es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Ir al canal en Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
195
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-730 días
Archivo de publicaciones
⛔የሶላተል ጀምዓ አሳሳቢነት!❗️ ⚠️ ➖➖➖➖➖👇➖➖➖➖ ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ ﴿وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَقَدْ هَمَمْتُ أَنْ آمُرَ بِحَطَبٍ فَيُحْطَبَ، ثُمَّ آمُرَ بِالصَّلَاةِ فَيُؤَذَّنَ لَهَا، ثُمَّ آمُرَ رَجُلًا فَيَؤُمَّ النَّاسَ، ثُمَّ أُخَالِفَ إِلَى رِجَالٍ فَأُحَرِّقَ عَلَيْهِمْ بُيُوتَهُمْ﴾ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ። ማገዶ እንዲሰበሰብ በማዘዝ፤ ከዚያም አንድ ሰው ለሶላት ‘አዛን’ እንዲል ካደረግኩ በኋላ ሌላ ሰው እንዲያሰግድ አዝዤ ከዚያም ሶላት ለመስገድ (ወደ መስጊድ) ያልመጡ ሰዎችን ቤት ከጀርባቸው ለማቃጠል አስቤ ነበር።” 📚ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 644

ለእየሱስ ባሪያዎች! ~ የመሲሕ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን ጌታ ግፍ አቅቶት - ሰዎች ከገደሉት አለቀ አከተመ - የታል አምላክነት?! ሰዎች የሰሩትን - በሱ ላይ ሲያደርሱ ጌታ ግብራቸውን - ፈቅዶ ነው በራሱ? እንዲያ ከሆነማ - ምንኛ ታደሉ?! ፍቅሩን ይቸራሉ - ፈቃዱን ሲሞሉ። ባደረሱት ሁሉ - አልፎ ከተከፋ እንግዲህ ምን ይባል? ሀይሉ ከኮሰሰ - ሀይላቸው ከሰፋ?! ግን እንጠይቃለን - ለመልስ አትንፈጉ ማለባበስ ይቅር - ይመለስ በወጉ "ፈጣሪዋን" አጥታ - ዐለም ስትዋትት ሰው ወደ ማን ነበር - የሚያስበው ፀሎት? ፍጡር "ፈጣሪውን" - ካ ~ፈ .ር ሲያደባየው ሰባቱን ሰማያት - ማን ነበር ያቆየው? ምስማር ተቸንክሮ - ሲያሸልብ "ፈጣሪ" ዓለም ቀርታ ነበር - ያለ አስተናባሪ? የሰማይ መላእክት - ምንኛ ለገሙ?! እጁ ተቸንክሮ - ዋይታውን ሲሰሙ? እንጨቱም ታምር ነው - አቅሙ መቋቋሙ "አምላክ" ያክል ነገር - ችሎ መሸከሙ ስለቱስ ጭቃኔው - ብረቱ ምስማሩ አካሉን ሰንጥቆ - ስቃይ ማሳደሩ ጉድ በሉ እሄን ጌታ - በአ ይ .ሁ ድ የሚርረታ ማጅራቱን ታንቆ - ታስሮ የሚመታ ኋላስ ራሱ ነቃ - ከሞት አንሰራራ ወይስ ጌታ አገኘ - ህይወት የሚዘራ?! ጉድ በሉ ለቀብር - ጌታ አቅፎ ለያዘ የባሰም ሆድ አለ - አምላክ ያረገዘ ዘጠኝ ወር ታሽጎ - ሲኖር በጨለማ ሐይድ እየተጋተ - ደም እየተጠማ ብልት ቀዶ ወጣ - አቡሻ ህፃኑ አፉን ለጡት ከፍቶ - አቤት ማሳዘኑ! አስቡ እሄን አምላክ - ሲጠጣ ሲበላ ከዚያም ያስገባውን - ሲያስወጣ በሌላ ጌታዬ ከፍ አለ - ከነሳራ ቅጥ .ፈት ሁሉም ይጠየቃል - ለቀባ .ጠረ .በት የመስቀል ባሮች ሆይ! - ግራ ገባኝ እኔ ያሽቀነጠረው ሰው - ፅድቅ ነው ኩነኔ ማ .ቃ .ጠል ሰባብሮ - ፈቃጁን ጨምሮ ህሊና ከዚህ ውጭ - ይፈርዳል አምርሮ? "አምላክ" አቅም አንሶት - ለተጠፈረበት ሰብሮ እንደማቃጠል - ጭራሹን አምሎኮት?! እውነትም እ ር .ጉ ም ነው - ለምንስ ይዝዘንጋ? በመሳለም ሳይሆን - በእግር ይሰጥ ዋጋ! ለተዋረ .ደበት - ጌታህ ከነ ነፍሱ አንተ ካመለክከው - የሱ ነህ የነሱ? ‘ጌታን ስላዘለ’ - ከሆነ አክብሮቱ አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ - ቢሆን እንጂ እንጨቱ መስቀሉ ከጠፋ - ሺ ስንት አመታቱ?! እንዲያ ከሆነማ - ሂሳቡ ቀመሩ ለመስገድ አትቦዝን - ለየመቃብሩ ያስታውሳልና - ነገረ ስርኣቱ "ጌታህ" ካፈር በታች - ለነበረበቱ። የመሲህ ባሪያ ሆይ! - ንቃ ተረጋጋ ይሄ ነው እውነታው - ካ'ልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡ የኢብኑል ቀዪም አልጀውዚያህ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም፡፡ ግጥሙን “ኢጋሠቱል ለህፋን ኪታክ ገፅ: 2/290 ላይ ያገኙታል፡፡ የግጥሙን የቪዲዮ ቅንብር ደግሞ ከ ትርጓሜው ጋር ከስር ይመልከቱ፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 27/2006) = ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ይህ ሰው የሆነ ጊዜ ክርስቲኖች የእየሱስ ፊልም ብለው ከሰሯቸው ውስጥ እየሱስን መስሎ የተወነ ሰው ነው። "እየሱስ ምን እንደሚመስል ማንም አያውቅም ..." እያለን ነው።

