✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Ir al canal en Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
195
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-730 días
Archivo de publicaciones
ከኮምቦልቻ ሰማይ ስር
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ከደሴ
▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ ከደሴ
▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ ከደሴ
▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን ከቢስቲማ
▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ
▪️ ሸይኽ አወል አሕመድ መነዮ ከመረሳ
▪️ ሸይኽ አወል አህመድ ከከሚሴ
▪️ሸይኽ ዒሳ አደም ከደሴ
🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ ከከላላ
🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከአ.አበባ
🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ ከአ.አበባ
🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ ከከሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ ዐብደሽኩር ከአሶሳ
🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን ከሀርቡ
🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ ሙርሰል ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር ከኮንቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን ከመርሳ
🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ
🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ ከደሴ
🔸 አንሷር መሀመድ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ ከደሴ
🔸ኡስታዝ ጀውሀር ክፍሌ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ ከኮንቦልቻ
🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ከደሴ
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
ሸይኽ ጀምረዋል
ገባ
ገባ
ገባ
በሉ
ከኮንቦልቻ ሰማይ ስር
https://t.me/ansuar_muhammed_0088?livestream=cef1b6f0db6f37a36f
[ المختصر في مصطلح أهل الأثر ]
فضيلة الشيخ علي بن أحمد الرازحي - حفظه الله - .
ሓፂር ዚክሪ
ኣርእስቲ፦ ቃል ተውሒድ
"ላ ኢላሃ ኢል-ለላህ" (ብሓቂ ዝምለኽ ኣምላኽ ብዘይካ ኣላህ የለን)።
እዛ ቃል እዚኣ፦
• ጠንካራ ገመድ እያ።
• ኣብ ሞንጎ ኢማንን ኩፍርን ፈላይት እያ።
• ናይ ጀነት መፍትሕ እያ።
• ልቢ እተህድእ ዓባይ ቃል እያ።
ከምቲ ነቢይ (ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ዘምሃሩና፡ እዚኣ ቃል እዚኣ ክንብል ከለና ትርጉማ ፈሊጥና፣ ብልብና ኣሚንናን ብግብሪ ተገዚእናን ክኸውን ኣለዎ።
በትዳር ህይዎት ውስጥ..
~ሁለታችሁም በተመሳሳይ ጊዜ የንዴትን ስሜት አትግለጡ፡፡
~ጭቅጭቅ እንዲፈጠር የሁለት ሰዎችን ተሳትፎ እንደሚፈልግ አስታውሱ፡፡ አንዱ ሲረጋጋ ጭቅጭቁ ይረግባልና አጋራችሁ ሲጨቃጨቅ እናንተ ተረጋጉ፡፡
~አንደኛችሁ የሌላኛውን ሐቅ ለማሟላት የተቻላችሁን አድርጉ፡፡
