es
Feedback
الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

Ir al canal en Telegram

​الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ​እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 186
Suscriptores
+2824 horas
+447 días
+45130 días
Archivo de publicaciones
📜🔗📌በትዳር ላይ ሆኖ ሌላ ቦታ መማተር የልብ መድረቅና የአላህን ቁጥጥር (ሙራቀባህ) የመርሳት ውጤት ነው።📌 ​ሂጃብንና ድንበርን መጠበቅ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ ቴሌግራም...) "ወንድም ነህ" "እህት ነኝ" በሚል ስም የሚጀመሩ አላስፈላጊ የፈገግታና የጫወታ ልውውጦች የዚና መግቢያ መንገዶች ናቸው። አላህ ወደ ዚና አትቅረቡ ነው ያለው መንገዱንም ጭምር ዝጉት ማለት ነው مَّا يَلۡفِظُ مِن قَوۡلٍ إِلَّا لَدَيۡهِ رَقِيبٌ عَتِيدٞ   ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡  (ሱረቱ አል ቃፍ 18) በዚህ መስመር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀደዱና ሳይዋረዱ  የአላህ ቁጣ ሳይወርድባቸው በአስቸኳይ ግንኙነቱን አቋርጠው ወደ አላህ ሊመለሱና ሐላላቸውን ሊያከብሩ ይገባል 📍እውነት ነው በጣም የሚያሳዝንና የሚያስገርም ነገር ነው! አላህ በሐላሉ ባርኮላቸው በትዳር ውስጥ ያለውን ክብርና ሰላም ሰጥቷቸው ሳለ ደግሞ ዞር ብለው ከሌላ ባለ ትዳር ወንድ ጋር የማይረባና የማይመጥን ግንኙነት ውስጥ የሚገቡ ሰዎችን ሲያዩ መታዘብ አይቀርም። ​ትዳር እኮ የአላህ ትልቅ ጸጋ መተማመኛና መከባበሪያ የፍቅር ቤት ነው። ታዲያ ያንን ሁሉ ክብር ጥለው  የአላህን ስትርና ጥበቃ አቅልለው ወደማይሆን ነገር የሚንሸራተቱት—ምናልባትም በልባቸው ውስጥ ባለው የኢማን ድክመት በስሜት መነዳትና ባላቸው ነገር ላይ ካለመብቃቃት (ቃናዓ ከማጣት) የተነሳ ነው። ​📌አላህ በሐላሉ ሰትሯቸው ከዚህኛው ምን አላቸው?"  ምንም የላቸውም! ከባዶ ስሜትና ከጸጸት ውጪ የሚያተርፉት ነገር የለም። የራስን ትዳር ማፍረስ ብቻ ሳይሆን የሌላውንም እህት የትዳር ህይወት ማናጋትና ቤተሰብ መበተን ትልቅ በደል ነው። 📌​ይህ የጊዜያችን አንዱ ትልቅ የሞራል ዝቅጠትና የማህበራዊ ሚዲያ መበላሸት ያመጣው ፈተና ነው። አላህ ልባችንን በሐላሉ የሚያረካ በትዳራችን ላይ በረካን የሚያወርድና ሁላችንንም ከእንዲህ አይነቱ የውሸትና የሃጢአት መንገድ የሚጠብቀን ይሁን። ስትሩን አይንሳን       📌አሏህ ሆይ ? በዚህ ነገር  የተሰማሩትን ወድም  እህቶች  አተ  ሂዲያውን ስጣቸው    አተ በሀላላቸው አብቃቃቸው  እኔንም ጠብቀኝ አሚን 📝

✋የዘንድሮው የዐሹራ ፆም (የሙሐረም 10ኛው) ቀን ሐሙስ ሰኔ 18 ላይ ይውላል። ይህንን ታላቅ ቀን መፆም ያለፈውን የ365 ቀናት (የአንድ ዓመት) ወንጀል ያስምራል። ​በላጩና ተመራጩ አፆፃም...ነብዩ (ﷺ) አይሁዶችን ለመለየት ዘጠነኛውንም ቀን አብሮ ለመፆም አስበው ስለነበር፣ በላጩ መንገድ ረቡዕ (ሰኔ 17) እና ሐሙስን (ሰኔ 18) አከታትሎ መፆም ነው። ሌሎችንም በማስታዎስ የአጅሩ ተጠቃሚ ያድርጓቸው! ~ t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

