es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Ir al canal en Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
193
Suscriptores
-224 horas
-47 días
-630 días
Archivo de publicaciones
ለዱዓት ~ ህዝባችንን ማንቃት፣ መሰረታዊ የዲኑን ክፍሎች እንዲለይ ማስተማር አብዝተን ልንረባረብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ስንፍናን እናባር። ኪታብ ማስተማር፣ በደዕዋ መጠመድ፣ በማህበራዊ መገናኛዎች በየዘርፉ መሳተፍ ችላ ልንለው የሚገባ ጉዳይ አይደለም። እኛ እንጣር። ለውጡ በአላህ ፈቃድ ይመጣል። ሰሞንኛ ግርግር ትኩረታችንን አይወስደው። ፖለቲካው አይወስውሰን። የጎን መገፋፋት ጊዜያችንን ትኩረታችንን ሁሉ አይውሰድብን። የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጣም ተለዋዋጭ ነው። ነገ ለማስተማር ፈታኝ ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል። የምንችልባቸውን ጊዜያትና ቦታዎች በሚገባ መጠቀም አለብን። ደዕዋችን ሁለገብ ይሁን። በተወሰኑ ነጥቦች ላይ ተገድቦ ጠዋት ማታ መነዛነዝ መንገድ የሳቱ አካላት አንድ መታወቂያ ነው። ስለዚህ በዐቂዳው፣ በአኽላቁ፣ በፊቅሁ፣ በሲራው፣ ቁርኣን በማስተማሩ፣ ... ስንገባ አንዱ ዘርፍ ለሌላው ደጋፊ ይሆናል። ዲኑንም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተመለከትን ማለት ነው። መዘጋጀት እንልመድ። ለደርስ ተዘጋጅተን እንቅረብ። ለደዕዋ ተዘጋጅተን እንነሳ። እናዳምጥ። እናንብብ። የእውቀት አድማሳችንን እናስፋ። እስቲ በዚህ አመት ስንት ኪታብ አነበብን? ስንት ደርስ ተከታተልን? እንዴት ጧሊበል ዒልም የሆነ ሰው ከአመት እስከ አመት ያለ ንባብ ያሳልፋል? ይሄ በጣም መታረም ያለበት ነው። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

የማለዳ መልእክት (ቁጥር 12) ~ ኢብኑ ዐብዲልበር (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ፦ "አስተዋይ የሆነ አማኝ የትኛዋንም በጎ ተግባር ሊንቅ አይገባውም። ምናልባትም ምህረት የሚያገኘው በትንሿ ሰበብ
የማለዳ መልእክት (ቁጥር 12) ~ ኢብኑ ዐብዲልበር (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ፦ "አስተዋይ የሆነ አማኝ የትኛዋንም በጎ ተግባር ሊንቅ አይገባውም። ምናልባትም ምህረት የሚያገኘው በትንሿ ሰበብ ሊሆን ይችላልና።" [አት-ተምሂድ፡ 13/539] ጥልቀት ያለው ኢኽላስ፣ አላህ እየተመለከተኝ፣ እየተከታተለኝ ነው የሚል ፅኑ እምነት (ሙራቀበህ) ትንሽን ተግባር ትልቅ ዋጋ እንዲኖረው ያደርጋል። እስቲ ከሰው እይታ ገለል በልና ከልብህ ተመስጠህ ዱዓእ አድርግ። ስብር ብለህ አልቅሰህ ጌታህን ለምነው። የምትስድቀው የረባ ነገር የለህም እንበል። እስቲ የዛሬ ሻይ፣ ማኪያቶ፣ የታክሲ፣ ምሳ ይቅርብኝ ብለህ ልጆቿን ይዛ መስጂድ በር ጥግ ላይ ኩርትም ብላ የወደቀችን እናት በሆነ መንገድ አግዛት። የኣኺራው ምንዳ የትና የት ነው። በዱንያ ራሱ ለሌሎች ሲሉ ትንሽም ብትሆን መስዋእትነት መክፈል ላጣጣመውኮ ጣእሙ ልዩ ነው። ዋናው ነገር አላህ ይታሰብበት። አቅሙ ካለህ ደግሞ በምን ለኣኺራዬ ተሻጋሪ ነገር ልስራ ብለህ አስብና አንድ ነገር ወስን። ትኩረት ባለመስጠታችን ስንት ኸይር ስራ ያልፈናል! እያሰብን ወገኖች! በዙሪያችን በየ እለቱ ብዙ የኸይር ገበያ አለ። አላህ ለመልካሙ ይወፍቀን። (ረጀብ 15/1447) = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

ጫት መቃም በሸሪአ እንዴት ይታያል?

* ኢንፍራሬድ የፎቶኮአጉሌሽን (Infrared Photocoagulation): በዚህ ሂደት ውስጥ የኢንፍራሬድ ብርሃን ሙቀትን በመጠቀም የኪንታሮቱን ሕብረ ሕዋስ እንዲደርቅና እንዲወድቅ ያደርጋሉ። * ቀዶ ጥገና (Haemorrhoidectomy): ከባድ ወይም ተደጋጋሚ ኪንታሮቶች ካሉ፣ ቀዶ ጥገና ኪንታሮቱን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ሊያስፈልግ ይችላል። መከላከል ኪንታሮትን ለመከላከል የሚረዱ ዋና ዋና መንገዶች የአንጀት እንቅስቃሴን መደበኛ ማድረግ እና በፊንጢጣ ደም ስሮች ላይ የሚፈጠረውን ጫና መቀነስ ነው። * ፋይበር የበዛበት ምግብ ይመገቡ። * ብዙ ውሃ ይጠጡ። * አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ። * የመፀዳዳት ፍላጎት ሲሰማዎት ወዲያውኑ ይሂዱ እና አይግፉ። * ከመጠን በላይ ክብደትዎን ይቀንሱ። * ለረጅም ጊዜ ከመቀመጥ ወይም ከመቆም ይቆጠቡ።

የፊንጢጣ ኪንታሮት (Haemorrhoids) ምንድን ነው ================================= የፊንጢጣ ኪንታሮት፣ ሄሞሮይድስ ተብሎ የሚጠራው፣ በፊንጢጣ አካባቢ ወይም በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ ደም ስሮች ሲያብጡ የሚከሰት የተለመደ ችግር ነው። እነዚህ ያበጡ ደም ስሮች እንደ መጠናቸው እና ቦታቸው ህመም፣ ማሳከክ፣ ምቾት ማጣት ወይም የደም መፍሰስ ሊያስከትሉ ይችላሉ። ኪንታሮት በወንዶችና በሴቶች ላይ በእኩልነት የሚከሰት ሲሆን በተለይም በዕድሜ እየገፉ ሲሄዱ ወይም አንዳንድ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የመከሰት ዕድሉ ይጨምራል። የፊንጢጣ ኪንታሮት ዓይነቶች በአብዛኛው ሁለት ዋና ዋና የኪንታሮት አይነቶች አሉ፦ 1. ውጫዊ ኪንታሮት (External Haemorrhoids): እነዚህ የሚከሰቱት ከፊንጢጣ መክፈቻ ውጭ ባለው ቆዳ ስር ባሉ ደም ስሮች ላይ ነው። እነዚህ ብዙ ጊዜ ይታያሉ ወይም ሲነኩ ይሰማሉ። ማሳከክ፣ ህመም እና የደም መፍሰስ ሊያስከትሉ ይችላሉ። የደም መርጋት በውስጣቸው ከተፈጠረ (thrombosed haemorrhoid) ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል ይችላል። 2. ውስጣዊ ኪንታሮት (Internal Haemorrhoids): እነዚህ የሚፈጠሩት በፊንጢጣ ውስጥ ነው። ብዙ ጊዜ ህመም አይሰማቸውም ምክንያቱም በዚያ አካባቢ ህመም የሚያስተላልፉ ነርቮች ጥቂት ስለሆኑ። ይሁን እንጂ አንጀት ሲጸዳ ደም መፍሰስ የተለመደ ምልክት ነው። አንዳንድ ጊዜ የውስጥ ኪንታሮቶች ከፊንጢጣ ውጭ ሊወጡ ይችላሉ (prolapsed hemorrhoids)። ይህ ሲሆን ህመም ሊሰማቸውና ሊያብጡ ይችላሉ። የፊንጢጣ ኪንታሮት መንስኤዎች ኪንታሮት የሚከሰተው በፊንጢጣ እና በፊንጢጣ አካባቢ ባሉት ደም ስሮች ላይ በሚፈጠር ግፊት መጨመር ምክንያት ነው። ለዚህ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የተለመዱ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። ✔️ ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት (Chronic Constipation): አንጀት በሚጸዳበት ጊዜ ከመጠን በላይ መግፋት በፊንጢጣ ደም ስሮች ላይ ጫና ይፈጥራል። ✔️ ተቅማጥ (Diarrheal): ተደጋጋሚ ተቅማጥም የደም ስሮችን ሊያበሳጭ ይችላል። ✔️ እርግዝና (Pregnancy): በእርግዝና ወቅት በማህፀን ላይ የሚፈጠረው ጫና፣ እንዲሁም በሆርሞን ለውጥ ምክንያት የደም ስሮች መስፋፋት ኪንታሮት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ✔️ ከመጠን ያለፈ ውፍረት (Obesity): ከመጠን በላይ ክብደት በፊንጢጣ አካባቢ ባሉት ደም ስሮች ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። ✔️ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ ወይም መቆም (Prolonged Sitting or Standing): ይህ በፊንጢጣ ደም ስሮች ላይ ጫና ሊጨምር ይችላል። ✔️ እርጅና (Aging): በእድሜ እየገፉ ሲሄዱ ፊንጢጣን