es
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Ir al canal en Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 483
Suscriptores
+224 horas
+677 días
+35330 días
Archivo de publicaciones
የ AFP ኮርሶች አዋቂ እና ብቀ የዲጀታል ሚዲያ ባለሙያ ያደርጓችኋል ጭራሽ የማታወቁትን ነው የምታውቁበት ፡ 👇 https://digitalcourses.afp.com/courses/

በአንድ ወቅት... ​በሶሻል ሚዲያ የምናያቸው መረጃዎች፣ ቪዲዮዎችና ዜናዎች እርስ በርሳቸው እየተጋጩ፣ የትኛው እውነት የትኛው ሀሰት እንደሆነ ለመለየት እጅግ ግራ የሚያጋባበት ወቅት ነበር። በየቀኑ
በአንድ ወቅት... ​በሶሻል ሚዲያ የምናያቸው መረጃዎች፣ ቪዲዮዎችና ዜናዎች እርስ በርሳቸው እየተጋጩ፣ የትኛው እውነት የትኛው ሀሰት እንደሆነ ለመለየት እጅግ ግራ የሚያጋባበት ወቅት ነበር። በየቀኑ በስልካችን ስክሪን ላይ የምናያቸውን ምስሎችና ወሬዎች በሙሉ ዝም ብሎ አምኖ መቀበል አደገኛ መሆኑን የተረዳሁት ያኔ ነበር። ​ልክ ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት (እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2024) በአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) እና በGoogle News Initiative የተዘጋጀ አንድ ልዩ ስልጠና ላይ የመሳተፍ እድል አገኘሁ። ስልጠናው ስለ "ዲጂታል ምርመራ ቴክኒኮች" (Digital Investigation Techniques) የሚተነትን ነበር። ​ይህ የAFP ኮርስ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ብዙ ነገር ያስተማረኝና ትልቅ ለውጥ በውስጤ የፈጠረ ነበር። ሶሻል ሚድያን በትክክል አውቄ እንድጠቀም ትልቅ አጋዥ ከመሆኑም በላይ፣ በዓለማችን ላይ ስላለው የመረጃ ፍሰት አይኔ እንዲሰፋ አስችሎኛል። ​ያየሁትን ዘገባ ሁሉ እውነት ወይም ሀሰት መሆኑን እንድለይ፣ የትኛውም ምስል መቼና የት እንደተቀረጸ (Reverse Image Search እና Geolocation በመጠቀም) እንድመረምር ረድቶኛል—ኧረ ስንቱ! ​ይህ ከስር የምታዩት ምስል ያኔ ያገኘሁት የ"Master Certificate" ምስክር ወረቀት ነው። ዛሬ ላይ ሆኜ ወደኋላ መለስ ብዬ ሳየው፣ ያኔ የወሰድኩት ውሳኔና ያገኘሁት እውቀት ዛሬም ድረስ በየቀኑ መረጃዎችን በጥንቃቄ እንድመረምርና ሶሻል ሚዲያን በብልሃት እንድጠቀም እየረዳኝ ይገኛል። ​በመረጃ ማዕበል ውስጥ ለምትዋኙ የሶሻል ሚዲያ ጓደኞቼና ቤተሰቦቼ የምመክረው አንድ ነገር አለ፦ የምናየውን ሁሉ አናምን፣ ከማጋራታችን በፊት እናረጋግጥ! Course

ኧረ አረጋጋው!
ኧረ አረጋጋው!