وَلَا يَأْتُونَ الصَّلَـٰوةَ إِلَّا وَهُمْ كُسَالَىٰ وَلَا يُنفِقُونَ إِلَّا وَهُمْ كَـٰرِهُونَ ሰላትንም ሰነፎች ሆነው እንጂ አይመጡባትም እነሱም ጠላቶች  የማይወዱ  ሆነው እንጂ አይለግሱም። ففي هذا غاية الذمِّ لمَن فعل مثل فعْلهم وأنه لاينبغي للعبد ان يأتي الصلاة إلا وهو نشيط البدن والقلب إليها ولا يُنفِق وهو منشرح الصدر ثابت القلب يرجو ذخرها وثوابها من الله وحده በዚህ ውስጥ የእነሱን ተግባር የመሰለ ሥራ ለሠራ ሰው የመጨረሻ የሆነ ውግዘት አለበት። ለአንድ የአላህ ባሪያም አካሉና ልቡ ለሰላት ንቁ ሆነው እንጂ ወደ ሰላት መምጣት እንደማይገባው ያሳያል። እንዲሁም ልቡ የጸና  ደረቱ የተከፈተ (በደስታ) እና ምንዳዋንና ዋጋዋን ከአላህ ብቻ የሚከጅል ሆኖ እንጂ ሊለግስ አይገባውም።

​🌟 የቁርአን ተፍሲር የቀጥታ ስርጭት ግብዣ 🌟 ​የልባችን ብርሃን የነፍሳችን ረፍት ከሆነው ከታላቁ የጌታችን ቃል ጋር የምናሳልፈው ድንቅ ጊዜ ደርሷል። እውቀትን መፈለግና በቁርአን ጥላ ስር መሰብሰብ ለሁለቱም ዓለም ትልቅ ስንቅና ስኬት ነው። ​ዘወትር ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሚቀርበውንና በኡስታዝ አቡ ሀኒፋ የሚሰጠውን ተወዳጅ የቁርአን ተፍሲር ቀጥታ ስርጭት (Live) ​ ሱረቱል አል-አዕራፍ (ከአንቀጽ 150 ጀምሮ) 🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ ተ    ጀ       መ           ረ 👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ ግቡ ተከታተሉ 📢 https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f

እየጠጣቹህ አንብቧት እማ ገና አልነቃንም ባገር ሰውነት ነው የምናወራው እኮ ሌላ ግንኙነት የለንም የሚልም ሞልቷል 🕶🕶🫖🫖 ሆ
እየጠጣቹህ አንብቧት እማ ገና አልነቃንም ባገር ሰውነት ነው የምናወራው እኮ ሌላ ግንኙነት የለንም የሚልም ሞልቷል 🕶🕶🫖🫖 ሆ

