአል። በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች ልማድና ደንብ መሰረት በቀብር የተገኘና ያልተገኘውን ለማጣራት የስም ጥሪ ይካሄድ ጀመር። ስም ጠሪው ባሻ መላኩ እርጅና ተጭኖአቸዋል። ቢሆንም ግን ድምፃቸው እንደ ባቡር ጡሩምባ ነው። በፀጥተኛው የመቃብር ስፍራ እየተምዘገዘገ ያለችግር ከአስከሬን ሸኚው ጆሮ ይደርሳል፣ “ወይዘሮ ፈትለወርቅ ሞላ” “አቤት!” “አስር አለቃ እርገጤ ሺባባው” “አለሁ!” “ወይዘሮ ከበቡሽ ደሜ” “አቤት!” “አቶ ዳኜ ተማም” ምላሽ አልነበረም፣ “አቶ ዳኜ!?” አሉ ስም ጠሪው በድጋሚ፣ “አለሁ! አለሁ! “ የሚል ድምፅ ተሰማ፣ ይህን ጊዜ ሽማግሌው ስም ጠሪ እብድ የሚያህለውን ዶሴ አጥፈው እርሳሳቸውን ጆሮአቸው ላይ ሰክተው ከፊታቸው ለተኮለኮሉት የእድሩ አባላት ማስጠንቀቂያ ይሰጡ ጀመር፣ “ስሙኝ ቀባሪዎች! እኔ ላንቃዬ እስቲዘጋ የምጮኸው እንደ ፊልፕስ ሬድዮ ባትሪ ውጬ አይምሰላችሁ። በዚህ እድር በቀን አንድ ሰው ይሞታል። በየቀኑ እጮሀለሁ! በ75 ብር ስጮህ መዋሌ ወገኖቼን ልጠቅም ካልሆነ ገንዘቧ ምን አላት? ስለዚህ ካንድ ጊዜ በላይ አልጠራም! ቀሪ ተባልሁ ተብሎ ቅያሜ እንዲመጣብኝ አልፈልግም። ተቀጣሁ ተብሎ ወቀሳ እንዲወርድብኝ አልፈቅድም። ጆሮአችሁን ተክላችሁ ስማችሁን አዳምጡ። እኔ የቁራ ዘር የለብኝም። በየሜዳው የሚጮህ ቁራ ነው። በየባህር ዛፉ፣ በየገደሉ፣ በዋርካ ላይ ተጎልቶ ሲጮህ የሚውል ቁራ ነው፣ እኔ ግን ቁራ አይደለሁም” ስም ጠሪው በተጨማደደች መሃረም ግንባራቸው ላይ ያቸፈቸፈውን ላብ አደራረቁና ጥሪውን ቀጠሉ፣ “ወይዘሮ የሁዋላሸት አለሙ” “አለሁ!” አለ የወጣት ወንድ ድምፅ፣ “ደሞ አንተ ማነህ?” ‘ልጃቸው ነኝ!” ጥሪው ቀጠለ፣ “አቶ ከበደ ማሞ” ምላሽ የለም፣ ቀሪ። “ፊታውራሪ የሽዋሉል ግርማቸው” ምላሽ የለም፣ ቀሪ። “እመት ጌጤ እሸቴ” “ታመዋል!” የሚል ድምፅ ተሰማ። “አቶ ተሰማ ታደለ” ምላሽ የለም፣ ቀሪ። የእድሩ ስም ጠሪ ግምባራቸውን በመሃረም እያበሱ ቀና አሉ፣ “ስሙኝ ቀባሪዎች! ቀሪ በዝቶአል። እንዴት ነው ነገሩ? አዲስ ድንኩዋን ገዝተን የምረቃ ግብዣ የተባለ ለታ ግን እድርተኛው ግልብጥ ብሎ ነበር የመጣው። ትርፍ ሰው ሁሉ ነበር። የቀበርናቸው ሰው ወክለው ነው? ቀብር ሲባል ግን ቀሪ ይበዛል? ነግ በኔ ነው። ዛሬ ያላቃበርነው ነገ አይቀብረንም…” ምክርና ተግሳፁን እንዳበቁ ጥሪውን ቀጠሉ፣ “አቶ ሃይለራጉኤል ተካ” “አቤት” “ወይዘሮ ኪሮስ ገብራይ” “አለሁ!” “ወይዘሮ አረጋሽ አባተ” ምላሽ የለም፣ ቀሪ። “አቶ ኩራባቸው ታዬ” “አቤት!” “መምህር ገረመው ደበላ” “አቤት!” “ወይዘሮ የወርቅውሃ ታደሰ!” ምላሽ የለም። የእድሩ ስም ጠሪ በድጋሚ “ወይዘሮ የወርቅ ውሃ! ‘ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጠሩ። መልስ የለም። ሽማግሌው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ። "እኝህ ሴትዮን ምን አግኝቷቸው ነው? በጣም ደግ ሰው ናቸው። ቀብር ቀርተው አያውቁም። ወይዘሮ የወርቅውሃ!" በዚህ ጊዜ አጠገባቸው ቆሞ የነበረ አንድ ጎልማሳ ወደ ጆሮአቸው ጠጋ ብሎ አንሾካሾከ። “ይዝለሉት ባሻ፣ ዛሬ የቀበርነው ወይዘሮ የወርቅውሃን ነው” ----- (ልቦለድ፣ 1989 አዲስ አበባ - ተስፋዬ ገብረአብ) @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😁 55👍 32😢 13 7
ገጠራማ እርሻ ቦታ ነው ባል እና ሚስት የሆኑ ገበሬዎች አዲስ ስለገዙት እቃ እያወሩ ነው - ትልቅ የአይጥ ወጥመድ ገዝተው እያወሩ ነው ይህንን ሲያወሩ ደግሞ አይጥ ሰምታለች 👇🏾 የወጥመዱ መገዛት ያሳሰባት አይጥ ዶሮ ጋር ሄዳ ትነግራታለች "ታዲያ እኔ ስለ አይጥ ወጥመድ ምን አገባኝ" ብላ ፊት ነሳቻት ከዚያም ፍየል ጋር ሄዳ ስትነግራት "የአይጥ ወጥመድ እኔን አያሰጋኝም :አትነዝንዢኝ" ብላ አባረረቻት አይጧ ተስፋ ሳትቆርጥ ላም ጋር ሄዳ ስጋቷን ስታስረዳት "የአይጥ ወጥመድ ላምን አይይዛት: ምን ጨነቀኝ" አለቻት አይጧ በመልሳቸው አዝና ልጆቿን እና ዘመዶቿን ሰብስባ ከጎሬዋ ገብታ ተደበቀች 👇🏾 ማታ ላይ ወጥመዱ የተጠመደበት ቦታ ላይ ከፍተኛ ጩኸት ተሰማ የቤት እመቤቲቱ ወጥሙዱ ያዘልኝ ብላ ስትሄድ ለካንስ ወጥመዱ የአንድ መርዛማ እባብ ጭራ ይዟል: አላየችውምና በመርዙ ነደፋት ባልየውም አካባቢው ያለ ሀኪም ቤት ወስዶ አሳክሟት ሀኪሙ የዶሮ ሾርባ አዘዘላት ዶሮዋ ለሾርባ ታረደች ቤተ ዘመድ ሚስትየውን ሊጠይቅ ሲመጣ ለመስተንግዶ ፍየሏ ታረደች ሴትዮዋ አልሆነላትም: ሞተች ባልየው ቀብር ማስፈፀሚያ አልነበረውምና ላሚቷን ለቄራ ሸጣት 👇🏾 አይመለከተኝም አትበል !! @wegoch @wegoch @paappii By Zemelak endrias
Mostrar todo...
34👍 27😁 7👏 3
እማማ እንዴት እንደሞተች...! ... አባባ የስራ ሰው ነው። ሰፈር ውስጥ ስለሱ ሲያወሩ «ከስራው በቀር ምንም የማያውቅ ጨዋ» ይሉታል። እሱ ደግሞ አንድ ቀን እማማን አይን አይኗን እያየ «ትርንጎየ…እኔኮ ከስራዬ ቀጥሎ እወድሻለሁ» ብሎ ሲያስቃት ሰምቼዋለሁ። እሷ ትሳቅ እንጂ እኔ ግን የምሩን እንደሆነ አውቅ ነበር። ብዙ ጊዜ ቀን ቀን ሲሰራ ውሎ ማታ በጊዜ ነው የሚመጣው። የሆነ ወቅት ላይ ግን ይህ ልምዱ ተቀየረ። የተቀየረው ባንዴ አይደለም ፤ ሚስቱ ትርንጎዬ እና እኔ ልጁ ሳናውቅበት ቀስ በቀስ ነው። በመጀመርያ ሰሞን… ትንሽ አምሽቶ ነበር የሚመጣው። ያኔ እማማ እና እኔ እራታችንን ሳንበላ ቴሌቬዥን እያየን እንጠብቀዋለን። እሱ ካልመጣ አንበላም። እኔ በርግጥ ስለሚርበኝ እሱን የምጠብቅበት ትዕግስት አልነበረኝም። ግን እማማ እሱ ካልመጣ አትበላም። አንድ ጊዜ ለምን እንደሆነ ጠይቄያት «የነፍስ ጉዳይ ቢመጣ እንኳ ትቼው አልበላም» ነበር ያለችኝ። እኔ ደግሞ እሷ ካልበላች አልበላም። እጆቿን እንደገዛ መዳፌ ለምጃቸዋለሁ። ለስሙ እሰየማለሁ እንጂ በጉርሻዋ ነው የምጠግበው። ይህንን አኗኗር ከለመድነው በኋላ ከበፊቱ የበለጠ አምሽቶ መምጣት ጀመረ። የእራት ሰአት አልፎ እንኳ ቶሎ አይደርስም። አሁን እማማ የምትፈተንበት ሰአት ደረሰ። የእኔ ረሀብ እና በትዕግስት የሚያስጠብቃት የአባባ ፍቅር። ግን ለመምረጥ አላመነታችም። ለራሷ አንድ ለእኔ ሁለት እያጎረሰች እራት በላን። የዚያ ሰአት «የነፍስ ጉዳይ ቢመጣ እንኳ ትቼው አልበላም» ያለችውን አስቤ… እናቴ ለካ ቃሏ ከልብ አልነበረም ብዬ… ተገረምኩ። የነፍስ ጉዳይ ቀርቶ የእኔ መራብ ሲመጣ እንኳ ሳታቅማማ አባባን ትከዳዋለች። ከዚያ አባባ የበለጠ ማምሸት ጀመረ። ማታ ማታ በፍጹም አላየውም። ጠዋት ወይም ቀን ብቻ ነው የማገኘው። ማታ የት እንደሚሆን አላውቅም። «አባትህ ስራ በዝቶበታል እሺ?» ትለኛለች ። እሷ እንደዛ ስትለኝ እየዋሸች ይሆናል ብዬ አላምናትም።ምክንያቱም ሌሎችን ልትሸውድ ትችላለች እንጂ እኔ ግን አንዳንዴ እንደምትዋሽ አውቃለሁ። አባባን ጠይቄው አዎ ሲለኝ ግን በደንብ አምነዋለሁ። በቃ እሱ የስራ ሰው ነው እላለሁ። ታድያ የሆነ ሰአት ለመጀመርያ ጊዜ ሲጨቃጨቁ ሰማኋቸው። … በወቅቱ በጣም ልጅ ብሆንም የተነጋገሩትን ግን አሁንም ድረስ አስታውሳለሁ። «…ሰምቻለሁ! ያዩ ሰዎች ነግረውኛል!…እኔን ከዳሺኝ ትርንጎዬ…እኔን?» ... በጣም እየጮኸና በእልህ እየተንቀጠቀጠ «…ልጄን ይንሳኝ እልሀለሁ!…ውሸት ነው! የነገሩህ ሁሉ… ውሸት ነው!» ትንሽ ከተጨቃጨቁ በኋላ ወዲያው ተስማሙ። አባባ ይቅርታ ጠይቋት… እየተሳሳቁ አየኋቸው። ምስኪን አባት በእኔ ከማለች ያምናታል ማለት ነው። እኔ ግን በጣም ተጠራጠርኩ…ለምን? ምክንያቱም ማታ ማታ የሌላ ሰው ድምፅ መስማት ጀምሬ ነበር። አባባ በጣም አምሽቶ ምናልባትም ሌሊት ነው የሚመጣው። እሱ በሚመጣበት ሰአት ስለምተኛ ሲገባ አላየውም። ግን ምሽት ላይ … የሌላ ሰው ድምፅ እሰማለሁ። የመኝታ ክፍሌ ውስጥ ሁኜ <<ገጭ ጓጓጓ! ገጭ ጓጓጓ!>> የሚል የእግር ኮቴ እሰማለሁ። የአባባ ኮቴ እንደዛ አይደለም። አባባ ሲገባ ደረጃ የሚወጣበት ስልት የለመድኩት ዜማ አለው። <<ገጭ ገጭ ጓ>> የሚል። ይሄ ግን ሌላ ኮቴ ነው። ከኮቴው በኋላ የተኮላተፈ አንደበት ሰላምታ (ት…ል..ን..ጎ..የ.. የሚል)…ከዚያ ደግሞ የመሳሳም ድምፅ ይሰማኛል። ያ የሚመጣው ሰው አንዳንድ ጊዜ ያስለቅሳታል። አላውቅም ለምን እንደሚያስለቅሳት። ከዚያ በኋላ ግን እየሳቀች ስትስመው ድምፁ ይሰማኛል። እና ደግሞ…ሲጥ ሲጥ የሚል የአልጋ ድምጽ! እስከሆነ ጊዜ ድረስ ሰውየውን በመልክ አላውቀውም ነበር። ሰውየው ከመምጣቱ በፊት እማማ የመኝታ ክፍሌ ውስጥ ስለምትቆልፍብኝ አይቼው አላውቅም። ነገር ግን ኮልታፋ እና የመራመድ ችግር ያለበት ሰው እንደነበር እርግጠኛ ነበርኩ። የሆነ ቀን ይህንን ሰው መንገድ ላይ ፊት ለፊት አገኘሁት። ዘሪሁን ነው ስሙ…ሲናገር ኮልታፋ እና...እግሩ ደግሞ ችግር ያለበት ነው። አንዳንዴ እኛ ቤት ሲመጣ እማማ እንጀራ ትሰጠው ነበር። ፊት ለፊት ስንገጣጠም አገላብጦ ከሳመኝ በኋላ << ያቺ ደግ እናትህ ት..ል…ን..ጎ..የ.. ደና ናት?