cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

IGNITE 🔥🔥🔥

በዚህ #channel የተለያዩ #ሀሳቦችን ፣ #ተሀድሶ ተኮር መፅሐፍቶችን ፣ #Videos እንዲሁም መልዕክቶችን እናስተላልፋለን ወጣቶችን ለተሀድሶ እንዲዘጋጁ ማድረግ ትልቁ ስራችን ነው ። ሐዋርያት 2 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የበዓለ ኀምሳ ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድነት፣ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው ነበር፤ ² ድንገትም እንደ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጥቶ ተቀምጠው የነበሩ

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
186
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሮሜ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና። ⁷ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ⁸ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ⁹ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ¹⁰ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤ ¹¹ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን። Rom 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ For when we were still without strength, in due time Christ died for the ungodly. ⁷ For scarcely for a righteous man will one die; yet perhaps for a good man someone would even dare to die. ⁸ But God demonstrates His own love toward us, in that while we were still sinners, Christ died for us. ⁹ Much more then, having now been justified by His blood, we shall be saved from wrath through Him. ¹⁰ For if when we were enemies we were reconciled to God through the death of His Son, much more, having been reconciled, we shall be saved by His life. ¹¹ And not only that, but we also rejoice in God through our Lord Jesus Christ, through whom we have now received the reconciliation. Happy Easter
Mostrar todo...
አቤቱ አድሰን! እንደ አይሁዳዊ፣ ካህንና ነብይ፣ ሕዝቅኤል በራእይ ራሱን ያገኘበት የድረቁ ዐጥንቶች የተበተኑበት ሸለቆ፣ የብሔራዊ ስብራት፣ መንፈሳዊ እፍረትና ጉስቁልና መገለጫ ነበር። እነዚህ ዐጥንቶች እንደገና በሕይወት ይኖራሉ ተብሎ ፈጽሞውኑ ተስፋ የማይጣልባቸው ነበሩ። የኪዳኑ ሕዝብ፣ “ዐጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ የለንም፤ ተቈርጠናል።” በማለት ለትድግናና ለተሐዶስ ያሰሙት የነበረው የተስፋ መቁረጥ ጩኸት የነበሩበትን የቀውስ ጥልቀት ያሳያል። የአሦር ዓለም ዐቀፍ ፖለቲካዊ ተጽእኖ በባቢሎን መዋጥ በጀመረበት ጊዜ ይሁዳ (የደቡቡ ክፍል) በመንፈሳዊ ቀውስ ውሰጥ ነበር፡፡ ቀደም ሲል እግዚአብሔር እስራኤልን (የሰሜኑ ክፍል) በኀጢአት መንገድ በመሄዱ ቃል ኪዳኑን ስላፈረሰ፣ በ722 ዓ.ቅ.