es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

ዮሳብ

ዮሳብ

Ir al canal en Telegram

Channel Description: Welcome to our channel, where we dive into the fascinating world of psychology! Here, you'll find insightful tips and practical advice to enhance your mental well-being and understand human behavior.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
220
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-330 días
Archivo de publicaciones
ከሶፊያ ጋር በቴሌግራም በኩል የምናደርገው ውይይት እንደተለመደው በጨዋታና በሳቅ የተሞላ ነበር። ሳይታሰብ ግን ውይይቱ ወደ ጠለቅ ያለ የሕይወት ጥያቄ ውስጥ ገባ። «በጊቢ ውስጥ በጣም የሚያስቸግርህ
ከሶፊያ ጋር በቴሌግራም በኩል የምናደርገው ውይይት እንደተለመደው በጨዋታና በሳቅ የተሞላ ነበር። ሳይታሰብ ግን ውይይቱ ወደ ጠለቅ ያለ የሕይወት ጥያቄ ውስጥ ገባ። «በጊቢ ውስጥ በጣም የሚያስቸግርህ ነገር ምንድን ነው?» ስትል ጠየቀችኝ—መልሴ የት እንደሚያደርሰን እንኳን ሳታውቅ። ሳልወዛገብ ፈጣን መልስ ሰጠኋት፦ «ገንዘብ ነዋ!» አልኳት፥ ከቃላቶቼ ጀርባ ያለውን እውነታ በሳቅ እያሸሸግኩ። 😂 እሷም በበኩሏ የሁኔታውን ውስብስብነት ተረድታ በሳቅ ታጀበችኝ፦ «😁😁😁 ይሄማ ... የሁላችንም እኮ ነው!» ነገር ግን ከገንዘብ እጥረት ይልቅ ከበድ ያለ ሌላ እውነት አእምሮዬን ይረብሸው ነበር። ውይይቱን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዝዞርኩት፦ ... ነፃነት!» እኔ ነፃነት ነው የሚፈትነኝ .. በሞባይሏ ስክሪን ላይ የላክሁላትን መልእክት ስታነብ ግራ መጋባቷ ታወቀኝ፦ «ነፃነት የለም እንዴ እዛ?» 😳 «ማለቴ... የእኔ ትልቁ ፈተና ነፃነት ነው» አልኳት፥ ቃላቶቼን በጥንቃቄ እየመረጥኩ። እሷ ግን አልተዋጠላትም። የእኔን አባባል የራሷ በሆነ መንገድ ተረጎመችው፦ «ስታጣው ነው እንጂ... አግኝተኸው ነዋ!» (አጣሁት የምትለው እኮ አግኝተኸው ነበር ለማለት ነው በሚል እምነት)። እኔ ግን የፈለግኩትን አልተረዳችኝም ነበር። በችኮላ መልስ ላክሁላት፦ «ሶፍ... እኔ እኮ ጨርሶ አላገኘሁትም!» የበለጠ ግራ ተጋባች። ጥያቄዋም ይበልጥ እየሳለ መጣ፦ «ታዲያ ሳታገኘው እንደነበረህ/እንዳገኘኸው አድርገህ ለምን ታስባለህ?» አሁንም የገባችበት መንገድ ስህተት እንደሆነ ልነግራት ሞከርኩ፦ «እኔ እኮ እንደዛ አላሰብኩም!» ውይይቱ ወደ ፈላስፋዎች ሙግት እየተቀየረ መጣ። ሶፊያ አልተመለሰችም፦ ህልም? የጊቢው ሕይወት እንቆቅልሽ እያበቃ አይደለም...

https://www.youtube.com/channel/UC-Ncaovv8nC8o_4cc9_0SeQ Let's go subscriber eyargachu abretatut🙏