የወንድ ጓደኛ  እና የሴት ጓደኛ ማለት  ሶስተኛው ሸይጧን እነዚህ ሶስት  ግለሰቦች አላህን  ለማመፅ ተስማምተው  አብረው  በጀሀነም እሳት ውስጥ  ለመቀጣት የሚደርጉት ግንኙነት ነው ይህ መልእክት በአሁኑ ሰዓት በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ትልቅ ክፍተት እና መታረም ያለበትን የሥነ-ምግባር ጉድለት በግልጽና በቁጭት የሚያሳይ ነው። ቁርዓንና ኪታብ እንቅራ  በሚል ስም ተደብቆ በድብቅ ግንኙነቶች ውስጥ ያለው ፈተና እና   ትልቅ አመፅ ​⚠️ ከራስ ማታለል እንንቃ! (የጓደኝነት ወጥመድ) ​የወንድ ጓደኛ እና የሴት ጓደኛ የሚባለው ግንኙነት... በውስጡ ሦስተኛ አድርጎ ሸይጧንን የያዘ ነው። እነዚህ አካላት በአላህ ትእዛዝ ላይ ለማመፅ ተስማምተው፣ መጨረሻቸውን ወደ ጀሀነም እሳት የሚያደርጉበት አደገኛ መንገድ ነው! ​ዛሬ ላይ በብዙ እህቶችና ወንድሞች ዘንድ የሚታዩ ዲናዊ  ሽፋን የተሰጣቸው ግንኙነቶች ግን እጅግ ያሳስባሉ ​✍️ ቁርዓን እንቅራ እየተባባሉ ሰዓታትን በትዕይንትና በትልጭት ማሳለፍ ​✍️ ኪታብ ልቅራ  በሚል ሰበብ ከወንዶች ጋር መላፋትና ልብን መፈታተን ​✍️ በወንድምና በእህትነት ነው በሚል ሽፋን 24 ሰዓት ሙሉ ማውራትና መጃጃል ​ የጓደኛዬ ባል ነው ወይም የእህቴ ባል ነው እያሉ አጥርን መጣስ! ​🛑 ኧረ ለመሆኑ እኛ ጤነኞች ነን?! ​በእውነቱ በአሁኑ ሰዓት በዚህ መርዛማ ግንኙነት ውስጥ ያላችሁ እህቶች መቼ ነው የምትነቁት? ይህ እውቀት ማጣትና አለመሰልጠን ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? ስንትና ስንት እህቶች ናቸው በዚህ የተነሳ ሕይወታቸውና ዲናቸው እየፈረሰ ያለው! ​🛑 ወንዶችም እረፉ! ​እባካችሁ እረፉ! በገዛ እህታችሁ ላይ እንዲደረግ የማትፈልጉትን መጥፎ ነገር በሌላዋ እህታችሁ ላይ ስታደርጉት እንዴት ደስ ይላችኋል? እያንዳንዱ ድርጊት ተመላሽ አለው።
​✍ መልእክቱ ዲንን ለራስ ስሜት ማሟያ ሰበብ አናድርገው። አላህ በውስጥም በውጭም እውነተኛና ለአኽላቃቸው የሚጨነቁ ያድርገን። ዛሬውኑ እንንቃ

Repost from N/a
🔴አሰደሳች ዜና ከኑር 𝗢𝗻𝗹𝗶𝗻𝗲 አካዳሚ!📖 📱በቤቶት ሆነው የቁርአንና የኪታብ ትምህርቶችን በተመጣጣኝ ክፍያ በኦንላይን ይማሩ!📖 📖የምንሰጣቸው ተምህርቶች 🫴 ⏩ ቃኢዳ፣ ⏩ ቁርአን
🔴አሰደሳች ዜና ከኑር 𝗢𝗻𝗹𝗶𝗻𝗲 አካዳሚ!📖 📱በቤቶት ሆነው የቁርአንና የኪታብ ትምህርቶችን በተመጣጣኝ ክፍያ በኦንላይን ይማሩ!📖 📖የምንሰጣቸው ተምህርቶች 🫴 ⏩ ቃኢዳ፣ ⏩ ቁርአን (ነዘር/ሂፍዝ) ⏩ እና ኪታቦች 📖🧕 (በሳምንት 6 ቀን) 📱 ማስተማሪያ፦ ⏩️ በቴሌግራም፣ ⏩️ ዋትስአፕ ⏩️ እና ኢሞ ​⏬ Join በማለት ይቀላቀሉን፦

