The 5% Club
Ir al canal en Telegram
Your Ultimate , Urgent and Accurate Guide | Work until it's Done!
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
882
Suscriptores
-224 horas
+137 días
+60230 días
Archivo de publicaciones
882
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ ምረቃ መደበኛ (በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሃ-ግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቀናት እና መስፈርቶች መሠረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
አስፈላጊ መስፈርቶች እና ቀናት
* የምዝገባ ቀን፡ ከነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ።
* መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡
* በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
* የመግቢያ ፈተና (UAT) የሚሰጥበት ቀናት ከጳጉሜን 02 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም
* ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://admission.aau.edu.et
882
🗣Everything you must know before taking the AAU UAT exam ⚠️‼️Check the Video Below 👉
https://youtu.be/nSgUct4nfygመልካም የዝግጅት ጊዜ! 🌟 The 5% Club | Your UAT Success Starts Here! ⚡️Work Until It's Done! 💪 #The5%club 📈 #TeamUAT 🤝 #AAUReady! 🎓 #UAT2026 Share Our Socials 🤝 Youtube || TikTok || Instagram || Telegram || Website
882
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም 200 (ሁለት መቶ) ልዩ የፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጅቷል።
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ፣ የተቀመጡ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ እና ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና በብቃት የሚያልፉ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ዕድሉ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡
የ Presidential Scholarship Program ዕድሉ ተጠቃሚዎች፣ ዩኒቨርሲቲው ባሉት ሰባት ኮሌጆች እና የሕግ ትምህርት ቤት ስር ባሉ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ይመደባሉ።
ነጻ የትምህርት ዕድሉ ሙሉ ነፃ የትምህርት ዕድል፣ መጠነኛ የኪስ ገንዘብ እና ከአጋር ተቋማት ጋር በሚኖር ትብብር ተጨማሪ ድጋፍና የስልጠና ዕድሎችን ያስገኛል፡፡
በዚህ የትምህርት ዕድል በወጥነት ተጠቃሚ ለመሆን፣ የዕድሉ ተጠቃሚዎች በየሴሚስተሩ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.50 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም የዕድሉ ተጠቃሚዎች በተመደቡበት የትምህርት ዘርፍ መቀጠል ይኖርባቸዋል።
የዚህ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች በቀጣይነት ዩኒቨርሲቲው የድኅረ-ምረቃ (Masters እና PhD) የትምህርት ዕድል ያገኛሉ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የ2019 ዓ.ም ምዝገባ እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም እንደሚከናወን መገለፁ ይታወቃል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://admission.aau.edu.et/UGAnnouncements
882
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
===============================
የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡
· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል፡፡
www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
🔗Join us:
👉 @aastu_info
🔵 ለጓደኞችዎ ያጋሩ (Share): 👉 The 5% Club Telegram Channel 🔴 የUAT ሞዴል ፈተና ለመውሰድ (UAT MOCK EXAM): 👉 Take UAT Mock Exam 👉 www.The5%Club.com ⚪️ የውይይት ግሩፓችንን ይቀላቀሉ (Join Group): 👉 The 5% Club Discussion Group ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 💪 የUAT ፈተናን በቀላሉ ለማለፍ ከእኛ ጋር ይዘጋጁ! 🎓 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመግባት ህልምዎን እውን ያድርጉ! ⚡️ Work until it's Done! #The5PercentClub #TeamUAT #AAUReady Share Our Socials ⚡️⚡️⚡️ Youtube || TikTok || Instagram || Telegram || Website
882
#Regular Undergraduate program of Addis Ababa University for the 2026/27 (2019 E.C.) academic year Step by Step Application process for GOVERNMENT SPONSERSHIP Applicants Check out this Video 👉
https://youtu.be/OOn2xRDbHQ4
882
#Regular Undergraduate program of Addis Ababa University for the 2026/27 (2019 E.C.) academic year Step by Step Application process for SELF SPONSERSHIP Applicants Check out this Video 👉
https://youtu.be/vmuWbPtsebM
882
Steps to create undergraduate applicant account
Step 9 : Log in and Access your Application Dashboard 👉
https://admission.aau.edu.et/dashboard
882
Steps to create undergraduate applicant account
Step 8 : Log in with the new registered Email and Password u submitted previously 👉
https://admission.aau.edu.et/login
882
Steps to create Undergraduate applicant account
Step 7: add your valid email and Password used for the entire application and admission Process 👉
https://admission.aau.edu.et/UndergradeRegister
882
Steps to Create Undergraduate Applicant account
Step 6 : After Verification Make sure All informations are filled Correctly . 👉
https://admission.aau.edu.et/UndergradeRegister
882
Steps to Create Undergraduate Applicant account
Step 5: Enter your Fayda Alliance Number (FAN) and verify with OTP code sent via your SMS. 👉
https://admission.aau.edu.et/UndergradeRegister
882
Steps to create Undergraduate Applicant account
Step 4: Click Verify with FAYDA to proceed the next step 👉
https://admission.aau.edu.et/UndergradeRegister
882
Steps to create undergraduate applicant account
Step 3: Click the National Applicant section to proceed the next step via this link 👉
https://admission.aau.edu.et/UndergradeRegister
882
Steps to create Undergraduate Applicant account
Step 2: Go to the login tab and Click register for undergraduate program vis this link 👉
https://admission.aau.edu.et/login
882
Steps to Create Undergraduate Applicant Account
Step 1: Go to this site via this link 👉
https://admission.aau.edu.et/
882
+1
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
💪 የUAT ፈተናን በቀላሉ ለማለፍ ከእኛ ጋር ይዘጋጁ!