>> ብሎ ሲጠይቀኝ ከእቅፉ ወጥቼ ሮጥኩ። አባባ እንደዛ አይኮላተፍም። የአባባ ድምፅ እንደሰውየው አይሻክርም። አባባ አያነክስም። አባባ በየመንደሩ እየዞረ እንጀራ አይለምንም። ታድያ ለምንድን ነው የተሻለ ሰው እያላት ከዚህ ሰው ጋር የምትገናኘው? ሁሌም እገረም ነበር። ለአባባ ለመንገር ብዙ ጊዜ ሞክሬ ፈራሁ። አንድ ቀን ምሽት እራት ካበላችኝ በኋላ ክፍሌ ውስጥ ልትቆልፍብኝ ስትል «እንቢ»አልኳት። <<ምን ሆንክ?>> «የሚመጣውን ሰው ማየት እፈልጋለሁ!!» ደነገጠች። ሲሰርቅ እንደተያዘ ሌባ… በረት ውስጥ ገብቶ ባለቤቱ እንደመጣበት ወሮበላ ፣ ማንም አያውቅብኝም ያለው ሚስጥር እንደወጣበት ወራዳ ሰው!…ተንቀጠቀጠች። እኔም ድርቅ ብዬ ቆምኩ። ቁና ቁና እየተነፈሰች ካፈጠጠችብኝ በኋላ ማጅራቴን አንጠልጥላ ወደ ክፍሌ አስገባችኝ። ከዚያ ቆለፈችው። ከሶስት ቀን በኋላ ት/ቤት ልሄድ ስል አባባን በር ላይ ቁሞ ጢሙን እየከረከመ አገኘሁት። አይኖቹ ደም ለብሰዋል ፤ የስራ ልብሱን እንደለበሰ ነው። አቅፎ ከሳመኝ በኋላ « ምን ሁነህ ነው? » አለኝ። ትኩር ብዬ ተመለከትኩት። ጉዳዩን ከዚያ በላይ ሚስጥር አድርጎ መሸከም ከብዶኛል። መናገር ነበረብኝ። « አባባ…ማታ ማታ የሚመጣ ሰው አለ »አልኩት… ድንጋጤ ለቅጽበት ድርቅ አደረገው! «እርግጠኛ ነህ አይተኸዋል?» እየተንቀጠቀጠ «ፊቱን አላየሁትም…ሰውየው ሊመጣ ሲል…እማማ ትቆልፍብኛለች»አባቴ እጆቹ ተንቀጠቀጡ። በንዴት ጦፈ «…እሺ የሰማኸውን በሙሉ ንገረኝ..» ነገርኩት…ስለ እግሩ ኮቴ…ስለ..ኮልታፋነቱ….እንደሚያስለቅሳት…እንደምትስመው….ስለ አልጋው… ከዚያ በኋላ አባባ ብድግ ብሎ ያደርጋል ያላልኩትን ነገር አደረገ። ጓዳ ገብቶ…መሳቢያውን ከፈተ….ከዚያ ሽጉጡን አወጣ…ከዚያ…. ሁለት ጥይቶችን ተኮሰ…ሞተች!!!!! ዷ! ጠሽ! የሰፈሩ ሰው ግልብጥ ብሎ ወጣ…ጉድ! ጉድ!.ኡኡኡ! ብዙ ድምጾች!!..ቀስ በቀስ የማየው ሁሉ ብዥዥዥ እያለብኝ .መሬት ላይ ወደኩ። ፖሊስ አባባን ፍለጋ ብዙ ደከመ። እሱ ግን ዱካውን አጥፍቶ ተሰወረ። ከዘመዶቹ ፣ ከጓደኞቹ ቤት…ብዙ ቦታ ተፈለገ! የውሃ ሽታ ሁኖ ቀረ። እኔም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከአጎቴ ጋር መኖር ጀመርኩ። መጀመርያ ላይ አጎቴ ከራሱ ቤት ነበር የሚያኖረኝ። ትንሽ ቆይቶ ግን ከወላጆቼ ቤት እንድንኖር ይወተውተኝ ጀመር። በተደጋጋሚ አንቢታየን በለቅሶና በጩኸት ገለጥኩለት። እሱ ግን ከእኔ የስነልቦና ጉዳት ይልቅ የቤቱ ማማር ማርኮት አስገድዶ አመጣኝ። ህይወት የጊዜ ባቡር አይደለች? ጥቂት አመታት እንደቀልድ አለፉ... በየ ቀኑ እንቅልፍ እንደራቀኝ…ሌሊት ሌሊት እንደቃዠሁ ነበር። ብዙ ጊዜ የማስበው ደግሞ…ያ….ዘሪሁን የተባለን ሰው መበቀል ነበር። ህይወታችንን ያመሰቃቀለው እሱ ነው ! አንድ ግዜ በተኛሁበት ላብ ሰውነቴን አጥምቆኝ ከቅዠቴ ባተትኩ። አልጋዬ ላይ እንደሆንኩ የሆነ ድምጽ ሰማሁ። መጀመርያ አይምሮዬ የፈጠረው መስሎኝ ነበር። በኋላ ግን ድምጹ…ጎልቶ መሰማት ጀመረ። አዎ ያን ድምጽ አውቀዋለሁ…የሰውየው ኮቴ ነው
Mostrar todo...
👍 23😱 4 2😁 1
«ገጭ ጓጓጓ! ገጭ ጓጓጓ!»…..ኮቴው ጆሮዬ ላይ አስተጋባ። አጎቴ እንዳንቀላፋ ነው። ደግሞ ምን ቀርቶት መጣ ? እማማ እንደሆነች ሙታለች! ….በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሁኜ በሩን ከፈትኩ… በሩን ከፍቼ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም። አባባ ነው። እጁ ላይ ትልቅ የቢራ ጠርሙስ አለ…እግሮቹ ይወላገዳሉ…መቆም አልቻለም። እሱ ሲወላገድ ወለሉ«ገጭ ጓጓጓ! ገጭ ጓጓጓ!» የሚል ድምጽ ያሰማል «ት…ል…ጎ…ዬ» …ስካር ባኮላተፈው ድምጽ (A masterpiece by ናትናኤል ጌጡ💙) @wegoch @wegoch @paappii By mickel asmeraw
Mostrar todo...
😢 68😱 22👍 7 4👏 3👎 1
ፉንግግ ያለ ፉንጋ ነበር። የጥርሶቹ ትልቀት፣ የአፍንጫው አቀማመጥ፣ የፀጉሩ ግንባሩ ድረስ አመጣጥ፣ አጉጩን ሳይቀር አለማስተዋል አይቻልም ... ተፈጥሮ እንዴት እንደጨከነችበት ሳየው ይገርመኛል ተቀራረብን... ከፉንጋነቱ ጎን ለጎን ጥሩ ያስባል አዛኝ ልብ አለው። እይታው ጥሩ ነው ፣ ጭንቅላቱ ላይ ቀድሞ የተንሻፈፈ ነገር አይታየውም ፣ ፉንጋነቱ አይታወቀውም ፣ መልኩ ላይ እየቀለደ ፉንጋነቱን ኖርማል ለማድረግ አይሞክርም፣ የፊቱን አቀማመጥ እረስቶታል .... ብዙ መደዋወል ያዝን .....ይሰማኛል፣ ይጠይቃል አሰማሙ እና አጠያየቁ እሱ ኑሮ ያለው አይመስልም ፤ ገጠመኝ የሚያገኘው አይመስለኝም። በመስማት ብቻ ለካ መጉላት ይቻላል !! ከአልአዛር ጋር ተዋደድን ። አልአዛር ፉንጋነቱ ተረሳኝ ...አይደለም ውበቱ ታየኝ ። አልአዛር ቆንጆ ነው። አንድ ቀን ከፍቶኝ ቤቱ ሄድኩ አልጋው ላይ ተኛን አስተቃቀፉ አለሁልሽ አለው ። እንደ እህቱ እንደታናሹ አቀፈኝ ። ቀዝቀዝ ያለ ውሃ በማስታጠቢያ አምጥቶ ቀለል አድርጎ፣ ለግልግል እንዳላመች አድርጎ እግሬን አጠበኝ። እንደቀዝቃዛ ውሃ መንፈስ የሚያረጋጋ ነገር የለም እያለ በውሃ ዙርያ ትንታኔ አቀረበ ። ንግስት የመሆን ስሜት ይሰማኛል ከሱ ጋ ስሆን Safe Zone ነው ። አልአዛር ቆንጆ እንደሆነ የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ መሰለኝ ። እናቱ ሳይቀር መልኩ ላይ እንደሚቀልዱ በጨዋታ መሃል አንድ ሁለቴ ነግሮኛል ። መቼ ነው ፎንጋነቱ የተነነብኝ ? መቼ ነው ከበጣም ቆንጆ ልጅ በላይ የደመቀብኝ?? መቼ ነው የቆነጀብኝ ?? አላውቅም ግን አላዛር ቆንጆ ነው !! አልአዛር ጋር ሳንገናኝ ወይ ሳንደዋወል አንውልም ። ገጠር ሄጄ ስመለስ ከድፍን ከተማው አልአዛር ብቻ ነው የሚናፍቀኝ ። ከአልአዛር ጋር ብሄድ ምን ምክንያት አለ ተመለሺ ተመለሺ የሚለኝ ?? አልአዛር ጋ አብሬው ተኝቼ ለሊት ላይ የተገለጠ ገላዬን ያለብሰኛል። ለጥቃቅኑ ስሜቴ ቦታ ይሰጣል ። አብረን እቤቱ ስናድር በጠዋት ተነስቶ የሆነ ነገር ገዝቶ ስነሳ የምንሰራው ወይ የምንበላው ያመጣል ...ለምዶኝ ችላ አላለኝም። ምቾት ተሰማኝ ፤ ማንም አይቀማኝም ብዬ መሰለኝ ፣ ጨዋ ነው ብዬ መሰለኝ፣ የሚሰማኝ፣ የሚያግዘኝ ስላገኘሁ ነው መሰለኝ እለት እለት ፍቅሬ ጠነከረ ። ድንገት የሆነ ቀን "እንለያይ" አለኝ ....ሳኩኝ። በርግጥ አንድ ሁለት ሳምንት ሙሉ ደብዝዞ ነበር ፣ እየራቀኝም ነበር። እኔ ከራሱ ጋር የተጣላ ነበር የመሰለኝ ። ላለማስጨነቅ ነበር ምን ሆንክ ላለማለት የሞከርኩት እሱ ፀቡ ከኔ ጋ ነበር መሰለኝ ... ቀለል አድርጎ ነበር እንለያይ ያለኝ ።እኔ እና እሱ መሃል ጭቅጭቅ፣ መዋደድ ፣ መሳቅ እንጂ የመለያየት ፅንሰ ሃሳብ እንዳለ አላውቅም ነበር ። "እንለያይ" አለኝ ..... "እየቀለድክ ነው አልአዛር ?" "እውነቴን ነው ሶሲ " የሆነ መፍራት ነገር ወረረኝ ። "ባይሆን አሪፍ ጓደኛ እንሆናለን እንደ ድሮ አለ ።" የማደርገው ስላጣሁ ዝም አልኩ: እምባዬ ግን ፈሰሰ። " ምን አደረኩ? ፣ ምን አደረገች ብለው ነግረውህ ነው? ፣ ምን ያልኩት ነገር ልብህ ውስጥ ሃዘን ፈጥሮ ነው? " "ተይ አታወሳስቢው ሶሲ ተይ you are one of the strongest women I know ጓደኝነታችን አይቆምም እኔ ሪሌሽንሺፕ ይሰለቸኛል።" እንዴ?! እንዴ ?! አላዛር አልመስል አለኝ ጥሩ ልብ መኖሩ ፣ አዛኝነቱ ፣ አይነግቡ አለመሆኑ መውደዴ .....የቱም እንዳይተወኝ ዋስትና አልሆነኝም ። ያስደነገጠኝ ፊቱ ላይ ያስነበበኝ የበቅቶኛል ሁኔታው ነው ። ደነገጥኩ !! ኖ ፈራው. ኖ አዘንኩ መጠን አልባ ሃዘን ልቤ ውስጥ ተንከላወሰ። መለመን ፈልጌ ነበር ፣ የሆነውን ማወቅ ፈልጌ ነበር ፣ተረጋግቼ ላናግረው ፈልጌ ነበር፣ ሲያቅተኝ ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ላይ አጎንብሼ አለቀስኩ ሰዎች ትኩረታቸው ወደ እኛ ሲሆን መሰለኝ ፦ "ኧረ አንቺ ልጅ This is totally attention-grabbering አረጋጊው ! ሁኔታው ንግግሩ ከእንለያዩ የበለጠ ጎዳኝ ።ቀጥ ብዬ እያለቀስኩ ከፊቱ ከካፌው ከኑሮው ሄድኩኝ አልተከተለኝም ..... በነጋታው ይመስለኛል ከእንቅልፌ ስነቃ ተስፋ ሙቁረጥ መላ አካላቴ ላይ ተጥለቅልቋል ። መነሳት አልቻልኩም ሁኔታው፣ አወራሩ፣ አኳኋኑ ፣ ልቤ ላይ መከዳት ተንጋለለብኝ ። የአልፈልግሽም ውሳኔው ፣ ለሱ የነበረኝ ቦታ ፣ ክህደቱ በደም ዝውውሬ ተሰራጭተው ስነቃ አላላውስ ብሎኝ ነበር ። ለሦስት ወር ከሃያ ቀን በራችን ጋ ካለው ሱቅ በቀር የትም አልሄድኩም። ስልኬን ዘጋሁት ፣ ተብሰለሰልኩ፣ ተምሰለሰልኩ ፣ ሙዚቃ አልሰማሁም፣ ፊልም አላየሁም፣ ከወዳጆቼ ጋር አልተገናኘሁም ፣ ስለገንዘብ አላሰብኩም ፣ ሁሉን እርግፍ አድርጌ ተውኩት ። ከአልጋዬ አልተላቀኩም ፣ ከተከረቸምኩበት ስወጣ ከብዙ ግዜ በኃላ መስታወት አየሁ ሽበት ጣል ጣል ብሎብኝ ነበር ፣ ገርጥቼ ነበር፣ ብዙ ግዜ ጨለማ ክፍል ውስጥ የነበርኩ እመስል ነበር ። የሆነ ቀን፤ ከሆነ ግዜ በኋላ ለፆታዊ ግንኙነት ያለኝ ቦታ ቀዝቅዟል። በወሬ መሃል ሳይታወቀኝ ከልቤ ግድ ነው እንዴ መጥበስ ? ግድ ነው እንዴ ፆታዊ ግንኙነት ፣ማግባት ግድ ነው ? የሰው ልጅን የተባለ ፍጡርን አምኖ ነገን በጋራ አብሮ ማለም መራመድ ይቻላል? ? ምንስ ፉንጋ ቢሆን ምንስ አዛኝ ቢሆን ምንስ አሳቢ ቢሆን ምንስ ቆንጆ ቢሆን የሆነ ቀን ቢከዳንስ ዋስትናችን ምንድን ነው ?? እያልኩ ለነገ ዋስትና የሚሰጠኝ ፍለጋ ስሞግት ድምፄን ሰማሁት ከጉዳቴ ያገገምኩ መስሎኝ ነበር ! ቁስሌ አልደረቀም ማለት ነው ? መዳን ስንት እድሜዬን ይበላ ይሆን ?? By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😢 51👍 36 16
