es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ሕያው ቃል ➟ 📖

ሕያው ቃል ➟ 📖

Ir al canal en Telegram

🕊️ ሕያው ቃል | Living Word 📖✨ "የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም ነው..." (ዕብ 4፥12) ➢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችና ጥያቄዎች 🔍 ➩ መንፈስን የሚያድሱ ትምህርቶችና ጥቅሶች 💡 ➠ ሕይወትን የሚቀይሩ ምሳሌዎችና መልእክቶች 🌱 🎬 YouTube 👤 አስተያየትና ጥያቄ ለመላክ፦ @EDIWOLDE

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
335
Suscriptores
Sin datos24 horas
+167 días
+4630 días
Archivo de publicaciones
እየሱስ ብቻውን በቂ ነው!! 😊🙏

ዘኍልቁ (13፥1)-(14፥24) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ። ³ ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ። …………………………… ²⁵ ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። ²⁶ በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። …………………………… ³⁰ ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ። ³¹ ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ። ³² ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፦ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው። ³³ በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፥ የዔናቅን ልጆች፥ አየን፤ እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ። 👇👇👇👇👇👇 እነዚህ 12 ሰላዮች አይተው የመጡት ተመሳሳይ ነገር ነበር፤ ይዘው የመጡት ሃሳብ ግን እንደየእምነታቸው በጣም የተለያየ ነበር፤ ስለዚህ እንዳዩት ልክ ሳይሆን እንዳመኑት ልክ ሆነባቸው። "እንደ አንበጣ ነን" ያሉት የፈሩት ነገር ደረሰባቸውና በምድረበዳ ቀሩ፤ "እንደ እንጀራ ይሆኑልናል" ብለው ያመኑት ኢያሱና ካሌብ ደግሞ ያመኑት ነገር ሆነላቸውና ከንአንን ወረሱ። 👉 እግዚአብሔር እስራኤላዊያንን ከግብፅ ምድር ሲያወጣቸው ያወጣቸው፦ "ማርና ወተት ወደምታፈሰው ምድር ወደ ከንአን አገባችኋለሁ" ብሎ ነበር። የወረሱት ግን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነው ቃሉንና ኃይሉን ያመኑቱ ብቻ ነበሩ፤ ሌሎቹ ግን ባለማመናቸው ምክንያት የፈሩት ነገር ደረሰባቸውና ሳይወርሱ ቀሩ። ♦️የፈራሀው ነገር ደርሶብሃል ማለት እግዚአብሔር መፍራትህን ይደግፈዋል(የደረሰብህ ነገር የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው) ማለት አይደለም። 🤷‍♀ እግዚአብሔር እኛ "እንጠፋለን" ብለን እያወጅን፣ እርሱ ፈቃዳችንን በማለፍ በግድ ተጋፍቶ ገብቶ ከመጥፋት አያድነንም። ምክንያቱም መፅሐፉ ሲናገር "ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል" ይለናልና እኛም እንጠፋለን ብለን ካመንን መጥፋታችን አይቀሬ። ይልቅ ያለእምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘትም ሆነ መከተል ስለማይቻል ፍርሃትን እያስወገድን እምነታችንን እናሳድግ!! 💡በመጨረሻም በዚህ ክፍል በጣም ካስገረሙኝ ነገሮች አንዱ አስሮቹ ሰላዮች፦ "በአይናቸው ፊት እንደ አንበጣ ነን" አሉ። 🐜አንበጣ ብቻውን ከሆነ ማንም ሊገለው(ሊያጠፋው) ይችላል፤ መንጋ(ብዙ) ከሆነ ግን የሀገር ጉዳይ ሆኖ መንግስትን የማስጨነቅ አቅም አለው።👍 👏 ኢያሱና ካሌብ ደግሞ ጠላቶቻቸውን "እንደ እንጀራ ይሆኑልናል" አሉ። 🥞እንጀራ ብቻውን ቢሆንም ትበላዋለህ፤ መንጋ ቢሆንም ትበላዋለህ እንጂ አይበላህም። 🙏 🙏 🙏 🙏 🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

