cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

* ይህ channel ሰለ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ከቅዱሱ መፀሀፍ የሚታይበት ነዉ፡፡ " ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃ 14 : 27

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 086
Suscriptores
Sin datos24 horas
+77 días
+1330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ጽናትና ውሳኔ (መጽሐፈ ሩት ምዕራፍ 1) ---------- 12፤ ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፤ ባል ለማግባት አርጅቻለሁና ሂዱ፤ ተስፋ አለኝ ብል፥ ዛሬ ሌሊትስ እንኳ ባል ባገባ፥ ወንዶች ልጆችም ብወልድ፥ 13፤ እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ። 14፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፤ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፤ ሩት ግን ተጠጋቻት። 15፤ ኑኃሚንም። እነሆ፥ ባልንጀራሽ ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፤ አንቺም ደግሞ ከባልንጀራሽ ጋር ተመለሽ አለቻት። 16፤ ሩትም። ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ 17፤ በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች። 18፤ ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች። "14 And they lifted up their voice, and wept again: and Orpah kissed her mother in law; but Ruth clave unto her." (Ruth 1:14)                     ** በዚህ የሩት መጽሐፍ ውስጥ ድንቅ ታሪክ እናነባለን፡፡  እሱም እንዴት አንዲት ሴት የወሰነችው ቁርጥ ውሳኔ ሕይወቷን ለዘላለም እንደቀየረው ነው፡፡ በዚህ ምድር ኹላችንም የምንኖረው የውሳኔዎቻችንን ፍሬ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ነገሮችን በጽናት ሳይኾን በስሜት ስንወስን ብዙ ዎጋ እንከፍልባቸዋለን፡፡ ከሩት የጸና የአልመለስም ውሳኔ ምን እንማለን                         **** 📖ሩት በውሳኔዋ በመጽናቷ ከአህዛብ ወገን ኹና ሳለ - የኢየሱስን ዘር ትውልድ ተቀላቀለች 📖ሩት የኑሀሚንን ችግር ሳታይ በእምነት ስለተከተለቻት የእስራኤል አምላክ ህይወቷን በበረከት አትረፈረፈው 📖ሩት ጸንታ ኑሀሚንን በመከተሏ ታሪኳ ዘላለማዊ ኾነ ዖርፋ ግን ከዛ በኀላ ምን እንደደረሰባት ራሱ አይታወቅም 📖ሩት ያመነችው ኑሀሚንን ሳይኾን የሷን አምላክ ነበር እና በውሳኔዋ እምነቷን ገለጠች አምላክም መልሶ ታመነላት ዛሬስ እኛ በሕይወታችን የጸናንባቸው ውሳኔዎች ምንድን ናቸው? ምን ያህል ነገሮችን ሁሉ አልፈን ሳንመለስ በጽናት ጌታን እየተከተልነው ነው?                            *** ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት በመጽናት ወደኀላ ላንመለስ ጌታን ይዘን መከተል ይኹንልን፡፡ ሩት ወደ ኑሀሚን በእምነት እንደተጠጋች እኛም ዘወትር ወደ ጌታ መጠጋት ፣ ወደሱ መቅረብ ይኹንልን🙏
Mostrar todo...
