Mohammed Seid - Miftah
Ir al canal en Telegram
🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
2 480
Suscriptores
-324 horas
+157 días
+35230 días
Archivo de publicaciones
ChatGPT እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 30 ቀን 2022 ሲለቀቅ መጀመሪያ የተጠቀመው GPT-3.5 የተባለውን የቋንቋ ሞዴል የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ በ5 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን እንዲሁም በሁለት ወራት ውስጥ 100 ሚሊዮን ወርሃዊ ተጠቃሚዎችን በማፍራት በታሪክ ፈጣኑ መተግበሪያ መሆን ችሏል። በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂው ዕድገት እጅግ የላቀ ደረጃ ላይ ደርሶ መድረኩ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በሰፊው የሚዘወተረው የChatGPT ኤአይ ሞዴልም ወደ GPT-5 የላቁ ስሪቶች ተሻግሯል።
ይህ የChatGPT አስገራሚ ዕድገት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በሰው ልጅ ታሪክ ከታዩት ማናቸውም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በላይ በፍጥነት እያደገ እና በቀላሉ በሰዎች እጅ እየደረሰ ለመሆኑ ዋነኛ ማሳያ ነው። የዓለም ባንክ እና የቴክኖሎጂ ተንታኞች እንደሚያመለክቱት፣ የድሮዎቹ ታላላቅ ፈጠራዎች (እንደ የእንፋሎት ሞተር፣ ኤሌክትሪክ እና ኢንተርኔት) በዓለም ዙሪያ ተስፋፍተው መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ህዝብ እጅ ለመድረስ ከ20 እስከ 80 ዓመታት ፈጅቶባቸዋል።
🤔ይገርማል!
ይህ የ AI ታላቅ እድገት እድል ወይስ ስጋት ምን ትላላችሁ ሀሳባችሁን ሼር አድርጉን?
ፈጣን ለውጥ ባለበት በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን፣ በየትኛውም የሙያ መስክ (ጤና፣ አስተዳደር፣ ትምህርት ፣ ግብርና ወይም ንግድ) ዲጂታል አስተሳሰብ (Digital Thinking) መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ቁልፍ ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ ዲጂታል አስተሳሰብ ምን ማለት ነው?
ዲጂታል አስተሳሰብ ማለት በቴክኖሎጂ ዘመን የሚመጡ ፈታኝ ችግሮችን ለመፍታት፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት እና ከሁኔታዎች ጋር በፍጥነት ለመላመድ ቴክኖሎጂን፣ መረጃዎችን (Data) እና ሰብአዊ ፍላጎቶችን አቀናጅቶ የመጠቀም የላቀ የአእምሮ ብቃት ወይም እይታ ነው።
የዲጂታል አስተሳሰብ ዋና መገለጫዎች፡
✅ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ (Data-Driven Decisions)፦ በግምት ወይም በባህላዊ መንገድ ብቻ ከመወሰን ይልቅ፣ ትክክለኛ መረጃዎችን ሰብስቦ በመተንተን ይበልጥ አስተማማኝ ውሳኔ ላይ መድረስ።
✅ አውቶሜሽን እና ቅልጥፍና (Automation & Efficiency)፦ በእጅ የሚሠሩ እና ጊዜ የሚወስዱ ሂደቶችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ (ለምሳሌ፦ የተለያዩ ሲስተሞችን በመጠቀም) ስራዎችን ፈጣን፣ ቀላል እና ከስህተት የጸዱ ማድረግ።
✅ ችግር ፈቺ አእምሮ (Problem-Solving Mindset)፦ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን እንደ ፈተና ሳይሆን፣ ያሉትን ችግሮች በቀላሉ ለመፍታት እንደ መልካም አጋጣሚና መሣሪያ ማየት።
✅ ቀጣይነት ያለው ትምህርት (Continuous Learning)፦ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚለወጡ አዳዲስ የዲጂታል ዕውቀቶችንና መሳሪያዎችን በፍጥነት ለመለማመድ እና ስራ ላይ ለማዋል ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን።
ስለዚህ በተሰማራንበት ዘርፍ በዲጀታል ማሰብ መጀመር የሚያመጣልን ዋጋ ትልቅ ነው ፤ ያውም ነገሮች በፍጥነት ወደ ዲጀታል እየሄዱ ባለበት በዚህ ጊዜ!