ክ ለአሦር አሳልፎ ሰጥቷል። በተመሳሳይ የኀጢአት ዐመፅ ይሄድ የነበረውን ይሁዳ (የደቡቡ ክፍል)፣ በወቅቱ ዓለም ዐቀፍ ኀይል ለነበረው የባቢሎን መንግሥት 70 ዓመታት ግዞት አሳልፎ ሰጠ። የመጨረሻው ንጉሥ ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ባቢሎናውያን በጭከና የገዛ ልጆቹን ገደሉበት፤ ከዚያም ሁለት ዐይኖቹን በማውጣት በናስ ሰንሰለት አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት። የእሥራኤል ውበት የነበረውና በአንድ ወቅት ካህናት ማገልገል እስኪሳናቸው ድረሰ የእግዚአብሔርን መገኘት ያስተናገደው ቤተ መቅደስ፣ እንዲሁም ክብራቸው የነበረቸው ኢየሩሳሌም በእሳት ጋዩ፤ ቅጥሯቸውም ፈረሰ- ክብር ከእስራኤል ላይ ሸሸ። የኤርምያስ ሰቆቃ፣ የኢየሩሳሌምን ዐመፅ፣ ውርደት፣ እፍረት፣ ስብራትና ሐዘን ይግለጣል። “እግዚአብሔር መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶቿን ቅጥሮች፣ ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤. . . ዐይኔ በለቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች።” (ሰቆ. 2:7-11)። የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁኔታ በደረቁት ዐጥቶች ተመስሏል። ለእነዚህ ዐጥንቶች እንደገና በሕይወት የመኖር ብቸኛ ተስፋና ምክንያት እግዚአብሔር ብቻ ነው! የቱንም የህል የደረቁና ከተስፋ ውጭ ቢሆኑም እግዚአብሔር ሲናገር መስማት ችለዋል። በሥርዐቱ መሠረት ሕዝቅኤል በደረቁት ዐጥንቶች መካከል በመገኘቱ ረክሷል። ሆኖም የእግዚአብሔር ምሕረት ሸፍኖታል። ዐጥንቶቹ የሚገልጹት ርኩሰት፣ እፍረት፣ ውርደትና ባዶነት ሊወገድ የቻለው በሕዝቅኤል ቃል ሳይሆን፣ ከእንደገና አምላክ በወጣው የምሕረት ቃል ነበር። እስራኤል ከኪዳኑ ውጭ ያላት ህልውና ምውት ነው። ብሔራዊ ትድግና እንዲሁ ትንሣኤና ተሐድሶ መገኛቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ በሚመጣ የትንቢት ቃል ነበር። ከእግዚአብሔር ምሕረትና ጉብኝት በስተቀር፣ በየትኛውም ሰዋዊ ዘዴና ቃል ወደ ቀድሞ የከበረ የቃል ኪዳን ኅብረት ሊመለሱ አይችሉም፤ ምክንያቱም የሸሻቸው የእግዚአብሔር መገኘት ነበርና! መድሃኒቱ፣ ወደ እርሱ በመመለስ የኪዳን እድሳት ማድረግ ብቻ ነበር። እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን፣ ““የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ዐጥንቶች በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉን?” ሲል በጠየቀው መንፈስ፣ እኛም ካለንበት ውስብሰብ የሆነ መንፈሳዊ ቀውስ ውስጥ መውጫውን ብንጠየቅ፣ ልክ እንደ ሕዝቅኤል፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ብቻ ታውቃለህ!”፣ ከማለት በስተቀር ምን ለማለት ዐቅም ያለን አይመስለኝም። ኀይል አጥተናልና! አስቀድሞ ያለንበት ውድቅት፣ እፍረትና ስብራት ዐጥንታችን ድረስ ዘልቆ ሊሰማን ይገባል። የዚህ ዐይነቱ የውስጥ ሐዘን ነው አፋዊ ላልሆነ ንስሐ ያሚያዘጋጀን። “በእኔ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ወደ ኋላ ጣሉት፤ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ? ማንም እንዲሞት አልሻምና፣ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ወደ እኔ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ! (ሕዝ. 18:31-32) እኛ ስንመለስ - በእርግጥ ለእግዚአብሔር ለራሱ እንደ ተለየ ሕዝብ መኖር ስንጀምር - እግዚአብሔር ያድሰናል። ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ራስና ጌታ አድርጋ ባለሰየመችበት፣ ቅዱስ ቃሉን የበላይ ባለሥልጣን ባላደረገችበት እንዲሁም መንፈስ ቅዱሰ ባየተዋር ባደረገችበት መንገድ እየሄደች የእግዚአብሔርን አብሮነት ልታገኝ አትችልም። ለደረቁት ዐጥንቶች እግዚአብሔር ይናገራል፦ "እናንት ደረቅ ዐጥንቶች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ፤ ዐጥንቶች እንዲህ ይላል፤ 'እስትንፋስ አገባባችኋለሁ፤ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ። ጅማት አደርግላችኋለሁ፤ ሥጋ አለብሳችኋለሁ፤ በቆዳ እሸፍናችኋለሁ፤ በውስጣችሁም እስትንፋስ አገባባችኋለሁ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።'” (37፡4-7) እግዚኢብሔር ሲናገር ሙታን ይሰማሉ፤ ሕይወት እንደገና መዝራት ይጀምራል። “የኵሽ ኵሽታ ድምፅ ተሰማ፤ ዐጥንቶቹም አንድ ላይ ሆኑ፤ ዐጥንት ከዐጥንት ጋር ተጋጠመ . . . እስትንፋስም ገባባቸው፤ ሕያዋንም ሆኑ፤ እጅግ ታላቅ ሰራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።" (37:7-10)። ምንም እንኳን የሚገባቸውን ፍርድ የተቀበሉ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ከምሕረቱ የተነሣ የሐድሶ ተስፋ ሰጥቶአቸዋል። “ሕዝቤ ሆይ፤ መቃብሮቻችሁን እከፍታለሁ፤ ከውስጣቸው አወጣችኋለሁ፤ ወደ እስራኤል ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ። ከዚያም እናንተ ሕዝቤ ሆይ፤ መቃብሮቻችሁን ከፍቼ ሳወጣችሁ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። መንፈሴን በውስጣችሁ አስቀምጣለሁ፤ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፤ በገዛ ምድራችሁ አስቀምጣችኋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ፣ እንዳደረግሁትም ታውቃላችሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።” (ሕዝ. 37:12-14) የታሪክ ባለቤትና ጌታ የሆነው እግዚአብሔር፣ ልክ እንደ ተናገረ፣ ሰባው የግዞት ዓመታት መጠናነቀቂያ ዋዜማ ላይ የፋርስን ንጉሥ ቂሮስን በማስነሣት የባቢሎንን ትዕቢትና ኩራት ሰበረ። ቀደም ሲል ኩራተኛውንና የልዑል አምላክን ክንድ በንቀት የተመለከተውን የአሦር ዓለም ዐቀፋዊ ኀይል በባቢሎንን በማስነሣት እንዳዋረደው ማለት ነው! የኪዳኑን ሕዝብ ብሔራዊ ሉላዊነቱን አጥቶ ከወደቀበት መንፈሳዊ ቅውስ ውስጥ አወጣ። እግዚአብሔር ስለ ቂሮስ፦ “ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ፤ መንገዱን ሁሉ አስተካክዬለታለሁ፤ ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል፤ ምርኮኞቼን ያለ ክፍያ ወይም ያለ ዋጋ፣ ነጻ ያወጣል፤” (ኢሳ. 45:13) ሲል የተናገርውን ፈጸመ። አቤቱ አምላክችን ሆይ፣ አንተን ተርበናል፣ ሕይወት ዝራብን፤ አደሰንም! ~ አሜን! ዶ/ር ግርማ በቀለ
Mostrar todo...
ሪቫይቫል ያስፈልገናል! ሌላ አማራጭ የለንም። ሪቫይቫል(Revival) የሚለውን ቃል መስማት አሁን የተለመደ ነዉ። አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ትክክለኛ ትርጉሙን ባልጠበቀ መልኩ መነገሩ ቃሉን አሰልቺ ያደረገው ይመስላል! ከዛም በላይ አልፎ አልፎ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሪቫይቫል ቁራጭ የሆኑ ነገሮችን "ይሄ ነው ሪቫይቫል! " የሚል የግል አመለካከት በመስጠት የእውነተኛ ሪቫይቫልን ዋጋ ያሳጠነውም መሆኑ ግልጽ ነዉ። ቢሆንም በዚህ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላይ እውነተኛ ሪቫይቫል ያስፈልገናል! ሌላ አማራጭ የለንም። ሪቫይቫል ምንድነው? ከታሪክ ሁለት የእውነተኛ ሪቫይቫል ምሳሌዎች በአጭሩ እንመልከት። በ1904 ዌልስ በምትባል አገር የሪቫይቫል ተምሳሌት መሆን የሚችል እውነተኛ ሪቫይቫል ነበር። ይህ ሪቫይቫል ሃገሩን ሙሉ በሙሉ ነበር የደረሰው፤ ሁሉንም ሰው በሁሉም ቦታም መንካት የቻለ ነበር። በጊዜው ዌልስ የድንጋይ ከሰል የሚወጣባት ሃገር ነበረች: አብዛኞቹ ሰዎችም በዚህ የድንጋይ ከሰል የማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩ ነበሩ እናም እጅግ በጣም ተሳዳቢ አንደበት ያላቸው ኃጢአተኞች ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን የሪቫይቫሉ ንፋስ ምድርቱና ሰራተኞቹን ከመታቸው በኃላ የከሰል አውጪዎቹ ስራ ሙሉ በሙሉ ተመሰቃቀለ! ምክንያቱም የሚያወጡትን ከሰል ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ይጠቀሙ የነበረው አህዮችን ነበር: አህዮቹ ደግሞ ቀድሞ መንቀሳቀስ የለመዱት በስድብ ነበር: እና ከሰል አውጪዎቹ ከሪቫይቫሉ የተነሳ መሰዳብ አቁመው ስለነበር አህዮቹ መታዘዝ አቆሙ😂። ይህ የዌልስ ሪቫይቫል በጥቂቱ ሪቫይቫል በሃገር ላይ ምን የህል መንፈሳዊ ተጽዕኖ ልኖረው እንደምችል የሚያሳይ ነዉ-እውነተኛ ሪቫይቫል። በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በዌልስ የሚኖሩ ሰዎች ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀው እንደነበር ይታወቃል። ሌላው በምድር አሜሪካ በአንዳንድ ከተማዎች ቻርልስ ፊኒ የሪቫይቫል ኮንፍራንሶች በሚያዘጋጅበት ወቅት ይሆን የነበረው ነገር ድንቅ ምሳሌ ነዉ። ፊኒ ኮንፍራንሶች በሚያዘጋጅበት ወቅት የእግዚአብሔር ሃይል በከተማው ውስጥ ከሰው የማቆጣጠር ችሎታ በላይ ይሆን ስለነበር የፊኒ ኮንፍራንስ ከተማው ውስጥ መኖሩን እንኳን የማያውቁ ከሌሎች ከተሞች የመጡ እንግዳ ሰዎች በሃይል መንገዶች ላይ እየወደቁ ራዕይ ይመለከቱና በጉልበታቸው በየመንገዱ ጥግ እየተንበረከኩ በለቅሶ ከእግዚአብሔር ምህረትን ይጠይቁ ነበር። ይህ ነዉ ሪቫይቫል። የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ አይደለም የሚድኑት! እግዚአብሔር የጠራቸው ሁሉ በሪቫይቫል ወቅት በየትኛውም ቦታና ጊዜ በሪቫይቫል ተጽእኖ ስር ይወድቃሉ። እናም በዚህም ወቅት እንደዚህ አይነት የእግዚአብሔር እንቅስቃሴ ያስፈልገናል! በእውነተኛ ንስሐ ወደ እግዚአብሔር ሕይወት እንመለስ! @TheDeepThingsOfTheSpirit @TheDeepThingsOfTheSpirit
Mostrar todo...
❝እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ፤❞ —ሰቆ. 5: 21 (አዲሱ መ.ት) ❝Turn us back to You, O Lord, and we will be restored; Renew our days as of old,❞ —Lam 5: 21 (NKJV)
Mostrar todo...
አሁኑኑ ይስሙት oh God Do it again #Revive_us ለ #Revival የሚያዘጋጅ ፀሎት እና መልዕክት with The Voice/Kirubel The Kingdom at Hand 👇ይቀላቀሉን👇 @kingdomathand @kingdomathand @kingdomathand
Mostrar todo...
ለ Revival የሚያዘጋጅ ፀሎት.mp34.61 MB
የቤተክርስቲያን ድምቀት 💒.............. ትንቢታዊ አገልግሎት❌ የፈውስ አገልግሎት ❌ የታምራት አገልግሎት ❌ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ድምቀት ራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በክብር ሙላት ከባዶ ተስፋ ገላግላት።🔥🔥🔥🔥🔥 መንፈስ ወደ ቤተክርስቲያን ይመለስ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ መንፈስ @new_life_ministry @new_life_ministry
Mostrar todo...
እንደገና አድርገው!? DO IT AGAIN!? እግዚአብሔር ሆይ በቀደመው ዘመን ያደረግከውን ስምቻለሁ፤ በቀደመው ዘመን ያደረግከው አስፈሪ ነውና ስሰማ ፈራሁ፤ እባክህ እግዚአብሔር ሆይ በቀደመው ዘመን ያደረግከውን እንደገና አድርግ፤ ያንን አስፈሪ ስራህን በእኛም ዘመን ያለው ትውለድ እንዲያውቅ በድጋሚ አድርግ፤ የሚያስጨንቅ ነገር በመጣ ጊዜ በምህረት ተመልከተን። “እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤ በእኛ ዘመን አድሳቸው፤ በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።” — ዕንባቆም 3፥2 (አዲሱ መ.ት) @TheDeepThingsOfTheSpirit
Mostrar todo...
አባቴ ድንገት በመንፈሱ እሳት ያግኛችሁ ✋✋✋✋✋
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sĂłlo permite el anĂĄlisis de 5 canales. Para obtener mĂĄs, elige otro plan.