es
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Ir al canal en Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 310
Suscriptores
-524 horas
-227 días
-8430 días
Archivo de publicaciones
🇷🇺 ሩሲያ የተፈጠረባትን የጋዛ እጥረት ለማሟላት፣ ካዛኪስታን ጋዝ እንድትሰጣት ጠይቃለች።
🇷🇺 ሩሲያ የተፈጠረባትን የጋዛ እጥረት ለማሟላት፣ ካዛኪስታን ጋዝ እንድትሰጣት ጠይቃለች።

🇷🇺 የሩሲያን መርከብ ካገኛችሁ አግቱ፣ ዝረፉ፣ ገንዘቡን ውሰዱ፣ ሆኗል ሕጉ፣ ነጣ ገንዘብ። እንግሊዝ ባለፈው ወር 'ማዕቀብ ጥሷል' በሚል የያዘችውን የሩሲያን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ ነዳጁን ሸጣ ገን
🇷🇺 የሩሲያን መርከብ ካገኛችሁ አግቱ፣ ዝረፉ፣ ገንዘቡን ውሰዱ፣ ሆኗል ሕጉ፣ ነጣ ገንዘብ። እንግሊዝ ባለፈው ወር 'ማዕቀብ ጥሷል' በሚል የያዘችውን የሩሲያን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ ነዳጁን ሸጣ ገንዘቡን ለዩክሬን ጦርነት ማስኬጃ ልትሰጥ እንደሆነ አስታወቀች። ከኡራል ሩሲያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መርከብ በእንግሊዝ ቻናል ሲያልፍ ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው። የሩሲያን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ከዚህ በፊት ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ስኮትላንድ፣ እንግሊዝ፣ ዩክሬን ይዘው ገንዘቡን ወደ ኪሳቸው ከተዋል። ሩሲያ፣ የተነፈሰችው የለም። *-*-*-*- እነዚህ ሀገሮች፣ አንዳቸውም፣ የኢራንን መርከብ ይዘው መሸጥ አይደለም፣ ይዘው ሳምንት ለማሳደር እንኳ አይደፍሩም። ድንገት እንኳ ከያዙ፣ አንዲት ነገር ሳትጫር ይመልሳሉ። ያን ያህል ነው፣ የፑቲን ሩሲያ በፑቲን አመራር ሥር ዛሬ የተናቀችው። ምንምም እንደማያመጡ እንግሊዝ በልታቻቸዋች።

🇺🇦🇷🇺⚡️ፑቲን ሩሲያን ጉድ ሰርተናታልከባባድ መሳሪያዎቿን ከግንባር እያወጣች ወደ መሃል ሀገር እየሰበሰበች ነውካሁን በኋላ መደበቂያ አይኖርም - ፕሬዝዳንት ቮልድማየር ዘለንስኪ
የስለላ ተቋሞቻቸን እና ጦር ሠራዊቱ ሩሲያውያን ጦርነቱን ለማስፋት በሚጠቀሙባቸው ተቋማቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ መመሪያ ሰጥቻለሁ። ብዙ ወታደራዊ ተቋሞቻቸውን፣ የምርምር ማዕከሎቻቸውን መምታት ችለናል፣ ኢንዱስትሪዎቻቸውን፣ በተለይ የኃይሉን፣ አሽመድምደናል። በግልፁ እላለሁ፣ ሁሉም የሩሲያ ግዛቶች ዒላማዎቻችን ናቸው። መግባት፣ መምታት ችለናል። ድብቅነት አብቅቷል። ሁሉም ሩሲያዊ ዛሬ ጦርነቱ ተሰምቶታል፣ እያመመው ነው። በአሁኑ ጊዜ የሩስያ አመራር ተጨማሪ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ወደ ሞስኮ፣ ወደ ፑቲን መኖሪያ ቫልዳይ እየጎተተ ነው፣ ይህም በሌሎች አካባቢዎች የአየር መከላከያ እንዳይኖር አድርጓል። በሞስኮ ክልል ውስጥ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ማስወንጨፊያዎች S-400 ፣ S-500 እና Pantsir ስርዓቶችን አሰባስበዋል። ከሌሎች የሩሲያ ክልሎች ወደ 90 የሚጠጉ የአየር መከላከያ ማስወንጨፊያዎችን ወደ ፑቲን መኖሪያ ቫልዳይ ያዛወሩ ሲሆን የሩስያ አመራር ሰላምና ደህንነትን ለመጠበቅ ልዩ የአየር መከላከያ ክፍልም እየተቋቋመ ነው።  ቅድሚያ የሚሰጧቸው ነገሮች ለእነዚህ ነው። ለሕዝብ አይደለም። የራሳቸውን ኃይል እየጠበቁ ነው - የዚህን ጦርነት ምንጭ እየጠበቁ ነው። ዛሬ፣ ከ 60 በላይ የሩሲያ ክልሎች የነዳጅ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ራሽን የተጀመረባቸው ክልሎች በርካታ ናቸው። የሩስያ የጸጥታ አገልግሎቶች ከገዥው ፓርቲ ዩናይትድ ሩሲያ እጩዎችን ለስቴት ዱማ የመምረጥ ሥነ ሥርዓትን ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ወይም ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ሀሳብ አቅርበዋል ተብሏል። አደጋ አለ።


🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን፣ ምሽቱን የድሮን መዓት፣ ከክሩዝ ሚሳዬሎች ጋር ደበላልቃ ወደ ሩሲያ ግዛቶች ልካለች።
🇷🇺⚡️🇺🇦 ዩክሬን፣ ምሽቱን የድሮን መዓት፣ ከክሩዝ ሚሳዬሎች ጋር ደበላልቃ ወደ ሩሲያ ግዛቶች ልካለች።

🇮🇷 ኢራን በአንድ ቀን 20 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ችላለች።
🇮🇷 ኢራን በአንድ ቀን 20 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ችላለች።

⚡️🇪🇹 ጊቤ መርከብ መንገድ ጀመረች። ለአምስት ወራት ሻርጃ ወደብ አካባቢ የከረመችው ጊቤ መርከብ ትላንት ማምሻውን የሆርሙዝ ወሽመጥን ማለፍ መቻሏ ታወቀ። አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የሆርሙዝ መተላለፊያ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች የፋርስ ባህረሰላጤ ወደቦች ላይ መልህቃቸውን ጥለው እንዲጠባበቁ ተገደው ነበር። ከነዚህም መካከል ጊቤ አንዷ ነበረች። *-*-*- አይ ጊቤ! አንቺም እንደ ትልልቆቹ ቆመሽ ከረምሽው? የሕፃናት አልሚ ምግብ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ እና የሚረጋውን የካምቦዲያ ዘይት ነው የጫንነው ብትሏቸው እኮ፣ ኢራኖች ራሱ ያሳልፏችሁ ነበር።

: 🇺🇸🇱🇾⚡ - "የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ የሀገሪቱን ታሪካዊ ውህደት መደበኛ ለማድረግ፣ ከምሥራቅ እና ምዕራብ ሊቢያ ተወካዮችን ወደ ዋሽንግተን ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል" Reuters

🇸🇩🇸🇴🇪🇷🇪🇹 የምሥራቅ ሊቢያ መንግሥት፣ አራት የአፍሪካ የደሃ ደሃ ሀገር ዜጎችን ወደ ሀገሩ እንዳይገቡ ከለከለ። በእነዚህ ሀገር ዜጎች ላይ የተጣለው ክልከላ፣ በባሕርም፣ በየብስም፣ በአ
🇸🇩🇸🇴🇪🇷🇪🇹 የምሥራቅ ሊቢያ መንግሥት፣ አራት የአፍሪካ የደሃ ደሃ ሀገር ዜጎችን ወደ ሀገሩ እንዳይገቡ ከለከለ። በእነዚህ ሀገር ዜጎች ላይ የተጣለው ክልከላ፣ በባሕርም፣ በየብስም፣ በአየርም እንደሆነ ተነግሯል። ምሥራቅ ሊቢያ እነዚህ የደሃ ደሃ ሀገር ዜጎች ወደ አውሮፓ የሚሻገሩበት ቁልፍ መተላለፊያ መስመር እንደሆነ ይታወቃል። ከኢትዮጵያ በተሻለ ሰላማቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ ከሚያስጠብቁት እና ከተረጋጉት፣ እንደ ኒጀር፣ ቻድ እና ጊኒ እንዲሁም የተቀረው የአፍሪካ ሀገራት፣ ዜጎች ወደ ሊቢያ እንዳይገቡ አልተከለከሉም። --- ከአራቱ የደሃ ደሃ ሀገሮች መካከል ደግሞ፣ የኛዋ ሦስተኛ የተሻለችው ሳትሆን አትቀርም።

