es
Feedback
የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

Ir al canal en Telegram

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
3 466
Suscriptores
+3924 horas
+2267 días
+39330 días
Archivo de publicaciones
التهنئة: وإن كان الأفضل بعد الصلاة، إلا أنه لا بأس بها ليلة العيد؛ لأن التهنئة تخضع للعادات والناس فيها في سعة.

የሁለቱን ዒዶች ስርኣት የሚመለከቱ ጥቂት ነጥቦች ከማስረጃዎቻቸው ጋር —————ክፍል 2 የተክቢራ አደራረግንና የዒድ ሶላት አሰጋገድን ያካተተ ክፍል 1 ለማግኘት ⤵️ https://t.me/IbnShifa/6788 ሴቶች የዒድ ሶላት ወደ ሚሰገድበት ቦታ ሲወጡ… »-» ሴቶች ሲወጡ ማንኛውም አይነት ማራኪ ሽታ ያለውን ነገር መቀባትና ጌጣ ጌጥ ያለውን ልብስ ለብሰው መውጣት ሀራም ይሆንባቸዋል። ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) የሴቶችን ወደ ዒድ ቦታ መውጣት በተመለከተ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ:- “ሴቶች የዒድ ቦታ ላይ ማንኛውም አይነት ሽታ ያለውን ነገር ሳይጠቀሙ፣ የጌጣ ጌጥና የዝነኞችን ልብስ ሳይለብሱ ቢወጡ ችግር የለውም። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና:- ምንም አይነት ሽታ ያለውን ነገር ሳይጠቀሙ ይውጡ…።” [ተውዲሁል አህካም ሸርህ ቡሉግ…] ይህ በሴቶች ላይ የተቀመጠ መስፈርት ነው። ይህን መስፈርት ስሜቴንና ሸይጧንን አሸንፌ ማሟላት አልችልም የምትል ሴት ከቤቷ ትቀመጥ!። ወደ ዒድ ቦታዎች እየወጣች ለጌታቸው ሊሰግዱና ጌታቸውን አላህን ሊያወድሱ የወጡ ወንዶችን ወንጀል ውስጥ እየጣለች ለራሷም ወንጀል ሸምታ ከመግባት ልትቆጠብ ይገባል!!። ሽቶ ተቀብተውና ተጋግጠው የሚወጡ እህቶች አላህን ሊፈሩት ይገባል!!። በደስታ ቀን አላህን ከማመፅ ሊቆጠቡ ይገባል። እህቴ ሆይ! በደስታ ቀን አላህን ካመፅሽ በዱኒያና ነገ በጭንቁ ቀን ጭንቀት እንዳይጨምርልሽና ስቃይሽን እንዳያበረታው ልትፈሪና ልትጠነቀቂ ይገባል!! እህቴ ወደ ዒድ ቦታ መውጣት ከፈለግሽ ሽቶና ዲዮድራንት… መሰል ነገሮችን ከመቀባት ርቀሽ፣ የሰውነት ቅርፅሽን የሚያሳዩ የተጣበቁና የተጋጌጡ ልብሶችን አሽቀንጥረሽ ጥለሽ ሰፋፊ ሸሪዓዊ አለባበስ ለብሰሽ ድምፅሽን አጥፍተሽ ወጥተሽ አምላክሽን አላህን አወድሰሽና አልቀሽ ለእርሱም ሰግደሽ ተመለሺ። ይህን ማድረግ ካልቻልሽ ግን አላህን ፈርተሽ ቤትሽ ይስፋሽ!!። »-» ወደ ዒድ ቦታ ሲኬድ ድምፅን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ማለት ተደንግጓል። አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:- وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ «ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡» አል-በቀረህ 185 ከዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ተይዞ፣ የአላህ መልእክተኛ ﷺ በሁለቱ ዒዶች ከፈድል ኢብኑ ዐባስ፣ ከዐብደላህ፣ ከዐባስ፣ ከዐሊይ፣ ከጀዕፈር፣ ከሀሰንና ሁሰይን፣ ከኡሳማ ኢብኑ ዘይድ፣ ከዘይድ ኢብኑ ሃሪሰህ፣ ከአይመን ኢብን ኡሙ አይመን (ረዲየላሁ ዐንሁም) ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተክቢርና ተህሊል እያሉ ይወጡ ነበር። [በይሀቂይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ በኢርዋእ አልገሊል 3/123 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።] የተክቢራውን አደራረግ በተመለከተ ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጠ ሶሂህ የሆነ ዘገባ የለም። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ግን የሚከተለውን የተክቢራ አይነት ይጠቀም እንደነበር ተረጋግጧል:- “አላሁ አክበር አላሁ አክበር፣ ላ! ኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወ ሊላሂል ሀምድ” [ኢብኑ አቢ ሸይባ በሶሂህ ሰነድ ዘግበውታል።] ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስም እንደሚከተለው ይል እንደነበር ተዘግቧል:- “አላሁ አክበር አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር ወ ሊላሂል ሀምድ፣ አላሁ አክበር ወ አጀልሉ፣ አላሁ አክበር ዐላ ማ ሐዳና” [በይሀቂይ ሶሂህ በሆነ ሰነድ ዘግበውታል።] »-» የተክቢራ ጊዜን በተመለከተ የዒደል ፊጥር ተክቢራ የዒዱን ቀን ተሰግዶ እስኪያበቃ ነው። የዒዱል አድሃ ተክቢራ ደግሞ ከዐረፋ ንጋት ሶላት ጀምሮ በተከታታይ አያሙ ተሽሪቅ እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው። (የውሙ ዐረፋ ማለት ከዙል ሒጃ 9ኛው ቀን ነው።) ይህ አጠቃላይ ሰለፎች፣ ሶሃባዎች፣ አራቱ መሪዎችና ፉቅሃዎች የተጓዙበት መንገድ ነው። [ሶሂህ ፊቅህ አስ-ሱና አቡ ማሊክ ከማል] »-» አንዳንድ ሰዎች ዒድ ሚሰገድበት ቦታ ሲደርሱ ሱና ብለው ይሰግዳሉ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ለሁለቱም ዒዶች ከፊታቸውም ሆነ ከኋላቸው ሱና ሶላት የላቸውም። ነገር ግን ነቢዩ ﷺ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ 2ረከዓ ይሰግዱ ነበር። ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከዒድ በፊት ምንም አይሰግዱም ነበር፣ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።” [ኢብን ማጀህ 1076 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ነው ብለውታል።] ለሁለቱም ዒዶች አዛንም ሆነ ኢቃም ማለት የለም። »-» የዒድ ሶላት የአሰጋገድ ሁኔታን በተመለከተ እንደሚከተለው ነው:- የዒድ ሶላት 2ረከዓ ነው። ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብሏል:- “የተጓዥ (የጉዞ) ሶላት 2ረካዓ ነው። የዒደል አድሃ ሶላትና የዒደል ፊጥር ሶላትም ሁለት ሁለት ረከዓ ነው። እርሱም አጥሮ ሳይሆን ሙሉው ነው 2ረከዓ በነቢያችሁ አንደበት የተደነገገ ነው።” [ነሳኢይ እና ኢማሙ አህመድ የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።] » የመጀመሪያውን ረከዓ ልክ እንደሌላው ሶላት  በኢህራም ተክቢራ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ ሰባት ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል። ሰባቱ ተክቢራ በሚደረግበት ወቅ እጅ ማንሳቱ ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጠ ነገር የለም። ነገር ግን ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር የነቢዩን ﷺ ሱንና አጥብቆ የሚከተል ከመሆኑም ጋር በሰባቱም ተክቢራ ጊዜ እጁን ያነሳ ነበር ይላል። ሌላው በየ ተክቢራው መሃል የሚባል ዚክር ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጠ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ ﷺ በየ ተክቢራው መሃል "አላህን ያወድሱም ያመሰግኑም ነበር” ብሏል። [በይሀቂ የዘገቡት ሲሆን ሰነዱ ሀሰን ነው።] ከሰባቱ ተክቢራዎች በኋላ ፋቲሃ ይቀራል ከዚያም ሱራዎች ይቀራሉ። ተወዳጅ ሱራዎች "ቃፍ፣ ወል ቁርኣኒል መጂድ፣ የሚለውና ኢቅተረበቲ ሰኣቱ… እንዲሁም ሰቢህ እስመ ረቢከል አዕላና ሐል አታከ ሀዲሱል ጋሺየህ…" ሱራዎች ናቸው። [ሙስሊምና ነሳኢይ ሌሎችም ዘግበውታል።] ከዚያም በሁለተኛው ረከዓ ተነስቶ ለመቆም ከሚለው ተክቢራ ውጭ አምስት ተክቢራዎችን ይላል። ከዚያ በኋላ ልክ በመጀመሪያው ረከዓ እንዳደረገው ፋቲሃን እና ሌሎችን ሱራዎች ይቀራል። ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ተይዞ፣ “የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዒደል ፊጥርና በዒደል አድሃ ሶላት በመጀመሪያው ረከዓ ሰባት ተክቢራዎችን በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ አምስት ተክቢራዎችን ይሉ ነበር።” ብላለች። [አቡዳውድ የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።] በመጨረሻም ከተሸሁድ በኋላ ያሰላምታል። »-» ወደ ዒድ ቦታ ከተጓዙባቸው መንገዶች በተቃራኒ መንገድ መመለስ ሱንና ነው። ከጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ እንዲህ አለ:- “ነቢዩ ﷺ የዒድ ቀን ከሆነ በተቃራኒ መንገድ ይጓዙ ነበር።” [ቡኻሪ ዘግበውታል] አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ነቢዩ ﷺ ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ከወጡ መጀመሪያ ከወጡበት መንገድ በተቃራኒው ይመለሱ ነበር።” [ኢብን ማጀህ ዘግበውታል] አላህ ዒዳችንን አላህን የምንታዘዝበትና አላህ በሚፈቅደው መልኩ የምንደሰትበት ዒድ ያድርግልን!! ✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን👇👇 #join  በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