🏃‍♂️ የማይቻልን የቻለው የጀግናው ስንቅ፡ የአሸናፊነት ምስጢር 🇪🇹 ታሪኩ የሚጀምረው አለም በጥቁር ህዝቦች ላይ በነበራት የተሳሳተ አመለካከትና ንቀት ነበር። በወቅቱ የነጮች የጥናት መደምደሚያ «ጥቁር ህዝቦች የማራቶን ሩጫን የመሮጥ ተፈጥሯዊ ብቃትም ሆነ የጽናት አቅም የላቸውም» የሚል የትዕቢት ድምዳሜ ነበር። በዚህ መሀል ነበር ከአረንጓዴዋ ምድር የበቀለው ጀግናው አበበ ቢቂላ ይህንን የዘመናት ታሪክ ለመቀየር ወደ አደባባይ የወጣው። ነገር ግን ጉዞው አልጋ በአልጋ አልነበረም። ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት «በዚህ ሰዓት መሮጥ አትችልም» ተብሎ ተንቆ፣ ብቃቱ ተጠራጥሮ፣ እንደ ውሸታምም ተቆጥሮ የነበረበት የፈተና ሰዓት ነበር። ሩጫው ተጀመረ... ጀግናው ባዶ እግሩን የሮማን አስፋልት እየቀደደ ወደ ፊት ይገሰግሳል። ነገር ግን ፈተናው ከውጭ ብቻ አልነበረም፤ ከውስጥም ጭምር እንጂ። እየሮጠ በጽናት ተጉዞ ሠላሳ አምስተኛው (35ኛ) ኪሎሜትር ላይ ሲደርስ፣ ከባድ የተኩስ ህመም የመሰለ ውጋት ሆዱ ላይ ተሰማው። አካሉ ዝላለች፣ ህመሙ ከአቅም በላይ ሆኗል፣ እግሮቹ ሊታዘዙት አልቻሉም። ያኔ አእምሮው «አቁም! ውድድሩን አቋርጠህ ውጣ!» የሚል የሽንፈት አማራጭን አቀረበለት። ነገር ግን... በዚያ የሞትና የሽረት መስቀለኛ መንገድ ላይ፣ እጅ ከመስጠት ያስቆመውና በውስጡ እንደ እሳት የነደደ አንድ ታላቅ የልብ ስንቅ ነበረው። እርሱም ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት አስተማሪውና መሪው ሻምበል አለቃው የለገሱት የወርቅ ቃል ነበር፦ “መጀመሪያ እንድትሸነፍ የሚያደርጉህን ምክንያትህን አሸንፍ!” ይህች ቃል በህመም ከተሰቀዘው አካሉ በላይ በረታች። አበበ ቢቂላ ያንን ህመሙን፣ ያንን ንቀቱን፣ ያንን «አትችልም» የሚለውን የነጮች የውሸት ጥናትና የራሱን የውስጥ ድካም — ሁሉንም ምክንያቶች መጀመሪያ በውስጡ አሸነፋቸው! ምክንያቶቹን ሲያሸንፍ ደግሞ አካሉ ታደሰች፣ እግሮቹ ክንፍ ሆኑ። በመጨረሻም ታሪክ ተሰራ! ያ ተንቆ የነበረው ጥቁር አንበሳ ባዶ እግሩን ሮማ ላይ ድልን ተቀዳጅቶ የነጮችን ጥናት አመድ አደረገው። ሁሉም ሰው በአንድ ድምፅ :- "THE MAN WHO BEAT THE WORLD WITHOUT SHOES" የታሪኩ መልዕክት ለሁላችንም፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው የሚገባው ትልቁ እውነት ይህ ነው፦ በህይወት ሩጫህ ላይ ስኬት ላይ እንዳትደርስ የሚከለክሉህ ውጫዊ መሰናክሎች ወይም ሰዎች አይደሉም። መጀመሪያ ማሸነፍ ያለብህ «አልችልም፣ አቅም የለኝም፣ ሰዓቱ አይደለም» የሚሉትን የውስጥህን ምክንያቶችና ሰበቦች ነው። ምክንያቶችህን ስታሸንፍ፣ የአለምን ታሪክ ትቀይራለህ!