የሚደግፉ ሕብረ ሕዋሶች እየላላ ይሄዳል። ✔️ ፋይበር የሌለው አመጋገብ (Low-Fiber Diet): በቂ ፋይበር አለመመገብ ለሆድ ድርቀት አስተዋጽኦ ያደርጋል። ✔️ ከባድ ነገሮችን ማንሳት (Heavy Lifting): ክብደትን በሚያነሱበት ጊዜ የሚፈጠረው ግፊት ኪንታሮት ሊያስከትል ይችላል። ምልክቶች # የኪንታሮት ምልክቶች እንደየአይነቱ እና እንደ መጠኑ ይለያያሉ። የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው። * ህመም ወይም ምቾት ማጣት: በተለይ በሚቀመጡበት ጊዜ ወይም አንጀት በሚጸዳበት ጊዜ። * ማሳከክ ወይም መበሳጨት: በፊንጢጣ አካባቢ። * የደም መፍሰስ: አንጀት ሲጸዳ ደማቅ ቀይ ደም በመጸዳጃ ወረቀት ላይ ወይም በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ማየት። (ይህ ምልክት ለሌሎች ከባድ የጤና ችግሮችም ሊሆን ስለሚችል የህክምና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው።) * እብጠት ወይም እብጠቶች: ከፊንጢጣ መክፈቻ አካባቢ የሚወጡ ወይም የሚሰማቸው እብጠቶች። * የአንጀት ሙሉ አለመሆን ስሜት: አንጀት ከተጸዳ በኋላም ሙሉ በሙሉ እንዳልጸዳ ስሜት ሊሰማ ይችላል። * ንፍጥ መውጣት (Mucus Discharge): አንዳንድ ጊዜ ከፊንጢጣ ንፍጥ ሊወጣ ይችላል። መቼ የህክምና እርዳታ ማግኘት አለብዎት? አብዛኛዎቹ ኪንታሮቶች በቤት ውስጥ በሚደረግ እንክብካቤ ሊሻሉ ቢችሉም፣ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የህክምና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው። * ከፍተኛ የደም መፍሰስ ካለ። * ከባድ ህመም ካለ። * የኪንታሮት ምልክቶች በሳምንት ጊዜ ውስጥ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ካልተሻሻሉ። * የአንጀት ልማድዎ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ካስተዋሉ። * ሰገራዎ ጥቁር ወይም ቀይ ሆኖ ከወጣ (ይህ ከፊንጢጣ በላይ ባለው የምግብ መፍጫ ሥርዓት ውስጥ የደም መፍሰስ ምልክት ሊሆን ይችላል)። * የደም ማነስ ምልክቶች (እንደ ድካም፣ የገረጣ ቆዳ) ካለብዎ። ህክምና እና የቤት ውስጥ እንክብካቤ ኪንታሮትን ለማከም እና ምልክቶቹን ለማስታገስ በርካታ መንገዶች አሉ። የቤት ውስጥ እንክብካቤ * ፋይበር የበዛበት ምግብ ይመገቡ: ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬዎች እና ሙሉ እህል የያዙ ምግቦችን መጨመር ሰገራን በማለስለስ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። * ብዙ ውሃ ይጠጡ: በቀን ከ6-8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ሰገራን ለማለስለስ ይረዳል። * የፋይበር ተጨማሪዎች (Fiber Supplements): እንደ Metamucil ወይም Citrucel ያሉ የፋይበር ተጨማሪዎች ሰገራን ለማለስለስ እና መደበኛ የአንጀት እንቅስቃሴን ለማበረታታት ይረዳሉ። * በሞቀ ውሃ ውስጥ መቀመጥ (Sitz Bath): በቀን ለ15-20 ደቂቃዎች በሞቀ ውሃ ውስጥ መቀመጥ ህመምን እና ማሳከክን ለመቀነስ ይረዳል። * ህመምን የሚያስታግሱ ክሬሞች/ቅባቶች: በሐኪም ትእዛዝ ውጭ የሚገኙ የኪንታሮት ቅባቶች (ለምሳሌ ሃይድሮኮርቲሶን የያዙ) ማሳከክን እና እብጠትን ለመቀነስ ይረዳሉ። * ህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች: እንደ አይቡፕሮፌን (Ibuprofen) ወይም ፓራሲታሞል (Paracetamol) ያሉ መድሃኒቶች ህመምን እና ምቾት ማጣትን ሊቀንሱ ይችላሉ። * አንጀት በሚጸዳበት ጊዜ አይግፉ: የመፀዳዳት ፍላጎት ሲሰማዎት ወዲያውኑ ወደ መፀዳጃ ቤት ይሂዱ እና ከመጠን በላይ ከመግፋት ይቆጠቡ። * ንፅህና: ከእያንዳንዱ የአንጀት እንቅስቃሴ በኋላ አካባቢውን በቀስታ ያፅዱ። ለስላሳ፣ ሽቶ የሌለው የመጸዳጃ ወረቀት ወይም እርጥብ የህፃናት መጥረጊያ (unscented baby wipes) ይጠቀሙ። የህክምና ህክምናዎች የቤት ውስጥ ህክምናዎች ካልሰሩ ወይም ኪንታሮቱ ከባድ ከሆነ፣ ዶክተርዎ የሚከተሉትን ሊመክር ይችላል። * የጎማ ባንድ ማስያዝ (Rubber Band Ligation): ይህ የተለመደ ሂደት ሲሆን ለውስጣዊ ኪንታሮት ያገለግላል። አንድ ትንሽ የጎማ ባንድ በኪንታሮቱ ስር በማስቀመጥ የደም አቅርቦቱን ያቋርጣሉ፣ ይህም ኪንታሮቱ እንዲደርቅና እንዲወድቅ ያደርጋል። * መርፌ መወጋት (Sclerotherapy): አንድ መፍትሄ ወደ ኪንታሮቱ ውስጥ በመርፌ መወጋት ኪንታሮቱ እንዲኮማተር ያደርጋል።