🎓 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመግባት ህልምዎን እውን ያድርጉ!
⚡️ Work until it's Done!
#The5PercentClub #TeamUAT #AAUReady
Share Our Socials ⚡️⚡️⚡️
Youtube || TikTok || Instagram || Telegram || Website
882
📌 ለማመልከት የሚያስፈልጉ ነገሮች ምንድን ናቸው? 📋
• የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ። 🪪 • Valid የሆነ Email Address ። 📧 • 9-12 የhigh school ትራንስክሪፕት scan የተደረገ በPDF format። 📄 • የ 12ኛ ክፍል ማትሪክ ውጤት መግለጫ Certificate በPDF format። 📜 • Passport size photo በ soft copy format ። 📸 • የቀበሌ ወይም ወረዳ ድጋፍ ደብዳቤ scan የተደረገ በPDF format (ለመንግስት ስኮላርሺፕ አመልካቾች)። 📄 • የcost sharing እዳ የተከፈለበት ደረሰኝ( ከ2018 ዓ.ም ውጪ ማትሪክ የተፈተናችሁ እና በተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ስትማሩ የነበራችሁ ተማሪዎች እና ሬሚዲያል በመንግስት ዩኒቨርስቲ ስትከታተሉ የቆያችሁ) scan የተደረገ በPDF format 💳📄 • ከሙያ ትምህርት ቤቶች(TVET) የተመረቃችሁ level 4 ማረጋገጫ ሰነድ(COC) scan የተደረገ በPDF format 🎓📄
882
📢 ለ 2019 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዲግሪ መርሃግብር በቀን እና በማታ 🎓 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምዝገባ ጀመረ። 🏛
🌐 ምዝገባው የሚሆነው በዩኒቨርስቲው የማመልከቻ ፖርታል admission.aau.edu.et ላይ በመግባት ከነሃሴ 19 እስከ ነሃሴ 29 2018ዓ.ም ብቻ ነው። ⏰ የመግቢያ ፈተናውም የሚሰጠው ከጳጉሜ 2 -4 2018 ዓ.ም ነው። 📝
አመልካቾች ለመደበኛ በቀን (REGULAR) መርሃግብር ለማመልክት 5 የማመልከቻ መንገዶችን መከተል እና መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል። 📋 እነሱም
🔹 1. አንደኛ በ self-sponsorship ነው። 🎓
በዚህ ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
• የ12ኛ ክፍል ማትሪክ በ 2015 ፥ 2016 ፥ 2017 እና 2018 ዓ.ም ተፈትናችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ መሆን አለባችሁ። ✅ • በ 2016 ፥ 2017 እና 2018 ዓ.ም በሌሎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ የCost sharing እዳ የከፈላችሁበት ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል 💳 • በ 2018 ዓ.ም ብቻ የሬሚዲያል ፈተና ተፈትናችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ መሆን አለባችሁ ። 📝 • በቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ድፕሎማ እና COC level 4 ያላችሁ መሆን አለባችሁ። 🎓እነዚህን መስፈርቶች ካሟላችሁ በሃላ ወደ ዩኒቨርስቲው ለመቀላቀል
• UAT ፈተና ተፈትናችሁ የሚፈለገውን ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል። 📝 • በ UAT እና በ ማትሪክ ውጤታችሁ መሰረት ዲፓርትመንት ማግኘት ካልቻላችሁ ዩኒቨርስቲው በሚመድባችሁ ዲፓርትመንት ተቀላቅላችሁ ለመማር ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል። 🏛🔹 2. ሁለተኛው በ መንግስት ስኮላርሺፕ (cost sharing ) ነው። 🎓💰 በዚህ ለማመልከት የሚያስፈለጉ መስፈርቶች
• በ 2018 ዓ.ም ብቻ የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ✅ • ከምትኖሩበት ወረዳ ፥ ቀበሌ የኢኮኖሚ ሁኔታን የሚገልጽ ከፍላችሁ መማር እንደማችሉ የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል 📄እነዚህን መስፈርቶች ካሟላችሁ በሃላ ወደ ዩኒቨርስቲው ለመቀላቀል
• UAT ፈተና ተፈትናችሁ የሚፈለገውን ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል። 📝 • እንዲሁም ዩኒቨርስቲው የሚያስቀምጠውን የመግቢያ ውጤት(Cut off) ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። 🎯🔹 3. ሶስተኛው በ presidential scholarship ነው። 🏆🎓 በዚህ ለማመልከት
