የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
Ir al canal en Telegram
📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
3 466
Suscriptores
+3924 horas
+2267 días
+39330 días
Archivo de publicaciones
3 466
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
➽የቶንኮል ጉድጓድ ስትቆፍር ኣታርቀዉ ራስህ ልትገባበት ትችላለህና ።
➥ጅብና ተኩላ ቀበሮን ለማስገደል ሴራ በመሸረብ ለአንበሳ ሄደው ቀበሮ እኮ አሪፍ ጫማ መስራት ትችልበታለች ለምን ይሆን በባዶ እግሮ እየሄዱ ዝም ያለችው ? ብለው አቃጠሩ !
➸አንበሳም ተናዶ ቀበሮን መፈለግ ጀመረ በመጨረሻም ቀበሮ ጉድጓዷ በር ለይ ተገኘች አንበሳም ትንሽ ከንጎራደደ በኋላ ግርማ ሞጎሱ ተላብሶ ተቀመጠና እንዲህ አለ "ለመሆኑ ምን ያህል ብትኒቅኝ ነው ጨማ መስራት እየቻልሺ በዶ እግሬን ስሄድ እያየሽ ዝም ያልሺኝ " አላት ።
➽ቀበሮም ይህ ጥንስስ ሴራ የጅብና ተኩላ መሆኑን በመገንዘብ እንዲህ አለች "መስራቱንስ እሰራለሁ ነገር ግን ለእርሶ የሚመጥን ደረጃውን የጠበቀ አሪፍ ጫማ ለመስራት ጥሬ እቃው አይገኝም ብዬ ነው " አለች ። አንበሳም እንዲህ በማለት መለሰላት "ነገሩ እንደዛ ነው እንዴ ታዲያ ለኔ የሚሆን ጫማ ለመስራት የሚያስችለው ጥሬ እቃው ከምንድንነው የሚገኘው " በማለት በለሙያዋን ቀበሮ ጠየቃት ቀበሮም "ከጅብ ቆዳና ከተኩላ ጅማት ነው "አለች ። ይህኔ አንበሳም ጅብንና ተኩላን እየተመለከተ የኔ ጫማ መሰራት ስላለበት እናንተ መሞት አለባችሁ በማለት ነገራቸው በውጤቱም ጅብና ተኩላ ተገደሉ።
➨ከዚህ አስተማሪ ታሪክ የምንማረው ፦
➢ጅብና ተኩላ የተገደሉት ሴራን ማሴር የጀመሩ ግዜ ነው
መገደላቸውን ያወቁት ደግሞ የሴራቸው ውጤት ተፈፅሞ ለማየት በመጓጓት ቦታውን በተገኙበት ሰዐት ነው ።
➥ሴረኞች የሴራቸው ውጤት እራሳቸው ጋ እንደሚመለስ ቢያውቁት ኖሮ በሌላ ሰው አያሴሩም ነበር ስለዚህ ነው በሁሉም ሴረኞች ስግብግብነትና ድንቁርና የሚስተዋልባቸው ።
ሴረኛ ከሳሾች የተከሳሽን መልስ ቢያውቁ ኖር በተንኮል ለመክሰስ ከቤታቸው አይወጡም ነበር ነገር ግን በሴረኝነታቸው የተነሳ ከተንኮል ውጪ ምንም የማያውቁ ፀሐይና ዝናም የማይፈራ የተጋደመ ግንድ ናቸው ።
➧በሌሎች ለይ መጥፎ ናፋቂ ምቀኛ እነ ሴረኛ ሆይ እወቅ የስራ ውጤት አንተ ለይ እንጂ ማኑም ጋ አይደርስም ።
ስለዚህ የተንኮል ጉድጓድህን ስትቆፍር ሳትርቅ በቅርብ ቆፍራው የምትገባበት አንተው እራስህ ሊሆን ይችላልና ።
◈◀ قال الله تعالى
{ وَلا يَحِيقُُ المَكْرُ السَّيِّئُ إِلا بِأَهْلِه }
[ فاطر : ٤٣ ]
➸የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል
"የመጥፎ ሴራ ጉዳቱ በባለቤቱ ለይ እንጂ በሌላ በማኑም አይደርስም ።"(ፋጢር 43)
📝ተጨማሪ ትምህርቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም Channeሉን ይቀላቀሉ !
https://t.me/MisbahMohammed_6682
3 466
ውሸትን እንጠንቀቅ!!