አንዳንድ ቀናት አሉ—ዝም ብለው የሚያልፉ ሳይሆኑ፣ ልክ እንደ ሰው «ለመሆኑ ወዴት እየሄድክ ነው?» ብለው የሚጠይቁን ። ዛሬ እንደዚያ ያለች ቀን ናት። የት ደርሼ፣ በየትኛው የሕይወት ምዕራፍ ላይ ቆ
አንዳንድ ቀናት አሉ—ዝም ብለው የሚያልፉ ሳይሆኑ፣ ልክ እንደ ሰው «ለመሆኑ ወዴት እየሄድክ ነው?» ብለው የሚጠይቁን ። ዛሬ እንደዚያ ያለች ቀን ናት። የት ደርሼ፣ በየትኛው የሕይወት ምዕራፍ ላይ ቆሜ እንደሆነ እንኳ ማወቅ አልቻልኩም። የሚገርመው ግን ፍላጎቴ ወዴት እንደምሄድ ማወቁ ላይ አይደለም፤ ይልቁንስ ስለዚች ስለ መዳፌ ላይ ስላለችው «ዛሬ» እንዴት አድርጌ እንደማወራ ማየቱ ነው የናፈቀኝ። ነገ ተነስቼ ስለ ዛሬ ማንነቴ ስተርክ... እንደ ትላንቱ ሳቅና ደስታዬ በፈገግታ ይሆን? ወይስ በቁጭት አፍን በሚያስይዝ ትንፋሽ? ልቤን የሚሞግተው ዋናው ጥያቄ እርሱ ነው። ለመሆኑ ዛሬ... ለነገዬ መሠረት የምጥልበት፣ ወደ ሕልሜ የምቀርብበት ማታ ተኝቼ ስታሰበው የሚያኮራኝ ቀን ነው? ወይስ ደግሞ «አሁንም ሌላ ቀን አባከንኩ» ብዬ በቁጭት እጄን የምነክስበት? አልያም ደግሞ ከትላንት የተኮረጀ፣ አዲስ ነገር የሌለው፣ ያው ሁልጊዜ የምደግመው አሰልቺ ድግግሞሽ? አላውቅም። ብቻ ማወቁን እጅግ ተጠምቻለሁ። ነገ ሆይ... ለመሆኑ በዚያ በሩቅ አድማስ ላይ ቆመህ እኔን እንዴት ታየኝ ይሆን? እንደ አሸናፊ? እንደ ታጋይ? ወይስ ዝም ብሎ በጊዜ ማዕበል እንደሚነዳ ምስኪን ተጓዥ? 🤔😄

ምንድ ነው አግቡ በቃ እኛም እናግባበት 😁

“አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።

መሸነፍን አላውቀውም የሚል ሰው ካለ፡ አልኖረም። መሸነፍ… ስሙ ሲጠራ ደረት ላይ ተጭኖ የመተንፈስ አቅምን የሚያጥር፣ አንገትን የሚያስደፋ፣ ይባስ ብሎ ደግሞ ልብን እንደ መስታወት ቀስ አድርጎ የሚሰብር ከባድ ስሜት ነው።

16 አመቴ ምድር ላይ እኔ—አንዱአለም (ዮሳብ)—ከህፃናት በላይ የምወደውና ልቤን የሚገዛው ምንም ነገር የለም። ለህፃናት ያለኝ ፍቅር እንዲሁ በድንገት የበቀለ አይደለም፤ ሥር የሰደደው ያኔ በልጅነት
16 አመቴ ምድር ላይ እኔ—አንዱአለም (ዮሳብ)—ከህፃናት በላይ የምወደውና ልቤን የሚገዛው ምንም ነገር የለም። ለህፃናት ያለኝ ፍቅር እንዲሁ በድንገት የበቀለ አይደለም፤ ሥር የሰደደው ያኔ በልጅነት ዘመኔ፣ ከእኩዮቼ ጋር አብረን በቦረቅንባቸው ወርቃማ ቀናት ውስጥ ነው። ያኔ... በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ አብረን ስንማማር፣ ስንጫወትና ስናገለግል የነበረን ጊዜ ዛሬም ድረስ በትዝታ ማዕበል ውስጥ ያናውጠኛል። ገና በለጋ ዕድሜያችን የመንፈሳዊው አገልግሎት ፍቅር በውስጣችን እንደ እሳት ነደደ። ለሌሎች ልጆች መጫወቻ መኪና፣ ሽጉጥ እና "ዕቃቃ" መጫወት የዘወትር ተግባራቸው በነበረበት በዚያ የልጅነት ዘመን፣ ለእኛ ግን ጨዋታችንም፣ ደስታችንም ሌላ ነበረ። መዝሙሩ፣ ቅዳሴው፣ ሱባኤውና ጾሙ... እርሱ ነበር የልጅነታችን ማጫወቻ፤ እርሱ ነበር የነፍሳችን ማረፊያ። ታዲያ ዘመናት ነጎዱ። እኔም አድጌ ዕድሜዬ 16 ዓመት ሲሞላ፣ በዚያው ባደግኩበት ቅዱስ ስፍራ የህፃናት ተጠሪ ለመሆን በቃሁ። ያኔ ነው እንግዲህ... ለህፃናት ያለኝ ፍቅር ከስሜት በላይ ሆኖ፣ በደም ስሮቼ ውስጥ የሚፈስ ሕይወቴ የሆነው!

