✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Ir al canal en Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
195
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-730 días
Archivo de publicaciones
مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ
قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ
وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ الْمِسْكِينَ
(المدّثر42-44)
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"የሰው ልጅ ከሚሞላቸው ሁሉ የከፋው ሆዱ ነው።የተወሰኑ ጉርሻዎች በቂው ነው።ከዚያ ካለፈ ግን የሆዱን ሲሶ ለምግብ ሲሶውን ለመጠጥና ሲሶውን ደግሞ ለእስትንፋስ ያድርግ።"
(አሕመድ ቲርሚዝይና ኢብኑ ማጃህ)
"ከብዙ ምግብና መጠጥ ተጠንቀቁ! ምክንያቱም ሰዎች ረመዷንን ለቀልባቸው ሳይሆን ለሆዳቸው እንደ ማዕድ አድርገው ነው የቆጠሩት!!"
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁሏህ
✍እኔኮ ቸር ነኝ የቤት አስቤዛ አሟላለሁ ለወጭ ሰጥቻት ነዉ ከቤት የምወጣዉ የምትል ባልሆይ እንኳን አቅም እያለህ ባይኖርህም ለአስቤዛ ለሚስትህ የምትሰጣት ገንዘብ ቸር ልያስብልህ ልያመፃድቅህ አይገባም ።
✍ አንደውም ያንተ ግዴታህ ነው ሁለትም ደግሞ አስቤዛውን ከሸመተችው በኋላ አብራቹ ነው እምትጠቀሙት ብቻዋን አትጠቀመዉም ።
ለራስህና እንድሁም ልጆች ካሉ ለልጆችህ ነው እስዋ የምትጠቀመዉ የአንድ ሰው ፈንታ ነው ።
✍ሚስት ከሰጠሃት ላይ ብር ቢተርፋት እንኳን ከስንት አንድ ሴት ካልሆነች በቀር የጎደላትን የቤት እቃ ወይም የጎደለ ነገር ካለ ለቤቴ ብላ ብትገዛበት ነው
የአስቤዛ ገንዘብ ለሚስቱ ስለሰጠ ተአምር እንደሰራላት የሚሰማዉማ አትሁን ።
✍ቸርነት ማለት ለራስሽ የምያስፈልግሽን ነገር ካለ ስታይዉ ያማረሽ ነገር ካለ አድርጊበት ወይም ፈታ በይበት ብለህ የምትሰጣት ገንዘብ ብቻ ነው👌 ።
✍ወይም እሷ ሳትጠይቅህ አንተ ስታየዉ ያማረህን ነገር ይኸስ ለሚስቴ ብለህ አስበህ በስጦታ መልኩ የምትሰጣት ነዉ ለሷ ደስታ አስበህ የምታደርግላት ነዉ እሱ ነዉ ቸርነትና መተሳሰብ ማለት ።
እና ደግሞ የቤት አስቤዛ ብለህ የሰጠሃት ላንተ ጥሩ ጎኑ ምን መሰለህ ?
በየትኛውም መልኩ የምታወጣው የአስቤዛ ገንዘብ ላንተ ሰደቃ መሆኑ ነው ።
ምን ይኸ ብቻ አስበዉ አይደለም ሌላ ነገር ፈገግ ብለህ ስላየኻት እንደ ሰደቃ ሲቆጠርልህ ይኸ ቀላል ነዉን ? ቀላህ አድርገህ አታስበዉ ።
አንተው በሰጠኻት ገንዘብ ሰርታ ባቀረበችልህ ምግብ ስላጎረስካት ብቻ በምንዳ ስትንበሻበሸ ይኸ ላንተ ቀላል ነዉን ? አይደለም ።
ግደታው እንዳለ ሆኖ የአስቤዛ ገንዘብ ስለሰጠ ለሚስቱ ታአምር እንደሰራላት ውለታ እንደዋለላት የሚያስብ የአስተሳሰብ ዘገምተኛ ሰውዬማ አትሁንጂ ።
እኔ የቤቱ መሪ ነኝ ግደታየና ሀላፊነቴ ነዉ ብለህ አስብ ስለዚህ ግዴታህን ነው የተወጣኸው ለማለት ነዉ !!
✍ ይኸን የጌታህን ቃል ረስተህ ነዉን ?
الرجال قوامون على النسياء بما فضل الله بعدهم على بعدٍ وبما أنفقو من أموالهم...
እናማ ምንም ብታደርግላት አትመፃደቅባት መሪዉ አንተ ነህ የበላዩ አንተ ነህ ።
✍አንደውም ለሴት ልጂ ለ ዱኒያዊ ቁስ እና ከ አስቤዛም ከምትመፃደቅባት በላይ ይልቅ ምርጥ ባል የሚያደርግህን እሷ ጋር ተወዳጂና ተፈቃሪ እንድትሆን የሚያደርግህን ልንገርህ !!