ሸይኽ ዐብዱል ቃዲር አልጂላኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “አንተ ችግርህን ለፍጡር የምታቀርበው ሆይ! ወደማይጠቅምህና ወደማይጎዳህ ፍጡር አቤት ማለትህ ምን ይፈይድሃል?! ብተመካባቸውና በጌታህ ሐቅ ላይ ብታጋራቸው ያርቁሃል። ከሱ ቁጣ ላይም ይጥሉሃል። … አንተ መሀይም! ፍጡርን በመማፀንህ ግልግልን እየተመኘህ አውቃለሁ ብለህ ትሞግታለህ!! … ወዮልህ! አላህ ከማንም የበለጠ ቅርብህ ሆኖ ሳለ ከሱ ሌላ ስትከጅል አታፍርም?!” [አልፈትሑ አርረባኒ ወልፈይዱ አርረሕማኒ፡ 117-118] IbnuMunewor

أَمَّا السَّفِينَةُ فَكَانَتْ لِمَسَاكِينَ يَعْمَلُونَ فِي الْبَحْرِ فَأَرَدتُّ أَنْ أَعِيبَهَا وَكَانَ وَرَاءَهُم مَّلِكٌ يَأْخُذُ كُلَّ سَفِينَةٍ غَصْبًا ( الكهف79) «መርከቢቱማ በባሕር ለሚሠሩ ምስኪኖች ነበረች፡፡ ከኋላቸውም መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚይዝ ንጉሥ ነበረና፤ (እንዳይቀማቸው) ላነውራት ፈቀድኩ፡፡ ....... መርከቧ ፍፁም በሆነ ሆኔታ ላይ ብትሆን ኖሮ የመርከቧ እጣ ፋንታ በንጉሱ መወረስ ይሆን ነበር። እንደዚሁ በህይወታችን ውስጥ አንዳንድ ያጣናቸው ወይም መጥፎ የሚመስሉን ነገሮች ለበጎ ይሆናሉና እንታገስ።