ዛሬ ግን ደስ ይላል ! 😊 አዎ ✅

ሰማዩ ዛሬ ለየት ያለ የብርሃን ልብስ የለበሰ ይመስላል። ወፎቹም ዜማቸውን የቀየሩት፣ ንፋሱም በለሰላሳ ድምፅ በጆሯችን የሚያንሾካሹከው የአንድን ድንቅ ሰው መምጣት ለማበሰር ይመስላል። የልጅ አዋቂ፣
ሰማዩ ዛሬ ለየት ያለ የብርሃን ልብስ የለበሰ ይመስላል። ወፎቹም ዜማቸውን የቀየሩት፣ ንፋሱም በለሰላሳ ድምፅ በጆሯችን የሚያንሾካሹከው የአንድን ድንቅ ሰው መምጣት ለማበሰር ይመስላል። የልጅ አዋቂ፣ እግዚአብሔርን ማገልገልን የህይወቷ ትልቅ ሀብትና ገንዘብ ያደረገች ልዩ ሴት... ዛሬ በእምነት ልደቷ ነው። ሌላ አዲስ አመት፣ ሌላ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ልትጀምር የደስታዋን ሻማ ፈገግ ብላ ታበራለች። እድሜ ማለት ዝም ብሎ የቁጥር መደመር ብቻ አይደለም፤ በውስጡ ብዙ ሳቆችን፣ ውብ ትዝታዎችን፣ የህይወት ውጣ ውረዶችንና መሳጭ ትምህርቶችን የሰፋንበት ውድ የህይወት ጨርቅ ነው እንጂ። በቅዱስ ሚካኤል ጥላ ስር የበቀለች አበባ ከልጅነቷ ጀምሮ በቅዱስ ሚካኤል ቤት ስትመላለስ፣ ስታገለግል ያሳየችው ቅንነት፣ የልቧ ንፅህና እና በዙሪያዋ ላሉት ሁሉ የምታካፍለው መልካም እምነት ዛሬ ለምታከብረው ልደት ትልቅ ግርማ ሞገስ ሆኗታል። እምነቷ ውበቷ ነው፤ ደግነቷ ደግሞ መለያዋ። አንዳንድ ሰዎች ወደ ህይወታችን ይመጡና ህይወት ምን ያህል ውብ ልትሆን እንደምትችል በተግባር ያሳዩናል። ለእኛ የዚያች ውብ ህይወት ማሳያና ምስክር ናት። እንኳን ተወለድሽልኝ! መልካም ልደት! ዘመንሽ በደስታ፣ በሰላም፣ በቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና በሙሉ ጤና ይሁን !

