es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Ir al canal en Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
195
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-730 días
Archivo de publicaciones
👉ለስበር-ራያ ሰለፍዮች አድርሱልኝ‼️ «ሁሌም ተውሒድ ይቅደም»
የወሎው ሳተና በርታ የኔ ጉብል፡ ወጥርና ፅና በመንሀጅህ ዞብል፡ ተነስ ተንቀሳቀስ ድቢ መንደፈራ፡ በተውሒድህ ጠንክር ማንንም ሳትፈራ፡ ሱና እየፈካ ነው በአለማጣ ዋጃ፡ ጠላት አንገት ደፍቷል በሐቅ መረጃ፡ አህባሽ ቅርቃር ገብቷል የነካውን እንጃ፡ በጠማሞች ሴራ ቢፈስም ንፁህ ደም፡ መርህ አልቀየርንም ዛሬም ተውሒድ ይቅደም፡
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi 👉የራያ ሰለፍዮች ቻናል ነው። t.me/+c8E_ovQaoLkyNTR t.me/+c8E_ovQaoLkyNTR

"በግልፅ እንደሚታወቀው ሙብተዲዕ የሆነ ሰው ሙብተዲዕ የሆነ አምሳያውን እንጂ ሌላን አይመርጥም ሱኒ የሆነውም ሱኒ የሆነ አምሳያውን እንጂ ሌላን አይመርጥም።" ሸይኽ ሙቅቢል ረሒመሁሏህ

የሰላምታ አደብ ~ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ትንሽ በትልቅ ላይ፣ አላፊ በተቀማጭ ላይ፣ ጥቂት በብዙ ላይ ሰላምታ ያቅርብ።" [አልቡኻሪይ ፡ 6231]

"ኢኽዋን ማለት የተቀጣጠለ ፈንጂ ነው የትም ቦታ ቢገኝ አጥፊ። "

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "የቢድዓ አራማጅን ያላቀ እስልምናን በመናድ ላይ ተባብሯል። [ሸርሁ አሱናህ ሊልበርበሃሪይ"(39)]