ከመሬት ተነስታ ስትነጫነጭ ድካሟን ስሜቷን ሊረዳት ሊጠይቃት የሚችል ባል ሁንላት ስታወራህ ሀሳቧን የምትረዳት የምታዳምጣት ልዩ ባል ሁንላት ።
የሆነ ነገር ስትጠይቅህ እንደ ጭቅጭቅ አትቁጠረዉ ስለ ሂወቱ ትኩረት የሚሰጥ ሰዉ ነዉ ለነገሮች ቦታ የሚሰጠዉ የሚጠይቀዉም እናም በአግባቡ አስረዳት ግልፅ ሁንላት ።
✍በልዩ ሁኔታ ተንከባከባት አክብራት ጊዜና ትኩረት ስጣት በምንም መልኩ ቢሆን ችላ አትበላት ቸልተኝነት ዉደታን ይገድላል ።
✍ የሷ የሆነን ነገር ሁሉ ወደድላት ቤተሰቦችዋን ወደድላት አክብርላት እሷንም አክብራት ለቀልድም ቢሆን ስሜቷን ዩሚጎዳ ነገር አትናገራት ላንተና ለትዳራችሁ ስትደክም ለሂወታችሁ መሆኑን ተረድተህ ማረፊያዋ ሁንላት !
በማንኛዉም የሂወት ጉዟችሁ ድጋፍ ሁናት ሁሌም ከጎኖ ሁን እመናት ሲደክማት አበርታት አለም እንኳን ቢሸሻት አንተ መቸም የማትተዋትና የማትለወጥባት ከአላህ በታች ድጋፍ ሁንላት ።
✍ሚስትህ ማለት እኮ ሁሉንም ሰዉ ጎደኛ ሂወት ቤተሰብ ወደ ኻላዋ ትታ አንተን መርጣ ወዳና አምና ከወንዶች መሃል ሁሉ መርጣህ የመጣች የምትወድህ ነፍስ ነችኮ 🤌 🩶
እናም ምንም ብታደርግላት የሚገባት አካል ሚስትህ ነች ማለቴ ነዉ ።
ባል ለሚስቱ ምንም ቢሆንላት ሊመፃድቅኮ አይገባም ይልቁንም መልካም ባል ነው ሊያስብለዉ የሚችለው ፡፡
ሚስትም እንደዚያው በጥቅሉ እንደውለታ ሳይሆን ሀላፊነት ተሰምቶት በፍቃደኝነት በፍቅር ሁሉን ነገር ሊሆንላት ነዉ ።
በ ሁሉም ሁኔታዎች ሁለቱም ሊደጋገፉ ነው የሚገባቸው ለማት ነዉ ፡፡
((ትግስተኞቹ (ታጋሾቹ) ምንዳቸውን የሚሠጡት ያለ ስፍር ቁጥር ነው።))
ሐፊዝ ኢብኑ ረጀብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
۞ ሶብር በሦስት ይከፈላል።
(❶) በኢባዳ ላይ መታገስ፤
(❷) ከሀራም መታገስ እና
(❸) አሳማሚ ከሆኑ የአላህ ውሳኔዎች መታገስ።
❍ ሦስቱንም የሰብር አይነቶች ጾም በሚባለው የአምልኮት አይነት ውስጥ ታቅፈው ይገኛሉ።
ምክንያቱም ጾም ውስጥ ፦
•በአላህ ትእዛዝ (ጾም) መታገስ፤
•ፆመኛ ላይ ሐራም የተደረጉ ስሜቶች መታገስ፤
•ጾመኛ በመጾሙ የተነሳ ጾሙ ረሐብ፤ ጥማት እና በነፍሱ እና በአካሉ ላይ ድክመት ያስከትልበታል ሆኖም እነዚህን ስቀይና ሕመም በመታገስ ይወጠዋል።
ይህ ህመምና ስቃይ መልካም ስራን ከመስራት የመነጨ በመሆኑ ግለሰቡ በዚህ ተግባሩ ከፍ ያለ ምንዳ ያገኝበታል።"
[ለጧኢፉ አልመዓሪፍ (1/150)]
🌙🌙🌙💫ሰበር ዜና💫🌙🌙🌙
አልሐምዱ ሊላህ! የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ እሮብ የካቲት 11/ 2018 ዓ.ል ረመዷን አንድ ብሎ ይጀምራል።ዛሬ ምሽቱንም ተራዊሕ እንጀምራለን።
ጥቂት እውነታዎች ስለ ረመዷን
~
1- የረመዷን ወር ፆም ከኢስላም አምስቱ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ምሰሶ ነው።
2- ረመዷን በኢስላማዊው አቆጣጠር 9ኛው ወር ነው።
3- የረመዷን ወር ፆም የተደነገገው በ2ኛው አመተ ሂጅራ ነው። ነብያችን ﷺ ባጠቃላይ የፆሙት 9 ረመዷን ነው።
4- ረመዷን ቁርኣን የወረደበት ወር ነው።
5- ልዩ የሆነችዋ ለይለተል ቀድር የምትገኘው በረመዷን ወር ውስጥ ነው።
6- በረመዷን የተፈፀመ ዑምራ የሐጅ ደረጃ ወይም ከነብያችን ﷺ ጋር የተፈፀመ ሐጅ ደረጃ አለው።
7- ረመዷን የጀነት በሮች የሚከፋፈቱበት፣ የጀሃነም በሮች የሚዘጋጉበት፣ ሸይጧኖች የሚጠፈሩበት ወር ነው።
8- የረመዷን ወር ከኢዕቲካፍ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።