———
በተለይ እራሳችን ወደ ሰለፊይነት ያስጠጋን ሰዎች በሐቀኝነት፣ ውሸት አጥብቀን በመጠየፍና በመጠንቀቅ ለሰዎች ጥሩ አርኣያ ልንሆን ይገባል!! የውሸትን ሀራምነትና ፀያፍነት የሚገልፁ የተለያዩ የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃዎች እጅግ በጣም በርካታ ናቸው። ይህ ከመሆኑም ጋር ግን አላህ ይጠብቀንና ብዙዎች በዚህ በሽታ ሲወድቁ ይስተዋላል፣ ይልቁንም ሰዎችን መልካም የሚያስተምሩ "አገሌማ አይዋሸም…" ተብለው የሚገመቱ ሰዎች በማይታሰብ መንገድ ውሸትና ያልተረጋገጠ ወሬ ሲያወሩ በሰማሀው ጆሮህ እስከማፈር ትደርሳለህ።
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ረቢዕ ቢን ሃዲ'ል መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
“በአላህ ይሁንብኝ አንድ ሰለፊይ ይዋሻል ብዬ አዕምሮዬ ላይ መቅረፅ አልችልም!። ለሚስት (በአንዳንድ ከአቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ ለማረጋጋት ሲባል) መዋሸት እንደሚፈቀድ አውቃለሁ፣ ነገር ግን አላደርገውም! ልዋሻት አልችልም። ለወንድ ልጅ (በአንዳንድ አስገዳጅ ሁኔታዎች ለቤተሰቡ፣ለሚስቱና ለልጆቹ) መዋሸት በስሱ የተፈቀደበት ሁኔታ አለ፣ ነገር ግን ወላሂ እኔ በቤተሰቤ ላይ ይህንም ቢሆን አላደርገውም። በእውነት ቢሆን እንጂ አልኗኗራቸውም። እኔ ቤተሰቦቼንም ልጆቼንም የማሳድገው በእውነት ነው፣ አልሀምዱ ሊላህ ምልክቱን (ውጤቱንም) እየተመለከትኩባቸው ነው። ተማሪዎቼንም የማንፀው፣ ሙስሊሙንም ማህበረሰብ በሙሃዶራዎቼና በኪታቦቼ የምመክረው በእውነተኝነት ነው። ከውሸት በማስጠንቀቅ!! በዲናዊና በዱኒያዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አደገኝነቱንም አብራራላቸዋለሁ!!።” [አል-ፉሱል አል'ሙዲየህ ሚን ሲረቲ ሸይኽ ረቢዕ 146-147]
ይህ የሸይኽ ረቢዕ ንግግር ለሚገባው ትልቅ መልእክት አለው!! የአንዳንድ ሰዎች ሁኔታ በጣም ይደንቀኛል!፣ "አይዋሸኝም" ብሎ የሚያስባቸውን ሰው በማስረጃ እስኪይዛቸው ዓይን ያወጣ ውሸት ይዋሹታል፣ በማስረጃ ሲጋለጥ ደግሞ ለራሱ ከኪሱ አውጥቶ በሰጠው ፈትዋ "ከዚህ ከዚህ… አንፃር መስለሃ አለው ብዬ ነው" ብሎ የሌባ አይነ ደረቅ… እንደሚባለው ድርቅ ሲል ይስተዋላል።
ውሸትን እንጠንቀቅ!! ውሸትን እንጠየፍ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ
#join ቴሌግራም ↘️↘️ ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel:
⤵️⤵️https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
3 466
➥ይህ በወራቤ ከተማ አስተዳደር የሰለፊዮች ኢሕሳን መድረሳ ➀ደርሶችና
➁ሙሐደራዎች የሚለቀቁበት ጉሩፕ ነው
➴➴➳➴➴➴➵➴➴
https://t.me/Ehsanmedresaworabe
3 466
📙 عنوان الرسالة: مجمل عقيدة السلف الصالح لشيخ صالح بن فوزان الفوزان
(የሸይኽ ሷሊሃልፈውዛን ሪሳላ የ ሆነችው ሙጅመሉ ዓቂ ደቲ አሰለፍመ አመሷሊህ)
ክፍል አምስት (05)
🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ
📚የኪታቡን pdf ለማግኘት👇👇
https://t.me/ibnbaz1212/66
📆 ዕለተ ጁሙዓ ዙልሂጃ 26, 1447
🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ
የቴሌግራም ቻነል
https://t.me/ibnbaz1212
3 466
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
➽ለረሱላችን ﷺ በኛ ለይ የላቸው ትልቁ ሐቃቸው ◄
صلوا عليه (6) - صلى الله عليه وسلم
https://t.me/MisbahMohammed_6682
3 466
በአላህ ፈቃድ በሌላ ርእስ እመለሳለሁ…
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
3 466
እውነተኛ ሠለፊይ ነኝ ካልክ፣
በቢድዐህ ሰዎች ላይ ትክክለኛ የሠለፎች አቋም ይኑርህ!!
