ምክር ለወጣቶች
Ir al canal en Telegram
"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
7 291
Suscriptores
+1824 horas
+1927 días
+83830 días
Archivo de publicaciones
7 294
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !
ክፍል ሶስት
— የሶሓቦች ደረጃ በነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – ምስክርነት !
አላህ ከሰዎች ነብያቶችን መርጦ ወደ ሰው ልጆች በቃሉ ላካቸው ። በዚህም ነብያቶች በአላህና በሰው ልጆች መካከል አገናኝ ሆኑ ። ከተቀሩት ሰዎች መርጦ ደግሞ ለነብያቶች ሀዋሪያት አደረገ ። የነብዩ ሙሐመድ ባልደረቦች (ሶሓቦች) አላህ ለነብዩ ረዳትነት የመረጣቸው ምርጥ ትውልዶች ነበሩ ። የነብዩን መልእክት ባለበት ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ውድ ሕይወታቸውን ፣ ክብራቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ቤዛ አድርገዋል ። ለዚህ ዲን ሲሉ አንገታቸው ተቀልቷል ፣ ገላቸው ተከታትፏል ። አጥታቸው ተሰብሯል ። በደማቸው የነብዩ ሸሪዓ ለምልሞ ለዓለም ደርሷል ። የአላህ መልእክተኛ ስለነዚህ ባልደረቦቻቸው ከተናገሯቸውና የሰደባቸውንና ክብራቸውን የነካን ምን እንዳሉ በሚቀጥሉት ሐዲሶች እንመልከት : –
عن أبي سعيد رضي الله عنه قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم –:
«لَا تَسُبُّوا أَحَدًا مِنْ أَصْحَابِي، فَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَوْ أَنْفَقَ مِثْلَ أُحُدٍ ذَهَبًا، مَا أَدْرَكَ مُدَّ أَحَدِهِمْ وَلَا نَصِيفَهُ»
أخرجه البخاري ومسلم .
" ከሶሓቦቼ አንዱንም አትሳደቡ ከናንተ ውስጥ አንዳችሁ የኡሑድ ተራራን የሚያክል ወርቅ በአላህ መንገድ ላይ ወጪ ቢያደርግ (የሶሓቦቼን) የአንዳቸውን እፍኝ ወይም ግማሹ አይደርስም " ።
عن عائشة أم المؤمنين قالت: قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم –:
«مَنْ سَبَّ أَصْحَابِي فَعَلَيْهِ لَعْنَةُ اللهِ وَالْمَلَائِكَةِ، وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ» .
وقد رواه الإمام أحمد في "مسنده"، والإمام الترمذي وقال: حسن غريب،
" ሶሓቦቼን የተሳደበ በሱ ላይ የአላህ የመላኢካዎችና የሰዎችም ባጠቃላይ እርግማን ይውረድ "።
عن عبد الله بن مغفل – رضي الله عنه– قال :
قال رسول الله – صلى الله عليه وآله وسلم–:
«اللهَ اللهَ فِى أَصْحَابِي، اللهَ اللهَ فِى أَصْحَابِي، لَا تَتَّخِذُوهُمْ غَرَضًا بَعْدِي، فَمَنْ أَحَبَّهُمْ فَبِحُبِّي أَحَبَّهُمْ، وَمَنْ أَبْغَضَهُمْ فَبِبُغْضِي أَبْغَضَهُمْ، وَمَنْ آذَاهُمْ فَقَدْ آذَانِي، وَمَنْ آذَانِي فَقَدْ آذَى اللهَ، وَمَنْ آذَى اللهَ فَيُوشِكُ أَنْ يَأْخُذَهُ».