9- ረመዷን እንደ የበድር ድል፣ የመካ መከፈት፣ የቃዲሲያ ድል፣ የዑዛ ጣኦት መወገድ፣ ሞንጎሎች የተሸነፉበት የዐይን ጃሉት ድል፣ ወዘተ ትልልቅ ክስተቶች የተከሰቱበት ወር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
ኒያ ማለት አንድን ነገር ለመፈፀም ቁርጠኛ እሳቤ ነው። ስለሆነም አንድ ሰው በሌሊት ተነስቶ ሱሑር የሚመገበው ለመፆም እንደሆነ ግልፅ ሆኖ ሳለ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን… " እያሉ ማነብነብ አያስፈልግም። ማታ ስትተኛ ለሱሑር እንደምትነሳ ወይም ነገ እንደምትፆም አስበሃል? በቃ ለሱሑር ነቃህም አልነቃህም ኒያ ማለት እሱ ነው።
ሌሎችም ዒባዳዎች ላይ እንዲሁ ነው። አንድ ሰው:–
— ኢስቲንጃእ አድርጎ፣
— ውዱእ አድርጎ፣
— ወደ መስገጃው ሄዶ በመቆም፣
— ወደ ቂብላ ዞሮ፣
— እጆቹን አንስቶ ተክቢራ ሊል ሲል:—
ትከሻውን ነካ ነካ አድርገህ "ምን ልትሰራ ነው?" ብትለው ምን የሚል ይመስልሃል? መቼም "ልቆፍር" አይልም። ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ሶላት ሊሰግድ አስቦ እንደሆነ ለሱም፣ ላንተም ግልፅ ነውና። እንዲያውም በዚህ ሁኔታ ላይ ያለን ሰው "ምን ልትሰራ ነው?" ብለህ ልትጠይቀው አትደፍርም። ለምን? ምን ሊሰራ እንዳሰበ ታውቃለሃ!! ገፍተህ ብትጠይቀው እንኳን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ያለ ጥርጥር ይገረምብሃል። ለምን? ምን ሊሰራ እንደቆመ ዝግጅቱ በበቂ ሁኔታ ይናገራልና። ይህ ነው ኒያ ማለት። ጉዳዩ ይህን ያክል ግልፅ ከሆነ:—
"ነወይቱ፣ ኡሶሊ፣ ፈርዶ ሶላቲ፣ ዙህሪ፣ አርበዐ ረከዓት፣ አዳአን፣ መእሙመን፣ ሙስተቅቢለል ቂብለቲ፣ " የሚለው ኮተት ልብ ብሎ ላሰበው ሰው መረጃ የሌለው ብቻ ሳይሆን የሚያስቅም፣ የሚገርምም ነው። አስበው እስኪ የልብህን ሁሉ ከሚያውቀው ጌታ ፊት ቆመህ:—
"ግዴታ የሆነውን፣ የዙህር ሶላት፣ አራት ረከዐ ልሰግድ አስቤያለሁ። ቀዷእ ሳይሆን በጊዜው ነው። ደግሞም ኢማም ተከትየ እና ወደ ቂብላ ዞሬ ነው።…"
ጌታህ ሁሉን አዋቂ ነው። ነብይ የላከው በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምህሮት መሰረት እንድትገዛው እንጂ በዘፈቀደ እንድትጓዝ አይደለም። ስለዚህ በዒባዳዎች ላይ ቁርኣንና ሱናው ይብቃህ። ሌላ ኮተት ውስጥ አትግባ። የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላት በተክቢራ ጀምሮ በተስሊም የሚጠናቀቅ ነበር። ከተክቢራ በፊት የሚባለው ነገር ትደክማለህ እንጂ የሶላቱ አካል አይደለም። ሶላትህ የሚጀምረው "አላሁ አክበር" የሚለውን የመክፈቻ ተክቢራ ከተናገርክ ጀምሮ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
ከነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓዎች ውስጥ..
اللَّهُمَّ آتِ نَفْسِي تَقْوَاهَا وَزَكِّهَا أَنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا أَنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلَاهَا اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخْشَعُ وَمِنْ نَفْسٍ لَا تَشْبَعُ وَمِنْ دَعْوَةٍ لَا يُسْتَجَابُ لَهَا
"አምላኬ ሆይ!ነፍሴን አንተን መፍራት ለግሳት። ከመጥራሪያ ሰበቦች ሁሉ በላጩ መጥራራት ባንተ ነውና (ከመጥፎ ባህሪያት) አጥራት...."
የመጨረሻህ ትሁን!