❌🗣️ ያወሩ 🗣️ ተዋቸው ❌ 🦋 ተናግሮ ነገሮችን መቀያየር የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። 🙏 💬 "ትነሳለህ" ካለህ ሊያነሳህ ነው፣ "ብርቱ ነህ" ካለህ ብርቱ ሊያደርግህ ነው። 💪✨ 👉 ሰው ግን "ትወድቃለህ" ሲልህ ሊጥልህ እንዳይመስልህ "እወድቃለው" ብለህ እንድታምንና የጀመርከውን ነገር እንድታቆም ነው። 🚫 ለዚህ ነው ደጋግሞ ሚነግርህ። 🗣️ ስለተናገረ የሚሆንለት ቢሆን ኖሮ አንዴ ተናግሮ ዝም ይል ነበር እንጂ ከተማ ለከተማ እየዞረ አያስወራብህም ነበር። 🚶‍♂️🗣️ ☑️ ስለዚህ ተቀብለህ በልብህ ቦታ ካልሰጠሀው በቀር ወሬው ዋጋ አይኖረውም፤ ከንቱ ታደርገዋለህ። ❤️🚫 🐕🗣️ ለጮኸ ውሻ ሁሉ ድንጋይ መወርወር ጊዜንና ጉልበትን ማባከን ነው። ⏳💪 ☑️ ለምትሰማው ድምፅ ሁሉ ድንጋይ መወርወሩን ትተህ ጉዞህን ቀጥል!! 🚶‍♂️🔥🎯 የዚያን ጊዜ ወሬው አንተን አለማስቆሙን ሲያውቅ በራሱ ይቆማል። 🤫✋ ለእያንዳንዱ ወሬ መልስ መስጠት ከጀመርክ ግን አንተ ራስህ ወሬውን ላልሰማ እያሰማህ ታሰፋዋለህ። 📢🔄 እና ወረኞቹም ደግሞ ትኩረት እንደሰጠኃቸውና ለእነርሱ መልስ እየሰጠህ ጊዜህን እንደምታጠፋ ሲረዱ ሌላ ወሬ ይፈጥራሉ፤ 🗣️🔄 ለሱም እንደገና መልስ እየሰጠህ ከአላማህ ውጪ ትሆናለህ። 🎯🚫 ⚠️ ይሀው ነው እቅዳቸው!!!! ⚠️ 💭 ስለዚህ "ማንም" ቢያወራ ለራሱ ነው፤ በኔ ሕይወት ምንም ማድረግ አይችልም" ብለህ ጉዞህን ቀጥል!!! 💪🔥🚶‍♂️ 🔴 ወረኞች ስላንተ ቤት ተከራይተው እንኳ ቢያወሩብህ አንተ ካልሰማሃቸው በባዶ ቤት እንደተከፈተ ሬድዮ 📻 ለራሳቸው ይለፈልፉና ባትሪያቸው ሲያልቅ 🔋 በራሳቸው ይዘጋሉ። 🤫😂 ❤️ ካነበቡ በኋላ ለሌሎችም ያጋሩ 🙏📲🔄 🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