🙏 2
"ወደ እኔ ጩኽ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና የማይመረመር ነገር እገልጥልሃለሁ"  ኤር 33፥3 ፨መጮኽ አቅም ሳይሆን እምነትን ነው የሚፈልገው፤ ጩኸት ሰሚ እንዳለው ማመን፤ ጩኸት አድራሻ እንዳለው ማመን። "ወደ እኔ ጩኽ" የሚለውን ድምፅ ሰምተን ስንጮህ ሁሉን ቻዩን አምላክ ክንድ እንመለከታለን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።
Mostrar todo...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም።" “ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ”  ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ፍጹም ሠላምና ደስታ ሆነ። እንደተነገረው ተነስቷልና ከዚህ  የለም ፣             ማቴ 28፣6 ጌታችን በአምስት ነገር በኩራችን መሆኑን መጻሕፍት ይነግሩናል    1.  በጥንት ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ኖሮ እኛን ፈጥሮ ለማስገኘት በኩራችን ነው፡፡     2. በተቀድሶ/በመመስገን/ በኩራችን ነው፡፡ ቅዱሳን የጸጋ ምስጋና የሚመሰገኑት እርሱን በኩር አድርገው ነውና፡፡     3. በትንሣኤ በኩራችን ነው፡፡ እርሱን በኩር አድርገን እንነሣለንና “አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአል በሁለተኛው ሰው ትንሣኤ ሙታን ሆነ” 1ቆሮ.15፥20፡፡     4. በዕርገት በኩራችን ነው፡፡ ቅዱሳን አረጉ መባሉ እርሱን በኩር አድርገው ነውና፡፡ “አርገ ከመ ያሌቡ ዕርገተ ጻድቃን ንፁሀን” የንፁሀን ጻድቃንን ዕርገት ያስረዳ ዘንድ አረገ ቅዳሴ ዩሐንስ ወልደ ነጎድጓድ”    5.  ነፍሳትን ከሲዓል አውጥቶ ምርኮን ማርኮ ገነት መንግሥተ ሰማያት በመግባት በኩራችን ነው፡፡ እንኳን ለብርሀነ ትንሳዬው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ                                                                                    @Christdisciples
Mostrar todo...
🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኾይ፡፡➊ ለእኔ ኃጢአት ብለህ በጎልጎታ ቀራኒዮ ተሰቅለህ ሞተኃልኛል፤ እኔ የእግዚአብሔር ጽድቅ እሆን ዘንድ አንተ ኃጢአት ኾነህልኛል➋ እኔ ኃጢአተኛ፣ በደለኛ ነኝ፡፡➌ ዛሬም በደምህ ከኃጢአቴ አንጻኝ፡➍ ጌታ ኾይ፥ በመስቀሉ ስራ እንዳምን በመንፈስህ ስላበራህልኝ አመሠግናለሁ። አሜን PS ➊" ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።" (የዮሐንስ ወንጌል 20:28) ➋" እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21) ➌" ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤" (ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23) ➍" ... የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7) @Christdisciples
Mostrar todo...
👍 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀን_ሃምሳ አምስት ፶፭/55 ቅዳሜ የመጨረሻ  ቀን.....🙏 " የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ #ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል ።" (ወደ ዕብራውያን 12:24) በመስቀል ላይ የፈሰሰልን ደም ተራ የአንድ ሰዉ ደም ብቻ አይደለም በመስቀል ላይ የፈሰሰዉ ደም አምላክ ሰዉ ሁኖ ስለኛ መተላለፍና በደል የከፈለዉ ዋጋ እንጂ ፡፡ ይህ ደም እንደ ዋዛ ፈሶም የቀረ ደም አይደለም ይልቁንስ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ስለ ምህረትና ይቅርታ ስለኛ የሚጮህ ነዉ ፡፡ " አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። " (ኦሪት ዘፍጥረት 4:10) በእርግጥ ቃየን ወንድሙ አቤልን ሲገለዉ የአቤል ደም ስለ ራሱ ፍትህ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር በመስቀል ላይ ስለኛ የፈሰሰዉ የንጉሳችን ኢየሱስ ደም ግን ስለ ራሱ ሳይሆን ስለኛ ምህረትና ይቅርታ ዘወትር ይጮኸል ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከአቤል ይልቅ ለሚጮኸዉ ደም እንዴት ምህረቱን በኢየሱስ በኩል ለህዝቡ አይሰጥ???! #መልካም_ቀን!