ሀሳባችሁን አጋሩን?⤵️
የኢኮደርስ ኮርስ ምዝገባ ይሰራል ምንም ችግር የለበትም ፤ በዚህ ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ 👇
https://www.facebook.com/share/v/18Lx9p2viw/
አንዳንድ ጊዜ ሶሻል ሚዲያ ላይ ስንገባ የቲክቶከሮችን፣ የዩቲዩበሮችን ወይም የፌስቡክ ኢንፍሉኤንሰሮችን የተቀባ፣ አሳሳች እና የቅንጦት ህይወት ስንመለከት ፤ ውስጣችን "ትምህርት የት አባቱ! ለካ አቋራጭ መንገድ አለ" ብለን ልናስብ እንችላለን።
የሶሻል ሚዲያ ብልጭልጭ ለቀረፃ የሚቀርብ ነው። እውነተኛው የህይወት ቅንጦት ግን በዕውቀት መታጠቅ፣ በዲሲፕሊን መመራት እና በትምህርት መገንባት ነው።
ነገ የዕድገትህን መሰረት የሚጥለው ዛሬ የምትቀስመው ትምህርት እንጂ የማለፊያ ስክሪን ላይ የሚታየው ትርኢት አይደለም። አንብብ፣ ተማር፣ ብቁ ሁን!
እኔ የሚሰማኝ እንደዚህ ነው እንግዲህ! ከተሳሳትኩ አውፍ በሉኝ
ወሳኝ እና ወቅታዊ ጥያቄ 🤔
በዩቲዩብም ሆነ በፌስቡክ ሬልስ ላይ የምናያቸው ቪዲዮዎች እውነተኛ መሆናቸውን ወይም በ AI (በዲፕፌክ - Deepfake) የተሰሩ መሆናቸውን መለየት ትችላላችሁ?
አሁን ላይ ቴክኖሎጂው እጅግ እየተራቀቀ ስለመጣ እውነትን ከሐሰት መለየት ከባድ ፈተና እየሆነ ነው።
እስኪ እናንተ በምን መንገድ ነው ዲፕፌክ ቪዲዮዎችን የምትለዩት? ወይስ አታስተውሉም? ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን!
አንዳንዱ AIን አልጠቀምም ተጠቅሜ አላውቅም ፣ ጠላት ነን ወዘተ እያለ ይፖስታል!
እንዴት?
በዚህ ወቅት አለመጠቀም ይቻላል? ምናልባት የምለቀው ይዘት ከ AI ሀሳብ ነፃ ነው ሊሆን ይችላል።
አውቀንም ይሁን ሳናውቅ Alን በእለት ተእለት የዲጀታል እንቅስቃሴ እንጠቀማለን። የዚህ አይነት ሀሳብ የሚያነሱ ምናልባት Al ምንድን ነው የሚለውን ጠለቅ ብለው እንዲረዱ እንመክራለን።
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ከANI እስከ ASI — የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጉዞ ወዴት ነው?
የዘርፉ ባለሙያዎች የ AIን የዕድገት ደረጃ በሦስት ይከፍሉታል፦
1️⃣ ANI (Artificial Narrow Intelligence)
2️⃣ AGI (Artificial General Intelligence)
3️⃣ ASI (Artificial Superintelligence)
አሁን በዓለም ላይ በብዛት እያየናቸው ያሉ የ AI ቴክኖሎጂዎች (ChatGPT, Gemini, Copilot, DeepSeek, Kimi K3) በየትኛው ደረጃ ላይ የሚመደቡ ይመስላችኋል?
የሦስቱስ መሠረታዊ ልዩነት ምንድን ነው?
በጉዳዩ ላይ ያላችሁን እውቀትና አስተያየት በኮሜንት አጋሩን⬇️
እውቀት ስነ-ምግባር እና ተግባር ጋር ሲሆን እንዴት ደስ ይል ነበር!?