አንዳንዶች ግን የነብዩን ﷺ ኑዛዜ ጥሰው፣ አደራቸውን በልተው፣ አጥብቀው የከለከሉትን ጉዳይ በተቃራኒው አጥብቀው ያዘዙት በሚመስል ሁኔታ በታላላቅ ሰዎችና በሱፊያ ቁንጮዎች መቃብር ላይ ምን የመሳሰለ ቤት ይገነባሉ። ከዚያም የተለያዩ ሺርኮችን ለመፈፀም ቀብራቸው ዘንድ ይመላለሳሉ። ኢስላም ማለት የመቃብር አምልኮት ማለት እስከሚመስል ድረስ የሙስሊሙ አለም በዶሪሕ ተጥለቅልቋል። በሶሪያ ደማስቆ ከተማ ውስጥ ብቻ መቶ ዘጠና አራት ዶሪሖች አሉ። ግብፅ ውስጥ ከስድስት ሺህ በላይ የሚመለኩ ዶሪሖች አሉ። በዒራቅ፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በህንድ፣ በፓኪስታን፣ በአፍጋኒስታን፣ በየመን፣ ... በሌሎችም የሙስሊም ሃገራት ያለው ነገር የከፋ እንጂ የተሻለ አይደለም። የበለጠ የሚያሸማቅቀው ደግሞ ቀላል የማይባሉ ዶሪሖች ከነ ጭራሹ ቀብርም ሆነ የተቀበረ ነገር የሌላቸው ባዶ መሆናቸው ነው። ለምሳሌ የሑሰይን ጭንቅላት የተቀበረበት ነው ተብሎ ካይሮ ውስጥ እርድ የሚፈፀምበት፣ ስለት የሚቀረብበት፣ ጠዋፍ የሚደረግበት፣ ሌሎችም ዘግናኝ የሺርክ ተግባራት የሚፈፀሙበት ዶሪሕ አለ። በተመሳሳይ ሶሪያ ውስጥ ደማስቆና ሐለብ (አሌፖ) ከተማ አቅራቢያ የሑሰይን ዶሪሕ አለ። ምን ይሄ ብቻ! ዒራቅ ውስጥ ከርበላእና ነጀፍ ከተሞች ውስጥ የሑሰይን ዶሪሕ አለ። በ“እ $ራኤል” ስር ባለችው በፍልስጤማዊቷ የዐስቀላን ከተማም የሑሰይን ዶሪሕ ይገኛል። ይህ ሁሉ እንግዲህ የሑሰይን ጭንቅላት የተቀበረበት የሚባል ነው። ለመሆኑ ሑሰይን ስንት ጭንቅላት ነው የነበራቸው? የዐሊይ ልጅ ዘይነብ የሞተችው መዲና የተቀበረችውም በቂዕ ነው። ነገር ግን ሶሪያ ደማስቆ ውስጥ እና ግብፅ ካይሮ ውስጥ በስሟ የተገነባ ዶሪሕ አለ። ግብፅ አሌክሳንድሪያ ከተማ ውስጥ የአቡ ደርዳእ ዶሪሕ አለ። ዓሊሞች ግን እርግጠኛ ሆነው እዚያ እንዳልተቀበሩ ይናገራሉ። ዐብዱረሕማን ብኑ ዐውፍ የተቀበሩት መዲና በቂዕ ውስጥ ነው። በዒራቋ የበስራ ከተማ ግን በስማቸው የተገነባ ዶሪሕ አለ። የነብዩ ﷺ ልጅ ሩቀያ የሞተችውም የተቀበረችውም መዲና ውስጥ ነው፣ ነብዩ በህይወት እያሉ። በሚገርም ሁኔታ ሶሪያ ውስጥም ግብፅ ውስጥም በስሟ ዶሪሕ አለ። ወደ ሀገራችን ስንመጣም በተመሳሳይ በርካታ የታወቁ ሰዎች መቃብር በላያቸው ላይ ዶሪሕ ተገንብቶባቸዋል። ከዚያም ዶሪሑ ዘንድ የሚፈፀሙ ብዙ ዘግናኝ ሺርኮች አሉ። ይሄ ሁሉ ኢስላም የሚያዘው ነው ወይ? በፍፁም! መረጃውስ? አቡል ሀያጅ አል አሰዲይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ قَالَ لِي عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ : أَلَا أَبْعَثُكَ عَلَى مَا بَعَثَنِي عَلَيْهِ رَسُولُ اللهِ ﷺ؟ ( ... وَلَا قَبْرًا مُشْرِفًا إِلَّا سَوَّيْتَهُ) "0ሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ እንዲህ ብለውኛል፦ 'አላህ መልእክተኛ ﷺ በላኩብኝ አምሳያ አልክህምን? { ...ከፍ ያለ ቀብር አይተህ (ከሌሎች ቀብሮች ጋር እኩል) ሳታስተካክለው እንዳታልፍ!}' " [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 969] ኢብኑ ዑመር - ረዲየላሁ ዐንሁማ - ከዐብዱረሕማን ቀብር ላይ ቤት ተሰርቶ ቢመለከቱ “አስወግደው አንተ ልጅ። የሚያጠልለው ስራው ነው” ብለዋል። [ተሕዚሩ ሳጂድ፡ 130]

መቃብር ላይ ቤት/ ዶሪሕ መገንባት በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታዋቂ ሰዎች መቃብር ላይ የተገነቡ ህልቆ መሳፍርት ዶሪሆች አሉ። ይሄ ተግባር አላዋቂ ሰዎች መቃብሮቹን እንዲያመልኳቸው በር