[ የዘገያችሁ ከመሰላችሁ .... ገና ናችሁ] አንዳንድ ሰው በ24 አመቱ ተመርቆ ስራ ለማግኘት 6 አመት ሊፈጅበት ይችላል አንዳንዱ በ24 አመቱ የድርጅት ስራ አስኪያጅ ሆኖ በ30 አመቱ ሊሞት ይችላል ሌላው ስራ አስኪያጅ ለመሆን የ26 አመት ልምድ አስፈልጎት 80 አመቱ ኖሮ ይሆናል አንዳንዱ በ49 አመቱ ገና ላጤ ሆኖ ህይወቱን ለመቀየር ሲታገል የትምህርት ቤት ጓደኛው የልጅ ልጅ አይቶ አያት ለመሆን በቅቶ ይሆናል ኦባማ በ55 አመቱ ጡረታ ሲወጣ ትራምፕ በ70 ባይደን በ77 አመታቸው ነው ፕሬዝዳንት የሆኑት በዚህች ምድር ላይ ሁሉም የራሱ ጊዜ አለው ሰዎች የቀደሙህ ወይም አንተ የዘገየህ ሊመስልህ ይችላል። አንተ ወደፊት ገስግሰህ ሌላው ወደኋላ የቀረ መስሎ ሊታይህም ይችላል። እውነታው ግን ሁሉም ሰው በራሱ ጊዜ፣ በራሱ ፍጥነት እየሮጠ ነው። አንተም በራስህ እነሱም በራሳቸው ጊዜ ከተፃፈላቸው ቦታ አይቀሩም። ልጅ ለመውለድ፤ ገንዘብ ለመያዝ፤ ትዳር ለመመስረት፤ አገራችሁ ለመግባት፤ ተምሮ ለመመረቅ፤ ለመዝናናት ...... የዘገየህ ለመሰለህ .... አልዘገየህም፤ ከማንም አትቀድምም፤ በራስህ ጊዜ ላይ ነህ !! By Abby abby @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
👍 55 34🔥 4
ከተለቀቀ ቡኃላ በሁላችንም ዘንድ እጅግ የተወደደው አልበም ሊያልቅ አንድ ዘፈን ቀርቶታል። ሙዚቀኛው "የመጨረሻዋን ዘፈን ነፍሷን አላገኘሁትም" በሚል ጭንቀት ከተወጠረ ወራት ተቆጥረዋል። ድምፃዊው ጥበቃው ደክሞት ዘፈኖቹን ከስቱዲዮ አስዘርፎ ስለሚያወጣበት መንገድ እያሰበ ነው። "የቀረው ግጥሙ ብቻ ነው አይደል? እሱን ደግሞ በአምስት ደቂቃ መጨረስ እንደምትችል በተደጋጋሚ አይተናል። ችግሩ ምንድን ነው?" አለ እየተማረረ። (ድካም ተሰማው ሙዚቀኛው) "እውነቱን ልንገርህ? ... እኔ አንተ እንደምታስበው አይነት እውነተኛ አርቲስት አይደለሁም።" አለ በተሸነፈ ድምፅ። "እንዴ? እና ታዲያ ምን ልትባል ነው?" "....እኔ አርቲስት ሳልሆን ሙዚቃ በመስራት የሚያገግም በሽተኛ ነኝ።" "አልገባኝም!" "ማለቴማ...የሆነ ህመም ሲያንሳፍፈኝ እንጂ እንደ'ናንተ በፈለግኩት ሰዓት ተነስቼ መብረር የምችልበት ክንፍ አልታደልኩም። እኔን አርቲስት ማለት እፉዬ ገላን 'በራሪ ፍጡር ነች' እንደማለት ነው።" "እስኪ ተው በናትህ!...አንተ አርቲስት ካልተባልክማ እኛ ስቱዲዮ ድርሽ ማለት የለብንም።" "አያይ...እናንተማ ባሻችሁ ሰዓት ድምፃችሁን ማዘዝ ትችላላችሁ። አዬህ? ክንፉ ተሰጥቷችኋል። ትክክለኛ ስታሮች እናንተ ናችሁ።" "ትሰማኛለህ?!...እኛ ኮከብ ከተባልን አንተ ፀሀይ ነህ። ምክኒያቱም የምናፀባርቀው ያንተን ብርሀን ነው። ይሔንን መቼም እንዳትረሳ።" (ሁኔታው ስላስፈራው በራስ መተማመኑን ሊመልስለት ታገለ።) "ፀሀይ?!.." ፂም አልባ ፊቱን እየደባበሰ "...ታውቃለሀ እሷንም እኮ ከርቀት ስለምናያት ነው እንጂ የምታበራ የሚመስለን ጠጋ ብለን ስናያት እየነደደች ነው። The sun is actually burning. ...እንደምትለው 'ፀሀይ' ከሆንኩ እንኳን... ወይ ነድጄ አልቄያለሁ። ወይ ደግሞ የሚለኩሰኝ አጋጣሚ አጥቻለሁ።" "እንዲህ እንደዋዛ የምትነግረኝን ወሬዎች ቤት እንዲመቱ ብታደርጋቸው እኮ ጨርሰናል ወንድሜ።" "ግጥሙ በውስጡ አምቆ የሚይዘውን ታሪክ ሳናገኝ? በድኑን ብቻ ልናውጣው? ያለ ነፍሱ? ተው እንጂ!!..ስንቴ ነው የምነግርህ እንደዚህ እንደማይሆን?!" "ምናለበት አንዳንዴ እንኳን ቀለል ብትል አንተዬስ?! ሁሉንም ነገር ካላመናፈስክ ደስ አይልህም እንዴ?!..." ሊስቅ ብሎ ፊቱ መቀያዬሩን ሲያይ ደንግጦ ዝም አለ። (ሙዚቀኛው እንዳኮረፈ ስቱዲዮውን ጥሎለት ወጣ።) ዘፋኞቹ ሁላ ወሬ አስጀምረውት ጠለቅ እያለ ሲሔድባቸው ጨዋታውን ወደ ሹፈት የሚቀይሩበት ነገር ሊለመደው ያልቻለ የጋራ አመላቸው ነው። "..'በልተህ ላትበላ አታስፈትፍተኝ፤ ጠተህ ላትጠጣ ጋን አታስከፍተኝ' የሚለው እኮ ወዶ አይደለም አያ ሙሌ።" እያለ ብቻውን እያነበነበ ወጣ። ሰዎች እንዳይለዩት አፉን በስካርፍ...አናቱን ደግሞ በኮፍያ ከልሏል። በአይኖቹ አካሔዱን የሚኮርጀውን ጉብል፤ ፈገግታዋን የሚዋሳትን ሴት ያማትራል። "በህይወት ካሉ ሰዎች ላይ ብቻ ነው ታሪኬን የምወስደው እንጂ ፈጥሬ አልፅፍም!" የሚል ፍልስፍና አለው። ለዚህም ነው ደራሲ ሲሉት "ደራሲ አትበሉኝ...የአምላክ ጋዜጠኛ ነኝ!" እያለ የሚሟገተው። (ሀይማኖተኛ ነኝ ቢልም ፍልስፍናው ሳይበዛ አይቀርም።) ጎዳናው ላይ እየኳተነ መሸበት። ቢጨንቀው ከአመታት ቡኃላ ግሮሰሪ ገብቶ ተቀመጠ። ሲገባ በተስፋ መቁረጥ እንጂ "ፍለጋዬ የሚቋጭበት ቀን ይሆናል!" በሚል ጥርጣሬ አልነበረም። ከተቀመጠበት ጠረጴዛ ላይ ብዙም ሳይቆይ ሁለት ጠብደል ጎረምሶች ሳያስፈቅዱት ተቀመጡ። ውሀውን ጨበጥ እያደረገ በሰቀቀን አያቸው። አንደኛው ሁኔታውን አይቶ..."ከደበረህ መነሳት ትችላለህ!..ይሔ የኛ ቦታ ነው።" አለው። "ኧረ...ኧረ ችግር የለውም። እንዲያውም ልሔድ ስል ነው የመጣችሁት።" አለና ሒሳቡን ለመክፈል አስተናጋጁን በእጁ ጠራው። ወዲያው ሶስተኛ ሰው ወደነሱ ጠረጴዛ መጥቶ እየተቀላቀላቸው..."አንድ ጮማ ወሬ ብነግራችሁ ድራፍት ትጋብዙኛላችሁ?" አለ። "እንደ ወሬው ጮማነት ይወሰናል!" አሉት። "በሱ ምንም ጥርጥር አይግባችሁ።" "እሺ ቀጥል!" ሙዚቀኛው ለአስተናጋጁ ሂሳብ መክፈሉን ትቶ ለራሱም ቢራ እያዘዘ ጆሮውን ቀሰረ። "እሺ..." አለና ወንበር ስቦ ድራፍት ካዘዘ ቡኃላ ግማሽ አድርሶ እስኪያስቀምጠው ድረስ "ቆዩ" እያለ ትግስታቸውን ተፈታተነው። ሙሉ ትኩረታቸውን ማግኘቱን ሲያውቅ...."ትላንትና ማታ ሌላ ሰፈር ሂጄ እየተዝናናሁ ነበር።" ብሎ ወሬውን ጀመረ።..."ከዛ ማንን ባገኝ ጥሩ ነው?" "ማንን አገኘህ?" "የቢኒን ሚስት ማሒን!" "እንዴ? ምን እየሰራች?" (ሌላኛው) ዘና ብሎ ወደኋላ እየተደገፈ..."ቂጧን አስጥታ እ የ ሸ ረ ሞ ጠ ች ነዋ!" ባለማመን አዩት። ስልኩን አውጥቶ ፎቶ እያሳያቸው ሌላ ድራፍት አዘዘ። ሙዚቀኛው ሰረቅ አድርጎ ሊያይ ቢሞክርም አልመቸው አለ። ጠብደሎቹ ፎቶውን በግርምት እያዩ .. "ጭራሽ ተኝተሀታል?...የፈጣሪ ያለህ!" (ፎቶው ከጠረጴዛ ጠረጴዛ መዟዟር ጀመረ። ግሮሰሪዋ ባንድ እግሯ ቆመች።) ድንገት አንድ ሰው እየገነፈለ ወደ ውስጥ ከገባ ቡኃላ ወሬኛውን ልጅ ተንደርድሮ በቦክስ ነረተውና ወለሉ ላይ ዘረረው። ሁሉም ፀጥ ብሎ ሲያይ ሙዚቀኛው ሩጦ ገብቶ መገላገል ጀመረ። ሌሎቹም ከድንጋጤያቸው ነቅተው መሀላቸው ገቡ። የወደቀውን ልጅ አፋፍሰው ወደ ጓዳ ወሰዱት። የሚገለገለው ልጅ መንጭቆ ወደ ገላጋዩ ሲዞር...ያዬውን ሰው ማመን አቅቶት...."እንዴ ኤላ? እዚህ ምን ትሰራለህ?" አለ ግራ ተጋብቶ። ሲያገላግል ስካርፍ እና ኮፍያው መውደቁ ታውቆት ፀጉሩን እያከከ ዝም አለ ሙዚቀኛው። "የምትተዋወቁ ከሆነ አንተ እሱን ይዘህልን ውጣ ወንድሜ!" አለው አንደኛው ወደ'ሱ እየመጣ። ተያይዘው ወጡ። ወጣቱ ከግሮሰሪው ከወጡ ቡኃላም በግርምት ማዬቱን አላቆመም። ጠቁሮበታል። ተጎሳቁሎበታል። ግን ሊጠይቀውም አልፈለገም። እንዳይሰማው ብሎ ... "ያው ብዙዎቻችን ከካሜራ ጀርባ ያሉ አርቲስቶችን በመልክ ስለማናውቅ ነው እንጂ ስምህን ብነግራቸው ሁሉም ያውቁህ ነበር!" አለ። "ይገባኛል።" አለ ሙዚቀኛው እንዴት ወሬውን እንደሚያስጀምረው እያውጠነጠነ። ትንሽ ዝም ዝም ተባብለው ቆዩ። ልጁ አሁንም እጁን እያፍተለተለ "ባይዘዌ ሚስቴ ሴተኛ አዳሪ አይደለችም።" አለ። "ኧረ? አይ ጥሩ...ጥሩ ነው።" አለ በሀፍረት አቀርቅሮ። "የምሬን ነው!..መንታ እህቷ ነች ያን ስራ የምትሰራው። ውሀ እና ፀበል ናቸው። መልካቸው እንጂ ውስጣቸው አይገናኝም። ወይም ጨረቃ እና ፀሀይ በላቸው። ቅርፃቸው እንጂ ብርሀናቸው አይመሳሰልም።" እጁን በእልህ ጨበጥ ዘርጋ እያደረገ..! "እና ውሸት ከሆነ ምን ስሜታዊ አደረገህ? ማስረዳት አይቀልም ነበር?" "ልክ ነህ እሱማ ግን....ባልዋለችበት ስሟ ሲነሳ...ባልሰራችው ወንጀል እየተቀጣች ሳይ በጣም ከፋኝ። ትዕግሥት አጣሁ እውነት!! መጀመሪያ ላቅምሰው አልኩ።" ሳቀ! ሙዚቀኛው ከረጅም ጊዜ ቡኃላ እፉዬ ገላ ነፍሱ ከያዛት አጥር ተላቅቃ በህይወት ንፋስ ወደላይ ስትንሳፈፍ ተሰማው። እሱም ፈግግ አለ። የዛኑ ምሽት ስቱዲዮ ገብቶ የመጨረሻዋን ዘፈን በግጥም ሞልቷት አደረ። ድምፃዊው ሲያዬው "እንኳን ጠበቅኩህ!" እያለ በደስታ አቀነቀነው። እንዲህ እያለ... "ግልፅ እውነትሽ መች ጠፋኝ? ባላዩት እንጂ ባሙሽ የከፋኝ! "ሌትም ወ'ታለች አሉ አንቺን በማታ...ጨረቃ እያዩ!.. "ስትመጭ አይን ያያል...መውጣትሽን ጧት ሲነጋ..ሲመሽ መግባትሽን የሞቀው ወርቃማ ብርሀንሽን ጨፍኖስ ማን ያጣል ተፈጥሮሽን? (×2)..