🔹"ይሰሙኛል! ይረዱኛል!" ብለህ ወደ እነርሱ የጮህክላቸው ትኩረት ላይሰጡህ ይችላሉ። 🔹መፍትሄ ያለው እነርሱ ጋር ብቻ ስለሚመስልህ ከእነርሱ አይን ለመግባት ብለህ ብዙ ለፍተህ ይሆናል። 🔹እራስህንም አወርደህ እነርሱን ለማገልገል ከሰው የበታች ሆነህ ይሆናል። 😔ቢሆንም እነርሱ ከምንም አልቆጠሩህም ይሆናል። 🔘ነገር ግን በሳምንት ለ7 ቀን፣ በቀን ለ24 ጆሮዎቹን ላንተ የከፈተ 🔘ሊሰማህና ሊረዳህ ተዘጋጅቶ "እርዳኝ" የሚለውን ያንተ ድምፅ የሚጠብቅ አምላክ እንዳለ #አስተውል❗ 🔸ለማይሰሙህ እየጮህክ፣ ለማይረዱህ እያስረዳህ ጊዜህን አታባክን! አቅምህንም አትጨርስ!   ወደ ፀሎት ስፍራህ ግባና ለሚሰማህ ተናገር! 👉ያስለቀሰህ ነገር ካለ በእርሱ ፊት አልቅስ 👉ያሳቀህ ነገር ካለ በእርሱ ፊት ሳቅ 👉ያስጨነቀህን ነገር ዝርክክ አድርገህ ንገረው 🔹ቃል እየመረጥክም አትቸገር! የተሰማህን እንደተሰማህ አድርገህ ነገረው! 🔸እርሱ አንደበትህን ሳይሆን ልብህን ቀድሞ ይሰማል አብዛኞቻችን ፀሎትን የምናስበው፦ ቀኑን ሙሉ እራሳችንና ሌሎችን ስንጠቅም ውለን አመሻሽ ላይ ደግሞ እግዚአብሔር ለመጥቀም ብለን የምናደርገው ድርጊት አድርገን ነው። ነገር ግን ፀሎት ማለት፦ ☑️የሚያስፈልገንን መጠየቅ ☑️ያስጨነቀንን መናገር ☑️አሁን በሕይወታችን እየሆኑ ስላሉና ነገ ላይ ሊሆኑ ስላሉ ነገሮች ከእርሱ መረዳት… ማለት ነው። ❕ፀልዩ የሚለው ትዕዛዝ ከእርሱ ስለመጣ ተጠቃሚውም እርሱ አይምሰለን❕ 🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል።
— መዝሙረ ዳዊት 147:11 Amharic Bible Bot

ከእለታት አንድ ቀን አንድ በጣም የምፈልገውን እቃ አባቴ እኔ ካስቀመጥኩበት ስፍራ አንስቶ ሌላ ቦታ አስቀመጠው።   እኔም ዕቃውን ባስቀመጥኩበት ስፍራ ሳጣ ፍለጋ ጀመርኩ። በጣም ብዙ ቦታ ፈለኩ፤ አንዳንድ ቦታወችን እንደውም ደጋግሜ ፈለኳቸው፣ ከባባድ እቃዎችን እንኳን እያነሳው ጉልበቴንና ጊዜዬን አባከንኩ። ቢሆንም አጣሁት🤷‍♂       ነገር ግን አላስተዋልኩም እንጂ እቃውን ለማግኘት አንድ መንገድ መጠቀም እችል ነበር፤ እርሱም ጊዜዬንና ጉልበቴን የማያባክን መንገድ ነው፦ "አባቴን መጠየቅ" አባቴን ብጠይቀው ወይ ይነግረኛል ወይ ደግሞ "ስለማይጠቅምህ ደብቄዋለው" ይለኝ ነበር።   🙇‍♂ ብዙዎቻችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ባለማወቅ ስኬትን ፍለጋ - መልካም መስሎ የታየንን መንገድ ሁሉ እየሄድን - መሸከም የሌለብንን እየተሸከምን - ጊዜያችንንና ጉልበታችንን እያባከንን "ጌታ ሆይ እርዳኝ" እንላለን። ግን አይሳካልንም። ደጋግመን እንሞክራለን ግን ምንም ለውጥ አናገኝበትም! 👉ነገር ግን ሁሉንም ነገር ወደ ጎን ትተን ከአባታችን ጋር ያለንን ህብረት ብናጠናክርና እርሱን ብንጠይቀው #ለዘላለም እናርፍ ነበር። ☑️ስኬት ያለው #ደጋግሞ በመሞከር ሳይሆን የእግዚአብሔርን #ፈቃድ አውቆ በመንቀሳቀስ ውስጥ ነው☑️ ✅ስንፀልይ እንዲሳካልን ብቻ ሳይሆን የስኬት መንገድ እንዲበራልንም እንፀልይ✅ 🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

