የቀጠናው ተመልካች
Ir al canal en Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 301
Suscriptores
-624 horas
-247 días
-9030 días
Archivo de publicaciones
4 301
🇮🇱⚡️ከአይሁድ እምነት ቅድስተ ቅዱሳን የጸሎት ቦታ የምሥራቅ ግንብ፣ የማለዳ ጸሎት አድራሾች፣ በጸጥታ አካላት ቦታውን እንዲለቁ ተነግሯቸዋል።
4 301
🇮🇱🇺🇦 አንዳንዶች፣ በሁለቱ የዓለማችን አደገኛ ቀጠናዎች የሚገኙት፣ ሁለቱ 'በአምላክ የተመረጠ ሕዝብ' ተወካዮች፣ ዓለምን ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት እያንደረደሩት ነው፣ ይላሉ።
4 301
+1
🇮🇷🇮🇱 ሰበር ዜና!! በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ጥቃቶች መደርሳቸው ተረጋግጧል!!!
ኢራን እና የመን ዛሬ በእስራኤል ላይ በጣም ትልቅ የጋራ ጥቃት ሰንዝረዋል።
የሚሳይል ማስወንጨፊያዎች በመላው ኢራን ከበርካታ አካባቢዎች መተኮሳቸውን ቀጥለዋል።
4 301
🇮🇷⚡️🇮🇱 ተናግረን ሳንጨርስ፣ ሚሳዬሎች ወደ እስራኤል ከኢራን ተተኩሰዋል። ኢየሩሳሌም፣ ማዕከላዊ እና ሰሜን እስራኤል ሳይረኖች እየጮሁ ነው።
4 301
🇮🇱 እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርጋቸው ጥቃቶች ለአሁን ቆም ብለዋል።
🇮🇷 ኢራን የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ ይጠበቃል።
*-*-*--*
ካሁን በኋላ ኢራን በመልስ ምት የምታጠቃ አይመስለኝም፣ ምክኒያቱም የሚፈለገውን መልዕክት ለእስራኤል አስተላልፋለችና፡ "ሊባኖስን መንካት፣ ዋጋ ያስከፍላል።"
በሌላ በኩል፣ እስራኤል በምትፈልገው ደረጃና መጠን ኢራንን እንዳታጠቃ እጇ በአሜሪካ የታሰረ ይመስለኛል። እስራኤሎች ፈልገው የነበረው የኢራንን መሠረተ ልማቶች በተቻለ ለማውደም ነበር። ለዚያም ትራምፕ አረንጓዴ መብራት እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር። ትራምፕም መልስ ምት ከፈለጋችሁ፣ ይሄ ነው የማይባል አነስተኛ ዒላማዎችን ለይስሙላ ምቱ፣ ነገር ግን ከዛ ያለፈ ድብደባ እንዳታደርጉ፣ ያላቸው ይመስለኛል። እንዲያ ከሆነ ኢራን ተቆጥታ ድርድሩ ውሃ ሊበላው ስለሚችል። ያንን ደግሞ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ አትፈልግም።
የሚሆነውን እናያለን።
4 301
🇮🇷⚡️🇮🇱 | ባለፉት ሁለት ሰዓታት ውስጥ፣ እስራኤል የአየር ላይ ጥቃቶችን፣ ከሜዲትራኒያን ባሕር ከሚተኮሱ የባሊስቲክ እና የክሩዝ ሚሳዬሎች ጋር በማጣመር፣ በኢራን ላይ ትልቅ የጦር ጥቃት ሰንዝራለች።
የመጀመሪያው የጥቃት ማዕበል እንደተጠናቀቀ የተዘገበ ሲሆን፣ በቴህራን፣ በካራጅ፣ በናጃፋባድ፣ በታብሪዝ፣ በኡርሚያ እና በካርግ ደሴት ላይ ጥቃቶች እንደተካሄዱ ተዘግቧል።
4 301
🇮🇷⚡️🇮🇱 | ባለፉት ሁለት ሰዓታት ውስጥ፣ እስራኤል የአየር ላይ ጥቃቶችን፣ ከሜዲትራኒያን ባሕር በሚተኮሱ የባሊስቲክ እና የክሩዝ ሚሳይል ጋር በማጣመር፣ በኢራን ላይ ትልቅ የጦር ጥቃት ሰንዝራለች።
የመጀመሪያው የጥቃት ማዕበል እንደተጠናቀቀ የተዘገበ ሲሆን፣ በቴህራን፣ በካራጅ፣ በናጃፋባድ፣ በታብሪዝ፣ በኡርሚያ እና በካርግ ደሴት ላይ ጥቃቶች እንደተካሄዱ ተዘግቧል።
4 301
🇸🇦🇮🇷 ሰበር ዜና፦ በሳዑዲ ፕሪንስ ሱልታን አየር ኃይል ማዕከል፣ አል-ካርጅ፣ በአሁኑ ጊዜ በባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃት ሥር ነው።
ኢራን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የሰነዘርኩት ጥቃት የለም ብላለች።
ምናልባት ከየመን ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።
4 301
+8
🇮🇷⚡️🇮🇱 እስራኤል ኢራን ላይ ሌሊቱን ጥቃት ሰነዘረች። ከዒላማዎቹ መካከል የሚሳዬል ማስወንጨፊያ ቦታዎች፣ የድሮን መጋዘኖች፣ የኢራን የአየር መከላከያ ቦታዎች እና ሌሎች ተዛማጅ መሠረተ ልማቶች ይገኙበታል።
እስካሁን የተረጋገጡ ዒላማዎች
● በቴህራን የሚገኘው የመህራባድ አውሮፕላን ማረፊያ
● በናጃፋባድ የሚገኘው የድሮን ማሰባሰቢያ መጋዘን
● የግድያ ሙከራዎች እና/ወይም የIRGC ተቋም
● በታብሪዝ የሚገኝ የባሊስቲክ ሚሳይል ጣቢያ
● በሺራዝ እና በኢላም ውስጥ ወደ 15 የሚጠጉ ዒላማዎች።
● በካርግ ደሴት ላይ የሚገኝ የሚሳይል ጣቢያ ናቸው።
4 301
🚨 የቴህራን ሕዝብ ቴል አቪቭ ላይ ጥቃት እንዲደረግ ምሽቱን በአደባባይ እየጮኸ ታይቷል።
በመሃል ቴህራን በሚገኘው በኤንግሄላብ አደባባይ የተሰበሰቡ ሰዎች እንዲህ እያሉ ሲጮኹ ተሰምቷል፦
“ሰይድ መጂድ፣ ጋኔኑን ምታ! ዛሬ ማታ፣ ቴል አቪቭን ምታ!”