ለመሆኑ... ይህንን ድንቅ ሦስትዮሽ በጋራ መመልከት ለምን እንዲህ ናፈቀን?
በዚህ ወቅት መሠረታዊ ዲጂታል ክህሎት (Basic Digital Skills) ማለት እንደ ማንበብ እና መፃፍ ሁሉ የግድ ሊኖረን የሚገባ መሠረታዊ እውቀት ሆኗል።
ነገሮች በፍጥነት ወደ ዲጂታል እያመሩ አይደል? 🚀
በዚህ ሰፊ የዲጂታል እንቅስቃሴ ውስጥ ስንገባ ደግሞ Safety and Security ሁልጊዜም ከምንም በላይ ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ ነው። መሣሪያዎችን መጠቀም ብቻ ሳይሆን፣ መረጃዎቻችንን እና ግላዊ ደህንነታችንን መጠበቅ መቻል የዚሁ ጉዞ ማዕከል ነው።
እስኪ እናንተም በዚህ ሀሳብ ላይ ያላችሁን ተሞክሮ ሼር አድርጉን! 👇
ዩቲዩብ የ Monitization ሕጉን አሻሻለ!
የዩቲዩብ አጋር ፕሮግራም (YouTube Partner Program) ማሻሻያዎች ከጥር 1 / 2027 ጀምሮ በይፋ ሥራ ላይ ይውላል።
በአዲሱ ህግ ሞኒታይዝ ለመሆን ወይም ገቢ ለማግኘት
✅ 1,000 ተመዝጋቢዎች (Subscribers)
✅ ከ8,000 የህዝብ እይታ ሰዓታት (Public watch hours) ባለፉት 12 ወራት ወይም 20 ሚሊዮን የሾርትስ እይታዎች (Shorts views) ባለፉት 90 ቀናት። ማሟላት ግዴታ ሲሆን ይህም ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት ከነበረው በእጥፍ የጨመረ ነው። በእርግጥ በአንድ ቪዲዮ ሁሉ ሊመጣ ይችላል ሀሪፍ ይዘት ከስራን ማለት ነው ፤ ለእኛ ሀገር ከባድ ቢሆንም !
ለማንኛውም እስካሁን መስፈርቱን ካላሟላችሁ ፣ አሁን የቀረውን ጊዜ በመጠቀም ወደ ግባችሁ ድረሱ። 6 ወር ጊዜ አላችሁ!
🚀 በዛሬው ዘመን ቴክኖሎጂን በመጠቀም፡
📚 Online መማር - ከየትኛውም የዓለም ማዕዘን ሆነው አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር፣
💻 Online ስራ መፍጠር - የገቢ ምንጭ መፍጠር እና ዲጂታል ንግድ መጀመር፣
🌐 Online ግንኙነት መፍጠር - ሀገር አቀፍ እንዲሁም ዓለም አቀፍ አጋሮችን እና ጓደኞችን ማፍራት ይቻላል።
አልጋ በአልጋ ነው እያልኩ አይደለም ቻሌንጅ አለው ነገር ግን የሚገጥሙን ችግሮች መቋቋ እና ማለፍ ያስፈልጋል!
እናንተ የትኛው ላይ ትኩረት አድርጋችሁ እየሰራችሁ ነው?
💬 ሃሳባችሁን ኮሜንት ላይ አካፍሉን!⬇️
አለመግባባትና ጦርነት የሚያመጣው ጥፋት እንጂ የሚፈታው ችግር የለም። ዛሬ ለምናሳልፈው ውሳኔ ነገ የምንከፍለው ዋጋ ከባድ ነው። ስለዚህ የሰላም መንገድ ይበልጣል!