​🌟 የዕለቱ ማስታወሻ እውነተኛው ስኬት ​كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن
​🌟 የዕለቱ ማስታወሻ እውነተኛው ስኬት ​كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ ​ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው። ከእሳትም የተራቀና ጀነትን የገባ ሰው በእርግጥ ዕድለኛ (ስኬታማ) ሆነ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ዕቃ እንጂ ሌላ አይደለችም። — (ሱረቱ አል-ዒምራን፡ 185) 👇👇 ​ዱንያ የቱንም ያህል ብታሸበርቅና ብታምር መጨረሻዋ ማለፍና መርገፍ ነው። እውነተኛውና ዘላቂው ስኬት ግን ከእሳት ከጂሀነም ርቆ በረህማኑ እዝነት የጀነትን በር መርገጥ  መግባት መቻል ብቻ ነው:: ​ዛሬ የምንሮጥላት ዱንያ የፈተና አድራሻ ናት ነገ የምንሰበስበው አኼራ ደግሞ የውጤት መግለጫ አደባባይ ነው። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን። 🤲✨

ማስታዎሻ! ~ በአንድ ቀን ፆም ብቻ የ365 ቀናት ወንጀላችንን ማሳበስ! ➥ የዐሹራ ፆም መቼ ነው? ➥ እንዴትስ እንፁመው? ➥ በላጩ የአፃፃም መንገድ የቱ ነው? ➥ ለመሆኑ የመፆማችን ምክኒያት ምንድን ነው? t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

 ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት      ተ                  ጀ                                    መ                                            ረ    ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ  ➘  ➘ ➘ ➘➘ ➘ ➘ ➘  ➘ ➘ ➘ https://t.me/+CX6Rc-ukGq9mN2Jk

ወንድማችን ችግር ላይ ሆኖ እንዲህ ባለው ወቅት ለምን ትኩረት እንደሌለን አልገባኝም። ኡስታዞች ስለ ወንድማችን ጉዳይ ውይይት ለማድረግ ቀጥታ ስርጭት ገብተው ነበር፤ ነገር ግን እስካሁን አንድም ሰው አልገባም። ለወንድማችን ያለን ክብርና ፍቅር የት አለ? እባካችሁ አሁንኑ በመግባት እንድናግዘው አደራ

✍ለራሱ ያለውን መብት ያክል ላንተም እንዳለህ ከማያስብ ሰው ጋር ወዳጅነት መልካም አይደለም!!።✅

✍ለራሱ ያለውን መብት ያክል ላንተም እንዳለህ ከማያስብ ሰው ጋር ወዳጅነት መልካም አይደለም!!።✅

✍ ሲጠበቅ የነበረዉ የዳእዋና የኒያ ፕ    ሮ      ግራም ሊ     ጀ         መ              ር ስለሆነ ፈጥናችሁ ግቡቡ ሊንኩን በየቻናሉ እንድታሰራጩት በአሏህ ስም እንጠይቃለን https://t.me/+Vp1lW-dOfOkwZjVk

​🌟 የቁርአን ተፍሲር የቀጥታ ስርጭት ግብዣ 🌟 ​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ እና የተከበራችሁ ወድሞች እህቶች ​የልባችን ብርሃን የነፍሳችን ረፍት ከሆነው ከታላቁ የጌታችን ቃል ጋር የምናሳልፈው ድንቅ ጊዜ ደርሷል። እውቀትን መፈለግና በቁርአን ጥላ ስር መሰብሰብ ለሁለቱም ዓለም ትልቅ ስንቅና ስኬት ነው። ​ዘወትር ከመግሪብ ሶላት በኋላ የሚቀርበውንና በኡስታዝ አቡ ሀኒፋ የሚሰጠውን ተወዳጅ የቁርአን ተፍሲር ቀጥታ ስርጭት (Live) አብረን እንድንከታተልሁላችሁንም በታላቅ አክብሮትና ፍቅር እጋብዛችኋለሁ። ​ ሱረቱል አል-አዕራፍ (ከአንቀጽ 150 ጀምሮ) ​እህት ወንድሞቼ! ሁላችሁም አሁኑኑ በሊንኩ በመግባት የዚህ መልካም ሒሳብ ተካፋይ እንድትሆኑና እውቀታችሁን እንድታሳድጉ አበረታታችኋለሁ። መልካም ቆይታ ይሁንልን 🎙 በኡስታዝ አቡ ሐኒፋ ሑሰይን ኢድሪስ ሰዒድ ሐፊዘሁሏህ ተ    ጀ       መ           ረ 👉 ሸር አድርጉት. ተቀላቀሉ አድም አድርጉ ግቡ ተከታተሉ 📢 https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris?videochat=59dc0e0734fd48907f