መቃብር ላይ ቤት/ ዶሪሕ መገንባት በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታዋቂ ሰዎች መቃብር ላይ የተገነቡ ህልቆ መሳፍርት ዶሪሆች አሉ። ይሄ ተግባር አላዋቂ ሰዎች መቃብሮቹን እንዲያመልኳቸው በር ከፍቷል። ይሄ ደግሞ ችግሩ ተከስቶ ሲታይ ብቻ ሳይሆን ስጋት ሲኖር ራሱ ቀድመን በጥብቅ ልንተዋወስበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:- اللَّهُمَّ لَا تَجْعَلْ قَبْرِي وَثَنًا يُعْبَدُ اشْتَدَّ غَضَبُ اللَّهِ عَلَى قَوْمٍ اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ {ጌታዬ ሆይ! ቀብሬን የሚመለክ ጣኦት አታድርገው። የነብዮቻቸውን መቃብር የአምልኮት ቦታዎች አድርገው የያዙ ሰዎች ላይ የአላህ እርግማን በረታ!} [ሚሽካቱል መሷቢሕ፡ 750] ይህን ያሉት እነዚያዎቹ የሰሩት ጥፋት በሳቸው ቀብር ላይ እንዳይደገም ስለሰጉ ለማስጠንቀቅ ነው። ይሄ ባይሆን ኖሮ ቀብራቸው ውጭ ላይ በግላጭ ይሆን እንደነበር እናታችን ዓኢሻ - ረዲየላሁ ዐንሃ - ተናግራለች። [ቡኻሪ፡ 1390] [ሙስሊም፡ 529] ሶሐቦች አደራቸውን ተወጥተዋል። የነብዩ ﷺ ቀብር የአምልኮት ቦታ እንዳይሆን በመስጋት ከሞቱበት ቤት ከጓዳቸው ቀብረዋቸዋል። ኢማም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ “የነብዩ ﷺ ቀብር ምድር ላይ ካሉ ቀብሮች ሁሉ በላጭ ነው። ሆኖም ግን መመላለሻ ተደርጎ እንዳይያዝ ከልክለዋል። ስለዚህ ከሳቸው ቀብር ውጭ ያለው ማንም ይሁን ምን ይበልጥ ለክልከላ የተገባ ነው።” [አልኢቅቲዷእ፡ 2/172]

#አፋር_ከታሪክ_ጥቆማ_ጋር_አድርሱልኝ!! ➻#የበረሀው_ነብር__!! ▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾ የአንድ እምነት ተከታይ በአንድ ክልል ጎራ፡ በየተራራው ላይ ክላሽህ ሲያጓራ፡ ወዳጅ ያስጨንቃል እንኳን ባላንጋራ፡ የሀበሻ ኩራት የምድር ፕላኔት፡ የኛ ባለ ታሪክ የኢስላም ሱልጧኔት፡ እንባዬ ይመጣል ታሪክህ ሲወሳ፡ ያኔ በዚያ ዘመን እንደት ነበር #ሀውሳ፡ ኢስላምን በደስታ አምነህ የምትኖረው፡ ሀቅን በነፃነት የምትናገረው፡ #የአፄወች_ጫና_ያላንበረከከህ፡ በኢስላም ጎዳና ያለህ ተሰክከህ፡ ስላንተ ምን ላውራ ሆንኩልህ አይናፋር፡ ተከፍተህ እንዳላይ ድል ይግጠምህ አፋር፡ ▷#መሳሪያቸው_ውሸት፤ ጥይታቸው ወሬ ሆነና ነገሩ፡ ▷#እሳት_እየገፉ፤ በአፋር በወሎ አመድ ሆነው ቀሩ፡ #የተረሳ_መስሎት፤ የፈፀመብን ግፍ ችግርም መከራ፡ በሁሉም አቅጣጫ፤ በወሎ በራያ በአፋር በሰመራ፡ አደራድሩኝ ይላል፤ ድጋሜ ሊያፍነን ደግሞ ሀገር ሊመራ!! ▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾ ▷#አብሽር_አፋር__!! #በዝቶ_የሚታየው_የመስጂድ_ሚናራ፡ ጀግና የወጣብሽ ሱልጧን አሊሚራ፡ የሙስሊሞች ምድር የምንኮራብሽ፡ አፋር ተጠንቀቂ #ቄስ_እንዳይመጣብሽ፡ በአሏህ እገዛ እንድዘልቅ ሳቅሽ፡ ጠላት እንዳይወርሽ ልጆችሽን ቀስቅሽ፡ #የትግራይን_ሙስሊም ሲጨቁን የኖረው፡ የአፋርን ምድር ድጋሜ እንዳይወረው፡ ተነስ የኔ አንበሳ በርታ ተነቃቃ፡ #ደብተራ_እንዳይደፍርህ_ለትንሽ_ደቂቃ፡ መልሶ ከመጣ በቋንቋው አናግረው፡ አፋር በልጆችህ #ጁንታን አሳፍረው፡ #ለትግራይ_ሙስሊሞች፤ #ድምፅ_እንደሆንክ_ያኔ፡ አትንካቸው እንዳልክ፤ #ደፍረህ_ለወያኔ__!! #ደምህ_ደሜ_እንዳልከው፤ #አልቅሰህ_በወኔ_!! #ዛሬም_ለነርሱ_እዘን_አደራ_ወገኔ፡ #ህዝብን_ጂምላ_ጠልተህ #እንዳትሰጥ_ብያኔ፡ ክርስቲያን ቢሆኑም ንፁሀን አትግደል፡ ጠላትህ ጁንታ ነው ያ ከርከሮ ወደል፡ ▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴ አፋርና ወሎ በታሪክ ተጣምሯል፡ በዘር በሀይማኖት ተዛምዶ ተሳስሯል፡ ይህንን እውነታ ደጋግሞ አስመስክሯል፡ ይህንን ያሳያል የአፋር ተራራ፡ ስያሜው ይመስክር #ልጅ_እያሱ_ጎራ፡ አብዐላ ዳሎል አሳይታና አፍሌራ፡ ጀግና በቅሎበታል ወንድ እንደ አሊሚራ፡ #ይልቅ_ይመለሱ_ተው_ንገሯቸው፡ #አፋር_እንዳይገቡ_ሰው_የለም_መስሏቸው፡ ▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴ የኢስላም ዘበኛ የጀግና መፍለቂያ፡ የአንድነት ማሳያ የኛ መታወቂያ፡ በአፋር ቤት