THE MAN WHO BEAT THE WORLD WITHOUT SHOES
THE MAN WHO BEAT THE WORLD WITHOUT SHOES

የኤሎን ማስክ 1 ትሪሊዮን ዶላር ወደ ብር ሲቀየር ወደ 156 ትሪሊዮን ብር አካባቢ ይሆናል። ለኛ ሀገር 🇪🇹 የስንት አመት በጀት መሆን ይችል ይሆን ? ለካ ተራርቀናል መስክ😂 $1,000,000,000,000! 😲 ለካ እንዲህም ይቻላል እንዴ! ትልልቆቹ የሀብቱ ምንጮች የሚከተሉት ናቸው፦ ​1. ቴስላ (Tesla) ​ይህ የኤሎን ማስክ ዋነኛውና ትልቁ የሀብት ምንጭ ነው። ማስክ በኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ ቴስላ ውስጥ የ20% አካባቢ የባለቤትነት ድርሻ (Stocks) አለው። የቴስላ አክሲዮን በዓለም አክሲዮን ገበያ ላይ ዋጋው በናረ ቁጥር የኤሎን ማስክም ሀብት በቀጥታ በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምራል። ​2. ስፔስ ኤክስ (SpaceX) ​የህዋ ምርምር እና የሮኬት አምራቹ ስፔስ ኤክስ ሁለተኛው ትልቅ የገቢ ምንጩ ነው። በዚህ በግል ይዞታነት በሚተዳደረው ኩባንያ ውስጥ ማስክ የ40% በላይ ድርሻ አለው። ስፔስ ኤክስ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ በመተኮስ እና የ"ስታርሊንክ" (Starlink) የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎትን በመላው ዓለም በማስፋፋት አሁን ላይ እጅግ ግዙፍ ዋጋ ያለው ኩባንያ ሆኗል። ​3. xAI (የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያ) ​በቅርብ ዓመታት ውስጥ ማስክ የመሰረተው የሰው ሰራሽ አስተዋፅዖ (AI) ኩባንያ xAI (Grok AIን የሰራው) እጅግ ፈጣን እድገት እያሳየ ይገኛል። ከኢንቨስተሮች በሚያገኘው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ድጋፍ እና በከፍተኛ ግምት (Valuation) ምክንያት ይህ ኩባንያ አሁን ላይ ሌላኛው ትልቅ የሀብቱ ምሰሶ እየሆነ መጥቷል። ​4. ሌሎች ኩባንያዎች ​X (የቀድሞው ትዊተር)፦ ምንም እንኳን የገበያ ዋጋው ቢዋዥቅም ሙሉ በሙሉ የእሱ ንብረት ነው። ​The Boring Company፦ የመሬት ውስጥ መተላለፊያ ዋሻዎችን የሚቆፍር ኩባንያ። ​Neuralink፦ በሰው አእምሮ እና በኮምፒውተር መካከል ግንኙነት ለመፍጠር የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ኩባንያ። ​ የኤሎን ማስክ ትልቁ "የገቢ ምንጭ" የኩባንያዎቹ የአክሲዮን ዋጋ ማደግ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎቹ በዓለም ገበያ ላይ ያላቸው የዋጋ ግምት (Net Worth Appreciatìon) ነው።

የ X ገፅን ያጨናነቀው ወሬ ኤሎን መስክ በአለም ታሪክ የመጀመሪያው ባለ $1 trillion ዶላር ባለፀጋ ሆነ ነው።
የ X ገፅን ያጨናነቀው ወሬ ኤሎን መስክ በአለም ታሪክ የመጀመሪያው ባለ $1 trillion ዶላር ባለፀጋ ሆነ ነው።

