cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

AFZAN MEDIA / አፍዛን ሚዲያ

አላህን በደስታህ ጊዜ ተዋወቅ በችግር ጊዜ ያውቅሀልና!!!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
396
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
ዘንድሮ ሀጅ ለምትሄዱ!!
Mostrar todo...
ግንቦት 13፣ 2016 | ዙል ቂዳህ 13፣ 1445 ዓ.ሂ. بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአል-ረህማን እንግዶችን መዲነቱል ሙነወራ ይዞ ገባ። •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• መዲና | በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሳፈሩት የ1445 ዓ.ሒ የመጀመሪያዎቹ የአል-ረህማን እንግዶች መዲነቱል ሙነወራ ገቡ። ሐጃጆቹ መዲና አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ሰብሳቢና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሸይኽ አብዱልሃሚድ አሕመድ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ሸይኽ ዛኪር ኢብራሂም አቀባበል አድርገውላቸዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ መዲነቱል ሙነወራ የገቡት የአል-ረህማን እንግዶች 263 ሲኾኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ 55 ያህል ሴቶች መሆናቸውን የአቀባበል አሥተባባሪው አቶ አብዲ ሲራጅ ተናግረዋል። መዲነቱል ረሱል (ሶ.ዐ.ወ.) የገቡት ሐጃጆች በቆይታቸው ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ እና ስለ ጤናቸው ጉዳይ አስፈላጊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። የ1445 ዓ.ሂ. የአል-ረህማን እንግዶች በመዲና በሚያደርጉት የሁለት ቀናት ቆይታ መስጂድ ቂብለተይንን፣ ኡሑድ ተራራን፣ በዚሁ ስፍራ ሸሂድ የሆኑትን የነሐምዛን ቀብር ይዘይራሉ። በመጨረሻም በመስጂደል ነበዊ የሚገኘውን ረውዳ በቡድን ኾነው ከዘየሩ በኋላ፣ ወደ መካ እንደሚጓዙ ከመስተንግዶ ኮሚቴው ለማወቅ ተችሏል። •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
Mostrar todo...
ሳዑዲ ዐረቢያ ምዕመናን በዑምራ ቪዛ ወደ መካ ከተማ መግባት የሚችሉት ለቀጣይ ሦስት ቀናት ብቻ ነው አለች የሳዑዲ ዐረቢያ ሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ወደ መካ መግባት የሚችሉትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች፡፡ ሚኒስቴሩ ከጁመዐ ግንቦት 16 አንስቶ እስከ ሰኔ 19//2016 የሐጅ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ብቻ ወደ መካ መግባት እንደሚችሉ ገልጿል፡፡ የዑምራ ቪዛ የያዙ ምዕመናን ላይ ቀነ ገደብ ያስቀመጠችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ከመላው ዓለም ለሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ሑጃጆችን በመቀበል ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ ከሑጃጀቹ መካከል 45 ኢትዮጵያውንን የያዘው የሳዑዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ንጋት ላይ መዲና መድረሱ ተነግሯል፡፡ ከመላው ዓለም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሑጃጆችን የምታስተናግደው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ሑጃጆችን ብቻ ለማስተናገድ በሚል ካስቀመጠችው ቀነ ገደብ በኋላ ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ የሚገቡ ምዕመናን ላይ መቀጮ እንደምትጥል ከዚህ ቀደም ማሳሰቢያ መስጠቷ ይታወሳል፡፡ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ያወጣው የመቀጮ ደንብ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 25/2016 ነው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ያለ ሐጅ ቪዛ ወደ መካ ከተማ የሚገቡ ምዕመናን ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ 10 ሺሕ የሳዑዲ ዐረቢያ ሪያል ነው፡፡ መቀጮው ተፈጻሚ የሚሆነው ከውጪ ሀገራት ወደ ሳዑዲ የሚገቡ ምዕመናን ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ ዜጎችም ላይ ነው ተብሏል፡፡ ደንቡን በተደጋጋሚ የሚጥሱ የውጪ ሀገራት ዜጎች 100 ሺሕ ሪያል ተቀጥተው ከሳዑዲ እንደሚባበሩ እንዲሁም ዳግመኛ እንዳይገቡ እገዳ እንደሚጣልባቸው የሐጅ እና ዑምራ ሚኒቴር መግለጫ ያመለክታል፡፡ አዲሱ ደንብ ከምዕመናን በተጨማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡ በዚህም ያለ ፍቃድ የትራንስፖርት አገልግሎ በሚሰጡ ላይ የ6 ወር እስር እንዲሁም 50 ሺሕ ሪያል መቀጮ ይጣላል፡፡ የትራንስፖርት አገለግሎት ሰጪው የሚጠቀምበት ተሽከርካሪ ሊወረስ እንደሚችልም ደንቡ ያትታል፡፡
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ይገኛሉ ‼️ ግንቦት 18 በከተማችን ኮምቦልቻ በሚዘጋጀው አገር አቀፍ የምስጋናና የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ይገኛሉ ‼️
Mostrar todo...