"وعقيدتنا في التبرؤ:إننا نتبرأ من الأصنام الأربعة:أبي بكر، وعمر، وعثمان، ومعاوية، والنساء الأربع:عائشة وحفصة، وهند، وأم الحكم، ومن جميع أشياعهم وأتباعهم، وأنهم شرُّ خلق الله على وجه الأرض، وأنّه لا يتم الإيمان بالله ورسوله والأئمة إلا بعد التبرؤ من أعدائهم". ​"ራስን ስለ ማራቅ ያለን እምነታችን እንዲህ ነው፦ እኛ ከአራቱ #ጣዖታት ማለትም ከአቡበከር፣ ከዑመር፣ ከዑሥማን እና ከሙዓውያ፤ እንዲሁም ከአራቱ ሴቶች ማለትም ከዓኢሻ፣ ከሐፍሷ፣ ከሂንድ እና ከኡሙ አልሐከም፣ ከደጋፊዎቻቸውና ከተከታዮቻቸውም ሁሉ እንርቃለን። እነርሱ በምድር ገጽ ላይ ከአላህ ፍጥረታት ሁሉ መጥፎዎች ናቸው። በአላህ፣ በመልእክተኛውና በኢማሞቹ ላይ የሚኖር ኢማን ከጠላቶቻቸው በመራቅ እንጂ ሙሉ አይሆንም።" [ሐቁል የቂን፡ 519] በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፦ لا مجال لعاقل أن يشك في ك+ فر عمر، فلعنة الله ورسوله عليه وعلى كل من أعتبره مسلما وعلى كل من يكف عن لعنه. "አስተዋይ ሰው በዑመር ከሃ ^ዲነት ላይ ሊጠራጠር አይገባውም። የአላህና የመልእክተኛው እርግማን በእርሱ ላይ፣ እርሱን እንደ ሙስሊም በሚቆጥረው ሁሉ ላይ እና እርሱን ከመርገም በሚቆጠብ ሰው ሁሉ ላይ ይሁን።" [ጀላኡል ዑዩን፡ 45] በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፦ أن عائشة و حفصة لعنة الله عليهما وعلى أبويهما قتلتا رسول الله بالسم دبرتاه ​"ዓኢሻ እና ሐፍሷ — የአላህ እርግማን በእነርሱና በአባቶቻቸው ላይ ይሁን፣ የአላህ መልእክተኛን በጠነሰሱት መርዝ ገድለዋቸዋል።" [ሐያቱል ቁሉብ፡ 2/700] 6. አልኹመይኒ (1409 ሂ.) ሶሐቦችን ቁርኣንን በርዘዋል እያለ እንዲህ ሲል ይከሳቸዋል፦     "فإنّ أولئك الذين لا يعنون بالإسلام والقرآن إلا لأغراض الدنيا والرئاسة، كانوا يتخذون من القرآن وسيلة لتنفـيذ أغراضهم المشبوهة، ويحذفون تلك الآيات من صفحاته، ويُسقطون القرآن من أنظار العالمين إلى الأبد، ويلصقون العار وإلى الأبد بالمسلمين وبالقرآن، ويُثبتون على القرآن ذلك لعيب-يقصد التحريف- الذي يأخذه المسلمون على كتب اليهود والنصارى". "እነዚያ ለዱንያ ጥቅምና ለስልጣን ካልሆነ በቀር ለእስልምናም ሆነ ለቁርኣን ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች፤ ቁርኣንን አጠራጣሪ ዓላማዎቻቸውን ማስፈጸሚያ መሣሪያ አድርገውት ነበር። እነዚያን (ለእነሱ የማይመቹ) አንቀጾችን ከገጾቹ ላይ ይሰርዙ ነበር። በዚህም ቁርኣን በዓለም ሕዝቦች እይታ ለዘላለም ዝቅ እንዲል አደረጉት፤ በሙስሊሞችና በቁርኣንም ላይ የዘላለም ውርደትን አጣበቁ። ሙስሊሞች በአይሁዶችና በክርስቲያኖች መጻሕፍት ላይ የሚነቅፉትን ያንን ነውር (መበረዝን) በቁርኣን ላይ አረጋገጡ።" [ከሽፉል አስራር፣ ሩሁላህ ኹመይኒ፡ 131] ልብ በሉ! ይሄ ሙሽ ^ ሪክ ሰው ሶሐቦችን ከማንቋሸሹ በላይ ቁርኣን ተበርዟል እያለ ነው። ይሄ ጥፋት ብቻውን ከእስልምና ያስወጣዋል። ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ ይሄ ሰው ሙስሊም አይደለም ብለው ሑክም ሰጥተዋል። ኹመይኒ አቡበክርና ዑመርን አስመልክቶም እንዲህ ይላል፦ "وإننا هنا لا شأن لنا بالشيخين، وما قاما به من مخالفات للقرآن ومن تلاعب بأحكام الإله، وما حللاه وحرّماه من عندهما، وما مارساه من ظلم ضد فاطمة ابنة النبي وضد أولاده، ولكننا نشير إلى جهلهما بأحكام الإله، والدين ... إن مثل هؤلاء الأفراد الجهال الحمقى والأفاقون والجائرون غير جديرين بأن يكونوا في موضع الإمامة، وإن يكونوا ضمن أولي الأمر". "እኛ እዚህ ላይ ስለ ሁለቱ ሽማግሌዎች (አቡበከርና ዑመር)፣ በቁርኣን ላይ ስለፈጸሙት ጥሰት፣ በመለኮታዊ ሕግጋት ላይ ስላደረጉት ማላገጥ፣ ከራሳቸው ፈጥረው ሐላልና ሐራም ስላደረጉት፣ እንዲሁም በነቢዩ ልጅ በፋጢማና በልጆቻቸው ላይ ስለፈጸሙት በደል ጉዳያችን አይደለም። ነገር ግን እኛ የምንጠቁመው በመለኮታዊ ሕግጋትና በሃይማኖት ላይ ስላላቸው መሃይምነት ነው... እንደነዚህ ያሉ መሃYሞች፣ ሞኞች፣ ቀጣ ^ ፊዎች እና በዳይ ግለሰቦች ለኢማምነት ቦታም ሆነ ከመሪዎች ለመሆን በጭራሽ ብቁ አይደሉም።" [ከሽፉል አስራር፣ ኹመይኒ፡ 107-108] * ዓኢሻን በዝሙት እየወነጀሏት የፃፉትም ብዙ ናቸው። [ተፍሲሩል ቁሚ፡ 2/377] [አልቡርሃን፣ አልበሕራኒይ፡ 4/358] [አጥጦራኢፍ፣ ኢብኑ ጧውስ፡ 492-493] ወዘተ. * ልብ በሉ! አላህ ንፅህናዋን ካወጀ በኋላ ዓኢሻን በዝሙት የወነጀላት ሰው ፈፅሞ ሙስሊም አይደለም። ወላሂ ሺዐዎች ሶሐቦችን የሚያንቋሽሹባቸው ንግግሮች በጣም ብዙ ናቸው። በዚህና ሌሎችም ከባባድ ጥፋቶቻቸው የተነሳ የኢስላም ሊቃውንት ከጥንት ጀምሮ በነሱ ላይ የከረረ አቋም ይዘዋል። ዝርዝሩን እመጣበታለሁ ኢንሻአላህ። ይህን ሐቅ ያዙና እነ ኢብኑ ባዝን፣ ኢብኑ ዑሠይሚንን፣ ፈውዛንን፣ ... ቅጥረኛ እያሉ ከዚያ ግን ኹመይኒን "ኢማም"፣ "ሩሑላህ"፣  "አየቱላህ" እያሉ የሚያወድሱ ሰዎችን ተመልከቱ። እነ አቡበክርና ዑመርን የሚያብጠለጥልና ቁርአን ተበርዟል የሚለው ኹመይኒ "ኢማም" ነው። የሱን ጥፋት የሚናገሩ የሱና ዑለማኦች ደግሞ የአሜሪካ ቅጥረኞች ናቸው። አሁን ይሄ ሙስሊም ነኝ ከሚል ሰው የሚጠበቅ ንግግር ነው? እነዚህን የኢስላም፣ የሶሐባ ጠላቶች መናገር ነው ለአሜሪካ መስራት ተብሎ የሚኮነነው? ይሄ ሁሉ የሺዐዎች ጥፋት ሳይጎረብጠው ጧት ማታ እነሱን የሚያውድስና በነሱ መነካት የሚከፋ ተንታኝ ብዙ ነው። የቀጠናው geopolitics አልገባችሁም ይላል ከዚያ ደግሞ። ኹመይኒንና ኻሚነኢን የማይለይ ሰው ነው እንግዲህ ከኔ ወዲያ የgeopolitics እውቀት ላሳር የሚለው። እንዲህ አይነቱ አካል ከዜና የለቀማትን እፍኝ መረጃ ይዞ ከዚያ በዐቂዳ ጉዳይ ላይ እኔን የማይጥመኝን ነገር ለምን ታወራላችሁ ሲል አስቡት እንግዲህ። ወላሂ ከዚህ "መንቃታችሁ" በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 15/1447) የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የሺዐዎች እምነት በሶሐቦች ላይ ~ ሰሞኑን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ የሱና ዑለማኦችንና 0ረቦችን በጅምላ እያብጠለጠሉ ሺ0ዎችን የሚያወድሱ ሰዎችን በተደጋጋሚ እያየን ነው። ይሄ በጦርነቱ ላይ አቋም ከመያዝ ያለፈ ጉዳይ ነው። ከጦርነቱ አንፃር ለኢስላምና ለሙስሊሞች የሚሻለው የዚህ ቡድን