—————
ልብህ የተምይዕ በሽታ ሳይመርዘው ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ያለህን መቀራረብ በፍጥነት አቋርጥ።
አንተ እውነተኛ የሀቅ ተከታይ ከሆንክ ስለ ቢድዐ ሰዎች ጠንከር ያለን ንግግር ስትሰማና ስታነብ አትበርግግ!። ይልቅ በስምህ ወደ ሰለፎች እንደተጠጋህ ሁሉ በተግባርህም ተከተላቸው!!
ብዙ ምስኪን የሆኑ ሰለፊይነትን የሚሞግቱ ወንድም እህቶች በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ከተለያዩ የቢድዐህ ባለ ቤቶች ግንኙነት አላቸው፣ ለዚያም ነው በየ ጊዜው አቋማቸውን የሚቀያይሩና በአቋማቸው መፅናት ሲያቅታቸው የሚስተዋለው። አንድ ሠለፊይ ነኝ ያለ ሰው በምንም መንገድ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር የሚገናኝበትና ንግግራቸውን የሚያደምጥበት መንገድ ሊኖር አይገባም!!። ምናልባት ጠንካራ እውቀት ኖሮት ረድ ሊያደርግባቸው (በስህተታቸው በማስረጃ መልስ ሊሰጥባቸው) አስቦ ካልሆነ በስተቀር ተንኮላቸውን አውቄያለሁ አልሸወድም ብሎ የትኛውም አካል ማድመጥም ሆነ የነሱን ፅሁፍ ማንበብ አይፈቀድለትም!! ትላልቅ እውቀት የነበራቸው ከቀደምቶችም በዚህ ዘመንም ስንቶች ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር ባላቸው መቀራረብና ማድመጥ የተቀየሩ አሉ። ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር በመቀራረብ ሰበብ ከተቀየሩ ቀደምት ሰው አንዱን ልጥቀስ…
የህ ኢብኑ መዒን (ረሂመሁላህ) የቡኻሪ ሸይኽ ናቸው እንዲህ አሉ:-
“ዳውድ ኢብኑ ሚህራን በሀዲስ የታወቀ ሀዲስን የሚፅፍ ሰው ነበር፣ ሀዲሱን ትቶ ከሙዕተዚላህ የሆኑ ሰዎችን ጓደኛ አድርጎ ያዘና አበላሹት።” [ተህዚቡል ከማል ፊ አስማኢ ሪጃል ገፅ 444 እና ተህዚብ አት-ተህዚብ ሊብኒ ሀጀር 3/174]
ታዲያ ኡሱል አስ-ሰላሳን እንኳን አስተካክሎ ያልቀራ ምስኪን በምን አቅሙ ነው የጥመት ባለ ቤቶችን ብዥታ እችላለሁ ብሎ ከስርስራቸው የሚልከሰከሰው?!፣ ታላላቅ የዲን መሪዎች እኮ ናቸው የቢድዐህ ባለ ቤቶችን ብዥታ በመፍራት በሩቁ ይጠነቀቁ የነበረው። የዲን ተማሪ የሆነ ሰው የአህሉሱንና መሻይኾችን ት/ት እየቀሰመ በመተግበር በተቻለው አቅም ሁሉ ለሌሎችም እንዲደርስ ሊያሰራጭ ይገባል እንጂ ማህበራዊ ሚዲያ ቀረበኝ ቀለለኝ ብሎ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በአካል ከስርስራቸው ሊልከሰከስ አይገባም!!