4 301
🇺🇦🇷🇺- በሩሲያ፣ በኡስት-ላቢንስክ የሚገኘው የነዳጅ ማከማቻ፣ በጠዋት ላይ የዩክሬን ጥቃቶች ከተከሰቱ በኋላ እስከ አሁን እየተቃጠለ ነው።
ባሳለፍናቸው ጥቂት ሳምንታት በሩሲያ መሠረተ ልማቶች ላይ የዩክሬን ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። በዚህም የተነሳ በአንዳንድ ከተሞች በማደያዎች ረጃጅም ሰልፎች መታየት ጀምረዋል።
4 301
🇮🇷 🇮🇱 - እስራኤል የበቀል እርምጃ ካልወሰደች በስተቀር፣ ቴህራን በእስራኤል ላይ የሚደረጉ ጥቃቶቿን እንዳጠናቀቀች እና ተጨማሪ ጥቃቶችን እንደማትፈጽም፣ ኢራን በሶስተኛ ወገኖች በኩል ለእስራኤል መልእክት ልካለች፣ የእስራኤል ቻናል 11
4 301
🇺🇸🇮🇷🇮🇱⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ Fincial Times እንደተናገሩት
ኢራን በእስራኤል ላይ የሰነዘረችው ጥቃት በድርድሮች ላይ “ምንም ተጽዕኖ” አይኖረውም። ይሄኮ በዚያ አካባቢ፣ ለ3,000 ዓመታት ወይም ለ47 ዓመታት፣ እንደ አቆጣጠርህ ነው፣ ሲደረግ የቆየ ነው። ኢራን ጋር ስምምነት ላይ እንደርሳለን የሚል ተስፋ አለኝ።
4 301
🇬🇧🇮🇷🇮🇱🇺🇸⚡️ — የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢቬት ኩፐር፦
በኢራን እና በእስራኤል መካከል የግጭት መቀጣጠል ለማንም ጥቅም የለውም። ሁለቱም ወገኖች ራሳቸውን መገደብ እና ወዲያውኑ እልባት ማምጣት አለባቸው። በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም የዓለም ንግድ ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ እና ሁላችንም የምንፈልገውን ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ድርድሮች መቀጠል አለባቸው።
4 301
🇵🇰🇺🇸🇮🇷⚡️ — የፓኪስታን ምንጭ ለእስራኤል ሃዮም፦
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ፈጣን ጊዜያዊ ስምምነት ላይ እየደረስን ነው።
መጪው፣ ወይ ፈጣን ስምምነት ነው ወይም የድርድሩ መፈራረስ ነው።
4 301
🇹🇷❌🇮🇱 — የአንካራ ከንቲባ ማንሱር ያቫሽ፣ ለእስራኤል መከላከያ ሚንስቴር፡
በኢየሩሳሌም ላይ አስደንጋጭ ድርጊት እየፈጸመ ያለውን የእስራኤል ሚኒስትር ላስታውስ እወዳለሁ። ማንም ሰው፣ የቱርክ ሪፐብሊክን እና የቱርክ ሕዝብን ከበላይ ሆኖ ሊያስተምር ወይም ስለ ታሪካችን በጣት እየጠቆመ ሊነግረን አይችልም። የአታቱርክን ስም ከመናገርዎ በፊት፣ የራስዎ መንግስት በአለም አቀፍ ሕግ ፊት ያለውን ሪኮርድ ይመልከቱ! ቱርክን ለመቃወም ለሚሞክሩ የምሰጠው ምክር፦ ከታሪክ ትምህርት ውሰዱ፣ ባዶ የቃላት ጨዋታ አትጫወቱ።የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር፣ የቱርክ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን፣ አንት በጬ፣ ኢየሩሳሌም ቆስጠንጢኖስ መሰለችህ እንዴ? ሲል መልሶለታል።
4 301
🇺🇸🇮🇷🇮🇱⚡️- "ኔታንያሁ "በሆነ መንገድ" እስራኤል ለኢራን የምትሰጠውን ምላሽ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ተስማምቷል" - አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ለእስራኤል ቻናል 12 ተናግሯል።