ሰላም ለሀገራችን!🇪🇹
ዲጂታል ክህሎትን ፈልገው የተሰባሰቡ ከ 97K በላይ ቤተሰቦች የተሰባሰቡበት የፌስቡክ ግሩፕ እንዳለኝ ይታወቃል።
ይህ ግሩፕ Ethio Coders ኢትዮ ኮደርስ ይሰኛል። በ 2 አመት ሂደት ውስጥ የተገነባ ነው። ይህን ግሩፕ አብዛሃኛውን ጊዜ መረጃ እና ሀሳብ ሼር የማደርግበት እኔ ነኝ ማለት ይቻላል።
ብዙ ጊዜ አስተማሪ ሀሳብ ያላችሁ ሀሳብ ሼር አድርጉ ብዬ አበረታታለሁ እስከአሁን ያሳመነኝ እና ጠቃሚ ሀሳብ ሼር ያደረገ አለ ለማለት ይከብደኛል በጣም ጥቂት ናቸው።
የ Aproval ጥያቄ ደርሶኝ ቼክ ሳደርግ ፦
1. Scam (አስቀያሚ ማስታወቂያዎች)
2. ያልተረጋገጠ ሪል ስቴት ገበያ
3. ፌሎወር ለማግኘት ብቻ እዚያ እዚህ የሚረግጥ ሀሳብ ናቸው።
4. Al የተገኘ ምንም Edit ያልተደረገ ሀሳብ ወዘተ
እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ተከታታይና አስተማሪ ነገሮችን በግሩፑ ላይ ሼር በማድረግ ሰዎችን ጠቅማችሁ እናንተም ማደግ ትችላላችሁ! እኔም በደስታ እቀበላለሁ ✅
ኑ በጋራ እንስራ! 🤝
የኮርስ ምዝገባ የኢትዮጵያዊው ዌብሳይት ካስቸገር እነዚህን ሊንኮች መጠቀም ትችላላችሁ :-
➡️ Global Chapters - Ethiopia - Android Fundamentals
https://www.udacity.com/org/gc-ethiopia/learning-plan/global-chapters-ethiopia-android-fundamentals
➡️ Global Chapters - Ethiopia - Programming Fundamentals
https://www.udacity.com/org/gc-ethiopia/learning-plan/global-chapters---ethiopia---programming-fundamentals
➡️ Global Chapters - Ethiopia - Data Fundamentals
https://www.udacity.com/org/gc-ethiopia/learning-plan/global-chapters-ethiopia-data-fundamentals
➡️ Global Chapters - Ethiopia - AI Fundamentals
https://www.udacity.com/org/gc-ethiopia/learning-plan/global-chapters-ethiopia-ai-fundamentals
ነሐሴ - ክረምት 🥰
"መውጫ መግቢያ የለም!" አለ የአዲስ አበባ ሰው... ዛሬ ግን ተራው ለእኛም ደርሶናል፤ የወሎ ምድር እየጠጣ ነው። 🌧️ ሌላውም የሀገራችን አካባቢ እየጠጣ መሆኑን ተስፋ በማድረግ!
አርሶ አደራችን አለኝታችን ሆይ! አሁን እንግዲህ ነቃ ብሎ መከሰብ ነው።
ለከል ሃምዱ ያረብ! ዘላቂም አድርግልን 🤲
#ክረምት #ወሎ #አዲስአበባ #Ethiopia
የኦንላይን ትምህርት የራሱ ፈተናዎች አሉት፤ ጥብቅ ዲሲፕሊን ካልተከተልንበት ሰርተፊኬት መሰብሰብ እንጂ እውነተኛ የሙያ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው። ይሁን እንጂ ዛሬ ያለንበት ዘመን ትልቁ በረከት “እውቀት” ከእንግዲህ በክፍል ግድግዳ የተወሰነ አለመሆኑ ነው።
ትጋት፣ ጽናት እና ቋሚ የጊዜ ሰሌዳን አጣምረን ስንጓዝ ቴክኖሎጂን በቤታችን ሆነን መቅሰም እና በሙያችን እጅግ የላቀ ደረጃ ላይ መድረስ እንችላለን። ርቀቱ ፈተና ቢሆንም፣ የሚከፈለው መስዋዕትነት የሚሰጠው ውጤት ግን ህይወትን የሚቀይር ነው።
የእናንተን ሀሳብ እና መከተል አለለብን የምትሉትን ዲሲፕሊን ሼር አድርጉ ን? ⤵️