የቢድዐህ ባለ ቤቶችን ድምፅ መስማትም ሆነ ፅሁፍ ማንበብ ሀራም እንደሆነ እያወቀ ወደነሱ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚልከሰከስ ሰው በሰለፊይነቱ ሊጠነክርም ሆነ ሊፀና አይችልም።
ደጋግ ቀደምቶቻችን በቢድዓ ሰዎች ላይ የሚከተለው አይነት አቋም ነው የነበራቸው፣ እውነት ከልብ እነሱን እንከተላለን ካልን በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ ይህ የሠለፎች አቋም ሊኖረን ይገባል!!
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ስለ ቀደሪዮች መከሰትና በቀደር ላይ ያላቸው የተዛባ የፈጠራ አመለካከታቸው ሲነገረው እንዲህ አለ:-
“…እነዚህን ሰዎች ካገኘሃቸው ንገራቸው:- እኔ ከነሱ የጠራሁኝ ነኝ፣ እነሱም ከኔ የጠሩ ናቸው። በዚያ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር በሚምልበት ጌታ (በአላህ) ይሁንብኝ እነዚህ ሰዎች የእሁድን ተራራ ያህል ወርቅ ቢኖራቸውና ሶደቃ ቢያደርጉት በቀደር እስኪያምኑ አላህ አይቀበላቸውም።” [ሙስሊም፣ ነሳኢይ፣ አቢዳውና ትርሚዚይ ዘግበውታል]
በይሀቂይ (ረሂመሁላህ) ስለ ኢማሙ ሻፊዒይ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:-
“ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) በአፈንጋጮችና በቢድዓ ሰዎች ላይ ጠንካራ ነበሩ፣ በነርሱም ላይ ያላቸውን ጥላቻቸውንና ኩርፊያቸውን ግልፅ ያወጡት ነበር።" [መናቂቡ ሻፊዒይ ጥራዝ 1/469]
ኢማሙ አህመድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“አንድ ሰው በሙብተዲዕ ላይ ሰላምታን ካቀረበ እሱ ያንን የቢድዐ ሰው ይወደዋል ማለት ነው።" [ጦበቃቱል ሀናቢላ ጥራዝ 1/196]
ይህ የኢማሙ አህመድ ንግግር የቢድዐ ሰዎችን መውደድ እንደማይፈቀድና ጭራሹኑ እነሱን መዝጋት ተገቢ እንደሆነ አመላካች ነው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይሉ ነበር:-
“አላህ ሆይ! እኔ ዘንድ ለቢድዐህ ባለቤት ውለታን አታድርግለት፣ (ውለታ ካለብኝ) ልቤ ይወደዋልና።" [ሸርህ ኡሱል ኢዕቲቃድ አህሉሱንነቲ ወልጀማዐህ ጥራዝ 1/140]
የቢድዐ ሰው ውለታ ያለበት እውነታውን ቢያውቀውም መናገር ይከብደዋል። ይህ ደግሞ አላህ ይጠብቀንና በተጨባጭ የታየ ነገር ነው። ብዙዎችን ገደል የከተተውም ይሄው ነው።
ፉደይል ኢብን ዒያድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“የቢድዐ ባለቤቶችን የወደደ ሰው አላህ ስራውን አበላሽቶበታል፣ የእስልምናን ብርሃንም ከልቡ አውጥቶበታል።"
[ሸርሁ ሱንነህ ሊልበርበሃሪይ 138–139 አል ኢባነህ ሊብኒ በጣህ ጥራዝ 2/460]
ልብ በሉ የቢድዐህ ባለ ቤትን መውድ ያለው አደጋ!!