"ኩራተኛ ጀነት አይገባም!" የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ «በልቡ ውስጥ የብናኝ ያክል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም።»
📔[ሶሒሕ ሙስሊም፡ 91]
https://t.me/HussinAssilty/3250

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

▪️السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🔀የተከበራችሁ የወራቤ ሃጢባ እነ ኢሕሳን መድረሳ ኮርስ ተከታታዮች በሁለቱም መድረሳዎች ይሰጡ የነበሩ ደርሶች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ለአረፋ በዐል የተቋረጡ መሆኑን አውቃችሁ ሁላችንም  በያለንበት በነዚህ ጥቂት ውድ ቀናት በተለያዩ ዒባዳዎች በፆም ፣ቁርኣን በመቅራት ፣የተቸገሩት በመርዳት ፣ቤተሰብ በማገዝ፣  በተክቢራ እነ በሌሎችም አዝካሮች ጠንከር እንበል ። አላህ ሁላችንንም ለመልካም ስራዎች ሁሉ ይግጠመን 📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል https://t.me/ibnbaz1212

📙 عنوان الرسالة: مجمل عقيدة السلف الصالح لشيخ صالح بن فوزان الفوزان (የሸይኽ ሷሊሃልፈውዛን ሪሳላ የሆነችው ሙጅመሉ ዓቂደቲ አሰለፍ አሷሊህ)         ክፍል ሶስት (03) 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ 📚የኪታቡን pdf ለማግኘት👇👇 https://t.me/ibnbaz1212/66 📆  ዕለተ ጁሙዓ ዙልሂጃ  06, 1447          🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ የቴሌግራም ቻነል https://t.me/ibnbaz1212