📢 አስቸኳይ የትብብር ጥሪ! 🙏 ሰላም የሕያው ቃል ቻናል ተከታታዮች። ❤️ አንድ አስቸኳይ ጉዳይ ላይ የእናንተን ትንሽ ትብብር እንፈልጋለን። ⚠️ ጉዳዩ፦ የቀድሞውን ቻናላችንን የቀድሞ አካውንት በመሰረዙ (Delete በመሆኑ)፣ የቻናሉን Owner/Admin መብት አጥተናል። አሁን ቻናሉን ወደ እኛ ለመመለስ Telegram Support ጋር ሪፖርት እያደረግን ነው። 🙏 እዚህ ላይ የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል! ቢያንስ 10 ፈቃደኛ አባላት በመሆን ሪፖርቱን በተገቢው መንገድ እንድናቀርብ እገዛችሁን እንጠይቃለን። 👉 ለማገዝ የምትፈልጉ ከሆነ፦ 📩 በውስጥ መስመር @gediwolde ላይ መልዕክት ላኩልኝ። እኔም ሪፖርቱን እንዴት ማቅረብ እንዳለባችሁ፣ የምትጠቀሙበትን አጭር ጽሑፍ እና አስፈላጊውን መረጃ እልካለሁ። ❤️ የእያንዳንዳችሁ ትንሽ ትብብር ለእኛ ትልቅ እገዛ ነው። 🙏 ቻናላችንን ለማስመለስ አብረን እንስራ! 📩 ለማገዝ፦ @gediwolde እግዚአብሔር ይባርካችሁ! 🙏❤️

ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
— ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22-23 Amharic Bible Bot

🤔 ሰው ከእግዚአብሔር ርቆ ሲኖር ምን ይሆናል? ብዙ ጊዜ ሰው የሚፈልገውን ሁሉ ካገኘ ደስተኛ እንደሚሆን ያስባል። ገንዘብ፣ ዝና፣ ስራ፣ ጓደኛ እና የዓለም ነገሮች ሁሉ ቢኖሩትም በልቡ ግን እውነተኛ ሰላም ሊጎድለው ይችላል። 👉 ምክንያቱም የሰው ልብ በዓለም ነገር ብቻ አይሞላም።
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። — ምሳሌ 4፥23
💭 እንግዲህ እራስህን ጠይቅ፦ 👉 ልቤን የሚመራው ምንድነው? 👉 በችግር ጊዜ የምታመነው ማን ነው? 👉 ደስታዬ በእግዚአብሔር ነው ወይስ በዓለም ነገር? 🔹 ሰው ከእግዚአብሔር ሲርቅ ባዶነት ይሰማዋል። 🔹 ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ግን እውነተኛ ተስፋን ያገኛል። ❤️ ዛሬ እግዚአብሔርን ለመፈለግ የሚያስፈልግህ ሌላ ቀን አይደለም። ዛሬውኑ ጀምር። 🙏 ጸልይ፣ ቃሉን አንብብ፣ ልብህንም ለእርሱ ክፈት።
📌 ወደ እግዚአብሔርም ቅረቡ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። — ያዕቆብ 4፥8
❤️ ይህ መልዕክት ለአንተ ከጠቀመህ፣ ለሌላ ሰውም እንዲደርስ አጋራው። 🙏 እግዚአብሔር ይባርካችሁ! 🙏 🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።
— የዮሐንስ ወንጌል 15:7 Amharic Bible Bot