ዐብዱላህ ኢብኑ ዳውድ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“ከሀቅ ምልክቶች ሀይማኖትን በስሜት የሚይዝን ሰው መጥላት ነው። ሀቅን የወደደ ሰው በእርግጥም የስሜት ባለቤቶችን (የቢድዓ ሰዎችን) መጥላት ግዴታ ሆኖበታል።"
[ሲየር አስሰለፍ አስሷሊሂን ሊተይሚይ ጥራዝ 3/1154]
ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን (ረሂመሁላህ) ዘንድ ሁለት የስሜት ባለ ቤት የሆኑ ሰዎች ገቡና እንዲህ አሉት:-
“አንተ የበክር አባት ሆይ! አንድ ሀዲስ እንንገርህ? አሉት፣ በጭራሽ አይሆንም፣ አላቸው፣ አንድ የቁርኣን አንቀፅ እንኳን እንቅራልህ? አሉት፣ በጭራሽ አይሆንም!፣ አላቸውና ትነሳላችሁ አለያ እኔ ተነስቼ እወጣላችኋለሁ፣ አለ፣ ተነስተው ወጡ። ከወጡ በኋላ ከአጠገቡ የነበሩ ሌሎች ሰዎች፣ የበክር አባት ሆይ! ቁርኣን ቢያነቡልህ ምንችግር አለው? ብለው ጠየቁት፣ እንዲህ በማለት ድንቅ መልስ መለሰ:- የቁርኣኑን አንቀፅ አንብበውት ያለ ትርጉሙ አዛብተው ተርጉመውት በልቤ እንዳይቀር ፈርቼ ነው።” [ሲየር አዕላም አንኑበላእ ሊዘሀቢይ ጥራዝ 11/285]
ይህ ታላቅ የኢስላም ሊቅ በዚህ መልኩ ከፈራ አንተ ማን ነህ እንደ ዝምብ ሁሉም ላይ ዘለህ ጥልቅ የምትለው?!፣
የጣውስ ልጅ (ረሂመሁላህ) አንድ የቢድዐህ ባለ ቤት የሆነ ሰው እያናገረው ለልጁ እንዲህ አለው:-
“ልጄ ሆይ የሚናገረውን እስከማትሰማ ድረስ ጣቶችህን ጆሮህ ውስጥ ክተታቸው፣ ከዚያም ቀጠል አደረገና በደንብ ጠንከር አድርገህ አስገባ አጠንክር። አለው” [አላለካኢይ እና ሲየር አዕላም አንኑበላእ]
በዚህን ጊዜ ሰለፊይነት ስም ብቻ እስኪመስል ድረስ አንዳንድ ወንድምና እህቶች ዘንድ ከቢድዐህ ሰዎች ጋር ሊኖር የሚገባው ጠንካራ የሰለፎች አቋም ወርዷል። የሰለፎቻችን በቢድዐህ ሰዎች ላይ የነበራቸው ጠንካራ አቋም ኪታብ ላይ ይቀራል ተግባር ላይ ግን አደጋ ላይ ነው። በተለይ ብዙ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ፕሮፋይል ላይ ሰለፊነትን ለማንፀባረቅ ማሻአላህ ናቸው፣ በተግባር ግን ከሙመይዓና ከኢኽዋን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስሮች ስር ሲልከሰከሱ ይስተዋላሉ፣ አላህ ይጠብቀንና የሆነ ኮሽታ ሲፈጠር ወደዚያው ለመጠቃለል ቅርብ ናቸው፣ ከዚህ ተግባር ልንቆጠብና ከቢድዐህ ባለ ቤቶች የተኛውንም መልእክታቸውን ከሚያብራሩባቸው የማህበራዊ ሚዲያም ሆነ ሌሎች መድረኮች መራቅና መጠንቀቅ ግዴታ ነው። ሙመይዓዎች ወርደው ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር የተደመሩበት አንዱ አደጋ ይህ ነበር። ሰለፊይ ነን ካልን በአቋማችን የፀናን ልንሆን ይገባል!! የሰለፎችን አቋም በሁለመናችን ተግባራዊ ልናደርግ ግድ ይለናል!! አላህ በሐቅ ላይ ያፅናን!!