∙ سورة الكهف √√

ቁርኣን…‼ ================= ⇛ከቁርኣን ርቄ ወደ ሶሻል ሚዲያው መመላለስ ካበዛሁ ሰነበትኩ፡፡ የቂያማ ቀን ቁርኣን ከሚከሣቸው ሰው አንዱ እንደሆንኩ አስባለሁ፡፡ አዎን የቂያም ቀን ቁርኣን የዘጉትንና ያኮረፉትን ሰዎች ይከሳል፡፡ አላህ በረሕመቱ ይሁነኝ፡፡ ⇨አሁን በመሃል ድንገት የሆነ ስለ ቁርኣን የተፃፈ ጽሑፍ አነበብኩና ከረጅም ጊዜ በኋላ ድንገት ብንን አልኩኝ፡፡ ያነቃኝን አላህ አብዝቶ ይመንዳው፡፡ ለካ ቁርኣንን ረስቼዋለሁ፡፡ በወሬ መሃልም መባነን አንድ ነገር ነው ወዳጆቼ፡፡ ደንዝዞ ከመቅረት አላህ ይጠብቀን፡፡ ⇛አላህ ቁርኣንን በረከት፣ ፈውስ፣ ቅናቻ አድርጎ አወረደልን፡፡ እኛ ግን አጠገባችን እያለ ረሳነው፡፡ እርስት አደረግነው …. ወላሂ፡፡  እኛ ግን ምን ዓይነት ሞኞች ነን በአላህ!! በሚጠቅመን ነገር ላይ ትንሽ ብዙ በማይጠቅመን ነገር ላይ ብዙ ሰዓት እናሳልፋለን፡፡ ⇛ከኪሣችን ሞባይላችንን አውጥተን፣ ከመደርደርያው ላይ አዉርደን ማንበብ ባንችል እንኳ ቁርኣንን ባገኘንበት አጋጣሚ ሁሉ ዒርፎናችን ሰክተን ለማዳመጥ እንሞክር፡፡ ስንቆምም ሆነ ስንቀመጥ በረከቱን እናትርፍ፡፡ ታክሲ ዉስጥ፣ ወረፋ ስንይዝ፣ እንቅልፍ አልወስድ ሲለን፣ የእግር መንገድ ስንጓዝ … ወዳጃችን እናድርገው፡፡ ትርጉሙን ባናውቅ እንኳ በረከቱ ይተርፈናል እኮ፡፡ ያ ረብ ቁርኣንን አስወድደን፤ ዘወትር ከሚያነቡትም አድርገን፡፡ ከአቡ ሱፍያን

የማንነት ፍፃሜ መሸርሸር የአካባቢውን ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች በማፈን ማህበረሰቡን ባይተዋር ለማድረግ የተሄደበት ርቀት ዛሬም ድረስ በታሪክ ውስጥ እንደ ጠባሳ ይኖራል። ደሴ የጀግኖችና የእምነት ጠባቂዎች ከተማ ናት። የገደለንን የምናነግስበት የታሪክ ግፈኞችን በክብር አደባባይ ላይ የምንሰቅልበት ምንም ዓይነት ሞራላዊም ሆነ ፖለቲካዊ ምክንያት የለንም። የጎጃም ቅ*ጥ*ረ*ኞ*ች*ም ሆኑ ሌሎች የጥፋት ኃይሎች የደሴን ሕዝብ ትዕግሥት እንደ ፍርሃት ሊቆጥሩት አይገባም ሐውልቱ ሊቆም የሚችለው የታሪክ ፍርዱን አግኝቶና የተበደለው ወገን ይቅርታን ሲያደርግ ብቻ ነው ያ ካልሆነ ግን ደሴ የነጻነትና የማንነት ምሽግ ሆና ትቀጥላለች።

