es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

ዮሳብ

ዮሳብ

Ir al canal en Telegram

Channel Description: Welcome to our channel, where we dive into the fascinating world of psychology! Here, you'll find insightful tips and practical advice to enhance your mental well-being and understand human behavior.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
220
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-330 días
Archivo de publicaciones
የምንወደው ወጥመድ ነገሩ እንዲህ ነው። ሰው መቼም ሲፈጠር ባዶነቱን የሚሞላለት፣ ልቡን የሚያሞቅለት ነገር ይፈልጋል። እናም ይወዳል—ሰውን፣ ንብረትን፣ ምቾትን፣ አልፎ ተርፎም የራሱን አስተሳሰብ። መው
የምንወደው ወጥመድ ነገሩ እንዲህ ነው። ሰው መቼም ሲፈጠር ባዶነቱን የሚሞላለት፣ ልቡን የሚያሞቅለት ነገር ይፈልጋል። እናም ይወዳል—ሰውን፣ ንብረትን፣ ምቾትን፣ አልፎ ተርፎም የራሱን አስተሳሰብ። መውደድማ መታደል ነው፤ አለምን የምናይበት መነፅራችን፣ የህይወታችን ጨው ነው። ነገር ግን ይሄው መውደድ ድንበር ሲያጣ፣ "ያለ እሱማ ህይወት የለችም" ወደሚል የልብ ስደት ሲቀየር ነገሩ መልክ ይቀይራል። ገርም እኮ ነው! ነፃነቱን ለማግኘት የአለምን ጦርነት ሁሉ ሊጋፈጥ የሚችለው ያ ጀግና ሰው፣ የሚወደው ነገር ሲመጣ ግን በገዛ እጁ ማርኮኛነቱን ያውጃል። "የወደዱት አይጥፋ" በሚል ሰበብ፣ የልቡን ቁልፍ አሳልፎ ይሰጣል። ነፃነቱን አቅልጦ፣ ህይወቱን አስይዞ ለዚያ ለሚወደው ነገር ይገብራል። በገዛ ፈቃዱ የወርቅ ቀፎ ሰርቶ፣ "እባክህን ዝጋብኝ" ብሎ ቁልፉን ለሌላ አካል ይሰጣል። ታዲያ ያኔ ነው ፈተናው የሚጀምረው። የያዝነው መስሎን ተይዘን እንቀራለን። መውደዱ ወጥመድ ሲሆን፣ እንደ ማር ወለላ የጣፈጠን ነገር እንደ እሬት መራራ መሆን ይጀምራል። "ላለመተው" ስንል ስንት የማንፈልገውን እንቀበላለን? ስንትስ የህሊና ዋጋ እንከፍላለን? ሰው የሚወደውን ላለማጣት ሲል ራሱን ሲያጣ ማየት ያኔ የተለመደ ይሆናል። ለካስ እውነተኛ መውደድ ማሰር ሳይሆን መልቀቅ፣ መሰዋት ሳይሆን ማኖር ነው! ለዚህ እኮ ነው አሁንም ጸሎታችን መሆን ያለበት፦ "ፈጣሪ በምንወደው ነገር አይፈትነን፤ የልባችን መውደድ የህይወታችን ወጥመድ ሳይሆን፣ የበረከታችን መንገድ ይሁን። ✍Andualem (ዮሳብ)

ሰው በዓይኑ ያየውን ማድነቅ ካልቻለ ጤነኛ ልብ አለው ለማለት ይከብዳል። እኔም ጤነኛ ነኝና ያንን ሁሉ ውበት አይቼ ዝም ልል አልቻልኩም። ነገር ግን የእሷ ነገር ለየት ይላል፤ የውበቷ ግርማ ብቻ ሳይ
ሰው በዓይኑ ያየውን ማድነቅ ካልቻለ ጤነኛ ልብ አለው ለማለት ይከብዳል። እኔም ጤነኛ ነኝና ያንን ሁሉ ውበት አይቼ ዝም ልል አልቻልኩም። ነገር ግን የእሷ ነገር ለየት ይላል፤ የውበቷ ግርማ ብቻ ሳይሆን ያ የተለማመደችው የዝምታዋ ፀዳል ራሱ ልብን ቆልፎ በፍቅር ማዕበል ውስጥ ጠልፎ የሚጥል እረኛ ሆነብኝ። አንዳንዴ ራሴን እታዘበዋለሁ። "ለመሆኑ ወድጃት ይሆን?" ብዬ ራሴን ስጠይቅ፣ መልሱን ለማመን ይከብደኛል። ልብ ፍቅርን ቀድማ ትረዳዋለች ይባላል፣ አእምሮ ግን ለማመን ጊዜ ይፈጃል። ያ ጣፋጭ መረበሽ፣ ያ ራስን የመጠራጠር ስሜት... እውነትም የፍቅር መጀመሪያ መሆኑን አሁን ተረዳሁት። ለመሆኑ ግን እንዴት አይነት አፈጣጠር ነው? የአይኖቿ ማማርማ ሌላ ዓለም ነው—ሰውነቷን ሳያዩ ዓይኗን ብቻ አይቶ መቅረት ይቻላል። የከንፈሮቿ ቅላት፣ የጥርሶቿ ንጣቱማ ፈገግ ስትል ጨለማን የሚገፍ ብርሃን ይመስላል። ያረማመዷ ውበት፣ ያ የእርምጃዋ ቃና ደግሞ የመሬቱን ስበት ራሱ የሚገዳደር ያህል በእርጋታና በውበት የተሞላ ነው። በቃ ምን ልበልሽ? ሁሉ ነገሯ ደምቆ መታየቱ እጅግ ያምርባታል። እኔ ግን አሁንም በዝምታዋ እሥር ቤት ውስጥ ሆኜ፣ .....ይቀጥላል ✍ዲ/ን Yosab ግንቦት 14/09/2018ዓ.ም