ሸይኽ ኢብን ዑሠይሚን አንድ ሰው ነቢን እያለ ሲምል አገኙትና ከዚህ በሗላ እንደዚህ አይባልም ይህ ሽርክ ነው ብለው አስረዱት እሱም ሀሳቡን ተረዳ ተቀበለ ከዚያ ግን "ነቢን ከዚህ በሗላ ነቢን አልልም" አለ።እሳቸውም
በል ይህች የመጨረሻህ ትሁን አሉት
ኢብኑ ሙነወር(ከኪታቡ ተውሒድ ደርስ ላይ የተወሰደ)
ማሳሰቢያዎች:-
1ኛ፡- የመጀመሪያዎቹን ምርጫዎች ባለመቻሉ ፆም የመረጠ ሰው አከታትሎ የመፆም ግዴታ የለበትም፡፡
2ኛ፡- ከፋራ ወይም ማካካሻ የሚመለከተው መሀላ፡-
2.1. ወደ ፊት ባለና ሊሆን በሚችል ጉዳይ ላይ ከተማለ ነው፡፡ ባለፈ ወይም ፈፅሞ ሊሆን በማይታሰብ ጉዳይ ላይ የማለ ሰው ከፋራ አይመለከተውም፡፡
2.2. መሀላው በአላህ ወይም በስሞቹ ወይም በሲፋዎቹ ከሆነ ነው፡፡ በፍጡር የተማለ መሀላ ወንጀል ስለሆነ ማካካሻ ሳይሆን ተውበት ነው የሚያስፈልገው፡፡
2.3. ተገዶ ሳይሆን በምርጫው የማለው መሀላ ከሆነ ነው፡፡
2.4. በቃሉ ሳይገኝ መሀላውን ካፈረሰ ነው፡፡
3ኛ፡- አንድ ሰው በሚምል ሰዓት “ኢንሻአላህ” የሚል ቃል አብሮ ካወጣ መሀላውን ቢያፈርስም ማካካሻ መፈፀም አይጠበቅበትም፡፡ [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 1237]
4ኛ፡- አንድ ሰው ሌላውን “ወላሂ እንዲህ ልታደርግ!” ብሎ ቢምልና ያኛው ሰውየ ሳያደርግ ከቀረ የማለውን ሰው ከፋራ ይመለከተዋል፡፡ ነገር ግን ሰውየውን ለማስገደድ ሳይሆን ለማክበር ብሎ ከሆነ ያደረገው ከፋራ ግዴታ አይሆንበትም፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ እንግዶች መጥተው ምግብ ሲያቀርቡላቸው “አንተም ብላ” አሉ ለአቡበክር፡፡ “ወላሂ እኔ አልበላም” አሉ፡፡ እንግዶቹም፡ “ወላሂ እኛም አንበላም” አሉ፡፡ ሁሉም ሲምሉ ጊዜ አቡበክር “ይሄ ከሸይጧን ነው” በማለት በሉ፡፡ እንግዶቹም በሉ፡፡ ነብዩ ﷺ ሲነገራቸው አቡበክርን፡ “አንተ ከሁሉም መልካም የሰራና በላጭ ነህ” በማለት ከማሞገስ ውጭ ከፋራ እንደሚመለከታቸው አልነገሯቸውም፡፡ [ሙስሊም፡ 2057]
5ኛ፡- አንድ ሰው ሌላውን “ወላሂ እንዲህ ልታደርግ ወይም ላታደርግ” ብሎ ቢምል ከሰውየው ጋር እልህ ከመጋባት ይልቅ በመሀላው እንዳይጠየቅ ብንተባበር መልካም ነው፡፡
6ኛ፡- መሀላን ማፍረስ የተለያዩ ብይኖች አሉት፡፡
6.1. ዋጂብ የሆነ ማፍረስ፡- ወንጀል ሊፈፅም የማለ ሰው መሀላውን ማፍረሱ ግዴታው ነው፡፡
6.2. ሐራም የሆነ ማፍረስ፡- የማለው ያለበትን ግዴታ ለመፈፀም ወይም ከሐራም ለመራቅ ከሆነ ቃሉን ማፍረሱ ሐራም ነው፡፡
6.3. ምርጫ ያለው ማፍረስ፡- በሸሪዐው የተፈቀደን ወይም ግዴታ ያልሆነን ነገር ለመስራት ወይም ለመተው ቢምል ፍላጎቱ ከሆነ መሀላውን የማፍረስ ምርጫ አለው፡፡
በሶስቱም ሁኔታዎች መሀላውን ያፈረሰ ሰው ማካካሻ መፈፀም ግዴታ አለበት፡፡ ይህ የሚሆነው ግን እያወቀ፣ በምርጫው እና እያስታወሰ መሀላውን ካፈረሰ ነው፡፡ እንጂ ባለማወቅ ወይም ተገዶ ወይም ረስቶ መሀላውን የሚፃረር ነገር ቢፈፅም ማካካሻ የመፈፀም ግዴታ የለበትም፡፡
7ኛ፡- አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ለምሳሌ “ወላሂ ይህን ላልሰራ” እያለ ደጋግሞ ቢምል የሚመለከተው ማካካሻ አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
#ክፍል_አምስት በምንድን ነው የሚማለው?
ሰዎች እንደ እምነታቸው በፈጣሪ፣ በደጋጎች፣ በወላጆች፣ በነብያት፣ በመላእክት፣ በመቃብር፣ ወዘተ ሲምሉ ያጋጥማሉ፡፡ በኢስላም ግን ከአላህ ውጭ ባሉ ነገሮች መማል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “በአባቶቻችሁ፣በእናቶቻችሁና ያለአግባብ ሰዎች ለአላህ ብጤዎች ወይም አቻዎች አድርገው በሚይዟቸው ነገሮች አትማሉ። በአላህ እንጂ አትማሉ።” “ከአላህ ሌላ ባለ ነገር የሚማል መሀላ ሁሉ ሺርክ ነው፡፡” “ከአላህ ሌላ ባለ የማለ በርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል፡፡” “አንዳችሁ በመሲሕ (በዒሳ) ቢምል አደጋ ላይ ወድቋል። መሲሕ ግን ከአባቶቻችሁ የበለጠ ነው፡፡” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7249] [አሶሒሐህ፡ 2042] [ኢርዋእ፡ 2561] [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 12278]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 01/2010)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
መሀላን የሚመለከቱ ሸሪዐዊ ህጎች!