Mostrar todo...
👍 20 4🔥 1
"አውቃለሁ አንቺ አይደለሽም! ... አንቺ ቀን ነሽ በቃ 'እሷው ነች አታርፍም' ቢሉም...ቢያሙሽም በጨረቃ እያዬው ሳይመሽ በጊዜ ... ቀን ተግተሽ ስትሰሪ ማታ ግን ተራሽ አይደለም...ምን በወጣሽ ልትበሪ?!.. "ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ ጀንበርዬ..." ፧ (፨ የግርጌ ማስታወሻ:- ይሕ "እንዲህ ቢሆንስ?" በሚል ስራ ፈትነት የተፃፈ ልብወለድ ብቻ ነው) @wegoch @wegoch @paappii By mickel Azmeraw
Mostrar todo...
20👍 10🔥 3👏 2
[ በመጀመሪያው መንገድ የሚተውሽ ሰው ደስታሽን ይሰርቅሻል ] የፍቅር ግንኙነት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በተመሳሳይ ግለት እና ስሜት አይዘልቅም። የትኛውም ፍቅር የራሱ ኡደት አለው። የፍቅርን ተአምር ለማየት ጊዜ ያስፈልግሻል። ፍቅር ጥንካሬን ብቻ ሳይሆን ብልሀትን ይፈልጋል። የተሳካ የፍቅር ጉዞ ተለዋዋጭ ነገሮችን ተቀብሎ እራስን እያስተካከሉ መሄድን ይፈልጋል። ፍቅርን ስንጀምር እጃችን ውስጥ የገባውን ውድ ሀብት እናስተውለውም። ለራሳችን የምንሰጠው ግምት ነገሩን ቀለል አድርገን አይተን ለጨዋታ አይነት በሚመስል መንገድ እንድንጀምር ያደርገናል። እንደቀልድ የፅሁፍ መልዕክቶችን ከመለዋወጥ ወደ ስልክ ማውራት፤ ለደቂቃዎች ከማውራት አብሮ ሲያወሩ ሌሊቱን ወደ ማንጋት ይሸጋገራል። በቃ ሁሉም ነገር ደስታ እና ፈንጠዝያ ብቻ ይሆናል። በአጋጣሚ ትንንሽ አለመግባባቶች ከተፈጠሩ ግብረ መልሶቻችን ከልክ በላይ ይሆናሉ። ተስፋ እና ፍርሀትን ጎን ለጎን ይዘሽ ለመሄድ ትሞክሪያለሽ። ሁሌም አሁን ያለው ወንድ ከበፊቶቹ የተሻለ እንደሆነ ታስቢያለሽ። ከጥሩ ጥሩው ነገር በዛ ያለውን፤ ከመጥፎ ከመጥፎው ደግሞ አነስ ያለ (አንዳንድ ጊዜ ጭራሽ ድክመት የሌለው) ነገሮችን የያዘ ወንድ እንዳገኘሽ ይሰማሻል። ችግሩ አብሮሽ ያለው ወንድ "የገባው" ካልሆነ ሊጫንሽ ይሞክራል። አንቺ ደግሞ ነፃነትሽ አሳልፈሽ መስጠት አትፈልጊም። ይህ ነገር ሲደጋገም አንቺ ፈላጊ እሱ ተፈላጊ አይነት ስሜትም ሊሰማሽ ይችላል። ይሄንን ፍቅር ለማስቀጠል ፍርሀትሽን ተቋቁመሽ ሊመጡ የሚችሉትን ያልተገመቱ ነገሮች እየፈታሽ፤ ራስሽን ገዝተሽ ለመኖር ትገደጃለሽ። ይሄ ግንኙነት ወደ ፍቅር ካደገ ለሰዎች ድብቅ የነበሩ ማንነቶችሽን ለዛ ወንድ ቀስ በቀስ መግለጥ እና ማሳየት ይመጣል። እነዚህን ነገሮች አብሮሽ ያለው ወንድ ለማሸነፊያነት ሊጠቀምባቸው ሲሞክር ይሄንን ተከትሎ ጭንቀት፣ ውጥረት እና አለመረጋጋት ሊሰማሽ ይችላል። በስሜትሽ ለራስሽ "ትልቅ" ነኝ ብለሽ ስታስቢ የኖርሽውን ሴት በአንዴ እንደ ህፃን የሆንሽ መስሎ ይታይሻል። እዚህ ጋር ነው አዲሱ ፍቅር ጉልበትሽን እየጨረሰው፣ ትኩረትሽን እየሰረቀሽ፣ አንድ ሰውን ከማሰብ በስተቀር ሌላ ነገር ለማድረግ አቅም እንዳሳጣሽ፣ ጨቅጫቃ እና ነዝናዛ የሆንሽ የሚመስልሽ፣ በግንኙነቱ ቀጣይነት ላይ ፍራቻ የሚሰማሽ ከሆነ፣ ከእነ አካቴው ረስተሽው የነበረው የቀደመ የፍቅር ህይወትሽን አፈፃፀም እየደጋገምሽ ማሰብ ከጀመርሽ ህልምሽ እንጂ ፍቅርሽ ሩቅ ተጓዥ አይደለም። ለዚህ ሁኔታ አብቅቶሽ ጥሎሽ የሚሄድ ወንድ ፍቅርን እንድትሸሺ ባያደርግ እንኳን ደስታሽን ይነጥቅሻል ! by Abby @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
29👍 21🔥 3👏 1
text ገባልኝ : "ግሩሜ ቸገረኝ ብር ላክልኝ " "ስንት ብር ልላክልሽ?" "አምስት ሺህ ብር አካውንት ቁጥር 100056.... " ቴክስቱን ሚስቴ አየቺው። 'ምን ማለት ነው ?! ፣ እ? ፣ ያልጨረሳችሁት ነገር አለ?!፣ በየግዜው ትገናኛላችሁ ማለት ነው ? ...." ብዙ ብላ በመጨረሻ "እንዳትሞክረው!" አለችኝ። ዝም አልኳት : የመስማማት አይነት ዝምታ ። እንደ ነጋ ባንክ ሄጄ አርባ ሺ ብር አስገባሁላት ! ሜሪ ላሁኑ ባሏ 'Achievement' ጥንካሬ ሰሊና ድርሻ ምን ያህል እንደነበር ብነግራት በሌላ ቀን ፣ በሌላ መንገድ ጭቅጭቅ ሆኖ ይመጣል ብዬ ነው ልቤ ውስጥ የቀበርኩት ! ። ሰሊና እንዴት አይነት ደግ ፣ መለመን የማትችል ፣ ለገንዘብ ግድ የሌላት ፍጡር እንደሆነች፣ ይሄን ቴክስት ለመፃፍ ስንት ቀን እንደፈጀባት ፣ የላከችውን አሃዝ ለመፃፍ ስንቴ አሰላስላ እንደፃፈች እኔ ነኝ የማውቀው ። እኔ አሁን የሆንኩትን እንድሆን የሆነችው መሆን ፣ የምወድቅ ሲመስላት ስንቴ እንደተጨቃጨቀች፣ እኔን ለማበርታት የሄደችው ርቀት፣ ሳገኝ በደስታ ፊቷ ላይ የሚነበበውን እልልታ ፤ማንም አያውቀውም ከኔ በቀር !። ቸገረኝ ብላ ስትፅፍ እያለቀሰች እንደሆነ አውቃለሁ ፣ ስንት ብር ስላት እየተሳቀቀች እንደሆነ የፃፈችው ... ከስሜ በላይ እርግጠኛ ነኝ ። የልብ እውነት ይኖራል እንጂ አይብራራም !! By Adhanom Mitiku @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
95👍 33🔥 6🥰 6👏 3😢 2
የሆነ ጊዜ አንድ ፍሬንዴ የሆነ ልጅ ትጠብስና ቤቱ ይወስዳታል:: ቁልፍ ይሰጣታል:: እንደቤትሽ እይው ብሎ:: ከዛ ዶሮ አሮስቶ እንደሚወድ ነግሯት ስለነበር ብትሰራልኝ ብሎ ከሱፐር ማርኬት ያለቀላት ዶሮ አምጥቶ ፍሪጅ ውስጥ አስቀመጠ:: ልጅት ቤቱ በሄደች ቁጥር ዶሮዋን ታያታለች: ፍሪጁን ልታፀዳ ታወጣትና : መልሳ ታስገባታለች:: ከሆነ ጊዜ በኃላ ልብ ስትል ዶሮዋ የለችም:: "ቤብ ዶሮዋስ?" አለችው:: እሱ:- "ውይ ሳልነግርሽ ተነሳች እኮ::"😂 ከዛ ብዙም አልቆዩ ተለያዩ:: @wegoch @wegoch @paappii By Mahi
Mostrar todo...