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀን_ሃምሳአራት ፶፬/54  #አርብ " ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6) ክርስቶስ ሞቶልኛል፡፡ የኔ ሕይወት የሚመዘነዉ ባለኝ ሀብት መጠን ፣ በእዉቀቴ ልክ ፣... ሳይሆን በወደደኝ ደግሞ ኃጢያተኛ ሁኜ በሞተልኝ በጌታዬ ፍቅር ነዉ ፡፡ በእርግጥ ክርስቶስ እጅግ በጣም ይወደኛል ፡፡ ለዚህም ሞቶልኛል ! ለዚህ ነዉ ፍቅሩን ላስታዉስ መስቀሌን የምሸከመዉ ፣ ለዚህ ነዉ አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነዉ የምለዉ ፣ #መስቀሉን ሳስብ እበረታለሁ #መስቀሉን ሳስብ እፅናናለሁ #መስቀሉን ሳስብ እታደሳለሁ #መስቀሉን ሳስብ ሀሴት አደርጋለሁ ለዚህ ነዉ ደቀመዝሙርነቴን የምወደዉ ፣ ለዚህ ነዉ አድራሻዬን የቀየርኩት ፤ ኢየሱስ ኃጢያተኛ ሁኜ ወዶኛል ደግሞም ሞቶልኛል ፡፡ እንዴት ያለ ፍቅር ነዉ ?! #መልካም ቀን
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀን_ሃምሳሶስት ፶፭/53 #ሀሙስ " ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ #ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ #ፍቅር ለማንም የለውም።" (የዮሐንስ ወንጌል 15:13) ፍቅር ! ፍቅር ! ፍቅር ! በዚህ ክፍል እራሱ ኢየሱስ ስለ ፍቅር ለደቀመዛሙርቱ ሲያስተምር እንመለከታለን ፡፡ ፍቅር ማለት ኢየሱስ እኛን እንደወደደን ሌሎችን መውደድ ነው ፡፡ እሱ ደግሞ የወደደን ነፍሱን ስለእኛ አሳልፎ እስኪሰጠን ድረስ ነው ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ሲለን ሌሎችን እንደዚህ መውደድ ቀላል ስለሆነ አይደለም ግን በቁጥር 4 ላይ በእኔ ባትኖሩ ማፍራት አትችሉም ብሏል ኀላም ወደአብ ሲሄድ ብቻችሁን እንዳትሆኑ መንፈስ ቅዱስን እልክላችኀለሁ ብሎናል ፡፡ ስለዚህ ሰዎችን ከልብ መውደድ (ክፉ ያረጉብንን ጭምር) በስጋ አይን በጣም ከባድና የማይታሰብ ነው ፡፡ ግን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እንችላለን ፡፡ ኹልጊዜ በልባችን ከነድካማችን መንፈሱን መጠማት ይኹንልን ፡፡ 🙏 (የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 15) ---------- 12፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። 13፤ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። 14፤ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ። #መልካም ቀን
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀን_ሃምሳሁለት ፶፪/52 ረቡዕ " ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።" (የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15) እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ጊዜ ህዝቡን ከስጋ ሞት ሊያድን ሙሴን የነሀሱን እባብ በመስቀል ላይ እንዲሰቅል አደረገ ፡፡ ያንን የተሰቀለ እባብ ያየ ሁላ ከስጋዉ ሞት ይድን ነበር ፡፡ በእርግጥ በመስቀል ላይ የተሰቀለዉ እባብ የሚወክለዉ እርግማንንን ሀጢያትን ክፋትን በደልን ነበር ፡፡ በሚሻለዉ በአዲሱ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ህዝቡን ከስጋዊ ሞት ሳይሆን ከስጋ ሞት ከሚከፋዉ ዘላለማዊ ሞት ሊያድን አንድያ ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት ወሰነ ፡፡ ኃጢያት የማያዉቀዉንም ቅዱስ ልጁን በመስቀል ላይ ስለሁላችን በደል ኃጢያት አርጎ ስለኛ ክፋት እኛን ለማዳን ሰቀለዉ ፡፡ ማጣቀሻ (ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ 21) 6፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ። 7፤ ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው። በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት። 8፤ ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን። እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው። 9፤ ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ  5:21 እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። መልካም ቀን