ኢየሱስ ጌታ ነዉ

ነጭ ቬሎ ለብሳ ያጌጠች ሙሽሪት ጭቃ ውስጥ ገብታ ብትገኝ። 🤔 ከጭቃው እንድትወጣ ከተፈለገ በትክክል ማወቅ ያለባት ነገር ምንድን ነው? 👉ጭቃ ውስጥ እንዳለች? 👉ጭቃው በጣም አስቀያሚ እንደሆነ? በእርግጥ እነዚህን ነገሮች ብታውቅ ይጠቅማት ይሆናል። ቢሆንም ግን ከጭቅው እንድትወጣ ማወቅ ያለባት ዋናው ነገር- የለበሰችው ንፁህ፣ ነጭ፣ ውድ እና ጭቃ #የማይመጥነው ልብስ መሆኑን ነው። የልብሱን ንፅህና እና ዋጋ ስትረዳ የት መዋል እንዳለባት ይገባታል። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ከሐጢአት ልምምድ ለመውጣት መፍትሄው በየቀኑ ስለሰራሀው ኃጢአት ዝርዝር ቁጭ ብለህ ማሰብ ሳይሆን አንተ ያለህን #ክብር ማወቅ ነው። #የንጉስ ልጅ መሆኑን ያልተረዳ የንጉስ ልጅ ቆሻሻ ሰፈር ቢውል፣ ለምኖ ቢበላ አይገርምም❗ በየመድረኩ አሁን ያለንበት አዘቅት ይነገረናል። ግን ምን እንደለበስን አይነገረንም።
አቤት! በክርስቶስ የለበስነውን ክብር ብናውቅ! ..እንኳን ኃጢአት፡ የምድር ክብሯ እራሱ አይመጥነንም እኮ!
🙏ጌታ አይኖቻችንን ይክፈትልን🙏 🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው።
— ኦሪት ዘጸአት 14:14 Amharic Bible Bot

መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
— የሐዋርያት ሥራ 4:12 Amharic Bible Bot

ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥ ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፥ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፥ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ። እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤ እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤ የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል። የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንና መልካም መንገድን ሁሉ ታስተውላለህ። ጥበብ ወደ ልብህ ትገባለችና፥ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለችና፤ ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል፥ ከክፉ መንገድ አንተን ለማዳን፥ ጠማማ ነገርን ከሚናገሩም ሰዎች፤ እነርሱም በጨለማ መንገድ ይሄዱ ዘንድ የቀናውን ጎዳና የሚተው፥ ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው በጠማማነትም ደስታን የሚያደርጉ፥ መንገዳቸውን የሚጠመዝዙ አካሄዳቸውንም የሚያጣምሙ ናቸው፤ ከጋለሞታ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃልዋን ከምታለዝብ ከሌላዪቱም ሴት፤ የሕፃንነት ወዳጅዋን የምትተው የአምላክዋንም ቃል ኪዳን የምትረሳ፤ ቤትዋ ወደ ሞት ያዘነበለ ነው፥ አካሄድዋም ወደ ሙታን ጥላ። ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ የሕይወትንም ጎዳና አያገኙም፤ አንተም በደጋግ ሰዎች መንገድ እንድትሄድ የጻድቃንንም ጎዳና እንድትጠብቅ። ቅኖች በምድር ላይ ይቀመጣሉና፥ ፍጹማንም በእርስዋ ይኖራሉና፤ ኃጥኣን ግን ከምድር ይጠፋሉ፥ ዓመፀኞችም ከእርስዋ ይነጠቃሉ። — መጽሐፈ ምሳሌ 2
🙏 SHARE 🙏 👉 JOIN:@LIVINGWORD11

እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። — መዝሙረ ዳዊት 121:7 🙏SHARE | SHARE🙏 👉 JOIN: @LIVINGWORD11
እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። — መዝሙረ ዳዊት 121:7
🙏SHARE | SHARE🙏 👉 JOIN: @LIVINGWORD11

Petition: Until when have you finished? Until when will you turn your face away from me? Until when will I take counsel in my spirit? Until when will I be in anguish in my heart? Until when will my enemy be exalted over me? Petition, my God; hear me; answer me. My enemy, let him not say, 'Let him who mocks me say, "I have triumphed," and let him who hates me not be glad when I am brought low. But I will trust in your mercy; my heart will rejoice in your salvation. I will praise the Lord, for he has helped me; I will sing to the name of the Most High God. — Psalms of David 13 Amen 🥰🙏

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። — መዝሙረ ዳዊት 23
     🫴 " Join "  በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉን፦                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11                        🫶 JOIN: @LIVINGWORD11

ጣፍጥልኝ | Yosef Aschalew (feat. Helina Dawit) የትም ቦታ ስለአንተ ብቻ ላውራ 🥰
ተገበዙልኝ በጣም ምወደው መዝሙር ነው!!
    🙏SHARE  |  SHARE🙏     👉 JOIN: @LIVINGWORD11 👉 JOIN: @LIVINGWORD11