~
መግቢያ፡-
መሀላ በህይወታችን በስፋት የሚያጋጥመን ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን አብዛኛው ህዝባችን ተያያዥ ነጥቦችን በውል ካለመለየቱ የተነሳ ብዙ ግድፈቶችን ይፈፅማል፡፡ በዚህ ረገድ ጠቃሚ እርምቶችን ይሰጣሉ ያልኳቸውን ነጥቦች ሰብስቤ አስፍሬያለሁ፡፡ ፅሑፉ የማንበብ ልማዳቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች ረጅም ሊባል ይችላል፡፡ ቢሆንም እንደምንም ጥርሳችሁን ነክሳችሁ እንድታነቡት አደራ እላለሁ፡፡ መቼም እኔ ለመፃፍ የፈጀብኝን የሚያክል ጊዜ አይወስድባችሁም፡፡ መልካም ንባብ፡፡
#ክፍል_አንድ ምንነቱ፡-
መሀላ ማለት አንድን ጉዳይ ለማጠናከር ሲባል በተለየ መልኩ የአላህን ስም ወይም መገለጫ /ሲፋ/ ማውሳት ማለት ነው፡፡ “ወላሂ!”፣ “ተላሂ!”፣ “ቢላሂ”፣ “ወረቢል ከዕባ”፣ ወዘተ በሚሉት መማል ይቻላል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው በቀጥታ የአላህን ስም ከምላሱ ባያወጣም “ይህን ላደርግ” ወይም “ላላደርግ ምያለሁ” ወይም “መሀላ አለብኝ” ካለ እንደ መሀላ ነው የሚቆጠረው፡፡ ለማሳጠር ያክል ማስረጃ አልጠቀስኩም፡፡ የፈለገ ሱረቱል ሙናፊቁን ከአንቀፅ 1 – 2፣ ሶሒሕ አልቡኻሪይ፡ ሐዲሥ ቁ. 7046 እና ሶሒሕ ሙስሊም፡ ቁ. 2269 ያሉትን ማስረጃዎች ረጋ ብሎ ያስተውል፡፡
#ክፍል_ሁለት የመሀላ ብይኖች
መሀላ በአምስቱ የሸሪዐ ህግጋት ስር ሊያርፍ ይችላል፡፡
1. አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥም መማል ግዴታ ነው፡፡
2. ፋይዳ ኖሮት ሲገኝ መማል የሚወደድ ነው፡፡
3. በተፈቀደ ጉዳይ ላይ እውነት እስከሆነ ድረስ ወይም እውነት ነው የሚለው ግምቱ ካደላ መማል የሚፈቀድ ነው፡፡ ማብዛቱ ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አላህ “መሀላዎቻችሁን ጠብቁ” ብሏልና። [አልማኢዳህ፡ 89] የመሀላ መብዛት ለውሸት ያጋልጣል፡፡ የኢማን መሳሳትም ነው፡፡
4. በሸሪዐው በሚጠላ ነገር ላይ መማል የተጠላ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ብቻውን ረጅም ጉዞ መጓዙ በሸሪዐው የተጠላ ነው፡፡ ይህን ሊያደርግ ቢምል መሀላው የተጠላ ይሆናል፡፡ በግብይት ላይ መማልም እንዲሁ የተጠላ ነው፡፡
5. እውነትን ለማፍረስ ወይም ሀሰትን ለማንገስ የሚማል ከሆነ መማሉ ሐራም ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- የአእምሮ ህመምተኛ፣ ራሱን የሳተ ሰው፣ ህፃን፣ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ቁጣ ውስጥ የገባ፣ የሰከረ፣ ሳያስበው መሀላ ከምላሱ ያመለጠው፣ የረሳ እና የተገደደ ሰው መሀልላቸው ከቁብም አይገባም፡፡ እንደ መሀላም አይቆጠርም፡፡
#ክፍል_ሶስት የመሀላ አይነቶች፡-
1. የዛዛታ መሀላ፡-
ታስቦበት ሳይሆን በወሬ መሀል ሳይስተዋል የሚወጣ መሀላ ነው፡፡ ይሄ የመሀላ አይነት እንደመሀላ አይቆጠርም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ
“አላህ በመሀላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፡፡” [አልማኢዳህ፡ 89]
2. በስርአት የተቋጠረ መሀላ፡-
ታስቦበት የሚወጣ የመሀላ አይነት ነው፡፡ “ወላሂ! ይህን ላደርግ፣ ወይም ላላደርግ” በሚል መልኩ፣ ባለፈ ሳይሆን ወደ ፊት ባለ ነገር ላይ፣ በማይታሰብ ሳይሆን መሆን በሚችል ጉዳይ ላይ ታስቦ የወጣ መሀላ ሲሆን ሰውየው መሀላውን ካልጠበቀ ማካካሻ (ከፋራ) ይጠብቀዋል፡፡
3. የሀሰት መሀላ፡-
የሰዎችን ሐቅ ለመብላት ወይም ለማታለልና ለማጭበርበር ወይም ለሌላም አላማ ቢሆን ሆን ተብሎ በውሸት ላይ የሚፈፀም መሀላ ነው፡፡ ይሄ ዛሬ በንግዱ እና በሌሎችም ማህበራዊ ህይወቶች ውስጥ የተንሰራፋ ጥፋት ነው፡፡ ሆን ብሎ በሀሰት እየማለ የሚሸጥ የሚለውጠው ዛሬ ቀላል አይደለም፡፡ ጌታችን አላህ በዚህ ላይ ምን አይነት ከባድ መልእክት እንዳስተላለፈ እንመልከት፡-