የ የ1445 አ.ሒ /2016 አ.ል ሑጃጆች ጉዞ ተጀመረ **** የ1445 አ.ሒ /2016 አ.ል የሐጅ ጉዞ ከዞን ሶስት የሃጅ የምዝገባ ጣቢያዎች ከጅግ ጅጋ እና ከጎዴ የመጀመሪያዎቹን ሑጃጆች የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚዎችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎች በበገኙበት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 13/2016 ከጧቱ 1:00 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል የሽኝት መርሀ ግብር አካሄደ፡፡
Mostrar todo...
የሀገራዊ ምክክር የተሳታፊ ልየታ ባለበት ከቀጠለ ለምክክሩ ዕውቅና እንደማይሰጥ የአማራ ክልል መጅሊስ አስታወቀ። የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር የተሳታፊ ልየታ አሠራር ሳይሻሻል ባለበት የሚቀጥል ከሆነ ለምክክሩ ዕውቅና እንደማይሰጥ በዛሬው እለት አስታወቀ። ምክር ቤቱ በአማራ ክልል ከዕውቅና ውጪ ሙስሊሙን በማግለል ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያ ዙር ጉባዔ ማካሄዱን ገልጿል። ምክር ቤቱ ይህንኑ ዛሬ ግንቦት 12/2016 ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ለአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር እና ለክልሉ ሰላምና ደኅንነት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ላይ አስታውቋል። በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጀውሐር ሙሐመድ በተጻፈው ደብዳቤ፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሉ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ያሳተፈው የኔ የሚለውን ብቻ እንደሆነ ተጠቁሟል። አካሄዱን የተቸው ምክር ቤቱ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን ያገለለ ሀገራዊ ምክክር የሚፈለገውን መልካም ውጤት ያመጣል የሚል እምነት እንደሌለውም አብራርቷል። ምክር ቤቱ በደብዳቤው፣ አሁን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል እየሄደበት ይገኛል ያለውን አሠራር እንዲያሻሽል ጠይቋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ የሚያካሄደውን የተሳታፊ አካላት ልየታ በፍትሐዊነት በድጋሚ እንዲቃኝ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ጠቅላይ ምክር ቤቱ ኮሚሽኑ በሚያካሄደው ምክክር ላይ የሕዝበ ሙስሊሙ አጀንዳ እንዲካተት፣ የተሳታፊ አካላት ልየታ በፍትሐዊነት በድጋሚ እንዲቃኝ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳላገኘ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አደርገዋለሁ ላለው ምክክር ተወካይ ያስመርጣሉ ተብለው ከተለዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ መምህራን እና የማኅበረሰብ መሪዎች፣ የተገለሉ ኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ዕድሮች እና የንግዱ ማኅበረሰብ ተካተዋል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተዘለዋል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሳምንት በፊት በእስላማዊ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ከሚሠሩ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች እና አንቂዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ በምክክር ኮሚሽኑ የተሳታፊ አካላት ልየታ የተመረጡ ሙስሊሞች ቁጥር ከ2 በመቶ በታች እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
Mostrar todo...