📙 عنوان الرسالة: مجمل عقيدة السلف الصالح لشيخ صالح بن فوزان الفوزان (የሸይኽ ሷሊሃልፈውዛን ሪሳላ የሆነችው ሙጅመሉ ዓቂደቲ አሰለፍ አሷሊህ)         ክፍል አራት (04) 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ 📚የኪታቡን pdf ለማግኘት👇👇 https://t.me/ibnbaz1212/66 📆  ዕለተ ጁሙዓ ዙልሂጃ  06, 1447          🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ የቴሌግራም ቻነል https://t.me/ibnbaz1212

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ነገ ቅዳሜ የሚሰጠው ደርስ ተንቢሃት ኪታብ በመደዋወል ላልሰሙት እነሳውቃቸው

ለዒድ አል-አድሃ በዓል የሀገር ቤት ጉዞ —————ክፍል 1 ለሙስሊሞች መደሰቻ ሁለት ታላላቅ በዓላትንና የጁምዓ እለትን ለደነገገው ለዓለማቱ ጌታ አላህ የላቀ ምስጋና ይገባው!!። እንደሚታወቀው ከነዚህ ውጪ ሌላ በሸሪዓ የተደነገገ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ያለው ኢስላማዊ በዓል የሚባል ነገር የለም!!። እነዚህ በዓላትም መለኮታዊና ከአምልኮ የተያያዙ ናቸው። በዚህ በተከበረው የዚል-ሒጃ ወር አቅማቸው የፈቀደላቸው ሰዎች፣ የጉዞውን ጣጣ የቻሉ ሰዎች የተከበረውንና መጎብኘቱ ግዴታ የሆነውን ብሎም መጎብኘቱ ከአምስቱ የእስልምና ማእዘናት የሆነውን የአላህን ቤት ለመጎብኘት የሚጓዙት በርካቶች ናቸው። ይህን ያልቻሉ ደግሞ ቤተሰባቸው የተለያየ ክ/ሀገራትና ገጠር ያሉ ወገኖች ከቤተሰባቸው ለማሳለፍ ወደተለያዩ ክ/ሀገር ከተሞችና ገጠር ይጓዛሉ። ይህ ጉዞ አላህን ማመፅ ካልተቀላቀለበትና እስከ ፍፃሜው አላህን መታዘዝ ከሆነ ምንኛ ያማረ ጉዞ ነው!። ይህ ጉዞ ለመልካም ነገርና ለቤተሰብ ዚያራ በመሆኑ የሚያስደስትና እጅግ የሚወደድ ቢሆንም፣ ተጓዦች አላህ (ይጠብቀንና) አላህን አያምፁበትም ፍፁም የሆነ ጉዞ ነው ማለት ግን አይደለም። በመሆኑም ተጓዦች ከእነዚህ አላህን በእጅጉ ከሚያስቆጡ ስህተቶች እንዲቆጠቡ ማስታወሱ ግድ ነው። » እንዲያውም ገና ጉዞው ሲጀመር በተከበረው ዘጠነኛው ቀን፣ ያንን (የዚል-ሂጃ 9ኛ) ቀን መፆሙ ያለፈውንና የሚቀጥለውን ዓመት ወንጀል ያስምራል በተባለው የተከበረ ታላቅ ቀን፣ አላህ ሀራም ያደረገውን የከበደ ወንጀል አደንዛዥ እፅ የሆነውን ጫት እየበላ የሚጓዘው ህዝብ ከተጓዦች አብዘሃኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም!። ጥቂት አላህ ያዘነላቸው ባሪያዎቹ ሲቀሩ አብዘሃኛው ተጓዥ ይህን አደገኛና አላህ ሀራም ያደረገውን አደንዛዥ እፅ እየበላ መጓዝ የተለመደ እየሆነ ነው። በዚሁ አጋጣሚ ጫትን ለማይቅሙትና የዲን እውቀት ላላቸው ለጥቂቶች አንድ መልእክት አለኝ:- (ከሚቅሙ ሰዎች ጋር ተቀላቅላችሁ የምትሔዱ ካላችሁ በራሳችሁ ላይ አንድ ግዴታ ነገር ጥላችኋል፣ እሱም:- የተወገዘን ነገር ማውገዝ ነው!። አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ሲተገበር ዝም ካላችሁ እንደ ዲዳ ሸይጧን መሆናችሁን አትዘንጉ!፣ ማውገዝ ወይም መከልከልና ደዕዋ ማድረግ ካልቻላችሁ ጫት ከማይቅሙና ዘፈን ከማይከፍቱ ከቢጤዎቻችሁ ነው መሄድ ያለባችሁ።) ታዲያ በጥቅሉ ጫትን በየተኛውም ጊዜ የምትቅሙ ሰዎች አላህን ልትፈሩ ይገባል!! ምንም ጥቅም የሌለውን አካልን የሚጎዳ፣ ገንዘብን የሚያባክን፣ አደንዛዥ የሆነን ነገር ሸሪዓችን እርም አድርጓል። ↪️ ጫት አካልን ጎጂ መሆኑን ታምኑበታላችሁ! እራስን የሚጎዳ ነገር መጠቀም ደግሞ አላህ ሀራም አድርጓል!! ↪️ ጫት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለውና ገንዘብን እንደሚያባክን ታውቃላችሁ!! አባካኞች የሸይጧን ጓዶች መሆናቸውን ደግሞ አላህ በቁርኣኑ ተናግሯል። ↪️ ጫት አዕምሮን እንደሚቀይር ታምናላችሁ! አዕምሮን የሚቀይር ነገር ደግሞ ከአስካሪ መጠጥ ነው። አስካሪ መጠጥ በእስልምና ሀራምነቱ ደግሞ እንኳን ለሙስሊሞች ለከሀዲውም ግልፅ ነው!! እነዚህን ጥቂት ጫትን ሀራም የሚያደርጉ ነጥቦች አብዘሃኛው ጫት ቃሚ "ለእውነት ሲባል" ብሎ ያመነባቸውና የጤና ባለ ሞያዎች ያረጋገጡት እውነተኛ ጫት የሚያስከትላቸው አደጋዎች እንጂ ከራሴ የሆኑ ፈጠራዎች አይደሉም!። ከላይ ለጠቀስኳቸው ነገሮች ማስረጃን ያልጠቀስኩት ከምንም በላይ ማስረጃው ግልፅና የሚታወቅ ከመሆኑ አንፃር ፅሁፉ እንዳይረዝም ብዬ ነው። ➡️ ከዚህ ጉዞ ሌላው ጥፋትና ከባድ ወንጀል ዘፈን፣ ነሺዳና መንዙማ እየተደመጠ መጓዙ ነው!!። ዘፈን አንዳንዶች ዘንድ ባህላዊ (በቋንቋቸው) ሲሆን ልክ እንደ ሙሃደራ (ሀዲስ) የሚቆጥሩት አሉ፣ ይህ ደግሞ በጥፋት ላይ ሌላ ጥፋት ነው።  በዘፈን ሀራምነት ሙስሊም ሆኖ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም። አውቆ ማጣመም ፈልጎ ካልሆነ በስተቀር!፣  ምናልባትም ከአንዳንድ ጠሞ አጥማሚዎች ብዥታ የሚወድቅበት ሊኖር ስለሚችል እስቲ በጥቂቱ የሚከተሉትን ማስረጃዎችን እንመልከት፣ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- {وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ} الإسراء ٦٤ “ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምፅህ አታል።” አል-ኢስራእ 64 “በድምፅህ አታል” የሚለውን በዘፈንና በአሎባልታ ጫወታ በዛዛታ ማለት ነው ተብሏል። ኢብን ከሢር የተሰኘው የቁርኣን ማብራሪያ ላይ ይህን አንቀፅ በሚያብራራው ቦታ ይመልከቱ። አላህ የመልካም ባሪያዎችን ባህሪ ሲገልፅ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- {وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا} الفرقان ٧٢ “እነዚያም በውሸት የማይመሰክሩ፣ በውድቅ ቃልም ተናጋሪ አጠገብ ባለፉ ጊዜ የከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው።” አል-ፉርቃን 72 “ውድቅ ቃል” በማለት የተጠቀሰው ዘፈን ነው ተብሏል። ኢብን ከሢርን ይህን የቁርኣን አንቀፅ በሚያብራሩበት ቦታ ይመልከቱ። አላህ በተቀደሰው ቃሉ ሙሽሪኮች ቁርኣን ከመስማት እንቢተኛ መሆናቸውንና ለቁርኣን ጀርባ መስጠታቸውን ሲያወግዝ እንዲህ ብሏል:- {أَفَمِنْ هٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ{٥٩}وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُون {٦٠}وَأَنتُمْ سٰمِدُونَ} النجم ٥٩–٦١ «ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?፣ ትስቃላችሁምን?፣ አታለቅሱምን? እናንተ ዘንጊዎች ናችሁ።» አን-ነጅም 59-61 “እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ” የሚለውን ታላቁ ሷሃባ ዐብደላህ ኢብን ዐባስ እና ሱፍያን አስሰውሪ…የመሳሰሉ ሌሎችም “እናንተ ዘፋኞች ናችሁ” ማለት ነው የተፈለገበት በማለት ተናግረዋል። ኢብን ከሢር የቁርኣን ተፍሲርን ይመልከቱ። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ በጠንካራ ሰነድ “ዘፈን በልብ ውስጥ ንፋቅን እንደሚያበቅል” መናገራቸውም ተዘግቧል። ስለ ዘፈን ሀራምነት ከቁርኣን አንቀፆች ባሻገር የተለያዩ እጅግ በርካታ ሶሂህ (ትክክለኛ) ሀዲሶች አሉ! ጊዜን ለመቆጠብና ፅሁፉ እንዳይረዝም ከሀዲስ ምንም አልጠቀስኩም። ዘፈንና ነሺዳን በተመለከተ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን በሰፊው ማንበብ የፈለገ የሚከተለውን ሊንክ ተጭኖ pdf ን አውርዶ ያንብብ። ስለ ነሺዳና ዘፈን ⤵️ pdf https://t.me/IbnShifa/933 ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