~በሌሎች ሰዎች ምልከታ መልካም ሆናችሁ ለመታየት ስትሉ አጋራችሁን አጋልጣችሁ አትስጡ፤ በቅድሚ እነሱ መልካም ሆነው እንዲታዩ የምትችሉትን አድርጉ፡፡
~አጋራችሁን በአንድ ሃሳብ መሞገት እንዳለባችሁ ስታምኑበት በትህትና አድርጉት፡፡
~ያለፈ፣ የቆየና የተዘጋን ጉዳይ እንደገና ጎትታችሁ አታምጡ፡፡
~አጋራችሁን ችላ ከምትሉ በዙሪያችሁ ያለውን ሰውና ሁኔታ ችላ ብትሉና ለአጋራችሁ ቅድሚያ ብትሰጡ ይሻላል፡፡
~ለአጋራችሁ ምስጋናንም አትንፈጉ
~ሁለታችሁም ከነበራችሁ የቀን ውሎ ስትገናኙ ፍቅር የተሞላበትን ሰላምታ መለዋወጣችሁን ተለማመዱ፡፡
~ስህተትን ስትሰሩ ስህተታችሁን በግልጽ በማመን ይቅርታን ጠይቁ፡፡
~ብትችሉ በፍጹም በብስጭትና ባለመግባባት ወደ መኝታ አትሂዱ፡፡
የንግድ በረከት ሰበቡ…
ከሐኪም ቢን ሂዛም (رضي ﷲ عنه) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿البَيِّعانِ بالخِيارِ ما لَمْ يَتَفَرَّقا، فإنْ صَدَقا وبَيَّنا بُورِكَ لهما في بَيْعِهِما، وإنْ كَذَبا وكَتَما مُحِقَتْ بَرَكَةُ بَيْعِهِما﴾
“ተገበያዮች እስካልተለያዩ ድረስ በምርጫ ላይ ናቸው። ‘እውነትን ከተናገሩና ያለበትን ነውር’ ግልፅ ካደረጉ ግብይታቸው ይባረክላቸዋል። ‘ያለበትን ነውር ከደበቁና ከዋሹ’ የግብይታቸው በረካ ትነሳለች።”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሙስሊሙ ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ በመሆኑ ሊፈተሽ እንደሚገባ ተመላከተ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ክፍል ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ይፋዊ የህዝብ ውይይት አካሂዷል ።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ በመድረኩ የተነሱ አስተያየቶች ረቂቅ አዋጁን ለማደበር በእጅጉ እንደሚያግዙ ጠቁመው፣ በቀጣይ ከአርቃቂ ቡድኑ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ነበሩ አዋጅ ላይ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን ሊቀርፍ የሚችል የተሻለ አዋጅ ለማውጣት ጥረት እንደሚደረግ ገልፀዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባል የተከበሩ ወ/ሮ ከድጃ ያሲን በበኩላቸው፣ በረቂቅ አዋጁ ሁሉም የእስልምና እምነት ተከታይ በሸሪዓ ፍርድ ቤት መዳኘት አለበት የሚለው ድንጋጌ የሰዎችን በፍላጎታቸው የመዳኘት ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ በመሆኑ መታየት እንዳለበት ገልፀው ረቂቅ አዋጁ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባካተተ መልኩ መቃኘት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ቴዎድሮስ ምህረት፣ ነባሩ አዋጅ ክፍተት የነበረበት በመሆኑ በርካታ አገልግሎት ፈላጊዎች ቅሬታ ሲያነሱ መቆየታቸውን ጠቁመው ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የአገልግሎት ተደራሽነትንና ቅልጥፍናን ማሳደግ በማስፈለጉ አዋጁ እንዲሻሻል መደረጉን ገልፀዋል።
የሸሪያ ፍርድ ቤት የፌዴራል ተቋም እንደመሆኑ በመንግስት በጀት የሚመደብለት፣ በሌሎች ተቋማት ተፈፃሚ የሚሆኑ የፋይናንስ፣ የአሰሪና ሰራተኛ እና ሌሎች ህጎችን አክብሮ የሚሰራ ተቋም መሆኑን ገልጸው ረቂቅ አዋጁ የሦስተኛ ወገን መብትን የማይነካ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል::