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ1445 ዓ.ሒ  ለሑጃጆች ያዘጋጀውን ማረፊያ ጎበኙ። … … ዛሬ ማታ በሚደረገው በረራ ለሚጀምረውና፣ ለ1445 ዓ.ል የተከበሩ የአሏህ እንግዶች ጉዞ አየር መንገዱ ያዘጋጀውን የማረፊያና የመስገጃ ቦታዎች የጎበኙት ፕሬዚደንቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለሚያደርገው የሐጅ ጉዞ ስኬት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበኩሉን ሀገራዊ አስተዋጽዖ እያደረገ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። … የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ  አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸዉ አየር  መንገዱ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በረራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አምሳ ዓመታት የሐጅ ተጓዦችን ሲያጓጉዝ መቆየቱን ተናግረዋል። … የ1445 ዓ.ሒ. የሐጅ ጉዞ ከታሪካዊቷ የአል ነጃሺ ሀገር ወደ ቅዱሲቷ መዲና የሚደረግ ጉዞ በመኾኑ፣ በሁለቱ ሀገር ሕዝቦች መካከል ያለውን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወንድማማችነት ያጠናክራል ብለዋል። … በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች ተርሚናል ላይ የተከፈተዉ የሑጃጆች ማስተናገጃ ቦታ፣ ለሑጃጆች ከሌሎች ተጓዦች የተለየ የመግቢያ፣ የማረፊያ እና የመስገጃ ቦታ ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል። …
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጎንደር ከተማ እየሰጠ ባለው ስልጠና ላይ ሙስሊሞች እንዳይሳተፉ መከልከሉ ተገለፀ! … የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጎንደር ክላስተር በአጀንዳ ማሰባሰብና ምክክር ላይ የሚሳተፉ የማህበረሰብ አባላትን ለመመልመል የሚያግዙ ተባባሪ አካላት ስልጠና እየሰጠ ሲሆን በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የመጡ ሙስሊሞችን እንዳይገቡ መከልከሉን የሀሩን ሚድያ ምንጮች ገልፀውልናል፡፡ … የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጎንደር ከተማ እየሰጠ ባለው ስልጠና አስመልክቶ "ሀሩን ሚድያ" ጉዳዩን አስመልክቶ ስልክ ደውልን ባጣራነው መረጃ መሠረት የደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ከተማ መጅሊስ አመራሮች ስልጠናው ላይ ለመሳተፍ ወደቦታው ቢያቀኑም ከበር እንዳይገቡ እንደተከለከሉ አንስተዋል። ... ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ምልመላ ያደረጉት ከክልሉ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንደሆነ በመግለፅ የክልሉ መጅሊስ ወክሏቸው ለመሳተፍ የመጡ ሙስሊሞችን አናስገባም ማለታቸውን ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል። … በጎንደር ከተማ እየተሰጠ በሚገኘው የጎንደር ክላስተር ተባባሪ አካላት ስልጠና ከ75 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ500 በላይ ሰልጣኞች እየተሳተፉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን የሙስሊሙ ቁጥር አነሳ መሆኑን እና የክልሉ መጅሊስ ባላወቀው መልኩ እንደተደረገ ተገልጿል፡፡ … ሀሩን ሚድያ ያነጋገራቸው አካላት እንደገለፁት ሙስሊሙን ያላሳተፈ ምክክር ውጤታማ አይሆንም በማለት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እየሄደበት ያለው መንገድ አግባብ ባለመሆኑ ሙስሊሙን እንዲያካትት ጥሪ አቅርበዋል። … ©ሀሩን ሚድያ
Mostrar todo...
👍 1
ፈረንሳዊው ሙሀመድ ቡላቢያር ህልሙ የነበረውን ኡምራ ለማድረግ ከስምንት ወራት የእግር ጉዞ በኃላ ሳዑዲ አረቢያ ደረሰ! … … ፈረንሳዊው ተጓዥ መሀመድ ቡላቢያር ከፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ተነስቶ ሳዑዲ አረቢያ መዲና ከተማ ዑምራ ለማድረግ እና ሁለቱን ቅዱሳን መስጂዶችን ለመጎብኘት "13" ሀገራትን ድንበር በማቋረጥ 8,000 ኪሎ ሜትር "የስምንት ወራት" በላይ በእግር በመጓዝ  ሳዑዲ አረቢያ መድረሱ ተገልጿል። … የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ መዲና ከደረሰ ከጥቂት ሰአታት በኋላ በነብዩ መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሙሀመድ ቡላቢያር ጋር ቆይታ ያደረገ ሲሆን ሙሀመድ ይህ ጉዞው ወደ መካ የሚቀጥል ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጿል ። … በፈረንሳይ ከቱኒዚያ አባት እና ከሞሮኮ እናት የተወለደው ሙሀመድ ቡላቢያር በጉዞ  ወቅት የተለያዩ የአየር ሁኔታዎችን እና አስቸጋሪ ቦታዎችን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችን እንደገጠመው የገለፀ ሲሆን በግሪክ ድንበር ላይ የበረዶ አውሎ ንፋስ ጉዞውን ለአንድ ሳምንት ያክል እንዳዘገየበት አንስቷል። … ሙሀመድ ቡላቢያር ፦ከመካ በኋላ መዲናን መጎብኘት ከልጅነቴ ጀምሮ ህልሜ ነበር ያለ ሲሆን መዲና ሲደርስም አይኖቹ በእንባ እንደተሞሉና ከሳውዲ ህዝብ ጋር በመገናኘቴ በጣም ተደስቻለሁ” ሲል አክሏል። …
Mostrar todo...
👍 1