Mostrar todo...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀን_ሃምሳአንድ ፶፩/51 ማክሰኞ " ... #የልጁም_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ደም_ከኃጢአት_ሁሉ_ያነጻናል።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7) ከአዳም ጀምሮ የሰዉ ልጅን ባሪያ አርጎ ሲገዛ የነበረዉ ፣ ወደማይፈልግበት የሚነዳዉ ትልቁ የሰዉ ልጅ ጠላት ኃጢያት ነበር ፡፡ ኃጢያት ደግሞ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን የሰዉ ማንነት ሆኖ ሰዉን ከአምላኩ አጣልቶ ከወንድሙ አባልቶ የሰዉ ልጆችን ሁሉ በምድር ያልተገባ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያስገድድ ሀይል ነበር ፡፡ የሰዉ ልጆች በዘመናቸዉ ከጥንት ጀምሮ ከዚህ ጨቋኝ ገዢ ለመላቀቅ ቢያስቡም የሚቻልና የሚዘለቅ አልነበረም ፡፡ አምላክም ፍጡሩን ስለሚወድ ከዚህ እንዲወጡ የተለያየ መንገድ ሲያዘጋጅላቸዉ እንደነበር መፀሀፍ ቅዱስ ይነግረናል ፡፡ ይሁን እንጂ የሰዉ ልጆች አምላክ የሰጣቸዉን ህግ ለመጠበቅ ሲጣጣሩ ነገር ግን ሳይችሉ ደግሞም መስዋት በማቅረብ ለኃጢአታቸዉ ስርየት ደም ሲያፈሱ እንደነበር ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል ፡፡ ይህም ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልተቻለም ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ሰዋች ሁሉ ኃጢያት መስቀል ላይ ሰዋዉ ፡፡ ልጁም ኢየሱስ ስለኛ ታዞ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰልን ይህንንም ደም ይዞ ስለኛ ዘወትር ሊማልድ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ አሁን በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ባፈሰሰዉ ደም ኃጢያታቸዉን ሊያነጻ ስለኛ በአብ ዘንድ ጠበቃ ሆኖ ተቀምጧል ፡፡ የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያድናል ፡፡ ወንድሜ ፥ በኃጢያት ዉስጥ አለህ ፣ ማንነትህ ኃጢያት ነዉ ? እንግዲያዉስ ኃጢአትህን ሁሉ ሊያነፃ ወደሚችል ወደ ኢየሱስ ተመለስ ፡፡ ማመሳከሪያ ጥቅስ ፦ " የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34) #መልካም_ቀን!
Mostrar todo...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀን_ ሃምሳ ፶/50 ሰኞ " እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። " (ወደ ዕብራውያን 9:28) በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነን ለዳንን እኛ ፦ በአብ ዘንድ ሁልጊዜ የሚታይልን ዘራችን ፣ iቋንቋችን ፣ የትምህርት ደረጃችን ፣ የሀብት መጠናችን ፣ የጤና ሁኔታችን ሳይሆን ስለኛ እንደተሰቀለ ያመነዉ ክርስቶስ ነዉ ፡፡ እሱ ደግሞ በእግዚአብሔር አብ ፊት ቅዱስ መስዕዋትና ለእኛ ጠበቃ ነዉ ፡፡ መስቀሉን ስናስብ ፍቅሩን እናስታዉስ ፤ መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን አንርሳ ፤ ይህ ሁሉ ስቃይ ፣ ይህ ሁሉ መከራ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰዉ እኛን ከዘላለም ፍርድ ለማዉጣት ስለኛም በአብ ፊት በፍፅምና ለመታየት ነዉ ፡፡ #መልካም_ቀን!
Mostrar todo...
👍 3
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.