መሸነፍ ወይም ማሸነፍ ነው ሊል ይችላል፣ የመገምገም አቅም ያለው ሰው። ጉዳዩን ከዚህ መጠን አውጥቶ የሱና ዑለማኦችንና 0ረቦችን እያብጠለጠሉ ሺ0ዎችን ማወደስ ግን አንደኛ ፍርደ ገምድልነት ነው። ሁለተኛ የሺዐዎችን መዝሀብ በቅጡ የማያውቅን ወገንም ማታለል ነው። ይህን መግቢያ የማስቀድመው "የሺዐ ችግር ይገባናል፣ ግን ለምን በዚህ ሰዓት ትናገራላችሁ?" ለሚሉ ነው። ይሄ ጥያቄ ዋጋ የሚኖረው ሌሎች ሙስሊሞችን እያጣጣሉ ሺዐዎችን ማወዳደስ ባይኖር ነበር። ሁሌ ጦርነት በተነሳ ቁጥር ሺዐዎችን ለሚያወድሱ አካላት ግን በተመሳሳይ ጊዜ የሺ0ዎችን ማንነት የሚያሳይ ማርከሻ ስራ ያስፈልጋል። "ድል ለኢራን፣ ሽንፈት ለዐረቦች" እያለ የፃፈ አይቻለሁ። ዐረብን ሆዳ ^ ም፣ ፈሪ፣ አድር ባይ ሙ ^ Na ^ ፊቅ፣ መሀ Yም አድርጎ መሳል የተለመደ ሆኗል። በዚህ ደረጃ ዐረቦችን መጥላት ለምን? ሙስሊም ያልሆኑ አካላት ይህንን ቢያደርጉ 0ላማቸው ይገባናል። እነዚህ ለኢስላም በመቆርቆር ስም 0ረቦችን ማጣጣልን የጠዋትና የማታ ዚክር ያደረጉ አካላት አላማቸው ምንድነው? ዐረቦች እንደማንኛውም ህዝብ ኸይረኛም ሸረኛም አላቸው። ነገር ግን በየትኛውም መለኪያ ዐረቦች ከኛ አያንሱም። በነገራችን ላይ ቀደም ባለው ዘመን "ሹዑቢያ" የሚባል ዐረቦችን የመጥላትና የማጣጣል ፀረ ኢስላም የህቡእ ንቅናቄ ነበር። ዛሬም መልኩን ቀይሮ በሰፊው እያየነው ነው። የሚያስቀው ግን በኢትዮጵያውያን ይሄ ሲቀነቀን ማየት ነው። የሃገር ውስጡ አልበቃ ብሎ ባህር አቋርጦ እንኳ በዘር የሚባላ፣ ለም መሬትና ምቹ የአየር ንብረት እያለው የሻገተ በቆሎ አጥቶ ኑሮውን እርዳታ ላይ የመሰረተ፣ አብዛኛው ህዝብ ከትምህርት፣ ከጤና፣ ከመብራት አገልግሎት ርቆ በመከራ የሚማቅቅ፣ ጦርነት ባህሉ የሆነ፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ እገታ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀል የተንሰራፋበት፣ ... ምናችን ተሽሎ ነው እኛ ዐረቦችን የምናጣጥለው? እኮ ምን? ከዐረብ ሃገራት ድሃዋ የመን ናት። በየመን እንኳ የሚኖረው ሐበሻ በጣም ብዙ ነው። "የአረብ ነገስታቶችና እና የቤተመንግሥት ሙፍቲዎቻቼው ኢራንን ጠላት አድርገው የያዟቸውና ከኢስላምም የሚያስወጧቸው ሺአ ስለሆኑ አይደለም የአሜሪካ ጠላት ስለሆኑ ነው።" ይላል ሌላው። የዐረብ ዑለማኦች ሺዐዎችን የሚተቹት የሚያስተች ጥመት ኖሮ ሳይሆን አሜሪካንን ለማስደሰት ነው እያለ ነው። በርካታ ሺዐዎች ቁርኣን ተበርዟል እንደሚሉ በማስረጃ አሳልፌያለሁ። ይሄ ለትችት በቂ ካልሆነ ከእስልምና ምን ቀረን? ይሄው ዛሬ ደግሞ የነብዩን ﷺ ታላላቅ ሶሐቦች የሚያብጠለጥሉበትን አቀርባለሁ። የማቀርበው የራሳቸውን ዓሊሞች ንግግር ሲሆን ምንጭ ያደረግኩትም የራሳቸውን ኪታቦች ነው። ይሄውና፦ 1. ሰሊም ብኑ ቀይስ አልሂላሊይ (90 ሂ .) እንዲህ ሲል በዐሊይ ስም ይዋሻል፦ (إن الناس كلهم ارتدوا بعد رسول الله صلى الله عليه وسلم غير أربعة إن الناس صاروا بعد رسول الله بمنزلة هارون ومن تبعه ومنزلة العجل ومن تبعه فعلي في شبه هارون وعتيق في شبه العجل وعمر في شبه السامري) "ሰዎች ሁሉ ከአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ ከአራት ሰዎች በስተቀር ከሃይማኖት ወጥተዋል። ሰዎች ከአላህ መልእክተኛ በኋላ በሃሩንና እርሱን በተከተሉት፣ እንዲሁም በጥጃውና እርሱን በተከተሉት ደረጃ ላይ ሆኑ። ዐሊይ የሃሩን ምሳሌ ሲሆን፣ ዐቲቅ (አቡበከር) የጥጃው ምሳሌ ነው፣ ዑመር ደግሞ የሳሚሪ ምሳሌ ነው።" [ሰሊም ብኑ ቀይስ፡ 598-599] 2. ሙሐመድ ብኑ የዕቁብ አልኩለይኒ (328 ሂ.) እንዲህ እንዲህ ብሏል፦ ( عن أبي جعفر عليه السلام، قال: كان الناس أهل ردة بعد النبي صلى الله عليه وآله إلا ثلاثة. فقلت: ومن الثلاثة؟ فقال: المقداد بن الأسود، وأبو ذر الغفاري، وسلمان الفارسي) "ከአቡ ጃዕፈር (ዐለይሂ ሰላም) ተይዞ 'ከነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወአሊሂ ወሰለም) በኋላ ሰዎች በሙሉ (ከእምነት) የተመለሱ ነበሩ፤ ከሦስት ሰዎች በስተቀር' አለ። እኔም፦ 'እነማን ናቸው እነዚያ ሦስቱ?' አልኩኝ። እርሱም፦ 'አልሚቅዳድ ብኑ አልአስወድ፣ አቡ ዘር አልጊፋሪ እና ሰልማን አልፋሪሲ ናቸው' አለ።" [ረውደቱል ካፊ፡ 213] 3. ዐሊይ ብኑ ሂላል አልከርኪይ (984 ሂ.) እንዲህ ብሏል፦ إن من لم يجد في قلبه عداوة لعثمان ولم يستحل عرضه ولم يعتقد كفره فهو عدو لله ورسوله ، كافر بما أنزل الله ​"በልቡ ውስጥ ለዑሥማን ጥላቻ የሌለው፣ ክብሩን (መደፈር) የማይፈቅድ እና ከሃ ^ ዲነቱን የማያምን ሰው እርሱ የአላህና የመልእክተኛው ጠላት ነው፤ በአላህ በወረደውም (ቁርኣን) የካደ ነው።" [ነፈሓቱ አልላሁት] 4.ኒዕመቱላህ አልጀዛኢሪይ (1112 ሂ.) እንዲህ ብሏል፦ إن أغلب الصحابة كانوا على النف/اق ولكن كانت نار نفاقهم كامنة في زمنه (أي النبي صلى الله عليه وآله وسلم) فلما أنتقل إلى جوار ربه برزت نار نفا* قهم لوصيه ورجعوا القهقرى. "አብዛኞቹ ሶሐቦች በሙ °Na - ፊ ^ ቅነት ላይ ነበሩ፤ ነገር ግን የሙ [ና F ^ &ቅነታቸው እሳት በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወአሊሂ ወሰለም) ዘመን ተዳፍኖ ነበር። ወደ ጌታቸው በሄዱ ጊዜ ግን ያ የሙ °Na - ፊ ^ ቅነት እሳት በሳቸው ተተኪ ላይ ወጣ፤ ወደ ኋላም (ወደ ክህ ^ደት) ተመለሱ።" [አልአንዋሩል ኑዕማኒያ፡ 1/81] አቡ በክር አስሲዲቅን አስመልክቶ ደግሞ እንዲህ ይላል፦ كان يصلي خلف رسول الله صلى الله عليه وآله والصنم معلق في عنقه يسجد له ​"ከአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወኣሊሂ) ኋላ ይሰግድ ነበር፤ ነገር ግን ጣዖት በአንገቱ ላይ አንጠልጥሎ ለእርሱ (ለጣዖቱ) ይሰግድለት ነበር።" [አልአንዋሩ አንኑዕማኒያህ፡ 1/53] በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፦ "والأخبار الدالة على ك+ فر أبي بكر وعمر وإضرابهما وثواب لعنهم والبراءة منهم وما يتضمن بدعهم أكثر من أن يذكر في هذا المجلد أو مجلدات شتى" ​"የአቡበከርን፣ የዑመርንና የእነሱን ቢጤዎች ክ ^ ህ - ደት የሚያሳዩ፣ እነሱን የመርገምንና ከእነሱ የመራቅን ምንዳ (ሠዋብ) የሚገልጹ፣ እንዲሁም የፈጠሯቸውን ቢድዐዎች የሚዘረዝሩ መረጃዎች በዚህ ጥራዝ ወይም በተለያዩ በርካታ ጥራዞች ውስጥ ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም።" [ቢሓሩል አንዋር፡ 30/230] 5. ሙሐመድ ባቂር አልመጅሊሲይ (1111 ሂ.) እንዲህ ብሏል፦