ታሪክ ባንዳ አይታወቅም፡ በአንድ ቀለሀ ነው አስር የሚለቅም። ታሪክህ ይናገር ልጅ እያሱ ጎራ፡ በእምነትህ ጠንክር አለብህ አደራ፡ ታግሎ አስረክቦሀል#ጀግናው_አሊሚራ፡ መገለጫህ ይሁን#የመስጂድ_ሚናራ፡ ▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴ ➻#አፋር_አብሽር__!! ------------------------ #በረጂም_ጠመንጃ፤ በጥቋቁር ክላሽ ጎኑን ካልዳሰሱት፡ ጠላት አይጎዳም፤ አኩርፈውት ቢያልፉ ንግግር ቢነሱት፡ አብሽር ያፋር ወጣት ሳይጨልም አይነጋም፡ አሏህ ይረዳሀል ፈፅሞ አያሰጋም፡ በኢስላም የፀና ሀቀኛና ደፋር፡ የበረሀ አንበሳ ጀግናችን ነው አፋር፡ የሰላም ተምሳሌት አንተ ያገር ዋርካ፡ በርታ አሏህ ያግዝህ ተዘጋጅ #ሉባካ፡ የአተኳኮስ ዘይቤህ ከማንም ይለያል፡ አንተን የተጠጋ ሆድ እቃው ይጋያል፡ ▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴የኑሬ ማስታወሻ

ባህር አቋርጣችሁ፣ ብዙ ስቃይና መከራ አሳልፋችሁ፣ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥታችሁ ሳዑዲ የምትገቡ ወገኖች ስራውንም፣ አኗኗሩንም፣ ገንዘብ አያያዙንም እወቁበት። "ህገ ወጥ" ለሆነ ሰው፣ የሰው ሃገር ኑሮ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ጣጣ ቢስ መሆን ዋጋ ያስከፍላል። ፀፀት ያስከትላል። ባገር በቀያችሁ ለመኖር ሰበብ የሚሆናችሁን ገንዘብ ለመቋጠር ሞክሩ። ችግር መጥፎ ነው። ከቅርብ ሰው ጋር ጭምር ያጨካክናል። የለፋችሁትን የምታስቀምጡበትም በጥንቃቄ ይሁን። ሌላ ሰው ጋር ለማስቀመጥ ከተገደዳችሁ በተቻለ ለአማና የሚሆን ሰው ምረጡ። ቢቻል የሀገራችሁ፣ የአካባቢያችሁ ሰው ቢሆን ጥሩ ነው። ችግር እንኳ ቢኖር በቤተሰብ፣ በዘመድ፣ በሽማግሌ ለመጠየቅ ይመቻል። ዋናው ሰበብ ማድረሱ ነው። ተጠንቅቀንም ችግር ሊያጋጥም ይችላል። ደግሞም ጥሬ ገንዘብ ከማስቀመጥ ይልቅ በሁነኛ ሰው በኩል መሬት ላይ፣ ቤት ላይ፣ ንብረት ላይ ማዋል ይሻላል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

አንተ ሶላትን የተውከው ወንድሜ ሆይ!! <===============> #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ!! ሶላትን ትተህ ከእስልምና ምን ቀረህ? ሶላት የኢስላም ምሰሶ፤ የኢማን መገለጫ -ካባ- መሆኑን አታውቅምን!? #አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! አንተ ስትቀር ሁሉም ፍጥረታት ለጌታቸው ሰጋጆች ናቸው። አላህ ﷻ እንዲህ ብሏል፡- أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَسْجُدُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ وَالنُّجُومُ وَالْجِبَالُ وَالشَّجَرُ وَالدَّوَابُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ النَّاسِ ۖ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيْهِ الْعَذَابُ ۗ وَمَن يُهِنِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن مُّكْرِمٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ ۩ አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም፣ ለርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን ብዙውም በርሱ ላይ ቅጣት ተረጋገጠበት፡፡ አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን ይሠራልና፡፡ (ሱረቱ አል-ሐጅ - 18) 👌አንተም የማትሰግድ ከሆነ ከነዚያ ቅጣት ከተወሰነባቸው አንዱ ትሆናለህ። #አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! #ሶላትን_መተው_ክህደትና (#በአላህ_ላይ) #ማጋራት_መሆኑን_አታውቅምን!? ነቢዩ ﷺ አንዲህ ብለዋል፡- «ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﻭﺑﻴﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻭﺍﻟﻜﻔﺮ ﺗﺮﻙ ﺍﻟﺼﻼﺓ» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ] «በሰውየውና በሽርክ ወይም በክህደት መካከል (ያለው) ሶላትን መተዉ ነው።” « ﺍﻟﻌﻬﺪ ﺍﻟﺬﻱ ﺑﻴﻨﻨﺎ ﻭﺑﻴﻨﻬﻢ ﺍﻟﺼﻼﺓ : ﻓﻤﻦ ﺗﺮﻛﻬﺎ ﻓﻘﺪ ﻛﻔﺮ ‏» ‏[ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ]. “በኛና በነሱ (በካህዲያን) መሀል ያለው ቃል-ኪዳን (ድንበር) ሶላትን መተው ነው። (ሶላትን) የተወ በእርግጥ ካደ።” #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! ሶላትን መተው እንዲሁም (ከሶላት) መዘናጋት ሙናፊቅነት መሆኑን አታውቅም!? አላህ እንዲህ ብሏል፡- إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ (ይቀጣቸዋል)፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ሰዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 142) ነቢዩም ﷺ  በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦ «ﺃﺛﻘﻞ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻤﻨﺎﻓﻘﻴﻦ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺸﺎﺀ ﻭﺻﻼﺓ ﺍﻟﻔﺠﺮ، ﻭﻟﻮ ﻳﻌﻠﻤﻮﻥ ﻣﺎ ﻓﻴﻬﻤﺎ ﻷﺗﻮﻫﻤﺎ ﻭﻟﻮ ﺣﺒﻮًﺍ‏» ‏ [ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ ]. “በሙናፊቆች ላይ እጅግ የሚከብደው ሶላት ኢሻዕ እና ሱብሂ ነው። (ሁለቱን በመስገድ) የሚገኘውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን (ወደ መስጊድ) ይመጡ ነበር።” #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! እስኪ አስተንትን ሙናፊቆች ለይዩልኝ (ሪያዕ) ቢሆንም እንኳ ይሰግዳሉ፤ አንተ ግን በፍጹም አትሰግድም!! #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! ሶላትን መተው ዝንጉነት እና የልብ መድረቅ መሆኑን አታውቅምን!? ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- « ﻟﻴﻨﺘﻬﻴﻦ ﺃﻗﻮﺍﻡ ﻋﻦ ﻭﺩﻋﻬﻢ ﺍﻟﺠﻤﻌﺎﺕ، ﺃﻭ ﻟﻴﺨﺘﻤﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻗﻠﻮﺑﻬﻢ، ﺛﻢ ﻟﻴﻜﻮﻧﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﻐﺎﻓﻠﻴﻦ» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ]. “ህዝቦች የጁምዓ ሶላትን ከመተው ይከልከሉ! ወይም አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽግባቸዋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።” #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! ሶላትን መተው ስራን ሁሉ እንደሚያበላሽ አልሰማህምን!? የሚከተለውን የነቢዩን ንግግር ተመልከት። « ﻣﻦ ﺗﺮﻙ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ ﺣﺒﻂ ﻋﻤﻠﻪ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ]. “የአስርን ሶላት የተወ ስራው በርግጥ ተበላሸበት።” #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! ሶላትን መተው ከከሀዲያንና ወንጀለኞች ጋር ለእሳት ቅጣት እንደሚዳርግ አታውቅምን!? የጀነት ሰዎች የጀሀነም ሰዎችን (ጀሀነም የገቡበትን ምክንያት) ሲጠይቋቸው የሚሰጧቸውን ምላሽ ሲናገር አላህ እንዲህ ይላል፡- كُلُّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ رَهِينَةٌ ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ተያዥ ናት፡፡ إِلَّا أَصْحَابَ الْيَمِينِ የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡ فِي جَنَّاتٍ يَتَسَاءَلُونَ (እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡ عَنِ الْمُجْرِمِينَ ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡ مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ (ይሏቸዋልም) «በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?» قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ (እነርሱም) ይላሉ «ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ ሰላትን ወቅቷን ጠብቆ አለመስገድ ሰቀር ለሚባለው የጀሀነም ሸለቆ ውስጥ ለመግባት ሰበብ ይሆናል። እንዲሁም በሌላ ምዕራፍ አላህ እንዲህ ይላል፦ ۞ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡ (ሱርቱ መርየም፣ - 59) ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- « ﺍﻟﺬﻱ ﺗﻔﻮﺗﻪ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ، ﻓﻜﺄﻧﻤﺎ ﻭﺗﺮ ﺃﻫﻠﻪ ﻭﻣﺎﻟﻪ‏» ‏ [ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ] “የአስር ሶላት ያመለጠው ቤተሰቦቹንና ንብረቱን እንደ አጣ (እንደ ተነጠቀ) ነው።” የአምስቱንም ወቅት ሶላት መተውህስ ምን ያስከትል ይሆን!? #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! ሶላትን መተው መረበሽን፣ አለመረጋጋትን፣ ጭንቀትን፤ የኑሮ ጥበትን (እንደሚያመጣ) አታውቅምን!? አላህ እንዲህ ይላል፡- وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِي فَإِنَّ لَهُ مَعِيشَةً ضَنكًا وَنَحْشُرُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَعْمَىٰ «ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡ قَالَ رَبِّ لِمَ حَشَرْتَنِي أَعْمَىٰ وَقَدْ كُنتُ بَصِيرًا «ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስኾን» ይላል፡፡ قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ آيَاتُنَا فَنَسِيتَهَا ۖ وَكَذَٰلِكَ الْيَوْمَ تُنسَىٰ (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ «ታምራታችን መጣችልህ፡፡ ተውካትም፡፡ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ» ይለዋል፡፡ #ዋ_ንዴትህ! #ዋ_ፀፀትህ! #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! እንዴት ጊዜ ያልፋል፤ እድሜህ (ያለ አግባብ) ይገባደዳል፤ ልብህ ከጌታህ ተጋርዶ ሳለ!? እንዴትስ በቅርቢቱ አለም (ዱንያ) ከሚገኙት ነገሮች ሁሉ ይበልጥ ጣፋጭ እና ማራኪ የሆነውን ነገር ሳትቀምስ ዱንያን ትሰናበታታለህ!? ይህም አላህን በማምለክ፣ በማውሳት፣ በማመስገን እና ለርሱም በመስገድ የሚገኝ ሲሆን። #አንተ_ሶላትን_የተውክ_ሆይ! ለሶላትህ ቀላል ስፍራ የሰጠኸው አንተ ዘንድ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ምን ይሆን? ሶላቱን ያጓደ ሌሎች ስራዎቹን ይበልጥ እንደሚያጓድል አታውቅምን!?

ጽንፈኝነት በዚህ ልክ
ጽንፈኝነት በዚህ ልክ

ከጭቁኑ መዝገበ ቃላት 1. አስተማሪ- ግንባር ቀደም የመብት አቀንቃኝ ቀንደኛ ተግባራዊ አንባገነን 2. ትምህርት ቤት- ስለ ሰብአዊ መብት በብዛት የሚሰበክበት የሙስሊሞች መብት በስፋት የሚጣስበት የግፍ አፀድ 3. የሀይማኖት መቻቻል- በቲቪና በሬዲየ የሚለቀቅ ሙስሊም አደንዛዥ ኬሚካል 4. ስላሴ- ህፃናት የማይስቱት ቀላል ሂሳብ “አዋቂዎች” ወደው የዋጡት ቅልጥም 5. እኩልነት ለሴቶች- ከወንዶች የግፍ ፌርማታ ተነስቶ ወደሌላ የወንዶች የግፍ ፌርማታ የሚያደርስ ልብስ የማስጣል ዘመቻ IbnuMunewor