♦️«ለዐረፋ ወደ ክፍለ ሀገር  ለምትሔዱ » 👌ጨባጠ አቱን ዋብ ዮበሃን ! 👌ስጥ ይሰጥሃል! — ስረም ለዐረፈ ቴዶሙ ፋኛኞ አደራሙ ተዝጋጁበየ ሂዱ! ቆት ዬለይሙ ዪንደተነ ገረዳዶ ኢክሱይሙ። — በተለይ ለዐረፋ በዓል ወደ ገጠር የምትሄዱ እህትና ወንድሞች በየምትሄዱበት አካባቢ እንዲህ አይነት በጎ ተግባራትን ለማድረግ ከወዲሁ አስባችሁበት ተዘጋጅታችሁ ብትሄዱ መታደል ነው። 🎙በኡስታዝ ኸይረዲን ቶኪቻ አላህ ይዘንለት https://t.me/ibnbaz1212

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የኢህሳን መድረሳ ቅርኣት ተከታታዮች ዐፍወን የዛሬ ደርስ  በሐጃ ምክንያት አይኖርም

ተጀምሯል አዲስ ተከታታይ ኮርስ ኪታብ:- ሺዐቱ ሸይጧን! Pdf ⤵️ https://t.me/IbnShifa/6377 የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) ሪሳላ 🎙ኮርስ ሰጪው:- ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ (ሀፊዘሁላህ) በሳምንት ረቡዕና ሐሙስ 👉ኮርስ የሚሰጥበት ሰዓት:- 🕰ከምሽቱ  4:00 ጀምሮ ነው ገባ ገባ በሉ 👇👇 https://t.me/IbnShifa?livestream