😁 38👎 8👍 5
' ለመሸወድ ከተዘጋጀህ ሁሉም እንዳቅሙ ሊያታልልህ ይጣጣራል ። '                                      ( ካሊድ አቅሉ) ቤት ውስጥ አንዱን ጥግ ይዤ መፅሀፍ አነባለው ፣ ታላቅ እህቴ የሁለት አመት ልጅዋን እላይዋ ላይ አስቀምጣ ትመግባታለች ። ልጅትዋ እሺታን አታሳይም ምግብ ወደ አፍዋ ሲጠጋ ጥርሶችዋን ትገጥማለች ። የእናትዋን የበዛ ቁጥ ስታይ በየመሀሉ ፈገግ እያለች አፍዋን ትከፍታለች አየሀት ካሉ ልትሸውደኝ ስትሞክር አለችኝ  እኔም ስመለከታት ደገመችው አብረን ተሳሳቅን ወድያው አንድ ሀሳብ አይሞሮዬ ላይ ብልጭ አለብኝ እንዲህ የሚል .... ለመሸወድ ከተዘጋጀህ ሁሉም እንዳቅሙ ሊያታልልህ ይጣጣራል ፤ የራሱን ምቾት ለመጠበቅ ያንተን ፍላጎት በሳቅ ቃሬዛው ከፍኖ አርቆ ይቀብረዋል ። "አልሸወድም" ማለት በራሰ መሸወድ ቢሆንም የቅንነት መንገዳችንን ሊሸራርፉ የሚፍጨረጨሩ የመንገዳችን ተጓዦች መስመጫቸውን እያመቻቹ እንደሆነ ማስገንዘብ ያሻናል ። by @kalidakelu @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
👍 25 9
ጃፓን ውስጥ አንድ ሬስቶራንት አለ ። እና የምግቡን ዝርዝር ወደኛ ቀይረን እንቀጥል ..... በመጀመሪያ ቀን በዚህ ሬስቶራንት የተጠቀመ ሰው ሲናገር ፡ ወደ ምግብ ቤቱ ገብቶ አረፍ እንዳለ ፡ አንድ በእድሜ የገፉ አስተናጋጅ ተቀበሉት ። ምን ልታዘዝ " ምሳ ምን አላችሁ ? " ትልቋ አስተናጋጅ ለሰውየው የሚፈልገውን ምግብ እንዲያዝ ሜኒውን ሰጡት አተኩሮ ካየ በኋላ ፡ ... "እሽ አንድ ጥብስና ፡ የሚጠጣ ደግሞ አምቦውሀ ያምጡልኝ " .... አስተናጋጇ ትእዛዙን ተቀብለው ሄዱና ፡ ትንሽ ቆይተው ተመለሱ ። ምግቡን ያዘዘው ሰው ፡ ባዶ እጃቸውን የመጡትን አስተናጋጅ እያየ ፡.... " ምነው አልደረሰም ? " ብሎ ጠየቀ . ኸረ ደርሷል ይኸው ይዤ መጥቻለሁ አሉና የሂሳብ መጠየቂያ ቢሉን አቀበሉት ። " ምንድነው ይሄ ፡ ከምግቡ በፊት ነው እንዴ ሂሳብ ? " አስተናጋጇ ፈገግ እያሉ .... ኸረ በፍፁም ፡ አሁን የበላኸው ቅቅልና የለስላሳ መጠጡ ሂሳብ ነው " እንዴ እኔ ያዘዝኩት ጥብስና አምቦውሀ ነው ፡ እሱም አልመጣልኝምኮ " የዚህ ጊዜ ትልቋ አስተናጋጅ ስህተት እንደሰሩ ገባቸውና ፡ ይቅርታ ለካ ያንተ አይደለም ብለው ቢሉን ከሱ አጠገብ ላሉ ተስተናጋጆች ሰጧቸውና ያንተን አሁን ይዤ እመጣለሁ ብለውት እየተቻኮሉ ወደ ኪችን ተመለሱ ። ..... እና ብዙም ሳይቆዩ በእጃቸው ምግብ የያዘ ሰሀን ይዘው መጡና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጠው ፡ ቆይ የሚጠጣውን ይዤልህ ልምጣ ብለው ሄዱ ። ...... ሰውየው የመጣለትን ምግብ አየው ። በቅቤ ያበደ የቋንጣ ፍርፍር ነበር ፡ አሁን ተናደደ እሱ ያዘዘው ጥብስና አምቦውሀ ነው ። በዚህ መሀል እያለ አስተናጋጇ የቀዘቀዘ ቢራ ይዘው ተመለሱና እየከፈቱ መልካም ምግብ ብለውት ሊመለሱ ሲሉ ፡ ጠራቸው ። " እየውሎት እኔኮ ያዘዝኩት " .....ብሎ እየተናገረ እያለ ፡ አለመግባባት መኖሩን ያስተዋለው የሬስቶራንቱ ሃላፊ መጣና ቀረብ ብሎ የሆነ ነገር ነገረው ። ሰውየው ልክ ይህን እንደሰማ መከፋቱን ትቶ እየሳቀ ምግቡን ተመገበ ። ........ በቃ እዚህ ቤት እንዲህ ነው ። የዚህ ቤት ደንበኞች በብዛት ስለቤቱ የሚያውቁና ፡ ዝናውን ሰምተው የሚመጡ ሰወች ናቸው ። እና ምሳህን ቁርጥ ልትበላ ገብተህ ፡ ዱለት ሊቀርብልህ ይችላል ። የመጣልህን መመገብ ነው ። ብዙ ሰወች ፡ ክትፎ አዘው ፡ ተጋቢኖ መጥቶላቸው ያውቃል ። እየሳቅህ በልተህ ትወጣለህ ። ...... ይህ ምግብ ቤት የተሳሳቱ ትእዛዞች ምግብ ቤት ( Restaurant of Mistaken Orders ) በመባል ይታወቃል ። የዚህ ምግብ ቤት አስተናጋጆች ፡ Dementia በሚባል ፡ መርሳትን በሚያስከትል በሽታ የተያዙ ሰወች ናቸው ። የምግብ ቤቱ ባለቤት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰወች የሚደርስባቸውን መገለልና ጭንቀት ለማስወገድ ሲል የከፈተው ነበር ። ..... አላማውም ሰወች እነዚህን ወገኖች ከማግለል ይልቅ ፍቅር እየሰጧቸው የሳቅና የደስታ ምንጭ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው ። ....... እና በዚህ ቤት ስትመገብ እድለኛ ከሆንክ ከስንት አንዴ በትክክል ያዘዝከው ሊመጣልህ ይችላል ። ብዙ ጊዜ ግን ፡ ኬክ አዘህ ፡ ቁርጥ ከቢላ ጋር ወይም እንደሰውየው ጥብስ አዘህ ሳትመገብ የሂሳብ ቢል ይመጣልሀል ። .... አሁን ላይ ይህ ሬስቶራንት በጃፓን ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ፡ ከሀገሬው ነዋሪ ሌላ ፡ ስለምግብ ቤቱ በሰሙ ቱሪስቶችም ይጎበኛል ። @wegoch @wegoch @paappii By wasihun tesfaye
Mostrar todo...
72👍 36🥰 11😁 5😱 4
አህያ ላይ ከከረምን አይቀር . . . ገሜ/ጦና ከተማ ውስጥ ዎክ እያደረገ አንድ ጠጅ ቤት በር ላይ "አህያውን ላሳቀው ሰው 5000 ብር እና ነፃ ጠጅ እንሸልማለን" የሚል ማስታወቂያ ያያል። ይገባና ባለቤቱን አናግሮ ወደታሰረው አህያ ሄደና በጆሮው የሆነ ነገር ሹክ አለው። አህያው ፍርፍር ብሎ መሳቅ ጀመረ። ጦናም ጠጁን ጠግቦ ብሩን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሄደ። በሳምንቱ እዚያው ጠጅ ቤት በር ላይ "አህያውን መሳቅ ላስቆመው ሰው 5000 ብር እና ነፃ ጠጅ እንሸልማለን" ተብሎ ተለጥፏል። ጦናም ባለቤቱን አናገረና ወደ አህያው ሄደ። ከደቂቃ በኋላ አህያው መሳቁን አቆመ። ጦናም ጠጁን ጠግቦ ብሩን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲል ባለቤቱ ተገርሞ ጠየቀው። "እንዴት እንደዚህ ማድረግ ቻልክ?" ጦና "ባለፈው በጆሮው የኔ ቸንቸሎ ከሱ ጀላ እንደሚበልጥ ነግሬው ነው የሳቀው" ሲል መለሰ። "እሺ አሁንስ ሳቁን እንዴት አስቆምከው?" "አውጥቼ አሳየሁት!" 😂 @wegoch @wegoch @paappii By Gemechu merera fana
Mostrar todo...
😁 39👍 12👎 10 1
የኢትዮጵያ ቡድን የዛሬ ምሽት ነገር ይህን አስታወሰን ከአመታት በፊት ነው ። Charlton Athletic እና Chelsea በለንደኑ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ጨዋታ ነበራቸው ። .... እና ጨዋታው ከተጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ ፡ ዝናቡ እየበረታ ፡ ጭጋግና ጉም ስታዲየሙን ሸፈነው ። ተጫዋቾች አደለም ኳሷን አይተው ፡ መምታት ፡ እርስ በርስ መተያየት ሁሉ እያቃታቸው መጣ ። ...... በዚህ ጊዜ ዳኛው ውጡ አሉ " ይሄ ጭጋግ እስኪገፍ ጨዋታው መቆም አለበት " ልክ ከዳኛው ይህ ቃል እንደተሰማ ፡ በሜዳው ላይ የነበሩት የቼልሲና የቻርልተን አትሌቲክ ተጫዋቾች በፍጥነት ሜዳውን ለቀው ወደ መልበሻ ክፍል ገቡ ። ..... ጭጋግና ጉሙ እየባሰ መጣ ። የስታዲየሙ ሜዳ የመጨለም ያህል ሆነ ። በሜዳው ላይ አንድም ተጫዋች የለም ። ከአንድ ሰው በስተቀር ። ይህ ሰው የቻርልተን አትሌቲኩ በረኛ Sam Bartram ነው ። ሳም ፡ በድቅድቁ ጭጋግና ጉም መሀከል ካሁን ካሁን ኳስ ወደሱ ግብ ከተመታ በማለት ፡ የጎሉን በር ይዞ እየተጠባበቀ ነው ። ...... ሆኖም እስካሁን ምንም ኳስ አልተሞከረበትምና ፡ ጭጋጉ ባያሳየውም ቡድኑ የቼልሲን የግብ ክልል እያጠቃ እንደሆነ እያሰበ ፡ ምንም በማይታየው ጭጋግና ጉም ውስጥ ብቻውን ቆሟል ። ............ በዚህ ሁኔታ እያለ ፡ አስራምስተኛው ደቂቃ ላይ ግን በስታዲየም ውስጥ ከሱ ብዙም ባልራቀ ቦታ ላይ የነበረ ፖሊስ ፡ የበረኛው ቦታ ላይ የቆመ የሚመስል ብዥታ ተመለከተ ። ፖሊሱ ለማረጋገጥ ወደ ግቡ ተጠጋ ። ግብ ጠባቂው Sam Bartram ጎሉን እየተጠባበቀ አገኘው ። ..... ወደ መልበሻ ክፍል ይዞት ከተመለሰ በኋላ ሲጠየቅ ፡ ፖሊሱ መጥቶ እስከሚያገኘው ድረስ ተጫዋቾች መውጣታቸውን አያውቅም ነበር ። የክለቡ ተጫዋቾችም በረኛው አብሯቸው እንደሌለ ልብ አላሉም ። @wegoch @wegoch @paappii By wasihun
Mostrar todo...
😁 37👍 17 5
ጀለስ . . . ጀለስ ወደ ሸገር ሊሄድ ፕሌን ውስጥ መቀመጫውን አግኝቶ ቦታውን እንደያዘ አንዲት ቀሽት ቺክ አይቶ ልቡ መምታት ጀመረ። ወደሱ አቅጣጫ እየመጣች መሆኑን ሲያውቅ አይኑን በለጠጠ። አጠገቡ መጥታ ስትቀመጥማ መተንፈስ አቃተው። እንደተቀመጠች በወሬ አጣደፋት። «የአዲሳባ ልጅ ነሽ?» «አይደለሁም» «እና ለሥራ ነው ለመዝናናት?» ፈገግ ብላ «አንድ በሥነ-ፆታ እና ወሲባዊ ግንኙነት ባለሙያዎች የሚደረግ ኮንፈረንስ ላይ ልሳተፍ ነው የምሄደው።» ምራቁን ጉርጭጭ ሲያደርግ እየሰማችው ነበር። ቀሽት መሆኗ ሳያንስ ወሲብ ነክ ነገር ላይ ልትሳተፍ እየሄደች . . . . በለው! ሁኔታው እንደያስነቃበት ተጠንቅቆ ጠየቃት፣ «እና አንቺ ምን በምን አግባብ ተሳታፊ ሆንሽ ኮንፈረንሱ ላይ?» «ጥናት አቀርባለሁ። ከሕይወት ልምዴ ተነስቼ በሕብረተሰቡ ውስጥ ሥነ-ፆታን እና ወሲብን በተመለከተ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማስተካከል ነው የምሄደው።» ጀለስ ምራቁን እየዋጠ «እንዴ? በሀገራችን ደግሞ ምን ዓይነት የተሳሳቱ ግንዛቤዎች አሉ?» «ለምሳሌ በሀገራችን ትልቅ ቸንቸሎ አላቸው የሚባሉት ኦሮሞዎች ሲሆኑ እውነታው ግን ትልቅ ቸንቸሎ ያላቸው ወላይታ ወንዶች ናቸው። ሌላው ደግሞ ሴት አያያዝ ያውቃሉ፣ አፍቃሪ ናቸው የሚባሉት ተጋሩ ወንዶች ሲሆኑ እውነታው ግን አፍቃሪዎቹ ኦሮሞ ወንዶች ናቸው።» ይሄንን ካለች በኋላ ሴትየዋ ትንሽ ደንገጥ ብላ . . . «ይቅርታ ምንም ለማላውቀው ሰው ስለራሴ ብዙ ነገርኩና uncomfortable አደረግኩህ መሰለኝ» አለችና አቆመች። ይሄኔ ጀለስ . . . «ኧረ ጣጣ የለውም፣ ገመቹ እባላለሁ። ጓደኞቼ ግን “ጦና” ብለው ነው የሚጠሩኝ» 🚶‍♂️🚶‍♂️🚶‍♂️ @wegoch @wegoch @paappii By Gemechu merera fana
Mostrar todo...