ደሴዎች ከተማችሁን ነቅታችሁ ጠብቁ!!!!! የደሴ ከተማ ማንነትና የታሪክ ጠባሳ የንጉሥ ሚካኤል ሐውልት ጥያቄ በደሴ ከተማ ልብ በሆነው ፒያሳ አደባባይ ላይ የንጉሥ ሚካኤልን ሐውልት ለመትከል የሚቃዡ
ደሴዎች ከተማችሁን ነቅታችሁ ጠብቁ!!!!! የደሴ ከተማ ማንነትና የታሪክ ጠባሳ የንጉሥ ሚካኤል ሐውልት ጥያቄ በደሴ ከተማ ልብ በሆነው ፒያሳ አደባባይ ላይ የንጉሥ ሚካኤልን ሐውልት ለመትከል የሚቃዡ አካላት ታሪክን የረሱ ወይም ሆን ብለው የከተማዋን ነዋሪ ስሜት ለመጎንተል የሚሹ ናቸው። የደሴ ሙስሊም ማህበረሰብ ማንነቱን በደምና በአጥንቱ ጠብቆ ያቆየ እንጂ ታሪካዊ ግፍ የፈጸሙበትን አካላት በክብር አደባባይ ላይ የሚሾምበት ሞራል የለውም። #የታሪክ #ማስታወሻ፡ #ከተንታ #እስከ #ደሴ ሊዘነጋ የማይገባው ሀቅ ዛሬ በተንታ ከተማ አደባባይ ላይ ቆሞ የሚታየው የንጉሥ ሚካኤል ሐውልት መጀመሪያ ታስቦ የነበረው በደሴ ከተማ ላይ እንዲቆም ነበር ሆኖም በወቅቱ የነበረው የከተማዋ ነዋሪ የንጉሡን ታሪካዊ ግፍ በማስታወስ በክብር ሳይሆን የገደለንን ግፈኛ ዘቅዝቃችሁ ትከሉት በሚል በጽኑ በመቃወሙ ሳይሳካ ቀርቶ ወደ ተንታ ተወስዷል። ዛሬም ቢሆን በታሪክ ምዕራፍ ላይ የተቀየረ ነገር የለም የደሴ ሙስሊሞች የትናንቱን ቁስል የሚዘነጉበት ምክንያት የላቸውም። #በንጉሥ #ሚካኤል (ራስ መሐመድ አሊ) ዘመን የተፈጸሙ ግፎች ንጉሥ ሚካኤል (በቀድሞ ስማቸው ራስ መሐመድ አሊ) በሥልጣን ዘመናቸው በወሎ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የፈጸሙት ግፍ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ በደም የተጻፈ ነው። በተለይም በቦሩ ሜዳ ጉባኤ ማግስት #እምነትን #የማስለወጥ #ዘመቻ በወቅቱ የነበሩ ገዢዎች በፈጠሩት ጫና በወሎ የሚገኘው ሙስሊም ማህበረሰብ እምነቱን እንዲቀይር የተደረገው በኃይልና በሰይፍ ነበር። #የንጹሃን #እልቂት በሺዎች የሚቆጠሩ (እስከ 30 ሺህ የሚደርሱ) ሙስሊሞች እምነታቸውን ባለመቀየራቸውና ማንነታቸውን አሳልፈው ባለመስጠታቸው ምክንያት ለጅምላ ጭፍጨፋና ለእንግልት ተዳርገዋል።

#የድንቁርና #ጥግ #እና #የሞራል #ዝቅጠት በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ይህ ምስል በወንድማችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የተዘጋጀውን የአላህን ቃልና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች እንዲሁ
#የድንቁርና #ጥግ #እና #የሞራል #ዝቅጠት በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ይህ ምስል በወንድማችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የተዘጋጀውን የአላህን ቃልና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች እንዲሁም የሰለፎችን ንግግር የያዘውን መጽሐፍ ሲቃጠል ማየት የድንቁርናን የመጨረሻ ጥግ ያሳያል። ይህ ድርጊት ከአላዋቂነት ባለፈ የሞራል ውድቀትንና የልቦና መታወርን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አሳፋሪ ክስተት ነው። አንድን ሃሳብ በሃሳብ መርታት ያቃተው፣ በዕውቀትና በምክንያት መከራከር የማይችል አካል የመጨረሻ አማራጩ ሃይልና ማጥፋት ነው። መጽሐፍን ማቃጠል በውስጡ ያለውን እውነት አያጠፋውም ይልቁንም አቃጣዩ ግለሰብ ምን ያህል ከዕውቀት የራቀና በጭፍን ጥላቻ የታወረ መሆኑን ለዓለም ያሳያል። ሃይማኖታዊ ስነ-ምግባር (አኽላቅ) ትልቁ መገለጫው ለዕውቀትና ለዕውቀት ባለቤቶች ክብር መስጠት ነው። በሰለፍያ ስም እየነገዱ ተግባራቸው ግን ከሰለፎች መንገድ የራቀ የሆኑት እነዚህ ግለሰቦች ይህን መሰል አስቀያሚ ድርጊት እንደ ትልቅ ጀብዱ ቆጥረው ሲለጥፉት ማየት ስነ-ምግባራቸው ምን ያህል እንደተበላሸ ማሳያ ነው። የአሏህን ቃል የያዘን መጽሐፍ ማቃጠል ሃይማኖታዊ እሴትን መጣስ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅን የማሰብና የመመራመር ነጻነት መርገጥ ነው። እውነቱ ግን አይቃጠልም የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መጽሐፍ ለቢድዓ ሰዎች ራስ ምታት መሆኑ የታወቀ ነው እውነት ሲመጣ ውሸት መክሰሙ አይቀሬ ነውና መጽሐፉን በማቃጠል በውስጡ ያለውን ብርሃን ማጥፋት አይቻልም። ይህ ድርጊታቸው የሚያሳየው መጽሐፉ የነካቸው ህመም ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ብቻ ነው።ወረቀት ሊቃጠል ይችላል በውስጡ ያለው እውነት ግን በሺዎች ልብ ውስጥ ታትሟል።