رَبَّنَا إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنْصَارٍ ጌታችን ሆይ! አንተ እሳትን የምታስገባው  ሰው በእርግጥ አዋረድከው። ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የላቸውም ​ታላቁ ሱሀባ አቡ ደርዳዕ ረ..ዐ) ንግግር ​قال أبو الدرداء: “يرحم الله المؤمنين، ما زالوا يقولون: ربنا، ربنا، حتى استجيب لهم አቡ ደርዳእ እንዲህ አሉ አላህ ምእመናንን ይዘንላቸው ጌታችን ሆይ! ጌታችን ሆይ! ማለትን አያቋርጡም—ዱዓቸው ተቀባይነትን እስኪያገኝ ድረስ እውነተኛ አማኞች በአላህ ተስፋ አይቆርጡም ሁልጊዜም ደጋግመው "ረበና" (ጌታችን ሆይ) እያሉ ይለምናሉ። አላህም ይሄንን መላልሶ መለመንን ስለሚወድ በመጨረሻ ዱዓቸውን ይመልስላቸዋል     አሏህ ሆይ  መቀጣጠያዋ ድጋይና ሰው ከሆነቺው  እሳት ጠብቀን ያረብ ....

       ጥያቄ ❓ 👉የሱብሂ ሶላት ስንት ረከዓ አለው ❔ ✔️ፈጥኖ የመልስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል

​🚨 አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ጥሪ / 🚨 አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተከበራችሁ የኸይር ሥራ ፈላጊዎች! ​በድንገተኛ የባጃጅ አደጋ ምክንያት በፅኑ ታሞ የሕክምና ወጪ አጥቶ
​🚨 አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ጥሪ / 🚨 አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድና የተከበራችሁ የኸይር ሥራ ፈላጊዎች! ​በድንገተኛ የባጃጅ አደጋ ምክንያት በፅኑ ታሞ የሕክምና ወጪ አጥቶ በችግር ላይ ለሚገኘው ውድ ወንድማችን የገቢ ማሰባሰቢያ ልዩ የቀጥታ ስርጭት (Live) ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ታዋቂ ኡስታዞቻችንም በዕለቱ ከእኛ ጋር ይቆያሉ ​የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል
​"አላህ ባሪያውን በመርዳት ላይ ነው፣ ባሪያው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ።" (ሙስሊም) قال رسول الله ﷺ: واللهُ في عونِ العبدِ ما كان العبدُ في عونِ أخيه (رواه مسلم)
​ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ወንድማ በደረሰበት የባጃጅ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት የህክምና ወጪው ከአቅሙ በላይ ስለሆነ የሁላችንንም አስቸኳይ ድጋፍ ይሻል። ​የቻልነውን ያህል በመለገስ እና መልዕክቱን ሼር በማድረግ የወንድማችንን ጭንቅ እናቅልልለት ​⏰ የፕሮግራሙ ቀን< ቅዳሜ ምሽት ​🎙 ተጋባዥ እንግዶች  እና ኡስታዞች 1) ኡስታዝ አቡ አስማእ (ሙሀመድ ሁሴን) 2) ኡስታዝ አቡ ሀዳፍ/ ሰኢድ ሙሀመድ 3) ወድማችን ኑረዲን አቡ ፋሩቅ 4) ወድማቺን አቡ ሂበቲላህ   ሌሎችም ስማቸው ያልተጠቀሱ ይኖራሉ ኢንሸአሏህ👍✅ ​🔗 የቀጥታ ስርጭት (Live) ሊንክ 👇👇 https://t.me/+Vp1lW-dOfOkwZjVk   ጆይን ይበሉ   ለሌሎቹም ሸር ያድርጉ  ባረከሏሁ ፊኩም