ክቡር አቶ ቴዎድሮስ አክለውም ረቂቅ አዋጁ አሁን ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትና የተቋሙ ፍላጎት ባደገ ቁጥር ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ ተቋማትና መዋቅር ለመፍጠር እንደሚያግዝም አንስተዋል።
+1
የሙስሊሙን ስስ ብልት በመለየት በስንዴና በዘይት በማታለል ኢስላምን በመብለጥ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ሆንኩ እያለ ነው ጼንጤ
አሁን መረጃውን ነው ያጋራኋችሁ
ለዝርዝሩ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ
የወጣትነት ሁለት ገፆች
~
ወጣትነት ፀጋ ነው። ለስራም ሆነ ለእውቀት ከየትኛውም የእድሜ ክልል በተለየ መነሳሳት የሚኖርበት ምቹ ጊዜ ነው። ወጣትነት በባህልም ይሁን በእምነት የመጡ ብልሹ ውርሶችን ለማራገፍ፣ የተዛነፉ ትርክቶችን ለማቃናት የተሻለ ድፍረትና ወኔ የሚገኝበት እድሜ ነው። ወጣቶች በኢስላም ታሪክ በተለያዩ የአለም አፅናፋት የእውቀትን ችቦ የለኮሱ የእውቀት ቀንዲሎች፣ የጥጋበኞችን እብሪት ያስተነፈሱ የነብር ጣቶች፣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ አለምን በመልካም ያነቃነቁ የለውጥ ሞተሮች፣ ታሪክ በደማቅ ብእር የሚያወሳቸው አሻራዎቻቸውን ለትውልድ ያሻገሩበት የእድሜ ክልል ነው። ወጣትነት ሌሎችም በዋጋ የማይተመኑ በርካታ ውድ ፀጋዎች አሉት።
በሌላ በኩል ወጣትነት በጥንቃቄ ካልያዙት ራስን፣ አልፎ ሌሎችንም የሚበላ እሳት ሊሆን ይችላል። በወጣትነት ውስጥ በእድሜና በተሞክሮ የሚገኝ ልምድ የለም። የእውቀት ማጠር ይጠበቃል። መንቀዝቀዥ ወይም የስክነት መቅለል፣ ጥሬነት ወይም የብስለት ማነስ፣ በተለያየ ዘርፍ ጤነኛ ያልሆነ ወሰን ያለፈ ድፍረት ወይም ጀብደኝነት፣ ራስን አለማሸነፍ፣ አደጋ ላይ የሚጥል ጉጉት፣ ስሜታዊነት፣ ... ይጎላበታል፣ ወጣትነት። በወጣቶች የተቀሰቀሱ ወይም ወጣቶች ፊታውራሪ የሆኑባቸው ዳፋቸው ሺህ አመታትን አቋርጦ ለዛሬም የተረፉ ብዙ ፈተናዎች ደርሰዋል። በወጣቶች ታላላቅ ኸሊፋዎችና በጀነት የተመሰከረላቸው እንቁዎች ህይወታቸው ተቀጥፏል። እልፍ አእላፍ የኡማው ብርቅየ ፍሬዎች አልቀዋል። ሃገራት ፈርሰዋል። የዑሥማን ግ.ድ. ያ ፣ የኸ.ዋ.ሪ.ጅ ንቅናቄ፣ የዘመናችን የተ^ ክ^ ፊ^ ር ጥንስስና መስፋፋት፣ ... ላይ የጉርምስና ግለት ድርሻው ከባድ ነበር። ሌላው ቀርቶ የዑሥማኒያ (የኦቶማን ተርክ) አገዛዝ ራሱ በከማል አታቱርክ ኦፊሻሊ መፍረሱ ከመታወጁ በፊት አውሮፓ ተምረው በመጡ ወጣቶች ሴራ ቀድሞውኑ ጣእረ ሞት ላይ ደርሶ ነበር። እነዚህ ጥራዝ ነጠቅ ወጣቶች "ኸሊፋዎቹን" በራሳቸው እስከመቀየር፣ ጥርስ የሌለው ውሻ አድርገው እስከ ማንገላታት ደርሰው ነበር። ብዙ ሰው ይህንን እውነታ አያውቅም። ስለ ኦቶማን ተርክ አገዛዝ የሚያወራው ቡድናዊ አላማ ያነገቡ አካላት የሚያቀርቡትን የሂደቱን የመጨረሻ ክፍል ብቻ ነው፣ ያውም በተዛነፈ መልኩ።
ይህንን ማወቃችን በወጣትነት የሚገኘውን ኸይር በወጣትነት ዘመን የሚመጡ ሸሮች እንዳያጠፉት ለመጠንቀቅ ይረዳል። ዑመር ብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ለአንዱ ወጣት እንዲህ ይሉታል፦
«قد يكون في الرجل عشرة أخلاق، تسعة منهن حسنة وواحدة سيئة، فتفسد الواحدة التسع، فاتَّقِ طيرات الشباب».
"በአንድ ሰው ላይ አስር የስነ ምግባር ቀንዘሎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ዘጠኝ መልካምና አንድ መጥፎ። ያቺ አንዷ ቀንዘል ዘጠኞቹን ልታጠፋ ትችላለችና የወጣነት ጥሬነቶችን ተጠንቀቅ።" [ሸርሑል ዑምደህ፣ 5/22]
#ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
( Ibnu Munewor ፣ ሸዋል 16/1444 (ሚያዚያ 28/2015))
IbnuMunewor