ሁላችንም በዲሲፕሊን የታነጸ ጠንካራ የመማር ጉዞ ይኑረን!✅
በርከት የፌስቡክ ገፅ እና የቴሌግራም ቻናላችን ተከታዬች የወስዷቸው እና የወደዷቸው ነፃ ኮርሶች:
1. Data Fundamentals and more free course
2. Networking Basics
3. Digital Marketing
ሶሻል ሚዲያን ለበጎ አላማ የሚጠቀሙትን ያብዛልን! 🤲
ዲጂታል መድረኮቻችንን ለትክክለኛና በጎ ዓላማ እንጠቀምባቸው።
✅ ሰዎችን ለመርዳትና ለማነቃቃት፣
✅ ማህበረሰባችንን በአዎንታዊ መልኩ ለመለወጥ፣
✅ ሀገራችንን በሰናይ ተግባር ከፍ ለማድረግ።
መልካም ነገር እናስብ፤ መልካም እናጋራ! 🌍🤝
🍿 "ፖፕኮርን ብሬን" (Popcorn Brain) ምንድን ነው? አእምሯችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ እየጠፋ ይሆን? 🧠📱
ስራ ላይ ወይም ፊልም እያያችሁ ስልካችሁን ትከፍታላችሁ? ወይስ መጽሐፍ ማንበብ ጀምራችሁ ገና ሁለት ገጽ ሳትጨርሱ ወደ ቲክቶክ ወይም ፌስቡክ ትሮጣላችሁ? ይህ አሁን ላይ የአብዛኞቻችን የዕለት ተዕለት ፈተና ሆኗል። ሳይንቲስቶች ይህንን ክስተት "ፖፕኮርን ብሬን" (Popcorn Brain) ይሉታል።
ይህ ስያሜ እ.ኤ.አ በ2011 በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ዴቪድ ሌቪ የተዋወቀ ሲሆን፥ ሀሳባችን ልክ በሙቀት ላይ እንዳለ የበቆሎ ፍሬ (ፖፕኮርን) ከአንዱ ርዕስ ወደ ሌላው፣ ከአንዱ መተግበሪያ ወደ ሌላው በፍጥነት የሚፈናጠርበትን የአእምሮ መበታተን ሁኔታ ይገልጻል። ይህ የህክምና በሽታ አይደለም፤ ነገር ግን አእምሯችን ከመጠን በላይ ለፈጣን የዲጂታል መረጃዎች በመጋለጡ ምክንያት ትኩረት የማሰባሰብ አቅሙ ሲዳከም የሚፈጠር "የለመደው ስንፍና" ነው።
🔍 የ"ፖፕኮርን ብሬን" ዋና ዋና ምልክቶች
የዚህ ክስተት የመጀመሪያው ምልክት ፈጣን የስራ መለዋወጥ (Task-Switching) ሲሆን፣ አንድን ስራ ወይም ጥናት ሳትጨርሱ በየደቂቃው ስልክ ማየትን ያካትታል። ሌላው ደግሞ ሁለት ስክሪን በአንድ ጊዜ መጠቀም ነው፤ ለምሳሌ ቲቪ ወይም ላፕቶፕ ላይ እየሰራችሁ በሌላ እጅ ስልክ መጎብኘት። በተጨማሪም ስልክን ያለ ምክንያት የመንካት አባዜ ይታያል፤ ማለትም ስልኩ ምንም አይነት ድምፅ ወይም የፅሁፍ ምልክት ሳይሰጥ "እስቲ ልክፈተው" በሚል ስሜት በየደቂቃው መክፈት ነው። በመጨረሻም እረፍት ማጣት እና መሰልቸት ይከተላል፤ ለምሳሌ ባንክ ውስጥ ወይም ትራንስፖርት እየጠበቃችሁ ለ5 ደቂቃ እንኳን ስልክ ሳትነኩ መታገስ አለመቻልን ያሳያል።
🔬 ከጀርባው ያለው ሳይንስ
እኛ ፌስቡክ ላይ ስንገባ፣ አጫጭር ቪዲዮዎችን (Reels) ስናይ፣ ወይም የላይክ (Like) እና ኮሜንት ቁጥሮችን በየደቂቃው ስናድስ በአእምሯችን ውስጥ "ዶፓሚን" (Dopamine) የተባለ የደስታ ኬሚካል ይረጫል። የማህበራዊ ሚዲያ ስልተ-ቀመሮች (Algorithms) የተሰሩት አእምሯችን ይህንን ፈጣን እና ቀላል እርካታ እንዲለምድ አድርገው ነው።
በዚህ ምክንያት፣ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስራ መስራት ወይም ጥልቅ ውይይት ማድረግ ያሉ "ቀስ ያሉ" እና ትኩረት የሚሹ ተግባራት ለአእምሯችን እጅግ አሰልቺ እና ከባድ ይሆኑበታል። በጥናቶች መሠረት፣ እ.ኤ.አ በ2004 የሰው ልጅ በአማካይ በአንድ ስክሪን ላይ የሚሰጠው ትኩረት 2.5 ደቂቃ የነበረ ሲሆን፥ አሁን ግን ከ50 ሰከንድ በታች ወርዷል!