🇷🇺 በዚህ ቀን፣ ከ 3 ዓመት በፊት፣ የሩሲያ PMC ዋግነር ቡድን በሩሲያ መንግሥት ላይ አመፅ አስነሳ። በዩክሬን ዋግነርን የመራው ሩሲያዊው Yevgeny Prigozhin, በግንባር የሩሲያን ጦር
+9
🇷🇺 በዚህ ቀን፣ ከ 3 ዓመት በፊት፣ የሩሲያ PMC ዋግነር ቡድን በሩሲያ መንግሥት ላይ አመፅ አስነሳ። በዩክሬን ዋግነርን የመራው ሩሲያዊው Yevgeny Prigozhin, በግንባር የሩሲያን ጦር ሠራዊት አባላት ሬሳ መሬት ላይ ዘርግቶ፣ 'አስጨረሳችሁን' በማለት በሩሲያ መንግሥት ላይ ዛተ። ፑቲን የጦር ሚኒስትሩን እንዲያባርር እና ጦሩን በአዲስ መልክ እንዲያዋቅር ከግንባር ሆኖ ተማፀነ። በስተመጨረሻም፣ ጦሩን እየመራ ሩሲያ ገባ፣ ከተማ ያዘ፣ ሕዝቡም፣ ሞስኮ ሂድ ከጎንህ ነን እያሉ በድጋፍ ከነ ሠራዊቱ ሲሸኙት ታይቷል። መሸ፣ ነጋ። ፑቲን ቤላሩስ እንድታሸማግለው ጠየቀ። የቤላሩስ ፕሬዝዳንት Yevgeny Prigozhin አነጋግሮ 'ሂድ ክሬምሊን፣ ከፑቲን ጋር በውይይት ፍታ' አለው። ሄደ፣ ተጨባበጠ፣ ፎቶ ተነሱ፣ ችግሩ ሁላ ይፈታል አሉት። በአይሮፕላን ከባልደረቦቹ ጋር ወደ ግንባር ሲመለስ ግን አይሮፕላኑ አየር ላይ ፈነዳ። ሞተ። አይሮፕላኑ ተመትቶ፣ ከውስጡ ፈንድቶ አልታወቀም ተባለ። Wagner PMC በዚሁ አብቅቷል። ዋግነር PMC ከሩሲያ ጦር ጋር ከግንባር እንደተመለሰ በመጠኑ ተዋግቷል። 6 የሩሲያ ሄሊኮፕተሮች ተመትተዋል። 11 ታንኮች ወድመዋል። ከ25-29 የሩሲያ ወታደሮች ተገድለዋል። ከWagner በኩልም በርካታ መኪኖች፣ ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እና ሠራዊት አባላት ተገድለዋል። ከዚያ በኋላ፣ አሁን፣ ነገሮች ተባብሰዋል። በፑቲን አመራር ሥር ሀገሩ መቀመቅ ውስጥ ነው። የሚታይ ነው፣ የተደበቀ አይደለም። ደጋግሜ የምለው ነው፣ የሩሲያ ታሪክ ቀልድ አያውቅም፣ ፑቲን በያዘው መንገድ የሚያስቀጥለው አይኖርም። ዓይናቸው እያየ ሀገራቸው ስትነድ ለማየት ይከብዳል። ፑቲን ብዙ ነገር በጦርነቱ አበለሻሽቷል። ይመለሳል ወይስ ይገለብጡታል?

🇮🇷🇺🇸 ፖይለቱ ያየውን የገለጠበት ሁኔታ
🇮🇷🇺🇸 ፖይለቱ ያየውን የገለጠበት ሁኔታ

🇵🇰🇮🇷🇺🇸 'ሊያበላሹት ይፈልጋሉ' - የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሸሪፍ፣ የአሜሪካ-ኢራን ውይይቶችን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ሀገራትን አስጠንቅቀዋል ‹‹አንዳንድ ደስተኛ ያልሆኑ ሀገራት ግራ መጋባትን፣ ጥርጣሬን እና እርግጠኛ አለመሆንን እየፈጠሩ ነው›› ‹‹ወንድማማቾቻችን እንደ ብረት ቅጥር በእነርሱ ላይ ይቆማሉ›› *-*-*- ማንን እያለ እንደሆነ የሚጠፋው የለም መቼስ። ፖርታ ሪኮን ይሆን?

🇺🇸 የዋሽንግተን ዲሲን የውሃ ገንዳ የተመለከቱት memes አስቂኝ ናቸው።
+5
🇺🇸 የዋሽንግተን ዲሲን የውሃ ገንዳ የተመለከቱት memes አስቂኝ ናቸው።

🇪🇹⚡️ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የእገታ እና ጠለፋ ካፒታል እየሆነች ነው። የባዕዳን ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን ሰው ለመጥለፍ ተመራጭ አድርገዋታል። በዜግነት ፖኪስታናዊ የሆኑ ግለሰቦች፣ በአዲስ አበባ ቤ
+5
🇪🇹⚡️ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የእገታ እና ጠለፋ ካፒታል እየሆነች ነው። የባዕዳን ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን ሰው ለመጥለፍ ተመራጭ አድርገዋታል። በዜግነት ፖኪስታናዊ የሆኑ ግለሰቦች፣ በአዲስ አበባ ቤት ተከራይተው ሰው ሲጠልፉና ሲያግቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል። እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለምን ጉዳይ እንደሚመጡ የማይታወቁ ሕንዳዊያንንና ባንግላዴሻዊያንን እያፈኑ ወደ ተከራዩት ቤት በመውሰድ፣ አስረው እየደበደቡና ቪዲዮ እያነሱ ለቤተሰቦቻቸው በመላክ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆይተዋል፣ ብሏል ፖሊስ። ተጠርጣሪዎቹ በአሁኑ ሰዓት ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ እና በእስር ላይ እንዳሉ ተነግሯል።