" በሶሓቦቼ ጉዳይ አላህን ፍሩ, (እኔ ከሞትኩ በኋላ) ክብራቸውን በመንካትና በመስደብ አዛ በማድረግ ኢላማ አድርጋችሁ አትያዟቸው ( በመጥፎ ነገር ወደነርሱ አታነጣጥሩ) እነርሱን የወደደ እኔን ለመውደዱ ነው የወደዳቸው ። እነርሱን የጠላቸው እኔን ለመጥላቱ ነው የጠላቸው ። እነርሱን አዛ ያደረገ እኔን አዛ አደረገ ! እኔን አዛ ያደረገ አላህን አዛ አደረገ ! አላህን አዛ ያደረገ ሊዘው ይቀርባል " ።
ጮሌ በምልክት ይገባዋል እንደሚሉት የነብዩና የሶሓቦች ወዳጆች ሶሓቦችን ለመውደድና ለማክበር አንድ የቁርኣን አንቀፅ ወይም የነብዩ ሐዲስ ይበቃቸዋል ። እነዚህ ስለሶሓቦች ክብርና እነርሱን መስደብ ወይም አዛ ማድረግ አደጋው ምን እንደሆነና ባለቤቱ ለአላህ እርግማንና ለሱ ቅጣት ራሱን የዳረገ መሆኑን የሚያሳዩ የነብዩ ንግግሮች ናቸው ። ሁሉንም እንዘርዝር ብንል መፅሐፍ ማሳተም ግድ ይለናል ። አላህ ካለ በሚቀጥለው ክፍል የሰለፍ ዑለሞች የሶሓቦችን ክብር የሚነካና የሚተች ሰውን አስመልክተው የሰጧቸውን ብይኖች እናያለን ።
https://t.me/bahruteka
7 294
👉 ተውሒድ የያዘ ሰው ሰላም ከሆኑት ይሆናል ።
يقول ابن القيم – رحمه الله –
" فالتوحيد حصن الله الأعظم، الذي من دخله كان من الآمنين " .
ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –
" ተውሒድ ያ የገባው ሰው ሰላም የሚሆንበት ትልቁ የአላህ መጠበቂያ ነው "።
https://t.me/bahruteka
7 294
📌የጁሙዓ ኹጥባ
ርዕስ ፦
وَقِفُوهُمْ إِنَّهُمْ مَسْئُولُونَ!
🎙አቡ አብዲረህማን አቡዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁሏህ)
📆 ረቢዑ አልወል 22 /1448
join #telegram ቻናል
https://t.me/abuabdurahmen
7 294
🌹የጁመዓ ቀን ሱናዎች 🌹
🌺سنن يوم الجمعة🌺
┈┈┈┈┈••●◉🌙◉●••┈┈┈┈┈┈┈
❶ الغسل
❷ الطيب
❸ السواك
❹ لبس الجميل
❺ قراءة سورة الكهف
❻ التبكير لصلاة الجمعة
❼ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي
┈┈┈┈┈••●◉🌙◉●••┈┈┈┈┈┈┈
➢
ገላን መታጠብ
➢ ሽቶ መቀባት ( ለወንድ ብቻ)
➢ ሲዋክ መጠቀም
➢ ጥሩ ልብስ መልበስ
➢ ሱረቱል ካህፍን መቅራት
➢ ለጁመዓ ሶላት ቀደም ብሎ መሄድ
➢ በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን ማብዛት
┈┈┈┈┈••●◉🌙◉●••┈┈┈┈┈┈┈
▫️እንዲሁም ብለዋል ﷺ የጁመዕ ሌሊትና ቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን አብዙ ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብልኛል
اللَّهُمَّ صلِّ عَلَى مُحمَّدٍ وعلى آلِ مُحمَّدٍ
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آل
إِبْرَاهيم إِنَّكَ حَميدٌ مَجيد
ﷺ
ﷺ✨ﷺ
ﷺ✨ﷺ✨ﷺ
ﷺ✨ﷺ✨ﷺ✨ﷺ
ﷺ✨ﷺ✨ﷺ✨ﷺ✨ﷺ
✨ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን ✨
Share
https://t.me/nejashi_nejashi7 294
ይሄ Legend ቃሪእ ስሙ ማነው?
በየቀኑ እንደዚህ አይነት አጫጭር ጣፋጭ ቲላዋዎች እንዲደርሳቹ ከታች ያለውን ሊንክ ጆይን በሉ👇👇👇
https://t.me/Sakinah_Quran_Post
https://t.me/Sakinah_Quran_Post
7 294
💥ነገ የሳምንቱ ምርጡ
ቀን ነዉ ሰሉ አለ ረሱል 🌹
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد!🌸🌸🌸
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد!🌸🌸🌸
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد!🌸🌸🌸
7 294
"ወሊይ ነው"
እንደዚህ አይነት አጫጭር ቪዲዮዎች እንዲደርሳቹ ከፈለጋቹ ቻናላችን ጆይን ይበሉ
👇👇👇
https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1
7 294
የአሕዛብ ምዕራፍ الأحزاب 33:56
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
7 294
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !
ክፍል ሁለት
— የሶሓቦችን ክብር የመንካትና የመዝለፍ ብይኑ :–
ሙሓመድ ሓሚዲን ሰይድ ቁጥብ ከነብዩ ሶሓቦች ውስጥ የብዙዎችን ክብር ከማጉደፉና ከማብጠልጠሉ በተጨማሪ ሙዓዊያንና አጋሮቹን በኒፋቅ ፣ በማታለልና በመሰሪነት ይፈርጃል ። የዚህ አይነቱ የኢስላም ጠላቶች በእስልምና ላይ ተአማኒነት እንዳይኖር ያስተላለፉትን ሶሓቦች ማነወር የሚሉትን መርህ ተከትሎ ሶሓቦችን የማብጠልጠል ስራ በተዋጣለት መልኩ ሰርቶ ከራፊዳዎች ሽልማት የተቸረውን ሰይድ ቁጥብ ተግባር ቀለል በማድረግ ነው የሚያጣፋው ጠበቃው ሙሐመድ ሓሚዲን ። የሰይድ ቁጥብን በሶሓቦች ላይ ዘመቻ ክብደት ለማወቅ ሶሓቦች በኢስላም ያላቸውን ቦታ ማወቅ ግድ ይላል ።
የሶሓቦች ክብር በቁርኣን ውስጥ : –
{ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ ۖ تَرَاهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا ۖ سِيمَاهُمْ فِي وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ السُّجُودِ ۚ ذَٰلِكَ مَثَلُهُمْ فِي التَّوْرَاةِ ۚ وَمَثَلُهُمْ فِي الْإِنجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْأَهُ فَآزَرَهُ فَاسْتَغْلَظَ فَاسْتَوَىٰ عَلَىٰ سُوقِهِ يُعْجِبُ الزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ الْكُفَّارَ ۗ وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ مِنْهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا }
الفتح (29)
" የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው ፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት ፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው ፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና ፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና ፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው ፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው ፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል "፡፡
{ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ }
التوبة (100)
" ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል ፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው "፡፡
لِلْفُقَرَاءِ الْمُهَاجِرِينَ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِمْ وَأَمْوَالِهِمْ يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا وَيَنصُرُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ፣ አላህንና መልክተኛውንም የሚረዱ ኾነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድኾች (ይስሰጣል)፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፡፡
وَالَّذِينَ تَبَوَّءُوا الدَّارَ وَالْإِيمَانَ مِن قَبْلِهِمْ يُحِبُّونَ مَنْ هَاجَرَ إِلَيْهِمْ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمْ حَاجَةً مِّمَّا أُوتُوا وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ ۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡
وَالَّذِينَ جَاءُوا مِن بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالْإِيمَانِ وَلَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِّلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا إِنَّكَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ
እነዚያም ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችን ምሕረት አድርግ፡፡ በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት (ሰዎች) ጥላቻን አታድርግ፡፡ ጌታችን ሆይ! አንተ ርኅሩህ አዛኝ ነህና» ይላሉ፡፡
الحشر (10–8)
{ وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ ۚ لَوْ يُطِيعُكُمْ فِي كَثِيرٍ مِّنَ الْأَمْرِ لَعَنِتُّمْ وَلَٰكِنَّ اللَّهَ حَبَّبَ إِلَيْكُمُ الْإِيمَانَ وَزَيَّنَهُ فِي قُلُوبِكُمْ وَكَرَّهَ إِلَيْكُمُ الْكُفْرَ وَالْفُسُوقَ وَالْعِصْيَانَ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الرَّاشِدُونَ }
الحجرات (7)
" በውስጣችሁም የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ ፡፡ ከነገሩ በብዙው ቢከተላችሁ ኖሮ በእርግጥ በተቸገራችሁ ነበር ፡፡ ግን አላህ አምነትን ወደናንተ አስወደደ ፡፡ በልቦቻችሁም ውሰጥ አጌጠው ፡፡ ክህደትንና አመጽንም እንቢተኛነትንም ወደናንተ የተጠላ አደረገ ፡፡ እነዚያ (እምነትን የወደዱና ክሕደተን የጠሉ) እነርሱ ቅኖቹ ናቸው "፡፡
እነዚህ የቁርኣን አንቀፆች በመቶዎች ከሚቆጠሩት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው ። የነብዩ ባልደረቦች ( ሶሓቦች) ደረጃቸው ቢለያይም ባጠቃላይ ፍትሓዊና ከኒፋቅና ኩፍር የጠሩ ለመሆናቸው በአላህ የተመሰከረላቸው ናቸው ። አንድ ከገጠር የመጣ ገበሬ ከነብዩ ጋር ተገናኝቶ በሳቸው አምኖ በዛው ኢማን ላይ ከሞተ ከዛ በኋላ ከሚመጣ ትውልድ ውስጥ የፈለገው የዒልም ደረጃ ላይ ቢደርስ ከዛ በላይ ለላኢላሃ ኢልለላህ ብሎ መስዋእት ቢሆን በደረጃ ከገጠር መጥቶ ካመነው ሶሓብይ ጋር አይገናኝም ። የሶሓብይነት ደረጃ ማንም ላይደርስበት በሩ ተዘግቷል ። እነዚህን አላህ የመሰከረላቸው ብርቅዬ የነብዩ ባልደረቦችን መተቸትና ክብራቸውን መንካት የመጨረሻው ደረጃ ሙብተዲዕ ያደርጋል ።
7 294
~~
በጣም አሳዛኝና ትምርት ሰጭ ታሪክ ❗
__
ኢምራን ኢብኑ ሓጧን ታላቅ ሰው ነበር ❗
ከእለታት አንድ ቀን የሆነችን የኸዋሪጅ አመለካከት ያለባትን ሴት ወደዳትና ለማግባት ፈለጋት ❗
ሰዎች - ተው ይች ሴት ትቅርብህ ❗ ምክኒያቱም እሷ የኸዋሪጅ አመለካከት አለባትና አሉት ❗
ነገር ግን የሴትዮዋ ውበት ስለሸወደው ሊሰማቸው አልቻለም አግብቼ አስተካክላታለሁ ብሎ አገባት ❗
ከዚያም በሚያሳዝን ሁኔታ ቀስበቀስ እሷ ወደ ኸዋሪጅ አመለካከት ቀየረችው ❗
ኢምራን ድብን ያለ ኸዋሪጅ ሆነ ❗
እድለቢሱ አብደራህማን ኢብኑ ሙልጂም የተባለው ሰው ታላቁን የረሱል ኸሊፋ አሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብን በገደላቸው ጊዜ ይህ ኢምራን ኢብኑ ሓጧን በዚህ ግድያ ተደስቶ ገዳዩን በማወደስ የደስታን ግጥም እስከመግጠም ደረሰ ❗
ወላሂ ትልቅ ትምህርት ነው ለሱና ወንድምና እህቶች ❗ አደራ አደራ እላችዋለው የሱና ሰው ካልሆነ እንዳታገቡ አንተም እንደዛው የሱና ሴት ካልሆነች እንዳታገባ ! ለዚህም ነው ረሱላችን "ዲን ያላትን መርጠህ አግባና እድለኛ ሁን" ያሉት ❗
አይ አግብቼ አስተካክላታለሁ ! ወይንም አግብቼ አስተካክለዋለሁ የሚል ሰይጣናዊ አመለካከት እንዳይሸውዳችሁና የኢምራን ኢብኑ ሓጧን እድል እንዳይገጥማችሁ❗አንተ እሷን የማስተካከል ዋስትና እንደሌለህ ልታውቅ ይገባል ! አንቺም እንደዛው !
የተወሰደ🙌
https://t.me/Abu_Umer1
https://t.me/Abu_Umer1
7 294
ለተሚዩ ኢብኑ ሙነወር
ኢብኑ ሙነወር የተመዩዕ ዋሻ ውስጥ ሳይገባ በፊት ስለ ፎቶ ያለውን አቋም ስሙት
ዛሬ ኢጅቲሃዲይ ነው ብሎ እራሱ ሚጮህበትን የፎቶ ርእስ ትናንት ምን ሲል እንደነበር ከራሱ አንደበት አድምጡን
በዲን ላይ ከመገለባበጥ አላህ ይጠብቀን
https://t.me/Ibnu_abu_habib