አንዱ በ Whatsapp ሊያጠምደኝ የላከልኝ መልዕክት ነው ... ጉድ እኮ ነው 😂 የእኔ principle "Never Trust, Always Verify " ✅ እንደሆነ ኦያውቅም መሰል🤔 በ"Telebirr" ስም እንደዚሁም በሽልማት መልክ እየተሰራጨ ስላለው አደገኛ የማጭበርበሪያ (Scam) ሊንክ! ​በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ግሩፖች እና በውስጥ መስመር (Inbox) "የቴሌብር አንቨርሰሪ ስጦታ" (Telebirr Anniversary Offer) በሚል እየተዘዋወረ ያለውን ሊንክ አስተውላችኋል? ​እባካችሁ በፍጹም እንዳትከፍቱት! ❌ ሊንኩ ሙሉ በሙሉ የውሸት እና የሰዎችን መረጃ ለመስረቅ የተዘጋጀ የፊሺንግ (#Phishing) ማጭበርበሪያ ነው። ​🛑 ሊንኩን ስንከፍተው ምን ይፈጠራል? (የደህንነት አደጋው) 1️⃣​የግል መረጃ ስርቆት (Data Theft): ሊንኩን ስትነኩ "እድለኛ ነዎት" በማለት ስም፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንድታስገቡ ይጠይቃል። ይህ መረጃችሁ በቀጥታ ወደ አጭበርባሪዎቹ እጅ ይገባል። 2️⃣​አካውንታችሁን ለሌላ አደጋ ማጋለጥ: የማረጋገጫ (Verification) ሂደት በሚል ስም ስልክ ቁጥራችሁን ወይም የቴሌብር መለያችሁን ለመስረቅ የሚሞክሩ አደገኛ ድረ-ገጾች ላይ ይወስዳችኋል። 3️⃣​እናንተን ተጠቅሞ ሌሎችን ማጥመድ: "ስጦታውን ለማግኘት ሊንኩን ለ15 ወይም ለ20 የዋትስአፕ/ቴሌግራም ወዳጆችዎ ወይም ግሩፖች ያጋሩ" ይላል። በዚህ ጊዜ ሳታውቁት የሳይበር ወንጀለኞቹን ተባባሪ በመሆን የቅርብ ጓደኞቻችሁን ለአደጋ ታጋልጣላችሁ። 4️⃣​የውሸት አስተያየቶች (Fake Comments): ከስር "እኔ ደርሶኛል"፣ "እውነት ነው" የሚሉ የሰዎች አስተያየቶች ታያላችሁ። እነዚህ ሁሉ ሰዎችን ለማታለል በሲስተም የተሰሩ የውሸት (Bot) አካውንቶች ናቸው። ​💡 ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ? (ቁልፍ ጥንቃቄዎች) ​ሊንኩን (URL) አስተውሉ: ማንኛውም የቴሌብር ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ትክክለኛ መረጃ የሚለጠፈው በይፋዊ ድረ-ገጻቸው (telebirr.et ወይም ethiotelecom.et) ላይ ብቻ ነው። tinyurl... ወይም ሌላ የተለየ ስም ያላቸው ሊንኮች በሙሉ ማጭበርበሪያ ናቸው። ​"በነጻ ስጦታ" አትታለሉ: በሶሻል ሚዲያ ላይ "ለማጋራት" ወይም "ፎርም ለመሙላት" በሚሰጥ ነጻ ስጦታ በፍጹም አትመኑ። ​አታሰራጩ፣ አታጋሩ: ሊንኩ ሲላከላችሁ ለሌላ ሰው ባለማጋራት ሰንሰለቱን ቁረጡት። ​በይፋዊ ገጾች ብቻ አረጋግጡ: ማንኛውንም አይነት ስጦታ ወይም ማስተዋወቂያ ስትመለከቱ የግድ አስፈላጊ ከሆነ በቀጥታ ወደ ቴሌብር ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ (የሰማያዊ ምልክት ወይም Verified Checkmark ያለበት) በመግባት እውነተኝነቱን አረጋግጡ። ይህን ጉዳይ ትላንትም ነግርያችኋለሁ Telegram Whatsapp ሌሎች ሶሻል ሚድያ ቻናሎች የማጥመጃ መንገዶች እየሆኑ ነው። በየጊዜው ይከሰታል በየጊዜው ሼር እናደርጋለን ፤ አሁንም ግን የሚሸወዱት በርካቶች ናቸው። ​ሳይበር ደህንነት በጋራ የሚገነባ ነው! ይህ መረጃ ለብዙዎች እንዲደርስ እና ወገኖቻችን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠበቁ Share እናድርግው። 👇 ​#CyberSecurity

NeverNever Trust, Always Verify ✅
NeverNever Trust, Always Verify ✅

🚀 የ Generative AI ነፃ ኮርስ ለጀማሪዎች ማይክሮሶፍት (Microsoft) ያዘጋጀውና በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለው "Generative AI for Beginners" ኮርስ አሁን በ 21 ክፍሎች (Lessons) ቀርቧል። ይህ ኮርስ የ AI መተግበሪያዎችን ከባዶ እንዴት መገንባት እንደምንችል በተግባር የሚያስተምር ነፃ ስልጠና ነው። 📚 ኮርሱ ምን ምን ይካተታል? እያንዳንዱ ክፍል በቀላሉ እንድትሩዱት ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን የሚከተሉትን ይዟል፡ 🎥 አጫጭር ቪዲዮዎች፡ ስለ ርዕሱ ማብራሪያ የሚሰጡ። 📝 የፅሁፍ ትምህርቶች፡ በዝርዝር የተፃፉ ማብራሪያዎች። 💻 የኮዲንግ ምሳሌዎች፡ በ Python እና TypeScript የተዘጋጁ ተግባራዊ ልምምዶች። 🔄 ሁለት የትምህርት መንገዶች፡ ቲዎሪ የሚያስረዱ ("Learn") እና በተግባር ኮድ የሚያሰሩ ("Build") ክፍሎች። 🛠️ ለመጀመር ምን ያስፈልጋል? መሰረታዊ እውቀት፡ የ Python ወይም TypeScript መሰረታዊ እውቀት (ለጀማሪዎች የሚሆኑ ኮርሶችም አብረው ተካተዋል)። የ GitHub አካውንት፡ የኮርሱን ፋይሎች ወስደው ለመለማመድ። ኮዱን ለመሞከር Azure OpenAI፣ OpenAI API ወይም አዲሱን GitHub Model Catalog መጠቀም ትችላላችሁ። 🤝 አብሮ የመማር እና የድጋፍ መድረኮች የ Discord ማህበረሰብ፡ በ Azure AI Foundry Discord ላይ በመቀላቀል ከሌሎች ተማሪዎች ጋር መገናኘትና እገዛ ማግኘት ይቻላል። ለስራ ፈጣሪዎች (Startups)፡ የራስዎን የ AI ድርጅት ማቋቋም ከፈለጉ፣ የ Azure Credits ድጋፍ የሚያገኙበት የ Microsoft for Startups ዕድል አለ። 💡 እንዴት መጀመር ይቻላል? ከስር ባለው ሊንክ ወደ GitHub ድህረ-ገጽ በመሄድ አካውንት በመክፈት እና መመሪያውን በማንበብ ወዲያውኑ መጀመር ትችላላችሁ። በቀላሉ መልሰው ለማግኘት ማከማቻውን (Repository) Star (🌟) ማድረግ አትርሱ! 👇 https://github.com/microsoft/generative-ai-for-beginners/tree/main?WT.mc_id=academic-105485-koreyst ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ላይ አሰቀምጡልኝ!