🇺🇸🇮🇷 CNN ብቻ ባገኘው ዘገባ መሠረት፣ በጦርነቱ ወቅት በኢራን የተከሰከሰው ፓይለት ለአሜሪካ ደህንነት አባላት የሰጠውን ቃል አዳምጧል። ፓይለቱ አይሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት ያየው ነገር እጅ
+1
🇺🇸🇮🇷 CNN ብቻ ባገኘው ዘገባ መሠረት፣ በጦርነቱ ወቅት በኢራን የተከሰከሰው ፓይለት ለአሜሪካ ደህንነት አባላት የሰጠውን ቃል አዳምጧል። ፓይለቱ አይሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት ያየው ነገር እጅግ ያስደነገጠው እንደነበር፣ ከዚህ በፊትም እንዳላየ ተናግሯል። የኢራን ድሮኖች በአንድ ተጣምረው በሰማይ ላይ እንደ ግዙፍ ጄሊፊሽ ሲንሳፈፉ እንዳየ፣ ትልልቅ ድሮኖች ከላይ፣ ትንንሽ ድሮኖች ከታች እንደ እግር ሆነው ሲጠጉት እንደተመለከተ ተናግሯል። እጅግ ያስፈሩ እንደነበርና "ኤልያን እንደመሰሉት" ቃሉን ሰጥቷል። የደህንነት ባለስልጣናቱ፣ ጤናውን በመጠራጠር "እርግጠኛ ነህ ይሄን አይተሃል?" እያሉ ጠይቀውታል፣ ቅዠት ነው፣ አእምሮው ጧ ብሎ ነው ብለው በማሰብ። የሚለው እውነት ከሆነ ይላሉ እኒህ የደህንነት ባለስልጣናት፣ "ጉዳችን ፈልቷል፣ ኢራን ካሰብነው በላይ በድሮን ቴክኖሎጂ ሄዳለች።" ፖይለቱ በሰጠው ቃል ላይ ተመርኩዘው የደህንነቱና የፔንታገን ባለስልጣናት ከፍተኛ መደነጋገጥና ሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል። ብሏል ዘገባው። ኢራን አሳየች የተባለው ቴክኖሎጂ አሜሪካ አልደረሰችበትም። *-*-*- ሙሉውን የCNN መረጃ ብትችሉና ብታነበት ጥሩ ነው። ኢራን ዛሬ ላይ በድሮን ቴክኖሎጂ በዓለም ግንባር ቀደም ሆናለች።

🇵🇰🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት ወደ ፖኪስታን ሲገባ፣ የፖኪስታን አየር ኃይል እጀባ አድርጎለታል። ሕንዶች፣ ፖኪስታን ከ$300 ቢሊዮን ዶላሩ ላይ ይቦጨቅልኛል ብላ ቋምጣለይ ይላሉ።

🇮🇷 🇺🇸የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ኢራን በኋታር በኩል $12 ቢሊዮን ዶላር እንደተለቀቀላት አረጋገጠ።
🇮🇷 🇺🇸የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ኢራን በኋታር በኩል $12 ቢሊዮን ዶላር እንደተለቀቀላት አረጋገጠ።

🇮🇱🇵🇸⚡️ - የእስራኤል ዲያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አሚቻይ ቺክሊ፡ - ፈጣሪ አይበለውና ይሄ Clown (ናፍታሊ ቤኔት) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ የፍልስጤም መንግስት ይመሰረታል። በዚህ መንግሥት የተከናወነው ነገር ሁሉ፣ ከነችግሮቹ እና ተግዳሮቶቹ፣ ገደል ይገባል።

🇮🇱🇺🇸⚡️ - የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት - እስራኤል ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ "እስራኤል" የሚለው ብራንድ ስም በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያለው ተወዳጅነት ኔጌቲቭ ገብቷል። ይሄ ክስረት ነው፣ ከስረት ነው!

🇮🇱⚡️ - የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት፡ የተበላሸውን እስራኤልን ገጽታ ለመቀልበስ ከፊታችን ትልቅ ሥራ አለብን። በእስራኤል መንግሥት ውስጥ ከቀን ወደ ቀን ለማንም የማይጠቅሙ፣ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ እና ውድ የፖለቲካ ካፒታልን የሚያሟጥጡ እና የሚያባክኑ አልባሌ ንግግሮችን የሚናገሩ ጨቅላ ሚኒስትሮችን በመተካት ይጀምራል።