• በ 2018 ዓ.ም ብቻ የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ 500 እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ መሆን ይጠበቅባቸዋል። 🏅 • ከመጀመሪያው ወይም ከሁለተኛው ሴሚስተር በኋላ፣ በመንግስት ወይም self sponsership ተማሪዎች ጋር ዩኒቨርስቲው በሚመድባችሁ ዲፓርትመንት ተቀላቅላችሁ ለመማር ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል። 🏛🔹 4. አራተኛው በ Teachers Education sponsorship ነው። 👩🏫👨🏫🎓 በዚህ ለማመልከት
• በ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 500 ወይም ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ አለባችሁ። 🏅 • UAT ፈተና ተፈትናችሁ የሚፈለገውን ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል። 📝 • ከመጀመሪያው ወይም ከሁለተኛው ሴሚስተር በኋላ፣ በመንግስት ወይም self sponsorship ተማሪዎች ጋር ዩኒቨርስቲው በሚመድባችሁ ዲፓርትመንት ተቀላቅላችሁ ለመማር ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል። 🏛5. አመልካቾች ለመደበኛ በማታ(EXTENSION) መርሃግብር ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦
· 📜የ12ኛ ክፍል ማትሪክ፦ በ2015፥ 2016፥ 2017 እና 2018 ዓ.ም ተፈትናችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ መሆን አለባችሁ። · 🧾 የኮስት ሼሪንግ (Cost Sharing) ክፍያ፦ በ2016፥ 2017 እና 2018 ዓ.ም በሌሎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ የዕዳ ክፍያ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባችኋል። · 📝 የUAT ፈተና፦ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ (UAT) ፈተና ተፈትናችሁ የሚፈለገውን ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገብ ይጠበቅባችኋል። · 🤝 የዲፓርትመንት ምደባ ፍቃደኝነት፦ በUAT እና በማትሪክ ውጤታችሁ መሰረት የፈለጋችሁትን ዲፓርትመንት ማግኘት ካልቻላችሁ፥ ዩኒቨርሲቲው በሚመድባችሁ አማራጭ ዲፓርትመንት ተቀላቅላችሁ ለመማር ፈቃደኛ መሆን ይኖርባችኋል።📌 ለማመልከት የሚያስፈልጉ ነገሮች ምንድን ናቸው? 📋
• የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ። 🪪 • Valid የሆነ Email Address ። 📧 • 9-12 የhigh school ትራንስክሪፕት scan የተደረገ በPDF format። 📄 • የ 12ኛ ክፍል ማትሪክ ውጤት መግለጫ Certificate በPDF format። 📜 • Passport size photo በ soft copy format ። 📸 • የቀበሌ ወይም ወረዳ ድጋፍ ደብዳቤ scan የተደረገ በPDF format (ለመንግስት ስኮላርሺፕ አመልካቾች)። 📄 • የcost sharing እዳ የተከፈለበት ደረሰኝ( ከ2018 ዓ.ም ውጪ ማትሪክ የተፈተናችሁ እና በተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ስትማሩ የነበራችሁ ተማሪዎች እና ሬሚዲያል በመንግስት ዩኒቨርስቲ ስትከታተሉ የቆያችሁ) scan የተደረገ በPDF format 💳📄 • ከሙያ ትምህርት ቤቶች(TVET) የተመረቃችሁ level 4 ማረጋገጫ ሰነድ(COC) scan የተደረገ በPDF format 🎓📄💰 እነዚህን መረጃዎች አሟልታችሁ በ Application portal 750 ETB የማይመለስ በቴሌብር ማመልከቻው portal ላይ በመክፈል ከ ነሃሴ 19 - ነሃሴ 29 2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላለችሁ። ⏰📲 🌐 ለበለጠ መረጃ ይፋዊውን የAAU ድረ-ገጽ ይጎብኙ: 👉 official AAU WebPage 💪 የUAT ፈተናን በቀላሉ ለማለፍ ከእኛ ጋር ይዘጋጁ! 🎓 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመግባት ህልምዎን እውን ያድርጉ! ⚡️ Work until it's Done! #The5PercentClub #TeamUAT #AAUReady Share Our Socials ⚡️⚡️⚡️ Youtube || TikTok || Instagram || Telegram || Website