😁 75👍 18 4👎 3🥰 1
#ማጣት እና ጊዜ          ……..ጊዜ የሆነ የውሃ አካል አይነት ቅርፅ አለው፡፡ አንሳፎ ወይንም አጣድፎ መውሰድ የመሰለ፡፡ በሄደ ቁጥር እያገላበጠ ያበስለናል፡፡  እድሜያችንም ይቆጥራል፡፡ ትንሽ እንኳን ፍጥነታችን ከፍጥነቱ ካልተመጣጠነ ደሞ ደርሰን ላንደርስበት ቀናት እያደነቃቀፉን እንካለባለን፡፡ እንግዲህ ድንገት አዝግመን ጊዜ ካመለጠን እንዲህ ነው፡፡ አካልና ጥላ እንሆናለን፡፡ ይሄዳል፣ እንከተላለን፡፡ ላንቀድመው ወይ ላንተካከለው መሮጥና መከተል እያዛለን እናረጃለን፡፡ በመደበኛ ሁኔታ ጊዜ እንደ ጎርፍ እሽሩሩ በሚመስል አሳስቆ መውሰድ አዝሎን የሚሄድ ከሆነ ግን ነገሩ ጊዜን እንደ ጥላ ከሚከተሉት ይለያል፡፡            ጊዜ ብቻውን ጊዜ ብቻ ሳይሆን የሁነቶች ጥርቅም ጭምር ነው፡፡ ከነዚያ ሁነቶች አንዱ አይሰብሩት ሊሰብረን ይችላል፡፡ ጊዜ ደግሞ ሁሌም የህመም እና የልብ ስብራት ወጌሻ ሆኖ ቶሎ ቁስልን መሻር አይቻለውም፡፡ ጊዜ እራሱ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ ይሄኔ እኛም ማጣታችንን መቀበል ሲሳነን፣ ከምናፈቅረው መለየታችንን ለማመን ሲያቅተን በጊዜ ታዝለን አንሄድም፡፡ ወይንም ጊዜን እንደ ጥላ አንከተልም፡፡ በውስጡ ሰጥመን እንጠፋለንን፡ ወይንም ጊዜ ሲሄድ ተገትረን እንቀራለን፡፡ ስለ ነገ ግድ አይኖረንም፡፡ አሁን የሚባል የጊዜ ልክን ክደን ‹ዛሬ› ባልነው ትላንት ላይ እንቆማለን፡፡ ያፈቀርነውን ካጣንበት ቅፅበት ወዲህ ዐለም ምኅዋሯን ስታ መሽከርከር አልገታችም፡፡ ፀሃይና ጨረቃ፣ ወቅቶች መፈራረቅ አላቆሙም፡፡ ወንዞች ሽቅብ ፈሰው፣ ሰማይ አልታረሰም፡፡ ቀናትም ቢሆኑ እንደ ሃውልት ተገትረው አልቀሩም፡፡ ይሆን የነበረው ሳይሻ ቀጥሏል፡፡ ጊዜም መሳሳቡን አልገታም (አይገታም)፡፡ እኛ ግን ላንዘም፣ ላንነቃነቅ አንዳች ‹አፍዝ፣ አደንግዝ› የተደረገብን ያህል ተገትረን እንቀራለን፡፡ ቀናት እየተጎተቱ ወራትን፣ ወራትም አመትን ያህላሉ፡፡ ዘመን ሲሄድ አኗኗር በየጊዜው ይቀየራል፡፡ ይሄኔ ትላንት ላይ የቆምን እኛ ከዘመን እና ከአኗኗር መቃቃር እንጀምራለን፡፡ ድርጊቶቻችን ሁሉ ጊዜን እንደሚከተሉ ወይንም ከሱ እኩል እንደሚሄዱ ብዙኃን ስላልሆነ ማህበራዊነታችን ሳናውቀውና ሳናስተውለው እንሸረሽረዋለን፡፡ ከሰው ፈልገን እየሸሸን የተገፋን ይመስለናል፡፡ ቅርባችን ላሉ ሁሉ ትላንት የነበረው ትዝታ፣ ለኛ ግን ‹ዛሬ› ሆኖ ሰፊ ቦታ ይይዝብናል፡፡ ‹ማጣት› እና ‹ጊዜ› በሆነ አይነት ቀጭን ክር ተጠላልፈው የተያያዙ ናቸው፡፡ ጊዜ ማጣትን አጠንክሮ የደደረ የሀዘንነት ቅርፅ ይሰጠዋል፡፡ ካልሆነም ደሞ ይሽረዋል፡፡ የጉዳቱ ልክም ጨምር የሚሰፈረው በጊዜ ነው፡፡ መቼስ በአብዛኛው ለአጭር  ወቅት ከምናውቀው ይልቅ ለረጅም ጊዜ አብሮን የቆየን ስናጣ ሀዘን ይበረታል፡፡ ቅርበትም ቢሆን እየተበበ የሚመጣው ጊዜ በገፋ ልክ ነው፡፡          ብቻ ማጣት የሚሉት እዳ ከጊዜ ያጓድላል፡፡ ከመኖር ያቃቅራል፡፡ ሞትንም ያረክሳል፡፡ መኖርም፣ አለመኖርም ጣዕም ያጡብናል፡፡ ጣዕም በራሱ ምንነቱ ይጠፋብናል፡፡ እንደ ፈሰሰ ውሃ በማይታፈስ አካሄድ የተለየን ሰው የሚሄድ ጊዜ ትዝታውን እያደበዘዘ እንዳያስረጀው እና በለጋነቱ እንዲቆይልን ስንል ካጣንበት ቀን እንቆማለን፡፡ በገዛ ራሳችን ፈንታ ትዝታችንን ‹እሹሩሩ› እንላለን፡፡ ግን አባባይ የሚያስፈልገን አልቃሾች እኛ ነን፡፡ By #Lewi @Lee_wrld777 @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
👍 11 2🔥 1😁 1
በዓለም ላይ በጣም ብልህ ሰው አንድ ዶክተር፣ ጠበቃ፣ ትንሽ ልጅ እና አንድ ቄስ በትንሽ የግል አውሮፕላን በረራ ላይ ነበሩ። በድንገት አውሮፕላኑ የሞተር ችግር አጋጠመው። አብራሪው ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም አውሮፕላኑ መውረድ ጀመረ። በመጨረሻም ፓይለቱ ፓራሹት ይዞ ተሳፋሪዎቹን ቢዘሉ እንደሚሻል ተናግሮ ጮኸ ወጣ ። እንደ አለመታደል ሆኖ የቀሩት ሶስት ፓራሹቶች ብቻ ነበሩ። ዶክተሩ አንዱን ያዘና "ሀኪም ነኝ ህይወትን አድናለሁ ስለዚህ መኖር አለብኝ" ብሎ ዘሎ ወጣ። ከዚያም ጠበቃው "እኔ ጠበቃ ነኝ እና ጠበቆች በአለም ላይ በጣም ብልህ ሰዎች ናቸው መኖር ይገባኛል." ብሎ ፓራሹት ያዘና ዘሎ ወጣ። ቄሱም ወደ ትንሹ ልጅ ተመለከተ እና "ልጄ ረጅም እና ሙሉ ህይወት ኖሬአለሁ አንተ ወጣት ነህ እና ሙሉ ህይወትህ ከፊትህ ይቅደም። የመጨረሻውን ፓራሹት ይዘህ በሰላም ኑር" አሉት ። ትንሹ ልጅ ፓራሹቱን ለካህኑ ሰጣቸውና "አይጨነቁ አባቴ በአለም ላይ በጣም ብልህ እና አስተዋይ ሰው ያስፈልጋልና እርሶ ኖረው ትውልድ ያንፁ " ብሎ እርሱ ብቻ ሊቀር ሲወስን ቄሱም " አይ ልጄ ታላቅን የሚያከብር እና ምሳሌ የሚሆን ሰው ያስፈልጋልና በአንዱ ፓራሹት ለሁለት መዝለል እንችላለንና ና ልዘልህ ብለው ተያይዘው ወረዱ ። ስራህ ሁል ጊዜ አይገልፅህም ጥሩ ሰው መሆን ግን ይገልፅሀል። @wegoch @wegoch @paappii By Tariku
Mostrar todo...
50👍 10👏 3👎 1🔥 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
2👍 1
በፍም እሳት ማቃመስ (እንደ ማስተዋወቂያ እነሆ...) (ያዕቆብ ብርሃኑ) * የሰውን ልጅ ከተራ አውሬነት ጎራ ነጥሎ ወደ መለኮታዊነት ያሸጋገረው እሳትን መፈልሰፉ ነበር፡፡ እሳትን ከማላመዱ በፊት የሰው ልጅ ከ20 በማይበልጡ ትንንሽ ቡድናት የሚንቀሳቀስ፣ የአዳኝ አራዊት ሰለባነትን ሽሽት የእውርድንብር የሚቃትት ድንጉጥ ፍጥረት ሆኖ አሳለፈ፡፡ እሳትን ማላመዱ ግን በአንድ ጊዜ ድርድርብ መሳሪያዎችን እንደመታጠቅ ሆነለት፡፡ አብስሎ መብላት ተቻለው፤ ጤናው ተሻሻለ፡፡ ምግቡም በረከተ፡፡ በአንድ ጊዜ ‹food chain›ኑ አናት ላይ ለመቀመጥ በቃ፡፡ እሳቱ ራሱን ከቅዝቃዜና ከአራዊት ጥቃት ለመከላከል እንደ ሁነኛ መሳሪያ አገለገለው፡፡ በእርግጥም የሰው ልጅ እሳቱን እስኪፈለስፍ ድረስ ለመጥፋት የተቃረበ፣ በስራ ፈትነት የሚንጀባረር ለአደጋ የተጋለጠ እንሰሳ ነበር፡፡ (Man was a meandering and jabbering around beast until he discover fire...) እሳትን ካላመደ በኋላ የሰው ልጅ ለስልጣኔው -ም-ት-ክ-የ-ለ-ሽ- መሠረቶች የሆኑትን የእሳት ግኝቶች - ምድጃን (hearth) - መሰዊያን (Altar) እና ማቅለጫን (forge) ፈለሰፈ፡፡ ምድጃው ሁለተናዊ ደኅንነት እና መረጋጋትን አቀዳጀው፡፡ ምድጃው እንደ ‹ሴል› (cell) ሆኖ የሰው ልጅ በዙሪያው እንዲሰባሰብ ምክንያት ሆነ፡፡ ቤተሰብ እንዲመሰረት አገዘው፡፡ ከቤተሰብ አስር ሃያ እያለ ወደ ትንንሽ ማኅበረብነት አደገ፡፡ መረጋጋት ቻለ፡፡ ቀስበቀስ መንደሮችን መገንባት ጀመረ፡፡ በምድጃው ዙሪያ ብዙ ዓይነት ተረቶችን አደራ፡፡ የሰው ልጅ ተረቶች፣ ታሪኮች፣ ሚቶች በሙሉ የመነጩት ከምድጃው ነበር፡፡ ተረቶቹ አፈታሪኮቹ ምናቡን ለመሳል ጠቀሙት፡፡ መሰዊያው መንፈሳዊ በጎነትን አጎናጸፈው፡፡ የዓለም ኃይማኖቶች በሙሉ የመነጩት ከመሰዊያው ነበር፡፡ ማቅለጫው ቅኝቱ የፈጠራ ሆነ፡፡ ከጦር አንካሴና ማጭድ ጀምሮ እስከ ሮኬት ሳይንስ ዛሬም ድረስ እየተራቀቀ ለቀጠለው ቴክኖሎጂያዊ መራቀቁ መነሻው እሱ ማቅለጫው ነበር፡፡ ነገርግን በግሪክና መሰል ጥንታዊ ተረታዊ ትርክቶች እንደሚባለው የሰው ልጅ እሳትን ከአማልክት አልሰረቀም፡፡ የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ጫረውም... እሳትን ከክዋክብት ገጽ ለመጫር ደግሞ ከገል እና ኩበት ይልቅ ምናብ ያስፈልጋል፡፡ ምናብ ምንጊዜም አሸናፊ ያደርጋል፡፡ ጥቂትስ ስንኳ የተሳሉ ምናቦችን ከመካከሉ መፍጠር የሆነለት ሕዝብ ምንጊዜም የትርክት የበላይነትን ይቀዳጃል፡፡ ስለምናብ ሳወራ ስለድርሰት ብቻ እየተናገርሁ የሚመስለው ካለ መቸስ ምን እላለሁ፡፡ ነገርግን ቴሌስኮፕ፣ ማይክሮስኮፕ፣ የማተሚያ ማሽን፣ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክን ጨምሮ በጠቅላላው የኤሮፓ ሥልጣኔ ግኝቶች የምናብ ውጤቶች መሆናቸው እሙን ነው፡፡ የእሳትንም ያህል ፍጹም ቅን፣ ገር እና በስነተፈጥሮው ቀጥተኛ ነገር መኖሩን አላውቅም፡፡ እሳት ከብሉያት፣ ነብያት፣ ወንጌላዊያን፣ ከአፈታሪኮች እና ባለቅንያት ዘመን ጀምሮ ብዙ የተባለለት መለኮት አከል ረቂቅ ክንውን ነበር፡፡ እሳት ሲፈጅ፣ ሲበላ እንጂ ሲያርፍ ማደሪያው የት፣ ሲግለበለብ መከሰቻው ከወዴት እንደሆንስ ስንኳ የሚያውቅም የለም፡፡ እሳት ስሪቱ የነበልባል፣ የፍላጻ ብቻ አይደለም፡፡ የቃል፣ የቀለም፣ የመንፈስ ልዩ ልዩ ዓይነት አለው፡፡ እሳት ንጹህ ነው፤ ቅን ነው፤ ገር ነው፡፡ ግን ደግሞ አውዳሚ፣ ጨራሽ፣ ፈጅ፣ ቀሳፊ፣ ቁጡም ነው፡፡ የዚህ ረቂቅ የነበልባል ቅኝት ጥሪ እና ምሪት ሰብዓዊነትን ማበልጸግ መሆኑ ጥንት ከአፈታሪክ፣ ከነፕሮሚተስ ዘመን ጀምሮ ይታወቃል፡፡ አሳት ሥሪቱ የእንከንየለሽነት፣ የምኅረትየለሽነት መሆኑም እሙን ነው፡፡ እሳት በመንፈሳዊውም (spirited) ይሁን በገቢራዊ (empirical) ባህሪው የሚያሻግር (fire of transmuting) እና የሚያሳርር (fire of destruction) መንታ ጉልበት ያለው ረቂቅ ሁነት ነው፡፡ እሳት የነካውን ሁሉ የሚያነጻ (purifying) ወይም የሚያገረጣ (terrifying) አቅም አለው፡፡ ቁም ነገሩ ለየትኛው አሰልጥነሽዋል/ አሰልጥነኸዋል የሚለው ብቻ ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት የሰው ልጅ በመጀመሪያ እሳትን የከዋክብቱ ገጽ ላይ ተጽፎ አየው፡፡ ያም በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈ - ምልክት ሆነለት - ... ነብዩ ኢሳያስ ለነብይነት የተመረጠበትን አኳኋን በሚናገርበት በትንቢተ ኢሳያስ ምዕ 6፡8 ላይ እንደምን በፍም እሳት መቃመስን ተቃምሶ መንጻትን እንደተቀዳጀ ሲገልጽ... ‹‹ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፡፡ በእጁም ከመሰዊያው በጉጠት የወሰደው ፍም ነበረ፡፡ አፌን ዳበሰበትና ‹እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል፡፡ በደልህም ከአንተ ተወገደ፡፡ ኃጥያትምህም ከአንተ ተሰረየልህ› አለኝ፡፡›› ይላል፡፡ የሰው ልጅም የእሳት አቀባበል እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ልክ የባላገር እናት የአራስ ቤት ጨቅላ ልጇን ወደ ሕይወት ለመጥራት በቅቤ እንደምታቃምስ እንዲያ የሰው ልጅ የነቢይ በሆነ በእሳት መቃመስን ተቃመሰ፡፡ ከእሳት ጋር መገናኘቱ ሁለንተናውን የሚያሻግር ክስተት ሆነለት፡፡ መቼ? የት? የሰው ልጅ ከእሳት ጋር ተዋወቀ ሳይንስ ባዝኖ ባዝኖ መልስ ቁርጥ ያለ መልስ ያጣላቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በደፈናው እስከ 2 ሚሊዮን ዓመታት ይገመታል ብሎ ማለፍ ይሻል ይመስለኛል፡፡ ነገርግንስ የሰው ልጅ እሳቱን ማላመዱ፣ በትንታግ መፈተኑ፣ ነበልባሉን መግራቱ ራሱ የሰው ልጅ ብዙ ዓይነት ሞራላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ሥነልቦናዊና አካላዊ ሽግግር እንዲያከናውን ረዳው፡፡ እሳትን ከፈለሰፉት የመጀመሪያዎቹ አውሬ መሰል የሰው ልጆች እስከ እሳትን ወደ ኤሌክትሪክ የቀሩት ድረስ ከ50 - 60 ሺህ ትውልዶች እንደተፈራረቁ ይገመታል፡፡ የእኛ ግን እርግማን ይመስላል፡፡ ሌላው ዓለም እሳቱን ከአመድነት ወደ ስማርት ምድጃነት ከፍታ ሲያሻግር እኛ ዛሬም ጉልቻዋን የሙጥኝ ብለናታል፡፡ ከጥንታዊነት (primitive sentiment) ያልተሻሻለ ቢሆንስ ስንኳ... ለዘመናት ጉልቻውን ታክከን ተረቱን ማንዘገጋችን አልቀረም፡፡ መሰዊያዎችንም (የአምልኮ ቦታዎች) በዓይነት እና በጥራት እየገነባን ስናደገድግ ምዕታት አልፈዋል፡፡ ለሰብዓዊ ልማት ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረውን ዋነኛውን የእሳት ግኝት ማቅለጫውን (forge) ግን ሆነ ብለን ረሳን፡፡ ማቅለጫውን ሙሉ ለሙሉ ብንረሳ ከብዙ መቶ ሺህ ዓመታት በፊት የመጀመሪያው የሰው ልጅ በተጠቀመበት ጦር ጀት የታጠቀውን ጣሊያንን ለመግጠም ተገደድን፡፡ የኢትዮጵያን የሥልጣኔ ታሪክ በተለይ ከአክሱም ውድቀት በኋላ የነበረውን ሂደት በጥልቀት የሚመረምር ሰው የጎደለን ነገር ማቅለጫው እንደነበር ግልጽ ይሆንለታል፡፡ ማቅለጫው ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሌላም ሌላም ብዙ ነገር ነው፡፡ በዚህ መጽሐፌ ከተካተቱ አስራ አንድ መጣጥፎች ውስጥ ስድሳ ገጾችን በሚሸፍነው የመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ ሥልጣኔ የጎደለው የመሰለኝን የማቅለጫውን ነገር በጥድፊያም ቢሆን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡ ሌሎች በዚህ መጽሐፍ ስር የተካተቱ ሌሎች አስሩም መጣጥፎቼ በልህቀት ለሚያነባቸው የእሳት ንክኪ እንዳላቸው አምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ በየመደብሩ ትገ ኛለች!!!