ነጋዴ ወደ ማምሻው ላይ ሱቁን ይዘጋል፣ ስለ እለት ዉሎውም ሒሳብ ይሠራል፣ መክሰር ማትረፉን ይገመግማል፣ ዕዳና ብድሩን ያወራርዳል… ☞ እስቲ መግሪብ ላይ ዉሏችንን አናወራርድ፣ ዛሬ ለነፍሣችን ምን ሠርተን ዋልን?  ⇛የነፍሴ አምላክ... ጌታዬ.. .. በስምህ አመሽን በስምህ እናነጋለን ምሽታችንን አሳምርልን። ከአቡ ሱፍያን

ደርስ ~ • ኪታቡ:- ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም • ክፍል:- 02 • የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን • የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ • የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:- https://t.me/IbnuMunewor/9250 • ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ሸይኽ ሙቅቢል ብኑ ሃዲ አልዋዲዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ: – · "የዲን ወንድሞቼ ሆይ! እነዚህ የዶክትሬት፣ የፕሮፌሰርነትና መሰል ማእረጎች ሱንና፣ ዲንና አላህን መፍራት ካልተቆራኛቸው በስተቀር እኛ ዘንድ የሽንኩርት ያክል ዋጋ የላቸውም። (يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ ذَكَرٍ وَأُنْثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِنْدَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ) "እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ብሔሮችና ጎሳዎች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው፡፡" [አልሑጁራት: 13] [ኢጃበቱ አስ - ሳኢል: 140] (ሸዕባን 15/1447) = IbnuMunewor