የኔታ ቀደመውን ከደረሱ በቃ አበቃልን አቤት ሩጫ! 🥹

+6
መድሎተ ዓሚን አድማሱ ጀንበሬ (1).pdf5.99 MB

ሰው የሚባለው ፍጡር የሚደክምበት ምክንያት ቢቆጠር አያልቅም። አንዳንዱ ዝናን ያሳድዳል፣ ሌላው በሚሊዮኖች አሃዝ የሚለካ ብር ፍለጋ እንቅልፍ ያጣል። አንዳንዱ የልብ አጋር ፍለጋ ማይሎችን ያቋርጣል፣ል
ሰው የሚባለው ፍጡር የሚደክምበት ምክንያት ቢቆጠር አያልቅም። አንዳንዱ ዝናን ያሳድዳል፣ ሌላው በሚሊዮኖች አሃዝ የሚለካ ብር ፍለጋ እንቅልፍ ያጣል። አንዳንዱ የልብ አጋር ፍለጋ ማይሎችን ያቋርጣል፣ልክ እንደ እኔ😁 ሌላው ደግሞ ክብርን ፍለጋ አንገቱን ቀና አድርጎ ይውላል። ግን ቆም ብለን እውነቱን እንነጋገር ከተባለ... ማንም ምንም ቢመኝ፣ ጉዞው ሁሉ ተጉዞ የሚደመደመው በአንድ መስመር ላይ ነው፤ እሷም "ደስታ" ትባላለች። ታዲያ ወገን የዚህ ሁሉ ትንቅንቅ፣ የዚህ ሁሉ ልፋት መጨረሻ ምን እንደሆነ ልንገራችሁ ። አንድ ስስ ፈገግታ! አዎ... በሚሊዮን ብር፣ በታላቅ ዝና እና በክብር መሀል የምትፈጠር፣ ጥርስን የምታሳይ አንዲት ሳቅ ። ሰፊው አለም የጠበበው፣ ትልቁ ሰው የደከመው ለዚችው ለአፍታ ፈገግታ ነው ..ማነሽ ውይ ማነህ አይደለም እንዴ ? አንዳንዶች ይህንን የህይወት ሂሳብ ሲያሰሉ "ለዚች ለጥቂት ሰከንድ ፈገግታ ይህን ያህል ዋጋ ከመክፈልስ ቢቀርስ?" ይላሉ። እኔ ግን አልደግፋቸውም። ህይወት ያለ ደስታ ምንድናት? ባዶ የሸክላ እቃ! ስለዚህ ደስታን ፍለጋ ዋጋ መክፈሉ አይቀሬ ነው፤ ይልቁኑስ ለሷ የበለጠ ዋጋ መክፈል ይገባል። ግን... አንድ ትልቅ ነገር አለ ወግን . የማይቋረጥ ደስታ አለ እሱም ለኔ .......የናተንም ፈልጉ ። ዋናው ቁምነገር ያለው ግን እዚህ ላይ ነው፡ የምንከፍለውን ዋጋ እንወቅ! ለደስታችን የምንከፍለው ዋጋ እራሳችንን፣ ሰብአዊነታችንን እና ሌሎችን የሚያጠፋ መሆን የለበትም። ንጹህ ደስታ ንጹህ መንገድ ትፈልጋለችና። አይደለም እንዴ ? yosab ng share adergut

ወገን አባቴ አኮራኝ 💪 እንኳን ደስአለህ ዲያቆን
ወገን አባቴ አኮራኝ 💪 እንኳን ደስአለህ ዲያቆን

ለመሆኑ እሱን ብቻ ነው "Electrical & Computer Engineering" የጨረሰ የሚመስለው? ያንን ክንዱን አጥፎ ያሳየንን ጡንቻ እዩትማ! 😂 ወገን እንዲህ በፈገግታ ሲፈጥን ስታዩት ዝም ብ
ለመሆኑ እሱን ብቻ ነው "Electrical & Computer Engineering" የጨረሰ የሚመስለው? ያንን ክንዱን አጥፎ ያሳየንን ጡንቻ እዩትማ! 😂 ወገን እንዲህ በፈገግታ ሲፈጥን ስታዩት ዝም ብሎ የመጣ ይመስላል? በፍጹም። ስንት ሌሊት በኮዲንግና በ circuit ዲዛይን አእምሮው ሲቀቀል፣ ስንት "error" እምቢ ብሎት ሲጨነቅ፣ 0 plan coffee night ላይ ሲያወጋን ሰምተናል😂 አንተ ጀግና፣ ዛሬ ያደረግከው ነገር ኩራት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ወኔ ነው ያሳየኸው ። ከአሁን በኋላ በአለም ላይ የምታገናኘው ኔትወርክ ሁሉ የስኬትና የሀብት ብቻ እንዲሆን እመኛለሁ። እና ቀጣይ ደግሞ Master's(ማስትርስህ) gf እነደምትሆን አልጠራጠርም 😁 እናደግሞ airforce እንገዛልሃለን 😁 እንኳን ደስ አለህ ወንድምዓለም! ዛሬ ያንተ ቀን ናት፣ ፈታ በልባት!