🛠 አእምሯችንን ለመታደግ እና ትኩረታችንን ለመመለስ የሚረዱ የመፍትሄ እርምጃዎች
ይህ የተለመደ ልማድ እንጂ የአእምሮ ጉዳት ስላልሆነ በትዕግስት እና በተግባራዊ እርምጃዎች መቀየር ይቻላል። በመጀመሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን (Notifications) አጥፉ፤ የላይክ፣ የኮሜንት እና የቡድን መልዕክቶች ድምፅ አእምሯችሁን በየደቂቃው እንዳይረብሸው ሙሉ በሙሉ (Turn Off) አድርጉት። ስልኩ አይጥራችሁ፤ እናንተ ስትፈልጉ ብቻ ክፈቱት። 📴
ሁለተኛው መፍትሔ ለማህበራዊ ሚዲያ የጊዜ ገደብ መስጠት (Time-Blocking) ነው፤ ለምሳሌ "ፌስቡክ የምከፍተው ጠዋት፣ ከሰዓት እና ማታ ለ15 ደቂቃ ብቻ ነው" ብላችሁ ወስኑ። ስልኩን ስትከፍቱ የሰዓት መቆጣጠሪያ (Timer) ሞልታችሁ ግቡ እና ሰዓቱ ሲያልቅ ወዲያውኑ ውጡ። ⏳
ሦስተኛው ደግሞ አንድ ስራ ላይ ብቻ ማተኮርን መልመድ (Single-Tasking) ነው፤ በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ስልካችሁን ሙሉ በሙሉ አጥፍታችሁ ወይም አርቃችሁ በማስቀመጥ መጽሐፍ አንብቡ፣ ፅሁፍ ጻፉ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ። 📖
በመጨረሻም አጭር የአእምሮ እረፍት መውሰድ ተመራጭ ነው፤ ደክሟችሁ ማረፍ ስትፈልጉ ስልክ ከመነካካት ይልቅ፥ ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ ለ5 ደቂቃ ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ ወይም ፀጥ ባለ ቦታ መቀመጥ አእምሯችሁ ራሱን እንዲያድስ (Reset) ይረዳዋል። 🚶♂️
📌 ማጠቃለያ
መልዕክቴ ለሁላችንም ነው፦ ቴክኖሎጂን ህይወታችንን ለማቅለል እንጠቀምበት እንጂ እሱ እኛን እና ውድ ጊዜያችንን እንዲቆጣጠረን አንፍቀድለት። ዛሬውኑ የመጀመሪያውን እርምጃ ጀምሩ!
💬 እስቲ እንወያይ፦
እናንተስ ዘንድ ይህ የ"ፖፕኮርን ብሬን" ምልክት ይታያል? ከላይ ከተጠቀሱት መፍትሔዎች ውስጥ የትኛውን ዛሬውኑ ለመጀመር ትመርጣላችሁ? (ማስታወቂያዎችን ማጥፋት ወይስ ስልክን ከአይን ማራቅ?) ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን ፤ ለወዳጃችሁም ሼር (Share) በማድረግ አድርሱት! 👇