⇛ይነጋል  ብለን ተኛን። ይኸው ነጋ… ⇛ያልፋል ብለን ተስፋ ስናደርግም ያልፋል ወላሂ። ከአቡ ሱፍያን

መተዛዘንን እንዴት እናዳብረው

«ሰለፍዮቻችን ወደ እንቁ ወደሆነችው መርሳ ከተማ ቀያይ ወርቆችን ፈለጋ መጓዝ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ«። መረሳ የሰለፍዮች መዲና ---------------------- አልሀምዱ ሊላሒ ምስጋና ይገባው፡ የሐቅ ሰዎችን በሐቅ ላግባባው፡ መንሀጀ-ሰለፍን ሞልቶ ለገነባው፡ አልሀምዱ ሊላሒ ይገባው ምስጋና፡ ስላሰባሰበን በተውሒድ በሱና፡ አንድ ስላረገን በጠራው ጎዳና፡ ይህ ነው የኛ ድምቀት ሞገስም ልቅና፡ ዛሬ ደግሞ ጭራሽ ሰርጋችን ሆነና፡ በአካል ተገናኘን ጣፋጭ ሰበር ዜና፡ ከሐይቅ ከደሴ ከዚያ ወረባቦ፡ ከወርቄ ከሐራ ከራያ ከቆቦ፡ ከሁሉም አቅጣጫ ጀግና ተሰብስቧል፡ በሚገርም መልኩ በፍቅር አብቧል፡ ዛሬማ መርሳ ላይ ታሪክ ተመዝግቧል፡ የጠራቸው ጀግኖች በተውሒድ በሱና፡ መጥተው ከወግዲ ገነቴ ቦረና፡ ይገርማል ይደንቃል ቅናት አሰከረኝ፡ ከመካከላችሁ መቀመጥ አማረኝ፡ እኔ ራቅ ብዬ በአካል ባልገኝም፡ ድምፃችሁን ሰማሁ አወ አልቀረብኝም፡ የምትሰሩት ስራ እኔን ለማስቀናት፡ ያወቃቅሰናል የአብሮነት ቀናት፡ ከመካከላችን እጂግ የምኖደው፡ ከአንከርዳዶች መሀል ተበጥሮ ስንደው፡ ዛሬ አንዱ ሸበላ ሆኗል ባለ ተራ፡ ወንድም አቡ-ረያን ተብሏል ሙሽራ፡ አይናችን እያዬ ተቀየረ ስሙ፡ ከላጤነት አለም ለቀቀ ድካሙ፡ ያላገቡ ሰዎች እንደት ይሆን ሁክሙ⁉️ ዑለሞች ሞልተዋል ፈተዋ ጠይቁ፡ አግቡ ይሏችኋል አትጨናነቁ፡ ....አወ... ክረምቱ ሳይገባ ሳይጀምር ተግቡ፡ ቁማችሁ ሳትቀሩ ወጣቶች ቶሎ አግቡ፡ ላጤነት እሳት ነው ቃጠሎ ውስጡ አለ፡ እሳትና ሰይጣን ያስፈራል አይደለ? እኔ ግን ብጠየቅ… መልስልኝ ብሎ አንድ ሰው ቢጠራኝ ቆንጆ በሞላበት፤ ከላጤነት በላይ የለም የሚያሰፈራኝ። ላጤዎች አግቡ ተሰብስቧል አሉ ሸህና ደረሳ፡ ለአንድ ትልቅ ደስታ ወሎ ምድር መርሳ፡ አንድ የሱና ወጣት አንድ የወጣት አስኳል፡ አንድ የሱና ወንድም በውብ ትዳር ሊኳል፡ ደስታ ለመካፈል ከየትም መጥተናል፡ ለዚህ ስለበቃህ እጂግ ደስ ብሎናል፡ መጥተዋል ጀግኖችህ ከሀርቡ ከሚሴ፡ ወጣት ተከማችቶ ከኮንቦልቻ ደሴ፡ ታላላቅ ዑለሞች ከፊት እየመሩ፡ ቀንቻለሁ በጣም አምሮኛል ሰፈሩ፡ የመርሳ ከተማ በውብ ጀግኖች ደሞቆ፡ ይሰማኛል ደስታ ከሀሳቤ እርቆ፡ የሱና ዑለሞች ወጣቱን ሲመክሩት፡ በሐቅ እንድፀና ደጋግመው ሲነግሩት፡ ከተውሒድ ጀምረው መንሀጅ ሲያስተምሩት፡ ይገርማል ውበቱ እንደት ነው የሚያምሩት፡ አሁን ምንም ብዬ ሲቃ አልቀሰቅስም፡ አላን ፉላን ብዬ እኔ ስም አልጠቅስም፡ ብቻ የሱናው ሰው ትንሹም ትልቁ፡ እወዳችኋለሁ ይህንን እወቁ፡ አውቃለሁ ምንም ነው የኔ መውደድ መጥላት፡ ግና በኔ ልብ ውስጥ መውደድ ትርጉም አላት፡ እናንተን እያሰብኩ ሰርጉን እረሳሁት፡ ሙሽራው የታለ!? ስሙን የጠራሁት፡ አንተማ ከንግዲህ ተቀመጥ በግንባር፡ ከላጤነት ወጣህ ኢብኑ አብደል-ጀባር፡ አለንጋውን ስጡት ታሪኩን ይፃፈው፡ ከመካከል ቁሞ ላጤውን ይግረፈው፡ እስኪ ግረፋቸው በአለንጋው ቢያስቡ ከላጤነት ወጥተው ምናልባት ቢያገቡ፡ ለማንኛውም እንኳን አደረሰህ እንኳን ለዚህ በቃህ፡ እንኳን ሳትዘወትር ከላጤነት ወጣህ፡ ከዚህ በላይ ደስታ በዱንያ ላይ የለም፡ ደስታህ ደስታችን ነው መብሩክ ወንድም አለም፡ በወንድምህ ኑረዲን ኢብኑል አረብ