إِنَّ الَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَأَيْمَانِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُولَئِكَ لَا خَلَاقَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ وَلَا يَنْظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
“እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን እና በመሀላዎቻቸው ጥቂትን ጥቅምን የሚለውጡ በመጨረሻይቱ አለም ምንም እጣ የላቸውም፡፡ በቂያማ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም፤ ወደነሱም አይመለከትም፤ አያጠራቸውም፡፡ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡” [አሊዒምራን፡ 77]
ነብዩ ﷺ ጥፋቱ ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ የሚመደብ እንደሆነ ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል፡- “በአላህ ማጋራት፣ ወላጆችን ሐቃቸውን መጣስ፣ ነፍስን ማጥፋት እና የቅጥፈት መሀላ ታላላቅ ወንጀሎች ናቸው፡፡” [አልቡኻሪይ]
የሀሰት መሀላ ከባድ ወንጀል ከመሆኑ የተነሳ ማካካሻ አልተደረገለትም፡፡ ይሄ የብዙሃን ዑለማእ እይታ ነው፡፡ ይህን የፈፀመ ሰው ያለው ምርጫ የወሰደው ሐቅ ካለ መልሶ፣ የፈፀመው በደል ካለ አስተካክሎ ትክክለኛ ተውበት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “አምስት ጥፋቶች ማካካሻ የላቸውም፡፡ በአላህ ማጋራት፣ ያለ አግባብ ነፍስን ማጥፋት፣ ሙእሚንን መዝረፍ፣ በጂሃድ ላይ በፍጥጫ ሰዓት መሸሽ እና ያለ አግባብ ገንዘብ የሚብበላበት ሀሰተኛ መሀላ።” [አልኢርዋእ፡ 2564] ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ፡ “ሆን ተብሎ የሚፈፀም የሀሰት መሀላ ማካካሻ ቅጣቶች ከሚያብሱት በላይ ነው” ብለዋል፡፡ [አልሙደወናህ፡ 1/577]
#ክፍል_አራት የመሀላ ማካካሻ /ከፋ -ራህ/
አንድ ሰው የሆነን ጉዳይ ሊፈፅም ከማለ በኋላ ቃሉን ቢያፈርስ ወንጀለኛ እንዳይሆን የሚያመልጥበትን ቀዳዳ አላህ አመቻችቶለታል፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “በአንድ ጉዳይ ላይ የማለ ሰው ከማለበት ጉዳይ የተሻለ ነገር ከታየው ይፈፅመው፡፡ ከዚያም መሀላውን ያካክስ፡፡” [አልቡኻሪይና ሙስሊም]
ማካካሻውን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፡-
فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ذَلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ
“ማበሻውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው (ምግብ) አስር ምስኪኖችን ማብላት ወይም እነሱነ ማልበስ ወይም ጫንቃን (ባሪያን) ነፃ ማውጣት ነው፡፡ (እነዚህን) ያላገኘም ሰው ሶስት ቀናትን መፆም ነው፡፡ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሀላችሁ ማካካሻ ነው፡፡” [አልማኢዳህ፡ 89]
ስለዚህ ማካካሻዎቹ፡-
- የቻለ አስር ምስኪኖችን ቤተሰቡን ከሚመግበው መካከለኛ የምግብ አይነት የአንድ ወቅት ምግብ ማብላት፣
- ወይም አስር ምስኪኖችን ሶላት የሚያሰግድ ልብስ ማልበስ፣
- ወያም ሙእሚን ባሪያ ነፃ ማውጣት
ከነዚህ ማካካሻዎች ውስጥ ቅደም ተከተል ሳይጠብቅ የቀለለውን መርጦ መፈፀም ይችላል፡፡ እነዚህን ካልቻለ ግን፡-
- ሶስት ቀን መፆም አለበት፡፡ የመጀመሪያዎቹን ሶስቱን አማራጮች መፈፀም የሚችል ሰው ዘሎ ወደ ፆም መግባት አይችልም፡፡
ነቢያዊ አደራ!
ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّي أُحَرِّجُ عليكم حقَّ الضعيفينِ: اليتيمُ، والمرأةُ﴾
“እኔ በናንተ ላይ በሁለት ደካሞች መብት ጉዳይ አደራ እላችኋለው (አሳስባችኋለው) የቲምንና ሴትን።”
ሶሂህ አልጃሚ፡ 2447
ጥንቃቄ!
ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿غَطُّوا الإناءَ، وأَوْكُوا السِّقاءَ، وأَغْلِقُوا البابَ، وأَطْفِئُوا السِّراجَ؛ فإنَّ الشَّيْطانَ لا يَحُلُّ سِقاءً، ولا يَفْتَحُ بابًا، ولا يَكْشِفُ إناءً، فإنْ لَمْ يَجِدْ أحَدُكُمْ إلّا أنْ يَعْرُضَ على إنائِهِ عُودًا، ويَذْكُرَ اسْمَ اللهِ، فَلْيَفْعَلْ؛ فإنَّ الفُوَيْسِقَةَ تُضْرِمُ على أهْلِ البَيْتِ بَيْتَهُمْ﴾
“የምግብ እቃችሁን ክደኑ። የመጠጥ እቃችሁን ክደኑ። በራችሁን ዝጉ (ቆልፉ)። ፋኖስ (ሻማችሁን/ስቶቫችሁን) አጥፉ። ሸይጣን የተከደነን እቃ አይከፍትም፣ የተዘጋን በር አይከፍትም፣ የተሸፈነን እቃ አይገልጥም። ከናንተ አንዳችሁ የሚሸፍንበትና የሚከድንበት ነገር ባያገኝ እንኳ የአላህን ስም በማውሳት እንጨትም ቢሆን ያስቀምጥባቸው። ምክንያቱም ፉወሲቀት (እንደ አይጥ አይነት ትናንሽ ተንኮለኛ እንስሶች እሳት በማቀጣጠል) ቤተሰብንና ቤትን የሚጎዳ ነገር ይፈፅማሉና።”
ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2012
ግን አንተ ለሚስትህ/ለባለቤትህ እንዴት ነህ??
🌿 የአማኞች አርአያ የሆኑት ረሱል (ﷺ) በሚስቶቻቸው ዙሪያ ፦
🔻 በእድሜ የገፋች ሴትን ረሱል (ﷺ) አግብተዋል
🔻የተፈታች ሴትን ረሱል (ﷺ) አግብተዋል
🔻ባሏ የሞተባት ሴትን ረሱል (ﷺ) አግብተዋል
🔻ሴቶችን በስራ በቤት ውስጥ ረሱል (ﷺ) ያግዙ ነበረ።
🔻በገበታ ወቅት ሚስታቸውን ረሱል (ﷺ) አጉርሰዋል።
🔻ለሚቶቻቸው ፍቅርን፣ አድናቆትንና ክብርን በቃላትና በተግባር ረሱል (ﷺ) ይገልፁ ነበር።
🔻ረሱል (ﷺ) የሚስቶቻቸውን ስህተት ይቅር ይቅር ባይ ነበሩ።
🔻ረሱል (ﷺ) ለሚስቶቻቸው ተውቦ ይቀርቡ ነበር።
🔻ረሱል (ﷺ) የሚስትቶቻቸውን ስሜት ይረዱ ነበረ።
🔻ረሱል (ﷺ) ከሚስቶቻቸው ጋር ተጫዋች ነበሩ።
🔻 ረሱል (ﷺ) ሚስቶቻቸውን በመልካም ስሞች ይጠሩ ነበር።
🔻ረሱል (ﷺ)የትዳር የግል ጉዳዮቻቸውን ለሌሎች አያጋሮም ነበር።
🔻ረሱል (ﷺ) የሚስቶቻቸው ወላጆችንና ወዳጆች ይወዱና ያከብሩ ነበር።
🔻ረሱል (ﷺ) ሚስቶቻቸውን የሚያፅናኑ ነበሩ።
🌿 የብዙዎች አርአያ የሆኑት ረሱል (ﷺ) ከሚስቶቻቸው ጋር ፦
🍃 ተጫዋች ነበሩ፣
🍃ጥሩ ጊዜዎችን በጋራ በመዝናናት የሚያሳልፉ፣
🍃 አንዳንድ ጊዜዎችንም በሩጫ የሚሽቀዳደሙ፣
🍃አብረው የሚያወጉ፣
🍃አስደሳች አጋጣሚዎችን ከሚስቶቻቸው ጋር በጋራ የሚያሳልፉ ድንቅ ነብይ ነበሩ።
🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿
ተማሪና ደዕዋ
~
በሀገራችን ተጨባጭ በርካታ ወጣት በትምህርት ተቋማት አካባቢ በሚገኙ የደዕዋ ንቅናቄዎች ሰበብ በመጠኑም ቢሆን ዲኑን አውቋል፣ ወደ ዲን ቀርቧል። ስንት ወጣቶች ካምፓስ ከገቡ በኋላ ቁርአን አሊፍ ብለው ጀምረው ጨርሰዋል! ስንቶች ሰልመዋል! ስንቶች ኪታብ ተምረዋል! ስንቶች ከሺርክና ቢድዐ ወጥተዋል! ስንት ወንዶች ልብሳቸውን አሳጥረው ፂማቸውን አሳድገው በሱና አሸብርቀዋል! ስንት ሴቶች በጂልባብ፣ በኒቃብ ደምቀዋል! ስንቶች ኢማንን መሰረት ያደረገ ትስስር ዝምድና መስርተዋል!