Repost from N/a
              ይህ ስነ ግጥም  .......ከምርጦቹ ለአንዱ ነው                ወጣቱ    በረሮ ባለ ብዙ ስሞች  ባለ ብዙ ሃብት ባለ ብዙ ጸጋ  ያለው በረከት አቤት ይሄኛው ሰው ምን አይነት  ፍጡር ነው? እንዲሁ በአይን ብቻ፣ እንዲው በእይታ የሚወደደ ሰው።             ወጣትን ከሰው በረሮን  ከነፍሳት             አሟልቶ ያደለው  አለም የትስ አላት?            ወጣቱ በረሮ ብዬ ስም ሰጠውት          ከእለታት  በ1ዱ ቀን ፣ እድለኛ ሆኜ  ስላገኘውት። እድለኞች ነን ሰዎች አስተዉሉ ወጣቱ በረሮ በመሃላችን አሉ፣ ያኔ ትዝ ይልሃል ከ3 አመት በፊት ሰልፍ ላይ ሆኖነክ ነው ያየውክ ፊት ለፊት           ሳታውቀኝ ሳላውቅ  "ተመዘገብክ እንዴ?" ብዬ ስጠይቅክ        ለስለስ ባለ ድምጽ  "ባክ አልከፈቱም"፣እንተዋወቅ..?"                                                             ነበር  ያኔ መልስክ        እሺ ብዬ እኔም ጀነን ባለ ድምጽ "ፍጹም" እባላለው፣        እሱም በፈገግታ ብሎ መለሰልኝ "አንዱአለም  የሐረር ሰው"           ኦ ደስ ይላል..." ጭሮን ታውቃታለ?" ብዬ ሳጫውተው           በፈገግታ እያየኝ "አሰበ ተፈሪ ታሪካዊ እኮ ነው"። እንዲ እንዲያ እያልኩኝ ተዋወኩላቹ ወጣቱ በረሮ  አለ ከጎናቹ። ባለ ብዙ ስሞች ብለን  ስንነሳ "አንዱ" አስቀድመን ፣ዮሳብን ፣One ን፣            ጭሌውን  ፣ወጣቱን.....አንርሳ። ባለብዙ  ጸጋ ብለን ስንቀጥል አይደራደርም  በቅዱስ ሚካኤል ፣ ቢናግሮ ተደማጭ፣  ቢጽፍ ሚነበብ እንዲ ያለ ፀጋ እንዴት ይገኝ ይሆን በሌላ ሰው ልብ።               ደግሞም  ወረድ ብሎ  ትንቹ ዘማሪ                ከቤቱ ማይጠፋ ከቤቱ ማይጠፋ የሳይኮ ተማሪ ። አረ  ይህ ሰውዬ አስቀናኝ በሃብቱ፣ ሁሉን አሟልቶ ነው የቸረው አምላኩ የታደለች ማህጸን አንተን ያፈራች ሊያውም እኮ ነው  ብኩርና መስራች።                    አንተ የኔ አስተዋይ ትንሹ ፈላስፋ               በብዙ ነገሮች ነው የሚታይብ ተስፋ። አንዳዴ ወጣት፣ አንዳዴ በረሮ እንዴት አልክልኝ ተመቸክ ወይ ኑሮ?      ነክ እኮ መካሪ ከልብ በአስተውሎት      ደግሞም ቆፍጣና እንደ ነብር ወጣት      በረሮም ነክ እሺ  ሊያውም ትንሽዬው      "እሺ" ብሎ ታዛዥ ለማንኛውም ሰው። ገጣሚ እንኳን አይደለውም  ግን ሞነጫችራለው ሃሳብ አስታየታቹን እባካቹ  ተቹኝ                                         