photo content

🚀 በዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለም ስኬታማ ለመሆን ማወቅ ያለብን 7 መሠረታዊ ነገሮች! 🚀 በአሁኑ ጊዜ የንግድ ድርጅትን ማሳደግም ሆነ በዲጂታል ክህሎት መበልጸግ ያለ ዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀት የማይታሰብ ነው! በምስሉ ላይ እንደሚታየው ፣ በዘርፉ ውጤታማ ለመሆን ማስተር ልናደርጋቸው የሚገቡ 7 ወሳኝና መሰረታዊ ነጥቦች፦ 1️⃣ SEO & SEM (የፍለጋ ሞተር ማርኬቲንግ)፦ SEO (Search Engine Optimization)፦ ድረ-ገጻችን በGoogle ፍለጋዎች ላይ ያለ ምንም ክፍያ (Organically) መጀመሪያ መስመር ላይ እንዲወጣ የማድረግ ጥበብ ነው። ይህንን ለማሳካት ቁልፍ ቃላትን (Keywords) በአግባቡ መጠቀም እና ጥራት ያለው ይዘት መፍጠር ይጠይቃል። SEM (Search Engine Marketing)፦ በክፍያ ማስታወቂያዎች (Paid Ads) አማካኝነት ምርት ወይም አገልግሎታችንን በፍለጋ ውጤቶች ላይ በግንባር ቀደምትነት ማሳየት ነው። ፈጣን ውጤት እና ደንበኛ ለማግኘት ተመራጭ ዘዴ ነው። 2️⃣ Content & Social Media Marketing፦ Content Marketing፦ "ይዘት ንጉሥ ነው (Content is King)" እንደሚባለው፣ ለታላሚ (Target Customers) ደንበኞቻችን እውነተኛ እሴት የሚጨምሩ ጽሑፎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም መረጃዎችን ማዘጋጀት ነው። ይህ ደንበኞች በእኛ ላይ እምነት እንዲጥሉ ያደርጋል። Social Media Marketing፦ እንደ Facebook, TikTok እና LinkedIn ያሉ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ከደንበኞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠር ነው። ብራንዳችንን በሰዎች አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ እና የራሳችንን ማኅበረሰብ (Community) ለመገንባት ወሳኝ ነው። 3️⃣ PPC (Pay-Per-Click)፦ ይህ ስትራቴጂ የታለሙ(ምርቶቻችንን እንዲጠቀሙ የምንፈልጋቸው) ደንበኞችን በቀጥታ ወደ ድረ-ገጻችን ለማምጣት የምንጠቀምበት የኦንላይን ማስታወቂያ ዘዴ ነው። ልዩነቱ ማስታወቂያው ስለታየ ብቻ ሳይሆን፣ ፍላጎት ኖሮት ማስታወቂያውን ጠቅ (Click) አድርጎ ወደ እኛ የመጣ ሰው ሲኖር ብቻ ክፍያ የምንፈጽምበት በመሆኑ የበጀት ብክነትን ይከላከላል። 4️⃣ Affiliate Marketing፦ ሰፊ የሽያጭ መረብ ለመዘርጋት የሚረዳ የትብብር ስትራቴጂ ነው። ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች (Influencers) ወይም ድርጅቶች የእኛን ምርት ለተከታዮቻቸው አስተዋውቀው ሽያጭ ሲያመጡ፣ ከሽያጩ ላይ የተወሰነ መቶኛ ኮሚሽን የምንከፍልበት አዋጭ የንግድ መንገድ ነው። 5️⃣ Email Marketing፦ ብዙዎች በዚህ ሰአት ውጤቱ የቀነሰ ቢመስላቸውም፣ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የትርፍ ምጣኔ (Highest ROI) ያለው ዘዴ ነው። አዳዲስ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ ቅናሾችን ለማሳወቅ እና ከነባር ደንበኞቻችን ጋር የረጅም ጊዜ የንግድ ትስስር ለመፍጠር በቀጥታ ወደ ኢሜይላቸው መልዕክት መላክን ያካትታል። 6️⃣ Inbound Marketing፦ ደንበኞችን በማስታወቂያ ከመውረር እና ከማስጨነቅ ይልቅ፣ እነሱ የሚፈልጉትን መፍትሔ እና ጠቃሚ ይዘት በማቅረብ በራሳቸው ፍላጎት ተማርከው ወደ እኛ እንዲመጡ የማድረግ ዘመናዊ ስልት ነው። ደንበኛው ራሱ ፈልጎ ስለሚመጣ የሽያጭ ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው። 7️⃣ Online PR (ዲጂታል ሕዝብ ግንኙነት)፦ በዲጂታል ዓለም ውስጥ ስምና ዝናን የመገንባት ሥራ ነው። በተለያዩ ታዋቂ ድረ-ገጾች፣ ዲጂታል ጋዜጦች፣ ብሎጎች እና ሪቪውዎች ላይ ስለ እኛ ብራንድ በጎ ገጽታ የሚፈጥሩ ጽሑፎች እንዲወጡ በማድረግ በገበያው ውስጥ ያለንን ተቀባይነት ማረጋገጥ ነው። 💡 "Master these fundamentals to succeed in digital marketing" እነዚህን ሰባት መሠረታዊ ስልቶች በሚገባ አጣምሮ መተግበር መቻል በኦንላይን ገበያ ውስጥ ሁልጊዜ መሪ እና ቀዳሚ ያደርገናል። እነዚህን ሁሉ በነጻ የት እንማር ብላችሁ መጠየቃችሁ አይቀርም ኮሜንት መስጫው ላይ ሁሉት ተመራጭ ኮርሶችን 👇 🔸.Digital Marketing Certification Course: Get Certified in Digital Marketing 🔸. Google Fundamentals of Digital Marketing ዛሬውኑ ይጀምሩ!😍 #DigitalMarketing

በዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለም ስኬታማ ለመሆን ማወቅ ያለብን 7 መሠረታዊ ነገሮች!
በዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለም ስኬታማ ለመሆን ማወቅ ያለብን 7 መሠረታዊ ነገሮች!

የዳታ ግላዊነት (Data Privacy)፦ ትርጉም ፣ ተግዳሮቶች እና የሕግ ማዕቀፎች https://www.linkedin.com/pulse/%E1%8B%A8%E1%8B%B3%E1%89%B3-%E1%8C%8D%E1%88%8B%E1%8B%8A%E1%8A%90%E1%89%B5-data-privacy-%E1%89%B5%E1%88%AD%E1%8C%89%E1%88%9D-%E1%89%B0%E1%8C%8D%E1%8B%B3%E1%88%AE%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%95%E1%8C%8D-%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%80%E1%8D%8E%E1%89%BD-mohammed-seid-endris-bkhfe?utm_source=share&utm_medium=member_android&utm_campaign=share_via በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቴክኖሎጂ የሰው ልጅን የእለት ተእለት ሕይወት ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል። በምናከናውናቸው ዲጂታል እንቅስቃሴዎች ሁሉ—ከማኅበራዊ ሚዲያ ግንኙነቶች እስከ ባንክ አሠራር፣ ከሕክምና መረጃዎች እስከ ኦንላይን ግብይት—ሰፊ የመረጃ አሻራዎችን (Digital Footprints) እንተዋለን። ሙሉ ጽሁፉን በ LinkedIn አካውንቴ ላይ ገብታችሁ እንድታነቡት ግብዣዬ ነው! ጠቃሚ ሀሳቦችን ታገኛላችሁ ብዬ አስባለሁ👇