Mostrar todo...
👍 19 5
ተካፍሎ የመብላት ፀጋ - አንድ የሕክምና ዶክተር አሜሪካ ውስጥ የሮዜቲ መንደር/ከተማ ነዋሪዎች የጤና ሁኔታ ይገርመውና ጥናት ይጀምራል። የዚያ ማህበረሰብ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ከእድሜ አቻዎቻቸው ሌሎች አሜሪካውያን በተለየ ሁኔታ የልብ ሕመም ወይም ችግር የለባቸውም። የሚሞቱት በዕድሜ አርጅተው ብቻ ነው። ፍፁም ጤነኞች ናቸው። ይሄ ያልተለመደ ነበረና ማጥናት ጀመረ። መጀመሪያ ከጣልያን ሮዜቲ ከተማ የመጡ እንደመሆናቸው መጠን ሌሎች ጣልያናውያን የሚመገቡትን የወይራ ዘይት ለምግብነት ስለሚጠቀሙ ነው የሚል መላምት ይዞ ነበር የተነሳው። ነገር ግን ሲያያቸው ሌላው ሕዝብ የሚጠቀመውን ተራ ዘይት ነበር የሚጠቀሙት። ሌሎች የአመጋገብና የጤና ልማዳቸውን ቢያጠናም የተለየ ነገር አላገኘም። ከሙያው አንፃር ብቻ ያደረገው ጥናት የትም አላደረሰውምና አንድ ሌላ አንትሮፖሎጂስት ወዳጁን ጋብዞ ጥናቱን ጀመሩ። በሂደት አንድ ነገር አገኙ። የሮዜቲ ማህበረሰብ አባላት ረጅምና ጤነኛ ሕይወት የሚመሩት ሌላውን የሚያስጨንቅ ሕይወት ስለሌላቸው ነው። ፉክክር የሌለበት ማህበረሰብ ነው። ከሀገራቸው የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞችም ሆኑ ነባሮቹ የከተማው ነዋሪዎች ለአንድ ተመሳሳይ ሕግ ይገዛሉ። ከሌላው የማህበረሰብ አባል በተለየ ሁኔታ ሀብትና ንብረት አጋብሰው ነጥረው አይወጡም። ሁሉም እኩል ኑሮ እንዲኖሩ የሚያደርግ ሥርዓት ነበራቸው። ይሄ የፉክክር ያለመኖር ነው አብዛኛውን ከ65 ዓመት በላይ የሆነ ግለሰብ የሚያጠቃው የልብ ሕመም እነሱን የማያጠቃው ሲሉ ይደመድማሉ። ይሄንን የሚነግረን ማልኮም ግላድዌል ነው - ካነበብኩ ረዥም ጊዜ በሆነኝ መፅሐፉ። - እኛ ጋር ~ ሀዋሳ ሁል ጊዜ ሀዋሳ ስሄድ የማደርጋት አንድ routine አለ - አሞራ ገደል ሄዶ ጥሬ አሳ በብዙ ዓይነት ዳጣ እየተለበለቡ መብላት። እዚያ ስሄድ ታዲያ ሁሌ የሚገርመኝ አንድ የምግብ/የሥራ ሰንሰለት አለ። ገና በሩ ላይ ስትደርስ የሚቀበሉህ አሳ ገፋፊ አለ። ሥራው አሳውን ገፍፎና በላልቶ ማቅረብ ነው። ከቻለ ከሚያውቀው አሳ አጥማጅ/ሻጭ ያገናኝሀል፣ ካልፈለግክ ግን ራስህ የመረጥከው ቦታ ትሄድና ትመርጣለህ። ቢላውን ይዞ ይከተልሀል። በመሀል ግን ልጅ እግር ሴት ልጆች የውሀ ጆግና ጄሪካን ይዘው ውሀ ልሽጥልህ ይሉሀል። አሳው በንፁህ ውሀ መታጠብ ስላለበት ከጠያቂዎችህ አንዱን እሺ ትላለህ። አሳ ሻጩን፣ በላቹንና ውሀ ቀጂዋን በእግርህ እየሄድክ ዞር ስትል ተጣምረው ታገኛለህ። ከዛ ቁጭ ብለህ የምትበላበት ቦታ ፍለጋ ዞር ስትል አሳውን የምትበላበት ቂጣ የሚሸጡ ሴቶች ታገኛለህ። መርጠህ ተናግረህ ታልፋለህ። ከዛ አምስት ስድስት ዓይነት ዳጣ የሚሸጡ ሴቶች ጋር ትሄድና ዳጣ ታዛለህ። ቀጥለህ ውሀ፣ ጠላ ወይም የአሳ ሾርባ የሚሸጡ ቤቶች ያዘጋጁት ወንበርና ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ትልና አሳህ አልቆ እስኪመጣ ትጠብቃለህ። ከአንድ ምግብ ላይ ስንት ሰራተኛ፣ ስንት ለዕለት ጉርስ ተሯሯጭ ቆጠርክ? ሁሉም ተካፍሎ ነው የሚበላው። አንዱ የሌላውን ሥራ ጠቅልሎ ሊያቀርብልህ ይችላልኮ። ግን አያደርጉትም። ለዓመታት ታዝቤያለሁ። ይሄንን ሳስብ ደስስስስስ ይለኛል። ይሄንን ምግብ ጥንቅቅ ብሎ አልቆ አንድ ያማረ ሆቴል ላይ በተመሳሳይ ዋጋ ባገኘው ያን ያህል አልደሰትም። ሁላችንም በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን፣ ሥራዎችን፣ ገቢዎችን፣ ሸክሞችን ወዘተ እንደነሱ ብናደርግ እንዴት አሪፍ ነበር! ሰላማዊ ሕይወት! @wegoch @wegoch @paappii By gemechu merara fana
Mostrar todo...
👍 36 19👏 7
ከሚስቴ ጋር በማይረባ ነገር ተጋጨን 👇🏾 ከነኩርፊያችን ሳንነጋገር ሁለታችንም ወደ ስራ አቀናን: እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግን ሁለታችንም የምንሳፈረው በአንድ ታክሲ ነው እኔ ካዛንችዝ ስወርድ እሷ ደግሞ ወደ ፒያሳ ትቀጥላለች ቀድሚያት ከቤት ወጣሁኝ: በሮቹን ዘጋግታ ተከተለችኝ:: የታክሲው ሰልፍ ላይ ምንም አላወራንም:: ተራችን ደርሶ ስንሳፈር እኔ የታክሲው መጨረሻ ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ: እሷ ደግሞ ከእኔ ፊት ለፊት ካለው ወንበር ላይ ተቀመጠች ታክሲው መንቀሳቀስ ሲጀምር ከሚስቴ ጎን የተቀመጠው ጎረምሳ ሚስቴን ማውራት ጀመረ አጠገቧ ከተቀመጠበት ሰአት አንስቶ ሚስቴን በተደጋጋሚ ሲመለከታት አይቼዋለሁኝ: አንዴ ፀጉሯን ሌላ ጊዜ ደግሞ ፊቷን እያየ ምራቁን ሲውጥ ተመልክቼዋለሁኝ ሚስቴን ወዴት እንደምትሄድ በመጠየቅ ነበር የጀመረው: ስራ እየሄደች እንደሆነ ስትነግረው ይሰማኛል "ስሜ ሚኪ ይባላል: ለከተማው አዲስ ነኝ:: ለብዙ አመታቶች ውጭ ሀገር ትምህርት ላይ ነበርኩኝ: እዚህ ሰፈር ቤት ተከራይቼ ገብቼ ነው" "በጣም ደስ ይላል: እኔ እንኳ እዚህ ሰፈር ከገባሁኝ ሁለት አመታቶች ሆኑኝ" ሚስቴ ፈገግ ስትል በጎን ይታየኛል ሰውዬው አላቆመም 👇🏾 “ለምን ታዲያ ሰሞኑን አንገናኝም: ቤታችን አንድ ሰፈር በመሆኑ ተደዋውለን መገናኘት እንችላለን:: በዚያ ላይ በጣም ነው የምታምሪው “አመሰግናለሁ በጣም" የታክሲው ረዳት ሚስቴን ሂሳብ ሲጠይቃት ጎረምሳው ከፈለ "ቁጥርሽን ልቀበልሽ?" ብሎ ስልኩን ለመመዝገብ ሲያዘጋጅ ጣልቃ መግባት እንዳለብኝ ተረዳሁኝ ሚስቴን ጀርባዋን መታ አድርጌ ወደ እኔ ስትዞር "ለግፋባቸው ወተቱን በጡጦ አድርገሽለታል?" ብዬ ጠየቅኳት ሚስቴ ግራ ተጋባች : ግፋባቸው ደግሞ ማነው ሳትል አልቀረችም "አልጋነሽን ደግሞ ከትምህርት ቤት ማምጣት እንዳትረሺ" ጨመርኩኝ ሚስቴ እንደ እብድ እያየቺኝ ሳቀች "አዎን ፍቅሬ ወተቱን አዘጋጅቼ ነው የመጣሁት: አልጋነሽንም ከትምህርት ቤት አመጣታለሁኝ" አለችኝ "ባልሽ ነው?" ጎረምሳው ጠየቀ ሚስቴ ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች የእኔ መውረጃ ላይ ስንደርስ ይዣት ወረድኩኝ: እየሳቀች ተከተለችኝ "ቆይ አንተ! ማነው ግፋባቸው ማናት አልጋነሽ?" "የወደፊት ልጆቻችን ናቸዋ" እየሳቅኩኝ መለስኩላት በሌላ ታክሲ አሳፍሪያት ወደ ስራ ቦታዬ አቀናሁኝ 👇🏾 በኩርፊያ መካከል ሰይጣን እንዳይገባ መጠንቀቅ ነው ቢቻልስ ተኮራርፎ አለመቆየት መልካም ነው ❤️🙌🏼 (አንብቤ ወደ እኛ ሀገር ለዛ የመለስኩት ነው) @wegoch @wegoch @paappii By zemelak
Mostrar todo...