እድለኛ ነኝ፤ ካደግኩበት አጥር ይልቅ የአጥሩ ጠባቂ ይበልጥ ይገዝፋል። እኔ ያደግኹት ተራ ቤት ውስጥ አይደለም—በመልአኩ ቤት እንጂ! ስለ እርሱ በቃላት ተለክቶ፣ በባለቅኔዎች ስንኝ ተቋጥሮ የማያልቅ
እድለኛ ነኝ፤ ካደግኩበት አጥር ይልቅ የአጥሩ ጠባቂ ይበልጥ ይገዝፋል። እኔ ያደግኹት ተራ ቤት ውስጥ አይደለም—በመልአኩ ቤት እንጂ! ስለ እርሱ በቃላት ተለክቶ፣ በባለቅኔዎች ስንኝ ተቋጥሮ የማያልቅ ልዩና ጥልቅ ፍቅር በውስጤ አለ። ይገርማችኋል... በሄድኩበት ስፍራ ሁሉ ስሙ በድንገት ሲጠራ ከሰማኹ፣ አንዳች የማይታወቅ ሰማያዊ የደስታ ስሜት መላ ሰውነቴን ውርር ያደርገዋል። ያኔ ልቤ በኩራትና በደስታ ትሞላለች። ግርም የሚለኝ ነገር ግን የትም ብሄድ መልአኩን አላጣውም። እርሱ ሁልጊዜ ቀድሞኝ ይደርሳል። ለትምህርት ካደግኩበት የትውልድ ቀዬ ወጥቼ ወደ ለምለሚቷ የዲላ ምድር እንኳን ብገባ፣ እዚያም "እኔ አለሁልህ" የሚለኝን የዲላ ሚካኤልን አገኘሁት። ከፍ ብሎ ከሞላ ይታያል ሚካኤል... በየመንገዴ ስሙን እየጠራሁ ያልቀለለኝ የሕይወት ሸክም፣ ያልተመለሰልኝ የልብ ጸሎት የለም። መቼም ቢሆን ጥሎኝ አያውቅም። መልአኩ በጣም ቅርቤ ነው፤ ስለ እኔ የሚጨነቅ፣ ከእኔ በላይ ለእኔ የሚሳሳልኝ፣ የዋህ፣ ትሑትና ሰውን ወዳጅ መልአክ! ሁልጊዜ በቤተመቅደሱ ስመላለስ፣ በገናው ሲደረደርና ማኅሌቱ ሲቆም ልቤን በደስታ የሚሞላው አንድ መዝሙር አለ። “ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው...” የሚለው። በተለይ ደግሞ ይቺን ስንኝ ስሰማ መንፈሴ ረጭ ይላል፦ “በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ አለሁ እስከ ዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ፤ ዛሬ ላለሁበት ማንነቴ ምስክሬ እርሱ ነው። ከታናሽነቴ ጀምሮ በፍቅሩ የጠበቀኝ፣ በቸርነቱ የመገበኝ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ክንፎቹን ዘርግቶ ያዳነኝ መልአክ... ቅዱስ ሚካኤል ነው! እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆቼ ! ዲ/ን አንዱአለም (yosab)

የሰው ልጅ በምድር ላይ ከጀመራቸውና እስካሁን ካልጨረሳቸው ትልልቅ ጦርነቶች አንዱ ምንድን ነው ቢሉ? “የኪስ እና የልብ ፍልሚያ” እላለሁ። ባለፈው ዝናባማ አመሻሽ ታክሲ ውስጥ ተሳፍሬያለሁ። ከመቀመጫዬ ጀርባ ሁለት ወጣቶች በቁጭት ይወያያሉ። አንደኛው በጥልቅ ትንፋሽ፣ “ኧረ ለመኖር ራሱ ‘ስፖንሰር’ የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ ደረስን እኮ!” ይላል። ሌላኛው ደግሞ፣ “ምን ይሄ ብቻ! አሁን እኮ ፍቅር ራሱ ‘ሜጋ ባይት’ እና ‘ካርድ’ ካልመገብከው አይንቀሳቀስም” ብሎት አረፈው። ሳቅኩኝ… ግን እውነት አለው። ድሮ ድሮ ፍቅር “እንጀራ እጋግርልሃለሁ፣ ውሃ እቀዳለሁ” በሚል የጉልበትና የልብ ስምምነት ነበር የሚመራው። ዛሬ ግን ልብህ የፈለገውን ያህል ቢመታ፣ ኪስህ ካልመታ “ፍቅር” የሚባለው መተግበሪያ ‘Network Error’ እያሳየ ያንገላታሃል። ነገሩ ግን በዚህ አያበቃም። በአሁኑ ጊዜ እኛ የሰው ልጆች ቴክኖሎጂን እንቀልባለን ስንል፣ እሱ መልሶ እየቀለበን ይመስላል። ስልካችን ባትሪ 10% ሲቀረው የሚይዘን ጭንቀትና ፍርሃት፣ የነፍሳችን ነገር ለአፍታም ቢሆን ጠፍቶብን የሚያውቅ አይመስልም። መንገድ ላይ ስንሄድ ሁላችንም አንገታችንን ደፍተናል። የሚገርመው ግን ወደ አምላክ የምንጸልይ መስለን፣ የምንሰግደው ግን ለስማርት ስልካችን መሆኑ ነው። ይህ ሁሉ ውክቢያና የኪስ መድረቅ መኖሩ ባይካድም፣ የሰው ልጅ ግን አሁንም የሚገርም ፍጡር ነው። በጭንቀት መሃል ሳቅን መፍጠር ይችላል። በባዶ ኪሱ “ነገ ሌላ ቀን ነው” ብሎ የመተኛት፣ በማለዳው ደግሞ “ዛሬ ይስተካከላል” ብሎ የመነሳት ልዩ ‘ሱፐር ፓወር’ አለው። ሕይወት እንደ ወፍራም መጽሐፍ ናት። እያንዳንዱ ቀን ደግሞ አዲስ ገጽ ነው። ዛሬ ያነበብነው ገጽ አሰልቺ ወይም አሳዛኝ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ቀጣዩ ገጽ ምን ይዞ እንደሚመጣ ሳናውቅ መጽሐፉን መዝጋት የለብንም። ፡ ባዶ ኪስ ጊዜያዊ በሽታ ነው፤ ባዶ ልብ ግን ዘላቂ ድህነት ነው። ስለዚህ ኪሳችን እስኪሞላ ድረስ፣ ልባችንን በደግነት፣ በሳቅና በተስፋ ሞልተን እንቆይ! ✍ yosab