🚀 የAI ውድድሩ ቀጥሏል ማይክሮሶፍት 7 አዳዲስ የ ‘MAI’ ሞዴሎች ይፋ አድርጓል! 💥 ​የ AI ዓለም ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሻግሯል! የማይክሮሶፍት AI ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ ሱሌይማን፣ ኩባንያው ከሌሎች ሳይቀዳ (Zero distillation) ሙሉ በሙሉ በማይክሮሶፍት አቅም የገነባቸውን 7 አዳዲስ የ MAI ሞዴሎችን አስተዋውቋል። እነዚህ ሞዴሎች ሰዎችን ለመተካት ሳይሆን፣ በሰው ልጅ ቁጥጥር ስር ሆነው ሰዎችን ለማገዝ የተሰሩ ናቸው (Humanist Superintelligence) በማለት ተናግረዋል። የኤአይ ሞዴሎች ሲሰለጥኑ መረጃ ያለ ፈቃድ ይጠቀማሉ ለሚለው ሀሳብ ምላሽ ሰጥተዋል ! "በራሳችን አቅም እና መረጃ ነው የገነባነው" በማለት አስፋርዋል። ​📌 ሙስጠፋ በማይክሮሶፍት ድረ-ገፅ እና በ X ገፃቸው ስለ ሞዴሎቹ ይህን አስፍረዋል፡- ​ 🧠 MAI-Thinking-1 (የማሰብ ብቃት)፦ በ Blind side-by-side evaluations ውድድር ታዋቂውን Sonnet 4.6 እኩል ተፎካክሮ የሰዎችን ምርጫ ማግኘት የቻለ ግዙፍ የአመክንዮ ሞዴል ነው። ​💻 MAI-Code-1-Flash (ለኮደሮች)፦ 5 ቢሊዮን ፓራሜትር ብቻ ያለው ፣ እጅግ ርካሽ እና ለ GitHub Copilot ልዩ ማሻሻያ የተደረገለት ፈጣን የኮዲንግ ረዳት ነው። ​ 🎨 MAI-Image-2.5 & Flash፦ በምስል ፈጠራ እና ማስተካከል (Editing) ረገድ የ Nano Banana Proን የ Arena ነጥብ በልጦ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ​🎙️ MAI Transcribe & Voice፦ ከተወዳዳሪዎቹ በ 5 እጥፍ ፈጣን የድምጽ ግልባጭ (በ43 ቋንቋዎች) እና የሰውን ድምጽ በአጭር ናሙና የመምሰል አስደናቂ አቅም ያለው ነው! ​ 💼 Microsoft Frontier Tuning፦ ተቋማት የራሳቸውን የውስጥ መረጃ ብቻ በመጠቀም የራሳቸውን Custom AI Agent እንዲሰሩ ይፈቅዳል። ለምሳሌ ለ Excel የተገነባው ሞዴል ከ GPT-5.4 ጋር እኩል እየሰራ እስከ 10 እጥፍ ቀልጣፋ ሆኗል! ሙሉውን ለማንበብ 👇 https://microsoft.ai/news/building-a-hillclimbing-machine-launching-seven-new-mai-models/