እና ትምህርት ከዱንያዊ አላማውና ከተዘዋዋሪ ጥቅሙ ባሻገር በኛ ሃገር ተጨባጭ ቀጥተኛ የሆነ ዲናዊ ፋይዳው ብዙ ነው። ስለሆነም በቂ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ከታች ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ እስከ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ድረስ ከተማሪዎች ጎን መቆም፣ ማነቃቃት፣ ጊዜ መስጠት፣ ሁለገብ ምክር መለገስና ለትልልቅ ኃላፊነቶች የአእምሮ ዝግጅት እንዲኖራቸው ማነፅ ይገባል። ተማሪ ላይ መስራት ማለት ባቋራጭ በደዕዋ ቀጥታ ልንደርስባቸው በማንችላቸው ገጠሮች ጭምር በር ማንኳኳት ነው የሚሆነው።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አስር ምክሮች ለሙስሊም መምህራን
~
① ሃላፊነት ይሰማህ። የምትገነባው ትውልድ ነው። የምታስተላልፈው ነገር እጅግ ውድ ነው።
"ሃላፊነት የሚሰማው ሰው እራሱን እንደ ህዝብ ንብረት አድርጎ ይቆጥራል።"
② የሚያዩህ፣ ምሳሌ የሚያደርጉህ አሉና ተጠንቀቅ። ክፉ ምሳሌ እንዳትሆን። ከባህሪህ፣ ከገፅታህ፣ ከአቀራረብህ ሰዎች ይማሩ ዘንድ መልካም ሁን።
③ ፍትሃዊ ሁን። አንዱ ባጠፋው በጅምላ አትቅጣ። በጥቂቶች ጥፋት ተማሪዎችን በትምህርት፣ በፈተና፣ በሌላ መንገድ አትቅጣ። በበደለኛ አስተማሪዎች ሳቢያ ስንቶች ትምህርት አቋርጠዋል?! ስንቶች የተወሰኑ የትምህርት አይነቶችን ጠልተዋል። የስንቶች ውጤት ተበላሽቶ ሞራላቸው ተነክቷል።
"የትምህርት ተቋማት በሰፊው ስለ መብት የሚቀነቀንባቸው፣ ብዙ ጭቆና የሚፈፀምባቸው የግፍ አፀዶች ናቸው።"
④ ልዝብ ሁን አታስበርግግ። ቁጥብ ሁን አትባልግ። ትሁት ሁን አትጨፍግግ። የቸገረው ሊያዋይህ የማይፈራህ፣ የከበደው ሊጠይቅህ የማይሰጋህ፣ ያበጠበት የማይደፍርህ ሁን። ሚዛንህን ጠብቅ። ለሁሉም የሚገባው ቋንቋ ይኑርህ።
⑤ ክፋትን፣ ዘረኝነትን አትመግብ። ትውልድ አትመርዝ። በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት ከገበሬው ይልቅ ምሁሩ ጋር ጎልቶ የሚታይበት ምክንያቱ አርቀው ማየት የማይችሉ የተማሩ መሀይማን በመብዛታቸው ነው። መምህራንን ኢላማ ያደረጉ አማፂዎች መነሻ አካባቢ ላይ የመምህራን ድጋፍ የነበራቸው ናቸው።
⑥ ብቁ ሁን። እራስህን በእውቀት ገንባ። ተዘጋጅተህ ወደ ክፍል ግባ። ካልሆነ ትናቃለህ። ካልሆነ ሃላፊነትህን በአግባቡ አትወጣም። ካልሆነ ልበ ሙሉነት /confidence/ ታጣለህ። የምትስሰለች ሳይሆን ልብ የምታንጠለጥል፣ የምትናቅ ሳይሆን የምትወደድ፣ የምትፍፈራ ሳይሆን የምትከበር ሁን።
⑦ ለችግር ደራሽ ሁን። የተማሪ ችግር ይግባህ። የጤና፣ የኢኮኖሚ ችግር ያለበት፣ ቤተሰባዊ ቀውስ ያጋጠመው፣ ስነ ልቦናው የተጎዳ፣ ልቡ በሀዘን፣ በጉዳት የተሰበረ ይገጥማልና ለመረዳት ቅርብ ሁን። "አይዞን"፣ "አብሺር" ማለት ለተጎዳ ሰው ዋጋው ትልቅ ነው።
⑧ ቂመኛ አትሁን። ያለፍክበትን ገና ያላለፉ፣ ነገን አሻግረው ለማየት አቅም የሚያጥራቸው ጨቅላዎች፣ ወጣቶች ጋር ቂም አትጋባ። ተማሪህ የሚናገረውን፣ የሚጠይቀውን ሁሉ በክፉ አትተርጉም።
⑨ ጥንቃቄ ይኑርህ። በአነጋገርህ፣ በአቀራረብህ፣ በሁለ ነገርህ ጥንቃቄ አይለይህ። በምታስተምራቸው ተማሪዎች ቁጥር ልክ በየቤቱ አጀንዳ እንደሆንክ ልብ በል። በክፉ ወይም በበጎ በየቤቱ ትነሳለህ። ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬም ድረስ በክፉ ወይም በበጎ የማንረሳቸው አስተማሪዎች አሉ። ለሰዎች ከልብ የማይጠፋ ክፉ ትዝታ አትሁን።
(10) ለዲንህ ዋጋ ስጥ። ዲንህን ስታውቅ ለተማሪዎችህ መልካም ምሳሌ ትሆናለህ። ዲንህን ስታውቅ የተሳሳተ አስተምህሮ ለተማሪዎችህ አትመግብም። መጠናቸው ቢለያይም ሁሉም የትምህርት አይነቶች ውስጥ ከዲን ጋር የማይሄዱ ነገሮች ይገጥሙሀል። ንቁና ብቁ ከሆንክ እርምት እየሰጠህ ማለፍ ትችላለህ። መስጂድ ስትመላለስ አርአያነትህ ከፍ ይላል።
ከ IbnuMunewor የተወሰደ