59😁 33👍 19🥰 5🔥 2👏 1
ይሔ ዘፈን ስለምንድን ነው? ስለ አባቱ? ስለ ሙዚቃ? ስለ ህይወት? ስለ አምላክ? ስለውበት? መተው ስለማይችሉት ፍቅር? ስለ ፀፀት? ስለ ኑዛዜ? ስለ ዕጣ ፋንታ? ስለ ምርጫ? ከራስ ጋ እርቅ ስለማውረድ? ስለሁሉም ነው በ'ርግጥ። ግን እንዴት ነው በአንድ ርዕስ ውስጥ ሁሉንም ስሜት ማንሳት የቻለው? ይሔ'ኮ ነፍ ሙዚቃ ነው። ይሔ'ኮ የመጥፎ ስራ ባህሪ ነው። እንዴት አስማምቶ እና አዋድዶ ሊሰራቸው ቻለ? እንዴት ነው ያልተበላሸበት? ሲገባኝ (የገባኝ ሲመስለኝ) መልሱ የጥያቄውን ያህል ውስብስብ አይደለም። ይሔ ዘፈን... ስለአባቱ፣ ስለሙዚቃ... አልያም ደግሞ ስለ አምላክ የተዘፈነ አይደለም። ይሔ... ቴዲ የሚባለው ሰውዬ እነዚህ ነገሮች ጋር ስላለው ግኑኝነት የተሰራ ስራ ነው። ስለ'ሱ ማወቅ የምትፈልጓቸው ነገሮች ሁሉ እዚህ ውስጥ አሉ። የሚፈራውን፣ የሚያፈቅረውን፣ የሚፀፅተውን፣ ራሱን ለማግኘት የሔደበትን ርቀት፤ ታግሎ የጣለውን ፈተና፤ ዛሬ ላይ የሚኖርለትን ፍልስፍና ጭምር ታገኟቸዋላችሁ። እጥር ምጥን ባለ መንገድ። ሳይጎረብጣችሁ። ሳያስጨንቃችሁ። የራሳችሁ ታሪክ እየመሰላችሁ። ብዙ ሰዎች ትረካ ከተራኪው ጋ ሲያያዝ....ጉዳዩን ማሳነስ ወይም ማጥበብ መስሎ ይሰማቸዋል። ግን አይደለም። ይሔ ማጥበብ ሳይሆን ማጉላት ነው። ለምሳሌ...ኤላ በመሰሉ ድምፅ "ወይ ምጣ ወይ ልምጣ" ሲል እንዴት ነው የሚጨንቅህ? ...ልጅ ሚካኤል ታቱውን እያሳዬ.."አትገባም አሉኝ" ሲልህ... "ኧረ በናታችሁ አስገቡት!" ብለህ ልትለማመጥለት አያምርህም? እንድታስብስ አያደርግህም? የወንዶች ጉዳይ ላይ እንዳለው ሰርግ ቤት "የእህቴ ልጅ ነው" ብለህ ይዘኸው መግባት አትመኝም?🙂 ...ጂጂ "ናፈቀኝ" ብላ የጎረቤቶቿን ስም እየጠራች ስታለቃቅስብህ...ከሀገርህ ሳትወጣ ሀገርህ አይናፍቅህም? ብቻ...ወዳጆቻችን እንደሚሉት..."The most personal is the most creative" ... ..."ሙዚቃ ህይወቴ" ደግሞ የቴዲ ፐርሰናል ስራው ነው። ምርጥ ስራው ነው። የቴዲ ምርጥ ስራው ነው ብቻ ሳይሆን ከምንጊዜም ምርጥ ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው። አውቃለሁ'ኮ ስለቴዲ ብዙ ተብሏል። አሰልቺ ርዕስ ነው ሁላ። ግን ስለፖለቲከኝነቱ እንጂ ስለጥበበኝነቱ የሚገባውን ያህል አልተባለም። እኔ እንዲያውም ምንም አልተባለም ባይ ነኝ። በፖለቲካው በጣም ከመወደሱ የተነሳ አንዳንድ ምዕመናን ቴዲ ቴዲ የሆነው በፖለቲካ ተሳትፎው እንጂ.....ያን ያህል ጥበበኛ ስለሆነ እንዳልሆነ ለማስረዳት ሲጣጣሩ ታገኟቸዋላችሁ። I am truly speechless እንደዚህ ለምታስቡ ሰዎች🙂 አንዱ እንዲህ ሲል ደርሼ አውቃለሁ እኔም። ያው በዝምታ ላልፈው ነው የሞከርኩት። ግን አስታወቀብኝ መሰል ልጁ ትንሽ ቆይቶ "ምነው ፊትህ ተቀያዬረ?...አይነኬውን ነክቼ አሳዘንኩህ እንዴ?" አለ የሹፈት ሳቅ እየሳቀ... "ኧረ በጭራሽ ወንድሜ!..ለሟች ማዘን የለም ባለው መፅናናት ነው!" ብዬ በህይወት ወደቀሩት ወዳጆቼ ዞርኩ😑 @wegoch @wegoch @paappii By mickel azmeraw
Mostrar todo...
👍 21👏 8 6👎 2😁 2
ድሮ አምስተኛ ክፍል ሳለን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ ሁለት ዲያቆናት ነበሩ። ከአብነት ትምህርት የጀመረ ፉክክራቸው ወደ ዘመናዊ ትምህርቱም አምጥተውት ነበር። በተለይ የሽምደዳ ትምህርቶችን የሚችላቸው አልነበረም። ልጅ እያሱ የት ተወልዶ.. .የት እንደሞተ ከነቦታው ከነ ዓመተ ምህረቱ ዱቅ ያደርጉታል። (በነገራችን ላይ አንድ ቀን ልጅ እያሱ ሀይቅ ዳር ተቀምጠው ሲፍታቱ መኮንኖች ከሩቅ ሾፏቸው ። ያን ጊዜ ልጅ እያሱ በርጫ እያደቀቁ ብን ብለው በምርቃና ፏ ብለው ነበር። ከዛ በኋላ ቤተ መንግስት አካባቢ ልጅ እያሱ የእስላም ቅጠል ያላምጣሉ ተብሎ እንደተወራባቸው ታሪክ ይናገራል 😂 ልጅ እያሱ አንቱ ለመባል የማያበቃ ልጅነት ነበራቸው። ሀገራችን በዘመኗ ካጋጠሟት የህፃን ባህሪ ካላቸው ንጉሶች ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ። በተለይ ጢዝ ያላት እንስት ካዩ ቅቤ እንደላሰ እባብ ይቅበዘበዛሉ ይባላል ። ብዙው የንግስና ዘመናቸው ላይ ሲወሸክቱ ራስ ተፈሪ በርቀት ይጠባበቋቸው ነበር። ራስ ተፈሪ ቤተስኪያን ተመሳም አንስቶ በቤተ መንግስት ዘንድ እጅግ የተወደደ ምግባር ነበራቸው። በንግስና ዘመናቸውም ትንሽ እንኳ ሳት ብሏቸው ከማጀት ሴቶች አንዷን ቢመቻቹ ለፀፀት ቅርብ ናቸው። ከአልጋ ወርደው ደበሎ አንጥፈው ጌታ ሆይ አፉ በለኝ ይላሉ በፍጥነት። ልጅ እያሱ ግን አንዷን ቆንጆ እየቀመሱ የሌላዋ እንስት ገላ ያሻፍዳቸው ነበር ) ወደ ዲያቆናቱ ልመለስ.. . እንዳለ ተብየው አንዲት ሸጋ ወዶ ጠየቀ። መጀመሪያ ይሄ የማርተሬዛ ሽልንግ የሚደብቅ ተረከዝህን አለስልስ ብላ ኩም አደረገችው ቆንጆዋ! እንዳለ ከዚህ የሞራል ስብራት በኋላ ሰይጣን በጆሮው አንድ በቀል ሹክ አለው። ጱጵ የሚል ድምፅ ከጎናችን ሰማን ። ደግሞ ለክፋቱ እኔ ከቆንጆዋ ልጅ ጎን ነው የተቀመጥኩት። ቆንጆ ይፈሳል ተብሎ ስለማይገመት ተሜው ሁላ አይኑን አጉረጠረጠብኝ። አፍንጫዬን በሹራቤ ስሸፍን ደግሞ ከሱ ብሶ ፈስ እንደሸተተው ሰው አፍንጫውን በጨርቅ ይሸፍናል እንዴ? ተባልኩ...ከ አምስት ደቂቃ ለጥቆ ቆንጆዋ ልጅ ሌላ ጋዝ ለቀቀች። ከመቅፅበት ደንግጣ ክፍሉን ለቃ ሮጠች። ዞር ስል ደብተራው እንዳለ ሆዱን እስኪቆርጠው ድረስ ይስቃል። የፈስ ድግምት ለቆባት መሆኑ ያኔ ገባኝ 🙂 በዚህ እውቀቱ የቀናው ደብተራው ሸዋ ሌላ ጉድ ይዞ ከተፍ አለ ። የበቀል በትሩ አንዲት ምስኪን መምህራችን ላይ አረፈ ። ቲቸር አስካል መክራን ዘክራን አልሰማ ስላልናት ብዙ ጊዜ በአርጩሜ መከራችንን ታበላናለች። ተማሪው ግርፊያዋን ስለሚጠላ እሷንም አብሮ አይወዳትም ነበር። በተለይ ሸዋ ... የክፍል መልመጃ 3/10 ስላመጣ ክፉኛ ጥርስ ነክሶባት ነበር ። የታሪክ ትምህርትን እንደ ውሀ የሚጠጣው ጎበዝ ተማሪ የሂሳብ ትምህርት ግን አናቱን እንደ ሀበሻ አረቄ ይነካዋል። በተለይ ማካፈል የሚባል ስሌት በቀን ሶስት ጊዜ አስረድተውት በቀን አስራ ሶስት ጊዜ ይስታል 😑 አሁን በምን ተዓምር ነው 19 /12.... 21 የሚመጣው ። መምህራችን በአዕምሮህ ነው ወይስ በእግርህ አውራ ጣት አስበህ ነው ይሄንን ውጤት ያመጣኸው ብላ ስትጣይቀው.. ." በ 16 ኪዳነምህረት ነች ። በ12 ሚካኤል ነው። እመቤቴንስ እንዴት ረሳታለሁ?" አለ አሉ 😑 በዚህ ጥርስ የነከሰው ሸዋ ዛዲያ አንድ ከሰዓት ላይ አደናግር ድግምቱን አነብንቦ ክፍል ውስጥ እንትፍ እንትፍ አለ። ቲቸር አስካልዬ እጇ ቄጠማ ሆነባት። እግሯ እንደ ህልም ሩጫ አልታዘዝ አላት። ጠመኔው ተሰሌዳው እንዴት ታዋህደው? አይነ አፋር ነች አይነ አፋርነቷ ጎልቶ አንገቷን ደፋች ። ደግሞ ለዛን ቀን ያለወትሮዋ እንኳን ሂሳብ ዓ ነገር መፃፍ አትችሉም ብላ አማርኛም እያስተማረችን ነበር። አማርኛ ብላ ለመፃፍ አገርኛ ብላ ስትፅፍ ሳቅንባት ። የግንባሯ ላቦት ተንዠቀዠቀ ። መልሳ መልመጃ ን ለመፃፍ መግለጫ ብላው አረፈች። ከተማሪው ሁሉ የሸዋ ሳቅ ጎልቶ ተሰማ ። መጨረሻ ላይ የሰራችው ስህተት ሲታከል ደግሞ ክፍሉ በሙሉ እንደ አደዋ ማስጀመርያ መድፍ አጓራ! አንብቡ አለችን ዓ ነገር ጥፋ.. . ምድረ ውሪ ተሰሌዳው የጣፈችውን ጥሁፍ እኩል አነበበው። "አበበ በሶ በዳ !"😆 ድንጋጤ ጨው አደረጋት ። የፃፈችውን ዞራ አነበችው ። ቂ....ቂ...ቂ ...ቂ...ቋቂ ሸዋንም ሳቁንም እኩል ጠላኋቸው 🙂 ሚካኤል .አ @wegoch @wegoch @paappii
Mostrar todo...
😁 15👍 12👎 4 4
ከሰሚት ወደ ሀያት የሚወስደው መንገድ ላይ አንድ ባለ መኪና እና የምግብ ማድረስ/ ብዩ ደሊቨሪ የሚሰራ ባለ ሞተር ሳይክል ቆመው እያወሩ ነው መንገዱ ተጨናንቆ ቆሜ ስለነበር ድምጻቸው ከፍ ብሎ ይሰማኛል:: እየተጣሉ ስለመሰለኝ ወደ መንገዱ ዳር ወጥቼ ሳጣራ ይህ ነው የሆነው ባለሞተሩ በከፍተኛ ፍጥነት እጁን ለቅቆ ጭራሹኑም ስልክ እያወራ ሲነዳ ያየው ባለመኪና ከኃላው ተከታትሎ አስቁሞት ነው ከዚያም ይህንን ታሪክ ይነግረዋል "እኔ እንዳንተ እሳት የላስኩኝ ባለ ሞተር ነበርኩኝ: በፍጥነትም ሆነ በብልጠት ማንም የማይስተካከለኝ:: ታዲያ በአንዱ ክፉ ቀን በከፍተኛ ፍጥነት ስበር ከመኪና ጋር ተጋጭቼ ከጥቅም ውጪ ሆንኩኝ:: ለህክምና ወጪ ያለኝን ሁሉ ሸጥኩኝ: አሁን እግሬ ውስጥ ብረት አለ:: እንደፈለግኩኝ አልንቀሳቀስም" ባለሞተሩ ፉቱ ላይ ድንጋጤ ይነበባል: አመስግኖት እና "ለልጆቼ ስል ከዚህ በኃላ ተጠንቅቄ ነው የምነዳው" ብሎ ቃል ገብቶለት ሄደ ሰውዬውን "ይህንን ሁሉ ህመም እንዴት ቻልከው?" አልኩት "አደጋው እኔ ላይ አልደረሰም:: ነገር ግን ፍጥነቱን አይቼ ለህይወቱ ስላሰጋኝ ነው እንደዚያ ብዬ የመከርኩት: አንዳንዴ ሰዎች ከሌሎች መከራ ይማራሉ " አለኝ አንዳንድ ሰው ብልህ ነው: ፈውስ ነው ❤️🙌🏼 @wegoch @wegoch @paappii By Andi lemenged
Mostrar todo...
59👍 18👏 7🥰 3🔥 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.