የጥቂት ቢሊየነሮች ወይስ የመላው የሰው ልጅ የጋራ ሀብት? 🤖 ​ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዛሬ ላይ የደረሰበት አስደናቂ ከፍታ የትናንት ምናብ የዛሬ እውነታ መሆኑን አሳይቶናል። ነገር ግን ከዚህ ታላቅ የቴክኖሎጂ ምጥቀት በስተጀርባ ማንም ሊሸሸገው የማይችለው አንድ መራራ እውነት አለ፦ AI የተገነባው በሰው ልጅ የጋራ እውቀት ላይ ነው ፣ አዎ! ለዘመናት በተደከመባቸው እውቀቶች። ​ ታዋቂው አሜሪካዊ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ በቅርቡ ባስተላለፉት መልዕክት (በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት) ይህንን እውነት ቁልጭ አድርገው አውጥተውታል። "AI የተገነባው በሰው ልጅ የጋራ እውቀት ላይ ነው፤ ስለዚህ የሚያመነጨው እጅግ ግዙፍ ሀብት መላውን የሰው ልጅ መጥቀም አለበት እንጂ እንደነ ሳም አልትማንና ኢሎን ማስክ ያሉ ጥቂት የኤአይ ኦሊጋርኮችን (ባለሀብቶችን) ብቻ ማበልጸግ የለበትም" ሲሉ ይከራከራሉ። ይህንን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥም ህዝቡ ቀጥተኛ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖረው የሚያደርግ "American AI Sovereign Wealth Fund Act" የተባለ ታሪካዊ የህግ ረቂቅ እንደሚያስተዋውቁ በ X ገፃቸው አስታውቀዋል። ​ ይህ ሃሳብ ዛሬ ላይ ሁላችንም ልናስብበት የሚገባ ትልቅ የፍትሃዊነት ጥያቄ ነው። በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሰውን ልጅ የጋራ እውቀት ያለክፍያና ያለ ግልጽ ፍቃድ እየወሰዱ (Scraping) ሞዴሎቻቸውን ያሰለጥኑበታል። ይህ አሰራር ህጋዊ ይሁን አይሁን ገና በህግ አውጪዎችና በፍርድ ቤቶች ዘንድ ግራጫ ቀጠና ቢሆንም፣ የሞራልና የፍትህ ጥያቄው ግን ግልጽ ነው፦ መረጃውንና እውቀቱን የሰጠው መላው የዓለም ህዝብ ሆኖ ሳለ፣ ትርፉና ስልጣኑ ለምን በጥቂት ግለሰቦች እጅ ብቻ ይከማቻል? ​ ኤአይ በሄደበት ፍጥነት የሰዎችን ስራ እየተካ ከመጣ፣ ተራው ህዝብ የኢኮኖሚ ተጎጂ እየሆነ፣ የቴክኖሎጂ ባለቤቶቹ ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እያጋበሱ የሀብት ልዩነቱን የሰማይና የምድር ያህል ሊያሰፉት ይችላሉ። የሴናተሩ መከራከሪያ ደግሞ ይህንን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል ነው፤ "መረጃው የህዝብ ከሆነ፣ ከትርፉ ላይም ህዝቡ ቀጥተኛ ድርሻ (Dividend) ሊኖረው ይገባል!" የሚል ፅኑ አቋም። ​ እናንተስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ታስባላችሁ? የኤአይ ባለቤትነትና የሚያስገኘው ጥቅም ለሁሉም ህዝብ በእኩልነት የሚከፋፈልበት የህግ ማዕቀፍ መፈጠሩን ትደግፋላችሁ? ወይስ የቴክኖሎጂ ፈጠራን ያቀጭጫል የሚል ስጋት አለባችሁ? ​ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇 "ይህ ሀሳብ በአንድ ወቅት ትልቅ አለም አቀፍ አጀንዳ የሚሆንበት ቀን ይመጣል ኢንሻአላህ! " ፅሁፋም ለታሪክ ይቀመጥ! ​#AI #ArtificialIntelligence #TechEquity

የጥቂት ቢሊየነሮች ወይስ የመላው የሰው ልጅ የጋራ ሀብት? ?
የጥቂት ቢሊየነሮች ወይስ የመላው የሰው ልጅ የጋራ ሀብት? ?

ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2026 እ.ኤ.አ በታይዋን በተጀመረው የ #Computex 2026 / GTC Taipei ኤግዚቢሽን ላይ የ NVIDIA ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ (Jensen Huang) የግል
ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2026 እ.ኤ.አ በታይዋን በተጀመረው የ #Computex 2026 / GTC Taipei ኤግዚቢሽን ላይ የ NVIDIA ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ (Jensen Huang) የግል ኮምፒውተሮችን እና የሮቦቲክስ ዘርፍን የሚቀይሩ በርካታ ታላላቅ ቴክኖሎጂዎችን አስተዋውቀዋል። ከእነዚህ ውስጥ ትኩረቴን የሳበው እና ዋነኛው፦ RTX Spark Superchip Nvidia ከ Microsoft እና MediaTek ጋር በመተባበር ለግል ኮምፒውተሮች (PCs) የሚሆን አዲስ RTX Spark Superchip የተባለ ፕሮሰሰር አስተዋውቋል። ይህ ቺፕ በ "Windows on Arm" ላፕቶፖች እና ዴስክቶፖች ላይ እጅግ ከፍተኛ የ AI አቅም እና የጌሚንግ ብቃት (High-end Gaming) ለማስገኘት የተሰራ ነው። ቺፑ 20 የ Arm CPU ኮሮች፣ 6144 CUDA ኮሮች ያሉት Blackwell GPU እና 128GB RAM ይዟል። ዋጋቸው የሚቀመስ ከሆነ ለመግዛት ዝግጁ ነኝ! ከዚያ በኋላ የራሳችንን Al ማበልፀግ እንጀምራለን! ሚጢጢ ኢንፍራ ስትራክቸር ልመና እናቆማለን ! በቃ ይመቻችሁ የቴክኖሎጂ ልዩነታችን ግን በጣም ሰፋ ........... እንደርስባችሁ ይሆን? ለማንኛውም ጧት ተከታተሉት ያልኳችሁ ለዚህ ነበር ሌሎቹንም ሼር አድርጋቸኋለሁ ! ባለፈውም "A New era of PC" ማለታቸው አይዘነጋም !