የጎዳና ፊጥራ.mp32.70 MB

ኢብኑ ተይሚያህ رحمه الله እንደሚሉት إياك نعبد وإياك نستعين የምትለውን የቁርአን አንቀፅ መልእክት በትክክል የተረዳ ሰው ለእዩልኛና ለኩራት አይጋለጥም። "አንተን ብቻ አመልካለሁ" ማለቱ ከአንተ ውጭ ላሉ ነገራቶች ብዬ የምፈፅመው አምልኮ አይኖረኝም እንደማለት ሲሆን  ይሄም ሪያእና ሱምዐን ይከላከላል። "በአንተ ብቻ እታገዛለሁ" የሚለው ደግሞ ደካማነኝና የአንተን እገዛ እሻለሁ። የሚያኮራኝ ነገር የለም ማለት ነው። مدارج السالكين١/٥٤

ባለቤት ከወሰነው በላይ ጨምሮ መሸጥ ይቻላል? ~ ጥያቄ፦ ሱቅ ውስጥ የሚሰራ አንድ ሰው አለ። እቃው ለምሳሌ አንድ ሺ ብር ዋጋ ወጥቶለታል። እሱ ግን 2 ሺ ይሸጠዋል። ከዚያም ጭማሪውን ይወስዳል። ይሄ ነገር ይፈቀዳል? መልስ፦ ይሄ ተግባር አይፈቀድም። እቃው አንድ ሺ ብር ዋጋ ወጥቶለታል። እሱ 2 ሺ ይሸጠዋል። ከዚያ ጭማሪውን ይወስዳል። ይሄ የማይፈቀድ ተግባር ነው። አንደኛ፦ ሰዎችን መጉዳት አለበት። በግብይቱ ለሰዎች በመልካም እንዲያስተናግድ ታዞ ሳለ እሱ እየጨመረ ነው። ሁለተኛ፦ ለባለ ሱቁ ክህደት መፈፀም ነው። ዋጋውን ከፍ ሲያደርግ ሌላ ዘንድ በቅናሽ ስለሚያገኙት ወደዚህ እንዳይመለሱ ያደርጋቸዋል። ይሄ አንድ ነጥብ ነው። በሌላ በኩል የሽያጩ ባለቤት ባለ ሱቁ ነው። ስለሆነም ያገኘው ጭማሪም የባለሱቁ ሐቅ ነው። እንጂ የተቀጣሪው አይደለም። وفقنا الله وإياكم. ፈትዋውን የሰጠው ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ምንጭ፦ https://t.me/ibnhezam/12749 = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

"አገልጋይ ያልሆነ ሀብት ጌታ ሆኖ ያርፋል!!"

ጨክን! ታተርፍበታለህ! ~ ሶደቃ ላይ ድፍረት ይኑርህ። ዘካህን ለማውጣትም አትንቀጥቀጥ። በርግጠኝነት ዛሬ ከምትጓጓለት ገንዘብ ይልቅ የአኺራው ሽልማት የበለጠ ነው። ብልጥ ሁን። ከዛሬ ለነገ ቅድሚያ ስጥ። ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታ እንዲህ ይላል፦ { وَٱلۡـَٔاخِرَةُ خَیۡرࣱ وَأَبۡقَىٰۤ (17)} "መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁልጊዜ ዘውታሪም ነች።" [አልአዕላ: 17] እወቅ! ነፍሲያን አሸንፎ ሶደቃ ላይ መሳተፍ፣ ዘካን ማውጣት ትልቅ ጀግንነት የሚጠይቅ ጀብዱ ነው። ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ فإن الصدقـة مـن جنس القتـال، فالجبـان يرجف والشجاع يثبت "ሶደቃ ከውጊያ አይነት ውስጥ ነው። ፈሪ ሲርገፈገፍበት ጀግና ይፀናበታል።" [አልፈታዋ: 14/95] = (ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 27/1444) የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMune https://t.me/IbnuMune

የጎዳና ፊጥራ.mp32.70 MB

አስነዋሪ ነገራቶችን ስንዳፈር ወንጀላችን በዛ። የወንጀላችን መብዛት ቀልባችንን አደረቀው።የቀልባችን መድረቅ ከዐይናችን እምባ የሚባል ነገር እንዳይፈስ ምክንያት ሆነ። የህያ ቢን ሙዓዝ

"መጥፎ ስሜትና ጎጂ ፍላጎንት መቃረን የሰው ልጅ ልቡ፣ አካሉና ምላሱ ብርቱ እንዲሆን ያደርጋል። አንዳንድ ቀደምቶች (ስሜቱን ማሸነፍ የሚችል ሰው ለብቻው አንድ ከተማ ድል አድርጎ ከሚቆጣጠር ሰው ይበልጥ ጠንካራ ነው) ይሉ ነበር" አል-ኢማም ኢብኑል ቀዩም ( ረውደቱል-ሙሒቢን) ዲንና አኽላቅን በሚጎዳ ነገር ጊዜ ማሳለፍና መዝናናት ጎጂ ፍላጎትን መከተል ነው።