cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

#ትርታዬ

Best channel concerning love affairs,educational, funny & health tips...☞♂⇜♥️⇝♀

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
276
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
+930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊 እንኳን ለ አዲሱ ዓመት አደረሳችሁ !! ዘመኑን 2016 💥የሠላም 💥💥የጤና 💥💥💥የፍቅር 💥💥💥💥የደስታ ያድርግልን💥 🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊 🌻🌻 መልካም 🌻🌻️ 🌻🌻 አዲስ 🌻🌻 🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️ 🌻️🌹⁣🌾🌻💐🌷🌻 🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🥱 ዝምተኛ ልቦች 🥱       〰️〰️〰️〰️ (ጌትነት እንየው) አምነው የወደዱ ወደው የተካዱ ተክደው የራዱ ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው? የትነው መድረካቸው? ማነው አጃቢያቸው? እንዴት ነው ምታቸው የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው? የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበደላቸው ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው? ከየት ነው ጥሪያቸው? በየት ነው ጉዟቸው? የት ነው መድረሻቸው? እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው? መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ ተገፍትረው ወድቀው ደቀው እንዳይቀሩ በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ::
Mostrar todo...
❤️ 7
Photo unavailableShow in Telegram
*የካፊያ ምች** ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ ካላጣችዉ ሰዓት ከቤት አስወጣቺኝ ጥርቅም ዕቅፍ አርጋ በካፊያ ሳመቺኝ የዕድሜ ልክ ልክፍቴን ያኔ አስለከፈቺኝ። መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ የኔ ልብ በሷ የሷ በኔ ጠፋ የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን ዉሃ ጠማኝ ዉሃ እየዘነበብን። ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ የዘመን ሕመሜን ያን ዕለት ታመምኩኝ። አሁን አሁን ታዲያ! ደመናዉ ሲጠቁር ነጐድጓድ ሲያጓራ ነፋስ ሲያስገመግም ክረምቱን ሊጣራ ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ፥ ምች ተሳልሜ።
Mostrar todo...
❤️ 4
Photo unavailableShow in Telegram
ሰው ፈልጌ ሰው አጣሁኝ ፣ ደከምኩ እኔስ ሰለቸሁኝ ፣ ሰው ናፈቀኝ ሰው አማረኝ ፣ የማይከዳ የማያማኝ ፣ ተንኮል ክፋት የማይመኝ ፣ ሰው አክባሪ የማይረሳኝ ፣ ጊዜ ሲጥል የሚያነሳኝ ፣ በልቡ ውስጥ የሚያኖረኝ ፣ ሰው ፈልጌ ሰው አጣሁኝ ፣ ደከምኩ እኔስ ሰለቸሁኝ ። ... ሰው ነው ብዪ የቀረብኩት ፣ በልቤ ውስጥ ያከበርኩት ፣ ሰላም ፍቅር ሰመኝለት ፣ ታምኝለት እያመንኩት ፣ ለካ አይደለም ተንኮለኛ ባዶ ፍቅር ፣ ሰላም አልባ ባዶ ህይወት ባዶ ነገር ፣ ባዶ ኑሮ ባዶ ሰላም ከንቱ ነገር ፣ ለህሊናው የማይሳሳ በክህደት የሰክረ ፣ ለሰው ክፉ የመከረ ፣ ሰው ፈልጌ ሰው አጣሁኝ ፣ ደከምኩ እኔስ ሰለቸሁኝ ። ... ሰው ቀርቤ ሰው አምኝ ፣ ሰው ቢጥለኝ ሰው ቢከዳኝ ፣ የማይተወኝ የማይከዳኝ ፣ የማይሸሽኝ የሚያቀርበኝ ፣ አጣህ ብሎ የማይጥለኝ ፣ እያመንኩት የታመነኝ ፣ እየወደኩ የሚያነሳኝ ፣ እየደከምኩ የሚይጽናናኝ ፣ አለ ከአርያም... እየነገርኩት የሚሰማኝ ። የማይሰለች የማይድክም ፣ አለ ከላይ ከአርያም ፣ የፍጥረታት ሁሉ ሰላም ፣ አለ... 🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜
Mostrar todo...
❤️ 6
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ ነገር የለም """""""""""""""""""""" ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣ ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣ ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣ አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣ መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣ ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣ የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣ ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣ እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣ እንከተላለን .... በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤ በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣ የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣ ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣ ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣ አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣ ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣ መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀወሰው፣ አይቻለሁ ባይኔ .... ጨርቁን ጥሎ ሲያብድ ጤነኛ ያልኩት ሰው፤ አዲስ ነገር የለም ስጠይቅ እራሴን .... ለምን እንደሆነ አንዱ አለፈ ሲባል ሌላው የሚተካ፣ ሲገባኝ እውነቱ .... ክብ አለም መዞር ነው ሂዎት ማለት ለካ። ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
Mostrar todo...
❤️ 4
Photo unavailableShow in Telegram
"       ተዋት!!!       "    ደስተኛ ትምሰል        ትሁን ከሰው እኩል፣    የትናንቱን እንባ        ትደብቀው በኩል፣    ዝንጥንጥ ትበል        እንዲለብሱት ለብሳ፣    ትደብቅ ትናንቷን        የአካሏን ጠባሳ፣    ምስቅልቅል ብስቁልቁል        ብትል ብትጎዳ፣    አይገኝም አፅናኝ....    እልፍ ሀዘኑን ትቶ        እርሷን የሚረዳ፣    ደስተኛ ትምሰል....    በሰዎች መካከል        ይመርባት በቀን፣    ትደርስበታለች ስትሆን ለብቻዋ....    የአምሮዋን ጩኸት       የውስጧ ሰቀቀን፣   ተ   ዋ   ት።      ⬜️⬛️⬜️⬛️⬜️⬛️⬜️⬛️⬜️⬛️⬜️⬛️⬜️⬛️
Mostrar todo...
❤️ 4
Photo unavailableShow in Telegram
በልብሽ  አስበሽ የኔን ልብ ለመስበር 💔 እግርሽ ከኔ ርቆ ወደሌላ ሲበር🏃‍♀️🏃‍♀️ እመኚኝ ፍቅሬ ሆይ ላለቅስ ይቅርና ሳቅ ሊገለኝ ነበር ሚል ግጥም ሰጥቼሽ ከቤቴ እንደገባሁ ልክ እንደ ህፃን ልጅ አንገቴን ቀብሬ ቁጭ ብዬ አነባው😢 አየሽ! አየሽ! መለየትሽ ቢያመኝ ሆዴን ቢያላውሰው ምን ላርግ ወንድ ልጅ ነኝና ባደባባይ ስቄ ቤቴ ነው የማለቅሰው 😥 「✿ሰዋዊ✿」
Mostrar todo...
❤️ 6
afd40bf7-b31c-4b4e-8b67-720a508ae778
Mostrar todo...
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
Mostrar todo...
❤️ 3
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.