3 466
ዐባድ ኢብኑ ዐባድ አረምሊይ አሻሚይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል:—
"
👉ለአኼራ ጉዳት ከሚያመጣ ነገር መጠንቀቅ የቀጠነበት (የተመናመነበት)
👉 ለአያሉ ጌታ እራስን ማዋረድ የቀነሰበት
👉እውቀትንም አበላሹ የተሸከመበት ግዜ ላይ ነው ያላችሁትና አላህን ፍሩ።"
✍አቡ ሙዓዝ3 466
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
🔷 የሙዓዊዘተይን (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱ አንናስ) ፋይዳ
ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :-
"ከሙአዊዘተይን - ከሁለቱ መጠበቂያዎች - የሚብቃቃ አንድም ሰው የለም። ሁለቱ መጠበቂያዎች ሲህርን ፣ አይነ-ናስ እና ሌሎች ክፉ ነገሮች በመከላከል ልዩ የሆነ ተጽእኖ አላቸው።
ለአንድ ሰው ከአየር ፣ ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ከልብስ የበለጠ እነዚህ ሁለቱ መጠበቂያዎች ያስፈልጉታል።"
بدائع الفوائد ٢/١٩٩
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
3 466
🛜 አሁን ቀጥታ ስርጭት ደርስ
➲ርዕሰ ዲንን አጥብቆ የመያዝ ምክንያቶች
╰┈➢ ገ
╰┈➢ ባ
╰┈➢ገ
╰┈➢ ባ
╰┈➢በሉ።
🎙 ┈──── ••⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
╰┈➢ በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ታጁዲን ዐብድራህማን (ከወራቤ)
https://t.me/mesjedibnuteymeya?videochat=6a3e695bff1cd270e6
3 466
Repost from መስጂዱ "ኢብኑ ተይሚያን "በጋራ ተባብረን እንጨርሰው
➣የፕረግራሙ ሰዐት ደርሷል
እንግዶቻችን ሊገቡ ነው
➥ገበ ገበ ገበ
➟ገበ ገበ ገበ
➣በሉ በሉ
➥https://t.me/mesjedibnuteymeya
https://t.me/mesjedibnuteymeya?videochat=6a3e695bff1cd270e6
3 466
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷 ከሐዲያንን መመሳሰል የሚያስከትለው ጉዳት
ኢማም አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል ፡ -
“ሙስሊም ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች በበዓላትም ይሁን በልዩ አለባበሳቸው ሙስሊም ካልሆኑ ከሐዲያን ጋር መመሳሰል እንደማይፈቀድላቸው በሸሪዓ ተረጋግጣል፡፡ ይህ በእስልምና ታላቅ መሰረታዊ ህግ ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ዛሬ የሃይማኖቱ ጉዳይ ይመለከተናል ፣ ወደርሱም ጥሪ እናደርጋለን የሚሉ ሙስሊሞች እምነታቸውን ባለመገንዘብ ወይም ዝንባሌያቸውን በመከተል ወይም ወደዘመናዊነት በመንዘንበል ወይም ከሐዲ በሆኑ የአውሮፓውያ ፋሽኖች በመጎተት ከእነዚህ ታለቅ የኢስላም መሰረታዊ ህጎች አግልለዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለሙስሊሞች ውርደት እና ድክመት ለውጭ ሀይላት የበላይነት እና ቅኝ ግዛት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡”
"جلباب المرأة المسلمة في الكتاب والسنة 161
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
3 466
አዲስ ሙሃዶራ
ርዕስ:- إصبر أيها المؤمن ولا تلتفت لكيد الكائدين ومكر الماكرين
(አንተ ሙእሚን ሆይ! ታገስ ወደ ተንኮለኞች ተንኮልና ወደ ሴረኞች ሴራ አትዙር!!!)
🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ (ሀፊዘሁላህ)
በሙሃደራው የተዳሰሱ ነጥቦች
👉ተንኮል(كيد) እና ሴራ (مكر) ምን ማለት እንደሆነ....
👉የከይድና የመክር አይነቶች......
👉ተንኮል፣ ሴራ፣ ክህደት፣ ማጭበርበር የመሳሰሉት በኢስላም የተወገዙ እንደሆነ...
👉ተንኮልና ሴራ በግለሰቦችና በማህበረሰብ ላይ የሚያስከትሉት ዱንያዊና አኼራዊ መዘዞች......
ተንቢህ(ማንቂያ)
👉የነብዩላሃ ዩሱፍ ወንድሞች ከነብያት ናቸውን በሚለው መስአላ ያለውን የዑለሞች ኺላፍና ራጂህው ቀውል ተብራርቷል እንደማስተካከያ‼
https://t.me/ibnbaz1212
3 466
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
+1
እውቀት የሚፈልግ አካል እንቅልፍ ማብዛትንና አካላዊ ምቾትን መፈለግ የለበትም !
قم يا طالب العلم ولا تنام ولا تغفل وكن مستيقظا نشيط
https://t.me/MisbahMohammed_6682