ጊዜ እድል የሰጠው እግሩን አሳቅሎ የሚቀመጥ ለቦርጩም ምቾት ሲል ዘርጠጥ ብሎ የሚቀመጥ ድብልብል ሰውዬ አደለም ይሉቁኑ ከምርም ጊዜ እድል የሰጠው ሰው ለደስታው ዘግይቶ ትላንት ያልተሻማው ለመቆጨት ጊዜ ዘግይቶት ያልከፋው ለመሻቱ መሆን ዛሬ የገባው ነው። ከሁሉ በላይ ደሞ የጊዜውን ጌታ ያከበረ ነው🙏

Mee koottu, waa'ee hiyyummaa xinnoo haa mari'annu. Yeroo baay'ee hiyyummaa yommuu jennu, hiyyummaa maallaqaa ykn kan qabeenyaa qofa natti fakkaata. Garuu hiyyummaan hundarra hamaan hiyyummaa sammuu ti! Maaliif seete? Namni qabeenya dhabe carraaqee, hojjatee hiyyummaa keessaa ba'uu danda'a. Namni sammuun hiyyome garuu, hiyyummaa sana keessaa ba'uuf carraan inni qabu baay'ee dhiphaa dha; sababiin isaas inni dura of jijjiiruuf iyyuu fedha hin qabu. Garuu beektaa? Dogoggorri keenya inni guddaan fi baay'ee nama miidhu maali? Waan hin beekne akka waan beeknuutti of dhiheessuu fi of amansiisuu dha. "Hunduma profession keessan ani" jedhanii dhaadachuun miidhaa malee bu'aa hin qabu. Egaa, waan tokko beekuun gaarii dha, faayidaas qaba. Garuu achumatti dhaabbachuu hin qabnu; caalaatti beekuuf carraaquun fi tattaaffachuun adda. Hundumaa caalaa immoo, yeroo yeroon of madaaluun, "An meeqa keessa jiran?" jedhanii of gaafachuu fi wantoota gadi fageenyaan hubachuun daran filatamaa dha. Nama jabaa fi guddate kan jedhamu eenyu beektaa? Inni hanqina ofii sirriitti beekee, "Kun hanqina kooti" jedhee amanee, isa sirreessuuf tarkaanfii sirrii fudhatu dha. Kun mallattoo guddina dhugaa ti! Adeemsi kun immoo har'a jalqabamee bor kan dhumatu miti; addaan cituu hin qabu. Sababiin isaas ogummaa fi qajeelummaa barbaaduun, akkasumas amala ofii fooyyessaa deemuun, adeemsa jireenya guutuu ti malee barreeffama harka keessa qabnu kan dhuma qabu miti.